አሴኮ

አሴኮ Just about love Love is more than money

02/12/2022

📌ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለብን 10 ወሳኝ ነገሮች

✔ 1ኛ :- ያለንበትን #ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልክለትን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላኪያዋን ከፍተን location የሚለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል ::

✔ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን ማዘጋጀት ይቻላል መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን እንነካለን ከዛ privacy and security የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::

✔ 3ኛ:- እንዴት ቴሌግራም ማድረግ ይቻላል
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የሚለዉን እንነካለን ከዛ
when using mobile data -OF-አድርጉት ::

✔4ኛ :- የላክነዉን message ከደረሰ በኃላ ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የላክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የሚለውን Also delete receive የሚለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል ::

5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ
በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት

✅6ኛ :- በተለይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን #በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከሚሰጠን የመልክ ምርጫ የፈለግነዉን እንመርጣለን ::

✔7ኛ :- ቴሌግራም ያሉ ጽሁፎች አልነበብ እያሎት ተቸግረዋል ማለት ፊደሎቹ አንሰዉ ለዓይን አልታይ ካለ ማድረግ ይቻላል እንዴት ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፈለግነዉን ያህል ትልቅ ማድረግ ይቻላል ::

✔8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም #ቻናል መክፈት እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን
ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የሚለውን ነክተን create new channel የሚለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፈለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን ::

✔9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም #ግሩፕ እንከፍታለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የሚለውን እንነካለን ከዛ create new group የሚለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፈለግነዉን የግሩፕ ስም እናስገባለን ::

✔10ኛ :- እንዴት አድርገን መቀየር እንችላለን ?
በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ set profile photo የሚለውን በመንካት የፈለግነዉን ፎቶ መቀየር ይቻላል ።

ከወደዱት ለወዳጅዎ #ያጋሩ!

21/11/2022
  የመክፈቻ የቁርአን አንቀፅ             ⬇️«እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላ...
20/11/2022

የመክፈቻ የቁርአን አንቀፅ
⬇️
«እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡»ቁርኣን 49:13

{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقۡنَـٰكُم مِّن ذَكَرࣲ وَأُنثَىٰ وَجَعَلۡنَـٰكُمۡ شُعُوبࣰا وَقَبَاۤىِٕلَ لِتَعَارَفُوۤا۟ۚ إِنَّ أَكۡرَمَكُمۡ عِندَ ٱللَّهِ أَتۡقَىٰكُمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِیمٌ خَبِیرࣱ }
[Surah Al-Hujurât: 13]

07/09/2022

ስልኬ ሊጠለፍ ይችላል የሚል ስጋት አለብዎ?

የሚያዋሩበት የእጅ ስልክዎ በተለያዩ ምክንያቶች ሊጠለፍብኝ ይችላል የሚል ስጋት ካለብዎ የሚከተሉትን ቁልፎች ተጭነው ይደውሉና ያረጋግጡ።

* #21 # ብለው ሲደውሉ
➊. Not forwarding የሚል ምላሽ ከሰጠዎ ስልክዎ አልተጠለፈም ከስጋት ነጻ ነው ማለት ነው።
➋. Forwarding የሚል ምላሽ ከሰጠዎ ግን በእርግጠኛነት ተጠልፎብዎታል ማለት ነው።
➋. የተጠለፈበዎትን ስልክ ለማስቆም እንዲሁም ወደፊት እንዳይጠለፍ ለማድረግ # #002 #ብለው ሲደውሉ call forwarding all erased successful ይልዎታል። በዚህ ሰዓት ከስጋት ቀጠና ወጡ ማለት ነው።
ነገር ግን ይህ ኮድ ሁሉም ስልኮች ላይ ይሰራል ማለት ላይሆን ይችላል ብቻ ይሞክሩት።
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬📌Share📌▬▬▬▬▬

በህይወት ያሉ እውነታወች
05/09/2022

በህይወት ያሉ እውነታወች

የቀድሞው የዙምባቤ ፕሬዚዳንት  #ሮበርት ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ፦ "የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት አስገራሚ ውጤቶች አሉት ።" ካሉ በኋላአንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜና ጎበዝ ...
04/09/2022

የቀድሞው የዙምባቤ ፕሬዚዳንት #ሮበርት ሙጋቤ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር ፦ "የአፍሪካ የትምህርት ስርዓት አስገራሚ ውጤቶች አሉት ።" ካሉ በኋላ

አንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜና ጎበዝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አምጥተው #ኢንጂነሪንግና #ሜዲሲን እንዲማሩ እድል ያገኛሉ ።

ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ #ህግና #ማኔጅመንት ነገር ተምረው አንደኛ ደረጃዎቹን ያስተዳድሯቸዋል ።

ዝቅ ብለው በሶስተኛ ደረጃ የሚገኙት ተማሪዎች ደግሞ #ፖለቲካ ውስጥ ይገቡና አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉትን ከላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ ።

በትምህርት ውዳቂዎች ደግሞ #ፖሊስና #ወታደር ይሆናሉ ። እነዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችን ይቆጣጠራሉ ደስ ያላላቸውን ፖለቲከኛ ደግሞ እስከ መግደል ድረስ ይደርሳሉ ።

ከሁሉም ከሁሉም ግን ምርጡ ጭራሽ ክላስም ሆነ ትምህርት ቤትም ገብቶ የማያውቀው ሰው ደግሞ #ነብይና #ጠንቋይ ይሆናል ። ይሄን ደግሞ ሁሉም ይከተሉታል ። ብለው ነበር ።

እኛስ በሃገራችን ያየነው ይህንን ነው ወይስ ሌላውን ነው ?
═════════❁✿❁ ═════════ የተለያዩ አስተማሪ መረጃወችን ከፈለጉ......የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ....

01/09/2022

1⃣ ምንም ነገር ዘላለማዊ አይደለም ፤ ሌላው ቀርቶ ችግሮቻችንም ጊዜያዊ ናቸው ።
2⃣ በዝናብ ውስጥ መሄድ እወዳለሁ ፣ ምክንያቱም ማንም እንባዬን አያይብኝምና ።
3⃣ በህይወታችን ታላቁ የባከነው ቀን ሳንስቅ የዋልንበት ቀን ነው ።
4⃣ በአለም ላይ ምርጥ ስድስት ዶክተሮች:-
#⃣ ፀሀይ
#⃣ እረፍት
#⃣ የሰውነት እንቅስቃሴ
#⃣ አመጋገብ
#⃣ የራስ-ክብር
#⃣ ጓደኞች

👍እነዚህን ጠብቃቸውና ህይወትህን አስደሳች አድርገው ።

👉ጨረቃን ካየህ ፥ የተፈጥሮን ውበት ታያለህ ፣
👉ፀሀይንም ካየህ፣ የፈጣሪን ኃይል ታያለህ ፣
👉 መስተዋት ካየህ ፣ የፈጣሪን ትልቅ ጥበብና ፍጡር ታያለህ ስለዚህ በፈጣሪህ እመን ።

✅✅ እኛ ሁላችንም ቱሪስቶች ነን ፣ የጉዞ ወኪላችን ፈጣሪ ነው ። እሱም የመጓጓዣ ቆይታችንን ፣ የመስተንግዶ ሁኔታችንንና መዳረሻችንን ሁሉ የሚያውቀው እመነውና በህይወት ደስተኛ ሁን!! ህይወት ጉዞናት እናም ዛሬን በአግባቡ ኑራት ነገ ላትኖር ትችላለህና!! የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን!!!
═════════❁✿❁ ═════════

27/08/2022

እስልምና በልብስ ብቻ አደለም

22/08/2022

Follow and like the page

17/08/2022

እስልካችሁ ላይ 3 ማወቅ ያለባችሁ ነገሮች

11/08/2022

የምንጠቀማቸው ስልኮች አይናችንን እንዳይጎዱን ይሄን ሲስተም እንጠቀም

በዛሬው እለት በልጓማ ከተማ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከባድ ዝናብ ጥሎ ሰወችን አፈናቅሏል በንብረት ላይም ከባድ ኪሳራ አድርሷ በከተማዋ ምሽት ላይ በጣለው ዝና ምክንያት የእርዳታ ጥሪ ሲተኮስ ...
04/08/2022

በዛሬው እለት በልጓማ ከተማ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ከባድ ዝናብ ጥሎ ሰወችን አፈናቅሏል በንብረት ላይም ከባድ ኪሳራ አድርሷ በከተማዋ ምሽት ላይ በጣለው ዝና ምክንያት የእርዳታ ጥሪ ሲተኮስ ነው ያመሸው።ህብረተሰቡ ወጥቶ በተለያየ አካባቢ ጎርፍ የገባባቸውን ቤቶች ጎርፉን ለመከላከል ቢሞክርም ካቅም በላይ ሆኖ ነበር። በከተማዋ መስመሮች ላይ የበረዶ ክምችት አለ

30/07/2022

መልካምነት ለራስ ነው

27/07/2022

አትሌት ጎይቶም ብትጨፍሪም ያምርብሻል

25/07/2022

ይመችሽ አቦ ጀግና

25/07/2022

እስኪ ዛሬ ደሞ እንሳቅ

25/07/2022

አሸንፈናል

24/07/2022

5000 ሜትር የሴቶች ኢትዮጵያኖች ድል በአሜሪካ 2022

እንኳን ደስ አለሽ ሀገሬ💚💛❤✅|| በኦሪገን እየተካሄደ የሚገኘው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በ5000 ሜትር የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ በጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ እና በዳዊት ስዩም ነሀስ ማግኘ...
24/07/2022

እንኳን ደስ አለሽ ሀገሬ💚💛❤

✅|| በኦሪገን እየተካሄደ የሚገኘው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በ5000 ሜትር የሴቶች ውድድር ኢትዮጵያ በጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ እና በዳዊት ስዩም ነሀስ ማግኘት ችለናል።

✅|| በዛሬው ሩጫው በጣም ከፍተኛ የሆነ የቡድን ስራ የታየበት እና ከፍተኛ ፉክክር የነበረበት ከባድ ውድድርም ነበር።

✅|| ኢትዮጵያ በኦሪገን እየተካሄደ የሚገኘው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 4ኛ ወርቅ ማግኘት ችለናል። 3 ወርቅ በሴቶች የተገኘ ሲሆን አንድ ወርቅ ደግሞ በወንዶች የተገኘ ነው።

✅|| በአምስት ሺ እና አስር ሺ ከፍተኛ ግምት አግኝታ የነበረችው ትውልደ ኢትዮያዊት በዜግነት ኔዘርላንዳዊት ሲፋን ሀሰን ምንም ሜዳሊያ ውስጥ ሳትገባ ውድድርዋን አጠናቃለች።

በ ጉግል ፎቶስ (Google Photos) - የእድሜ ልክ፣ ገደብ የለሽ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ! በካሜራዎ ላይ አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ አፍታዎችን ለመያዝ ሞክረዉ ዝቅተኛ ማከማቻ ስላልዎት ...
22/07/2022

በ ጉግል ፎቶስ (Google Photos) - የእድሜ ልክ፣ ገደብ የለሽ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ!

በካሜራዎ ላይ አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ አፍታዎችን ለመያዝ ሞክረዉ ዝቅተኛ ማከማቻ ስላልዎት ማንሳት አይችሉም የሚል ችግር አልገጠምዎትም? ጉግል ፎቶስ፣ ለዚህ ችግር ሁነኛ መፍትሄ የሚሆን ያልተገደበ፣ የእድሜ ልክ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ አገልግሎት ይዞ ብቅ ብሏል፡፡

ጉግል ለፎቶ(እስከ 16 ሜጋፒክስል) እና ቪድዮ(እስከ 1080ፒ ባለ Full HD ድረስ) ያለገደብ ለእድሜ ልክ መጫን እና ማስቀመጥ እንደሚቻል አስታዉቋል። የ ጉግል ፎቶስ መተግበሪያ በ Android, iOS, Mac እና Windows ጨምሮ በሌሎቸም ፕላትፎርሞች ይገኛል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክዎ ላይ ይህን መተግበሪያ በሚከፍቱበት ጊዜ, ለመጠባበቂያዎቹ (backup) የሚጠቀሙበትን የጉግል መለያዎን (account/email) ይጠይቅዎታል። አንዴ ከተዋቀረ እና ከተስተካከለ በኋላ ስልክዎ ከ WiFi ጋር ሲገናኝ ሁሉንም ፎቶዎች እና ቪድዮዎች መጠባበቂያ ላይ ያስቀምጣል። መጠባበቂያዉ ላይ አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ ከስልክዎት ላይ ማጥፋት እና የስልክዎን ማከማቻ መጠን ማሳደግ ይችላሉ።

በተጨማሪም፦
👉 ሁሉንም ፎቶዎችዎን እና ቪድዮዎችዎን ለመጠባበቂያ በሰጣችሁት መለያዎ ሲገቡ ከማንኛውም ኮምፒተር፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ላይ ወይም ብሮውሰር (photos.google.com በመክፈት) ማግኘት እና ማየት ይችላሉ።
👉 ፎቶዎትን መከርከም (cut)፣ ማሽከርከር (rotate) ወይም ቀለሙን (color setting) ማስተካከል ካስፈለገዎት መሰረታዊ የፎቶ አርትዖት በመተግበሪያው ውስጥ ራሱ ቀርቧል።
👉 በኮምፒተርዎ ላይ የ Mac ወይም Windows መተግበሪያን ማውረድ እና በጉግል ፎቶስ ላይ በጠቅላላ አለኝ የሚሏቸውን ፎቶዎች ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ በሚፈልጓቸው ጊዜም ከጉግል ፎቶስ ድህረ ገጽ (photos.google.com) ላይ በቀላሉ ሊያገኟቸው ይችላሉ።

ይህን ከማድረግዎ አስቀድመዉ ግን ለመለያዎ በቀላሉ ሊገመት የማይችል አስተማማኝ የይለፍ ቃል መስጠት እንዳለብዎት እንመክራለን፡፡ እናም ይሄንን መንገድ በመጠቀም ስለስልክዎ ማከማቻ መጠን እና ስልክዎ ሲጠፋ አብረዉ ስለሚጠፉት ማስታወሻ ፎቶዎች መጨነቅ ያቁሙ።

Google Photos is the home for all your photos and videos, automatically organized and easy to share.

22/07/2022

ፌስቡክዎ መጠለፉን ለማወቅና ከጠለፋ እራስዎን ያውጡ!
1. Setting and Privacy ይግቡ
2. Setting ይንኩ
3. Security
4. Security and login
5. Where you are logged in ከዚህ ውስጥ በምን ሞባይል ወይም ኮምፒውተር፣ የት ቦታና ሀገር፣ በምን ብራውዘር፣ ወይም አፕልኬሽን፣ መቼ ቀን ከዚህ በፊት እንደከፈታችሁት ያሳያችኋል። ነገር ግን ደግሞ Active now በሚል በአረንጓዴ የተጻፈው አሁን የከፈታችሁበትን ይነግራችኋል። ከዚህ በታች የተዘረዘረውን Session ስትመለከቱ የናንተ ካልሆነና የሚያጠራጥር ከሆነ ከታች ላይ Logout All Sessions የሚለውን በመጫን Logout የሚለውን በመጫን እራስዎን ከጠላፋ ማውጣት ይኖርብዎታል።
የተጠለፈ መሆኑ ከተጠራጥሩ በፍጥነት Password መቀየር ይኖርብዎታል።
ከአምስተኛው ተራ ቁጥር በመቀጠል ካለው Step Where you are logged in በታች Login ከሚለው በታች Change password የሚለውን በመጫን current password እና New password በማስገባት Save Changes የሚለውን ይጫኑ።

✅ በተጨማሪም Two factor Authentication On ቢያደርጉት ጥሩ ነው። ይህ On መሆኑ ምንም እንኳን የፊስቡክ አካውንትዎን Password ሰው ቢያውቅብዎ በስልካችሁ የሚላከውን Security code እስካላወቁ ድረስ መክፈትና መጠቀም አይችሉም። ስለዚህ On በማድረግ እንድትጠቀሙ እመክራለሁ። በፈለጋችሁ ሰአት Off ማድረግ የምትችሁ ይሆናል!

እራስዎን ከጠላፊዎች ይከላከሉ!

22/07/2022

Facts about wollo WolloPedia

* በአማራ ክልል አካባቢወች ውስጥ የኤሌክትሪክና ስልክ አገልግሎትን ቀድሞ በማግኘት ወሎ ቀዳሚው ነው። #ደሴ ከተማ ከክልሉ ከተሞች ውስጥ ስልክ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት በማግኘት ቀዳሚዋ ነች።

* ባቲ፣ ትዝታ፣ አንቺ ሆዬ እና አምባሰል የሚባሉት አራቱ የኢትዮጲያ የሙዚቃ ቅኝቶች መሰረታቸው ወሎ ነው (ሌሎች ኢትዮጲያውያን ወገኖቻችን ደስ እንዲሰኙባቸው ምክንያት መሆናችን ደስ አሰኝቶናል)።

* በአማራ ክልል ውስጥ ቀዳሚው ዘመናዊ ትምህርት ቤት የተጀመረው ወሎ ደሴ ላይ ነው።

* በኢትዮጲያ እስልምና ታሪክ ውስጥ ስማቸው ገናና ሆኖ የሚታወቁት እነደ ዳና፣ ጥሩ ሲና፣ ሾንኬ፣ ጫሊ፣ ገታ፣ ደገር ወዘተ አይነት መድረሳወች የሚገኙት ወሎ ውስጥ ነው።

* ኢትዮጲያዊ የሆነው መንዙማ የተጀመረው በወሎ ነው

* በአማራ ክልል ከሚገኙ ጥንታዊ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ እጅግ ጥንታዊ የሆነችው እና ቀደምቷ ተድባበ ማርያም የምትገኘው በወሎ ነው።

* አማራ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ከ1000 ዓመት በላይ እድሜ ካስቆጠሩ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ በግርድፉ ከ70% በላይ የሚሆኑት የሚገኙት በወሎ ውስጥ ነው።

* የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ አማኞች በታላቅ ክብር ከተለያየ የኢትዮጲያ ክፍልና ከአለም ተሰባስበው ለሃይማኖታዊ የሚታደሙባቸው ግሸን ደብረ ከርቤ እና ቅዱስ ላሊበላ የሚገኙት በወሎ ነው።

* ኢትዮጲያን ለዘመናት የገዟት የዛጉዌ፣ የሰሎሞናዊ፣ የወረሴህ እና የማመዶች ሥርወ መንግስታት የተመሰረቱት በወሎ ነው። መራ ተክለ ሃይማኖት፣ ዓጤ ይኩኖ አምላክ ፣ አባ ሴሩ ጓንጉል፣ አባ ጂቦ መሀመድ አሊ የተሰኙት የእነዚህ ሥርወ መንግስታት መስራቾች ከዚሁ ከወሎ ምድር የተፈጠሩ ናቸው።

* የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የአገው እና የአርጎባ ህዝቦች በወሎ ውስጥ ይገኛሉ ።

* በዘመናዊ የኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ የወሎየወች ከፍታ የሚባለው አቤቶ እያሱ ስልጣን ሲወርሱ አባታቸው ሚካኤል ዓሊ ንጉሠ ጽዮን ተብለው የወሎ፣ የጎንደር ፣ የትግሬና የጎጃም የበላይ ገዥ ሲባሉ ነው።

* ከአማራ ክልል አካባቢወች ግንባር ቀደም በመሆን የአክስዮን ማህበር ያቋቋሙት ወሎየወች ናቸው። የወሎ ፈረስ ትራንስፖርት አክስዮን ማህበርን በእነ ፊታውራሪ አመዴ ለማ አማካኝነት በግንባር ቀደምነት ተመስርቷል።

* ወሎ የበርካታ ማዕድኖች መገኛ እንደሆነ ይነገራል። የብረት፣ የድንጋይ ክሰል ፣ የነዳጅ ፣ የወርቅ ፣ የከበሩ ድንጊያወችና ላይም ስቶን ወዘተ እምቅ ሀብት አለው።

* የተከዜ ወንዝ መነሻ ወሎ ውስጥ ነው። ለአባይ ገባር የሆነው ታላቁ በሽሎ እና የአዋሽ ገባር የሆነው ቦርከናም ከወሎ የተለያዩ አካባቢወች የሚነሱ ናቸው።

Address

Addis Ababa

Telephone

+251910004223

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አሴኮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አሴኮ:

Videos

Share

Category



You may also like