Belachew Belay - በላቸው በላይ

Belachew Belay - በላቸው በላይ All Your Favorite is Here 👈

23/11/2023

#በጋሞ ዞን #ምዕራብ ዓባያ 2ኛ ደ/ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ #ሚናሴ አዲሱ የተሰራት መኪና

23/11/2023

ድንቅ ልጆች✌️✌️እሸቱን በእንግሊዝኛ አጣደፈችው!!

23/11/2023

😢😢

22/11/2023

!!

INSA- ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተላለፈ የጥንቃቄ መልክት!WinSCP (Windows Secure Copy) የተሰኘ  የፋይል ማስተላለፊያ ፕሮቶኮልን በመጠቀም  ተጠቃሚዎችን ኢ...
22/11/2023

INSA-
ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የተላለፈ የጥንቃቄ መልክት!

WinSCP (Windows Secure Copy) የተሰኘ የፋይል ማስተላለፊያ ፕሮቶኮልን በመጠቀም ተጠቃሚዎችን ኢላማ ያደረጉ አሳሳች እና ተንኮል አዘል ሶፍትዌሮችን በጎግል ማስታወቂያዎች ላይ በማጣበቅ ወደ ኮምፒውተራችን/ስልካችን እንድንጭናቸው ከሚያደርጉን አጭበርባሪዎች እንጠንቀቅ ሲል ዘሃከር ኒውስ በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

የሳይበር ጥቃት ፈጻሚዎቹ እንደ WinSCP ያሉ ህጋዊ ሶፍትዌሮችን ለማውረድ የሚፈልጉ ተጠቃሚዎችን ተመሳስሎ የተሠራ ማልዌር እንዲጭኑ በማድረግ የተጭበረበሩ የፍለጋ ውጤቶችን እና ሀሰተኛ የጎግል ማስታወቂያዎችን እየጠቀሙ እንደሆነ ዘገባው አመላክቷል።

አጥቂዎቹ በተንኮል አዘል ማስታወቂያ አማካኝነት ተጠቃሚውን ወደ ተንኮል አዘል የዎርድፕረስ ድረ-ገጽ gameeweb[.]com ይመራዋል፣ ይህም ተጠቃሚውን በአጥቂው ቁጥጥር ስር ወዳለው የማስገሪያ(phising) ጣቢያ በመምራት መረጃዎችን ይዘርፉታል፡፡

ማልዌርባይት የተባለ ካምፓኒ ዘገባ እንዳስታወቀው የጎግል ተለዋዋጭ ፍለጋ ማስታወቂያዎች (Google's Dynamic Search Ads) ማልዌርን ለማሰራጨት ተግባር ሲውሉ ይህ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ተገልጿል ። ባለፈው ወር መገባደጃ ላይ PyCharm የተሰኘው እና ቀላል የፕሮግራሚንግ ኮድ ለመጻፍ የሚያገለግል ፕላትፎርምን ለሚፈልጉ ተጠቃሚዎች ማልዌርን በማሰራጨት መረጃን ወደሚሰርቅ ድረ-ገጽ የሚያሻግር እኩይ ሶፍትዌር እንደነበር እና በኋላም እንዲነሳ በተደረገ ዘመቻ ሊነሳ መቻሉን ማልዌርባይት ጠቁሟል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ደግሞ ይኸው ካምፓኒ እ.አ.አ. በጥቅምት 2023 በክሬዲት ካርድ ላይ የማጭበርበር ዘመቻ መጀመሩን ገልጾ ነበር፡፡ ይህም የማጭበርበር ዘመቻ የፋይናንስ መረጃን ለመስረቅ ያለመና አሳማኝ የሚመስሉ ነገር ግን የውሸት የክፍያ ገጾችን በማሰራጨት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢ-ኮሜርስ ድረ-ገጾች ላይ ጥቃት እንዳደረሰ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም እውነተኛውን መተግበሪያ መስለው ከተሠሩ ከጎግል አሳሳች ማስታወቂዎች እራሳችንን እንጠብቅ፡፡
INSA- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸዉ ምሁራን መካከል ፕ/ሮ መምበሩ መንገሻ ይገኛል::እንኳን ደስ አለህ
22/11/2023

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ከሰጣቸዉ ምሁራን መካከል ፕ/ሮ መምበሩ መንገሻ ይገኛል::

እንኳን ደስ አለህ

22/11/2023

ለመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ

ሦስተኛ ዙር ቦንጋ ማዕከል ሠልጣኝ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች  በስልጠናው ሂደት  ቦንጋ ዩኒቨርስቲው ላበረከተው  ድንቅ አስተዋጽኦ ለዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርግስ  ስጦታ አበረከቱ።    &    ...
22/11/2023

ሦስተኛ ዙር ቦንጋ ማዕከል ሠልጣኝ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በስልጠናው ሂደት ቦንጋ ዩኒቨርስቲው ላበረከተው ድንቅ አስተዋጽኦ ለዶ/ር ጴጥሮስ
ወ/ጊዮርግስ ስጦታ አበረከቱ።

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የማናጅመንመንት አባላት በጊምቦ ወረዳ ዩኒቨርሲቲዉ ላደረጋቸዉ የልማት እንቅስቃሴ የምስጋና ፕሮግራም ተደረገ።የካፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻ ከበደ ዩኒቨርሲቲ...
21/11/2023

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትና የማናጅመንመንት አባላት በጊምቦ ወረዳ ዩኒቨርሲቲዉ ላደረጋቸዉ የልማት እንቅስቃሴ የምስጋና ፕሮግራም ተደረገ።

የካፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻ ከበደ ዩኒቨርሲቲዉ በዞኑ በሚገኙ ወረዳዎች የግብርና የትምርት እና የማህበረሰብ አገልግሎት በመስጠት የዞኑን መንግስት በመደገፍ የበኩሉን ሚና እየታጫወተ መሆኑን ገልጸዉ በቀጣይ ከዩኒቨርሲቲዉ ጎን ማህበረሰቡ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል ።

የወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ ትብብሩ አሰፋ የቦንጋ ዩኒቨርቲ በትምርት በግብርና በርካታ ስራዎችን ከማከናወን ባሻገር በ2016 ዓ.ም በጊምቦ ወረዳ የግብርና ምርምር ማዕከል ለመገንባት ወደ ስራ መግባቱን በመግለጽ የግብርናን ስራ ዉጤታማ በማድረግና በማዕከሉ የስራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል መሆኑን በመግለጽ በቀጣይ በዑፋ ከተማ ደረጃዉን የጠበቀ ግንባታ እንዲገነባ ለዩኒቨርሲቲዉ አቶ እንዳሻው ከበደ እና አቶ ትብብሩ አሰፋ ፎቅ የሚገነባበት ሳይት ፕላን አዘጋተዉ ሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጴጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ በግላቸዉ ካፋን በዓለም መድረክ በማስተዋወቅና ለአከባቢዉ ማህበረሸብ በሰሯቸዉ የልማት ስራዎች ላይ ባሳዩ ዉጤት የዕዉቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። የጊምቦ ወረዳ መን/ኮሚ/ጉዳ/ጽ/ቤት::

ዓለም ላይ ያሉ ቢሊየነር 10  ሴቶች ዝርዝር
21/11/2023

ዓለም ላይ ያሉ ቢሊየነር 10 ሴቶች ዝርዝር

21/11/2023

Comedian napi in addis abeba street.

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮ መኸር  22800 ሄ/ር በላይ ሩዝ ለምቷል፣ ከዚህ ውስጥ 511 ሄ/ሩ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በ contract farming ያለማው ነው...
21/11/2023

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮ መኸር 22800 ሄ/ር በላይ ሩዝ ለምቷል፣ ከዚህ ውስጥ 511 ሄ/ሩ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በ contract farming ያለማው ነው።በመኸር ከለማው ማሳ 820,872 ኩ/ል ምርት ይጠበቃል። በኮርፖሬሽኑ አቅራብነት ምርት በኮሚባይነር መሰብሰብ ተጀምሯል።

የደ/ም/ ኢ/ህ/ ክ/ ም/ ፕሬዚዳንት

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

   እና  "በርካታ ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አንዲት መርከብ በድንገት በተከሰተ ከባድ ማዕበል ምክንያት ባህሩ ውስጥ ትሰጥማለች ። ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታድያ በአላህ ተአምር አንድ ሰው...
21/11/2023

እና

"በርካታ ሰዎችን አሳፍራ ትጓዝ የነበረች አንዲት መርከብ በድንገት በተከሰተ ከባድ ማዕበል ምክንያት ባህሩ ውስጥ ትሰጥማለች ። ከተሳፋሪዎቹ መካከል ታድያ በአላህ ተአምር አንድ ሰው ብቻ ይተርፋል ። ይህም ሰው በውሃው እየተገፋ አንዲት ደሴት ላይ ራሱን ያገኘዋል ።

እርዳታ ለመጠየቅ በደሴቷ እየተዘዋወረ ሰው ለማፈላለግ ቢሞክርም ምንም ዓይነት የሰው ዘር ማግኘት አልቻለም ። በአካባቢው ማዕብሉ ከሚያናውጠው ባህርና ከወፎች ድምፅ በስተቀር የሚሰማ ነገርም የለም ። በዚህን ግዜ በትንሽየዋ #ደሴት ውስጥ የሚኖረው ብቸኛው ሰው እርሱ ብቻ መሆኑን ሲያረጋግጥ በጣም ተጨነቀ ። ፍርሃትም አደረበት ። ከዚህ አስፈሪ ችግር ያወጣውም ዘንድ አላህን ለመነ ።

አንዳች የአላህ ተዓምር መጥቶ ወደ ቤቱ የሚመለስበት ሁኔታ እስኪፈጠር ግን በደሴቷ ውስጥ መቆየቱ እንደማይቀር በማሰብም የሚጠለልበት ትንሽ ግዜያዊ ጎጆ ቤት ሰራ ። አንገቱ ላይ ባንጠለጠለው ቦርሳ መሰል ይዞት የነበረውንም እቃ ጎጆዋ ቤት ውስጥ አስቀመጠ ።

ወደ ጫካው በመግባትም የተለያዩ የሚበሉ ፍራፍሬዎችንና ቅጠላ ቅጠሎችን ማግኘት ቻለ ። በዚሁ ሁኔታ በደሴቷ መኖር ጀመረ.....

ከዕለታት አንድ ቀን ምግብ ፍለጋ ወደ #ጫካው ሄዶ ሲመለስ ትንሿ ጎጆ ቤቱ በእሳት እየተቀጣጠለች ደረሰ ። በተመለከተው አጋጣሚ በጣም አዘነ ። የበለጠ ተስፋ የመቁረጥ ስሜትም አደረበት ።

"አላህ ሆይ! ለምንድን ነው እንዲህ ዓይነት ነገር የምትፈፅምብኝ!?" በማለትም በጣም አለቀሰ ።

በተከታዬ ቀን የሆነ ድምፅ ከእንቅልፋ ቀሰቀሰው ። ወደ ደሴቷ እየቀረበች የነበረች አንዲት መርከብ ናት ከእንቅልፋ የቀሰቀሰችው ። መርከቧ እሱን ለመውሰድ ነበር ወደ ደሴቱ የመጣችው ።

ሁኔታውን ማመን ያቃተው ሰውዬው "በዚህ አካባቢ እኔ መኖሬን ማን ነገራችሁ?" በማለት መርከቧ ላይ የነበሩትን ሰዎች ጠየቀ ። እነርሱም "ትናንት ከዚህ አካባቢ የሚወጣ #ጭስ አይተን ነው የመጣነው" ሲሉ መለሱለት ።

.....
እኛ ሰዎች አጋጣሚዎች ሁሉ መጥፎ ሲሆኑብን በቀላሉ ተስፋ እንቆርጣለን ። እንዲህ በቀላሉ መሸነፍ የለብንም ። ምክንያቱም አላህ እኛን በተመለከተ ሁል ጊዜ ስራ ላይ መሆኑን መዝምንጋት የለብንም ። በመከራችንና በህመማችን ወቅትም እንኳ ቢሆን እርሱ አይረሳንም ።"

fb ላይ ያነበብኩትና የወደድኩት ጽሁፍ ነው!!

መልካም ቀን

የአዲስአበባ ዩንቨርስቲ ከቦንጋ ዩንቨርስቲ ጋር በቅንጅት በቢጣ ወረዳ በጋወቲ ቀበሌ በስነ-ህይወት(Bio Technology) ዙሪያ የምርምር ስራዎችን ማከናወን የሚያስችለውን ጉብኝት አደረገበጉ...
20/11/2023

የአዲስአበባ ዩንቨርስቲ ከቦንጋ ዩንቨርስቲ ጋር በቅንጅት በቢጣ ወረዳ በጋወቲ ቀበሌ በስነ-ህይወት(Bio Technology) ዙሪያ የምርምር ስራዎችን ማከናወን የሚያስችለውን ጉብኝት አደረገ

በጉብኝቱም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ መስፍን በፍቃዱ፣ የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ አሻግሬ እንዲሁም ከሁለቱ ዩንቨርሲቲዎች የተዉጣጡ ምሁራን ተገኝተዋል።

ይህ አንጋፋ ዩንቨርሲቲ ከቦንጋ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለባዮ ቴክኖሎጂ ምርምር ስራዎች የሚሆነዉን ቦታ በወረዳው ጋወቲ ቀበሌ የመጀመሪያ ዙር ጉብኝት ያደረገው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስት በሀገርቱ ካሉ የተለያዩ ከፍተኛ የት/ትና ምርምር ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰራ ሲሆን አሁን ከቦንጋ ዩኒቨርስት ጋር በቅንጅት ከስነ ህይወት ጋር በተያያዘ የአካባቢዉን ኢኮኖሚና ስነ-ምህዳር የሚደግፉ ሳይንሳዊ ምርምሮችን ለማካሄድ የሚያስችል ቦታ ከሁለቱ ዩንቨርሲቲዎች የተዉጣጡ ምሁራን መጎብኘታቸው ነዉ የተገለፀው። መረጃው የቢጣ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን ነው

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

በኦሮሚያ ክልል ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች ከ5ኛ ክፍል በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ሰብል እንዲሰበስቡ መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል...
20/11/2023

በኦሮሚያ ክልል ሰብል በደረሰባቸው አካባቢዎች ከ5ኛ ክፍል በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ሰብል እንዲሰበስቡ መወሰኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን እንዳያበላሽም ከ5ኛ ክፍል በላይ የሆኑ ተማሪዎች ከሕዳር 11 እስከ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመመለስ ሰብል እንዲሰበስቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ትምህርት ቤቶችም ተማሪዎች ከሰብል ስብሰባ ሲመለሱ የባከነውን ክፍለ ጊዜ እንዲያካክሱ ማሳሰቢያ መሰጠቱን የክልሉ ኮሙኒኬስሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰቡ ዘንድ በፈዋሽነት የሚታወቅ ባህላዊ መድሃኒቶችን እያለማ ይገኛል::    &    በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አ...
20/11/2023

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰቡ ዘንድ በፈዋሽነት የሚታወቅ ባህላዊ መድሃኒቶችን እያለማ ይገኛል::

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በጊምቦ ወረዳ ጎጀብ አካባቢ ከባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት የተዘራው  ሩዝ ዘር ብዘት ማሳ የምርት ማሰባሰብ ስራ እየተካሄደ ይገኛል ።    &    በተጨማ...
20/11/2023

በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን በጊምቦ ወረዳ ጎጀብ አካባቢ ከባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት የተዘራው ሩዝ ዘር ብዘት ማሳ የምርት ማሰባሰብ ስራ እየተካሄደ ይገኛል ።

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

የ❤️ ከተማ 👈ከመላው ኢትዮጵያ መተው በአብሮነት የሚኖሩት ህዝቦቿ የፍቅር ከተማ ስለመሆኗ ይመሰክራሉ፣  የፍቅር ከተማ በመባልም ትታወቃለች ቦንጋ ከተማ!!ባለብዙ በር የንግድና እንቨስትመንት ...
20/11/2023

የ❤️ ከተማ 👈

ከመላው ኢትዮጵያ መተው በአብሮነት የሚኖሩት ህዝቦቿ የፍቅር ከተማ ስለመሆኗ ይመሰክራሉ፣ የፍቅር ከተማ በመባልም ትታወቃለች ቦንጋ ከተማ!!

ባለብዙ በር የንግድና እንቨስትመንት ከተማ እንድሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአስተዳደር እና ፓለቲካ ማዕከል እና የካፋ ዞን መናገሻ ናት ቦንጋ ከተማ ።

በማራኪ ስፍራ የተከበበች ዉብ ከተማ፣ ከ70 ሜትር በላይ ከፍታ ያለው ባርታ ፏፏቴ ከከተማዋ በ5 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል::

ከከተማዋ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኝ ጉርጉቶ የእግዜር የተፈጥሮ ድልድይ ሌላኛዉ ዉበቷ ነው::

ቦንጋ!! ዉብ፣ ፅዱ እና ነፋሻማ ስፍራ ያላት፣ ዙርያዋን በደኖች ተከባ በአራቱም አቅጣጫ ክረምት ከበጋ በሚፈሱ ወንዞች ባለቤት √ ታዲያ የት ይገኛል ዉበቷ!!!
ቦንጋ የ❤️ ከተማ

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

19/11/2023

እንጀራ በተለያየ ቀለም በቦንጋ የማምረቻ ማዕከል!
በቦንጋ ማምረቻ ማዕከል በመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚመረቱ ምርቶች ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆኑ ናቸው። dawuro tube

   (የአፋሩ እንግዳ) መሄዴ ነው ካፋ ፥ መሄዴ ነው ማጂ ፣እሱን ተከትዬ ፥ እንደ እናቴ ልጅ ፣ ይሉ ነበር  የሚለው ግጥም ለካስ እዉነት ነው አለኝ  ዛሬ ከአፋር ክልል ለሦስተኛ ዙር ስልጠ...
19/11/2023

(የአፋሩ እንግዳ)

መሄዴ ነው ካፋ ፥ መሄዴ ነው ማጂ ፣
እሱን ተከትዬ ፥ እንደ እናቴ ልጅ ፣ ይሉ ነበር የሚለው ግጥም ለካስ እዉነት ነው አለኝ ዛሬ ከአፋር ክልል ለሦስተኛ ዙር ስልጠና የመጣዉ አንድ ከፍተኛ አመራር

እናማ ቀጠለ ስለ ቦንጋ...

ቦንጋ የፍቅር ከተማ ናት

እንግዳ ስመጣ ቦንጋዎች #ኖር ብለው በፍቅር ሲቀበሉ አይቻለው::

ለካስ ለዚህ ነው #ሰው ከፈለክ ወደ ካፋ ሂድ ይባል ነበር እኛ አከባቢ አለኝ::

👉እና እንዴት አየሄዉ?? ቦንጋ ላይ ቆይታ እንዴት ነበር ስለው?? መልሱ አለኝ በአጭሩ

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል ርዕስ መንግስት የያዘዉን አቅጣጫ ተግባራዊ ለማድረግ በተለይ ደቡብ ምዕራብ ክልልና አካባቢዉ እጅግ በጣም ምቹ ነው አለኝ!! በርግጥ እዉነት ነው::

ከዛም ቀጠለና ዳግም እድሉን ባገኝ ካፋና አካባቢዉን ዙሬ ሀብቷን፣ ታሪኳን፣ ፍቅሯን ቢጎበኝ ደስታዬን አልችልም ብሎኝ ከቦንጋ ከተማ እስከ ዉሽ-ውሽ ሻይ ልማት ያለንን ቆይታ አጠናቀን ቻው ቻው ተባብለን ተቃቅፈን ተለያየን::

19/11/2023

ረጅም እድሜ ለእናቶቻችን

አርሶ አሳዳሪአችንን «አሻም» እንበለው!                  (በዮሐንስ ክፍሌ)ታላቁ ሙዚቀኛ ባህሩ ቀኜ “የገበሬ ለዛ” የሚል ርዕስ በሰጠው ዜማው እንዲህ ብሏል።..«እነጋገራለው ከገበ...
19/11/2023

አርሶ አሳዳሪአችንን «አሻም» እንበለው!
(በዮሐንስ ክፍሌ)
ታላቁ ሙዚቀኛ ባህሩ ቀኜ “የገበሬ ለዛ” የሚል ርዕስ በሰጠው ዜማው እንዲህ ብሏል።
..«እነጋገራለው ከገበሬው ጋራ፥
እነጋገራለው ከገበሬው ጋራ
እንዲያመርት ደግ አርጎ በደጋ በቆላ
የኢትዮጵያ ሰው ሁላ
ችግር እንዳይገባ
ችግር እንዳይገባ...»

ከብዙ ዘመናት በፊት የተዜመ ቢሆንም የንግግር፣ የመመካከር ዋጋ አሁን ላይ ገብቶን “የምክክር ኮሚሽን” አቋቁመናል። የምክክሩ አካል የሀገሪቱን ዋልታና ማገር ገበሬውንም ያሳትፋል።

ይህቺ የምንወዳት፣ ጉዳቷ እረፍት የሚነሳን፣ ረሃቧ ጠኔ የሚጥልብን፣ ሽርፍራፊ ደስታዋ ከዓለም ፍጥረታት ሁሉ የበለጥን ደስተኞች የሆንን ያህል የሚንጠን እና የእርሷን ጉዳይ አስበንም ይሁን ያሰብነውን ሁሉ ሰርተንላት የማይሆንልን «ውለታችን ኢትዮጵያ» የተወሳሰበ ችግሯ ብዙ ነው። ስሟ ለአፋችን ቢጣፍጠንም፣ ውበቷ ቢማርከንም፣ ችግሯ ይደቁሰናል። ሀዘኗ ይጎዳን-ይገድለን። [ግን ግን] በፍቅሯ ሁሉን እንችላለን! የሀገሩን ደስታና ሀዘን ከምድሯ ሆኖ ለሚቋደስ ተስፋ መቁረጥ ነውር ነው።

እንደው፤ የሀገር ሰው ወዳጃችን!

መፍትሔ የሌላቸው ሳይሆን ከሰራን የምናሸንፋቸው ስንክሳሮቿ በሙሉ ከእኛ ጉብዝና የበለጠ ጉልበት ያላቸው አይደሉም። እኛ በሀገር ተስፋ መቁረጥ ሆኖልን የማያውቅ ለመፃፍም ለመናገርም የከበደ ተዓምር ተሰርቶ የተገነባች ሀገር ሰዎች ነን። ተስፋዎቿም እንደ ብሒሉ “ላም አለኝ በሠማይ” ዓይነት አይደሉም። በፍፁም። ምክንያት ከተጠየቀ ደግሞ ከህዝቧ ቁጥር ሰባ እጅ ከመቶ ጉልበተኛና እውቀት ያለው ወጣት ነው እንላለን።

ስናጠይቅ ግን፤ ይህ ከጠዋት እስከ ማታ ሲያርስ፣ ሲኮተኩት፣ ሲታትር የሚውለው የሀገሬው ገበሬ ለምን ጠግቦ ማደር ተሳነው? ያንን «ጥረህ ግረህ ብላ» የተባለውን ቃል አክባሪ የሀገር ሰው አርሶ አሳዳሪአችን ለምን የልፋቱን ያህል ምርት አልታፈስ አለው? እንዴትስ ከማሳው እየዋለ ጎታው አልሞላልህ አለው?

ለዚህ መጠይቅ መልሱን ገበሬው እንዲያውቅ በበቂ ሁኔታ አለመሰራቱ፣ በትንሽ ጉልበት ብዙ ምርት እንዲያገኝ የሰለጠነውንም ዓለም አሰራር በማስተማር እንዲተገብረው አለመደረጉ፣ ከመቶ ዓመታት በፊት ባገለገሉ መሳርያዎች መጠቀሙና “ልጆቼ ከሰው ደጅ እንዳይውሉ አንተ አገዝከኝ” እያለ ውለታ ከሚቆጥርለት በሬው ጫንቃ ያላለፈ የአስተራረስ ልማዱ እዚህ ጋር እንዲገኝ አድርገውታል።

በሌላው ዘርፍ ምንም ያህል ቢሰራም ሆነ ቢለፋ የገበሬው ማሣ አብቦና አሽቶ ፍሬ ካልተገኘበት የትም አይደረስም። ያልበላ ሰው በቅጡ ማሰብም ሆነ መስራት አይቻለውም። የሚበላው ሁሉ ከገበሬው የሚበረከት ስለሆነ። እርሱና ያ ምስጋናውን ይቀበልለት አገናዛቢ ልቦና ያልታደለው፣ በዜማና በእንጉርጉሮ እየተሞካሸ ከሁሉ በላይ አጋሩ የሆነለት በሬው ያረሱት ሀገር ሊያጠግብ አልቻለም። እናም ኢትዮጵያ የከበረ ስሟ (የምንወደው) ከስንዴ ተረጂዎች ዝርዝር ውስጥ አለ። “በልተው ማደር ለማይችሉቱ ኢትዮጵያውያን” እያለ ገለባ የሚሰፍርልን መበርከቱን እንደ ውለታ መቁጠር የለብንም።
«እጅህን ስጥ አለኝ ፈረንጅ፥ እጅ ተይዞ ሊወሰድ» ያልነው ጥንት ነዋ!

የግብርናችን ወደኋላ መቅረት በርካታ ምክንያቶች አሉት።

የመጀመርያው ከላይ እንዳስነበብነው ዘመናዊውን የስራ ባህል፣ ቴክኖሎጂውን ያም ካልሆነ የተሻለ ምርት በሚያስገኙ ሀገር በቀል እውቀቶች እንዲጠቀም ማድረግ አለመቻሉ ነው።

ሁለተኛው ትውልዱ ሁሉ ግብርናን እንደ አንድ የሙያ መስክና ኑሮን የማሻሻል አቅም ያለው ዘርፍ አድርጎ የማሰብ ሁኔታ በሚያስገርም ሁኔታ ዝቅ ያለ መሆኑ ነው። ለአብነትም አንድ አምስት ቤተሰብ የሚያስተዳድር አባወራ ጉልበቱ እስካልከዳው ድረስ እያረሰ ቤተሰብ ያስተዳድራል፣ ልጆቹን ያስተምራል፣ ሀገር የምትፈልገውን ግብርም ሆነ የእርሱን እርዳታ ለሚሻ ሀገራዊ ጉዳይ ያዋጣል። አንዳንዴም ከአቅሙ በላይ ሲያበረክት ተስተውሏል። ለህዳሴ ግድብ ይሰጠው ያልነበረው አንድ የዚህች ሀገር ፍቅር ያንገበገበው አርሶ አደር ከጫካ ሚዳቆ አድኖ መስጠቱን ሰምተናል። ለሀገር እንዲህም ይኮናል። ይህ የስነ-ልቦናችንን ውቅር ረቂቅነት እንድናስተውል እድል የሚሰጥ ነው።

እንዲህ የሚያደርግ አባወራ አቅሙ ሲደክም ግን የእርሱን ጉብዝና ተረክቦ እንኳንስ ሀገርን በግብርና ስራ ቤተሰቡን ከችግር የሚያስመልጥ እሳቤ እንዲይዝ አልተደረገም።

“መሬታችንን በበቂ ሁኔታ አለማልማታችን ሀገራችንን ለልመና እጅ አስዘረጋት” ተብሎ በደንብ አልተነገረውም። ይህን ተረድቶ ቢሆን ኖሮ፣ በነጭ አፍ “ተረጂ” መባሏን በሚገባው ቋንቋ ከቀዬው ተደርሶና ተነግሮት ሲገባው እርግጥም እንቅልፍ አይተኛም። ክብር በተረት የሰማው ሳይሆን ዋጋ የተከፈለበት ቁም-ነገር መሆኑን ይረዳል። “በሀገርህ መደህየት ይኽንን ክብርህን እያጣኸው፤ ለገርህ ላይ ሊዘባበቱባት ነው” ሲባል አያስችለውም። እምባው ሊቀድመው ይችላል እንጂ ደሙ ይፈላል። ተማርን የምንለውም ይህንን አላስረዳነውም። ይሰራላታል!

እንደሰለጠነ የሚነገርለት ከተሜውም ልጆች የግብርናን እና የገበሬውን የሀገር ዋልታና ማገርነት እንዲረዱ በማድረጉ በኩል አዎንታዊ አበርክትዎ አለው ብሎ ማሰብ አይቻልም። ከተሜው ጓሮውን አርሶ በቀላሉ በተጣሉበት በቅለው ለምግብነት የሚውሉ አትክልትን እንኳን አያለማም። ካለማም እጅግ ትንሽ ነው። የቤቱ ራስ እድሜ ሲጫነውና ሙያውን አዲሱ ትውልድ ባለመረከቡ እማወራ እህል ልትሸምት ገበያ ትወጣለች፤ ከመሸጥ ወደ መግዛት ስትገባ የከተማ ኑሮ “ሲኦል” ወደመሆን ተሸጋገረ። የከተማ ሰው በተለይም መንግስት ሰራተኛው ሊናገረው የሚያሳፍረው ችግር በዝቶበታል።

ዛሬ ላይ ሀገራችን ላጋጠሟት አብዛኞቹ ችግሮች ግብርና በቂ መልስ አለው። አምርቶ የሚመገብ ሀገር እና ህዝብ ፈፅሞ የባዕድ ሀገር ተፅዕኖ አያርፍበትም። ማንም እየተነሳ የራሱን እሳቤና የጥቅም ቀንበር ሊጭንበት አይደፍርም። “ስንዴ ስለሰጠውህ እኔ ነኝ የማውቅልህ” ዓይነት ዛቻና የቀን ህልመኝነት ከወዲያ ሀገራችን ላይ ሊወረወር ምኞት ያሳደረው ሌማታችን በመጉደሉ እንጂ ለሀገራችን ክብር ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀን መሆናችንን ራሱ ባዕድ ያውቀዋል። አሁን ግን ሀገር ክብሯን የሚያሳጣት የቅኝ ገዢነት ቅዠት ያናወዛቸው ብቻ ሳይሆን መሬታችንን አለማልማታችን መሆኑን በግልፅ መተማመን ያስፈልጋል።

እየራበንም ቢሆን ስንቱን ማስፈራርያ እንዳለፍነው እናውቃለን። ይህ በሀገራችን ላይ በመሞከሩም ቁጭት ይንጠናል። ሁሉን ተቋቁመን ያለፍነውም ያሳለፍነውም ምን ቢከፋን ምን ብናጣ ገመናችንን መሸፈኛ ሀገር ስላለችን ነው። ከሀገር የሚቀድም ምንም፤ ከኢትዮጵያ የሚበልጥብን አንዳች የለም-ታሪክ ምስክራችን ነው።

በቁጭት መንገብገባችንን በስራ ማድረግ ይገባናል። ባንራብና ባንቸገር እርዳታ አያስፈልገንም። እርዳታ ባንሻ ደግሞ ሀገራችንን ሊቀማን ጠላት አያሰፈስፍም ነበር። በግራ እጁ ሽራፊ ፍራንክ ወርውሮልን ስንት ተዓምር ተሰርቶ፣ ስንትና ስንት ዋጋ ተከፍሎ የቆየችን ሀገር ሊወስድብን አይሞክርም ነበር። ስራ፥ ከስራም ግብርና እኛን እና ሀገራችንን ከችግር ፈልቅቆ የሚያወጣን መዳኛችን ነው። ለኢትዮጵያ ጠላቶች ደግሞ የቀን ህልማቸው “ሲሳይ” እንዳልሆነ መናገሪያ ቋንቋችን ስራ ነው።

ሰማይ የደረሱ የሚመስሉ የችግሮቻችንን ተራሮች መደርመሻ ድማሚት ያለው በማሳችን አፈር ላይ ነው። መጠቃታችን ዕረፍት ነስቶንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጀምሮ “መቸገራችን በበቂ ሁኔታ ባለማረሳችን ነው” በሚል እሳቤ መሬት ፆም እንዳያድር ተማምለናል። በየመድረኩም በየማሳውም። መሪው ጠረጴዛ እየደበደበ፤ አርሶ አደሩም በእልህ አፈሩን እየቆፈረው በሬውም ከእርሱ እኩል ነጭ ላብ እያላበው እየሰራን ነው። ግን እጅግ በጣም ጥቂት ነው።

ከአርሶ አደሩ ማሳ የሚውሉ፣ ኑሯቸውን ከገበሬው በጉርብትና ያደረጉ፣ እየተዋቀሱም እየተመሰጋገኑም ውሎአቸውን በባላገር፣ በገበሬው ቀዬ ያደረጉ ባለሙያዎችን “ከቀልደኛው” መለየት ከመንግስት ይጠበቃል። ከእውነት መሸሽ እስካልተቻለ ድረስ፤ በዘመን ብዛት አሻራቸው እንዳይደበዝዝ አድርገው ደማቅ ታሪክ የሰሩ የግብርና ባለሙያዎች አሉን። ከገበሬው ጋር አብረው የመኖርን ያህል የሚተጉትን ባለሙያዎች መሸለምና ማበረታታት፤ ለስራቸውም እውቅና መስጠት ይገባል።

በአንፃሩ ደግሞ ገበሬውን የማያውቁት እርሱም የማያውቃቸው፤ አድራሻውም የማይታወቅ የግብርና ባለሙያ ብዙ ነው። ኑሮው በከተማ ገበሬው ያለው ደግሞ በባላገር። ይኼ ሊታረቅ የማይችል ተቃርኖ መሆኑ ልብ ይባል። ከገበሬ እማ ወራ ጋር [ገበያ ላይ ብቻ] የሚተያይ የግብርና ባለሙያ እንዳለ መንግስት ሊያውቅ ይገባል።

የመሬት አስተዳደር ህጎችን መፈተሽና እንደየአካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ ሌላኛው መፍትሔ ነው። “መሬት ፆም ማደር የለበትም” በሚል መርህ እየተሰራ ነው ቢባልም አሁንም ለዓመታት ዳዋ የለበሱ መሬቶች መኖራቸውን ፈትሾ ማረጋገጥና ማልማት ግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል።

ለአብነትም የተለያዩ ተቋማት የያዟቸውን መሬቶች በሚፈለገው ልክ እያለሙ እንዳልሆነ መገንዘብ ይቻላል። ሌላው ቀርቶ ጠመኔ እና ወረቀት መግዛት ከተሳናቸው ትምህርት ቤቶቻችን መካከል አብዛኞቹ በጫካ የተዋጡ፤ ጫካዎቻቸውም የሙዝና የብርቱካን፣ የማንጎና አቮካዶ ደኖች አይደሉም። የባህር ዛፍ እንጂ። ባህር ዛፍ መሬታችንን ይበላዋል እንጂ አንመገበውም። ቤት መስሪያ ነው ከተባለ ደግሞ ሳይበላ የሚታደርበት ቤት አይደላም። ተሽጦ ገንዘብ ነው ከተባለ ደግሞ ገንዘብ የሚገዛው ዞሮ ዞሮ ምግብን ነውና ምግቡ በቂ ስለማይሆን ጠንከር ያለ የመሬት አስተዳደር ህግ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል።

የእምነት ተቋማትን ሰፋፊ መሬቶችም በቀላል ውይይቶች በበቂ ሁኔታ እንዲያመርቱ ማድረግ ይቻላል።

በርካታ ወጣቶች የመንግስት ሰራተኝነትን ብቻ እንደ ትልቅ ስኬት የመቁጠራቸው አባዜ በእውቀት እንዲሸነፍ መስራትና ማስተማር የሁሉንም አካላት ትብብር ይጠይቃል። በቂ መሬት በመስጠት በግብርናው ዘርፍ እንዲሰማሩና ውጤታማነታቸው እንዲረጋገጥ ትኩረት መስጠትም መፍትሔ ነው። በአዲሱ ስርዓተ-ትምህርት የእርሻ ትምህርት መካተቱን ልብ ይሏል።

ያላቸውን መሬት በበቂ ሁኔታ አልምተው የገበያውን ቃጠሎ የሚያበርዱ አርሶ አደሮች አሉ። እነኚህ አርሶ አደሮች ምርቶቻቸውን ለገበያ የሚያቀርቡበት የመንገድ መሠረተ-ልማት እና በቂ የሆነ የገበያ ትስስር ሊፈጠርላቸው ይገባል። በተያዩ አካቢዎች፤ በርካታ አርሶ አደሮች የሚያጓጉዙበት መንገድና የሚሸጡበት ገበያ አጥተው ምርታቸው ሲበሰብስና ሲጣል ቦንጋ ኤፍ 97.4 በተደጋጋሚ ዘግቧል። የሚመለከታቸው አካላትም ጥያቄን በንግግር ከመመለስ ያለፈ እርምጃ ሲወስዱም በበቂ ሁኔታ አልተስተዋለም። ይህ ለነገ ሳይባል ያለ እረፍት ታስቦበት አቅም በፈቀደ መጠን ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

የከተማ ግብርና ቅንጦት ሳይሆን በልቶ የማደር ጉዳይ ተደርጎ እንዲታሰብ መስራት ያስፈልጋል። የዘመነው ዓለም ተርፎት ለድሃ መለገሱን እና ተመፅዋቹም ድሃ መሆኑን ደጋግሞ የሚናገረው በዚህ ዘርፍ በማስተዋል በመስራቱ ነው። ህንፃዎች አትክልት ማብቀል እንዲችሉ ተደርገው እየተገነቡ ነው ባደገው የዓለም ክፍል። ስለዚህ የእኛ አካባቢ የከተማ ነዋሪ ቢያንስ ጎመን እና ሰላጣ ተክሎ ያልጠወለገ ነገር ተመግቦ ጣዕሙና ጥቅሙ ለበለጠ ስራ እንዲያበረታታው መሞከር ይቻላል። በዚህ የገበያውን ሁኔታ ማረጋጋት እንደሚቻል ይታመናል።

በመጨረሻም ሁሉም ሙያ ገበሬውን፤ ሁሉም እውቀት ግብርናውን ቢደግፍ ውጤትና እርካታው ዘመናት የሚፈጅ እንደማይሆን ትልቅ ተስፋ አለ። ይህንን ተስፋ በቁጭትና በሀገር ፍቅር ስሜት በመስራት እርካታ ማድረግ ይቻላል።

በመግቢያችን ላይ ያነሳነው የባህሩ ቀኜ ሙዚቃ ገበሬን እያወደሰ ሀገር መውደድንም በእርሱ በኩል የገለፀበት ግጥሙ፤

«ፈረንጅ ካመጣው ከዚያ ሁላ ብረት፣
ከዚያ ሁላ ብረት፥ ከዚያ ሁሉ ጣቃ
ለልማት የሚሆን ማረሻ እንዴት ይውጣ?
ስጋ ጠቅሞ ጠቅሞ ለነፍስ የሚበቃ
አሁን ማን ያውቃታል የገበሬን ለዛ?
አሁን ማን ያውቃታል የማረሻን ለዛ?
ስጋ ጠቅሞ ጠቅሞ ከንፈር የሚያወዛ

እህል በያይነቱ የሚገኝብሽ
ጠቦትም ሙክትም ሁሉም በያይነቱ የሚገኝብሽ
ማርና ቅቤውም ሁሉም በያይነቱ፣
ኬሚካል የሌለው የሚገኝብሽ
አየርሽ ጨፌሽ ወደርም የለሽ
የሀገር መዲና ኢትዮጵያ አንቺ ነሽ...»

እያለ ይቀጥልና ገበሬው ጋር ቀርቦ መነጋገርና ሀሳብ ማጋራት አስፈላጊ መሆኑን ይጠቁማል።

«...ምርት አምራች ደግ ነው የኢትዮጵያ መሬቱ
ገበሬው ሲሰለፍ ቀን እስተለሊቱ
ያበድራል እንጂ አይወጣም ከቤቱ።
እነጋገራለሁ ከገበሬው ጋራ
እንዲያመርት ደግ አርጎ በደጋ በቆላ...» ይላል

እኛም፤ አርሶ አሳዳሪአችን ገበሬውን «አሻም» እንበለው!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ  በከፋ ሀገረ ስብከት ዴቻ ወረዳ  የጭሪ አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱ በተከበረበት  መርሐ ግብር  ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የ...
18/11/2023

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በከፋ ሀገረ ስብከት ዴቻ ወረዳ የጭሪ አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተጠናቆ ቅዳሴ ቤቱ በተከበረበት መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሐላፊና የከፋ ቤንች ሸኮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ቶማስ የመተከልና የአዊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጸሎተ ቡራኬ ተባርኮ ታቦተ ሕጉ እንዲገባ ሆኗል።

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

Green and productive land
18/11/2023

Green and productive land

18/11/2023

ትግራይ: ኦሮሞ የሚል ስም እግዚአብሔር አያዉቀንም

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንሰቲትዩት ቦንጋ ማዕከል  በቋሚና ዓመታዊ  ሰብሎች ላይ በርካታ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህም የቡና ምርምር ስራ ዋነኛው ሲሆን...
18/11/2023

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንሰቲትዩት ቦንጋ ማዕከል በቋሚና ዓመታዊ ሰብሎች ላይ በርካታ የምርምር ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል። ከእነዚህም የቡና ምርምር ስራ ዋነኛው ሲሆን አካባቢው እንደ ቡና መገኛነቱ በርካታ ምርታማ የዘረ-መል ክምችት ያለ መሆኑን ሰፊ ጥናታዊ ጽሁፎች ላይ ማግኜት ይቻላል።

ይህ ብቻ በቂ ያለመሆኑን ያመኔው ማዕከሉ በካፋ ባዮስፈር የሚገኙትን 130 ዘረ_መሎችን እና ከክልሉ ከተለያዩ ዞኖች 136 በድምሩ 266 የተለያዩ ዘረ_መሎችን በመሰብሰብ የcharacterization and evaluation ስራዎች በሞዲዮ ንዑስ ማዕከል እየተከናወነ ይገኛል:: ውጤቱ ስጠናቄቅ የአካባቢው የቡና ምረታማነትና በሽታ የመቋቋም ችግርን ይፈታል ተብሎ ይታመናል።
&

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:
📌 #ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D
📌 #በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914
📌 #ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

18/11/2023

በ1529 የተመሠረተው የጭር አ/ም/ቅ/ም/ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ በድምቀት ይመረቃል::የቤተ ክርስቲያኑ  ዉብ ገፅታ::    &    በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን...
17/11/2023

በ1529 የተመሠረተው የጭር አ/ም/ቅ/ም/ቤተ ክርስቲያን ህንፃ ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ በድምቀት ይመረቃል::
የቤተ ክርስቲያኑ ዉብ ገፅታ::
&

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:

📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914

📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

የታሪካዊው የጭሪ አንቀፀ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ ከነገ ጀምሮ በድምቀት ይደረጋል።በ1529 ዓ.ም የተመሠረተውና ታሪካዊው እንዲሁም ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ ሊሆን የ...
17/11/2023

የታሪካዊው የጭሪ አንቀፀ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ ከነገ ጀምሮ በድምቀት ይደረጋል።

በ1529 ዓ.ም የተመሠረተውና ታሪካዊው እንዲሁም ከፍተኛ የቱሪስት መስህብ ሊሆን የሚችለው አንቀፀ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ግዙፉ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን የግንባታ ስራው ተጠናቆ ከነገ ህዳር 8 ቀን 2016 እስከ ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም በድምቀት ምዕመናን በተገኙበት ይካሄዳል።

በካፋ ዞን በአውራዳ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው በህንጻ ቤተክርስቲያኑ ምረቃም ስነስርዓት መርሀግብር ላይ ሊቃነጳጳሳት፣ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞን፣እንድሁም የተለያዩ የሀይማኖቱ ተከታዮችና ሌሎችም በተገኙበት በደማቅ ስነስርዓት የሚከበር መሆኑ ነው የተገለፀው። መረጃው የአዉራዳ ከተማ መ/ኮ/ ጉ ነው::

&
በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:

📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914

📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ከዓለም ባንክ የሥራ ሀላፊዎች ጋር በከተማ አጀንዳ ድጋፍና አተገባበር ዙሪያ ውይይት አደረጉየከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ...
17/11/2023

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች ከዓለም ባንክ የሥራ ሀላፊዎች ጋር በከተማ አጀንዳ ድጋፍና አተገባበር ዙሪያ ውይይት አደረጉ

የከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ የዓለም ባንክ የሚያደርገው ድጋፍ ኢትዮጵያ ሀገራችን ያላትን የቆዳ ስፋት፣ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥርና የከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የከተሞችን መሠረታዊ ፍላጎትና ጥያቄዎችን ለመመለስ ከፍተኛ አቅም የፈጠረ መሆኑን አንስተው ነገር ግን ተጨማሪ የድጋፍ አማራጮ እንድታዩ ለልዑኩ አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:

📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914

📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ባለሙያዎች ድጋፋዊ ክትትል ሳይንሳዊ ይዘቱን ጠብቆ በክፍል ውስጥ መማር ማስተማር ላይ እንደሚያተኩር ገለጹ።የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ባለሙያዎች ከተለ...
17/11/2023

የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ባለሙያዎች ድጋፋዊ ክትትል ሳይንሳዊ ይዘቱን ጠብቆ በክፍል ውስጥ መማር ማስተማር ላይ እንደሚያተኩር ገለጹ።

የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ባለሙያዎች ከተለምዷዊ የድጋፍና ክትትል ስርዓት ተላቆ በክፍል ውስጥ መማር ማስተማር ፣የተማሪው የመማር ሁኔታ፣ የክፍል አደረጃጀት፣ የተከታታይ ምዘና ስርዓትና የዕለታዊ ትምህርት ዕቅድ ዝግጅትና አተገባበር ላይ ሳይንሳዊ ይዘቱን ጠብቆ ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ጥናት ላይ የተመሰረተ ዉይይት አካሂዷል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የካፋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ተፈሪ ታደሰ የተማሪዎችን የመማር ሁኔታ በመቀየር ተማሪዎች በቂ ዕውቀት እንዲይዙ ማድረግ ያስፈልጋል ብሏል።

የትምህርት ባለሙያዎች አዳዲስ ዕውቀቶችን በማስፋት የተሻለ የማስተማሪያ ስነ-ዘዴ ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ሳይንሳዊና ወቅታዊ የምርምር ውጤቶችን የትምህርት ስርዓታች እንዲጠቀም በማድረግ ድጋፋዊ ክትትሉ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ እንድሆን ኃላፊዉ አሳስቧል።

አዲሱ ፍኖተ ካርታ የተማሪዎች ዕውቀት ምዘና ከኩረጃ የፀዳ እንዲሆን ያተኮረ በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሩ ተማሪዎች ብቁ እንዲሆኑ የማስቻል ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት የተጣለባቸው በመሆኑ ከመቸውም ጊዜ በላይ ታሪክ በመቀየር ከውድቀት ማንሳት እንዳለባቸው አቶ ተፈሪ ታደሰ ተናግሯል።

ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተማሪ ተኮር የማስተማሪያ ስነ-ዘዴ በመጠቀም የትምህርት ስርዓቱ ላይ እየታየ ካለዉ ዉድቀት ለመነሳት የሚደረገው ጥረት በግንባር ቀደምትነት እንዲመሩ ጥሪ አቅርቧል። ዘገባው የዞኑ መንግስት ኮ/ ነው

ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በባሏ እናት ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመችዉ ግለሰብ በዕድሜ ልክ እስራት መቀጣቷ ተገለጸ። የጭዳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የምርመራ መዝገብና የኮንታ ዞን የልዩ ልዩ ወን...
16/11/2023

ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በባሏ እናት ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመችዉ ግለሰብ በዕድሜ ልክ እስራት መቀጣቷ ተገለጸ።

የጭዳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የምርመራ መዝገብና የኮንታ ዞን የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳዉ ተከሳሽ አብዮት ኡታ የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንባት የቻለዉ የባሏን ወላጅ እናት በስለት በመዉጋትና አስክሬናቸዉን በእሳት በማቃጠሏ ጥፋተኝነቷ በማስረጃ በመረጋገጡ ነዉ።

በኮንታ ዞን የጭዳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ፈለቀ ታምሩ የወንጀሉን ዝርዝር እንደገለፁት ተከሳሽ አብዮት ኡታ በከተማ አስተዳደሩ መዳ ያጃ ቀበሌ ነሐሴ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 5:00 ሰዓት የባሏ እናት ጋር በመካከላቸዉ በተፈጠረዉ አለመግባባት ምክንያት የግል ተበዳይ ወላጅ እናቴን ሰድበዉብኛል በሚል ቂም በመያዝ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ ግድያ በመፈፀሟ በቁጥጥር ስር እንድትዉል መደረጉን ተናግረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት የምርመራ ቡድን በማደራጀት ባደረገዉ ምርመራ የግል ተበዳይን ልጃቸዉን አግብታ ስትኖር ከአማቿ ጋር ዘወትር እንደማይግባቡና በዕለቱ የተፈጠረዉን አለመግባባት ምክንያት በማድረግ የግል ተበዳይ ማዕድ ቤት ድረስ በመሄድ በቡና ዘነዘነ ማጅራታቸዉ ላይ በመመምታት የደረሰባቸዉን ምት መቋቋም አቅቷቸዉ መሬት ላይ በወደቁበት ትታ መሄዷን ገልፀዋል።

በመቀጠልም ወደመጣችበት በመመለስ ቢላዋ በማምጣት የግል ተበዳይን በወደቁበት ጉሮሮዋቸዉን በመቁረጥ፣በቀኝ ጆሮ ግንድ እስከየላይኛዉን መንጋጋቸዉን በመክፈል ህይወታቸዉ እንድያልፍ ካደረገች በኃላ ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ አስክሬኑን በእሳት ማቃጠሏን ተጠርጣሪዋ ለፖሊስ በሰጠችዉ የእምነት ቃል እና በህክምና ማስረጃ መረጋገጡን አስረድተዋል።

የጭዳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን በተከሳሿ የእምነት ቃልና በህክምና ማስረጃ በማደራጀት መዝገቡን ለኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ክስ እንዲመሠረት እንደተላከ ገልፀዋል።

በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ የደረሰዉን የምርመራ መዝገብ መርምሮ ግለሰቧን በከባድ የሰዉ ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶባት ኮንታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧታል።

የኮንታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከዐቃቤ ህግ የቀረበልትን የክስ መዝገብ ግራ ቀኙን ሲመረምር ተከሳሿ የገዛ ባሏን እናት ለምን ሰደቡኝ በሚል ቂም በመያዝ አሳቻ ጊዜ በመጠበቅ በሰዉ ልጅ ላይ ሊፈፀም በማይገባና በዘግናኝ ሁኔታ የግል ተበዳይን በመግደልና አስክሬኑን በእሳት በማቃጠል በፈፀመችዉ ከባድ የግድያ ወንጀል በማስረጃ በመረጋገጡ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ነች ሲል የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

በዚሁ መሠረት የኮንታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ባስቻለዉ የወንጀል ችሎት የተከሳሿን የህይወት ታሪክ፣የትምህርት ደረጃ እና ለወንጀሉ መፈፀም ያነሳሳዉን ከግምት ዉስጥ በማስገባት ሌሎችን ያስጠነቅቃል ተከሳሿን ያስተምራል በሚል ተከሳሽ አብዮት ኡታ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ዉሳኔ መስጠቱን የኮንታ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና ገፅታ ግንባታ ያደረሰዉን መረጃ ጠቅሶ የክልሉ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚንኬሽን ዘግቧል።

ከዩንቨርሲቲ ተመርቆ አሁን በግብርና ሥራ ላይ ያለ ወጣት በጠሎ ወረዳ!!Camara  በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡: ...
16/11/2023

ከዩንቨርሲቲ ተመርቆ አሁን በግብርና ሥራ ላይ ያለ ወጣት በጠሎ ወረዳ!!
Camara

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:

📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914

📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

16/11/2023

ካፋ ዞን በተፋጥሮ የታደለ ሲሆን ከቦንጋ ከተማ በ12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኝ ጉርጉቶ የእግዜር የተፈጥሮ ድልድይ በጋዜጠኛ ታምሩ ማሞ

🔵🔴ሁላችሁም invite አድርጉ , & page

https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:

📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914

📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

16/11/2023

Anteneh Birihanu, Lukas Bini, and Alazar-

&

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነየሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥ...
16/11/2023

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ገብተው በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠና የሚወስዱ ተማሪዎች የመግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል፡፡

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተገድቦ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእድገት መሰላል እስከ ደረጃ 8 ድረስ እዲሆን መደረጉ ተገልጿል።

ይህም ፖሊሲው ደረጃ ስድስትን ከመጀመሪያ ዲግሪ፣ ደረጃ ሰባትን ከማስተርስ እንዲሁም ደረጃ ስምንትን ከዶክትሬት ዲግሪ ትይዩ እንዲሆን አድርጓል።

ስለሆነም በዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ መግባት ቢፈልጉ በደረጃ 6 ገብተው መሰልጠን እንደሚያስችላቸው አመላክተዋል፡፡

ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ 6 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች እንደሚስተናገዱ ጠቁመው÷ በዚህ ዓመት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በክልሎች አማካኝነት የሰልጣኞች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል፡፡

በዚህም በተያዘው የሥልጠና ዘመን 632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን የሰው ሃይል ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 እንደ ውጤታቸው ተመድበው እንደሚሰለጥኑም ጠቅሰዋል፡፡

በወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ደረጃ አንድ እና ሁለት 110 ሺህ 15 ፣ በደረጃ ሦሰት እና አራት 412 ሺህ 557 እንዲሁም በደረጃ አምስት 110 ሺህ 15 ሰልጣኞች እንደሚሳተፉ አንስተዋል፡፡

በደረጃ ስድስት ደግሞ 2 ሺህ የሚሆኑ ሰልጣኞችን ለቀመበል ዝግጅት እንደተደረገ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የ2016 የስልጠና ዘመን የተዘጋጀው መቁረጫ ነጥብ የ2015 ትምህርት እና የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናልም ብለዋል፡፡

ከ2014 ዓ.ም በፊት ለነበሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደግሞ በስልጠና ዘመኑ በነበረው መቁረጫ ነጥብ መሰረት እንደሚስተናገዱ ተጠቁሟል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ያዘጋጀው የመግቢያ ነጥብ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ቀርቧል።

በካፋ ዞን በጠሎ ወረዳ ሽናቶ ቀበሌ በፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች አክስዮን ማህበር በሃሻ ክላስተር የለማ የብዜት ገብስ በፎቶበተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻ...
16/11/2023

በካፋ ዞን በጠሎ ወረዳ ሽናቶ ቀበሌ በፐርፐዝ ብላክ ኢቲኤች አክስዮን ማህበር በሃሻ ክላስተር የለማ የብዜት ገብስ በፎቶ

በተጨማሪም የቪዲዮና ሌሎች መረጃዎቻችንን ለማግኘት የትክክለኛዎቹ አድራሻዎቻችን አባል በመሆን ይከታተሉ፡:

📌 ዩቲዩብ- https://youtube.com/?si=hajx0x5IpJi4y1_D

📌በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100067771953914

📌 ትዊተር - X https://x.com/BelachewBe698?t=qsgVKlpw33zmVb2o7iI_lg&s=09

22/07/2023

Address

Kafa
Bonga

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Belachew Belay - በላቸው በላይ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Nearby media companies