Ethiopian Verified News

Ethiopian Verified News We bring you information from verified sources
(2)

ህወሓት የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ወነጀለበፖለቲካዊ አቋማቸው በአባላቶቼ ላይ ከሓላፊነት የማንሳት፣ የማገድና የማሰር እርምጃዎች በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እየተወሰደባቸው ነው ሲል ህወሓት...
09/09/2024

ህወሓት የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ወነጀለ

በፖለቲካዊ አቋማቸው በአባላቶቼ ላይ ከሓላፊነት የማንሳት፣ የማገድና የማሰር እርምጃዎች በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እየተወሰደባቸው ነው ሲል ህወሓት ከሰሰ። የህወሓት ከፍተኛ አመራር የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር እርምጃዎች ሕገወጥ ሲሉ ገልፀዋቸዋል። በሌላ በኩል የህወሓት አባላት እና አመራሮች በሽረ ልያካሂዱት የነበረ የተቃውሞ ሰልፍ ተከልክሏል። (DW Amharic)

  አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል።ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋ...
07/09/2024



አቶ ጌታቸው ረዳ የጤና አክል ገጥሟቸዋል።

ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ ጳጉሜን 2/2016 ዓ.ም የወጣ መግለጫ እንዳመለከተው ፥ ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት ተሰርዟል።

ፅ/ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ሳይካሄድ በመቅረቱ ይቅርታ ጠይቋል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ያጋጠማቸው የጤና እክል ቀላል ይሁን ከባድ በመግለጫው የተጠቀሰ የለም ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

ከሰሞኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የአመራሮች ቡድን በየከተማው ህዝባዊ ምክክር እያደረገ እንደነበር ይታወቃል።

በቡኖ በዴሌ ዞን በበደሌ ወረዳ ሃሮ ጋፋሬ መንደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ። አደጋው የደረሰው ቆሎ ሲሪቲ  መንደር አከባቢ ሲሆን ወደ በደሌ ከተማ ይጏዝ የነበረ ተሳ...
07/09/2024

በቡኖ በዴሌ ዞን በበደሌ ወረዳ ሃሮ ጋፋሬ መንደር በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አደጋው የደረሰው ቆሎ ሲሪቲ መንደር አከባቢ ሲሆን ወደ በደሌ ከተማ ይጏዝ የነበረ ተሳፋሪዎችን የጫነ አይሱዙ (3AA-A22886) መኪና ተገልብጦ ነበር። አደጋው በጭነት መኪና ወደ ገበያ በሚሄዱ ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሱን አቶ ቶላሳን ተናግረዋል። (OBN)

 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል።የዘንድሮው ብሔራዊ ...
06/09/2024



የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል።

የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

የተባበሩት መንግሥታት በሱዳን ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ኃይል እንዲሰማራ ጠየቀየተባበሩት መንግሥት የባለሙያዎች ቡድን ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ባለባት ሱዳን “ገለልተኛ ኃይል” እንዲሰማራ ...
06/09/2024

የተባበሩት መንግሥታት በሱዳን ገለልተኛ ዓለም አቀፍ ኃይል እንዲሰማራ ጠየቀ

የተባበሩት መንግሥት የባለሙያዎች ቡድን ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እየደረሰ ባለባት ሱዳን “ገለልተኛ ኃይል” እንዲሰማራ ጠየቀ።

የባለሙያ ቡድኑ የሱዳን ተዋጊ ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን መጠበቅ አልቻሉም ብሏል።

17 ወራት ያስቆጠረው የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችን ሕይወትን ከመቅጠፉ በተጨማሪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን በማፈናቀል በአገሪቱ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ አድርሷል።

የሱዳን ጦርነት የተጀመረው በአገሪቱ ጦር አዛዥ ጄኔራል አብድል ፋታህ አል ቡሩሃን እና በፈጥኖ ደራሹ ኃይል መሪ ጄኔራል ሞሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሜቲ) መካከል ሱዳን እንዴት ትመራ በሚለው ላይ መግባባት ሳይደረስ ከቀረ በኋላ ነው።

ይህ ጦርነት በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እያደረሰ ስለመሆኑ በሰብዓዊ መብት ቡድኖች ሲገለጽ ቆይቷል።BBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ህወሓት  #የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት እንደማልደግፍ ተደርጎ ስም ማጥፋት እየተካሄደብኝ ነው ሲል ገለጸ “የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት እንደማልደግፍ ተደርጎ በመነገር ላይ ያለው ሀሳብ ...
06/09/2024

ህወሓት #የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት እንደማልደግፍ ተደርጎ ስም ማጥፋት እየተካሄደብኝ ነው ሲል ገለጸ

“የፕሪቶርያውን የሰላም ስምምነት እንደማልደግፍ ተደርጎ በመነገር ላይ ያለው ሀሳብ ሀሰት ነው፣ ስም ማጥፋት ነው” ሲሉ #ህወሓትን በመወከል በፕሪቶርያ ተደራዳሪ የነበሩት እና በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው የህወሓት ቡድን ውስጥ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ፍስሃ ሃፍተፅዮን (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፕሪቶርያው ስምምነት በተፈረመበት ወቅት “ትግራይን ወክለው በተሳተፉ ተወካዮች መካከል ከፍተኛ ልዩነት” እንደነበረ ያወሱት ስራ አስፈጻሚው “በወቅቱ ሁሉም ተስማምቶ ስምምነቱ መፈረሙ አንድ ጸጋ ሲሆን ቀሪ ጉድለቶችን ደግሞ በሂደት እንሞላቸዋለን የሚል እምነት ነበረን” ብለዋል።

#የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አንድ አመት ከአምት ወራት ቢያስቆጥርም “በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ማቋቋምን በተመለከተ በፕሪቶርያው ስምምነት የመጀመሪያ ሰነዶች ውስጥ አልነበረም፣ በኋላ ላይ በሂደት ነው የተካተተው፣ በወቅቱ ለምን ብለን ሞግተናል” ሲሉ ገልጸዋል፤ “የጊዜያዊ አስተዳደሩ እድሜም ከስድስት ወር እስከ አንድ አመት ጊዜ ብቻ” መሆኑን አውስተዋል።

“ህወሓት ከሻዕብያ ጋር ግንኙነት አለው በሚል የሚገለጸው ፍጹም ሀሰት ነው” ብለዋል።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ሠራዊቱ የተስፋፊዎችን የጦርነት ነጋሪት ጉሸማ ለመመከት የሚያስችል የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል – ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላመከላከያ ሠራዊት የተስፋፊዎችን የጦርነት ነጋሪት ጉሸማ ለመ...
05/09/2024

ሠራዊቱ የተስፋፊዎችን የጦርነት ነጋሪት ጉሸማ ለመመከት የሚያስችል የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል – ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

መከላከያ ሠራዊት የተስፋፊዎችን የጦርነት ነጋሪት ጉሸማ ለመመከት የሚያስችል የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ ይገኛል ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ፡፡

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በ47ኛው የምስራቅ ዕዝ ምስረታ በዓል ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የዕዙን የምስረታ በዓል ከሰላም ወዳዱ የሶማሌ ህዝብና ከጀግናው የዕዙ አመራርና አባላት ጋር ለማክበር በመቻሌ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል፡፡

ዕዙ ከምስረታው ማግስት ጀምሮም ተስፋፊውን የዚያድ ባሬ ጦር ጨምሮ የተለያዩ የሽብር ሀይሎችን በመከላከልና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰጠውን ግዳጅ በጀግንነት ሲመክት የቆየ አንጋፋና ጀግና ዕዝ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡

ዕዙ የዚያድ ባሬ ጦር ወደ መሀል ሀገር ያደረገውን ወረራ መስዋዕትነት በመክፈል ጭምር የሀገሩን ዳር ድንበር እንዳስከበረ አስታውሰዋል።

ዕዙ የሀገር ሰላም፣ ሉዓላዊነትና አንድነትን በማስጠበቅ ከፍተኛ ዋጋ መክፈሉና የሰራዊቱ መመኪያ መሆኑን ገልጸው፤ ሠራዊቱ ሀገርን ለመውረር የሞከሩ ሀይሎች ለመመከት የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለመውረር ግፊት ሲያደርጉና ግጭት ሲያባብሱ የነበሩ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች አብረው የቆሙ ቢመስሉም በሽንፈት ጊዜ እንደማይገኙ ከታሪክ መማር ይገባል ብለዋል፡፡

ሠራዊቱ በቀጠናው ያለውን የተስፋፊዎች የጦርነት ነጋሪት ጉሸማ ለመመከት የሚያስችል የተሟላ ወታደራዊ ቁመና ላይ እንደሚገኝም ነው የገለጹት ፊልድ ማርሻሉ፡፡

ውስጣዊ ችግሮች ቢኖሩም ሀገርን ከጥቃት ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ከሞከሩ ዳግመኛ እንዳያስቡት አድርጎ ለመመከት የሚያስችል ዝግጁነት መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ ህዝብ ለሠራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። (ኤፍ ቢ ሲ)

የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።የመስከረም ወር 2017 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ነሃሴ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና...
05/09/2024

የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የመስከረም ወር 2017 ዓ/ም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ምንም የዋጋ ጭማሪ ሳይደረግበት ነሃሴ ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አሳውቀዋል።

ሚኒስትሩ ፥ የነዳጅ ማደያዎች ካልተገባ የምርት ማከማቸት እና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ኡጋንዳዊቷ ሯጭ ረቤካ ቼፕቴጊ በወንድ ጓደኛዋ በደረሰባት ጥቃት ህይወቷ አለፈ ሲል የሀገሪቷ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኃላፊ አስታወቀዋል።
05/09/2024

ኡጋንዳዊቷ ሯጭ ረቤካ ቼፕቴጊ በወንድ ጓደኛዋ በደረሰባት ጥቃት ህይወቷ አለፈ ሲል የሀገሪቷ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ኃላፊ አስታወቀዋል።

04/09/2024

"የሚዲያ አዋርዱ" ያልተወራረዱ ትዝብቶች ‼

📌... ለመሆኑ ‹‹ምርጥ ዜና አንባቢ ማለት ምን ማለት ነው?›› የድምፁ ማማር ከሆነ፤ መወዳደር ያለበት የድምፅ አይዶል ነው፡፡

📌 የአካላዊ ቁመናው ማማር ከሆነ፤ መወዳደር ያለበት የቁንጅና ውድድር ነው፡፡

📌 ያነበበው ዜና ሀሳብ ከሆነ፤ መሸለም ያለበት ዜናውን የሠራው ዘጋቢ ነው፡፡

📌 ብዙ ዜና አንባቢዎች ራሳቸውም ጋዜጠኛ ናቸው፡፡ ስለዚህ ያነበበውን ዜና የሠራው ራሱ ከሆነ መደነቅ ያለበት በሠራው ዜና ነው፡፡

📌 በአንባቢነት ብቻ ከሆነ ግን አንድ የፋና ወይም የኢቲቪ ዜና አንባቢ ከዋልታ ወይም ኤን. ቢ ሲ ዜና አንባቢ የሚለየው በምንድነው?

📌 አቀራረብን በተመለከተ ሁሉም የየራሳቸው ‹‹ስታይል›› አላቸው፤ ምኑ ከምን ተወዳድሮ ነው ‹‹ምርጥ›› የሚሆነው? ሙያዊ መለኪያው የተለየ አይሆንም ወይ?

📌 ዜና ወይም አርቲክል ከሆነ ግን ‹‹የማኅበረሰብ ችግር ፈችነቱ፣ መረጃ ሰጪነቱ፣ አስተማሪነቱ፣ ምርመራነቱ….›› እየተባለ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ስለዚህ ሽልማቱ ትኩረት ያደረገው ሙያዊ ጉዳይ ላይ ሳይሆን ታዋቂነት ላይ ነው፡፡
ከኢኘድ የተገኘ

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከመስከረም 1 ጀምሮ ይተገበራል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትበታሪፍ ማስተካከያው በአራት ዓመት ውስጥ የሚተገበር የ6.01 ብር ጭማሪ መደረጉ ታውቋልተግባራዊ የሚደ...
04/09/2024

አዲሱ የታሪፍ ማሻሻያ ከመስከረም 1 ጀምሮ ይተገበራል - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በታሪፍ ማስተካከያው በአራት ዓመት ውስጥ የሚተገበር የ6.01 ብር ጭማሪ መደረጉ ታውቋል

ተግባራዊ የሚደረገው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ የመኖሪያ ቤት፣ የንግድ፣ የአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራትን ያካተተ ነው፡፡

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ጂቡቲ  #ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን በቀጥታ እንድታስተዳድር አማራጭ ሃሳብ አቀረብኩ እንጂ የባህር ሀይል ጦር ሰፈር እንድትገነባ አልፈቅድም አለችኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን በቀጥታ እንድታስተዳድር...
04/09/2024

ጂቡቲ #ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን በቀጥታ እንድታስተዳድር አማራጭ ሃሳብ አቀረብኩ እንጂ የባህር ሀይል ጦር ሰፈር እንድትገነባ አልፈቅድም አለች

ኢትዮጵያ የታጁራ ወደብን በቀጥታ እንድታስተዳድር አማራጭ ሃሳብ ማቅረቧን ያስታወቁት #የጂቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ኢትዮጵያ የባህር ሀይል ጦር ሰፈር መገንባት እንደማትችል አስታወቁ።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጅቡቲ ከኢትዮጵያ ድንበር በ100 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኘውን ታጁራ ወደብ እንድትጠቀምበት ሃሳብ ማቅረቧን አስታውቀው “ሆኖም ይህ አማራጭ ኢትዮጵያ የባሕር ኃይል ለመገንባት ያላትን ፍላጎት እንደማያካትት” አመልክተዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ፍላጎቷን ለማሟላት ቢያንስ አስር ወደቦች ያስፈልጋታል ሲሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

የአማራ ክልል መንግሥት በክልሉ በግድያ እና እገታ የጸጥታ ኃይሎች እጅ እንዳለበት አስታወቀየአማራ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ የሕዝብ ቁጣ በቀሰቀሰው ግድያ እና እገታ የጸጥታ አስከባሪዎች ተሳታፊ...
04/09/2024

የአማራ ክልል መንግሥት በክልሉ በግድያ እና እገታ የጸጥታ ኃይሎች እጅ እንዳለበት አስታወቀ

የአማራ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ የሕዝብ ቁጣ በቀሰቀሰው ግድያ እና እገታ የጸጥታ አስከባሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገለጸ።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ትናንት ነሐሴ 28/2016 ዓ.ም. ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች ግድያ እና እገታ መኖሩን ጠቁሟል።

መግለጫው የወጣው በጎንደር ከተማ የሁለት ዓመት ህጻን በአጋቾች መገደሏን ተከትሎ ቁጣቸውን ለመግለጽ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች “በመንግሥት ኃይሎች” መገደላቸው ከተገለጸ በኋላ ነው።BBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

በቻይና - አፍሪካ ጉባኤ ላይ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።ቻይና ከተገኙት መካከል የሶማሊያ እና ኤርትራ ፕሬዜዳንቶች ይጠቀሳሉ።ሁለቱ መሪዎች ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ማድ...
04/09/2024

በቻይና - አፍሪካ ጉባኤ ላይ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።

ቻይና ከተገኙት መካከል የሶማሊያ እና ኤርትራ ፕሬዜዳንቶች ይጠቀሳሉ።

ሁለቱ መሪዎች ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ውይይቱ " አሳሳቢ ነው " ባሉት የቀጠናዊ ጉዳይ እንዲሁም ግንኙነታቸውን በማጠናከር ላይ የተስመሰረተ እንደሆነ ተነግሯል። TIKVAH-ETHIOPIA

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

 #የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሳያውቅ ኤርፖርት እንዳይገነባ መመሪያ እንደተሰጠው አስታወቀየኢትዮጵያ አየር መንገድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሳያውቅ የኤርፖርት ግንባታ እንዳያካ...
04/09/2024

#የኢትዮጵያ አየር መንገድ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሳያውቅ ኤርፖርት እንዳይገነባ መመሪያ እንደተሰጠው አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሳያውቅ የኤርፖርት ግንባታ እንዳያካሂድ መመሪያ እንደተሰጠው አስታወቀ።

የኤርፖርቶችን ተደራሽነት ፍትሐዊ ለማድረግ እንዲቻል፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሳያውቀው ኤርፖርት እንዳይገነባ መመሪያ እንደተሰጣቸው የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማስጀመርያ መርሐ ግብሩን ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ሲያካሂድ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ገልጸዋል።

አየር መንገዱ ብሔራዊ የኤርፖርቶች የልማት ፕላን እያዘጋጀ መሆኑን የገለጹት አቶ መስፍን፣ ይህንንም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተከታተለው መሆኑን አስታውቀዋል፤ ‹‹ከእያንዳንዱ ክልል ኤርፖርት ሥሩልን የሚል ብዙ ጥያቄ ይቀርብልናል›› ያሉት ዋና ሥራ አሥፈጻሚው፣ እየተዘጋጀ ያለው ፕላንም ይህን ጫና የሚቀንስ ይሆናል ብለዋል።

አዲስ አበባን ጨምሮ 23 ኤርፖርቶች መኖራቸውንና በአሁኑ ወቅትም ተጨማሪ የአምስት ኤርፖርቶች ግንባታ እየተካሄደ ከመሆኑ በተጨማሪ፣ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ አቅራቢያ ስድስተኛ ኤርፖርት ለመገንባት ኮንትራክተር ተመርጦ የመሬት እርክክብ ብቻ እንደሚቀር አብራርተዋል።

ካለው ፍላጎት አኳያ አሁን ካሉትም ሆነ እየተገነቡ ከሚገኙ ኤርፖርቶች በተጨማሪ ሌሎች ኤርፖርቶችንም መገንባት እንደሚያስፈልግ፣ ነገር ግን ምን ዓይነት ኤርፖርት መገንባት አለበት? የትና መቼ ይገንባ? የሚሉ ጉዳዮችን ምላሽ ለመስጠት ፕላኑ እንደሚያግዝ መግለጻቸውን ከሪፖርተር ጋዜጣ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

 +የNATO አባል ሀገሯ ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን በይፋ ማመልከቻ ማቅረቧን የቱርክ ገዥ ፓርቲ ቃል አቀባይ ኦመር ሴሊክ አረጋግጠዋ...
04/09/2024

+

የNATO አባል ሀገሯ ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች።

ቱርክ የBRICS አባል ለመሆን በይፋ ማመልከቻ ማቅረቧን የቱርክ ገዥ ፓርቲ ቃል አቀባይ ኦመር ሴሊክ አረጋግጠዋል።

ቃል አቀባዩ " ፕሬዝደንታችን የBRICS አባል መሆን እንደምንፈልግ ደጋግመው ተናግረዋል። ጉዳዩ በሂደት ላይ ነው " ብለዋል።

" በአባልነት ሂደት ላይ ያለውን እምርታ ለህዝብ እናሳውቃለን " ሲሉም ተናግረዋል።

ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም የBRICS+ ስብስብን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳላት ማሳወቋ የሚዘነጋ አይደለም።

ቱርክ የ አባል ሀገር እንደሆነች ይታወቃል።

+ ኢትዮጵያን ጨምሮ የሩስያ ፣ የብራዚል ፣ የቻይና ፣ የህንድ ፣ የደቡብ አፍሪካ ፣ የኢራን ፣ የግብፅ ፣ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ስብስብ ነው።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

03/09/2024

Live Update
“Shire, Dembi Dollo, and Nekmte will soon get new world class airports” Mesfin Tasew, Ethiopian Airlines CEO,

03/09/2024

Live update
“Ethiopian airlines gives equal due respect to local flights as international flights” Mesfin Tasew, Ethiopian Airlines CEO

03/09/2024

BREAKING!
“Eritrea blocked Ethiopian Airlines Bank Account in the country” Mesfin Tassew, Ethiopian Airlines CEO

 #በአማራና  #በኦሮሚያ ክልሎች እገታዎች እየተባባሱ ያሉት ከትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በተፈጠረ “የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት” ሳቢያ ነው - ኢሰመኮ #የኢትዮጵያ ሰብአዊ...
03/09/2024

#በአማራና #በኦሮሚያ ክልሎች እገታዎች እየተባባሱ ያሉት ከትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በተፈጠረ “የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት” ሳቢያ ነው - ኢሰመኮ

#የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተለይም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እገታዎች በአሳሳቢ ሁኔታ መባባሳቸውን አስታውቆ መንግስት ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስድ ጠየቀ።

ኢሰመኮ ዛሬ ነሃሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ “የእገታ ተግባርን ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማስቆም ለሰዎች እገታ መነሻና አባባሽ ምክንያት የሆነውን የሰላም መደፍረስና የትጥቅ ግጭትን በዘላቂነት፣ በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይገባል ብሏል፤ በተጨማሪም ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ ነው” ሲል አሳስቧል።

እገታዎቹ የተባባሱት በተለይም “በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች” ከተራዘሙ የትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ “በተፈጠረው የሕግ ማስከበር እና የመንግሥት መዋቅር መላላት ሳቢያ ነው” ሲል ጠቁሟል።

የኢሰመኮ አደረኩት ባለው ክትትልና ምርመራ ውጤት መሰረት ተባብሰው የቀጠሉት እገታዎች የሚፈጸሙት “ለዘረፋ በተደራጁ ቡድኖች እና በአንዳንድ የመንግሥት የጸጥታ አካላት አባሎች” መሆኑን አመላክቷል። Addis Standard

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

የኢትዮጵያ ጦር ባለፉት አስርት ዓመታት በተለያዩ የአገር ውስጥ እና የውጭ ጦርነቶች ውስጥ አልፏል። የግብጽ ጦር በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራዊቱን ያጣበት ወታደራዊ ዘመቻ ያካሄደው በሲናይ በረ...
03/09/2024

የኢትዮጵያ ጦር ባለፉት አስርት ዓመታት በተለያዩ የአገር ውስጥ እና የውጭ ጦርነቶች ውስጥ አልፏል።

የግብጽ ጦር በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ሠራዊቱን ያጣበት ወታደራዊ ዘመቻ ያካሄደው በሲናይ በረሃ ከኢስላሚክ ስቴት (አይኤስ) ሰርጎ ገቦች ጋር ባደረገው ግጭት ነው።BBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

የሀውቲ ታጣቂዎች ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ማጥቃታቸውን የአሜሪካ ጦር ገለጸሀውቲዎች ይህን ጥቃት የማያቆሙት በጋዛ ተኩስ ሲቆም ነው ብለዋልየአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ሀውቲዎች ሁለቱን መርከቦች...
03/09/2024

የሀውቲ ታጣቂዎች ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ማጥቃታቸውን የአሜሪካ ጦር ገለጸ

ሀውቲዎች ይህን ጥቃት የማያቆሙት በጋዛ ተኩስ ሲቆም ነው ብለዋል

የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ሀውቲዎች ሁለቱን መርከቦች በሁለት ሚሳይሎች እና ድሮን ኢላማ ማድረጋቸውን እና መምታታቸውን ገልጿል
የሀውቲ ታጣቂዎች ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን ማጥቃታቸውን የአሜሪካ ጦር ገለጸ።

የአሜሪካ ጦር በኢራን የሚደገፉት የሀውቲ ታጣቂዎች ሁለት ድፍድፍ ነዳጅ የጫኑ መርከቦችን በትናንትናው እለት በቀይ ባህር ላይ አጥቅተዋል ብሏል።

ጦሩ እንደገለጸው ከሆነ ጥቃት የደረሰባቸው መርከቦች የሳኡዲ ሰንደቅ አላማ ስታውለበልብ የነበረችው አምጃድ እና የፓናማ ሰንደቅአላማ ስታውለበለብ የነበረችው ብሉ ላጉን ናቸው።

ሀውቲዎች ሰኞ ምሽት ብሉ ላጉንን በበርካታ ድሮኖች እና ሚሳይሎች ማጥቃታቸውን ያመኑ ሲሆን ስለሳኡዲ መርከብ ጉዳይ ግን ምንም ያሉት ነገር የለም።

የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ሀውቲዎች ሁለቱን መርከቦች በሁለት ሚሳይሎች እና ድሮን ኢላማ ማድረጋቸውን እና መምታታቸውን ገልጿል።

ሁለቱም መርከቦች ነዳጅ ጭነው ነበር ያለው የአሜሪካ ጦር መግለጫ ጥቃቱን "ሀውቲዎች የፈጸሙት ኃላፊነት የጎደለው የሽብር ድርጊት" ሲል ገልጾታል። Al Ain

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

በጎንደር ከተማ የሁለት ዓመት ሕጻን በአጋቾቿ መገደሏ ቁጣን ቀሰቀሰበአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የሁለት ዓመታ ሕጻን ታግታ ከተወሰደች በኋላ ትናንት ሰኞ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም. ተገድላ አስ...
03/09/2024

በጎንደር ከተማ የሁለት ዓመት ሕጻን በአጋቾቿ መገደሏ ቁጣን ቀሰቀሰ

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ የሁለት ዓመታ ሕጻን ታግታ ከተወሰደች በኋላ ትናንት ሰኞ ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም. ተገድላ አስክሬኗ በወላጆቿ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ተጥሎ ተገኘ።

ይሁን እንጂ አጋቾች ከጠየቁት የማስለቀቂያ ገንዘብ አብዛኛውን መጠን ቢቀበሉም “ጡጦ ያልጣለችውን” ታዳጊ ገድለው መጣላቸውን የቤተሰብ አባሉ ለቢቢሲ አስረድተዋል።

የሕጻኗን በአጋቾቿ ተገድሎ መጣል አስመልክቶ የተቆጡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በትናንትናው ዕለት አደባባይ የወጡ ቢሆንም፣ ከከተማዋ የጸጥታ ኃይሎች ጋር መጋጨታቸውን እና ጉዳት መድረሱን የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ኖላዊት ዘገየ የተባለችው ይህች የሁለት ዓመት ታዳጊ ለቤተሰቧ ብቸኛ ልጅ ነበረች።

ታዳጊዋ የተወሰደችው ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አርብ ነሐሴ 24/2016 ዓ.ም. ረፋድ 3፡30 ላይ ግቢዋ ውስጥ ስትጫወት መሆኑን የቤተሰብ አባሉ ይናገራሉ።

የኖላዊትን መጥፋት ተከትሎ የአካባቢው ሰው ታዳጊዋን ፍለጋ በየአቅጣጫው ወጥቶ ነበር።

ይሁን እንጂ የታጋቿ ወላጆች ተከራይተው በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ በአጋቾቹ የተጣለ ማስታወሻ ወረቀት ከተገኘ በኋላ ኖላዊት መታፈኗ እንደታወቀ የቤተሰብ አባሉ አስረድተዋል።

“በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ እኛ አግተን ወስደናታል እስክንደውልላችሁ ታገሱ” የሚል መልዕክት የሰፈረበት ወረቀት መገኘቱን የቤተሰብ አባሉ ይናገራሉ።

በመኖርያ ቤቱ ውስጥ ወዳጅ ዘመድ ተሰብሰብቦ በነበረበት ወቅትም አጋቾቹ “ይህንን ካልበተናችሁ እንገላታለን። ለፖሊስ ብታመለክቱም እንገላታለን” የሚል ማስፈራርያ አዘል ጽሑፍ ግቢ ውስጥ መጣላቸውን አስረድተዋል።BBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

የፐርፐዝ ብላክ የቦርድ አስፈጻሚን ጨምሮ 5 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡበማታለል ሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የፐርፐዝ ብላክ የቦርድ አስፈጻሚን ጨምሮ አምስት ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።የፌደራል ...
02/09/2024

የፐርፐዝ ብላክ የቦርድ አስፈጻሚን ጨምሮ 5 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በማታለል ሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የፐርፐዝ ብላክ የቦርድ አስፈጻሚን ጨምሮ አምስት ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድንን ያቀረበውን የጥርጣሬ መነሻና የጊዜ ቀጠሮ መነሻንና የተጠርጣሪዎች ጠበቆችን የመከራከሪያ ነጥብ ተመልክቷል።

ተጠርጣሪዎቹ 1ኛ የፐርፐዝ ብላክ የቦርድ አባልና የቦርድ ዋና ስራ አፈጻሚ ኤርሚያስ ብርሀኑ፣ 2ኛ የድርጅቱ ኦፕሬሽን ኦፊሰር ናቸው የተባሉት ወ/ሮ ኤፋታት (ሶፍያ) ነጋሽ ፣ 3ኛ የድርጅቱ ሰራተኛ የሆኑት ብሩክ በነበሩ ደስታ፣ 4ኛ ገበሬ ቲቪ (ቴቪ) ባለሙያ ዋሲሁን ዋጋ አሰፋ፣እና 5ኛ የቦርድ አባል እና የብሔራዊ ቴያትር ቤት የሴቶች ማህበር ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ዘይል ኢብራሒም ናቸው።FBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ታጣቂዎች የመተማ ዮሐንስ ከተማን በመቆጣጠራቸው ሳቢያ ሱዳን  #ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን የገለባት መስመር መዝጋቷ ተገለጸ  #በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ድንበር...
02/09/2024

ታጣቂዎች የመተማ ዮሐንስ ከተማን በመቆጣጠራቸው ሳቢያ ሱዳን #ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን የገለባት መስመር መዝጋቷ ተገለጸ

#በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ያለውን መስመር መቆጣጠራቸውን ተከትሎ #ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን የጋላባት ድንበርን መዝጋቷ ተገለጸ።

“የሱዳን ባለስልጣናት በድንበሩ አቅራቢያ ሰፍረው የነበሩ የፌደራል ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ጦር አባላት ትጥቅ ፈትተው ወደ ሱዳን ግዛት እንዲገቡ መፍቀዱን የሱዳን ወታደራዊ ምንጮችቹን ዋቢ በማድረግ ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል።

በምላሹም “የፋኖ ታጣቂዎች በድንበር ላይ የሚገኙ ሱዳናውያን እንዲሄዱ እና እንዲወጡ መፍቀዳቸው” ተገልጿል ።

የጋላባት ድንበር ማቋረጫ መዘጋቱን ተከትሎ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረገው የድንበር ንግድ እንቅስቃሴ መቆሙን ዘገባው አስታውቋል።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂዎች ኢትዮጵያን ከሱዳን ጋር የሚያዋስናትን መስመር በመቆጣጠር “የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ እና ነዳጅ እንዳይገባ በማድረግ፣ ወታደራዊ እንቅስቃሴውንም በመመያዝ የአማራ ክልልን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር በማለም መስመሩን መቆጣጠራቸው የመረጃ ምንጮች ነግረውኛል ሲል ሱዳን ትሪቡን በዘገባው አመልክቷል።

የመተማ ዮሐንስ በርካታ ነዋሪዎች እና ነጋዴዎች ለፋኖ ሀይሎችን ስለሚደግፉ ከተማዋን እንዲቆጣጠሩ ማመቻቸታቸውንና ድጋፍ ማድረጋቸውን ምንጮች ነግረውኛል ያለው ዘገባው የኢትዮጵያ ጦር ከከተማዋ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው በሻሂዲ ግዛት ሰፍሮ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

በሺህዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ስደተኞች በኢትዮጵያ መተማ አካባቢ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ስጋት ላይ መውደቃቸውን ዘገባው አስታውቋል።Addis Standard

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

በቀጣዮቹ 10 ቀናት ከመደበኛ በላይ ዝናብ ስለሚኖር ጥንቃቄ እንዲደረግ ኢንስቲትዩቱ አሳሰበበሚቀጥሉት 10 ቀናት በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ...
02/09/2024

በቀጣዮቹ 10 ቀናት ከመደበኛ በላይ ዝናብ ስለሚኖር ጥንቃቄ እንዲደረግ ኢንስቲትዩቱ አሳሰበ

በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠን ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ፡፡

በመደበኛ ሁኔታ በቀጣዮቹ 10 ቀናት የክረምቱ ዝናብ በስርጭትም ሆነ በመጠን ከምሥራቅ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ቀስ በቀስ የመቀነስ አዝማሚያ እንደሚያሳይ ተገልጿል፡፡

በአንጻሩ በመካካለኛው፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እንዲሁም በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ ጠንካራ እና የተስፋፋ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖር ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በመካከለኛው፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራል ተብሏል፡፡

በመሆኑም በሚቀጥሉት 10 ቀናት ከመደበኛ በላይ የዝናብ መጠንና ስርጭት ስለሚኖር የጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡

በአጠቃላይ በምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ ምሥራቅ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ሸዋ፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮጉዱሩ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉአባቦር፣ ጅማ፣ ባሌ፣ ምሥራቅ ባሌ፣ አዲስ አበባ፣ ሰሜን፣ ደቡብ፣ ማዕከላዊ እና ምዕራብ ጎንደር፣ ምሥራቅ እና ምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን እና ዋግኽምራ ዞኖች በበርካታ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ ነው የተባለው፡፡

በተመሳሳይ መተከል፣ አሶሳ፣ ካማሺ እና የማኦኮሞ ልዩ ዞን፣ የኢታንግ ልዩ ዞን፣ ኑዌር፣ አኝዋ እና ማጃንግ ዞኖች፣ ስልጤ፣ ጉራጌ እና ምዕራብ ጉራጌ ዞኖች፣ ቀቤና፣ ጠምባሮ እና ማረቆ ልዩ ወረዳዎች፣ ሀላባ፣ ሀዲያ፣ የም ዞኖች፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲኦ እና ወላይታ ዞኖች፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ከፋ፣ ሸካ፣ ኮንታ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች፣ ሁሉም የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ የምሥራቅ፣ የደቡብ ምሥራቅ፣ የማዕከላዊ፣ የሰሜን ምዕራብ እና የምዕራብ ትግራይ ዞኖች፣ ሐረር እና ድሬዳዋ በበርካታ ቦታዎቻቸው ላይ ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል፡፡

ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች አልፎ አልፎ በፀሐይ ኃይል ታግዞ ከሚፈጠሩ ደመና ክምችቶች ጋር ተያይዞ ነጎድጓዳማ ዝናብ እንደሚኖራቸው የኢንስቲትዩቱ መረጃ አመላክቷል፡፡FBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

በ  #ኢትዮጵያ ከጥር እስከ ነሀሴ 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ  ሰዎች በወ...
02/09/2024

በ #ኢትዮጵያ ከጥር እስከ ነሀሴ 2016 ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ የወባ በሽታ ስርጭት መከሰቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ከ4 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውንና 918 ሰዎች ህይወት ማለፉን ድርጅቱ ገልጿል።

በ2016 በተከሰተ የወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት አጠቃላይ ቁጥር የሚበልጥ መሆኑም ተገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር የወባ በሽታን ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም የበሽታው ተጠቂዎችና የሟቾች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።

ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበው በ ኢትዮጵያ ክልል ሲሆን እና #ጋምቤላ ክልሎችም በርካታ ሰዎች በበሽታች መያዛቸው ተገልጿል።

አዳዲስ የወባ በሽታዎች በ #ኦሮሚያ (53 በመቶ) ፣ በ #አማራ (15 በመቶ) ፣ በ #ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (11 በመቶ) ፣ በ (5 በመቶ) እና በ #ቤኒሻንጉል ጉሙዝ (5 በመቶ) መከሰቱ ተመላክቷል።

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

አትሌት ያየሽ ጌቴ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈችበ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች አትሌት ያየሽ ጌቴ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የዓይነ ስውር (T-11) ፍጻሜ ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭም...
02/09/2024

አትሌት ያየሽ ጌቴ ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈች

በ17ኛው የፓራሊምፒክ ውድድሮች አትሌት ያየሽ ጌቴ በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የዓይነ ስውር (T-11) ፍጻሜ ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈች፡፡

አትሌቷ ቀደም ሲል 4 ደቂቃ ከ27 ሰከንድ ከ68 ማይክሮ ሰከንድ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን በአራት ሰከንድ በማሻሻል አንደኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች።

ማሸነፏን ተከትሎም ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ ማስገኘቷን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

በእስራኤል ትናንት ግማሽ ሚሊየን ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው ተነገረሰልፈኞቹ የኔታንያሁ አስተዳደር ቀሪዎቹን 101 ታጋቾች እንዲያስለቅቅ ጠይቀዋልበጋዛ ስድስት ታጋቾች መገደላቸውን ተ...
02/09/2024

በእስራኤል ትናንት ግማሽ ሚሊየን ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው ተነገረ

ሰልፈኞቹ የኔታንያሁ አስተዳደር ቀሪዎቹን 101 ታጋቾች እንዲያስለቅቅ ጠይቀዋል

በጋዛ ስድስት ታጋቾች መገደላቸውን ተከትሎ እስራኤላውያን ቁጣቸውን በአደባባይ እያሰሙ ነው።

የኔታንያሁ አስተዳደር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሶ ታጋቾችን ማስለቀቅ አልቻለም ያሉ 500 ሺህ የሚገመቱ ሰልፈኞች በቴል አቪቭ፣ እየሩሳሌምና ሌሎች ከተሞች ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ በእየሩሳሌም መንገድ ዘግተው በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ዙሪያ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ውለዋል።

የቴል አቪቭ ጎዳናዎችም የሟቾቹን ታጋቾች ምስሎች በያዙ ሰልፈኞች ተሞልተው መዋላቸውን ነው ሬውተርስ ያስነበበው።

ሰልፈኞቹ የኔታንያሁ አስተዳደር ቀሪዎቹን 101 ታጋቾች ለማስለቀቅ በፍጥነት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደርስ ጠይቀዋል።

የእስራኤል ሌበር ፓርቲ በዛሬው እለት ዜጎች ለተቃውሞ አደባባይ እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል። Al Ain

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

ለሩሲያ ይሰላል ተብሎ የሚጠረጠረው ዌል ኖርዌይ ውስጥ ሞቶ ተገኘለሩሲያ እንዲሰልል ስልጠና ተሰጥቶታል ተብሎ የሚጠረጠረው ቤሉጋ ዌል የተባለው የባሕር እንስሳ በኖርዌት ጠረፍ ሞቶ ተገኘ።ህቫልድ...
02/09/2024

ለሩሲያ ይሰላል ተብሎ የሚጠረጠረው ዌል ኖርዌይ ውስጥ ሞቶ ተገኘ

ለሩሲያ እንዲሰልል ስልጠና ተሰጥቶታል ተብሎ የሚጠረጠረው ቤሉጋ ዌል የተባለው የባሕር እንስሳ በኖርዌት ጠረፍ ሞቶ ተገኘ።

ህቫልድርሚር የተሰኘ ቅፅል ስም የተሰጠው ይህ ዌል በደቡብ ምዕራቧ ሪሳቪካ ከተማ ሞቶ ሲንሳፈፍ ከተገኘ በኋላ ለምርመራ ተወስዷል።

የሩሲያው “ሰላይ ዌል” የሚል ስም የተሰጠው ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት በኖርዌይ ግዛት ከታየ በኋላ ነው።

በወቅቱ ዌሉ ጎፕሮ የተባለው ካሜራ ተገጥሞለት የተገኘ ሲሆን ካሜራው “የሴይንት ፒተርስበርግ ንብረት” የሚል ፅሑፍ ይነብበት ነበር።

ይህን ተከትሎ ይህ እንስሳ ሰላይ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወሬዎች መዛመት ጀመሩ። ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም ሰላይ ዌሎች ነበሩ ይላሉ።

ሩሲያ ለዚህ ወሬ ምንም ዓይነት ምላሽ ሰጥታ አታውቅም።

የዌሉን እንቅስቃሴ ላለፉት ዓመታት ሲከታተል የነበው ማሪን ማይንድ የተባለ ድርጅት ነው የእንስሳውን ሞት ያረጋገጠው።

የማሪን ማይንድ መሥራች ሴባስትያን ስትራንድ ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት የሞቱ ምክንያት እስካሁን የማይታወቅ ሲሆን የህቫልድርሚር ሰውነት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አይታይም።

የዌሉ ሬሳ ወደ ቤተ-ሙከራ ተልኮ ምርመራ እንደሚደረግበት የድርጅቱ ኃላፊ ተናግረዋል።BBC

ትክክለኛታቸዉ የተረጋገጡ ዜናዎች በትኩሱ እንዲደርስዎ ገፃችንን Follow በማድረግ ይከተሉን!
Follow our page… share our stories
Get latest news via our telegram
https://t.me/+8DfsAG11pqk4YmVk

Address

Ghana Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Verified News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share