Momona FM96.4 ሞሞና ኤፍኤም96.4

  • Home
  • Momona FM96.4 ሞሞና ኤፍኤም96.4

Momona FM96.4  ሞሞና ኤፍኤም96.4 This is Mekelle University's Momona FM 96.4 Community Centered Community Radio Station's Official Pa
(1)

ለቀደሞ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት "የእድገት፣ ስኬት እና የሰላም መሪ" በሚል የዩኒቨርስቲው ማሕበረስብ ያዘጋጀው የምስጋና እና የእውቅና መድረክ በመቐለ ዩኒቨር...
25/10/2020

ለቀደሞ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት "የእድገት፣ ስኬት እና የሰላም መሪ" በሚል የዩኒቨርስቲው ማሕበረስብ ያዘጋጀው የምስጋና እና የእውቅና መድረክ በመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ ምትኩ ሃይለ የባህል ማዕከል ዛሬ ጥቅምት 15/2013 ዓ/ም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

16/10/2020

ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ
=========================
የበረሃ አንበጣ ትግራይ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በአዝርዕት ላይ ጥቃት እያደረሰ እንደሆነና በተለያየ መንገድ ድጋፍ እያደረጋችሁ እንደሆነ ይታወቃል። የአንበጣው መንጋ በፍጥነት ሰፊ ቦታ እያዳረሰ ስለሆነ እንደ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ነገ ጠዋት ደቡብ ምብራቅ ዞን ተገኝተን ድጋፍ ለማድረግ ኣውቶቡስ አዘጋጅተናል። በመሆኑም በዘመቻው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ መነሻ ሚላኖ ሆቴል ነገ በ07/02/2013 ዓ/ም ከጥዋቱ 12:00 ሰአት መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

https://www.facebook.com/386169541477229/posts/3331072850320202/
04/10/2020

https://www.facebook.com/386169541477229/posts/3331072850320202/

We are happy to announce that Mekelle University administration Board has given recognition to Prof. Kindeya G. Hiwet on his successful management of the university. Within the next two weeks the university community will organize a THANK YOU program for for our dear ex -president.

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ በዛሬው ዕለት (24/01/2013 ዓ/ም) ፦- ለዶክተር አፈወርቅ ሙሉጌታ- ለዶክተር ኢብራሂም ፍት- ለዶክተር ክንፈ አብርሃ- ለዶክተር ምሩፅ ሓጎስ- ለዶክተር ገብረህ...
04/10/2020

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ በዛሬው ዕለት (24/01/2013 ዓ/ም) ፦

- ለዶክተር አፈወርቅ ሙሉጌታ
- ለዶክተር ኢብራሂም ፍት
- ለዶክተር ክንፈ አብርሃ
- ለዶክተር ምሩፅ ሓጎስ
- ለዶክተር ገብረህይወት ታደሰ
- ለዶክተር መሃመድ እስማኤል
- ለዶክተር አለማየሁ ባይራይ እና ለዶክተር ሃፍቱ በርሄ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል።

https://www.facebook.com/386169541477229/posts/3330875257006628/

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይን ይተዋወቋቸውሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 (07/01/2012 ዓ/ም)ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ በሰሯቸው የምርምር ስራዎች በስፋት ይታወቃሉ። በሀገራችን ከሚገኙ ...
17/09/2020

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይን ይተዋወቋቸው

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 (07/01/2012 ዓ/ም)

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ በመቀለ ዩኒቨርሲቲ በሰሯቸው የምርምር ስራዎች በስፋት ይታወቃሉ። በሀገራችን ከሚገኙ ጥቂት የፕሮፌሰርነት ማእረግ ካላቸው ሴት እንስቶች መካከልም አንዷ ናቸው። የመቐለ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎቶች ምክትል ፕሬዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ፕሮፌሰር ፈቴን አባይ ተወልደው ያደጉት በትግራይ ክልል በውቕሮ ከተማ ሲሆን የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመቐለ እና አዲግራት ተከታትለዋል። ከዛም በመቀጠል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ በማቅናት በሀዋሳ ግብርና ኮሌጅ በPlant science በዲፕሎማ በ1976 ዓ/ም ተመርቀዋል።

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በእርሻ ወኪልነት ካገለገሉ ሲሆን በቀድሞ የአለማያ ግብርና ዩኒቨርስቲ በPlant science የዲግሪ ትምህርታቸውን በ1984 ዓ/ም አጠናቀዋል።

በመቀጠልም ለሁለት አመታት በመቐለና ደብረብርሃን የእርሻ ምርምር ተቋም ካገለገሉ በኃላ መቐለ ዩኒቨርስቲ ሲመሰረት በ1986 ዓ/ም መቀላቀል ችለዋል። ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ ከጀማሪ መምህርነት በመነሳት የዩኒቨርስቲውን እርሻ በማስጀመር፣ በምርምር ፣ገበሬዎችን የሚያሳትፉ ፕሮጀክቶች በማካሄድ፣ በግብርናው ዘርፍ ስድስት የሚደርሱ አዳዲስ ዝርያዎችን ከተለያዩ ተመራማሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ለአርሶ አደሮች አድርሰዋል።

በዩኒቨርስቲው ውስጥ ጥናቶችን በማድረግ አዳዲስ የትምህርት ስርአቶችን በመቅረፅ የምግብ ሳይንስ እና የድህረ ምርት ብክነት ትምህርት ክፍልን በማቋቋም
የአካባቢ፣ የሥርዓተ-ፆታ እና የልማት ጥናት ተቋም በምስረታ ሂደትና በዋና ዳይሬክተርነት አገልግለዋል። እንዲሁም የተለያዩ የቤተ ሙከራዎችንም በመክፈት ዩኒቨርስቲው አሁን ለደረሰበት ደረጃ የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ ችለዋል ።

ፕ/ር ፈቴን ኣባይ በ1986 ዓ/ም ወደ አንግሊዝ በማቅናት ከዌልስ ዩኒቨርሲቲ በገጠር ሀብት አስተዳደር (Rural Resource Management) በ1988 ዓ/ም የሁለተኛ ዲግሪያቸውን አጠናቀዋል። በማስከትልም በ ኖርዊዬ Plant Breeding and Seed Science የሶስተኛ ዲግሪያቸውን (PHD) በ1999 ዓ/ም አጠናቀዋል ።

በአጠቃላይ ፕሮፌሰር ፈቴን አባይ 87 ሳይንሳዊ ፅሑፎችን በአለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ማሳተም ችለዋል። የመቐለ ዩኒቨርስቲ ሴኔት ባፀደቀው መሰረት ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ የሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግን አግኝተዋል። በዚህም በሀገራችን ከሚገኙ ጥቂት የፕሮፌሰርነት ማእረግ ካላቸው ሴት እንስቶች መካከልም አንዱ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል።

ፕሮፌሰር ፈቴን ኣባይ ባከናወኗቸው ጠንካራ ስራዎቻቸው በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ሽልማቶችን እና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ባሳዩት የላቀ ውጤት እና የስራ አመራር ብቃት ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ የመቐለ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎቶች ምክትል ፕረዚዳንት በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አሁን ላይ በመቐል ዩኒቨርስቲ የሰኬት ጉዞ ላይ የማይነጥፍ አሻረቸውን ካተሙት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወትን በመተካት ተጠባባቂ የመቐለ የኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በመሆን በሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ተሹመዋል።

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የማይረሳ አሻራን ያተሙት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወትበሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 የተዘጋጀፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ከመጀመሪያ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከፕሮፌሰር ምትኩ ሃ...
15/09/2020

በመቐለ ዩኒቨርስቲ የማይረሳ አሻራን ያተሙት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት

በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 የተዘጋጀ

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ከመጀመሪያ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከፕሮፌሰር ምትኩ ሃይለ እና ከጀርመናዊው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጆአኪን ከርዚግ በመቀጠል ሶስተኛው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ናቸው።

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ (ከቀድሞዉ አለማያ) በስነ-እፅዋት (forestry) በጥቅምት 1985 ዓ/ም የወርቅ ሜዳሊያ በመውሰድ የተመርቁ ሲሆን የማስተረስ ዲግሪያቸውን ደግሞ እንግሊዝ ሀገር ተምረዋል፡፡ መቐለ ዩኒቨርሲቲን በአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንትነት ለአምስት ዓመታት ካገለገሉ በኋላ ወደ ጀርመን ሀገር በመሄድ የፒ ኤች ዲ ትምርህታቸውን ተከታትለዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ዩኒቨርስቲውን ከጥቅምት 1986 ዓ/ም ጀምሮ በመምህርነት፣ በትምህርት ክፍል ሃላፊነት፣ በምርምርና ስርፀት ሃላፊነት፣ በምርምህርና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ተባባሪ ምክትል ፕሬዚዳንትነት፣ በጥናትና ማሕበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንትንነት፣ በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትንነት እንዲሁም ከግንቦት 28/2005 ዓ/ም ጀምሮ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት በመሆን በታታሪነት እና በቁርጥኝነት አገልግለዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት በዓለም አቀፍ ጆርናሎች የታተሙ በርካታ ሳይንሳዊ ፅሑፎችን በመገምገም፣ የማስተርስ እና የፕ ኤች ዲ ተማሪዎችን በማማከር በአካዳሚክ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፆ ያበረከቱ ሲሆን በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ከ64 በላይ ሳይንሳዊ ፅሑፎችን አሳትመዋል። በሃምሌ 26/2009 ዓ/ም የመቐለ ዩኒቨርስቲ ሴኔት ባፀደቀው መሰረት የሙሉ ፕሮፌስርሺፕ ማዕረግ አግኝተዋል።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት በምርምር እና በትምህርት ዘርፍ እንዲሁም በአመራር ክህሎታቸው ባደረጉት አስተዋፅዖ በብዙ ዓለም አቀፍ ተቋማት ዘንድ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቿል፡፡ በምርምር development Cooperation prize እ.ኤ.አ. በ2004፣ በአመራር ክህሎት የAfrica leadership Award for Education leaders እ.ኤ.አ. በ2015 እና የዓመቱ ምርጥ ሽልማት ከHargeisa University እ.ኤ.አ. በ2019 ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ከተሰጧቸው ዓለም አቀፍ እውቅናዎች እና ሽልማቶች ተጠቃሽ ናቸው።

ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት እንደ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት በሁሉም ዘርፎች እና ፕሮጅክቶች አዘወትረው ጠንካራ ድጋፍና ተሳትፎዎችን ያደረጉ ሲሆን መቐለ ዩኒቨርስቲ ከተመሰረተ ጀምሮ ከሁለት ካምፓሶች ወደ ስምንት ካምፓሶች ሲያድግ በነበረው ጉዞ ግንባር ቀደም በመሆን፣ የዩኒቭርስቲው የምርምር ዘርፍ እንዲያድግ፣ የማሕበረሰብ አገልግሎት እንዲጠናከርና ተጨባጭ ማሕበራዊ ለውጥ እንዲመጣ፣ የአካዳሚክ ዘርፉ እንዲዘምን በማድረግ፣ የዩኒቨርስቲውን ዓለም አቀፋዊነት ከፍ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅዖ በማድረግ እንዲሁም በሀገረችን እና በክልላችን ጉዳዮች ላይ የድርሻቸውን በማበረከት በመቐል ዩኒቨርስቲ የማይረሳ አሻራቸውን አትመዋል።

የዩኒቨርስቲያችን ማሕበረሰብ ሬዲዮ ሞሞና ኤፍኤም 96.4 ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወት ለመቐለ ዩኒቨርስቲ እና ለማሕበረሰባችን ላባረከቱት ታላቅ ስራ ክብርና ምስጋና እያቀረበ ለውድ አድማጮቻችን የፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሂወትና የመቐለ ዩኒቨርስቲ ጉዞን ሚዳስስ ልዩ ፕሮግራም ወደፊት ውደናንት የሚያደርስ ይሆናል።

የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!
ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4  ንኹለኹም ኢትዮጵያዊያን ንፍትዋት ተኸታተልቲ ማሕበረሰብ ተኮር ሬድዮና፣  ሰራሕተኛታት ዩኒቨርሲቲናን መዳርግቲ ኣካላትናን ርሑስ በዓል ሓድሽ ዓመት ይምነ። እዚ በዓል ...
10/09/2020

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ንኹለኹም ኢትዮጵያዊያን ንፍትዋት ተኸታተልቲ ማሕበረሰብ ተኮር ሬድዮና፣ ሰራሕተኛታት ዩኒቨርሲቲናን መዳርግቲ ኣካላትናን
ርሑስ በዓል ሓድሽ ዓመት ይምነ።

እዚ በዓል ናይ ሰላምን ዕብየትን ክኾነልኩም ልባዊ ትምኒትና ንገልፅ!!

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4

ተናሓነሕቲ ዉድባት ፖለቲካ ትግራይ 2,640 ደቓይቕ ኣብ ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ብነፃ ተጠቒሞምኣብ ዝመፅእ ዘሎ ሮቡዕ ኣርባዕተ ጳጉሜን 2012 ዓ/ም ኣብ ትግራይ ዝካየድ ሻድሻይ ዙር መረፃ ...
05/09/2020

ተናሓነሕቲ ዉድባት ፖለቲካ ትግራይ 2,640 ደቓይቕ ኣብ ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ብነፃ ተጠቒሞም

ኣብ ዝመፅእ ዘሎ ሮቡዕ ኣርባዕተ ጳጉሜን 2012 ዓ/ም ኣብ ትግራይ ዝካየድ ሻድሻይ ዙር መረፃ ትግራይ ዝነሓነሑ ሓሙሽትኦም ዉድባት ፖለቲካ ትግራይ ኣብ ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ንተኸታታሊ 22 መዓልቲታት 2,640 ደቓይቕ ብነፃ ከም ዝተጠቐሙ ተሓቢሩ።

እቶም ዉድባት ፖለቲካ ካብ 06 ክሳብ 29 ነሓሰ 2012 ዓ/ም ኣብ ጣብያና ኣብ ፈነወ ወሰንቲ ሰዓታት/ Prime Time/ ማለት'ውን ንጉሆ ድሕሪ ዜና ስዓት 1:30, ቐትሪ ድሕሪ ዜና ስዓት 6:30 ከምኡ'ውን ምሸት ድሕሪ ዜና ሰዓት 2:00 ኣማራፂ ዝብልዎ ፖለቲካዊ ሓሳብ ንህዝቢ ከቕርቡ ፀኒሖም'ዮም።

እቲ ንጎስጓስ ምረፁኒ ብነፃ ዝተጠቐሙሉ ፈነወ ግዘ ኣየር ብገንዘብ እንትትመን ብናይ ጣብያና ተመን ኪራይ ኣየር ስዓት መሰረት ልዕሊ ብር 1 ነጥቢ 1 ሚልዮን ከምዝኾነ ድማ ንምፍላጥ ተኻኢሉ ኣሎ።

እቲ ወፍሪ ጎስጓስ ምረፁኒ ትማሊ ዓርቢ 29 ነሓሰ 2012 ዓ/ም ኣማሲዩ መፈፀምታ ዝረኸበ እንትኸውን እቲ ከይዲ መረፃ ክሳብ ዝዛዘምን ከምኡ'ውን ኣብ እዋን መረፃን ድሕረ መረፃን ዝህልው ምዕባለታት እናተኸታተለ ሚዛናዊ ዝኾነ ሓበሬታ ናብ እዝኒ ሰማዕቲ ዘብፅሕ ምኳኑ ድማ ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 በዚ ኣጋጣሚ እዚ ክሕብር ይፎቱ።

 !  ሬዲዮ ጣቢያችን ሞሞና ኤፍኤም 96.4 ከህዳር 06/2012 ዓ/ም ጀምሮ በይፋ ከተመረቀበት ጊዜ አንስቶ በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤት በስርጭት ላይ ይገኛል። ጣቢያው የተቋቋመበትን ዓላ...
02/09/2020

!

ሬዲዮ ጣቢያችን ሞሞና ኤፍኤም 96.4 ከህዳር 06/2012 ዓ/ም ጀምሮ በይፋ ከተመረቀበት ጊዜ አንስቶ በከፍተኛ ተነሳሽነት እና ውጤት በስርጭት ላይ ይገኛል። ጣቢያው የተቋቋመበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን እያሻሻለ እና እያደራጀ በስኬት ጎዳና ላይ ይገኛል።

ጣቢያው በአሁን ሰዓት በአስር ቋሚ ጋዜጠኞችና የቴክኒክ ባለሞያዎች፣ በዘጠኝ ትጉህ በጎ ፍቃደኛ ጋዜጠኞች፣ በአስራ አንድ መምህራን (ከጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ሶስት ሳምንታዊ ፕሮግራም አዘጋጅ መምህራን፤ ከሳይኮሎጂ እና ትያትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ሁለት ፕሮግራም አዘጋጅ መምህራን፤ ከስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ሶስት ፕሮግራም አዘጋጅ መምህራን፤ ከዓይደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በህፃናት ጤና አጠባበቅ፣ በስነ ልቦና እና ኢንላይትመንት ላይ ያተኮሩ ፕሮግራም አዘጋጅ ሶስት መምህራን በአጠቃላይ በ30 ባለሞያዎች በቀን ለ16 ሰዓታት በሳምንት 112 ሰዓታት በስርጭት ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም ሁለት ይዘት ማናጀሮች፣ ስምንት ከፍተኛ ሪፖርተሮች፣ ሁለት ጀማሪ ሪፖርተር እና አንድ ቴክኒክ ቁጥጥር አስተባባሪ በድምሩ 13 ባለሞያዎች ቅጥር ለመፈፀም ሂደት ላይ ነው።

ሞሞና ኤፍኤም 96.4 የዩኒቨርስቲውን መምህራን ለማበረታታት እና ለማሕበረሰባችን በሞያቸው ዘርፍ መረጃ እንዲሰጡ፣ እንዲያስተምሩ፣ እንዲያስገነዝቡ እና እንዲያዝናኑ እንዲሁም በዘርፉ ላሉ መምህራን ሞያዊ የተግባር ልምምድ እንዲከውኑ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ከ30 ደቂቃ እስከ ሁለት ሰዓት ነፃ የአየር ሰዓት በመፍቀድ መምህራንን ለማበረታታት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።

ጣቢያው ስርጭቱን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ በሚገኝ ጊዚያዊ ስቱድዮ በማሰራጨት ላይ ያለ ሲሆን ከህዝብ እና ከግል ሬዲዮ ጣቢያዎች ባልተናነሰ ደረጃ የወቅቱን ቴክኖሎጂ የተላበሱ ሬዲዮ ማሰራጭያ እቃዎች በመጠቀም ስርጭቱን ይከውናል።

የሞሞና ኤፍኤም 96.4 ቋሚ ማሰራጭያ ስቱድዮ በዘርፍ ላሉ ተማሪዎች እና መምህራን (በተለይ ለሕብረተሰብ ሳይንስ እና ቋንቋዎች ኮሌጅ) እንዲመች በአዲ-ሐቂ ግቢ በመገንባት ላይ ባለ አንድ ህንፃ ላይ በቂ ቦታ የተዘጋጀ ሲሆን የህንፃው ግንባታ ተጠናቆ የስቱድዮ ውስጥ የአኩስቲክ ስራዎች እንዲከናወኑ በ26/12/2012 ዓ/ም በፕላኔት ሆቴል በተደረገ የባለሞያዎች የውይይት መድረክ ላይ የስቱድዮ የውስጥ ዲዛይን እና የአኩስቲክ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር ቀርቦ በባለሙያዎች አስተያየት የተሰጠበት ሲሆን የዩኒቨርስቲያችን የግንባታ ፕሮጀክት ዳይሬክቶሬት ፅ/ቤት በባለሞያዎች በተሰጠ አስተያየት መሰረት በፍጥነት እንዲከውንና እንዲያጠናቀቅ ክትትል የሚያደርግ ይሆናል።

በአዲ-ሐቂ ግቢ ውስጥ ያለው የኮሚኒቲ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ የስቱድዮ ግንባታ የሬዲዮ ማሰራጭያ፣ የቴሌቪዥን ማሰራጭያ፣ የማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ማሰልጠኛ እና የሕትመት ሚዲያዎችን እንዲያካትት ተደርጎ በመሰራት ላይ ነው።

ጣቢያው የማሕበረሰቡን ተሳትፎ ለማጎልበት በጎ ፍቃደኛ ጋዜጠኞችን በመመልመል እና በማሰልጠን በማሳተፍ እንዲሁም በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ ሰባት የቦርድ አባላት (ከጋዜጠኝነት እና ኮሚኒኬሽን ሶስት መምህራን፣ ከዩኒቨርስቲው ማኔጅመንት አንድ ሰው፣ ከከተማው ማሕበረሰብ 2 ሰው እንዲሁም ከተማሪዎች ህብረት አንድ ተማሪ) ያካተተ ነው። በየሶስት ዓመቱ የሚከናወነው የጣቢያው -ጠቅላላ ጉባኤ 240 አባላት ያሉት ሲሆን በሰኔ 2012 ዓ/ም መከናወን የነበረበት ሁለተኛ ዙር ጠቅላላ ጉባኤ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ማከናወን ስላልተቻለ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ጋር በመወያየት እና በደብዳቤ በማሳወቅ ጠቅላላ ጉባኤው ላልተወሰነ ጊዜ በሕጋዊ መንገድ እንዲራዘም ተደርጓል።

በአጠቃላይ ጣቢያው በትግርኛ ቋንቋ 65% በአማርኛ ቋንቋ 35% በመቶ ስርጭቱን በማድረግ በስራ ላይ ይገኛል። በተለይ ደግሞ በሀገራችን ከፍተኛ የሆነ የጤና ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረሰ ስርጭት ለመከላከል እንዲቻል ሰፊ የአየር ሰዓት በመስጠት ማሕበረሰባችንን ለማሰተማር፣ ለማሳወቅ፣ ለማስገንዘብ እና ለማንቃት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ጣቢያው ያለበትን ክፍተት ለማስተካከል ከአድማጮች እና ከባለሞያዎች አስተያየት በመውሰድ እንዲሁም ወደፊት የአድማጮች ጥናት በማከናወን ያለበትን ክፍተት በመለየት እና የማሰተካከያ እርምጃዎችን በመውሰድ ዓላማውን ለማሳካት ይተጋል። ስራ ላይ ነን!!!

የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!
ሞሞና ኤፍኤም 96.4

መቐለ ዩኒቨርስቲ የሞሞና የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋመ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናዎን ላይ ይገኛል ዩኒቨርስቲያችን የማሕበረሰብ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ እና የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን የተግባር...
01/09/2020

መቐለ ዩኒቨርስቲ የሞሞና የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋመ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናዎን ላይ ይገኛል

ዩኒቨርስቲያችን የማሕበረሰብ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ እና የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን የተግባር ማሰልጠኛ ማእከል ለማቋቋም የተለያዩ ስራዎችን በማከናዎን ላይ ሲሆን ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለማቋቋም የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናዎን ላይ ይገኛል። በዋናነት የማሳራጭያ እቃዎች ዝርዝር ጥናት እና የስቱዲዮ ግንባታ ዝግጅት ዛሬ በ26/12/2012 ዓ/ም በዘርፉ ላሉ ባለሞያዎች ቀርቦ አሳብ እና አስተያየት ተሰጥቶበታል።

በውይይት መድረኩ ላይ የኮሚኒኬሽንና ምህንድስና ኢንጂነሮች፣ የእንፃ ግንባታ እና ዲዛይን ባለሞያዎች፣ የኤሌክትሪክ ኢንጂነሮች፣ የጋዜጠኝነት እና ኮሚኒሽን መምህራን፣ የትያትርና ጥበባት መምህራን እና ባለድርሻ አካልት ተሳትፈዋል።

የቴሌቪዥን ጣቢያውን ለማስጀመር የሚያስፈልጉ የቴክኖሎጂ እቃዎች ዝርዝር በአዘጋጅ በለሞያዎች የቀረበ ሲሆን በተሳታፉ በባለሞያዎች ግንቢ አስተያየት እና ማስተካከያዎች ቀርበዋል። በተጨማሪም በመጠናቀቅ ላይ ባለው የስቱዲዮ ግንባታ የውስጥ ዲዛይን እና የስቱዲዮ ክፍሎች አኮስቲክ ቁሳቁሶች ዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቿል። እንዲሁም በማእከሉ ውስጥ የሚካተት የማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ማስልጠኛ ማእከል ንድፈ አሳብ ቀርቧል።

በመቋቋም ላይ የሚገኘው የማሕበረሰብ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ውስጥ በስርጭት ላይ የሚገኘው የሞሞና ኤፍኤም 96.4 ሬዲዮ ጣቢያ፣ በመቋቋም ላይ የሚገኘው የሞሞና ቴሌቪዥን፣ የማሕበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ማሰልጠኛ እና የሕትመት ሚዲያዎችን አካቷል።
ማእከሉ በዘርፉ ላሉ ባለሞያዎች፣ ተማሪዎች እና መምህራን የተግባር ትምህርት ማሰልጠኛ እንዲሁም የማሕበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥበት ይሆናል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በኢንተርኔት በመታገዝ 28ኛውን የምረቃ ስነ-ስርዓት በማካሄድ ላይ ይገኛል። ዩኒቨርስቲው በዛሬ የምረቃ ስነ-ሰርዓት በመጀመርያ ድግሪ 1572፣ በሁለተኛ ድግሪ 2652፣ በስ...
29/08/2020

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በኢንተርኔት በመታገዝ 28ኛውን የምረቃ ስነ-ስርዓት በማካሄድ ላይ ይገኛል። ዩኒቨርስቲው በዛሬ የምረቃ ስነ-ሰርዓት በመጀመርያ ድግሪ 1572፣ በሁለተኛ ድግሪ 2652፣ በስፔሻሊቲ 46፣ በፒኤችዲ 18 እና ንዑስ ሰፔሻሊቲ 2 በአጠቃላይ 4290 እጩ ምሩቃንን በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በኢንተርኔት በመታገዝ 28ኛውን የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ በ23/12/2012 ዓ/ም ከ8:30 ጀምሮ ያስመርቃል። የምረቃ ስነ-ስርዓቱን:- 👉በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ሬዲዮ ጣ...
29/08/2020

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በኢንተርኔት በመታገዝ 28ኛውን የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ በ23/12/2012 ዓ/ም ከ8:30 ጀምሮ ያስመርቃል።

የምረቃ ስነ-ስርዓቱን:-

👉በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ሬዲዮ ጣቢያ
👉በትግረይ ቴሌቪዥን እና
👉በመቐለ ዩኒቨርስቲ official page እንዲሁም www.mu.edu.et በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በኢንተርኔት በመታገዝ 28ኛውን የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ በ23/12/2012 ዓ/ም ከ8:30 ጀምሮ ያስመርቃል። የምረቃ ስነ-ስርዓቱን:-👉በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ሬዲዮ ጣቢ...
29/08/2020

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በኢንተርኔት በመታገዝ 28ኛውን የምረቃ ስነ-ስርዓት ዛሬ በ23/12/2012 ዓ/ም ከ8:30 ጀምሮ ያስመርቃል።

የምረቃ ስነ-ስርዓቱን:-

👉በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ሬዲዮ ጣቢያ
👉በትግረይ ቴሌቪዥን እና
👉በመቐለ ዩኒቨርስቲ official page እንዲሁም www.mu.edu.et በቀጥታ ስርጭት መከታተል ትችላላችሁ።

Mekelle University is found at the town of Mekelle in Tigray region of Northern Ethiopia , at a distance of 783 Kilometers from the Ethiopian capital. The merger the two former colleges: Mekelle Business College and Mekelle University College established the University in May 2000 by the Government....

ርሑስ በዓል አሸንዳ!
22/08/2020

ርሑስ በዓል አሸንዳ!

የማሕበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያችን ሞሞና ኤፍኤም 96.4 ከነገ 21/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ የቀን ስርጭታችንን በማሳደግ የምሽት ፕሮግራሞችን በአዲስ መልክ በማካተት ከሰኞ እስከ እሁድ ከንጋቱ 12...
28/05/2020

የማሕበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያችን ሞሞና ኤፍኤም 96.4 ከነገ 21/09/2012 ዓ/ም ጀምሮ የቀን ስርጭታችንን በማሳደግ የምሽት ፕሮግራሞችን በአዲስ መልክ በማካተት ከሰኞ እስከ እሁድ ከንጋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 4:00 (በቀን ውስጥ የ16 ሰዓታት ስርጭት) በማድረግ እንዲሁም የአንድ ኪሎዋት የስርጭት ማሽናችንን ወደ ሁለት ኪሎ ዋት (2K transmitter) በማሳደግ ተደረሽነታችንን እና ተደማጭነታችንን ከፍ በማድረግ ከነገ ጀምሮ እንደመጣለን።

ስርጭቱን ነገ ለማስጀመር ከጋዜጠኞቻችን፤ ከበጎ ፍቃደኛ ጋዜጠኞችና ቴክኒሻኖች ጋር ውይይት አድርገናል።

የማሕበረስብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!
ሞሞና ኤፍኤም 96.4

19/04/2020
 ዛሬ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በመቐለ ከተማ በሚገኙ የበግ ገበያዎች በመገኘት የግንዛቤ መፍጠር ስራ ሰርተዋል። በቦታዉ ተገኝተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረ...
18/04/2020



ዛሬ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በመቐለ ከተማ በሚገኙ የበግ ገበያዎች በመገኘት የግንዛቤ መፍጠር ስራ ሰርተዋል።

በቦታዉ ተገኝተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አግልግሎት ሃላፊነቱን እየተወጣ ሲሆን አሁንም በማህበረሰቡ ዘንድ ያለው ምላሽ ግን አጥጋቢ አለመሆኑን ጠቅሰዋል። እንደዚህ አይነት ስራዎችን በቀጣይነት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

በቦታዉ ተገኝቼ የታዘብኩት ነገር አሁንም ድረስ ሰው በባለሙያ ለሚሰጡ ምክሮች ቦታ እንዳልሰጠ ነው። በተፋፈነ ቦታ ሁነው ከሚገበያዩት ውስጥ የፊት መሸፈኛ ማስክ ያደረጉት በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው። አካላዊ መራራቅ የሚባለውም ምንም ተግባራዊ እየተደረገ አይደለም።

የከተማ አስተዳደሩ ይህን ችግር ለመቅረፍ በከተማው ከ20 በላይ የበግ መገበያያ ቦታዎችን ያዘጋጀ ሲሆን እስካሁን ግን አይደር እና ሽላናት አካባቢ ያሉት ብቻ ናቸው በሰው ተጨናንቀው ያሉት።

በተስፋገብርኤል ተኮላ
ከ #ቲክቫህኢትዮጵያ

18/04/2020

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት።

ሶስት ደቂቃ+ ወስደው ቪዲዮውን እንዲመለከቱት ጋብዘናል።

መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ🙏

መቐለ ዩኒቨርስቲ

ወናኒ ሓፈሻዊ ቤተ ሙከራ ቸንጅ ሓ/ዝ/ው/ማ  (Change General Laboratory PLC) ንመከላኸሊ ቫይረስ ኮሮና ዝውዕሉ ክዳውንቲ ሓካይም ንዩኒቨርስቲ መቐለ ኣረኪቡ፡፡በዓል ዋና እቲ...
16/04/2020

ወናኒ ሓፈሻዊ ቤተ ሙከራ ቸንጅ ሓ/ዝ/ው/ማ (Change General Laboratory PLC) ንመከላኸሊ ቫይረስ ኮሮና ዝውዕሉ ክዳውንቲ ሓካይም ንዩኒቨርስቲ መቐለ ኣረኪቡ፡፡

በዓል ዋና እቲ ቤተ ሙከራ ዶ/ር ተስፋይ ከበደ ከምዝሓበሩዎ፡ እቶም ክዳውንቲ "ሓኻይም፥ ህይወት ሰብ ከድሕኑ፡ ህይወቶም ክስእኑ የብሎምን" ብዝብል መሪሕ ሓሳብ፡ ኣብ ዩኒቭርስቲ መቐለ ቀፅሪ መለስ ዜናዊ-ኲሓ ብግዝያውነት ከገልግሉ ንዝተመደቡ ሓካይም ዝውዕሉ እዮም።

እቶም ንመከላኸሊ ቫይረስ ኮሮና ዝተዳለዉ ክዳውንቲ በዝሖም 250 ፅምዲ እንትኸውን ን250 ዶካትር ከገልግሉ ዝኽእሉ እዮም።

ሓፈሻዊ ቤተ ሙከራ ቸንጅ ብዝገበሮ ፃዕሪ ዝተረኸበ እቲ ናይ ክዳውንቲ ሕክምና ሓገዝ ክሳብ 200 ሽሕ ዝግመት ናይ ገንዘብ ወፃኢ ከምዝተገበረሉ ዶ/ር ተስፋይ ገሊፆም።

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ሬዲዮ ጣቢያ  ከት/ብ/ክ/መ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከ05/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት በሬዲዮ ከ5ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ ...
11/04/2020

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ሬዲዮ ጣቢያ ከት/ብ/ክ/መ ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከ05/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት በሬዲዮ ከ5ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 5:00-6:00 እንዲሁም ከቀኑ10:00-11:00 ይተላለፋል። ትምህርት በሬዲዮ በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ሬዲዮ እንድትከታተሉ ለተማሪዎች እናሳውቃለን።

በዚሁ አጋጣሚ ለተማሪዎች ተጨማሪ የትምህር መማርያ እድል እንዲሆን ትምህርት በቴሌቪዥን ማሰረጨት እንዲቻል በዩኒቨርስቲያችን ሃሳብ አመንጪነት ከት/ብ/ክ መንግስት ትህምርት ቢሮ ጋር በጋራ መከናዎን ባለባቸው የትብብር ስራዎች ዙርያ ገንቢ ስራ መጀመርኑ እናሳውቃለን።

የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!
ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4

ሓበሬታ ንኩልኹም ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ክትከታተሉ ትኽእሉ ተምሃሮ=====================================ሬድዮ ጣብያ ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ምስ ቢሮ ትምህርቲ ብሄራዊ ክ...
11/04/2020

ሓበሬታ ንኩልኹም ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ክትከታተሉ ትኽእሉ ተምሃሮ
=====================================
ሬድዮ ጣብያ ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ምስ ቢሮ ትምህርቲ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስቲ ትግራይ ብምትሕብባር ካብ 05 ሚያዝያ 2012 ዓ/ም ጀሚሩ ፈነወ ትምህርቲ ብሬድዮ ከመሓላልፍ እዩ። ዝመሓላለፈሉ መዓልቲ፡ ኩሉ ግዜ ሶንይ ክሳብ ዓርቢ ኣብ ዘለዉ መዓልትታት ኮይኑ፥ ቅድሚ ሰዓት 5፡00-6፡00 ድሕሪ ሰዓት ድማ 10፡00-11፡00 ክትከታተሉ ነፍልጥ።

በዚ ኣጋጣሚ ንተምሃሮ ተወሳኺ ናይ ምምሃር ዕድል ብምስፋሕ ብቴሌቪዥን ምፍናው ዝከኣለሉ ኩነታት ንምፍጣር ብናይ ዩኒቨርስቲ መቐለ ኣፍላቕነት ሓሳብ ምስ ቢሮ ትምህርቲ ክልል ትግራይ ተሓባቢርካ ንምስራሕ ዘኽእል ኩነታት እናተፈጠረ ይርከብ።

ኤፍ ኤም ሞሞና 96.4

"ተሳትፎ ማሕበረሰብ ንዘላቒ ልምዓት!!"

ብኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ዝመሓላለፍ ፕሮግራም ፈነወ ትምህርቲ 5ይ-12 ክፍሊ==================================ቅድሚ ሰዓት 5:00-6:00 ድሕሪ ሰዓት ድማ 10:00-11:...
11/04/2020

ብኤፍ ኤም ሞሞና 96.4 ዝመሓላለፍ ፕሮግራም ፈነወ ትምህርቲ 5ይ-12 ክፍሊ
==================================
ቅድሚ ሰዓት 5:00-6:00
ድሕሪ ሰዓት ድማ 10:00-11:00 ካብ ሶንይ 05 ሚያዝያ 2012 ዓ/ም ጀሚሩ ክመሓላለፍ 'ዩ።

03/04/2020

የዩኒቨርሰቲያችን የቀድሞ (Almuni) እና የአሁን ተማሪዎቻችን በቀጥታ ስልክ መስመር በሞሞና ኤፍኤም 96.4 ሬዲዮ ጣቢያችን በአከባቢያቸው በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን እና ትዝብታቸውን በቀጥታ ስልክ መስመር #በሞሞና በኩል ሃሳባቸውን እያካፈሉን ይገኛሉ።

እናንተም በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 በኩል ከታች👇ባሉት ስልክ ቁጥሮቻችን ሃሳባቹን አካፍሉን።

👉+251 34 241 0378
👉+251 34 899 0425

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4
የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!

https://youtu.be/oQaHqJHS2_k
02/04/2020

https://youtu.be/oQaHqJHS2_k

ዶ/ር ዘካሪያስ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዓይደር ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ናቸው። በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 በነበራቸው ቆይታ ስለ ወቅታዊው .....

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት በወቅታዊ   ሀገረዊ እና ክልላዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ዩኒቨርስቲው እያከናወነ ስላለው የቅደመ ዝግጅት ስራዎች በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4...
01/04/2020

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት በወቅታዊ ሀገረዊ እና ክልላዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ዩኒቨርስቲው እያከናወነ ስላለው የቅደመ ዝግጅት ስራዎች በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ስቱዲዮ በመገኘት በሰፊው አጋርተውናል። ጊዜ ገዝተው ቪዲዮውን እንዲመለከቱ ጋብዘኖታል።

የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!
ሞሞና ኤፍኤም 96.4

https://youtu.be/zMrfBLlSovY

በዚህ ቃለ መጠይቅ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የሆኑት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሂወት በወቅታዊው የኮቪድ-19 ሀገራዊ እና ክልላዊ ሁኔታዎች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲያቸው እየሰራ ስላለው የ....

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ቀጣይ ሀገራዊ ግዴታውን ለመወጣት ካምፓሶቹን ለለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ በማዘጋጀት ላይ ይገኛልየሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዩኒቨርስቲዎችን...
01/04/2020

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ቀጣይ ሀገራዊ ግዴታውን ለመወጣት ካምፓሶቹን ለለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዩኒቨርስቲዎችን ለኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ በስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መቐለ ዩኒቨርስቲ አዲሱን የኲሓ መለስ ዜናዊ ቴክኖሎጂ ካምፓስ ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሰቲው የዶርሚተሪ አቀማመጥ የመቀየር፤ ሰፋፉ ውርክሾፖችን የማዘጋጅት፣ መፀዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶችን በበቂ ሁኔታ የማዘጋጀት፣ የምግብ አቅርቦት እና አሰፈላጊ የሆኑ ግብሃቶችን የማሟላት ስራ በማከናዎን ላይ ይገኛል። በተጨማሪ ዩኒቨርስቲው ተጨማሪ ካምፓሶችን ለለይቶ ማቆያና በቫይረሱ ለተያዙት ማገገሚያ እንዲሆኑ የማዘገጃጀት ሂደት ላይ ይገኛል።

መቐለ ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስን (COVID-19) ለመከላከል እና በሀገር ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስና ለመቆጣጠር ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረቱ የመፍትሄ አሳቦችን ለማመንጨት በዩኒ...
31/03/2020

መቐለ ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስን (COVID-19) ለመከላከል እና በሀገር ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስና ለመቆጣጠር ጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረቱ የመፍትሄ አሳቦችን ለማመንጨት በዩኒቨርስቲው የምርምና ማሕበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፈቲን አባይ የሚመራ ከዩኒቨርስቲው የተለያዩ የጥናትና ምርምር ማዕከላት እና የሞያ ዘርፎች የተውጣጡ ሙሁራንን ያካተተ የጥናትና ምርምር ብድን ዛሬ (በ22/07/2012 ዓ/ም) አቋቁሟል።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ የጥናትና ምርምር ማሕበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፈቲን አባይ ከሞሞና ኤፍኤም 96.4 ትግርኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍላችን ጋር ዩኒቨርስቲያችን በኮሮና ቫይረስ መከ...
31/03/2020

የመቐለ ዩኒቨርስቲ የጥናትና ምርምር ማሕበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ፈቲን አባይ ከሞሞና ኤፍኤም 96.4 ትግርኛ ቋንቋ ዝግጅት ክፍላችን ጋር ዩኒቨርስቲያችን በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ በጥናትና ምርምር ማከናወን በሚገባው ስራ ዙርያ በቀጥታ ስርጭት ጠንከር ያለ ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው። ጊዜ ገዝታቹ እንድትከታተሉ ጋብዘናል።

እንዲነሱ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በሰልክ ቁጥራችን:-

👉+251 34 241 0378
👉+251 34 899 0425

ወይም ደግሞ በቴሌግራም ቻናል በፅሁፍ መልዕክት-

👉MU info

ማድረስ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4
የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!

መቐለ ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በዩኒቨርሰቲው ኬሚስቶሪ ትምህርት ክፍል ያመረተውን 140 ሌትር ሳኒታይዘር በዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት በኩል ለዓይደር ...
30/03/2020

መቐለ ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በዩኒቨርሰቲው ኬሚስቶሪ ትምህርት ክፍል ያመረተውን 140 ሌትር ሳኒታይዘር በዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት በኩል ለዓይደር ኮምሬንሲቨ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስረክቧል።

ዩኒቨርስቲው በሁለተኛ ዙር 200 ሌትር ተጨማሪ ሳኒታይዘር በማምረት ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ኣመራሮች: የቦርድ ሰብሳቢ ኣቶ የማነ ዘርኣይ  እና የክልል ጽ/ቤት ሃላፊ ኣቶ ብርሃኑ መኮንን ማህበሩ በኮርና ቫይረስ መከላከል ስራዎች...
30/03/2020

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ትግራይ ክልል ቅርንጫፍ ኣመራሮች: የቦርድ ሰብሳቢ ኣቶ የማነ ዘርኣይ እና የክልል ጽ/ቤት ሃላፊ ኣቶ ብርሃኑ መኮንን ማህበሩ በኮርና ቫይረስ መከላከል ስራዎች ዙሪያ እያከናወነ ባለው ስራዎች ዙርያ ከጣብያችን ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ናቸው ። እንድትከታተሉ ጋብዘናል።

መቐለ ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በመጀመርያ ዙር በዩኒቨርሰቲው ያመረተውን  140 ሌትር ሳኒታይዘር ዛሬ 10:00 ላይ ለተለያዩ አካላት ያስረክባል። በሁለተኛ ዙር 200 ሌትር ተ...
30/03/2020

መቐለ ዩኒቨርስቲ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በመጀመርያ ዙር በዩኒቨርሰቲው ያመረተውን 140 ሌትር ሳኒታይዘር ዛሬ 10:00 ላይ ለተለያዩ አካላት ያስረክባል።

በሁለተኛ ዙር 200 ሌትር ተጨማሪ ሳኒታይዘር በማምረት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሂደቱን የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት ጎብኝተዋል።

25/03/2020

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ማኔጅመንት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የተወሰነውን ውስኔ የዩኒቨርስቲውን አፈፃፀም በተመለከተ ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት ከሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ጋር ቆይታ በማድረግ ላይ ናቸዉ ተከታተሉ።

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ማኔጅመንት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የተወሰነውን ውስኔ በጥንቃቄ ለማሰፈፀ አሰቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ላይ ይገኛል።
25/03/2020

የመቐለ ዩኒቨርስቲ ማኔጅመንት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የተወሰነውን ውስኔ በጥንቃቄ ለማሰፈፀ አሰቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ-----የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚከተለው ከዚህ በታች ቀርበዋል
23/03/2020

ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በሙሉ
-----
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የሚወሰዱ ተጨማሪ እርምጃዎች እንደሚከተለው ከዚህ በታች ቀርበዋል

መቐለ ዩኒቨርስቲ COVID-19 ለመከላከል የሚረዱ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። ይህንንም አሰመልክቶ በዩኒቨርሰቲው በመከናወን ላይ ያሉ ሰራዎችን በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርስ...
23/03/2020

መቐለ ዩኒቨርስቲ COVID-19 ለመከላከል የሚረዱ የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል። ይህንንም አሰመልክቶ በዩኒቨርሰቲው በመከናወን ላይ ያሉ ሰራዎችን በተመለከተ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት ከሞሞና ኤፍኤም 96.4 ጋር በቀጥታ ቆይታ በማድረግ ላይ ናቸው። ያድምጡ፣ ይሳተፉ።

22/03/2020

በዶ/ር ዘካሪያስ ገሰሰ COVID-19ን በተመለከተ በእየለቱ የሚቀርበውን ሞያዊ ትንታኔ በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 በየቀኑ ይከታተሉ፣ ይሳተፉ

በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ዙርያ ሞያዊ መረጃ ለማግኘት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3:00-3:30 በሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ላይ ዶ/ር ዘካሪያስ ገሰሰ
በዓይደር ኮምፓሬንሰቪ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት እና የተላላፊ በሽታዎች አሰተባባሪ የሆኑት ከነገ ጀምሮ በየቀኑ ሙያዊ ትንታኔ እና ወቅታዊ መረጃዎች ይቀርባሉ።

እንዲነሱ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በሰልክ ቁጥራችን:-

👉+251 34 241 0378
👉+251 34 899 0425

ወይም ደግሞ በቴሌግራም ቻናል በፅሁፍ መልዕክት-

👉MU info

ማድረስ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን እንድታደምጡ እንጋብዛለን።

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4
የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!

22/03/2020

መቐለ ዩኒቨርስቲ መረጃ



የኮሮና ቫይረስን እና በዩኒቨርስቲያችን እየተወሰደ ያለውን የቅድመ መከላከል እርምጃዎች በተመለከተ ሬዲዮ ጣቢያችን ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ሕይወት ጋር በ14/07/2012 ዓ.ም ሰኞ ከጠዋቱ 4:00 ላይ በቀጥታ ሰርጭት ቆይታ እናደርጋለን።

እንዲነሱ የምትፈልጓቸውን ጥያቄዎች በሰልክ ቁጥሮቻችን:-

👉+251 34 241 0378
👉+251 34 899 0425

ወይም ደግሞ በቴሌግራም ቻናል በፅሁፍ መልዕክት-

👉MU info

ማድረስ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ሬዲዮናቹን ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4 በማድረግ እንድታደምጡ እንጋብዛለን።

ሞሞና ኤፍ ኤም 96.4
የማሕበረሰብ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት!

Address


Website

.edu.et

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Momona FM96.4 ሞሞና ኤፍኤም96.4 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share