ሀገሬ ቴቪ- Hagerie TV

ሀገሬ ቴቪ- Hagerie TV Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሀገሬ ቴቪ- Hagerie TV, TV Channel, HA BET Building, Comoros Street, Kebena, Addis Ababa.
(1)

Hagerie TV is an upcoming television station that has started broadcasting and caters to a wide array of the Ethiopian public as well to many others in the target vicinity of the channel.

ሚያዚያ 10፣ 2016የደቡብ አፍሪካው የቀድሞው ፕሬዝዳንትና በሙስና ቅሌት ወህኒ ወርደው የነበሩት ጃኮብ ዙማ ሌላ ፓርቲ አቋቁመው በ7ኛው የሀገሪቱ ምርጫ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።የ8...
18/04/2024

ሚያዚያ 10፣ 2016

የደቡብ አፍሪካው የቀድሞው ፕሬዝዳንትና በሙስና ቅሌት ወህኒ ወርደው የነበሩት ጃኮብ ዙማ ሌላ ፓርቲ አቋቁመው በ7ኛው የሀገሪቱ ምርጫ ላይ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተነግሯል።

የ82 ዓመቱ አዛውንት ዙማ ወደ ስልጣን የሚመጡት ከኔልሶን ማንዴላ ወደስልጣን መምጣት ጀምሮ በመሪነት የነበረውንና እርሳቸውም ያገለገሉትና አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስን በመገዳደር ነው።

ከፈረንጆቹ 1994 ጀምሮ በስልጣን ላይ ያለው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረሥ በመጪው ምርጫ የዙማን መወዳደር ተከትሎ ሊያሸንፍ እንደሚችሉ ትንበያዎች ያሳያሉ።

ዙማ ድል ቀንቷቸው ወደስልጣን ቢመጡ የቀድሞ አጋሮቻቸውን ሊበቀሉ ይችላሉ የሚል ስጋትም እንዳለ ተነግሯል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 10፣ 2016የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለገጠመው የበጀት እጥረት ፖለቲካዊ ውሳኔ ይሰጠኝ አለ። ዩኒቨርሲቲው ከመንግሥት የተለቀቀለት በጀት ለሚያደርገው የጥናትና ምርምር ስራ በቂ አለመሆኑን ጠ...
18/04/2024

ሚያዚያ 10፣ 2016

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ለገጠመው የበጀት እጥረት ፖለቲካዊ ውሳኔ ይሰጠኝ አለ።

ዩኒቨርሲቲው ከመንግሥት የተለቀቀለት በጀት ለሚያደርገው የጥናትና ምርምር ስራ በቂ አለመሆኑን ጠቁሟል።

በበጀት እጥረት ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት እየተሳነው መሆኑንም ጠቁሟል።

ተቋሙ ይህን የገለፀው የኅዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዩኒቨርሲቲው ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነው።

ተቋሙ በበጀት እጥረት ሳቢያ የአይደር ሪፈራል ሆስፒታል አደጋ ላይ መውደቁን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው የበጀት እጥረቱ እንዲፈታ ለሚመለከታቸው የተለያዩ አካላት ጥያቄ ቢያቀረብም ምላሽ አለመገኘቱን የጠቆሙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፋና ሐጎስ ጥያቄው ፖለቲካዊ ውሳኔን የሚጠይቅ መሆኑ ገልጸዋል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 10፣ 2016ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ከኾኑት ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ስለከተማ ልማት እና የመሬት አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። አምባሳደሩ በሀገራቸ...
18/04/2024

ሚያዚያ 10፣ 2016

ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ከኾኑት ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ስለከተማ ልማት እና የመሬት አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ በሀገራቸው በከተማ ዕቅድ እና መሠረተ ልማት ዝርጋታ ላይ በተለይም ከማኀበረሰቡ አጋጥመው ስለነበሩ ተግዳሮቶች ለከንቲባ አዳነች ማብራራታቸውን ኤምባሲው በኤክስ ማኀበራዊ ገፁ አስታውቋል።

ኤርቪን ማሲንጋ ከዚህ ሥራ ዜጎችን በግልጽ ማወያየት እና ማሳተፍ እንደሚገባ እንዲሁም ትዕግስት መውሰድ ትምሕርት የወሰድንበት ነው ማለታቸውም ተገልጿል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

18/04/2024

ሀገሬ ዜና | ሚያዝያ 10፣ 2016 ዓ.ም | አዲስ አበባ | ሀገሬ ቴቪ

አጫጭር መረጃዎች

-በአ.አ የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች ሕዝብን ያሳተፋ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ
-የመቀሌ ዩኒቨርስቲ በጀት አጥሮኛል አለ
-ድጋፍ ያቋረጡ ረጂ ተቋማት ወደ ሥራ መመለስ
-ትኩረት የተነፈገው የኮንጎ ግጭት
-አዲሱ የቲክቶክ መተግበሪያ ግምገማ እንዲያቀርብ ተጠየቀ
-ኳታር የአሸማጋይነት ሚናዋን እየገመገመች ነው

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

ሚያዚያ 10፣ 2016ኳታር በእስራኤል እና በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ድርድር ላይ የአሸማጋይት ሚናዋን እንደገና እየገመገመች ነው ተባለ።ሀገሪቱ ይህን ታድርግ እንጂ ...
18/04/2024

ሚያዚያ 10፣ 2016

ኳታር በእስራኤል እና በፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ መካከል የተኩስ አቁም ድርድር ላይ የአሸማጋይት ሚናዋን እንደገና እየገመገመች ነው ተባለ።

ሀገሪቱ ይህን ታድርግ እንጂ በአንዳንድ ፖለቲከኞች ጥረቷ እየተናጋ መሆኑን ጠድቅላይ ሚኒስትር ሼክ መሐመድ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ይበሉ እንጂ ማንነታቸውን በስም ከመጥቀስ ተቆጥበዋል ሲል ሬውተርስ ዘግቧል።

ሀገሪቱ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲኖር እና የእስራኤል ታጋቾችን ለማስፈታት ከግብፅ እና ከአሜሪካ ጋር በመሆን ከፍተኛ ሚና እየተጫወተች መሆኑ ይታወቃል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

17/04/2024

ተጠባቂው የአውሮፓ ሻምፕዮንስ ሊግ ጨዋታ
ከ15 አመታት በኋላ የቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜን ለመቀላቀል አርሰናል ወደ አሊያንዝ አሬና በማቅናት ባየርን ሙኒክን ይገጥማሉ፡፡

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

17/04/2024

“ሀሳቤን በፍጹም አልቀይርም” ኪልያን ምባፔ
ፈረንሳዊው ኮከብ ኪልያን ምባፔ የፓሪሴንት ዤርሜይን ቆይታው በተመለከተ ሀሳቡን በፍጹም እንደማይቀይር ተናግሯል፡፡

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

17/04/2024

ከ11 አመታት በኋላ ታሪክ የሰራው ቦሩሲያ ዶርትመንድ
ቦሩሲያ ዶርትመንድ ከ11 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ በመድረስ ታሪክ ሰርተዋል፡፡

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

17/04/2024

የኦዲት ግኝቱን ያላረመው ተቋም
የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሰልጣን 8 ሚሊዮን ብር በጀት አልተጠቀመም ተብሏል
ባለስልጣኑ አሁን ላይ የእርምት እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

17/04/2024

አጫጭር መረጃዎች

-የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአራት ክልሎች ምርጫ ሊያካሂድ ነዉ
-ኮርፖሬሽኑ ከጀርመን ኩባንያ ጋር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ
-የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ከቻይና ሹማምንቶች ጋር እየተወያዩ ነው
-ሩሲያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን አስወጣች
-ዩክሬይን በሚሳኤል ጥቃት 13 ሰዎች ተገደሉባት

17/04/2024

አቅም የፈተነው የካንሰር ታማሚዎች ማዕከል
ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ማዕከል የቦታ ችግር አለብኝ ብሏል
በማዕከሉ ላለፉት 20 ዓመታት ለበርካታ አቅም ለሌላቸው የካንሰር ታማሚዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

17/04/2024

የሕንድ የኢኮኖሚ ግስጋሴ
በቻይና በአሜሪካ ዉዝግብ ባለሀብቶች ፊታቸዉን ወደ ህንድ አዙረዋል፡፡
በኢትዮጵያ እና ሕንድ መካከል የተካሄደዉ የንግድ ልዉዉጥ ከ1 ቢሊዮን ተሻግሯል

17/04/2024

ዕለቱን ከታሪክ:-ቤንጃሚን ፍራንክሊን ሲታወሱ
ቤንጃሚን በአሜሪካ ህገ መንግሥት ረቂቅ ላይ ደማቅ አሻራን አኑረዋል
በሰሩት ስራም በአሜሪካ በባለ 100 ዶላር ኖት ላይ ምስላቸው ታትሟል

17/04/2024

ለልጃቸውደስታ ንብረታቸው የሸጡ ወላጆች
ቻይናውያን ጥንዶች ልጃቸውን ለማዝናናት መኪናዎቻቸውን ሸጠዋል
የልጁ አባት ድርጊታቸው የቅንጦት እንዳይደለ ተግሯል

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

17/04/2024

ጦርነት ያጠላበት የክልሎቹ መግለጫ
የፌዴራል መንግስት በክልሎች መካካል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖር መስራት አለበት፡፡
የትግራይ እና አማራ ክልል ወሰን ችግር በውይይት ሊፈታ ይገባል ተብሏል

ሚያዚያ 9፣ 2016ዛሬ ረቡዕ በሰሜናዊ ዩክሬን ቸርኒቭ ከተማ ላይ በተወነጨፈ የሩሲያ ሚሳኤል ከ13 በላይ ዩክሬናውያን ለሞት ተዳረጉ።ከሞቱት በተጨማሪ ከ60 በላይ ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት መ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

ዛሬ ረቡዕ በሰሜናዊ ዩክሬን ቸርኒቭ ከተማ ላይ በተወነጨፈ የሩሲያ ሚሳኤል ከ13 በላይ ዩክሬናውያን ለሞት ተዳረጉ።

ከሞቱት በተጨማሪ ከ60 በላይ ዜጎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን የሃገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

በዚህች ከሩሲያና ቤላሩስ ቅርብ ርቀት በምትገኘው ከተማ ከሰዎች በተጨማሪም በርካታ መንደሮች፣ መኪኖችና፣ መሰረተ ልማቶች መውደማቸውም ታውቋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮልዶሚር ዘለንስኪ ብዙዎችን ለጉዳት ከዳረገው ጥቃት በኋላ የአውሮፓ ሀገራት የአየር መቃወሚያ እንዲሰጧቸው አጋሮቻቸውን ደጋግመው በመማፀን ላይ ናቸው።

ሆኖም ግን ዩክሬን እያስተናገደችው ያለው ጥቃት በአጋሮቻቸው ቸልተኝነት እንደሆነ ሳይተቹ አልቀሩም።

ጥቃቱን አስመልክቶ ከሩሲያ በኩል ምንም የተሰጠ ምላሽ እንደሌለ ተዘግቧል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016ሩሲያ፤ አዘርባጃን እና አርመኒያ በሚወዛገቡበት ናጎርኖ-ካራባህ ግዛት አስፍራ የነበረቻቸዉን ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ማስወጣት እንደጀመረች ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።የሩሲያ ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

ሩሲያ፤ አዘርባጃን እና አርመኒያ በሚወዛገቡበት ናጎርኖ-ካራባህ ግዛት አስፍራ የነበረቻቸዉን ሰላም አስከባሪ ወታደሮቿን ማስወጣት እንደጀመረች ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።

የሩሲያ ወታደሮች ወደ ስፍራዉ ያቀኑት ከአራት ዓመት በፊት ለስድስት ሳምንታት የዘለቀዉን የአርመኒያ እና አዘርባጃንን ጦርነት ለማቆም በሚል ነበር።

ሁለቱ ሀገራት የሚወዛገቡበትን ናጎርኖ-ካራባህ ግዛት ላለፉት 30 ዓመታት አርመኒያ ይዛዉ የቆየች ሲሆን፤ ባለፈዉ መስከረም ወር ላይ የሩሲያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ባሉበት አዘርባጃን ስፍራዉን መቆጣጠሯ ይታወቃል።

ሩሲያ በስፍራዉ የነበሩ ከሁለት ሺህ የሚልቁ ወታደሮቿን የምታስወጣዉ ወደ ዩክሬን የጦር ግንባር ለማሰማራት ይሁን ወይም ሌላ ምንም የተባለ ነገር እንደሌለ መረጃዉ ጠቁሟል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ እሁድ ዕለት ወደ ቻይና አቅንተው ከፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ጋር ተወያይተዋል።የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ ትኩረቱን ያ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ እሁድ ዕለት ወደ ቻይና አቅንተው ከፕሬዝዳንት ሺ ጂን ፒንግ ጋር ተወያይተዋል።

የሁለቱን ሀገራት የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በነበራቸው ውይይት የሀገራቱን ግንኙነት ወደ አዲስ የሁለትዮሽ ግንኘነት ከፍ እንዲል ኦላፍ ሾልዝ መጠየቃቸውን ሽንዋ የተሰኘ የዜና ምንጭ ዘግቧል።

የሁለቱን ሀገራት የአጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት 10 ዓመት እንደሞላው ያስታወሱት ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ናቸው።

አሁንም ቢኾን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እንዲያድግ ቻይና ዝግጁ መኾኗንም ገልፀዋል።

የጀርመኑ መሪ ቻይና የገቡት የምጣኔ ሀብት እና የሩሲያ ዩክሬንን ጦርነት አስመልክቶ ለመወያየት ነው ተብሏል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከሁለት ዓመት በፊት ምርጫ ባልተደረገባቸዉ እና ድጋሚ በሚካሄድባቸው አራት ክልሎች ዉስጥ፤ በመጪዉ ሰኔ ወር ምርጫ እንደሚያከናዉን አስታወቀ።ክልሎቹም...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከሁለት ዓመት በፊት ምርጫ ባልተደረገባቸዉ እና ድጋሚ በሚካሄድባቸው አራት ክልሎች ዉስጥ፤ በመጪዉ ሰኔ ወር ምርጫ እንደሚያከናዉን አስታወቀ።

ክልሎቹም አፋር፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሲሆኑ ምርጫው የሚከናወነው በመጪዉ ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን ቦርዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ አድርጓል።

በድጋሚ ምርጫ የሚከናወንበት የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባ እና ምርጫዉ በአንድ ቀን እንደሚካሄድ ቦርዱ አሳዉቋል።

በዚህም ከሚያዚያ 21 እስከ ግንቦት 5 ባሉት ቀናት ዉስጥ መራጮች ምዝገባ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸዉ ጥሪ ቀርቧል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከጀርመን ኩባንያ ጋር የ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።ኮርፖሬሽኑ በዛሬው እለት ከጀርመን የስራ እድል ፈጠራ ማስ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከጀርመን ኩባንያ ጋር የ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ።

ኮርፖሬሽኑ በዛሬው እለት ከጀርመን የስራ እድል ፈጠራ ማስተባበሪያ ቢሮ ጋር የተፈራረመው ስምምነት በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የንፁህ ውሀ አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያደርግ ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪ የአምራች ኩባንያዎችን እርካታ በመጨመር ፓርኩ በሙሉ አቅሙ እንዲንቀሳቀስና ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር ያለመ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑንም ከኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ገፅ ተመልክተናል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ በባለፉት ሦስት ወራት 200 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቶኛል ሲል አስታወቀ።ይህን ገቢ ያጣሁት ቦይንግ 737 ማክ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ በባለፉት ሦስት ወራት 200 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አሳጥቶኛል ሲል አስታወቀ።

ይህን ገቢ ያጣሁት ቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖችን ከበረራ አግጄ በማቆየቴ ነው ሲል አየር መንገዱ ተናግሯል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

ከጥቂት ወራት በፊት ንብረትነቱ የአላስካ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ ሰራሹ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በረራ ላይ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሩ ተገንጥሎ መውደቁ ይታወሳል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016የአሜሪካ እና የቻይና የጦር ኃላፊዎች ከዓመት በላይ ተቋርጦ ከቆየዉ የሁለትዮሽ ዉይይት በኋላ፤ መወያየት መቻላቸዉን ፔንታጎን አስታዉቋል።የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

የአሜሪካ እና የቻይና የጦር ኃላፊዎች ከዓመት በላይ ተቋርጦ ከቆየዉ የሁለትዮሽ ዉይይት በኋላ፤ መወያየት መቻላቸዉን ፔንታጎን አስታዉቋል።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስቲን እና የቻይናዉ አቻቸዉ ዶንግ ጁን በቪዲዮ ኮንፈረንስ ዉይይት ማድረግ መቻላቸዉን የፔንታጎን ጸሐፊ ጀነራል ፓት ሬይደር ተናግረዋል።

ከዓመት በኋላ በተደረገዉ የሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሚኒስትሮች ዉይይት፤ አሜሪካ አሁንም ቢሆን ለአንድ ቻይና ፖሊሲ ቁርጠኛ መሆኗን የአሜሪካዉ መከላከያ ሚኒስትር ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ሀገራቱ፤ ስለ ደቡባዊ ቻይና ባህር፣ ስለ ሩሲያ ዩክሬን ጦርነት እና ስለ ሰሜን ኮሪያ መወያየታቸዉን አናዶሉ ዘግቧል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016የናይጄሪያ የዋጋ ግሽበት በመጋቢት ወር ከ1.50 በመቶ ወደ 33.20 በመቶ ከፍ ማለቱን የሀገሪቱ ስታቲስቲክስ ቢሮ አስታወቀ።ይህ አሃዝ በ28 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

የናይጄሪያ የዋጋ ግሽበት በመጋቢት ወር ከ1.50 በመቶ ወደ 33.20 በመቶ ከፍ ማለቱን የሀገሪቱ ስታቲስቲክስ ቢሮ አስታወቀ።

ይህ አሃዝ በ28 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል።

ለዋጋ ግሽበቱ መጨመር ምክንያት የምግብ እና የኃይል ወጪ መናር መሆኑን ቢሮው ገልጿል ሲል አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል።

የዋጋ ግሽበቱን ለማረጋጋት በማሰብ በዚህ ዓመት ብቻ የናይጄሪያ ማዕከላዊ ባንክ ሁለት ጊዜ የወለድ ተመን ጭማሪ ማድረጉ ተነግሯል።

ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኔቡ ለበርካታ ዜጎቻቸው መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት እየሰሩ እንደነበሩ መነገሩ ይታወሳል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016የኬንያ ወደብ ባለስልጣን የላሙ ወደብን ለመጠቀም ያቀደችውን ኢትዮጵያ እና ወደቡን የሚጠቀሙ ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአገልግሎት ታሪፍ ቅነሳ ሊያደርግ መሆኑን ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

የኬንያ ወደብ ባለስልጣን የላሙ ወደብን ለመጠቀም ያቀደችውን ኢትዮጵያ እና ወደቡን የሚጠቀሙ ጎረቤት ሀገራትን ተጠቃሚ የሚያደርግ የአገልግሎት ታሪፍ ቅነሳ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ።

ሀገሪቱ ከአገልግሎት ታሪፍ ቅነሳው ባሻገር አስመጪዎች በላሙ ወደብ እስከ 60 ቀን ጭነታቸውን በነፃ ሊያከማቹ የሚችሉበትን አሰራር ልትተገብር እንደሆነም ተጠቁሟል።

ኢትዮጵያ ወደቡን መጠቀም እንድትጀምር የአገልግሎት ታሪፉ እንዲከለስ ሀሳብ እንደቀረበ የዘገበው ቢዝነስ ዴይሊ ነው።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

17/04/2024

ሀገሬ ዜና | ሚያዝያ 09 ፣ 2016 ዓ.ም | አዲስ አበባ | ሀገሬ ቴቪ

አጫጭር መረጃዎች

-ለጋሽ ሀገራት ለኢትዮጵያ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለመስጠት ቃል ገብተዋል
-በኢትዮጵያ የተስፋፉት ርሀብ እና በሽታዎች የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ ጥለዋል
-ኢትዮጵያን ተጠቃሚ የሚያደርግ ወደብ የታሪፍ ቅነሳ
-በናይጄሪያ የዋጋ ግሽበቱ ወደ 33 በመቶ ከፍ አለ
-የአሜሪካ እና ቻይና የጦር ሚኒስትሮች ከዓመት በኋላ ተወያዩ
-“ቦይንግ 200 ሚሊዮን ዶላር አሳጥቶኛል” ዩናይትድ አየር መንግድ

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016በኢትዮጵያ የተስፋፉት በሽታዎች እና ርሃብ የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ። በተለይም በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች ለ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

በኢትዮጵያ የተስፋፉት በሽታዎች እና ርሃብ የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ገለጸ።

በተለይም በትግራይ፣ አማራ፣ አፋር እና ኦሮሚያ ክልሎች ለዓመታት በዘለቁት ግጭቶች ምክንያት አብዛኛዎቹ የጤና ስርዓቶች እና መሰረተ ልማቶች ወድመዋል አልያም ተጎድተዋል።

በዚህም የሚሊዮኖች ህይወት አደጋ ላይ ነዉ ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በጽሁፍ ባስተላለፉት መግለጫ አሳዉቀዋል።

የኮሌራ፣ ኩፍኝ እና ወባን የመሳሰሉ ወረርሽኞች መከሰትም በኢትዮጵያ ያለዉን ችግር እናዳባባሰዉ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ የዓለም ጤና ድርጅት ከአጋሮቹ ጋር እየሰራ ቢገኝም ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ ለመቀጠል ፈታኝ መሆኑን ተናግረዋል።



በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

ሚያዚያ 9፣ 2016በኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያግዝ 630 ሚሊዮን ዶላር እንደሚለግሱ የተለያዩ ሀገራት ገልፀዋል። ይህ የተገለፀው በኢትዮጵያ በዩኬ እና በአሜሪካ አስተባባሪነት በ...
17/04/2024

ሚያዚያ 9፣ 2016

በኢትዮጵያ የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ የሚያግዝ 630 ሚሊዮን ዶላር እንደሚለግሱ የተለያዩ ሀገራት ገልፀዋል።

ይህ የተገለፀው በኢትዮጵያ በዩኬ እና በአሜሪካ አስተባባሪነት በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ ነው።

የኢትዮያ መንግሥት ቀዳሚ አጀንዳ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን መታደግ እንደኾነ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀሥላሴ በኤክስ ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

#ድጋፍ

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: http://facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): https://twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: http://instagram.com/hagerie_television…
ቴሌግራም: http://t.me/Hagerie_TeleVision…
ዩቲዩብ: http://youtube.com/hagerietv
ዌብሳይት: http://hagerie.tv

16/04/2024

አነጋጋሪው ኮከብ ኮል ፓልመር
ኮል ፓልመር ባለፉት 7 የፕሪሚየር ሊጉ ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ በስታምፎርድ ብሪጅ ግቦችን በማስቆጠር የመጀመርያው የቼልሲ ተጨዋች ሆኗል፡፡

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

16/04/2024

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2 ጨዋታ ቅጣት ተላልፎበታል
በሳውዲ ሱፐር ካፕ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ላይ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የ2 ጨዋታ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

16/04/2024

“ለአፍሪካዊያን ልዩ ፍቅር አለኝ” ግራኒት ዣካ
ከባየር ሌቨርኩሰን ጋር የቡንደስሊጋ ዋንጫ ያሳካው የቀድሞ የአርሰናል አማካይ ግራኒት ዣካ ለአፍሪካውያን ልዩ ፍቅር እንዳለው ተናግሯል፡፡

በማኅበራዊ መገናኛዎች ያግኙን

ፌስቡክ: facebook.com/hagerietv
ትዊተር (ኤክስ): twitter.com/HagerieT
ኢንስታግራም: instagram.com/hagerie_television
ቴሌግራም: t.me/Hagerie_TeleVision
ዩቲዩብ: youtube.com/hagerietv
ዌብሲይት: www.hagerie.tv

Address

HA BET Building, Comoros Street, Kebena
Addis Ababa
18506/1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሀገሬ ቴቪ- Hagerie TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሀገሬ ቴቪ- Hagerie TV:

Videos

Share

Category



You may also like