Abela longena News

  • Home
  • Abela longena News

Abela longena News Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Abela longena News, Media/News Company, .

07/04/2024
07/04/2024

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ለተካሄደው ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና አቀረቡ

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በክልላችን በሁሉም አከባቢዎች ከለውጡ በኃላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል በተካሄደው ህዝባዊ ድጋፍ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ለክልሉ ነዋሪዎች ምስጋና አቅርበዋል።

ምድራዊ ሃይል ሊያስቆመው የማይችለውን የለውጥ ጉዞ ገብቷችሁ ድጋፋችሁንና ደስታችሁን ለገለፃችሁ በሙሉ ምስጋናዬን ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።

በህዝባችን የለውጥ መሻት የተጀመረው ጉዞ ብልፅግና ፓርቲን ወልዶ፣የዴሞክራሲ ባህላችንን አሻሽሎ፣ኢትዮጵያን ከብተና ስጋት ታድጎ፣በግብርና፣በኢንዱስትሪው በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሊታዩ የሚችሉ ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግቦ እነሆ መገስገሱን ቀጥሏል ነው ያሉት።

እንደሀገር ባለፋት ስድስት ዓመታት የተገኙ ውጤቶች የጋራ ስኬቶችና ድሎች ናቸው ያሉት ም/ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን አጠናክረን ለማስቀጠል ህብረብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር እና ለአንድ ዓላማ በጋራ መቆም አለብን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ክልላችን የሠላም፣ የብልፅግና እና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ አቅደን እየሰራን ባለው ሂደት የህዝባችን ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑንም አመላክተዋል።

የለውጥ ዓመታት ያጋጠሙና ወደ ፊትም የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን በአብሮነትና በወንድማማችነት ለመሻገር ሁላችንም ከችግር በላይ ሆነን በተሰማራንበት መስክ ቁርጠኛ ሆነን መስራት ይጠብቅብናል ብለዋል።

በለውጡ ጥቅማቸው የሚነካባቸው ግለኛና ስግብግብ አደናቃፊ ሃይሎች እዚህም እዚያም የሚፈጥሩትን ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ በማውገዝ ህዝባችን ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር የማጋለጥና ዕድል እንዳይኖራቸው የማድረግ ሚና በላቀ ደረጃ በቀጣይነት ልንወጣ ይገባል ነው ያሉት።

በመጨረሻም ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፉ በሠላምና በስኬት እንዲጠናቀቅ ሚናቸውን ለተወጡ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።

30/03/2024

እስካሁን ከ2.4 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰብስቧል

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 20/2016 ለወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለማጠናከር የተጀመረው ድጋፍ እስካሁን ከ2.4 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰብስቧል።

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር እንደሚባለው ከተባበርን የትኛውንም ነገር ማሳካት እንችላለንን።

በገንዘብ ብር 1,380,796.82 ሲሆን በአይነት ድንጋይ በቢያጆ 10፣ ፌሮ ብረት በቁጥር 419፣ አሸዋ በቢያጆ 5፣ ሲሚንቶ በኩንታል 200፣ ጠቅላላ የዓይነት ገቢ በብር ሲገመት 1,038,750.00 መሆኑን ታውቋል።

ጠቅላላ የገንዘብና የዓይነት ገቢ በብር 2,419,546.82 መሆኑን እናሳውቃለን።

በድጋፉ የተሳተፋችሁትን በሙሉ ምስጋና እያቀረብን የተጀመረው ድጋፍ ግቡ እስከሚሳካ ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረ ቀርቧል።

30/03/2024

እስካሁን ከ2.9 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰባስቧል

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 21/2016 ለወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለማጠናከር የተጀመረው ድጋፍ እስካሁን ከ2.9 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰብስቧል።

በገንዘብ ብር 1,674,251.82 ሲሆን ጠቅላላ የዓይነት ገቢ በብር ሲገመት 1,278,650.00 መሆኑን ታውቋል።

ጠቅላላ የገንዘብና የዓይነት ገቢ በብር 2,952,901.82 መሆኑን እናሳውቃለን።

በድጋፉ የተሳተፋችሁትን በሙሉ ምስጋና እያቀረብን የተጀመረው ድጋፍ ግቡ እስከሚሳካ ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረ እናቀርባለን።

Oottiidi Wolaytta Worqaa Mayzzana!

30/03/2024

ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰባስቧል

ወላይታ ሶዶ፤ መጋቢት 21/2016 ለወላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ለማጠናከር የተጀመረው ድጋፍ እስካሁን ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ በአይነትና በገንዘብ ተሰብስቧል።

በገንዘብ ብር 1,780,251.82 ሲሆን ጠቅላላ የዓይነት ገቢ በብር ሲገመት 1,278,650.00 መሆኑን ታውቋል።

ጠቅላላ የገንዘብና የዓይነት ገቢ በብር 3,058,901.82 መሆኑን እናሳውቃለን።

እስካሁን በድጋፉ የተሳተፋችሁ በሙሉ ምስጋና እያቀረብን የተጀመረው ድጋፍ ግቡ እስከሚሳካ ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥረ እናቀርባለን።

Oottiidi Wolaytta Worqaa Mayzzana!

25/03/2024

የብልፅግና ፓርቲ መለያ ዕሴቶች ምንድናቸው ?

ዕሴቶቻችን ቅድሚያ ዋጋ የምንሰጣቸውና የምንታገልላቸዉ ወደ ብልፅግና ዓላማ የመድረሻ መንገዳችን አመላካቾች ናቸዉ። በምንጓዝበት መንገድ ሁሉ በሚገጥሙን የተለያዩ አጣብቂኞች ቅድሚያ የምንሰጠው፦

የዜጎችና የሕዝቦች ክብር፣

ነፃነት፣

ፍትሕ፣

ኅብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት፣

መከባበርና መቻቻል፣

ኅብረ-ብሔራዊ አንድነት፣

አሳታፊነት፣

ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ይሆናሉ።

25/03/2024
25/03/2024

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 3ኛ ወርቋን አገኘች

ወላይታ ሶዶ፣ መጋቢት 10፣ 2016 በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በሴቶች 800 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያ 3ኛ ወርቋን በፅጌ ዱጉማ አማካኝነት አግኝታለች፡፡

በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የ800 ሜትር የሴቶች ውድድር ተካሂዷል፡፡

በዚኅም ኢትዮጵያ 3ኛ ወርቋን በፅጌ ዱጉማ አማካኝነት አግኝታለች፡፡

ፅጌ ባለፈው ወር በተደረገው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር የወርቅ ሜዳልያ ማሸነፏ ይታወሳል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abela longena News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share