Kidist Birhan - ቅድስት ብርሀን

Kidist Birhan  -  ቅድስት ብርሀን “የአማራን ህልውና እስኪረጋገጥ ድረስ ከአማራ ፋኖ እና ልዩ ኃይል ጋር በመሆን እስከ ህይወቴ ፍጻሜ ድረስ እታገላለሁ፡፡“

05/03/2022
04/03/2022
Today    ,snapshot
02/03/2022

Today ,snapshot

በቅድሚያ የአክብሮት ሰላምታዬን እያቀረብኩ በሀገር ውስጥ እና በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ126ኛው ታላቁ የአድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልእ...
01/03/2022

በቅድሚያ የአክብሮት ሰላምታዬን እያቀረብኩ በሀገር ውስጥ እና በመላው አለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ126ኛው ታላቁ የአድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልእክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ኢትዮዽያዊ ስሜት ነው።

በዓሉ እንደቀድሞው ሁሉ ላለፉት 125 አመታት ይከበርበት በነበረው በገናናው ጀግና ዳግዊው አጤ ምንሊክ አደባባይ በኢትዮጵያ ውድ ልጆች በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ይውላል። ለዚህም አንዳች ጥርጥር የለውም።

መልካም የአድዋ የድል በዓል!

ፍቅር ያሸንፋል!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)

01/03/2022

በማርያም ስም ምሎ ለሀገር ነጻነት ሕዝቡን የጠራው ንጉሥ ሀውልቱ የቆመው ፒያሳ፣ለሀገር ነጻነት ወደ አድዋ የዘመተው ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ታቦቱ ያለው ፒያሳ፣ታዲያ ባለድሎቹ ንጉሱና ታቦቱ ያሉበትን አደባባይ ትቼ ወዴት ልሂድልህ???

21/02/2022
Ethio pretty
19/02/2022

Ethio pretty

  የሰራው የእጅ ስዕል አለክስ እጅህ ይባረክ  አመሰግንለው!!
11/02/2022

የሰራው የእጅ ስዕል አለክስ እጅህ ይባረክ አመሰግንለው!!

30/01/2022

ጀግናዬ

ቻናሉን ይቀላቀላሉ
29/01/2022

ቻናሉን ይቀላቀላሉ

ፋኖ፤ ፋኖነት!

ብዙ ጊዜ በተለይ አንዳንድ ከተሜዎች፣ ከተማ ቀመስ ነን የሚሉ እና የመንግሥት አካላት ፋኖን ዘራፊ፣ ሥራ ሲያጣ ፋኖን የተቀላቀለ የሚመስላቸው በርካቶች አሉ።

ፋኖነት ግን ጠመኔናቸውን እና ጋዋናቸውን እስከምጠው መምህርነቱ ይቆየኝ ብለው የከተቱ፣ እጃቸው ያለውን ነገር ሳይጨርሱ ለሀገር ቅድሚያ በመሥጠት የፈነኑ እንዳሉ መዘንጋት የለበትም።

መንግሥት ደግሞ ደጋግሞ ያስብበት!

እስኪ ሁላችሁም "ፋኖ ማለት እኔ ነኝ" በማለት ይሄን መንደር አጥለቅልቁት!

ፋኖ ማለት እኔ ነኝ!

28/01/2022
05/01/2022
፨ስምንት ቀን በዶባ ጫካ ወድቆ የተገኘው የደ/ማርቆሱ ፖሊስ ምስል ነው።ዶባ ላይ ቆስሎ ከስምንት ቀን በኀላ  በህይወት ያገኙት ከታች የሚታዩት አባታችን ናቸው።እኛም አካባቢውን አፅድተን ወደ ...
04/01/2022

፨ስምንት ቀን በዶባ ጫካ ወድቆ የተገኘው የደ/ማርቆሱ ፖሊስ ምስል ነው።ዶባ ላይ ቆስሎ ከስምንት ቀን በኀላ በህይወት ያገኙት ከታች የሚታዩት አባታችን ናቸው።እኛም አካባቢውን አፅድተን ወደ "ትክሴ" ስንጠጋ ቆስሎ አረመኔዎች እንዳይገድሉት ወደ መስጂድ ያስጠጉትን የፖሊስ አባል አግኝተን ወደ ቤተሰቦቹ ደ/ማርቆስ መጥቶ ህክምና እንዲያገኝ አድርገነዋል።

፨ለአካባቢው ማህበረሰብ እና ለአባታችን ምስጋና እያቀረብን ባለሃብቶቻችን ወንድማችንን እንድትረዱት ለመጠቆም እንወዳለን።

ትግላችን ይቀጥላል!!!
Like ,share 🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️🏃‍♂️

ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በመርጡለ ማርያም ከተማ ያሰለጠናቸውን የፋኖ አባላት አስመርቋል!በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እኔ እና ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ 50 አ...
03/01/2022

ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በመርጡለ ማርያም ከተማ ያሰለጠናቸውን የፋኖ አባላት አስመርቋል!

በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እኔ እና ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ 50 አለቃ መንበሩ ካሴን ጨምሮ ከተለያዩ ወረዳወች የመጡ የህዝባዊ ኃይሉ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በተጨማሪም ግምባር የነበሩ የከተማዋ እና የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ የህዝባዊ ኃይሉ አባላት የምረቃ ስነ ስርዓቱን ታድመዋል።

ግምባር ላይ ለተሰው የህዝባዊ ኃይል አባላት እና ከወገን ጦር ጋር ተሰልፈው ለወደቁ ሁሉም ሰማዕታት በፕሮግራሙ ላይ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ለስልጠናው እና ለምረቃው መሳካት ለተባበሩ ሁሉ ምስጋና ያቀርባል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕርዳር-ኢትዮጵያ

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል(ፋኖ) ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በሞጣ ከተማ በደማቅ ፕሮግራም አስመርቋል።https://youtu.be/32iMBKAo23A
03/01/2022

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል(ፋኖ) ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች በሞጣ ከተማ በደማቅ ፕሮግራም አስመርቋል።
https://youtu.be/32iMBKAo23A

Marda media Is Ethiopian multi-platform entertainment and media company ,Powered by its own proprietary technology. Marda media is the go-to source for tech,...

እንኳን  ደስ ያለን"የንጉሱ ሹሩባ  ወደ ነገስታቱ  ሀገር  ጎንደር " ተመልሷል !!!ያንተን  ህልም እናሳካለን ።
02/01/2022

እንኳን ደስ ያለን"የንጉሱ ሹሩባ ወደ ነገስታቱ ሀገር ጎንደር " ተመልሷል !!!
ያንተን ህልም እናሳካለን ።

ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በሞጣ ከተማ ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር ሰልጣኞች አስመርቋል!በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝባዊ ኃይሉ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ...
02/01/2022

ዛሬ ታህሳስ 24 ቀን 2014 ዓ.ም የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በሞጣ ከተማ ያሰለጠናቸውን 2ኛ ዙር ሰልጣኞች አስመርቋል!

በምርቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የህዝባዊ ኃይሉ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስረስ ማረ ዳምጤ፣ ተጠባባቂ ስራ አስፈፃሚ አባላችን አርበኛ ጥላሁን አበጀ፣ ከተለያዩ ወረዳወች የመጡ የህዝባዊ ኃይሉ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በተጨማሪም ግምባር የነበሩ የከተማዋ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች የምረቃ ስነ ስርዓቱን ታድመዋል።

ግምባር ላይ ለተሰው የህዝባዊ ኃይል አባላት እና ከወገን ጦር ጋር ተሰልፈው ለወደቁ ሁሉም ሰማዕታት በፕሮግራሙ ላይ የህሊና ፀሎት ተደርጓል።

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ለስልጠናው እና ለምረቃው መሳካት ለተባበሩ ሁሉ ምስጋና ያቀርባል።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

ታህሳስ 25 ቀን 2014 ዓ.ም
ባሕርዳር-ኢትዮጵያ

ቤተሰብ  ያልሆናችሁ ቤተሰብ  ሁኑ ፣ like  share....
01/01/2022

ቤተሰብ ያልሆናችሁ ቤተሰብ ሁኑ ፣ like share....

28/12/2021

Marda media Is Ethiopian multi-platform entertainment and media company ,Powered by its own proprietary technology. Marda media is the go-to source for tech,...

27/12/2021

በውጭ ሀገራት ለምትገኙ የትግላችን ደጋፊወች በሙሉ:-

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በውጭ ሀገራት ያሉ ወገኖቻችን በተደራጀ አኳኋን የትግላችን አካል የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት በውጭ ከሚገኘው ግዜያዊ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት የውጭ እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ላይ የሚሰራ ኮሚቴ ተቋቁሟል። ኮሚቴው ያወጣዉን መግለጫ እነሆ:-
----------------------------
ከአማራ ሕዝባዊ ሃይል ( ፋኖ ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ:-

ከዛሬ ሃምሳ ዓመታት በፊት ጀምሮ አማራው በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ካለው በጎ አስተዋፅኦ በተቃራኒ በስሁት የታሪክ ትንተና እና የፈጠራ ትርክት ላይ የተመሰረተ የስም ማጠልሽት ፕሮፖጋንዳ ተሰርቶበታል። በህወሃት-ኢህአዴግ መሪነት ለሃያ ሰባት ዓመታት መዋቅራዊ ቅርፅ እና ህገ-መንግስታዊ መሰረት ያገኘው ይህ ፀረ-አማራ ፕሮጀክት አማራው በማንነቱ ላይ ለተመሠረተ ጥቃት እንዲጋለጥ አድርጎታል። በዚህም ምክንያት በህዝባችን ላይ ያልተቋረጠ ጅምላ ግድያ፣ የዘር ማጥፋት እና ማፈናቀል ተካሂዷል። እየተካሄደም ነው። በተለይም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ክልሎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የዘር ማጥፋት ተፈጽሞበታል፤ እየተፈጸመበትም ነው።

እንዲሁም አማራ ክልል በሚባለው ግዛት ውስጥም በከሚሴ፣ በጎንደር፣ በሸዋሮቢትና በአጣየ ለተመሳሳይ ጥቃት እንዲጋለጥ ከመደረጉም በላይ አጣዬና ሸዋሮቢትን ጨምሮ የአማራ ከተሞች እንዲወድሙ ተደርገዋል።

ከጥቂት አመታት በፊት በከፍተኛ ሕዝባዊ ትግልና መስዋእትነት ከማዕከላዊ የመንግስት ሥልጣን የተወገደው ሕወሃት እንደገና አንሰራርቶ በቂ ዝግጅት እና ትጥቅ በሌለው በአማራ ክልል ህዝብ ላይ ባደረገው ወረራ ሰሜን ወሎን፣ ደቡብ ወሎን፣ ደቡብ ጎንደርን፣ ሰሜን ጎንደርን እና ሰሜን ሸዋን ለማውደምና ለመዝረፍ በቅቷል።

ወራሪው ኃይል የጅምላ ጭፍጨፋ ከማካሄዱም በላይ በእናቶቻችን ፣ በእህቶቻችን እና በልጆቻችን ላይ የመድፈር ተግባር ፈፅሟል። ቤተ-እምነቶችን ደፍሯል፤ ብዙ የታሪክ ቦታዎችን እንዳልነበሩ ለማድረግ ችሏል።

በቅርቡ የአማራ ክልል አስተዳደር ወራሪው ያደረሰውን ውድመት አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት ዩንቨርስቲዎችን ጨምሮ በትምህርት ተቋማት ላይ፣ በዋና ዋና ሆስፒታሎችና የጤና ጣቢያዎች ላይ እንዲሁም ሌሎች የእምነትና የልማት ተቋማት ላይ የደረሰው ውድመት የክልሉን ኢኮኖሚ ለበርካታ ዓመታት ወደኋላ እንደመለሰው ማመን ይቻላል።

ይህንን የአማራ መከራ ለመቀልበስ ግንባር ቀደም በመሆን ከወራሪው ጋር በመፋለም ከፍተኛ መስዋእትነት በየቀኑ በመክፈል ላይ ላሉት የአማራ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ዛሬም እንደትናንትናው ከፍተኛ አድናቆት ያለን መሆኑን እንገልፃለን።

ትናንት ደብረሲና ደርሶ የነበረው የሕወሃት ወራሪ ኃይል በወገን ጦር ተጋድሎ ዛሬ ወደመጣበት እየተመለሰ ቢሆንም፤ ገና ያልተለቀቁ በጎንደርና በወሎ ያሉ የአማራው አጽመ እርስቶች አሉ።

በወያኔ የተተከለው የአፓርታይድ ሥርአት እስካልተወገደ፣ በተለይም የወያኔ የጥፋትና ጥላቻ ድርጅት ከኢትዮጵያ ምድር ሙሉ በሙሉ እስካልጠፋ ድረስ የአማራ ሕዝብ ሌላ አውዳሚና ህልውናውን
አደጋ ላይ የሚጥል ተደጋጋሚ ወረራ እና ፖለቲካዊ ክህደት እንደማይፈፅልምበት ማንም እርግጠኛ መሆን አይችልም። ይልቁንም በግራም በቀኝም ካሉ ጠላቶቻችን ባህሪ መረዳት የሚቻለው ህዝባችን ዛሬም ከአደጋ የፀዳ የፖለቲካ አየር ለመተነፈስ የሚችልበት ግዜ ያልደረሰ ስለመሆኑ ብቻ ነው።

ስለሆነም አማራው ከምንጊዜውም በበለጠ ጠንክሮ ከመደራጀት እና ከመሰልጠን እንዲሁም ከትንሽ እስከትልቅ ድረስ የጠላቶቻችንን ቀመር በጥልቀት እየመረመረ እንደ ህዝብ ለመኖር፣ እንደ ሀገር ለመቀጠል እራስን ከማዘጋጀት ውጭ የተሻለ አማራጭ የለውም።

በዚህ ጦርነት ውስጥ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ያለውን የፋኖ ገድል ስንመለከት መደራጀት እና መሰልጠን የህዝባችንን ህልውና በማስከበር ረገድ ያለውን የማይተካ ሚና በአግባቡ መገንዘብ እንችላለን።

ይህ ኃይል የስንቅ፣ የትጥቅና የትራንስፖርት ችግር
ቢኖርበትም በዚህ ጦርነት በሁሉም አውደ ውጊያወች ከአማራው ሕዝብ ጠላት ጋር ተናንቋል፤ እየተናነቀም ይገኛል። ፋኖ በባዶ እግሩ፣ በባዶ ሆዱ፣ ያለበቂ አልባሳት፣ ያለበቂ ትጥቅ፣ አጋዥ ሕክምና ሳይኖረው፣ በራሱ ወጭ ሥራውን፣ ቤተሰቡን ትቶ ለወገኑ እየተዋደቀ ያለ የነፃነታችን ቀንዲል ነው።

ስለሆነም ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበትን የአማራውን ህልውና ለማስከበር ቆመናል የሚሉ በውጭ ሀገር ያሉ ድርጅቶችን ጨምሮ አቅሙ እና ፍላጎቱ ያለን ሁሉ ይህንን ኃይል በሃሳብ፣ በቁሳቁስ፣ በገንዘብ እና በሞራል የመደገፍ የውዴታ ግዴታ አለብን።

ይህን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በተደራጀ እና በተቀናጀ መንገድ ለመተግበር ይቻል ዘንድ ተጠሪነቱ አገርቤት ላለው ለዋናው ድርጅት ለአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የሆነ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ተቋቁሟል።

በዚህም መሠረት ኮሚቴው የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአማራ ህዝባዊ ኃይል የውጭ ግንኙነት እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴዎች የሚመራ አካል ለማቋቋም የተጠራ ጠቅላላ ምክር ቤት ታህሣሥ 3 ቀን 2014 ዓ.ም (December 12, 2021) የምስረታ ጉባኤዉን አድርጎ 13 የስራ አስፈፃሚ አባላትን መርጧል።

የሰባት የሥራ ዘርፍ መሪዎችን እና አባላትን ያካተተው ይህ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለታላቅ አላማ ታላቅ። ሀላፊነትን ተቀብሎ ስራ ጀምሯል። በሥራ አስፈጻሚ አጀንዳ ቀራጭነት የአማራውን የህልውና ትግል በእውቀትና በፖሊሲ ዝግጅቶች የሚያግዝ ምሁራን የተሰባሰቡበት የጥናት እና አማካሪ ቦርድ ቀደም ብሎ ተቋቁሞ ሲሰራ የቆየ ሲሆን፣ በቀጣይነትም እራሱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ምክር ቤቱ ወስኗል። የፋይናንስ እና የሚዲያ ቅስቀሳ ኮሚቴውዎችም በሥራ አስፈጻሚው ስር ተካትተው እንዲቀጥሉ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል።

ይህ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል የውጭ ጉዳይ ኮሚቴውም በተዋረድ መዋቅር ዘርግቶ መሥራት እንዲችል በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካ በስፋት የማደራጀት ሥራ ያከናወናል።

ስለዚህ በውጭው ዓለም የምትኖሩ የአማራ ወገኖቻችን እና የትግላችን ደጋፊዎች በየውጭ ጉዳይ ኮሚቴው በየእርከኑ ለሚፈጥራቸው አካላት በአባልነት እንድትሳተፉ፣ በገንዘብ፣ በእውቀት እና በሞራል ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ጎን እንድትቆሙ የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን።

ከአማራ ህዝባዊ ኃይል ( ፋኖ ) ጎን በመሰለፍ የአማራን ህልውና እናረጋግጣለን!!!

አማራ በረጅሙ ያሸንፋል!!!
ሰሜን አሜሪካ

 #በህይወት ላቆየን ለድልም ላበቃን የአባቶቻችን አምላክ ለሆነው  ለድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይግባው።፨የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች በሙ...
18/12/2021

#በህይወት ላቆየን ለድልም ላበቃን የአባቶቻችን አምላክ ለሆነው ለድንግል ማርያም ልጅ እየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይግባው።

፨የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) በተንቀሳቀሰባቸው አካባቢዎች በሙሉ ለአማራ ህዝብ የቆመ መሆኑን አባሎቹን በመገበር ጭምር አረጋግጧል።

#ለአማራ ህዝብ መስዋዕት በመሆን ክብሩ ከፍ እንዲል እና አንገቱን በኩራት ቀና እንዲያደርግ "ፋኖ"ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጓል።በዚህም ኩራት ይሰማናል።

፨ጦርነቱ በድል የሚጠናቀቀው በሁሉም አቅጣጫ የአማራ ህዝብ ጠላት እና የኢትዮጵያ ህዝብ ካንሰር ሲቆረጥ በመሆኑ ማንኛውም ዜጋ እንዳይዘናጋ እያሳሰብን፤"በሰሞኑ ጦርነት ያገኘነውን ልምድ አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል።"

ትግላችን ይቀጥላል!!!
መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳችሁ ፔጁን like and share ያድርጉ ፣ለጓደኞችዎም የጋሩ።

16/12/2021

Marda media Is Ethiopian multi-platform entertainment and media company ,Powered by its own proprietary technology. Marda media is the go-to source for tech,...

ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ካምፕ እየከተተ ያለው የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) በከፊል!//አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ //
28/10/2021

ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ካምፕ እየከተተ ያለው የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) በከፊል!

//አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ //

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ)!የተለያዩ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ በተለያየ መንገድ በጠየቃችሁት መሰረት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሒሳብ ተከፍቷል። በመሆኑም ከስር የተያያዘውን የሂሳብ ቁጥ...
25/10/2021

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ)!

የተለያዩ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ በተለያየ መንገድ በጠየቃችሁት መሰረት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሒሳብ ተከፍቷል።

በመሆኑም ከስር የተያያዘውን የሂሳብ ቁጥር መጠቀም የምትችሉ መሆኑን ሕዝባዊ ኃይሉ ያሳውቃል።

//አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

24/10/2021
23/10/2021

#ቀረርቶ Official marda media Is Ethiopian multi-platform entertainment and media company ,Powered by its own proprietary technology. marda...

Address

Bahir Dar
Addis Ababa
6000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kidist Birhan - ቅድስት ብርሀን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category



You may also like