ሎሚ ሚድያ/Lomi Media/

ሎሚ ሚድያ/Lomi Media/ Promote free sprech

03/02/2024

ኢንተርቪው ኣስገዶም ተወልደ ተኣንገዱታደ🙏🙏🙏

01/08/2023

ንሓበሬታ !!

ሎሚ ኣማስዩ ሰዓት 2 : 15 ኣብ ትግራይ ሓዊሱ ኣብ ቐርኒ ኣፍሪካ ኢትዮጵያ : ኤርትራን ሱዳንን ፅዕንቶ ዝነበሮ ብሬክተር ስኬል 5.6 መጠን ዝነበሮ ምንቅጥቃት መሬት ከምዘጋጠመ ተሓቢሩ ።

ምስ መሬት ዝተኣሳሰር ሳይነስ ዘፅንዕ ፥ ማእኸል ምርምር ጂኦ ሳይነስ ጀርመን (GFZ) ከምዝገለፆ ካብ ምፅዎዕ 65 ኪሎ ሜትሮ ብ ኣንፈት ደቡባዊ ምብራቕ ዝተሰምዓ ርእደ መሬት ኣብ ከባቢታት ቐርኒ ኣፍሪካ ኢትዮጵያ ፥ ኤርትራን ሱዳንን ፅዕንቶ ዝነበሮ መጠኑ 5.6 ሬክተር ስኬል ዝተመዝገበ ከቢድ ዝበሃል ምንቅጥቃጥ መሬት ኣጋጢሙ እዩ ።

በቲ ዝተመዝገበ መጠን ርእደ መሬት ዛጊድ ዝበፅሐ ዝኸፍኣ ጉዳት ከምዘየለ ዝገለፀ እቲ ማእኸል ኣብ ገዛውቲን ኣቑሑትን ምንቕናቕ ከምዝፈጠረ ሓበሬታት ከምዘሎ ሓቢሩ ኣሎ ።

ኣብ ትግራይ ፅዕንቶ እቲ ምንቅጥቓጥ መሬትን መጠኑን ንፁር ዝኾነ ሓበሬታ ዋላ እንተዘይገለፀ ኣብ ብርክት ዝበሉ ከባቢታት ከዘጋጠመ ማእከል ምርምር ጂኦ ሳይንስ ጀርመን ሓቢሩ ኣሎ ።

ኣብ ትግራይ ኣብ መቐለ ሓዊሱ ኣብ ዞባታት ሰሜን ምዕራብ ማእኸልን ምብራቕን ብርክት ዝበሉ ከባቢታት ፅዕንቶ እቲ ምንቕጥቃጥ መሬት ከምዝተሰምዓ ብርኽት ዝበሉ ወገናት ሓቢሮም ኣለው።

14/06/2023

መረፃ ቦርዲ ድማ ብሓፂሩ " ኣይኾነይ ናትኹም ዕሸል ህወሓት ፣እቲ ዝነበረ ህወሓት እውን ዳግማይ ኣይንምዝግቦይ " ዝዓይነቱ መልሲ ከምዝሃቦም ሪኢና። ብጥይት ኣይጠፍእን ዝበለ ውድብ ፣ ብእስክርቢቶ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

ምርጫ ቦርዲ ፌድሪኢ ኣብ ልዕሊ ፖለቲካዊ ውድባት ትግራይ ዝወሰዶ ስጉምቲ መዘራረቢ ኾንኑ ቀንዩ። ብፍላይ ኣብ ልዕሊ ህወሓትን ኣብተን ኣብ መረፃ 2012 ዓም ዝተሳተፉ ውድባት ዘሕለፎ ውሳነ ንብዙሓት ወገናት ኣደንጊፁ እዩ። ብቀንዱ ግን መራሕትን ደገፍትን ህወሓት ዘይገመትዎ መርድእ ወሪድዎም -ዋላኳ ነገራት ንዘስተውዕል ሰብ ምንም ሓድሽ ነገር ተዘይሃለዎ!

ኣብዚ ሰሙን ለለ ገብረሚካኤል ተስፉይ ዝበሃል ትግራዋይ ሓውና ፣ ውሳነ መረፃ ቦርዲ መሰረት ገይሩ ህወሓት ዝበሃል ኻልእ ውድብ ክምስርት ስለዝደለኹ ይፈቀደለይ ኢሉ ምምልኻቱ ሰሚዕና። መረፃ ቦርዲ ድማ ብሓፂሩ " ኣይኾነይ ናትኹም ዕሸል ህወሓት ፣እቲ ዝነበረ ህወሓት እውን ዳግማይ ኣይንምዝግቦይ " ዝዓይነቱ መልሲ ከምዝሃቦም ሪኢና። ብጥይት ኣይጠፍእን ዝበለ ውድብ ፣ ብእስክርቢቶ።

ብዝኾነ እዞም ሓደሽቲ ምዕባለታት ናብ ዕድል ክንቅይሮም ንኽእል ኢና። ብፍላይ ኣባላት ውድብ ህወሓት ዝነበርኹም ኽልተ ኣማራፂ ኣለኩም ፣

ሓደ ፣ ውድብኹም ስለዘየለን ንቀፃሊ እውን ስለዘይህልው ብሓድሽ ኣተሓሳስባን ኣወዳድባን መፂእኹም ንህዝብኹም ምኽሓስ ፣

ኽልተ ፣ ኣብተን ዘለዋ ሕጋዊ ውድባት ተፀንቢርኹም ፣ኣድላይ ዘበለ ተሃድስ ወሲድኹም ነተን ውድባት ብምጥንኻር ህዝብኹም ምክሓስ!

እዚ ሓድሽ ምዕራፍ ብብልሓት ኣንቢብና ናብ ረብሓና ክንልውጦ ይግባእ።

ካብ ብቅልፅም ምሕሳብ ናብ ብርዕሲ ምሕሳብ ንሰጋገር! ✊

ብ Tesfamichael Nigus

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=779062817151246&id=100051426044210&mibextid=Nif5oz
03/06/2023

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=779062817151246&id=100051426044210&mibextid=Nif5oz

ዋኒንና እንታይ ይኹን? እንታይ ነቐድም-እንታይ ነስዕብ? ኣብ እንታይ ነድህብ?!!

ህዝብና ኣብ ሕሱም ዓንኬል ድኽነት ኮይኑ ሓገዝ እናተሰፍረሉ ድኽነት እናተኻፈለ ዝፀንሐሉ እዋን ክሓፅር፣ ናብ ልሙድ ዕለታዊ ናብርኡን ልምዓቱን ክምለስ ቅድሚኹሉ ክንረባረብ ይግባእ። “ጊዘ እንተለካ-ጊዘ ኣይትፀበ” እዩ ‘ሞ ነዚ ጋህዲ ንምግባር ድማ፣ ቆላሕታና ኣብ ዘላቒ ረብሓ ህዝቢ ትግራይን ውሽጣዊ ዓቅምናን ክኸውን ይግባእ-ግድን እውን እዩ።

ህዝብና መፃኢ ጉዕዝኡ፥ ጉዕዞ ልምዓት፣ ሰላምን ህድኣትን ክኸውን እንተኾይኑ፣ እዚ ክኸውን ዘኽእሉ ወሰንቲን ጠለብ እዚ እዋን ዝኾኑ ስራሕቲ ቅድሚያ ሂብና ነድምዕ። ኣብ ሓፂርን ነዊሕን ጊዜ ዝስርሑ ዛዕባታት ንፍለ፤ ኣብ ቅደም ሰዓቦም ንመያየጥ፣ ንረዳዳእ።

ካብዚ ወፃእ፥ መዓልቦ ዘይረኸቡ ዋኒናት ህዝብናን ክልልናን እናሃለዉ ብውልቃውን ጉጅላውን ረብሓታት ተጎልቢብና ንውሽጣዊ ሕልኽልኽን ዕንቅፋትን ኣይንቃላዕ። እኳደኣስ፣ ኣብ ውሽጥና ነቓዕ ፈጢሮም ከተፋኑኑና፣ ዓቕምና ከላሕልሑ፣ ሓድነትና ክዘርጉ፣ ቆላሕታና ክዕምፅፁን ከዛብዑን ቀትሪ ምስ ለይቲ ዝሰርሑ ዘለዉ ውልቀ ሰባት ኮኑ ጉጅለ ልእኽቶኦም ተረዲእና ክንፈልጦም፣ ክነዐግሶምን ብሓድነት ብፅንዓት ክንቃለሶምን ይግባእ።

ወድዓዊ እዋናዊ ፀገማት ንምፍታሕ ዝውሰዱ ዘለዉ መፍትሕታት ልማድ ኾይኖም፣ ነዊሕ እማተና ከየንፀላልዉና፣ ከየዘናግዑና ልዑል ጥንቃቐ ክንገብር ኣለና። ስለዝኾነ እውን፣ ጎናጎኒ ምፍታሕ እዋናዊ ፀገማት፣ ህዝብና ጥሉል ረብሕኡ ናብ ዘረጋግፀሉ ልምዓት ሆ! ኢሉ ብምልኣት ክዓስል፤ ናብራ ህዝብና ብዘላቅነት ክንቅይር፣ ኣበይ ኣድሂብና ክንሰርሕ ከምዝግበኣና ንመሚ፤ ንተልም፤ ብፍጥነት ኣድሚና ንስራሕ።

ሓገዝን ልመናን፥ እዋናዊ ፀገም ንምዝሓል፣ ብዂናት ዝዓነዉን ዝተጉሓሉን መሰረተ-ልምዓት ንምህናፅን ንምትካእን፣ ካብ መረበቶም ዝተመዛበሉ ኣሕዋት-ወኣሓት ናብ መረበቶም ንምምላስ እንበር፤ ሱር ድኽነት ንምምሓው ከቶ ኣይሕግዝን። ድኽነት ዝቡርቆቕ፥ ህዝብና ኣብ ዓርሱ ዝተመርኮዘ፣ ውሽጣዊን ከባብያዊን ዓቕሙን ሃፍተ-ገነቱን እንተደንፍዕ ጥራሕ እዩ። እዚ መሰረት ዝገበረ ብጊዜ የለን መንፈስ ፅንኩር ስራሕ ብምስራሕ ህዝብና ብዝግባእ ክንክሕሶ ይግባእ።

ስለዝኾነ እውን፣ ህዝብና ሐዚ ዝሓቶም ህፁፃት ሕቶታት፥ ከም ግዝኣት ሓድነት፣ ሓይልታት ደገ ይውፅኡ ፣ ተሓታትነት ይረጋገፅ ወዘተ. ዝኣምሰሉ ዛዕባታት መዕለቢ ንምሃብ ዘኽእል ምስትውዓል፣ ስኽነት መሰረት ዝገበረ፣ ዘላቒ ሰላምን ህድኣትን ደሕንነትን ህዝብና ከረጋግፅ ብዝኽእል መንገዲ ክፍፀም ምግባር ከድሊ እዩ ፤ እዚ ድማ ናይ ግድን ክኸውን እዩ ።

ብኣንፃሩ፣ ዘይረብሕ ፖለቲካዊ ኾነ ውልቃዊን ጉጅላዊን ረብሓ ንምርካብ ኣብዙይን-ኣፍቱይን ዝግበር ደፋእፋእ ክእረም ይግባእ፤ ስለዘይጠቅም፤ ስለዘይጠቐመ፤ ኣዕናዊ ስለዝኾነ። ዝጠቕመና፥ ዝሃንፀና፥ ራህዋን ቅሳነትን ህዝብና ዘኾለዐልና፥ ሕብረት እዩ፤ ሓድነት እዩ፤ ኢሂን-ምሂን እዩ፤ ፍጥነት ዝተመልኦ ሓዱሽ ኽያዶ ኣብ ናይ ሓባር ኣጀንዳ ብሓባር ምኻድ እዩ።

ብኻሊእ መዳይ፥ ጓጓኻን ደንበኻን ከየቓለብካን ከይተረዳእኻን፣ ካብ ድርኩዂት ገዛኻ ወፃእ ኣብ ዞባዊን ዓለማውን ትንታነ ተፀሚድካ ምዓል ልምዓትን ብልፅግናን ህዝብኻ ወስ ኣየብልን። ጨና ዲሞክራሲ ዘይትፈልጥ፥ ስለኻልኦት ኢ-ዲሞክራሲነት፣ ሕፍኒ ልምዓት ዘይዓኾትካ፥ ኻፈር ልምዓት ኻልኦት ምንሻው፣ ዝሩግ ሰላምን ህድኣትን ውሽጥኻ ገዲፍካ፥ ፀገም ሰላምን ህድኣትን ካልኦት ክትንትን ምውዓል “ፅንብላሊዕስያ ‘መዓኮራ’ ዘይከደነት-ምድሪ ከደነት” ከምዝበሃል ከይኸውን ኣብ ውሽጥና መሰረት ኣብ ዝገበረ ስራሕ ብምድሃብ ህዝብና ዓለም ዝበፅሐቶ ብርኪ ማሕበረ-ቁጠባ ከብፅሕ ዝኽል ስራሕቲ ንስራሕ።

ኣብ መወዳእታ፥ ኣብ ዝኾነ ይኹን ኩርናዕ ዓለም ዘሎ ትግራዋይን ፈታዊ ትግራይን፣ ብዝኽእሎ ዓቕሚ ኣብ ዳግመ ህንፀትን ዘላቂ ለውጥን ትግራይ እጃሙ ከወፊ ይግባእ፤ ካብ እምነ-ኹርናዕ ክሳብ ኮረት ከቐብል ትፅቢት ይግበር፤ ኢደይ ኢድካ ኢልና ንዘላቒ ራህዋን ቅሳነትን ህዝብና ብሓባር ንዕሰል።

እዋናዊ ብድሆታትና ክንሰግሮም-ንሕበር!!

ሰላም ንመላእ ህዝብና!!

መለስ ዜናዊን በጨረፍታ----ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ---በኢትዮጵያ ታሪክ ለረጅም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ መለስ ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1/1947 በትግራይ ክልል በአድዋ ከ...
09/05/2023

መለስ ዜናዊን በጨረፍታ
----
ጸሐፊ: አፈንዲ ሙተቂ
---
በኢትዮጵያ ታሪክ ለረጅም ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት አቶ መለስ ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1/1947 በትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ ነው፡፡ መለስ የልደት ስማቸው “ለገሠ ዜናዊ” ነበር፡፡ ተማሪ ለገሠ ዜናዊ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ እንደነበረ ብዙ የተባለለት ጉዳይ ነው። እስከ ስምንተኛ ክፍል የተማረው በአድዋው ንግሥተ ሳባ ትምህርት ቤት ሲሆን የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ (Highschool) ትምህርቱን ደግሞ በጄኔራል ዊንጌት ሁለተኛ ትምህርት ቤት ነው ያጠናቀቀው።

ለገሠ ዜናዊ በ1966 ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከገባ በኋላ በህክምና ፉኩልቲ ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ህክምናን አጥንቷል። የፖለቲካ ተሳትፎውንም የጀመረው በዩኒቨርሲቲው የሚማሩ እና በመንግሥት ስራ የተሰማሩ የትግራይ ተወላጆች በህቡዕ የመሠረቱት "ማኅበር ገስገስቲ ብሄረ ትግራይ" (የትግራይ ብሄር ተራማጆች ማኅበር) አባል በመሆን ነው። የዚሁ ህቡዕ ማኅበር አባል የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በየካቲት 1967 ወደ ደደቢት በረሃ ወርደው የትጥቅ ትግል መጀመራቸው ሲሰማ ተማሪ ለገሠ ዜናዊ በሚያዚያ ወር 1967 ትምህርቱን አቋርጦ ወደ በረሃ ወርዷል።
-----
እንግዲህ የያኔው ተማሪ ለገሠ ዜናዊ “መለስ” በሚለው ስም መጠራት የጀመሩት ለትግል ወደ ደደቢት በረሃ ከገቡ በኋላ ነው፡፡ በወቅቱ እርሳቸው በተቀላቀሉት ተሓሕት (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ) ደንብ መሰረት ለቤተሰብ ደህንነት ሲባል ስምን መቀየር የተለመደ ስለነበረ ነው መለስም ስማቸውን የቀየሩት፡፡ “መለስ” የሚለው ስም በ1967 መጋቢት ወር “ከኤርትራው ጀብሃ ወንበዴዎች ጋር ተባብረህ የአዲስ አበባን ማዘጋጃ ቤት በፈንጂ አጋይተሃል” ተብሎ ከተረሸነው “መለስ ተኽለ” ከተባለው ወጣት ስም የተወሰደ ነው፡፡ እዚህ ገደማ ግን አንድ ነገር ልብ ሊባል ይገባል፡፡

እነ መለስ ዜናዊ የመሰረቱት “ተሓሕት” ለትግራይ ህዝብ በመፋለም ረገድ የመጀመሪያው ድርጅት አይደለም፡፡ ከዚህ ድርጅት በፊት በ1966 መገባደጃ ላይ “ግንባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ” (ግገሓት) የተባለ ድርጅት በትግራይ ተራማጅ ወጣቶች ተመስርቶ ነበር፡፡ ይህ ድርጅት በአብዛኛው በኤርትራው “ጀብሃ” የሚደገፍ ሲሆን እስከ የካቲት 1967 ድረስ በትግራይ ገጠር አካባቢዎች አንዳንድ እንቅስቃሴዎችን አካሂዶ ነበር፡፡ እንደዚሁም ጀብሃ በአዲስ አበባ ባካሄዳቸው የቦምብ ፍንዳታዎች ተሳትፎ እንደነበረው ይነገራል፡፡

በየካቲት 11/1967 የተመሰረተው ተሓሕት ከእርሱ በፊት ከተመሠረተው ግገሓት ጋር ለመዋሀድ ጥያቄ አቅርቦ ነበር ይባላል፡፡ ይሁንና ሁለቱ ድርጅቶች ሊስማሙ አልቻሉም፡፡ በሁለቱ መካከል ለተከሰተው ፍጥጫ ትክክለኛው ምክንያት ምን እንደነበረ መገመት ያስቸግራል፡፡ የተሓሕት አባላት የነበሩት ግገሓት ገበሬውን በማስጨነቅና የሀገሬውን ህዝብ አስገድዶ በመዝረፍ የሽፍታ እንቅስቃሴ ተሳታፊ በመሆኑ ተሓሕት እርምጃ ለመውሰድ እንደተገደደ ይናገራሉ፡፡ ከግገሓት ጋር ቅርበት የነበራቸው ምንጮች ግን "ተሓሕት የትግራይ መሬት ከአንድ ድርጅት በላይ የመሸከም አቅም የለውም" በሚል መሰሪ ዓላማ ተነሳስቶ ድርጅታቸውን እንዳጠፋው ነው የሚገልጹት፡፡ ከሁለቱም ወገን ያልነበሩ ወገኖች ደግሞ ድርጅቶቹ እስከ መጠፋፋት የደረሱት ሻዕቢያ እና ጀብሃ ከጀርባቸው ስለነበሩ ነው ይላሉ፡፡

ያም ሆነ ይህ ግገሓት በትግራይ ምድር ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ መቆየት አልቻለም፡፡ እርሱ ሲጠፋ የትግል ሜዳው ለተሓሕት አመቺ ሆኖለት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡
------
መለስ ዜናዊ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ በድርጅቱ አመራር ውስጥ አልነበረም፡፡ ከርሱ ይልቅ ድርጅቱን ይመሩ የነበሩት እነ አረጋዊ በርሀ (በሪሁ)፣ ፋንታሁን ዘርዓ ጽዮን (ግደይ)፣ መሓሪ ተኽለ (ሙሴ )፣ ዘርዑ ገሠሠ (አግዓዚ)፣ አታኽልቲ ጸሐየ (ኣባይ)፣ እምባዬ መስፍን (ስዩም) እና ወልደሥላሴ ነጋ (ስብሓት) ነበሩ፡፡ የመለስ ዜናዊ ፖለቲካዊ ስብዕና ጎላ ብሎ መታየት የጀመረው በ1969 በድርጅቱ ላይ የመበተን አደጋ በተጋረጠበት (በድርጅቱ ታሪክ “ሕንፍሽፍሽ” ተብሎ በሚጠራው) አስቸጋሪ ወቅት በተለይም የገለልተኝነት ስሜት ከነበራቸው ወጣቶች ጋር በማበር ድርጅቱን ለማትረፍ ብዙ በመልፋታቸው ነው ይባላል፡፡

በወቅቱ መለስ በፖለቲካ ስራዎች ላይ የተመደቡ ኮሚሳር ነው የነበሩት፡፡ አንዳንድ የሕንፍሽፍሽ ንቅናቄ መሪዎች “መለስ ዜናዊ አንድ ውጊያ በማበላሸቱ የሞት ፍርድ ሊፈረድበት ይገባል” የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ቢጽፉም ይህንን ጉዳይ ከነጻ ወገን ለማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ ሆኖም ብዙሃኑ ጸሐፊያን መለስ በወቅቱ ገለልተኛ ነበረ በሚለው ይስማማሉ፡፡
----
በ1971 ድርጅቱ ስያሜውን “ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ” (ሕወሓት) ብሎ ሲቀይር መለስ ዜናዊ የድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሆኑ፡፡ በዚህ ወቅት መለስ የድርጅቱ የፖለቲካ ትምህርት ቤት ኃላፊ በመሆን የካድሬዎችና የፖለቲካ ኮሚሳሮችን ስልጠና በበላይነት ይመሩ ነበር፡፡ ለአቶ መለስ ዜናዊ ይህ ጊዜያቸው ወርቃማ ዘመናቸው ነበረ ለማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ይህ ወቅት ለስልጠና የሚያስፈልጉ ማቴሪያሎችን ለማዘጋጀት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከፕራግማቲክ ታጋይነት ወደ ጥልቅ አንባቢነት የተለወጡበት ጊዜ ስለሆነ ነው፡፡ ይህ ከንባብ ጋር ያዳበሩት ቁርኝታቸው ውጤቱ በ1977 በተካሄደው የድርጅቱ ጉባኤ እና የማሌሊት ንቅናቄ ወቅት በግልጽ ወጥቷል፡፡ በነገራችን ላይ መለስ ዜናዊ ከባለቤታቸው ከአዜብ መስፍን ጋር በፍቅር የወደቁት በዚህ ወቅት ነበር፡፡ ሆኖም በድርጅቱ ደንብ መሰረት በወቅቱ ጋብቻ ቀርቶ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ እንኳ ለከባድ ቅጣት የሚዳርግ በመሆኑ መለስ አዜብን ለማግባት ስድስት ዓመታትን መጠበቅ ነበረባቸው፡፡
----
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1977
መለስ ዜናዊ እጅግ ከፍተኛ እመርታ በማሳየት የድርጅቱ የወደፊት ዐይን መሆናቸውን ያስመሰከሩበት ዓመት ነበር፡፡ በዚህ ወቅት በድርጅቱ ውስጥ ኮሚኒዝምን በሰፊው ማስረጽ ይገባል በሚል እሳቤ አንድ የፓርቲ አስኳል ተመስርቶ ነበር፡፡ ይህም “ማርክሲስት ሌኒኒስት ሊግ ትግራይ” (ማሌሊት) የሚባለው ሲሆን የዚህ እንቅስቃሴ መሪዎች ኣባይ ጸሐየ እና መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፡ ይህ ፓርቲ “ኮሚኒስታዊ ርዕዮት በትክክለኛ መልኩ ወደ ታጋዩ እና ወደ ህዝቡ ካልሰረጸ ትግላችን ውጤታማ አይሆንም፤ ውጤታማ ቢሆን እንኳ አብዮታችን ሊቀለበስ ይችላል የሚል” እይታ ነበረው፡፡ ድርጅቱ በወቅቱ ኮሚኒስታዊ በመሆኑ እነ መለስ ታጋዩን ለማሳመን ብዙም አልቸገራቸውም፡፡ ነገር ግን “እነ መለስ የሚሉት ነገር ጽንሰ ሃሳባዊ እንጂ ፕራግማቲክ አይደለም፤ በተጨባጭ ለመተግበር የማይቻል ጽንሰ- ሃሳብ እያመጣን ታጋዩን ማወዛገቡ ይቅርብን” የሚል ተቃውሞም ተነስቶ ነበር፡፡ የዚህ ተቃውሞ መሪዎችም አረጋዊ በርሀ እና ግደይ ዘርዓ ጽዮን ነበሩ፡፡

ሁለቱ እይታዎች በየፊናቸው ድጋፍ ለማግኘት ሲንቀሳቀሱ በወቅቱ የገለልተኝነት አቋም ያሳዩ የድርጅቱ አመራሮች “ነገሩ ሌላ ውዝግብ ከማምጣቱ በፊት በጉባኤ ይለይለት” የሚል የመፍትሔ ሃሳብ አቀረቡ፡፡ በዚህ መሰረት መለስ ዜናዊ የማሌሊትን አቋም፣ በመወከል ግደይ ዘርዓ ጽዮን ደግሞ የአፍቃሬ-ፕራግማቲክ ጎራውን በመወከል በ600 ጉባኤተኞች ፊት እንዲከራከሩ ተጋበዙ፡፡ (በወቅቱ ክርክሩን በዳኝነት የመሩት አርከበ ዕቁባይ ነበሩ)፡፡

መለስ ዜናዊ እና ግደይ ዘርዓ ጽዮን ለሁለት ሰዓታት ያህል የጦፈ ክርክር አደረጉ፡፡ በመጨረሻ ግን አንደበተ ርቱእ የሆኑት መለስ ዜናዊ ጉባኤተኛውን ወደ ራሳቸው ለመሳብ ቻሉ፡፡ በተለይም ግደይ ዘርዓ ጽዮን “በቀኝ በኩል ካፒታሊዝምንና ኢምፔሪያሊዝምን፤ በግራ በኩል የሶቪየት ከላሽነትን የምትዋጋና የራሷን ሉዓላዊነት በማስከበር ሶሻሊዝምን መገንባት የቻለች አንዲት ሀገር በምሳሌነት ማቅረብ ትችላለህ?” በማለት ላቀረቡት ጥያቄ አቶ መለስ ዜናዊ “እንዴታ! አልባኒያ ጥሩ ምሳሌ ትሆናለች” የሚል ቅጽበታዊ መልስ መስጠታቸው ጉባኤተኛውን በረጅሙ አስጨብጭቦት እንደነበረ ታሪኩን የሚያውቁ ሰዎች በተደጋጋሚ የጻፉት ጉዳይ ነው፡፡

ከዚህ ጉባኤ በኋላ ግደይ ዘርዓ ጽዮን እና አረጋዊ በርሀ በድርጅቱ ውስጥ ብዙም አልቆዩም፡፡ መለስ ዜናዊ ግን የድርጅቱ የፖሊት ቢሮ አባል ሆኖ የተመረጠው በዚህ ጊዜ ነው፡፡
----
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 1981

መለስ ዜናዊ ከፖሊት ቢሮ አባልነት ወደ ድርጅቱ ሊቀመንበርነት ያደጉበት ዓመት ነው፡፡ በዚህም ወቅት ነው ሕወሓት እና ኢህዲን በጥምረት የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የሚባለውን ድርጅት የመሰረቱት፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ከህወሓት ሊቀመንበርነታቸው በተጨማሪ የኢህአዴግ ሊቀመንበርም ሆኑ፡፡ በሚቀጥሉት 23 ዓመታትም በዚሁ ስልጣናቸው ላይ ቆይተዋል፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ ከግንቦት 28/1983 ጀምሮ ኢትዮጵያን በመሪነት አስተዳድረዋል፡፡ ምዕራባዊያን በስልጣን ዘመናቸው ኢትዮጵያን አሳድገዋል እያሉ ያሞካሹአቸዋል፡፡ እነ ኢሰመጉ፣ ሂዩማን ራይትስ ዋች እና አምነስቲ ኢንተርናሽናል ግን በስልጣን ዘመናቸው ለተፈጸሙት ህገ-ወጥ ግድያዎች፣ አፈናዎች፣ እስራቶችና የአካላት መጉደል ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚያደርጉት እርሳቸውንና ድርጅታቸውን ነው፡፡ እነ ሲፒጄ እና Reporters without borders ደግሞ በየጊዜው የፕሬስ ጠላት ሲሉዋቸው ነበር፡፡

አቶ መለስ ዜናዊ በአንባቢነታቸው፣ ነገሮችን ቶሎ በመገንዘብ ብቃታቸው፣ ቅጽበታዊ ዘዴ በመፍጠር ችሎታቸው፣ ከጠላቶቻቸው ፈጥነው እርምጃ በመውሰዳቸው ብዙ ተብሎላቸዋል፡፡ ታዛቢዎች ግን ራሳቸውን ብቻ እየካቡ ድርጅቱን ገድለውታል በማለት ይወቅሷቸዋል፡፡ በእርግጥም በያኔው ኢህአዴግ ውስጥ የመለስ ዜናዊን የፖለቲካ ክህሎት፣ አንደበተ ርቱዕነትና ዘዴ የመፍጠር ችሎታን የተካነ ሌላ ሰው ነበረ ለማለት አይቻልም፡፡ እስከ 2010 በአመራር ላይ ከነበሩት የኢህአዴግ መሪዎች አንዱም እንኳ የመለስ ዜናዊን ያህል ወዝ ያለው ፖለቲከኛ ሆኖ አይታይም፡፡

ይሁንና ለዚህ ክፍተት መፈጠር መለስ ዜናዊን ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ማድረግ ይከብዳል፡፡ ምናልባት ድርጅቱን ለዚህ የዳረገው ከኮሚኒስቶች የተወረሰው “ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት” የሚባለው አሰራር ሊሆን እንደሚችል ይታመናል፡፡ ምክንያቱም ይህ አሰራር ብዙ ጊዜ የፓርቲ መሪዎችን ስብዕና እያጎላ ከነርሱ ህልፈት በኋላ መሪዎቹ የነቢይን ያህል እየገዘፉ የሌሎቹ አስተዋጽኦ ሙሉ በሙሉ እንዲዘነጋ የሚያደርግበት የታሪክ ክስተት ታይቷይልና፡፡ ለምሳሌ የሩሲያው “የሶቪየት ህብረት ኮሚኒስት ፓርቲ” (ቦልሼቪክ) በስልጣን ላይ በነበረበት ዘመን የሁሉም ሶሻሊስት ሀገራት ካድሬዎችና ኮሚሳሮች “ሌኒን እንዳለው” የሚል አባባል ሲደጋግሙ የነበሩበትን ሁኔታ መጥቀስ ይቻላል፡፡
------
ኢትዮጵያዊያን መለስ ዜናዊን በልዩ ልዩ መልኩ ነው የሚያዩዋቸው፡፡ ተቃዋሚዎቻቸው “ኢትዮጵያን ለማጥፋት የተላከ የሰይጣን መልዕክተኛ ነው” ይሏቸዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸው ግን “ለመበታተን የቀረበውን የኢትዮጵያን አንድነት የታደጉና ኢትዮጵያን ያሳደጉ ታላቅ ነቢይ ናቸው” ይላሉ፡፡ ሁለቱም አባባሎች ከእውነታው ዓለም ያፈነገጡ ናቸው፡፡ መለስ ዜናዊ ሰይጣንም ነቢይም አልነበሩም፡፡ እርሳቸው እንደ ሁላችንም ግለሰብ ነበሩ፡፡ ለመሪነት ያበቃቸው ያለፉበት የትግል ሂደት እና የወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ነበር፡፡

መለስ በርግጥ ኢትዮጵያን ከድህነት ለማውጣት በመሰላቸው መንገድ መድከማቸው በትክክል ይታወቃል፡፡ በዚህም ልዩ ልዩ ውጤቶችን ማስመዝገባቸው ተመስክሯል፡፡ በተለይም ኋላቀር የሚባሉት ክልሎች ሰፋፊ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የተወጠነላቸው በርሳቸው ጊዜ ነበር፡፡ መለስ በዲፕሎማሲው መስክም የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ ሚና ለማጉላት ብዙ ሰርተዋል፡፡ የህዳሴ ግድብ የተባለውን ፕሮጀክት በመወጠን ረገድም ከማንም በላይ ሚና የነበራቸው እርሳቸው ናቸው (በነገራችን ላይ “ይህ ግድብ የዐረብ አብዮት ስለተቀጣጠለ በሀገር ቤት ተመሳሳይ አብዮት እንዳይቀሰቀስ ለመከላከል ሲባል የተፈጠረ የአትኩሮት ማስቀየሻ ነው” የሚባለው አነጋገር ትክክል አይደለም፡፡ መለስ የግድቡን ግንባታ በይፋ ከማሳወቃቸው ትንሽ ቀደም ብሎ “ግብጽ ጫካ ሳይኖራት፣ ለጫካ ውጊያ የሰለጠነ ሠራዊት አላት፣ እኛ ያሻቸውን ቢያደርጉ እንኳ በውሃው የመጠቀም መብታችንን እናስከብራለን” በማለት የሰጡት መግለጫ ግንባታው አይቀሬ እንደነበረ የሚያሳውቅ ነው)፡፡

ይሁንና መለስ ዜናዊ ለህዝባቸውና ለወገናቸው ዲሞክራሲና ፍትሕን በማምጣት ረገድ ያን ያህል አልተጓዙም፡፡ ለምሳሌ መለስ በ1997 ጥሩ የተባለ ምርጫ አካሂደው ነበር፡፡ በምርጫው ዙሪያ የተፈጠሩ ውዝግቦችን በሽምግልናና በግልግል መፍታት እየቻሉ የንጹሐንን ደም ያፈሰሰ እርምጃ መውሰዳቸው የታገሉለትን ዓላማ ወደ ኋላ የቀለበሰ ጥቁር ነጥብ ተደርጎ ተቆጥሮባቸዋል፡፡ እንደዚሁም በርሳቸው ዘመን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የኦሮሞ ተወላጆች የኦነግ አባል ነህ በሚል ጥርጣሬ ብቻ ታፍሰው ያለ አንዳች ፍርድ በእስር ቤት መማቀቃቸው መንግስታቸው ከብዙ ኦሮሞዎች ጋር ሆድና ጀርባ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በእርሳቸው ዘመን በርካታ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ያለ ፍርድ ተገድለዋል።

አንድ የማይታበል ሐቅ ግን አለ፡፡ ሰውዬው ችሎታቸውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎለበቱ መምጣታቸውን መካድ አይቻልም፡፡ ለምሳሌ መለስ ዜናዊ ስልጣን በተቆጣጠሩበት ዘመን ስለሚናገሩት ነገር ብዙም አይጨነቁም፡፡ ወደ ኋላ ላይ ግን ይህ አመላቸው በብዙ መልኩ ተቀይሯል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ጣሊያን ላይ በጠፉበት ጊዜ “ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ከምናወጣው ብር ይልቅ ለገበሬዎቻችን የምናደርገው ድጎማ ይበልጥብናል” ያሉት መሪ ወደ መጨረሻው አካባቢ የስፖርት ተቆርቋሪ ሆነው መገኘታቸው የዚሁ ምስክር ነው፡፡

መለስ ዜናዊ የአፍሪቃ ህብረት ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ እንዲወጣ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት እርምጃውን ለማስቀልበስ ያደረጉት ጥረትና የወሰዷቸው እንቅስቃሴዎች ከተቃዋሚዎቻቸው ጭምር ድጋፍ አስገኝቶላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ያለ አንዳች ልዩነት መለስ ዜናዊን ያደነቁበት ንግግር ቢኖር የአዲስ አበባን የአፍሪቃ ህብረት መቀመጫነት ለማረጋገጥ እልህ በተሞላው ስሜት የተናገሩት ያ የሎሜው (ቶጎ) ታሪካዊ ንግግር ነው፡፡ ኢትዮጵያ ደሃ ሆና ሳለ በየጊዜው በጂ-8 ስብሰባ ላይ እየተጋበዙ መገኘታቸውም ከድርጅታቸው ይልቅ የርሳቸውን ፖለቲካዊ ብቃት የሚያሳይ ምልክት ተደርጎ ነው የተወሰደው (እርሳቸው ካረፉ በኋላ የመጡት የኢትዮጵያ መሪዎች በአንድም ወቅት ለG-8 ስበብሳ አለመጋበዛቸውን ልብ በሉ። አሁን ሩሲያ ስለተቀነሰች G-7 ተብለዋል)።

በሌላ በኩል መለስ አላግባብ የሚከሰሱበት ሁኔታም አለ፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተነሳበት ወቅት መለስ ዜናዊ “ጦርነት መዋጋት ሀገራችንን ይጎዳል፤ እኛ ደሃ ነን፤ ካለፈው ጦርነት ለማገገም ብዙ መስራት ይጠበቅብናል። ችግሩን በውይይት እና በድርድር መፍታት ይመረጣል” በማለት የሰነዘሩት ሀሳብ ትክክል ነበር። ይሁን እንጂ በተቃዋሚዎቻቸው ዘንድ “ተንበርካኪነት” ተብሎ ተተርጉሞባቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ የእናታቸውን ትውልደ-ኤርትራዊ መሆን በመጥቀስ “ኤርትራዊ ደም ስላለው ነው እንዲህ የሚለው” በማለት የዘረኝነት ቅስቀሳ አካሂደውባቸዋል፡፡

ያም ሆነ ይህ የኢኮኖሚው ነገር ሲነሳ መለስ ዜናዊ ጥሩ አስተዋጽኦ ኖሮአቸው ይሆናል፡፡ የዲሞክራሲውና የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ሲነሳ ግን ድሮ ያሳዩት ጭላንጭል ሁሉ በመጨረሻ የህይወት ዘመናቸው እየከሰመ ነው የመጣው፡፡ መለስ በ1984 እና በ1997 በተካሄዱት ምርጫዎች ወቅት ለተቃዋሚዎቻቸው ያሳዩትን ሆደ ሰፊነት በህይወታቸው መጨረሻ ገደማ ጠቅልለው ወስደውታል፡፡ የጸረ-ሽብር ህግ እየተጠቀሰ ጋዜጠኞችን ማሰር፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን ማንገላታት፣ በእምነቶች ጣልቃ በመግባት አንዱን ቡድን ደግፎ ሌላውን በአጥፊነት መፈረጅ ወዘተ… በህይወታቸው መጨረሻ ገደማ ገሃድ ሆነው የወጡ የመንግሥታቸው ህጸጾች ነበሩ፡፡

እንዲያም ሆኖ ግን መለስ ዜናዊ በዘመናዊው የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደነበራቸው መካድ አይቻልም፡፡
-----
መለስ ዜናዊ በቀልደኝነታቸውና ተረት በመተረት ችሎታቸውም ይታወቃሉ፡፡ ይህ ቀልደኝነታቸው በርሳቸው ስም የተለያዩ ፈጠራዎች እንዲከሰቱ ምክንያት ሆኖኣል፡፡ እኛም ጽሑፋችንን የምናገባድደው በመለስ ስም የተፈጠሩትን ሁለት ቀልዶች በመጋበዝ ይሆናል፡፡
---
ምርጫ-97 ከተካሄደ ከጥቂት ወራት በኋላ አንዱ ጋዜጠኛ ለአቶ መለስ ዜናዊ እንዲህ የሚል ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡

ጋዜጠኛ፡ “ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር፤ ምርጫው ቲያትር ነበር ይባላል፡፡ በርግጥ ምርጫው ቲያትር ነበር እንዴ?”

መለስ ዜናዊ፡- “ቲያትር አልነበረም፡፡ ደበበ እሸቱ በምርጫው በመሳተፉ ቲያትር የመሰላቸው ካሉ ተሳስተዋል”
----
መለስ ዜናዊ ወደ ቤልጅየም ለጉብኝት ሄደው ነበር፡፡ እዚያ ባደረጉት ስብሰባ ከተጋበዙት ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዷ ሃሳብ ለመስጠት ተነሳች፡፡

ወጣቷ፡- “የርስዎ መንግሥት በጣም አስጠሊታ ነው፤ ስርዓታችሁ አስጠሊታ፤ አካሄዳችሁ አስጠሊታ፤ ባለስልጣኖቻችሁ አስጠሊታ፤ ሁለመናችሁ አስጠሊታ ነው”::

መለስ ዜናዊ፡ -“ጥሩ ነው፤ አስጠሊታ ልንሆን እንችላለን፤ አሁን እዚህ የመጣነው ግን ለቁንጅና ውድድር አይደለም”፡፡
------
ግንቦት 1/2007
በሀረር ከተማ ተጻፈ።
-----
ትክክለኛዎቹ የሶሻል ሚዲያ አድራሻዎቼ የሚከተሉት ናቸው።

= የፌስቡክ ፔጅ (My New page)

https://www.facebook.com/AfendiEthno2018

=> የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel)

https://t.me/afandishaHarar

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=701597695307409&id=100063715553997&mibextid=Nif5oz

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=189557243843584&id=100083679284546&mibextid=Nif5oz
11/04/2023

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=189557243843584&id=100083679284546&mibextid=Nif5oz

==============
ሙሩፅ ይፍጠር “ማርሽ ቐያሪ”
ኣብ 1980 ሞስኮ ኦሎምፒክ ኣብ መበል 40 ዓመቱ ኽልተ ወርቒ ሜዳልያ ንሃገሩ ብምምፃእ ታሪኽ እንዳዘከሮ ዝነብር ህያዊ ትግራዋይ ኣትሌት። 5 ጥቅምቲ 1937ዓ.ም ኣብ ወረዳ ኩሎ መኸዳ ፍሉይ ሽሙ ሓበን (እንበይቶ) ኣብ ዝብሃል ቦታ ዝተወለደ ፍርያት ክልልና ዝኾነ ሻምበል ኣትሌት ምሩፅ ይፍጠር ቅድሚ ናብ ውድድር ኣትሌቲክስ ምእታዉ ኣብዝተወለደሉ ኸባቢ ብሕርሻ ይመሓደሩ ንዝነበሩ ንወላዲ ኣቡኡ ኣይተ ይፍጠር ተኽለሃይማኖትን ንወላዲቱ ኣዲኡ ወይዘሮ ለተገብርኤል ገብረኣረጋዊ ንምሕጋዝ ኣብ ሓደ ፋብሪካ ተቖፂሩ ብምስራሕ ይሕግዞም ነይሩ።

ጐናጐኒ ንስድርኡ እንዳሓገዘ ኣብ ስፖርት ይነጥፍ ዝነበረ ሻምበል ኣትሌት ምሩፅ ይፍጠር ድሕሪዙይ ንውድድር ጉያ ብዝነበሮ ዝለዓለ ፍቕሪ ናብ ኣስመራ ብምኻድ ሽዑ ናብ ዝነበረት ጋንታ ኣትሌቲክስ ሓማሴን ተፀንቢሩ እዩ። ኣብቲ ጊዜቲ ድማ ኣብ ኣስመራ ኣብዝተኻየደ ውድድር ጉያ ፍርቂ ማራቶን ምስ ኣትሌታት ሻምበል ኣበበ በቒላ፣ ማሞ ወልዴን ምስ ኻልኦት ፍሉጣት ኣትሌታት ብምውድዳር ሻድሻይ ደረጃ ብምሓዝ ውድድሩ ዛዚሙ እዩ። ኣብቲ ውድድር ድማ ብቕዓት ኣጎይያ
ምሩፅ ይፍጠር ዝተዓዘበ ሻምበል ኣበበ በቒላ ንዓየይ ክትክእ ይኽእል እዩ ብምባል ሓደ ጥሪ 1961ዓ.ም ናብ ጋንታ ኣትሌቲክስ ሓይሊ ኣየር ንክፅንበር ነገራት ኣጣዓዒምሉ እዩ።

ሻምበል ኣትሌት ምሩፅ ይፍጠር ኣብቲ ጊዜቲ በቢዓመቱ ይካየድ ኣብዝነበሩ ናይ ምክልኻል ሰራዊት ውድድር ብተደጋጋሚ ብምስዓር ኣብ ኢንተርናሽናል ውድድር ንክካፈል ብዝረኸቦ ዕድል ኣብዝተፈላለዩ ውድድራት ውሽጢ ዓድን ወፃኢን ብምስታፍ ዓወታት ካብ ምምዝጋቡ ሓሊፉ ጥንካርኡ ዘመስከረሉ ጊዜ እዩ ነይሩ። ማርሺ ቐያሪ ሻምበል ኣትሌት ምሩፅ ይፍጠር ኣብ ዓለምለኸ ውድድር ንሃገሩ ወኪሉ
ንፈለማ እዋን ኣብ ውድድር ዝተሳተፈ ኣብ 1968ዓ.ም ውድድር ኣሎምፒክ ሜክሲኮ እዩ። ቐፂሉ ኣብ 1972ዓ.ም ኣብ ውድድር ኦሎምፒክ ሙኒክ ተሳቲፉ ብ10ሽሕ ሜትሮ ንሃገርና ሜዳልያ ብሩር ኣምፂኡ እዩ።

በዞም ውፅኢታት ተዓጂቡ ብኣትሌቲክስ ንቅድሚት ዝተጉዓዘ ሻምበል ኣትሌት ምሩፅ ይፍጠር ኣብ 1973 ኣብ ናይጀሪያ ሌጎስ ኣብዝተኻየደ ኻልኣይ መላእ ፀዋታታት ስፖርት ኣፍሪካ፣ ብ10ሽሕ ሜትሮ ሜዳልያ ወርቒ ብ5ሽሕ ሜትሮ ሜዳልያ ብሩር ኣብ 1979ዓ.ም ኣብ ሴኔጋል ዳካር ኣብዝተኻየደ ፈላማይ ሻምፒዮና ኣትሌቲክስ ኣፍሪካ ብ10ተን ብ5ተን ሽሕ ሜትሮ ሜዳልያታታት ወርቒ፣ ኣብ 1977 ኣብ ምዕራብ ጀርመን ኣብዝተኻየደ ፈላማይ ሻምፒዮና ኣትሌቲክስ ዓለም ብ5ተን 10ተን ሽሕ ሜትሮ ወርቒ ሜዳልያ፣ ኣብ 1979 ኣብ ካናዳ ሞንትሪያል ኣብዝተኻየደ ኻልኣይ ሻምፒዮና ኣትሌቲክስ ዓለም ብ10ተን 5ተን ሽሕ ሜትሮ ወርቒ ሜዳልያ ካብዚ ብተወሳኺ ኣብ 1980 ኣብ መበል 22
ውድድር ኦሎምፒክ ሞስኮ ብ10ተን 5ተን ሽሕ ሜትሮ ወርቒ ሜዳልያ ዝረኸበ ኾይኑ ካብቶም ፍሉያት መለለይኡ ድማ ንሃገሩን ንኣፍሪካን ኣብ ሓደ ውድድር ኦሎምፒክ ኽልተ ወርቒ ሜዳልያ ዘምፅኣ ፈላማይ ኣትሌት እዩ።

ውድድር ጉያ ካብዘቋረፀሉ ጊዜ ጀሚሩ ቴክኒካል ሓላፍነት ነዊሕ ርሕቐት ብደረጃ ሕርይቲ ጋንታ ኣትሌቲክስ ኢትዮጵያ ዝለዓለ ውፅኢት ኣመዝጊቡ እዩ። ድሕሪዙይ ኣብ ዕረፍቲ ዝፀንሐ ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ኣብ ምስትንፋስ ብዘጋጠሞ ፀገም ኣብ ካናዳ ቶሮንቶ ሕክምና ክወስድ ድሕሪ ምፅናሕ ኣብ መበል 72 ዓመቱ 14 ታሕሳስ 2009ዓ.ም ካብዛ
ዓለም ብሞት ተፈልዩ። ይኹን እምበር ታሪኽን ጂግንነትን ዘልኣለም እናተዘከረ ነባሪ እዩ።

ንዕቤት👉 ኣትሌትክስ ትግራይ 🔥

🎯 ኣይትረስዑ !!♥
➖➖ ➖➖➖➖ ➖➖➖➖ ➖

21/03/2023
እዚኣ ጋቢዘኩም ኣለኹ
04/03/2023

እዚኣ ጋቢዘኩም ኣለኹ

Goytom Hailemariam ( ጎይትኦም ሃይለማርያም ) - ንዓ ሙሴ ( Nea Mussie) New Tigrigna Music 2022 (Official Video)SUBSCRIBE 👇👇👇👇https://www.youtube.com/c/HOHOMAENTERTA...

https://www.facebook.com/1490190331223441/posts/3426248227617632/?mibextid=Nif5oz
27/02/2023

https://www.facebook.com/1490190331223441/posts/3426248227617632/?mibextid=Nif5oz

ወደ መቀሌ እና ሽሬ በሚደረጉ በረራዎች ከታሪፍ በላይ በማስከፈል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው

የካቲት 20/2015 (ኢዜአ) ወደ መቀሌ እና ሽሬ በሚደረጉት በረራዎች ከታሪፍ በላይ በማስከፈል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን ተጠያቂ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ እና ሽሬ በሚያደርጋቸው በረራዎች በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ተመድበው የሚሠሩ አንዳንድ ባለሙያዎችና ከአየር መንገዱ ጋር የሚሠሩ ኤጀንቶች ጉዳይ እናስፈጽማለን ከሚሉ ግለሰቦች ጋር ተመሳጥረው ከተቀመጠው የክፍያ ታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ ስለተደረሰባቸው ተጠያቂ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ከታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉና ኅብረተሰቡን ለእንግልት ሲዳርጉ የተደረሰባቸው በሙሉ ጉዳያቸው ተጣርቶ ተጠያቂ የማድረግ ሥራ በጋራ እየተሠራ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ወቅት በቀን ወደ መቀሌ የሚደረገው የበረራ ቁጥር ወደ አምስት ማደጉን እንዲሁም ወደ ሽሬ የሚደረገው በረራም በሳምንት ወደ ዘጠኝ ከፍ ማለቱን የጠቆመው መግለጫው፤ አስፈላጊው የሰው ኃይል በየበረራ መዳረሻው ተመድቦም ደኅንነቱ በተረጋገጠ ሁኔታ ተጓዦች በቂ አገልግሎት እንዲያገኙ በቁርጠኝነት እየተሠራ መሆኑንም አመልክቷል፡፡

ሆኖም በርካታ ሰዎች የአየር ትራንስፖርት የመጠቀም ፍላጎታቸው መጨመሩን እንደመልካም አጋጣሚ የወሰዱት በአዲስ አበባ እና በመቀሌ የተመደቡ ሙያዊ ሥነ-ምግባር የጎደላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንዳንድ ሠራተኞችና ከአየር መንገዱ ጋር የሚሠሩ ኤጀንቶች ከጥቅም ተጋሪ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር ከተቀመጠው የክፍያ ታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ እንደነበር ተደርሶበታል፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የኢትዮያ አየር መንገድ በጉዳዩ ዙሪያ ክትትል ሲያደርጉ ቆይተው በድርጊቱ ሲሳተፉ የነበሩ አራት ግለሰቦች በመለየታቸው እጅ ከፍንጅ ተይዘው ጉዳያቸው መቀሌ ፖሊስ ጣቢያ በምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ መግለጫው አስታውቋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሢሠሩ የነበሩ አምስት ኤጀንቶች ከሥራ ታግደው ጉዳያቸው እየተጣራ ሲሆን፤ ሌሎች በጉዳዩ የተሳተፉ አካላትን በመለየት እርምጃዎች ለመውሰድ መረጃዎችን የማጠናቀር ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክቷል፡፡

ኅብረተሰቡ በሕጋዊ አሠራር እና ይህንኑ ለማከናወን ከተደራጀ ቢሮ ብቻ ቀርቦ ትኬቱን በመቁረጥ በተቀመጠው የተቋሙ ታሪፍ ብቻ አገልግሎት ማግኘት የሚችል መሆኑን ያመለከተው መግለጫው፤ ባልተገባ መንገድ በሕገ-ወጦች ተታሎ እላፊ ገንዘብ እንዳይከፍልና እንዳይጭበረበር መጠንቀቅ እንዳለበት አስገንዝቧል።

ከዚህ ውጭ ኅብረተሰቡ በማንኛውም ሁኔታ ለማጭበርበር የሚሞክሩ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት በአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታ እና የደኅንነት አካላት መረጃ በመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ያቀረበው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፤ በተቋሙ ነፃ የስልክ መስመር 910 ጥቆማ መስጠት እንደሚቻልም ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መረጃ አመልክቷል።

Address

Bole
Addis Ababa
251

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሎሚ ሚድያ/Lomi Media/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category