South West Ethiopia people RegionaState Gov.t Transport & Road Dev.t Bureau

  • Home
  • Ethiopia
  • Bonga
  • South West Ethiopia people RegionaState Gov.t Transport & Road Dev.t Bureau

South West Ethiopia people RegionaState Gov.t Transport & Road Dev.t Bureau SWEPRS Transport & Road Dev.t Bureau

በክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኑሮ ማሻሻያ ኘሮጀት(LLRP) የሚገነባው  የጨበራ መንገድ በተያዘለት ጊዜው ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የኘሮጄክቱ አስተባባሪ አቶ ደረጀ በቀለ ...
21/02/2024

በክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ ኑሮ ማሻሻያ ኘሮጀት(LLRP) የሚገነባው የጨበራ መንገድ በተያዘለት ጊዜው ለማጠናቀቅ እየተሠራ መሆኑን የኘሮጄክቱ አስተባባሪ አቶ ደረጀ በቀለ ተናገሩ።

የካቲት 13/2016 ዓም ሚዛን አማን

መነሻው ከባቹማ ከተማ አድርጎ እስከ ጨበራ ከተማ እየተሰራ ያለው 18ኪ/ሜ ደረጃ የጠበቀ የጠጠር መንገድ በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ስፊ እየተሠራ መሆኑን አርብቶ አደር ኑሮ ማሻሻያ ኘሮጀት(LLRP) አስተባባሪ አቶ ደረጀ በቀለ ተናግረዋል

በ39 ሚሊዮን ብር የመንገዱን ግንባታ ጫራታ ያሸነፈው ይብራ ገ/ ትንሳኤ የመንገድ ስራ ተቋራጭ ኮንስትራክሽን መንገዱን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሠራ የመንገዱ የአፈር ቆረጣና የጠረጋ ስራ ፣ የፓይኘ ቁፋሮ ስራ እየተሰራ ሲሆን የሰርጢ ድልድይ በአዲስ ግንባታ እንደሚሰራም ነው የተገለፀው።

የመንገዱ ግንባታውን ጥራት ለማስጠበቅ ከክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ፣ ከኘሮጄክት እንዲሁም ከዞንና ከወረዳ የተወጣጡት የመንድሶች ቡድን ለመንገድ ግንባታ ክትትልና ድጋፍ እንድያደርጉ በቋሚነት መመደባቸው ነው። የተገለፀው። የፌስቡክ ገፃችን ስለሚከታተሉ እናመሰግናለን https://www.facebook.com/profile.php?id=100078221053769

የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ  አራት የአርብቶ አደር አካባቢዎች መንገድ ዲዛይንና ጥናት ለማድረግ የሥራ ሳይት ርክክብ አደረገ። የካቲት 7_2016 ዓ.ም         ቦንጋ...
15/02/2024

የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ አራት የአርብቶ አደር አካባቢዎች መንገድ ዲዛይንና ጥናት ለማድረግ የሥራ ሳይት ርክክብ አደረገ።

የካቲት 7_2016 ዓ.ም
ቦንጋ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት አርብቶ አደርና ቆላማ አከባቢ ጉዳይ ቢሮ አራት የአርብቶ አደር አካባቢዎች በአጠቃላይ 189 ኪ/ሜ የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ስራዎችን በአጠቃላይ 3,740,765.82 ብር ወጪ ለማሰራት ከአራት አማካሪ መሐንዲሶች ጋር የሳይት ርክክብ ማድረጉን ገለፀ።

የቢሮ ሀላፊዉ ይኺ ሥራ ለህብረተሰቡ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት ጨረታውን ተወዳድረዉ አሸንፎ ሥራዉን የተረከቡ አማካሪዎች እስኬ ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም መጨረሻ ድርስ ሙሉ ሥራዉን አጠናቀው እንዲያስረክቡ በስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

የቢሮ ሀላፊዉ አራቱ የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራዎች የሚሰራባቸው የአርብቶ አደር አካባቢዎች፣የመንገዱ እርቀት እና ወጪዎችን በተመለከተ የሚከተለውን መረጃ ሰጥተዋል።

1,በምዕራብ ኦሞ ዞን ሱሪ ወረዳ ቱሊግት_ካሪሞጋ 38 ኪ/ሜ በ805,757.83 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከእኛ በእኛው አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ ዘገዬ ቶሎሣ ጋር ዉል ተገብቷል፣

2,በምዕራብ ኦሞ ዞን ሜኒኤት ጎልዲያ ወረዳ ባቹማ_ኮላይ_ጠንክሪ 41 ኪ/ሜ በ796,922.7 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከጦና አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ በረከት ባሌ ጋር ዉል ተገብቷል፤

3, በምዕራብ ኦሞ ዞን ሜኒኤት ጎልዲያ ወረዳ ጨበራ_ያርጣ 60 ኪ/ሜ በ1,166,228.34 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከቤሌማ አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ ስሳይ አስፋው ጋር ዉል ተገብቷል፤

4, ካፋ ዞን ጎባ ወረዳ ኡፊት_ ጋራሙጅ_ናቡር 50 ኪ/ሜ በ971,856.95 ብር ወጪ የሚሰራው የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ ከ3D አማካሪ መሐንዲሶች ተወካይ ከአቶ ዘረሰናይ ታደሰ ጋር ዉል ተገብቷል።

አራቱም የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ሥራ አማካሪ መሐንዲሶች ተወካዮች እንደገለፁት ለአከባቢዎቹ የሚንሰራዉ የመንገድ ጥናትና ዲዛይን ስራዎች የአከባቢዎቹን ህብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ በመሆኑ ሥራዉ በተያዘው ጊዜ ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ ሥራዉን ለማጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን በመድረኩ ገልጸዋል

በሳይት ርክክብ ወቅት የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳይ ቢሮ የአርብቶ አደር ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ታጠቅ ብርሃኑ ፣ የቆላማ አካባቢ ልማትና ኤክስቴሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ሀላፊ አቶ ባራሪ ሲራሉጉ እና የባለድርሻ አካላቱ ተሳትፈዋል ሲል የክልል አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል።

08/02/2024
የክልሉ ትራንስፓርትና መንገድ ልማት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በመንገድ ትራፊክ ፍስት ቁጥጥር ዙሪያ በጋራ እየሠሩ ነው ቅንጅታዊ የመንገድ ትራፊክ ፍስት ቁጥጥር ሥራዎች ለአደጋ ...
25/01/2024

የክልሉ ትራንስፓርትና መንገድ ልማት ቢሮ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በመንገድ ትራፊክ ፍስት ቁጥጥር ዙሪያ በጋራ እየሠሩ ነው

ቅንጅታዊ የመንገድ ትራፊክ ፍስት ቁጥጥር ሥራዎች ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ እና ፍሰት በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ በተጠናከር መልኩ እየተሰራ ሲሆን ዛሬ በሚዛን መናሀሪያ ጀምሮ የቁጥጥር ሥራ ተጀምሮዋል።

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ትራንስፓርት እና መንገድ ልማት ቢሮ እና ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ቅንጅታዊ የመንገድ ትራፊክ ፍስት ቁጥጥር ሥራዎች ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ እና ፍሰት በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ በተጠናከር በሁሉም ዞኖች እንደሚከናወን ታወቋል።

በሶማሌ ክልል በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰው ህይወት አለፈ።     ጥር 5/2016 ዓ/ምን ሚዛን አማንበሶማሌ ክልል ከጅግጅጋ ወጣ ብላ በምትገኘው ሸበሌ  ከተማ በደረሰ የትራፍሪክ አደጋ...
14/01/2024

በሶማሌ ክልል በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰው ህይወት አለፈ።

ጥር 5/2016 ዓ/ምን ሚዛን አማን
በሶማሌ ክልል ከጅግጅጋ ወጣ ብላ በምትገኘው ሸበሌ ከተማ በደረሰ የትራፍሪክ አደጋ የ11 ሰው ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሶማሌ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ ።

አደጋው የደረሰው ከጅግጅጋ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሚኒባስ ከሸቤሌ ወደ ጅግጅጋ ሲሄድ ከነበረ ሲኖትራክ የጭነት መኪና ጋ በተፈጠረ ግጭት መሆኑን የገለፀው ፖሊስ በአደጋው የ11 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ12 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም ነው የጠቆመው።

በአሁኑ ሰዓት የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለህክምና ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ሼህ ሃሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታል መላካቸውንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

መረጃውን ያገኘነው ከሶማሊ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

በሸካ ዞን በክልሉ መንግስት የተገነቡ የጌጫ - ሸክበዶ መንገድና የገማህ ድልድይ በክልሉና በዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተጉበኙ ።     ጥር 2/216ዓ/ም ሚዛን አማን   ጉብኝቱ የመሩት በ...
11/01/2024

በሸካ ዞን በክልሉ መንግስት የተገነቡ የጌጫ - ሸክበዶ መንገድና የገማህ ድልድይ በክልሉና በዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተጉበኙ ።

ጥር 2/216ዓ/ም ሚዛን አማን
ጉብኝቱ የመሩት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክብር አቶ ፋጂዮ ሳፒና የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ
በሸካ ዞን በክልሉ መንግስት ከሚገነቡት የመንገድና የድልድይ ኘሮጄክቶች የጌጫ ሸክበዶ የመንገድ ኘሮጄክትና የገማህ ድልድይ ተጠቃሽ ናቸው።

በተለይ ግንባታ በቀድሞ ደቡብ ክልል የተጀመረና ለረጂም ጊዜ ግንባታው የቆየ ከጌጫ - ሸክበዶ መንገድ አሁን በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን ሚዛን ዲስትርክት ግንባታው እየተከናወነ በመሆኑ ግንባታ 80% በመድረሱ ቀሪው ሥራ በፍጥነት ተሠርቶ እንድጠናቀቅ ክብር አቶ ፋጅዮ ሳፒ አሳስበዋል።

በክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በሁሉ አቀፍ ቀበሌ ተደራሽ መንገድ ዘርፍ እየተገነባ ያለው የገማህ ድልድይ አፈፃፀም ዝቅተኛ በመሆኑ የግንባታ ቁሳቁስ በማሟላት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ይሠራል ተብለዋል።

ከጉብኝት በኃላ ከሸክበዶ ማህበረሰብ ጋር በተደረገው ውይይትም የክልሉ መንግስት በቀድሞ ክልል የተጀመሩት ኘሮጄክቶች ጨርሶ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ በመሆኑ መደስታቸውን ገልጸው ግንባታው በቶሎ እንድጠናቀቅ ጠይቀዋል።

የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ክልል ወደ ህዝቡ የመቅርቡን ምስጥር የክልሉ ማህበረሰብ በኢኮኖምያዊና በማህበራዊ ተጠቃሚ ማረጋገጡን ገልጽዋል።

ዋና አስተዳዳሪ አክለው በክልሉ መንግሥት እየተገነቡ ያሉ የጌጫ ሸክበዶ የመንገድ ኘሮጄክትና የገማህ ድልድይ የህዝብ ጥያቄ በመሆኑ ክትትልና ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
በጉብኝቱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክብር አቶ ፋጂዮ ሳፒና ምክትላቸው አቶ አሸብር ኢካሎ የክልሉ የመንገዶች ባለስልጣን ምክትል ሥራአስኪያጅና የኦኘሬሽን ዘርፍ
ኃላፊ ኢንጂነር ውዳለም ፍቃዱ ፣የሚዛን ዲስትሪክት ሥራ አስክያጅ አቶ አሸናፊ ወልዴ እንዲሁም የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞና ሌሎች የተገኙ ሲሆኑ በነገው መርሃግብር ቀሪ በዞኑ የተከናወኑ ሥራዎችን ይመለከታሉ ተብለዋል ።

የሚዛን መደበኛ ሦስት የህዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ባለንብረት ማህበር  አመታዊ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሚዛን አማን ከተማ  አካሄደ ።ጉባኤ የ2015 ዓ/ም የማህበሩ አፈጻጸም በመገምገም የ201...
02/01/2024

የሚዛን መደበኛ ሦስት የህዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ባለንብረት ማህበር አመታዊ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በሚዛን አማን ከተማ አካሄደ ።
ጉባኤ የ2015 ዓ/ም የማህበሩ አፈጻጸም በመገምገም የ2016ዓ/ም ዕቅድ ላይ ውይይት አድርጓል ።

ታህሳስ 23/2016ዓም ሚዛን አማን
ጉባኤ አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገኘው ወርቁ እንደተናገሩት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የህዝብ ትራንስፖርት ፈላጎት ምላሽ ለመስጠት ተሽከርካሪዎች በማህበር ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ማህበር በ2003ዓ/ም የተቋቋመ ሲሆን በተለይ የትራፊክ ደንቡን በማክበር የትራፊክ አደጋ ተከላክሎ እንድያሽከረክር ማህበር ኃላፊነት እንድወስድ አቶ አገኘው ገልጸዋል ።

የማህበሩን ሪፖርት ያቀረቡት የማህበሩ ሥራ አስክያጅ አቶ ደነቀ ወንዱ ማህበሩ በ2015ዓም ከ1.4 ሚሊዮን ተሳፋሪዎችን በማመላለስ የዕቅዱን 76 ከመቶ ማከናወን መቻሉ ተናግሯል።

ማህበሩ ድጋፍ በሚሹት ጉዳዮች በባለፈው ዓመት 86 733 ብር ድጋፍ ማድረግ መቻሉን ነው የተገለፀው።

ጉባዔ የ2015 ዓ/ም የማህበሩ አፈጻጸም በመገምገም የ2016ዓ/ም ዕቅድ ላይ ውይይት አድርጓል ከውይይት ተሳታፊዎች የተነሳውን ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" 5ኛ ዙር የሚዛን ክልል ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና ዛሬ ተጀመረ ።      ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም ሚዛን አማን  "ከዕዳ ወደ ምንዳ" 5ኛ ዙር የሚዛን ክ...
22/12/2023

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" 5ኛ ዙር የሚዛን ክልል ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና ዛሬ ተጀመረ ።

ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም ሚዛን አማን
"ከዕዳ ወደ ምንዳ" 5ኛ ዙር የሚዛን ክልል ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ አባል የመንግስት ሠራተኞች ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጀምረዋል ።

ስልጠናው ለተከታታይ አራት ቀናት በሚዛን ከተማ የሚሰጥ ሲሆን ሰልጣኞች በማህበራዊ ፣ በኢኮኖሚና በአስተዳደር ዘርፍ ተከፋፍሎ ስልጠናውን እየወሰዱ ይገኛሉ።

በዚህ መሠረት በኢኮኖሚ ዘርፍ የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ እና የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ በጋራ ሆነው ስልጠናውን እየወሰዱ ነው።

ስልጠናውን አሰመልክቶ የተናገሩት የክልሉ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ም/ኃላፊና የኢንቨስትመንት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከበደ ተስፋዬ እንደገለፁት "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል የሚሰጠው ስልጠና የብልጽግና ጉዞን እውን ለማድረግ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ ገልጽው ስልጠናው በአባሉ ዘንድ የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት ለማምጣት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል ።
በተለይም ተለዋዋጭ አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ጉዳዮችን በውል በመገንዘብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችንአባላቱ በብቃት እንድትወጡ ያስችላል ብለዋል።

አቶ ከበደ ተስፋዬ አክለውም የተቀመጡ እሳቤዎችና ፕሮግራሞችን የህዋስ አመራሩና አባሉ በመረዳት በሚቀርቡ ሰነዶች ትኩረት ሰጥቶ መከታተልና መውያየት እንድሁም ሀገረ መንግስት ለመገንባት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ያሉንን ውስን ሀብት በቁጠባ መጠቀም ይገባል። አቶ ፋጂዮ ሳፒ።ታህሳስ 12/2016ዓም ሚዛን አማንየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵ...
22/12/2023

የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ያሉንን ውስን ሀብት በቁጠባ መጠቀም ይገባል። አቶ ፋጂዮ ሳፒ።

ታህሳስ 12/2016ዓም ሚዛን አማን
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ላይ ያተኮረ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየሰጠ ነው።

በስልጠናው መድረክ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ የፋይናንስ አሰራር ስርዓት ጠንካራና ከብልሹ አሰራር የጸዳ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ያሉንን ውስን ሀብት በቁጠባ በመጠቀም የህዝቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች በተገቢው መመለስ ይገባልም ብለዋል።

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በበኩላቸው ከክልሉ ምስረታ ወዲህ የመንግስት ፋይናንስ አሰራር ስርዓት ለማሻሻል መጠነ ሰፊ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በፋይናንስ አሰራር ውስጥ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ሊሞላ የሚችል ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

ውስን የሆነውን ሀብት በቁጠባ የመጠቀም ባህልን በማዳበር ብክነትንና ብልሹ አሰራሮችን ማረም እንደሚገባም ወ/ሮ ወሰነች ተናግረዋል ።

በዚህም ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለውን አሰራር ለማስፈን የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተቀርጸው ስራ ላይ እየዋሉ እንደሆነም አንስተዋል።

የመንግስት ፋይናንስ አሰራሮችን ለማሻሻል የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ከ5.7 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን በማስታወስ ለተደረገውም ድጋፍ በክልሉ መንግስት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የፋይናንስ መረጃን ለዜጎች ግልጽ ማድረግ የፋይናንስ አስተዳደር አፈጻጸሞችን እንደሚያሻሽል ወ/ሮ ወሰነች ገልጸዋል።

በኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር የመንግስት ፋይናንስ ማሻሻያ ዲቪዥን ኃላፊ አቶ ዳዊት ሽመልስ ስልጠናው የመንግስት ሂሳብ አሰራርን ክፍተት የሚሞላና ክልሎች ከፌዴራል ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል ።

እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና ላይ የክልሉን ብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ መቱ አኩን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊዎች ባለሙያች እንዲሁም የየዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው ሲል የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል።

ሁለቱ ተቋማት የተጠናከረ ቅንጂታዊ አሠራርን በማስፈን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ እንደሚሠሩ ገለፁ ። ታህሳስ 02/2016ዓ/ም ሚዛን አማን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ...
12/12/2023

ሁለቱ ተቋማት የተጠናከረ ቅንጂታዊ አሠራርን በማስፈን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ እንደሚሠሩ ገለፁ ።

ታህሳስ 02/2016ዓ/ም ሚዛን አማን
የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ድህንነት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ክፍል ጋር የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ በሚቻልበት ዙሪያ የጋራ ውይይት አድርገዋል

ውይይቱም አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ትራፊክ ድህንነት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ቀለመወርቅ በክልሉ እየታየ ያለው የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ
የተጠናከረ ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።

ሁለቱ ተቋማት ክብር በሆነውን የሰው ህይወትና ንብረት ከውድመት የሚከላከሉ እንደመሆናቸው በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።
የክልል ፓሊስ ኮሚሽን የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር በድሩ ማሞ በክልሉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው አደጋ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመደጋገፍ ሳምንታዊና ወራዊ ኘሮግራሞች በማውጣት በጋራ መስራት እንደሚቻል ገልፀው ህብረተሰብ ከትራፊክ ፓሊስና ከመንገድ ደህንነት ባለሙያዎች ጎን እንድሆን ጭምር ገልጸዋል።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።ሚዛን አማን ፤ ህዳር 26/2016ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ...
06/12/2023

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል።

ሚዛን አማን ፤ ህዳር 26/2016ዓ/ም
የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ በየጊዜው እየተከለሰ ስራ ላይ የሚውል መሆኑን ጠቅሷል።
በዚህም መሰረት ከዛሬ ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም ነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በወቅቱ ወይም ስራ ላይ ባለበት ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን አስታውቋል።

በበኮንታ ዞን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርሱ ቦታዎችን በመለየት የመንገድ ዳር ምልክቶች እየተተከሉ መሆኑን ተገለፀ ።  ህዳ...
06/12/2023

በበኮንታ ዞን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣው የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርሱ ቦታዎችን በመለየት የመንገድ ዳር ምልክቶች እየተተከሉ መሆኑን ተገለፀ ።
ህዳር 26/03/2016ዓ/ም ሚዛን አማን
በኮንታ ዞን በትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ በመንገድ ትራፊክ ደህንነትና ኢንፎርሜሽን ቴክናሎጂ ብቃት ማረጋገጫ ቡድን መሪ አቶ ፈርዲሳ ሀላና እንደገለፁት ከአመያ ዙሪያ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የመንገድ ትራፊክ ደህንነትና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ብቃት ማረጋገጫ ቡድን መሪዎች ጋር በጋራ በመሆን በአመያ ዙሪያ ወረዳና በአመያ ከተማ አስተዳደር በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርሱ በቁጥር አምስት ቦታዎችመለየቱን ተናግረዋል።
እነዚህ የአደጋ ምልክቶች የተተከለባቸው ቦታዎች ከባድ ናዳ ያለበት ቦታ ፣ አደገኛ ቁልቁለት፣ ኩርባና ጠመዝማዛ መንገድ መኖሩን ገልጽው ምልክትና አመልካቻ የመትከል ሥራ የተሠራ ኦየተሠራ መሆኑን አብርራርተዋል።
አሽከርካሪዎችም የተተከለውን ምልክትና አመልካቾችን በአግባቡ በማየት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ያለውን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የበኩላቸውን ድርሻ እንድወጡ መልዕክት እያስተላለፍን የትራፊክ አደጋን በጋራ እንከላከል

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር  ከቴፒ ሚዛን እና ከቴፒ ሽሽንዳ በመሠራት ላይ ያለው አስፓልት መንገድ አስመልክቶ ኮንትራክተሮችና ከአማካሪዎች ጋር በሚዛን አማን ከተማ ተወያዩ።  ሚዛን አማን...
06/12/2023

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከቴፒ ሚዛን እና ከቴፒ ሽሽንዳ በመሠራት ላይ ያለው አስፓልት መንገድ አስመልክቶ ኮንትራክተሮችና ከአማካሪዎች ጋር በሚዛን አማን ከተማ ተወያዩ።
ሚዛን አማን ህዳር 26/2016ዓም

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደጄኔ ፍቃዱ ህዳር 24/2016ዓም ባደረጉት ውይይት
እንደገለፁት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በመገንባት ላይ ያሉት የአስፖልት መንገዶች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቁ በማህበረሰቡ ቅሬታ እያስነሳ መሆኑን ገልጽዋል።

በሁለቱም ኘሮጄክቶች የመስክ ምልከታ ማድረጋቸውን በውይይቱ ያነሱት ከሚዛን ቴፒ ያለው የመንገድ ኘሮጄክት 43 በመቶ መድረሱን በምልከታውም መመልከታቸውን ተናግረው።

በውይይቱም ኘሮጄክቶቹ የዘገዩት በዘርፍ ብዙ ምክንያትች መሆኑን የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዚህ ችግሮች ተፈተው መንገዶቹ በፍጥነት በሚሠራበት ሁኔታ አቅጣጫ አስቀምጧል
ሌላኛው በውይይቱ የተነሳው የመንገድ ኘሮጄክት ከቴፒ ሽሽንዳ ያለው ሲሆን የኮንትራክተር የሃቅም ውስንነት እንደሚታይባቸው በውይይቱ ተነስተው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥተዋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕስ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጅዮ ሳፒ መንገዶችን አስመልክቶ እንደተናገሩት የመንገድ ኘሮጄክቶች ፈጥኖ ወደ ሥራ ባለመግባት የተነሳ በደሞ ከይገባኛል ነፃ የተደረጉት አካባቢዎች ማህበረሰብ መልሶ እንድያለማ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ገልጾው የፌዴራል መንግስት ትኩረት እንድያደረግ መንገዶቹ እንድጠናቀቁ አሳስቧል።
ኘሮጄኮቶችን በቅርበት የሚከታተለው በኢትዮጵያ መንገዶችአስተዳደር የሚዛን አካባቢ ኮንስትራክሽን ኘሮጄክት ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ካልድ አሊ
ከሚዛን ቴፒ የሚገነባው 48 ኪ/ሜ የመንገድ ኘሮጄክት 30ኪ/ሜ ከይገባኛል ጥያቄ ነፃ በመደርጉ ገልጽው ቀሪው በከተሞች መግቢያ አካባቢ ላይ ያለው 18ኪ/ሜ ከይገባኛል ነፃ አለመደረጉን ተናግረው ከቤንች ሸኮና ከሸካ ዞኖች ከክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በጋራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከሽሽንዳ ቴፒ የሚገነባው በጣም ከፍተኛ ችግር ያለመሆኑን ኢንጂነር ካልድ አሊ ገልጸው የነበሩበትን ችግሮች ተፈተው በሙሉ ሃቅም ወደ ሥራ እንድገቡ መግባባት መድረሱን ነው።የተገለጸው።

በአጠቃላይ ለኘሮጄክቶቹ መዘግየት በምክንያትነት ከሚነሱ የይገባኛል ጥያቄ፣ የግንባታ ቁሳቁስ መናር፣ የኮትራክተሮች የሃቅም ውስንነትና በጀት በጊዜ ባለመለቀቅ ነው ተብለዋል።

በሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ አስተዳደር  የተዘጋጀ የአሠራር ማኑዋል ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር  የጋራ መግባባት ላይ ተደረሰ።ህዳር 21/2016ዓ...
01/12/2023

በሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ገንዘብ አስተዳደር የተዘጋጀ የአሠራር ማኑዋል ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት ላይ ተደረሰ።

ህዳር 21/2016ዓ/ም ሚዛን አማን
ውይይቱ ከዞን ት/መ/ል/መምሪያ ኃላሪዎች፣ የሁ/አ/ገ/ተ/መ/ል/ ዘርፍ ኃፊዎች እንዲሁም የአማካሪ እና የተቋራጭ ማህበራት በተገኙበት የአሰራር ማኑዋሉ ላይ ውይይት አድርገዋቸዋል።
ውይይቱን የመሩት በምክትል ርዕስ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጅዮ ሳፒ አንደገለጹት ቀደሞ በደቡብ ክልል በዞኖች ደረጃ የክፍያ ሥርዓት እንድወረድ የተደረገው በርካታ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በመኖሩ የተነሳ እንደሆነ ተናግረው አሁን በቀደሞ ክልል ለዞኖች ተሰጥተው የነበረው የURRAP ኘሮጄክት የገንዘብ ክፍያ አስተዳደር ሥርዓት ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት ከተደራጀ በኃላ በትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ በሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ልማት ዘርፍ በዞን ደረጃ ያሉ ስራዎችን በቅርበት ክትትል ማድረግ በመጀመሩ የፕሮጀክቶች አፈጸጸም በመገምገም ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት የመፍተሄ አቅጣጫ ሲያስቀምጥ መቆየቱና አሁንም መቀረፍ ሲኖርባቸዉ ያልተቀረፉ ጉዳዮች በመለየት ለችግሩ መፍቴሄ የሚሆን የአሰራር መኑዋል ለውይይት ሲቀርብ ለኘሮጀክጀቶች የሚላኩት ገንዘቦች ለታለመለት ዓላማ በማዋል የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሆነም ተገልፆአል።
የURRAP ኘሮጄክት ገንዘብ አስተዳደር ላይ የአሠራር የአሰራር ለውጥ ማድረግ ያሰፈለገው ክልላችን ከተመሰረተ በኋላ የታዩ ክፍተቶችን ለማስተካከል እና የተሻለ የፕሮጀክት አስተዳደር እንዲኖር እነዲሁም ለኘሮጄክቶች የተበጀተውን በጊዜና ለታለመለት አላማ እንድውል እንደሚያደርግ የቢሮ ም/ኃላፊና የሁሉ አቀፍ ገጠር ተደራሽ መንገድ ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ጌድዮን እስጥፋኖስ ተናግረዋል።

በውይይቱ የተሳተፉት የዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ስፊ ውይይት ከተድርገ ፤ ለተነሱት አስተያየቶች ማብራርያና ምላሽ ከተሰጠ በኃላ በአሰራር ማኑዋሉ አስፈላጊነት ላይ መግባባት በመድረስ ማኑዋሉ አንደንድ የተሰጡ አስተያቶች ተካተውበት እንዲወጣ በመስማማት ውይይቱ ተጠናቋል።

ሙስና ዜጎችን ለከፋ ድህነት የሚዳርግ  ህጋዊ አሠራርን ያልተከተለ አደገኛ ተግባር መሆኑ ተገለፀ ፡፡በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ቀንን ምክንያት ...
29/11/2023

ሙስና ዜጎችን ለከፋ ድህነት የሚዳርግ ህጋዊ አሠራርን ያልተከተለ አደገኛ ተግባር መሆኑ ተገለፀ ፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሠራተኞች ወይይት አድርጓል ።

ሚዛን አማን ህዳር 19/ 2016 ዓ.ም

የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሠራተኞች የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ ውይይት አድርጓል። በውይይቱም የኃላፊ ተወካይ አቶ ኢቢሳ ፊጣ ሙስና በሀገር ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ መስኮች ላይ ተጽዕኖ የሚያመጣ ሀገርን እስከመበተን የሚያደርስ አጸያፊ ተግባር መሆኑን ሁሉም አካላት በጋራ ልከላከሉ እንደሚገባ ተናገረዋል።

አቶ ኢቢሳ አያይዛው እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ ከሚፈታተኑት ምክንያቶች አንዱ ሙስና እንደሆነ በማንሳት ሁሉም የሴክተሩ ባለሙያዎች በተሠማራው የሥራ መስክ ፈጣንና ከሙስና የፀዳ አገልግሎት በመስጠት ሀገርንና ህዝብን በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለውይይቱ የተዘጋጀ ሠነድ ያቀረቡት የተቋሙን የልማት ዕቅድና በጀት ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ትዝታ ብርሃኑ ባቀረቡት የመወያያ ሠነድ ሙስና ዜጎችን ለከፋ ድህነት የሚዳርግ ህጋዊ አሠራርን ያልተከተለ አደገኛ ተግባር መሆኑ ተናግረው ሰፋ ያለ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በቀጣይ ቀናት የሚከበረው የፀረሙስና በዓል በጋራ እንደሚያከበር ገልጸዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የቢሮ ባለሙያዎች ውይይቱ አስፈላጊ እና ገንቢ መሆኑን አንስተው በዓሉ በየዓመቱ ብቻ ሳይሆን ያለውን ነባሪያዊ ሁኔታዎች ላይ ያማከለ እና በየጊዘው ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ያለበት መሆኑን አስገንዝበዋል።

በኮንታ ዞን ወደ ኮንታ ኮይሻ ወረዳ የሚወሰደዉ መንገድ የመሰንጠቅ አደጋ ደርሶበታል ሲል የዞኑ ፖሊስ ገልፃል።እንደፖሊስ መረጃ የመንገዱ ጉዳት የደረሰዉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እና የግዙፉ ...
31/10/2023

በኮንታ ዞን ወደ ኮንታ ኮይሻ ወረዳ የሚወሰደዉ መንገድ የመሰንጠቅ አደጋ ደርሶበታል ሲል የዞኑ ፖሊስ ገልፃል።

እንደፖሊስ መረጃ የመንገዱ ጉዳት የደረሰዉ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት እና የግዙፉ ኮይሻ ኃይድሮ ኤሌክትሪክ ፓወር ግንባታ በሚከናወንበት ኮይሻ መንገድ ላይ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ዲጅታል ቴክኖሎጅ አንጠቀምም በሚል ቅርታ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች  በሚዛን መነኃሪያ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሥራ ማቆም ተደርጎ ሂደቱም ተስተጓጉሎ ነበር ተስተጓጉሎ የነበረውም  ...
27/10/2023

ዲጅታል ቴክኖሎጅ አንጠቀምም በሚል ቅርታ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች በሚዛን መነኃሪያ በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሥራ ማቆም ተደርጎ ሂደቱም ተስተጓጉሎ ነበር ተስተጓጉሎ የነበረውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ጀምሮ በሙሉ ሃቅም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።

"አጥፍተናል ፤ የበደልነውን ህዝብና መንግስት ለመካስ ከነገ ጀምሮ በዲጂታል መነኃሪያ አገልግሎት ስራ እንጀምራለን" ፦ አሽከርካሪዎች ፣ ባለንብረቶችና የቦርድ አመራሮች

ሚዛን አማን ፣ ጥቅምት 16/2016 የዞኑን ሰላም ፣ አንድነትና አብሮነት ለማይፈልጉ አካላት መጠቀሚያ መሆን አይገባም ፦ አቶ ኮጁ ባደከች

በሚዛን አማን መነኃሪያ ዲጂታል የመነኃሪያ አገልግሎት ስራ ውስጥ አንገባም በማለት ላለፉት 3 ቀናት የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ አድማ በማድረግ ስራ መስተጓጎሉ የሚታወስ ሲሆን የዞኑ የፀጥታ መዋቅርም ህግ ለማስከበር በድርጊቱ የተሳተፉ አካላትን በቁጥጥር ስር ማድረጉ የሚታወስ ነው። እጥረቱን ለመቅረፍም በጊዜያዊነት የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ወደ ስምሪት በማስገባት ሲሰራም ተቆይቷል።

የቤንች ሸኮ ዞን ሠላምና ጸጥታ መምሪያ ፣ የዞኑ ፖሊስና የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አመራሮች ዛሬ ከሰዓት በኀላ ከአሽከርካሪ ባለንብረቶች ፣ ከቦርድና ከማህበራት አመራሮች እንዲሁም ከአሽከርካሪዎች ጋር በፖሊስ መምሪያ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውይድት አድርገዋል።

የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ኮጁ ባደከች እንደተናገሩት ድርጊቱ አሳፋሪ ፣ ሰው ተኮር በሆነው የትራንስፖርት ዘርፍ ውስጥ መፈጸም የሌለበት ድርጊት መሆኑን ገልጸው ድርጊቱ ከወንጀልም በላይ ኢ ሞራላዊ ነው ብለዋል። የጸጥታ መዋቅሩ ችግሩን ለመቅረፍና ህግ ለማስከበር የተኬደበትን ርቀትም አድንቀው ድርጊቱ መደገም የሌለበት ነው ብለዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ ባለንብረቶች ፣ የማህበራት አመራሮች እና አሽከርካሪዎች "በተፈጠረው ችግር አፍረናል ፤ የዞኑ መንግስት የሰጠንን ዕድል ባለመጠቀማችን የተፈጠረ ነው ፤ ስሜታዊ በመሆን በዞኑና በከተማዋ ገጽታ እንዲሁም ህዝቡን በማጉላላታታችን ይቅርታ እንጠይቃለን ብለዋል።

"የበደልነውን ህዝብና መንግስት ለመካስ ከነገ ጀምሮ በመነኃሪያ በመገኘት በዲጂታል የመነኃሪያ አገልግሎት ወደ ስራ እንገባለን" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ እንደተናገሩት በአመፅ ፣ ህግን በመጣስና አድማ በመምጣት የሚሰጥ ምንም አይነት ምላሽ አይኖርም ብለዋል። በተቃራኒው በመነጋገር ፣ በመደማመጥና በጠረጴዛ ዙሪያ በርካታ ችግሮችን መፍታት እየተቻለ በአመፅ ህዝብን ማንገላታትና ገጽታን ማበላሸት ተገቢ አይደለም ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች መንግስትና ህዝቡን ይቅርታ መጠየቃቸው ተገቢና ተቀባይነት ያለው ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ለተፈጠረው ችግር ተገቢውን የገንዘብ ቅጣት የሚቀበሉ ሲሆን በጊዜ ቀጠሮ የሚገኙትን ደግሞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ በበኩላቸው አመጽና አድማው በዞኑና በከተማዋ ገጽታ ላይ ጥላሸት ቀብቶ አልፏል ብለዋል። በመሆኑም በጠየቁት ይቅርታ መሰረት ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ የሚገባ ሲሆን የህዝብ ፍሰት መኖሩን እየወቁ ለማሳት አለመፈለግ በሚል የቅጣት ልክ እያንዳንዱ በአመፅ ውስጥ የተሳተፈ ተሽከርካሪ ባለቤት 2ሺ 500 ብር የሚቀጣ ሲሆን በጥቅሉ ከ785ሺ ብር በላይ ይቀጣሉ ብለዋል።

ይሁን እንጂ ከነገ ጀምሮ ወደ ስምሪት በማይገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍቸኛውን የቅጣት ጣሪያ ተቀጥተው ወደ መስመር እንደሚገቡ ኃላፊው ጠቁመዋል። በመሆኑም ህዝቡ ከነገ ማለዳ ጀምሮ

በምዕራብ ኦሞ ዞን ዛሬ በጣለው ከባድ ዝናብ ከጀሙ ከተማ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገናኙ መንገድ በናዳ ምክነያት መዘጋቱ ተጠቅሷል።ሚዛን አማን:-ጥቅምት 16 ቀን 2016ዓምበምዕራብ ኦ...
27/10/2023

በምዕራብ ኦሞ ዞን ዛሬ በጣለው ከባድ ዝናብ ከጀሙ ከተማ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገናኙ መንገድ በናዳ ምክነያት መዘጋቱ ተጠቅሷል።

ሚዛን አማን:-ጥቅምት 16 ቀን 2016ዓም
በምዕራብ ኦሞ ዞን ጀሙ ከተማ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም ጀሙ ከተማ ከባቹማ ከተማ እንዲሁም ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የሚያገናኘው መንገድ በሁለት ቦታ ናዳ መድረሱን እና ለትራንስፖርት ዝግ መሆኑ ተገልጿል።

ናዳ የደረሰው የመጀመሪያው ከባቹማ ከተማ መግቢያ እና ሁለተኛ በተለመደው ልዩ ስሙ ዝንግራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ መሆኑ እና ምክንያት በዛሬው ሌልት በጣለው ከባድ ዝናብ መሆኑ ተጠቅሷል።

በዚህ ምክንያት ለትራንስፖርት ዝግ በመሆኑ እና
የዞኑ መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መንገዱን ለማስከፈት ጥረት እያደረገ ይገኛል ሲል የምዕራብ ኦሞ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቦል።

በመናኸሪያዎች የሚደረገው የዲጅታል  ቴክኖሎጂ አገልግሎት ትግበራ መጀመር የተሳፋሪዎች እንግልት የሚቀነስ ብልሹ አሠራርን የሚያስቀር ነው አሉ ፦ ክብር አቶ ፋጅዮ ሳፒ።በ4ቱ ከተሞች የዲጅታል ...
20/10/2023

በመናኸሪያዎች የሚደረገው የዲጅታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ትግበራ መጀመር የተሳፋሪዎች እንግልት የሚቀነስ ብልሹ አሠራርን የሚያስቀር ነው አሉ ፦ ክብር አቶ ፋጅዮ ሳፒ።
በ4ቱ ከተሞች የዲጅታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ለማስጀመር ውይይት ተደርጎ ከስምምነት ተደረሱዋል።

ሚዛን አማን፦ጥቅምት 9/2016 ዓ.ም

በክልሉ 36 የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን አሉ። ከእነዚህ መናኸሪያን በ4ቱ መናሪያዎች በሙከራ ደረጃ በሚዛን አማን ፣በቴፒ፣ በቦንጋና በታርጫ መናሪያዎች ለማስጀመር ውይይት ተደርጓል።

ውይይቱን የመሩት በምክትል ርዕስ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጅዮ ሳፒ በመናኸሪያዎች የሚደረገው የዲጅታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ትግበራ መጀመር የተሳታፊዎች እንግልት የሚቀነስ ብልሹ አሠራርን የሚያስቀር ነው ብለዋል።

የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን ወደ ዲጅታል አገልግሎት ማስገባት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ዲጅታል ቴክኖሎጅ መጠቀም ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ አጭር ሰነድ በህዝብ ትራንስፖርት ዳይሬክተር በአቶ ኤቢሳ ፊጣ ቀርቦ ውይይት ተደረጓል።

በውይይቱ የተገኙት የክልሉ ፖሊሲ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰብስቤ ሻዎኖ እንደገለፁት ማህበረሰቡን የዲጅታል ቴክኖሎጅ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ከታሪፍ በላይ ክፍያና ከአቅም በላይ የመጫንን ስርዓት የሚያስቀር በዘርፉ የተሠማራውን ባለንብረት ጥቅሙን የሚያጠብቅ ቴክኖሎጅ መሆኑ ተደርጓል። በክልሉ በተመረጡት 4 መናኸሪያዎች በቅርብ ዲጅታል ቴክኖሎጅ ለመጀመር ስምምነት ተደርጓል።

በውይይቱ የክልልና የዞን የፖሊስ መሪዎች የዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት አመራሮች የመናኸሪያ ኃላፊዎች የህዝብ ትራንስፖርት ቦርድ ተሰብሳቢዎችና ሥራ አስክያጆች ተገኝተዋል።

በምዕራብ ኦሞ ዞን በደረሰው የትራፊክ አደጋ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።ሚዛን አማን፦ጥቅምት 7/2016 ዓ.ምአደጋዉ የደረሰዉ  ዞኑ በመኤንት ሻሻ ወረዳ ባሲ ቁጥር ...
18/10/2023

በምዕራብ ኦሞ ዞን በደረሰው የትራፊክ አደጋ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።
ሚዛን አማን፦ጥቅምት 7/2016 ዓ.ም
አደጋዉ የደረሰዉ ዞኑ በመኤንት ሻሻ ወረዳ ባሲ ቁጥር 5 ተብሎ በሚጠራ መንደር ውስጥ ባለሶስት እግር ባጃጅ ከፖሊስ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነው የዞኑ ፖሊስ የገለጸው።

በዞኑ ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር አስተባባሪ ም/ኢ/ር ጎቹ ቦቹባብ እንደገለፁት ጥቅምት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል በደረሰ አደጋ በባጃጅ ውሰጥ የነበሩ 5 ሰዎች ከባድ ጎዳት የደረሰ ሲሆን በ3 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

እንደ ኃላፊዉ ገለፃ የፖሊስ መኪና በፍርድ ቤት ወሳኔ ያገኙትን የህግ ታራሚዎችን ዞ ወደ ማረሚያ ተቋሚ ለማድረስ ቀኝ መስመር ይዛው እየተጓዘ ባለበት የባጀጅ አሽከርከረሪ ከአቅም በላይ 11 ሰዎችን ጭኖ የራሱን መስመር በመተው በፍጥነት እየተጓዘ መንገዱ ኩርባ ወይም ጠመዝማዛ በመሆኑ መስመሩን በመተዉ መስመሩን ይዞ ይጓዝ ከነበረ መኪና ጋር ተገጨቶ በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ዘግቦዋል።

የጥንቃቄ መልክቶችን ተግባራዊ በማድረግ የትራፊክ አደጋን ይከላከሉ።
13/10/2023

የጥንቃቄ መልክቶችን ተግባራዊ በማድረግ የትራፊክ አደጋን ይከላከሉ።

ለመለስተኛና መካከለኛ የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከሪካሪዎች የታርፍ ማሻሻያ ተደረገ።
11/10/2023

ለመለስተኛና መካከለኛ የህዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከሪካሪዎች የታርፍ ማሻሻያ ተደረገ።

የመሰረተ ልማት ስራ ቁልፍ የሰላም ፣ የልማት ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በትኩረት ይሰራል፦ ክቡር አቶ ቀበሌ መንገሻሚዛን አማን ፣ መስከረም 26/2016 የቤንች ሸኮ ዞን...
07/10/2023

የመሰረተ ልማት ስራ ቁልፍ የሰላም ፣ የልማት ፣ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በትኩረት ይሰራል፦ ክቡር አቶ ቀበሌ መንገሻ

ሚዛን አማን ፣ መስከረም 26/2016 የቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መመሪያ የ2015 አፈጻጸም እና በ2016 ዕቅድ ግምገማውን በሚዛን አማን ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀበሌ መንገሻ መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት እንደ ዞን ከህዝቡ መሠረታዊ ጥያቄዎች ውስጥ የመሰረተ ልማት ስራ ቀዳሚውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል። የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ዘርፍ አጠቃላይ በሰዎች ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ውስጥ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በዞኑ ደቡብ ቤንች ወረዳ በራስ አገዝ የወረዳውን ህዝብ ፣ አመራሩ ፣ አልሚ ባለሀብቱና መንግስት ሰራተኛውን አቅም በማድረግ 3 ትልልቅ ድልድዮችን በመገንባት ህዝቡን ባለቤት በማድረግ ከሰራን የማይቻል ነገር እንደሌለ እንደ ክልል ተሞክሮ ሊሆን የሚችል ተግባር ተፈጽሟል ብለዋል።

በተለይ በትራንስፖርት ዘርፉ ላለፉት አመታት የነበረውን የመልካም አስተዳደር ችግርና የህዝቡን እሮሮ አሰራሩን በማዘመንና በቅንጅት በመስራት ለውጦች እየታዩ መጥተዋል ብለዋል። አሁንም ችግር ሆኖ የቀጠለውን የትራፊክ አደጋ መቀነስና መሰረተ ልማትን ተደራሽ ማድረግ በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ መስራት እንደሚያስፈልግ ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል።

የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የመንገድና ትራንስፖርት ዘርፍ እንደ ሀገር አጠቃላይ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል። በዞኑም ባለፉት አመታት መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ወረዳን ከወረዳ ፣ ወረዳን ከቀበሌና ወረዳን ከዞን ማዕከል የሚያገናኙ መንገዶች ፣ ድልድዮች ና የውስጥ ለውስጥ የከፈታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

በትራንስፖርት ዘርፉ አደጋዎችን ለመቀነስ በከተሞች የፍጥነት መቀነሻ ፣ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና በተለያዩ አካባቢዎች የንቃተ ህሊና ትምህርቶች ለአሽከርካሪዎችና ለእግረኞች ተሰጥቷል ብለዋል። ህዝቡን አሳትፈን በሰራንባቸው ዘርፎችም ለውጦች እየታዩ ሲሆን እነዚህን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ኃላፊው ጠቁመዋል።

በመድረኩ የመምሪያው ኃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ የ2015 የተቋሙን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በመምሪያው የልማት ዕቅድ ባለሙያ አቶ ውዳዬ ገዳዎ የ2016 ጠቋሚ ዕቅድ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በመድረኩ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች ፣ የዘርፉ ኃላፊዎች ፣ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ኃላፊዎች ፣ የትራንስፖርት ማህበራትና የልዩ ትራንስፖርት ዘርፍ አመራሮች በመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል።

በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የህሊና ፀሎትም ተደርጓል ሲል የቤንች የሸኮ ዞን መንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/አቤት ነው።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የተጀመረው 1ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የትራፊክ ቁጥጥሩ 4ኛ ቀኑን ይዞ ቀጥሎዋል።    መስከረም 8/2016ዓ/ም ሚዛን አማንከመስከረም ...
19/09/2023

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የተጀመረው 1ኛ ዙር ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የትራፊክ ቁጥጥሩ 4ኛ ቀኑን ይዞ ቀጥሎዋል።
መስከረም 8/2016ዓ/ም ሚዛን አማን
ከመስከረም 4/2016ዓ/ም በክልላችን በቤንች ሽኮና በካፋ ዞኖች በተደረገ የትራፊክ ቁጥጥር ትኩረት የተደረገባቸው ነጥቦች የማስተማርና የቁጥጥር ሥራ ተሰርቶ መቆየቱን ቀድመን መዘገባችን የሚታውቅ ነው ።

ትኩረት የተደረገውም የ3ኛ ወገን መድን ሽፋን፣ የቦሎ የዕድሳት ጊዜ ያለፍባቸውና የቴክኒክም ምርመራ ያላደርጉ፣ ቀበቶ የማያስሩት፣ የመረጃ ፍቃድ የሌላቸውና የዕድሳት ጊዜው ያለፈባቸው እና ፍቃድ ሳይኖራቸው የሚያሽከረክሩ አሸከርካሪዎች ላይ የቁጥጥር ሥራ በሁለቱም ተደረጉዋል እየተደረገም ይገኛል።
በቀን7/2016ዓ/ም በበካፋ ዞን ጨና ወረዳ የትራፊክ አደጋ በተደጋጋሚ የሚከሰትበት ቀኔች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመስከረም 5/2015ዓ/ም በቆሎ ጭኖ ከሲዝ ከተማ እንደተነሣ እና ከምሽቱ 5 ሣዓት የወደቀውን ስኖትራክ አይተናል ።

ረዳትና ሾፌር ይዞ ከምሽቱ 5 ሣዓት የወደቀውን ስኖትራክ የአካባቢው ህብረተሰብ ተረባርቦ መኪናው የወደቀው በሹፌሩ በኩል ስለነበረ ሾፌሩ ለማዳን ባደረጉት ጥረት ከምሽቱ 5 ሣዓት እስከ ንጋት 12 ሣዓት ድረስ እንደፈጀና ሹፌሩ በህይወት ተርፊው ሁለቱም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ጀማ ሪፈራል ሆስፒታል ላይ እንደሚገኙ አሰረድተውናል በቦታውም በመገኘት ምልከታ አድርገናል ።
ዛሬ በቀን 8/2016ዓ/ም በካፋ ዞን በተደረገ የመንገድ ላይ የተቀናጀ የትራፊክ ቁጥጥር 8 ባጃጆች የሦስተኛ ወገን መድን ሽፋን ባለመኖር ተይዞ ጉዳያቸው በህግ ማዕቀፍ እየታየ ይገኛል። የቁጥጥሩ ሥራም በሁሉም የዞኖችና ከተማ አስተዳደር እየተደረገ ነው።ፈጣን መረጅዎች ለማግኘነት የፌስቡክገጽያችን።
ይከታተሉ Like Comment share አይዘንጉ!!https://www.facebook.com/profile.php?id=100078221053769

በክልሉ የትራንስፖርት ዘርፉን ዲጂታላይዝ በማድረግ በዘርፉ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ገለጸ።ሚዛን አማን ፣ መስከረም 7...
18/09/2023

በክልሉ የትራንስፖርት ዘርፉን ዲጂታላይዝ በማድረግ በዘርፉ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ገለጸ።

ሚዛን አማን ፣ መስከረም 7/2015 ቢሮው ከምዕራብ ሶፍትዌርና ትራንስፖርት ማህበር አማካኝነት በሚዛን አማን የህዝብ ትራንስፖርት የዲጂታል አገልግሎት ማስጀመሪያ መድረክ ተካሂዷል።

የምዕራብ ሶፍትዌርና ትራንስፖርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ዶክተር ታረቀኝ ታፈሰ ለባለድርሻ አካላት ባቀረቡት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ሶፍትዌሩ በዘርፉ የሚስተዋሉ ስር የሰደዱ ችግሮችን የሚቀርፍ ነው ብለዋል።

ሶፍትዌሩ ከዚህ ቀደም በትርፍ መጫንና ከታሪፍ በላይ ማስከፈልን ሙሉ ለሙሉ የሚያስቀርና ህገ ወጥ ስምሪቶችን መቀጣጠር የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። አሰራሩን ከመነኃሪያዎች ጀምሮ እስከ ክልል ተቋማት ድረስ ወጥና የአንድ ቋት አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ አሰራሩን ዘመናዊ ያደርጋል ብለዋል።

በክልሉ ፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ በስምሪት ላይ የሚገኙ ተሽከርካሪዎችን ለማወቅና ለመቆጣጠር ፣ የመኪና ባለቤቶች ትክክለኛ የጉዞ ታሪክ መረጃ እንዲያገኙ ፣ በመነኃሪያ ውስጥ ረጅም ሰልፎችን ፣ እንግልትና ዘረፋን የሚያስቀር ነው ብለዋል። ሰዎች ባሉበት ሆነው በሞባይል መተግበሪያ ትኬት መቁረጥ የሚችሉበትና የትራፊክ ፖሊሶችን ስምሪት በቀጠናና በኦን ላይ መከታተል የሚያስችል አሰራር ይተገበራል ብለዋል።

የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሸብር ኢካሎ በመድረኩ እንደተናገሩት የትራንስፖርት ዘርፉ እንደ ሀገር የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ሞተር ነው ብለዋል። እየጨመረ ከመጣው የህዝብ ቁጥር ፣ የተሽከርካሪና የትራንስፖርት መዳረሻ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ ዘርፉን ለመምራት ዘመናዊ አሰራርን መከተል የግድ የሚልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ብለዋል።

በዚህም ቀልጣፋ ፣ ጊዜ ቆጣቢና ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎትን በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል ብለዋል። በተለይም በክልሉ 4 ብዝሀ ከተሞች ላይ እስከ መስከረም 20 የዲጂታል አገልግሎቱ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

በክልሉ ትራንፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የትራንስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ኤቢሳ ፊጣ እንደተናገሩት በክልሉ 34 መነኃሪያዎች ፣ 12 የትራንስፖርት ማህበራትና ከ800 በላይ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በስራ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ሶፍትዌሩም በተሳፋሪዎች ላይ የሚደርሱ እንግልቶችን ፣ ህገ ወጥ ታሪፍ ፣ ስምሪትና ትርፍ መጫንን ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ በበኩላቸው በትራንስፖርት ዘርፉ ትርፍ መጫንና ትርፍ ማስከፈል መሰረታዊ ችግር ሆኖ ቆይቷል ብለዋል። ዘርፉን ከነዚህ ችግሮች ለማላቀቅና የተሳፋሪዎችን እንግልት ለመቀነስ ቴክኖሎጂው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል።

በመነኃሪያዎች ውስጥ የነበሩ የትኬት አቆራረጥና ስምሪት ስራን ዘመናዊ የሚያደርግና ቀልጣፋ አገለግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል። ስራውን በጀመሩ አካባቢዎች በመሄድም የልምድ ልውውጥ መደረጉን ገልጸዋል።

በመድረኩ የክልል ፣ የዞን ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮች ፣ የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊዎች ፣ የማህበራት አመራሮችና የመነኃሪያ ስምሪት ተቆጣጣሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የቤንች ሸኮ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ዘግቦል

የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን ወደ ዲጅታል አገልግሎት ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።የቴፒ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን ወደ ዲጅ...
17/09/2023

የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን ወደ ዲጅታል አገልግሎት ለማስገባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቴፒ የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን ወደ ዲጅታል አገልግሎት ለማስገባት ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቴኘ ከተማ ተሰጥቷል ።

ሚዛን አማን፦መስከረም 6/2016 ዓ.ም

የግንዛቤ ማዕጨበጫ መድረክ ላይ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምረያ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ሀራ እንደገለፁት እጨመረ የመጣው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የመጓጓዝ ፈላጎት ለማረካት ትራንስፖርት ወሳኝ ሚና እንዳለዉ ተናግሯል።

የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን ወደ ዲጅታል አገልግሎት ማስገባት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ዲጅታል ቴክኖሎጅ መጠቀም ከፍተኛ ጠቀመታ እንዳለዉ ኃላፊዉ ገልጸዋል።

በዚህ ዲጅታል ቴክኖሎጅ አገልግሎት ተጠቃሚ ማህበረተሰቡን ከታሪፍ በላይ ክፍያና ከአቅም በላይ የመጫንን ስርዓት የሚያስቀር ቴክኖሎጅ መሆኑ አስረድቷል

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊና የትራንስፖርት ኃላፊ አቶ አሸብር ኢካሎ መድረኩ ላይ ተገኝተዉ መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ትራንስፖርት ሰዉንና ዕቃዎችን ከቦታ ወደ ቦታ ከማቀሳቀስ ዘንድ ትልቅ ሚና ያለዉ ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል ።

ወቅቱ የደረሰበት ዲጅታል ቴክኖሎጅ በመጠቀም የህዝባችን ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ስርዓቱን ማዘመን አስፈላጊ ነዉ ብለዋል።

የትራንስፖርት ዲጅታል ቴክኖሎጅ ተሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች የማይጎዳ መሆኑን የገለጹት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ይህ ዲጅታል ቴክኖሎጅ የጎላ ጠቀመታ እንዳለ ገልጿል ።

የህዝብ ትራንስፖርት መናኸሪያን ወደ ዲጅታል አገልግሎት ለማስገባት ምዕራብ ሶፍትዌርና ትራንስፖርት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

የተዘጋጅ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ምዕራብ ሶፍትዌር ካምፓኒ ስራ አስክያጅ ዶ/ር ታረቀኝ ተደሰ ቀርባ በተሳታፊዎች ዉይይት ተደረጎ በተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራርያ ተሰጥተው የመናኸሪያ ጉብኝት በማድረግ ተጠናቆል ።

አንደኛ ዙር  ሀገር አቀፍ የትራፊክ ቁጥጥር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መረሃ ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ተጀመረ።      መስከረም 5/2015ዓ/ም ሚዛን አማንበመርሀ...
16/09/2023

አንደኛ ዙር ሀገር አቀፍ የትራፊክ ቁጥጥር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መረሃ ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ተጀመረ።
መስከረም 5/2015ዓ/ም ሚዛን አማን
በመርሀ ግብሩን ለምስማሩት አካላት ኦሬንቴሽን የሰጡት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ እና የትራንስፖርት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አሸብር ኢካሎ እንደገለጹት ከጊዜ ወደ ጊዜው እየጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር የትራፊክ ቁጥጥር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፊት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።
በክልል በ2015ዓም 362 ከባድና ቀላል አደጋዎች ሲመዘገቡ 108 የሞት አደጋ መከሰቱን ጠቅሶ ከፌዴራል የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ባለሙያዎች።

የክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ደህንነትና ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ቀለመወርቅ ከመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ከመስከረም 03/2016 ጀምሮ እስከ መሰከረም 30/2016 የምቆይ ሀገር አቀፍ የትራፊክ ቁጥጥር እና ግንዛቤ ማስጨበጫ በክልሉ አደጋ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እንደሚደረግ ገልጸዋል።

በትራፊክ ቁጥጥርና የግንዛቤ ማስጨበጭያ ትኩረት የሚደረገውም የ3ኛ ወገን መድን ሽፋን፣ የቦሎ የዕድሳት ጊዜ ያለፍባቸውና የቴክኒክም ምርመራ ያላደርጉ፣ ቀበቶ ፣ የመረጃ ፍቃድ የዕድሳት ጊዜው ያለፈበት እና ፍቃድ ሳይኖራቸው የመስታወት ማጥቆሪያ ስቲከር እየተጠቀሙ የተያዙ አሸከርካሪዎች ላይ የቁጥጥር እየተደረገ መሆኑንም ማየት ተችሎዋል።

በመረሃ ግብሩ ከፌዴራል መንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት፣ ከክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ፣ከክልል ፖሊስ ኮሚሽን ከዞኖች እንዲሁም ከከተማ አስተዳዳሪ የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ ፖሊስ ተሳታፊ ሲሆኑ በሚዛን አማን ከተማ አማን ክፍለ ከተማ ዲማ በር እና በርጌስ አካባቢዎች ላይ ሥራው ተጀምሯል።

ዘገባው የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ነው።

አርብቶ አደሩን በእንስሳት ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ድርቅን በዘላቂነት የሚቋቋሙ ተግባራት ማከናውን እንደሚገባ የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ።የምግብና ስርዓት ም...
07/09/2023

አርብቶ አደሩን በእንስሳት ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ድርቅን በዘላቂነት የሚቋቋሙ ተግባራት ማከናውን እንደሚገባ የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የምግብና ስርዓት ምግብ ደህንነት እንዲሁም የአደጋ ስጋት ቅነሳ አካታችና የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት በቁም እንስሳት መድህን ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና እየሠጠ ነው።
ጳጉሜ 2/2015 ዓ/ም ሚዛን አማን
በግንዛቤ ማስጨበጭያ መድረክ ተገኝተው ውይይቱን የከፈቱት የክልሉ አርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ታምሩ ቦኒ የአርብቶ አደሩን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር የምግብና ስርዓት ምግብ ደህንነት እንዲሁም የአደጋ ስጋት ቅነሳ አካታችና የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት የአርብቶ አደሩን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግና የአኗኗር ዘይቤን በማሻሻልና የማህበረሰቡን ዘላቂ ተጠቃሚነትን እያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል ።

አርብቶ አደሩን በእንስሳት ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ድርቅን በዘላቂነት የሚቋቋሙ ተግባራት ማከናውን አስፈላጊ በመሆኑ ኘሮጄክት በቁም እንስሳት መድህን አሰራር ዙሪያ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ለተሰማሩት ለህብረት ስራ ማህበራት አመራሮችና ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጭያ ስልጠና እየሠጠን

የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ የምግብና ስርዓት ምግብ ደህንነት እንዲሁም የአደጋ ስጋት ቅነሳ አካታችና የኢኮኖሚ እሴት ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ ኦይጌሌች በበኩላቸው የሚቀረጺ የልማት ፕሮጀክቶች የአርብቶ አደር ህይወት በእንስሳት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ እንስሳትን የመድህን ሽፋን በመስጠት ከሰው ስራሽና ከተፈጥሮ አደጋ እንስሳቶችን በመጠበቅ ይቻላል ብለዋል።

ኘሮጄክቱን የአርብቶ አደሩን ግንዛቤ በመጨመር በእንስሳት ውጤታማ ሥራዎች እያከናወነ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በቀረቡት ሰነዶች ውይይት እየተደረገ ይገኛል ።

Address

All
Bonga

Telephone

+251917154319

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South West Ethiopia people RegionaState Gov.t Transport & Road Dev.t Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share