Asham TV

Asham TV Asham TV is a privately owned media company, based in Addis Ababa, Ethiopia, that provides news and other programs
(11)

18/04/2024

ዛሬ ምሽት ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአሻም ዜና

- የአውሮፓ ህብረት ለሶማልያ ያደረገው የገንዘብ ድጋፍ ሃያላን ሃገራቱ በቀጠናው ላይ ላደረባቸው ስጋት ማሳያ መሆኑ ተገልፆዋል፡፡ በዝርዝር እንመለከተዋለን፡፡

- በቦይንግ ኩባንያ ይሰሩ የነበሩ መረጃ ጠላፊዎች አሁንም ድረስ በቦይንግ 787 ድሪምላይነር አውሮፕላኖች ላይ የደህንነት ጉድለት እንዳለባቸው ምስክርነታቸውን በአሜሪካ በካፒቶል ለሴናተሮች ሰጥተዋል፡፡ ሌላኛው ርዕሰ ጉዳያችን ነው፡፡

- የተባበሩት አረብ ኢሜሬተስ ዱባይ፤ ጎርፍን ለመከላከል በቂ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርአት የላትም ተብሏል፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል።

አሻም ኢትዮጵያችን !!!

Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

ለሰሞንኛው ግጭት የተላለፉ መልዕክቶች,
17/04/2024

ለሰሞንኛው ግጭት የተላለፉ መልዕክቶች,

ለሰሞንኛው ግጭት የተላለፉ መልዕክቶችሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴሌቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝታልች፡፡ አሻም ሰባት እን....

17/04/2024

ዛሬ ምሽት ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በአሻም ዜና

- በአማራ ክልልም ሆነ በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚነሱ የማንነት ጥያቄዎች በህገ-መንግስቱ ሊታዩ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

- በራያ አላማጣና አካባቢው ያለውን ግጭት ለመፍታት የፌደራሉ መንግስት ዝምታውን መስበር እንደሚገባው ተመላከተ፡፡
በሰሞንኛው ግጭት ዙሪያ ሁለት የፖለቲካ ሳይንስ አዋቂዎች ለአሻም ምልከታቸውን አጋርተዋል፡፡

- የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ግዛት ጥሶ ወረራ ቢፈጽምም የፌደራሉ መንግስት ትኩረት አልሰጠውም ሲሉ የዛላምበሳ ከተማ ከንቲባ ለአሻም ተናግረዋል፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል።

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

16/04/2024

ዛሬ ምሽት ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በአሻም ዜና

- የፌደራል መንግስቱ በህግና በስርዓት በአወዛጋቢ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን እልባት እንዲሰጥ የደቡባዊ ትግራይ አስተዳደር ጠየቀ፡፡

- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን በራያ አላማጣ አካባቢዎች የተከተውን ግጭት በተመለከተ የመንግስታቸውን አቋም አንፀባረቁ፡፡

- እስራዔል በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት የማስፋፋት ፍላጎት እንደሌላት በኢትዮጵያ የእስራዔል አምባሳደር ለአሻም ተናገሩ፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል።

አሻም ለኢትዮጵያችን !!!

‹‹ ሸኔ ወለጋ እንጂ ሸዋሮቢት የለም ››
15/04/2024

‹‹ ሸኔ ወለጋ እንጂ ሸዋሮቢት የለም ››

‹‹ ሸኔ ወለጋ እንጂ ሸዋሮቢት የለም ››ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴሌቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝታልች፡፡ አሻም ሰባት እ....

15/04/2024

ዛሬ ምሽት ሚያዚያ 7 ቀን 2016 ዓም በአሻም ዜና

- ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በአዋሽ አርባ በእስር ላይ የሚገኙ የህዳር 30 ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች አካልን ነጻ የማዉጣት ክስ መመስረታቸዉን መጋቢ ብሉይ አብርሃም ኃይማኖት ለአሻም ተናግረዋል፡፡ አካልን ነጻ የማዉጣት ክሱ የተመሰረተላቸዉ ግለሰቦችንም በዝርዝር ጠቅሰዋል፡፡ ምሽት በዜና ሰዓታችን ጠብቁን፡፡

- በሸዋሮቢት ዙሪያ የቀወት ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢዉ በሚቀሳቀስ ታጣቂ ቡድን ለድጋሚ ጥቃት እንጋለጣለን በሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸዉ ተናግረዋል፡፡

- የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ(ኢሰመጉ) በሶስት ክልሎች የሕይወት እና የአካል ደህንነት መብቶች ላይ ተፈጽመዋል ያለቸውን ጥሠቶች የተመለከተ ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል።

አሻም ለኢትዮጵያችን !!!

ፋቡላ ባር በዚህ ሳምንት
12/04/2024

ፋቡላ ባር በዚህ ሳምንት

ቴአትርን ያላካተተ ልማት ምን ፈጠረ ? ክፉል 1 አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ ፤ እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየታችሁን አካፍሉን፤ ላይክ...

አቶ በቴ ኡርጌሳ ከመገደላቸው አንድ ወር በፊት ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ
11/04/2024

አቶ በቴ ኡርጌሳ ከመገደላቸው አንድ ወር በፊት ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ

" አቶ በቴ ኡርጌሳ ከመገደላቸው አንድ ወር በፊት ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉት ቆይታ "አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ ፤ እንዲሁም ሃሳብ....

11/04/2024

ዛሬ ምሽት በአሻም ዜና

1. የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ዘርፍ ኦፊሰር በቴ ኡርጌሳ ግድያ በኢትዮጵያ ካለው የፖለቲካ ምህዳር ጋር ተያይዞ እያነጋገረ ነው፡፡ ምን አዲስ ነገር ይኖር ይሆን በምሽት የዜና ስዓታችን ጠብቁን!!

- የተባበሩት መንግስታት ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሚጠብቅ የህግ ማእቀፍ እድታወጣ ሲጠይቅ በዚህ ጉዳይ ላይ ምለከታቸውን ለአሻም ያጋሩ የሕግ በላሞያ ድግሞ ሀገሪቱ ተግባራዊ የማድረግ እንጂ የሕግ ማእቀፍ ችግር የለባትም ሲሉ ሞግተዋል፡፡ ሌላኛው ጉዳያችን ነው።

- ከሁለት የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት በስተቀር በሁሉም ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ለተለያዩ ጥቃቶች የተጋለጡ መሆናቸዉ ተነግሯል፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዙህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ። ኢድ ሙባረክ! እሻም አሻም!
10/04/2024

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን፣

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

ኢድ ሙባረክ!

እሻም አሻም!

> የህግ ባለሙያዎች ወደ አዋሽ አርባ ተወሰዱ።አሻም ዜና | ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ምለህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም > በሚል በአዲስ አበባና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተጠራው ሰላማ...
09/04/2024

> የህግ ባለሙያዎች ወደ አዋሽ አርባ ተወሰዱ።

አሻም ዜና | ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

ለህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም > በሚል በአዲስ አበባና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች ትናንት ሌሊት 7:00 ወደ አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ መወሰዳቸውን አሻም ከታማኝ ምንጮቿ አረጋግጣለች።

እነርሱም የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ) ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ፣ የህግ ባለሙያና ጠበቆች አበራ ንጉስ፣ ዮሴፍ ተሻገር፣ እዮብ ገ/ሥላሴ ናቸው።

የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ከነበሩት ውስጥ የኢህአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አብርሃም ሐይማኖት፣ የትንሳዔ ሰባ እንደርታ ፓርቲ(ትሰእፓ) ምክትል ሊቀመንበር ጊደና መድህን አራት ወራት ከተጠጋ እስር የተፈቱት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ነበር።

ሁለቱ አስተባባሪዎች ቢፈቱም፣ ሌሎቹ የሰልፉ አስተባባሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን እነኚሁ የአሻም ምንጮች ገልፀዋል።

ከፖለቲከኞቹ ባሻገር የህግ ባለሙያዎቹና ጠበቃዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድን ጨምሮ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ላይ ከሰላማዊ ሰልፉ ጎን ለጎን ክስ መስርተው እንደበነበር መዘገቡ ይታወሳል።

ይህ ዘገባ አስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ከመንግስት በኩል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ አልያም ማስተባባያን አሻም አልተመለከተችም።

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

09/04/2024

ዛሬ ምሽት ሚያዝያ 1 ቀን 2016 ዓም. በአሻም ዜና

- በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ከ31 ሰዎች በላይ መሞታቸው ነዋሪዎች ተናገሩ። በዝርዝር መረጃውን እናደርሳቹሀለን።

- በአማራ ክልል የተፈጸመዉ የሽብር ተግባር መሆኑን አረጋግጫለሁ ያለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሙስሊሞችን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን በጽኑ አወግዛለዉ ሲል አስታውቋል፡፡ ሌላኛው ጉዳያችን ነው።

- የመቀሌ ዩኒቨርስቲ ከሰሞኑ የመመረቂያ ጊዜያችን ረዘመብን ያሉ ተማሪዎች ቅሬታ ከዩኒቨርስቲዉ ቅጥር ግቢ ዉጭ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ምን እንደተፈጠረ አሻም ያጠናቀረችው መረጃም አካተናል። በዝርዝር እንመለከተዋለን፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዚህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል።

አሻም ለኢትዮጵያችን !!!

Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

08/04/2024

ዛሬ ምሽት መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአሻም ዜና

- ለመንግስት የድጋፍ ሰልፍ ካልወጣችሁ ቅጣት አለዉ በሚል ማስፈራሪና ግዳጅ ሰልፍ እንድንወጣ ተደርጓል ሲሉ የገንደዉሀ ከተማ ነዋሪዎች ቅሬታ አሰምተዋል፡፡ በዓብይ ርዕሰ ጉዳይ የምንመለከተው ይሆናል፡፡

- የፓርቲው ሊቀ መንበር ካልተፈታ ራሱን ከሃገራዊ ምክክር ሂደቱ እንደሚያገል የኢትዮጵያ ህዝባዊ አቢዎታዊ ፓርቲ አስታወቀ፡፡ በዝርዝር ጠብቁን

- በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት ለ17 ወራት ተቋርጦ የነበረው የጡረተኞች ክፍያ በክልሉ ክፍያ እየተከናወነ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዙህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል::

አሻም ለኢትዮጵያችን !!!

Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

‹‹ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ ከእስር ካልተፈቱ ራሴን ከሀገራዊ ምክክሩ አገላለሁ ›› - ኢህአፓአሻም ዜና | መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ምይህን ለአሻም የተናገሩት የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊ...
08/04/2024

‹‹ ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ ከእስር ካልተፈቱ ራሴን ከሀገራዊ ምክክሩ አገላለሁ ›› - ኢህአፓ

አሻም ዜና | መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ይህን ለአሻም የተናገሩት የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አብርሀም ኃይማኖት ሲሆኑ ‹‹ በትጥቅ የታገዘ ግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ወደ ሰላማዊ ትግል ይምጡ እየተባለ ሰላማዊ ሰዎች መታፈን የለባቸውም ›› ብለዋል፡፡
ሊቀመንበሩ በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል ከሚያደርጉት የፋኖ ኃይሎችን በፌስቡክ ገፃቸው ደግፈው ጽፍዋል በሚል እንደተጠረጠሩ አሻም በታሰሩበት ወቅት መዘገቧ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ(ኢህአፓ) ሊቀመንበር ዝናቡ አበራ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀጠሮ ቢኖራቸውም ፖሊስ ‹‹ በወቅታዊ ጉዳዮች ›› በሚል እንዳላቀረባቸው አብርሃም ለአሻም ነግረዋታል፡፡

የእርሳቸውን የእስር ጊዜ አስታውሰው የሚናገሩት ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበሩ ሰላማዊ ትግል በማካሄድ ላይ የነበሩትን ሊቀመንበራቸውን በማሰር እና ካሁን ቀደም ከፋኖ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ችሎት ያቀረቧቸው ቢሆንም የችሎቱን አዝማሚያ ገምግመው ምን አልባትም በዋስ ይፈታም በሚል ግምት ዛሬ ሳያቀርቧቸው ቀርተዋል ብለዋል፡፡

በሊቀመንበራቸው ላይ አላግባብ ሲሉ የጠሩትን እስር ፓርቲው በቀላሉ የሚመለከተው አይደልም ብለዋል፡፡ ሊቀመንበሩ አግባብ ባልሆነ መንገድ ‹‹ ታፍነው ›› መቆየት እንደማይችሉ ጠቅሰው ሊቀመንበሩ ከዛሬ አንስቶ የረሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የሊቀመንበሩ የረሃብ አድማ ላይ መሆን ለፓርቲውና ለአባላቱ ታላቅ ሀዘን መፍጠሩንም አክለው ገልጸዋል፡፡ እንደ ኢህአፓ ደግሞ ‹‹ ሊቀመንበራቸው በአጭር ቀናት ውስጥ የማይፈቱ ከሆነ ሀገራዊ ምክክር ከሚባለው ሂደት ራሳቸውን ሊያገሉ መዘጋጀታቸውን ›› ጠቅሰው አስጠንቅቀዋል፡፡

‹‹ ሀገራዊ ምክክሩ በእርግጥም ለሀገር መመካከር የሚሰራ ከሆነ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን እያፈኑ በትጥቅ የታገዘ ትግል ያሉ አካላትን ኑ ላመካክራችሁ ማለት አግባብነት ያለው አይሆንም ›› ብለዋል፡፡

‹‹ ሀገሪቷ መከራ ውስጥ በገባችበት በዚህ ወቅት በሀሰትና መሰል እንጀላዎች ሰላዊ ሰዎችን እና ታጋዮችን ማፈን ሀገር ያፈርስና ወደ ለየት ብጥብጥ ይከት ካልሆነ በቀር መፍትሄ እንደማይሆንም ›› ተናግረዋል፡፡

መሠረት ነቃ

(በምሽቱ የዜና አወጃችን ዝርዝር ዘገባውን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን)

አሻም ለኢትዮጵያችን !!!
Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

04/04/2024

ዛሬ ምሽት በአሻም ዜና

- በአማራ ክልል አንዳንድ ከተሞች የተሻለ ሰላምና ጸጥታ ቢኖርም ስጋቶች ግን አለመቀረፋቸዉን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ አልፎ አልፌ የሚከሰቱ የተኩስ ድምጽ፣ዝርፊያ፣ ድብደባና ግድያዎች ህብረተሰቡ ከደህንነት ስጋት እንዳይላቀቅ አድርገዉታል ሲሉ አስተያታቸዉን ለአሻም የሰጡ ነዎሪዎች ተናግረዋል፡፡ ምሽት በዜና ስዓታችን ጠብቁን፡፡

- የመንግስታቱ ድርጅት በአማራ ክልል የሚደርሰውን በደል በገለልተኛ አካል የማጣራት ስራ እንዲጀምርና የኢትዮጵያ ሃይል ከሰላም ማስከበር ስራ እንዲታገድ ሂዩማን ራይትስዎች ጠየቀ፡፡ በዝርዝር እንመለከተዋለን።

- የዶንጋ ህዝቦች ዲሞራሲያዊ ፓርቲ አባሎቼ ያለአግባብ ታስረውብኛል ሲል ቅሬታውን ለአሻም አሰምቷል፡፡ ሌላኛው ጉዳያችን ነው።

ምሽት 1፡30 ላይ ቀጠሯችሁን ከአሻም ቴሌቬዥን ጋር ካደረጋችሁ እነዙህንና ሌሎች ጉዳዮች የምትከታተሉ ይሆናል::

አሻም ለኢትዮጵያችን!!!

Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

በአምስት ዓመት 5ሺህ ግጭት የተከተሰባት ኢትዮጵያ
02/04/2024

በአምስት ዓመት 5ሺህ ግጭት የተከተሰባት ኢትዮጵያ

በአምስት ዓመት 5ሺህ ግጭት የተከተሰባት ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴሌቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝታልች፡፡ አሻ.....

ጋዜጠኞችና መገናኛ ብዙሃን ስድስት ዓመታቱን እንዴት ከረሙ?
02/04/2024

ጋዜጠኞችና መገናኛ ብዙሃን ስድስት ዓመታቱን እንዴት ከረሙ?

ጋዜጠኞችና መገናኛ ብዙሃን ስድስት ዓመታቱን እንዴት ከረሙ? ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴሌቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝታል.....

02/04/2024

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) በእንደራሴዎች ምክር ቤት ቃለ መሃላ ከፈፀሙ ስድስት ዓመታት ተቆጠሩ፡፡

አሻም ቲቪ | ጥቆማ | መጋቢት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

የቀድሞው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ሊቀመንበር የአሁኑ ብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ልክ የዛሬ ስድስት ዓመት በወርሃ መጋቢት በ24ኛው ቀን በ2010 ዓ.ም በዕለተ ሰኞ ነበር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን በእንደራሴዎች ምክር ቤት ቃለ መሃላ የፈፀሙት፡፡

ወደ 36 ደቂቃ ገደማ በወሰደው በዚያ ንግግራቸው በርካታ ቃልኪዳኖችን ገብተዋል፡፡ ስላለፈው ጊዜም ይቅርታም ጠይቀዋል፡፡

አሻም ይህን ንግግራቸውን መነሻ በማድረግ ሰፋፊ ጥንቅሮችን አሰናድታለች፡፡

በዋናነት፡- የፖለቲካ ሁኔታ ክራሞት፣ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ ጦርነትና ግጭቶች፣ የመገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ነፃነት … በጥልቀት ተዳስሰዋል፡፡

ዛሬ ምሽት በአሻም የምሽት የዜና እወጃችን ቅደመ ተከተላቸውን ጠብቀው ይስተናገዳሉ፡፡

የምሽት 1፡30 ቀጠሯችሁ ከአሻም ቲቪ ጋር እንዲሆን ከወዲሁ እንጋብዛለን፡፡

አሻም ለኢትዮጵያችን !!!

Facebook -https://www.facebook.com/AshamMedia
Youtube. - https://www.youtube.com/channel/UCNhqoLI39f7u5Bb6Fe60ECQ...
Telegram - https://t.me/Asham_TV
Twitter. - https://twitter.com/tv_asham
Get The Latest Brand New Ethiopian Entertainment Videos by Subscribing

01/04/2024

የምክክር ኮሚሽኑ ለመንግስት ያቀረበው ጥሪ | የአሻም ዜና - Asham News

የአዲስ አበባ አካባቢዎች ስያሜ ለውጥ   TV @አሻም ቲቪ
01/04/2024

የአዲስ አበባ አካባቢዎች ስያሜ ለውጥ TV @አሻም ቲቪ

የአዲስ አበባ አካባቢዎች ስያሜ ለውጥ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴሌቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝታልች፡፡ አሻም ሰባት እን.....

የአባይ ግድብ 5 ቢሊዮን ብር ይቀራል ።
01/04/2024

የአባይ ግድብ 5 ቢሊዮን ብር ይቀራል ።

የአባይ ግድብ 5 ቢሊዮን ብር ይቀራል አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ ፤ እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየታችሁን አካፍሉን፤ ላይክ፣ ሼር፣ ....

በደርግ ስርዓት መንግስት ጊዜ ኪነ-ጥበብን እንዴት ይጠቀሙ ነበር?
31/03/2024

በደርግ ስርዓት መንግስት ጊዜ ኪነ-ጥበብን እንዴት ይጠቀሙ ነበር?

አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ ፤ እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየታችሁን አካፍሉን፤ ላይክ፣ ሼር፣ ሰብስክራይብ አድርጉን፤ በተቀመጡት...

"የቁም እስረኛ  ሆኛለሁ "
30/03/2024

"የቁም እስረኛ ሆኛለሁ "

አዳዲስ መረጃዎችና የአሻም ቲቪ ዝግጅቶች እንዲደርሱዎት የአሻም ቤተሰብን ይቀላቀሉ ፤ እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየታችሁን አካፍሉን፤ ላይክ፣ ሼር፣ ሰብስክራይብ አድርጉን፤ በተቀመጡት...

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል | የአሻም  ዜና - Asham News
29/03/2024

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል | የአሻም ዜና - Asham News

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል | የአሻም ዜና - Asham Newsሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴላቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝታልች፡፡ አሻ.....

‹‹ የጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የለንም ››   | የአሻም  ዜና - Asham News
29/03/2024

‹‹ የጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የለንም ›› | የአሻም ዜና - Asham News

‹‹ የጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የለንም ›› | የአሻም ሰባት ዜና - Asham Newsሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴላቪዥን ከፍተኛ ተቀ.....

የአሻም ሰባት ዜና መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም
29/03/2024

የአሻም ሰባት ዜና መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

‹‹ ገዢው ፓርቲ የሚያስርበት አሰራር ፍፁም አምባገነናዊነት ነው ›› | የአሻም ሰባት ዜና - Asham Newsሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴ.....

በድሬዳዋ የተፈጠረው ምንድን ነው?  | የአሻም  ዜና - Asham News
28/03/2024

በድሬዳዋ የተፈጠረው ምንድን ነው? | የአሻም ዜና - Asham News

በድሬዳዋ የተፈጠረው ምንድን ነው? | የአሻም ዜና - Asham Newsሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴላቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝታልች፡፡ ...

‹‹ የአብን መግለጫ አይወክለንም ›› | የአሻም  ዜና - Asham News
28/03/2024

‹‹ የአብን መግለጫ አይወክለንም ›› | የአሻም ዜና - Asham News

‹‹ የአብን መግለጫ አይወክለንም ›› | የአሻም ሰባት ዜና - Asham Newsሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ጉዲዮችን በትኩሱ ለተመልካች በማድረስ አሻም ቴላቪዥን ከፍተኛ ተቀባይነት አግኝ...

Address

Dembel, Bole, አዲስ አበባ
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 14:30
Saturday 08:30 - 00:00

Telephone

+251902484020

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asham TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Asham TV:

Videos

Share

Category

Nearby media companies