15/02/2024
የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ አራት የአርብቶ አደር አካባቢዎች መንገድ ዲዛይንና ጥናት ለማድረግ የሥራ ሳይት ርክክብ አደረገ።
የካቲት 7_2016 ዓ.ም
ቦንጋ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት አርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢ ጉዳይ ቢሮ አራት የአርብቶ አደር አካባቢዎች በአጠቃላይ 189 ኪ/ሜ የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ስራዎችን በአጠቃላይ 3,740,765.82 ብር ወጪ ለማሰራት ከአራት አማካሪ መሐንዲሶች ጋር የሳይት ርክክብ ማድረጉን ገለፀ።
የቢሮ ሀላፊዉ ይኺ ሥራ ለህብረተሰቡ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ጨረታውን ተወዳድረዉ አሸንፎ ሥራዉን የተረከቡ አማካሪዎች እስኬ ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም መጨረሻ ድርስ ሙሉ ሥራዉን አጠናቀው እንዲያስረክቡ በስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።
የቢሮ ሀላፊዉ አራቱ የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራዎች የሚሰራባቸው የአርብቶ አደር አካባቢዎች፣የመንገዱ እርቀት እና ወጪዎችን በተመለከተ የሚከተለውን መረጃ ሰጥተዋል።
1,በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ ቱሊግት_ካሪሞጋ 38 ኪ/ሜ በ805,757.83 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከእኛ በእኛው አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ ዘገዬ ቶሎሣ ጋር ዉል ተገብቷል፣
2,በምዕራብ ኦሞ ዞን ሜኒኤት ጎልዲያ ወረዳ ባቹማ_ኮላይ_ጠንክሪ 41 ኪ/ሜ በ796,922.7 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከጦና አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ በረከት ባሌ ጋር ዉል ተገብቷል፤
3, በምዕራብ ኦሞ ዞን ሜኒኤት ጎልዲያ ወረዳ ጨበራ_ያርጣ 60 ኪ/ሜ በ1,166,228.34 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከቤሌማ አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ ስሳይ አስፋው ጋር ዉል ተገብቷል፤
4, ካፋ ዞን ጎባ ወረዳ ኡፊት_ ጋራሙጅ_ናቡር 50 ኪ/ሜ በ971,856.95 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከ3D አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ ዘረሰናይ ታደሰ ጋር ዉል ተገብቷል።
አራቱም የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ አማካሪ መሐንዲሶች ተወካዮች እንደገለፁት ለአከባቢዎቹ የሚንሰራዉ የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ስራዎች የአከባቢዎቹን ህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ በመሆኑ ሥራዉ በተያዘው ጊዜ ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ ሥራዉን ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን በመድረኩ ገልጸዋል
በሳይት ርክክብ ወቅት የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳይ ቢሮ የአርብቶ አደር ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ታጠቅ ብርሃኑ ፣ የቆላማ አካባቢ ልማትና ኤክስቴሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ባራሪ ሲራሉጉ እና የባለድርሻ አካላቱ ተሳትፈዋል ሲል የክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል።