Ethio Press

Ethio Press Official FaceBook page of Ethio Press

ሐሰተኛ መረጃበአማራ ክልል የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ይመለከታል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው  ሰሞኑን በአማራ ክልል ‘የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታትን ይመለከታል’ በሚል ሐሰ...
24/04/2024

ሐሰተኛ መረጃ

በአማራ ክልል የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታት ይመለከታል በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ነው

ሰሞኑን በአማራ ክልል ‘የሚልሻ አባላትን ትጥቅ ማስፈታትን ይመለከታል’ በሚል ሐሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተጠቆመ።

ለሁሉም ዞንና ከተማ አስተዳደሮች በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ደብዳቤ የተጻፈ በማስመሰል የወጣው መረጃ ፍጹም ሐሰት መሆኑን ክልሉ አረጋግጧል።
ድርጊቱ የተፈጸመው በክልሉ የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ ያለመ እንደሆነም ተነግሯል።

በዚህም በክልሉ ያሉ የጸጥታ ኃይሎች ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ተቀናጅተው እያመጡት ያለው ውጤት ኪሳራ ያደረሰባቸው ኃይሎች በሚልሻውና ህብረተሰቡ ውስጥ መደናገርን ለመፍጠር አልመው የፈጸሙት እኩይ ድርጊት መሆኑ ተገልጿል።

 #ትዝብት"ረሃብን በሪሞት- አዲሱ ፈጠራ!?" 🤔ረሃብን ከፖለቲካ ፍጆታነት አልፎ  #በሪሞት መቆጣጠር የተቻለበትን ፈጠራ ከሰሞኑ ከወደ ትግራይ እያየን ነዉ፡፡ ከወራት በፊት የክልሉ ጊዜያዊ አ...
17/04/2024

#ትዝብት
"ረሃብን በሪሞት- አዲሱ ፈጠራ!?" 🤔

ረሃብን ከፖለቲካ ፍጆታነት አልፎ #በሪሞት መቆጣጠር የተቻለበትን ፈጠራ ከሰሞኑ ከወደ ትግራይ እያየን ነዉ፡፡

ከወራት በፊት የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕ/ንት ጨምሮ በርካታ ወሬ አቀባይ አፎቻቸው በትግራይ ክልል ከ 1977ዓ.ም የከፋ #ረሃብ እንዳለ ለአለም ሚዲያዎች መረጃ ሲያቀባብሉ አስተዉለናል።

በሚባለዉ ደረጃ ረሃብ ስለመኖሩ ምንም ማስረጃ በሌለበት ከፍተኛ ዘመቻ የተካሄደ ቢሆንም ነገሩ ብዙም ሳይቆይ ከረሃብ ጩሀት ወደ ጥይት ጩሀት ተቀይሯል፡፡
እንግዲህ... ከወደ ህወሃት መንደር ረሃብ ሲፈለግ የሚመጣ ሳይፈለግ በቀላሉ በሪሞት የሚጠፋ ነው ማለት ነው?
ሪሞቱም በህወሃት እጅ ነው ያለው ብለን እንድንጠረጥር አድርጎናል።
ህወሃት ይቺን የርሃብ ሪሞት በአእምሮ ንብረት ፈጠራ ስራ አስመዝግቧት ይሆን?! 😂

#ትዝብት 🤔
ህዝቤ ረሃብ ዉስጥ ነው ያለ ክልል ገንዘብ አውጥቶ መግዛት ያለበት ስንዴ ወይስ ጥይት?

ህወሓት አሁንም የትግራይን ህዝብ መከራ ለማስቀጠል የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚያፈርሱ ትንኮሳዎችን እያደረገች ነው።

የፕሪቶሪያዉ ስምምነት አከራካሪ ቦታዎችን በሚመለከት
# የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ #ቀያቸው መመለስ እና አካባቢዎቹን በመከላከያ ሰራዊት ስር ማስገባት
# ለተፈናቃዮች ከትራንስፖርት እስከ ስንቅ ድረስ እንዲሁም ወደ መደበኛ ኑሮ #የሚመለሱበት ሁኔታን ማመቻቸት
# ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸዉ ከተመለሱና መደበኛ ህይወታቸዉን መምራት ከጀመሩ በኋላ በማካሄድ እራሳቸዉን የሚያስተዳድሩበትን ሁኔታ መፍጠር የሚሉት የሚጠቀሱ ናቸዉ ፡፡

ነገር ግን ከወደ ትግራይ የምንሰማዉ ነገር ለትግራይ ተወላጅ እና ህዝብ እጅግ አስጊ ነገር ነዉ፡፡

የህወሃት ስብስብ ይህንን ሁሉ የሰላም አማራጭ ረግጦ "ጠብ ያለሽ በዳቦ" የሚያስብለው የጦርነት ሱስ እንጂ ሌላ ምን ይባላል?

በትግራይ የሚነፍሰዉን የሰላም አየር አደፍርሶ ከጎረቤት ክልሎች ጋር የሚያናክሰውን ይህንን የጦርነት አዙሪት የተጠናወተውን ስብስብ ከጫንቃው ላይ ካላወረደ የትግራይ ህዝብ የሰላም እንቅልፍ እንደራቀው ይቀራል!

ድህነት የተጫነው ሕዝብ ይዘን በላዩ ላይ ጦርነት ከጨመርንበት የክፍለ ዘመኑ ማሰብ የተሳነን ሰዎች ሆነናል ማለት ነው። ትልቁ ማሰላሰል የሚገባን ቁምነገር ከርሃብ እንዴት መውጣት አለብን የሚለ...
13/04/2024

ድህነት የተጫነው ሕዝብ ይዘን በላዩ ላይ ጦርነት ከጨመርንበት የክፍለ ዘመኑ ማሰብ የተሳነን ሰዎች ሆነናል ማለት ነው።

ትልቁ ማሰላሰል የሚገባን ቁምነገር ከርሃብ እንዴት መውጣት አለብን የሚለው ጉዳይ ላይ ነበር። እኛ ግን በተቃራኒው ርሃብን ሊያባብስ፤ ድህነትን ሊያስፋፋ የሚችለውን ጦርነት መርጠናል።

ከቦታ ቦታ ተዘዋውረን ባለመነገዳችን፤ አርሰን ባለማዝመራችን፤ መማር ባለብን ጊዜ በግጭት ውስጥ በመሆናችን፤ ... ድህነት እየተስፋፋብን ይገኛል።

ስለሆነም ከርሃብ፣ ከድህነትና ጉስቁልና ለመውጣት የሚያስፈልገን ዘላቂ ሰላም ነው። ሰላም ያስፈልገናል።

ሰላም ለሕዝባችን❗️

ቢሊዮኖችን ለመመገብ የሚችል የሚታረስ መሬት አለን። ሁኖም ግን ለምናርሰው መሬት የተቀየረ አስተሳሰብና አስተሳሰቡን መሬት ላይ የሚያወርድ የተለወጠ የሰው ሃይል ያስፈልገናል።በዚህ ጊዜ የአማራ...
13/04/2024

ቢሊዮኖችን ለመመገብ የሚችል የሚታረስ መሬት አለን። ሁኖም ግን ለምናርሰው መሬት የተቀየረ አስተሳሰብና አስተሳሰቡን መሬት ላይ የሚያወርድ የተለወጠ የሰው ሃይል ያስፈልገናል።

በዚህ ጊዜ የአማራ ክልል አርሦ አደር ለዓመት ቀለቡ ሳይሆን፤ ለገበያ፣ ለፋብሪካዎችና ለኤክስፖርት ማምረት መቻል ይኖርበታል። ይህንን ለማድረግ ደግሞ ለግብርናችን ብቻ ሳይሆን ለሕዝባችን ጥያቄዎች ያለን እይታም መለወጥ አለበት።

የሃገራችን አርሦ አደር ግብአት በሃገሩ በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አለበት። ምርጥ ዘር በተሟላ ሁኔታ ማግኘት አለበት። አሲዳማው አፈር ምርቱን ስለሚቀንስበት መሬቱን ለማከም የሚያስችል በቂ የኖራ ግብአት ያስፈልገዋል። የአማራ አርሦ አደር ለብዙ ሺ ዓመታት ያረሰበትን ማረሻ ጥሎ የምርት ጥራትና መጠንን የሚያሳድጉ ጊዜ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን የሚያስታጥቁትን ልጆቹን ይሻል።

ሕዝባችን በየአካባቢው የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ያስፈልጉታል። የሚመረቱ ጥሬ እቃዎችንም ሆነ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ለሃገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ገበያ የሚያደርስበት የተሟላ የየብስ፣ የአየርና የኢንተርኔት መሰረተ ልማት እንዲሁም የሃይል አቅርቦት ከምንጊዜውም በላይ ዛሬ እጃችን ላይ ሊገቡ ይገባል።

ይህ ሲሆን የፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት ጥያቄያችን መልስ ማግኘቱ ብቻ ሳይሆን የሥራ እድልና የሥራ ፈጠራ ያድጋል። ሥራ አጥነት ይቀንሳል። ባለን አቅም ልክ ኢኮኖሚ እናመነጫለን። ባመነጨነው ኢኮኖሚ ልክ ለመንግሥት የሚፈለገውን ገቢ እናስገኛለን። ባስገኘነው ገቢ ልክ ደግሞ የማኅበራዊና መሰረተ ልማት በማያቋርጥ መስፋፋትና እድገት ውስጥ እንዲገቡ እናደርጋለን።

ሕዝባችን በዚህ ጊዜ የሚሻው ጀግንነት ይህ አይነቱን ጀግንነት ነው። አርሶ አደራችን "ለምን ከብልጽግና ማዳበሪያ ተቀብለህ መጣህ" ብለህ በማሰቃየት በአንዱ ሰኔ እንዳያርስ አድርገህ ሰባት ሰኔ እየነቀልከው አንተን የሚፈልግ ይመስልሃል። ይህ ሁኔታ አሠራሩ ባልተቀየረ ግብርና ውስጥ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው።

አሁን ሕዝባችን የሚፈልገው ክላሽ ወይም የስናይፐር ጥይት አይደለም። ከሰባት ሰኔ እየነቀልክ ከርታታ ልታደርገው እየሠራህ "እጠቅመዋለሁ ፤ ጥያቄውንም እመልስለታለሁ" ማለትም አትችልም። በመጽሐፍ “... ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ ድንጋይን የሚሰጠው ከእናንተ ማን ሰው ነው?” እንደተባለው ዳቦ ለሚጠይቀን ወገናችን ጥይት መስጠት ዘለዓለምህን ዳቦ ሲያምርህ ኑር ማለት እንጂ የዳቦ ጥያቄውን መፍታት የሚያስችል ስልት ሊሆን አይችልም። Atleast በአሁኗ ኢትዮጵያ ጦርነት የዳቦ ጥያቄን መፍቻ ዘዴ ሊሆን አንችልም።

ስለዚህ ጀግንነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገማሸር ሳይሆን ሠርቶ መለወጥ መሆኑ ሊገባን ይገባል። እንደ አማራ ሕዝብ በመሰረታዊነት ሠርተን ከምንለወጥባቸው ጉዳዮች አንዱ ደግሞ አሁን በእጃችን ላይ ያሉት በቂ የሚታረስ መሬት፣ ለዘርፋ የሚሆን የሰው ሃይል እና ትንሽ ሠርተንና ወጪ አድርገንበት ልናሳካው የምንችለው የግብርና ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆናችን ነው።

ሰላም ለሕዝባችን❗️

ማሸነፍ የውዴታ ግዴታችን ነው❗️******ትምህርት የለውጦች ሁሉ መሰረት ነው። ሁኖም ግን "አንድ ሰኔ የነቀለውን ሰባት ሰኔ አይተካውም" እንዲሉ አበው ትምህርትም እንደዛው ነው። አንድ ዓመት...
12/04/2024

ማሸነፍ የውዴታ ግዴታችን ነው❗️
******
ትምህርት የለውጦች ሁሉ መሰረት ነው። ሁኖም ግን "አንድ ሰኔ የነቀለውን ሰባት ሰኔ አይተካውም" እንዲሉ አበው ትምህርትም እንደዛው ነው። አንድ ዓመት ትምህርት ያለፈው ሰው በብዙ ማኅበራዊ፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ውስጥ በማለፍ ከእነአካቴው ከትምህርት ገበታ ውጭ የሚሆንበት እድል ብዙ ነው።

በዛው ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአንድና ሁለት ትውልድ የሚለካ የተወዳዳሪነት ችግር ይፈጥራል። በአጭሩ በምንም መመዘኛ የተወዳዳሪነት መንፈስ ውስጥ የማይገባ ትውልድ ይፈጠራል። በትምህርት መበደል ደግሞ ከሌሎች ሁሉ በደሎች የከፋና ከዘር ማጥፋት ወንጀል የሚስተካከል ነው ማለት ይቻላል።

"ፍለጠው፣ ቁረጠው ... ትንሽ ቀርቶናል ..." ወዘተ እያለ የሚጃጃለው ሃይል በአዲሱ ትውልድ መጻኢ እድል ላይ አደጋ መደቀኑና በየትኛውም መመዘኛ በሃገሪቱ ውስጥ ከሚገኙ ወጣቶች ጋር ተወዳዳሪ ያልሆነ ልፍስፍስ አልያም ተጣሞ የበቀለ ትውልድ መፍጠሩ የማይቀር ነው።

ስለሆነም ይህንን ሃይል የምንታገለው ዛሬ ላለንበት ሁኔታ መረጋጋትን ለመፍጠርና የሕዝባችንን ስቃይና እንግልት ለማስቆም ብቻ ሳይሆን ነጋችን ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት ጭምር መሆኑ ታውቆ ትግላችን አሁንም በጽናት በማስቀጠል ልናሸንፍ ይገባል። ማሸነፍ የውዴታ ግዴታችን ነው።

ከንሥሮቹ ዓይን ለመሰወር ጫካ ለጫካ እየተሹለከለከ የመጥፊያው ንጋት ላይ የሚገኘው ቡድን በያዛቸው ቀበሌዎች ላይ መሬት እደለድላለሁ ማለቱን ሰማን።አላዋቂነት ቤት ሲሠራብህ እንዲህ ትሆናለህ። ...
11/04/2024

ከንሥሮቹ ዓይን ለመሰወር ጫካ ለጫካ እየተሹለከለከ የመጥፊያው ንጋት ላይ የሚገኘው ቡድን በያዛቸው ቀበሌዎች ላይ መሬት እደለድላለሁ ማለቱን ሰማን።

አላዋቂነት ቤት ሲሠራብህ እንዲህ ትሆናለህ። የአማራን ሕዝብ መሬት ነጥቆ ለአማራ መስጠት የሚኖረው ፋይዳ ምንድን ነው ብትሉ ሕዝቡ እርስበርስ በጠላትነት እንዲተያይ ማድረግ ብቻ ነው።

ከጊዜ ጊዜ አቅሙ እየተዳከመና የያዛትን ትንሽየ ቀበሌ እንኳን መሻገር ያቃተው ቡድን አሁን ደግሞ እውር ድንብሱን የድንጋጤ ዘፈን እየዘፈነና በሌለው አቅም እንደ እንቁራሪቷ እየጮኸ ይገኛል።

አመንንም አላመንም ወጣቱ ሠርቶ መለወጥ ይፈልጋል። እንደ ባርያ ሠርቶ እንደ ንጉሥ የሚዝናናው የዘመኔ ወጣት ለአንጋቹ ቡድን አልተመቸውም። ምክንያቱም ይህ ቡድን የአማራን ሕዝብ ጥያቄ ለመፍታት ስልቱም፣ አቅሙም፣ እውቀቱም የለውም። ይህንን ሕዝባችን ጥርት አድርጎ ካወቀ ቆይቷል።

እነ ጋሸ ፋኖ ተብየ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ላይ ፣ በመዝናኛ ቦታዎች፣ በዩኒቨርሲቲዎች፣ ...ወዘተ ቦንብ ቢያፈነዱና ሕጻናትን ጭምር በመግደል ሕዝቡን ለማስፈራራት ቢሞክሩም አልሆነም።

እንዲያውም እንዲህ አይነቱ ተግባር ከመፈጠራቸው መጥፋታቸው የሚያስብል ደረጃ ላይ እንዲደርሱ አግዟል።

ሕዝቡ ማንነታቸውን በትክክል እንዲረዳና ወደ ለየለት የሽብር ሥራ ውስጥ በመግባታቸው አንቅሮ እንዲተፋቸውም ሁኗል።

ስለሆነም ዝሆኑ ሕዝባችን እንቁራሪቶችን ሊሰማ የሚችልበት እድል የለም። እንቁራሪቶች ጩኸታቸው ይረብሽ ይሆናል እንጂ አንዳች ነገር የሚፈጥሩበት አቅም የለም።

በሕዝብ ድምጽ የተመረጠውን መንግሥት በአፈሙዝ ለመግልበጥ ማኅበራዊ መሰረት ያላገኘው ቡድን እታገልለታለሁ የሚለውን ሕዝብ መልሶ ማጥቃት ከጀመረ ውሎ አድሯል።በዛሬው ዕለት በምዕራብ ጎጃም ፍኖተ...
04/04/2024

በሕዝብ ድምጽ የተመረጠውን መንግሥት በአፈሙዝ ለመግልበጥ ማኅበራዊ መሰረት ያላገኘው ቡድን እታገልለታለሁ የሚለውን ሕዝብ መልሶ ማጥቃት ከጀመረ ውሎ አድሯል።

በዛሬው ዕለት በምዕራብ ጎጃም ፍኖተ ሰላም ከተማ በአንጋፋው ዳሞት ቁጥር 1 መሰናዶ ትምህርት ቤት ላይ ተማሪዎች በሚማሩበት ክፍል ውስጥ ተማሪዎች ፈተና ላይ እንዳሉ የቦንብ ጥቃት በመፈጸም ሩጠው ባልጠገቡ ታዳጊዎች ላይ አሰቃቂ ጉዳት አድርሷል። የሕዝብ ጠላት መሆኑንም አሳይቷል።

እንዲህ አይነቱ የሽብር ሥራ የዚህን ቡድን "ሳይበቅሉ መርገፍ" እያሳየን ይገኛል። ከመፈጠሩ አርጅቶ መሞቱንም እያስተዋልን ነው።

ታጣቂ ሆይ ሕዝብ ካልደገፈህ አልደገፍህም አለቀ። ሕዝብ ባለመደገፍ ስህተትህን እያሳየህ ... እንደገና በሕዝብ ላይ ሌላ ስህተት የምትሠራ ከሆነ እየተንሰራፋህ ሳይሆን እየጠፋህ መሆኑን እወቅ።

" ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተን በወረዳችን ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን እንሠራለን" -የሰከላ ወረዳ ነዋሪዎች ይህ የሰከላ ወረዳ ሕዝብ አቋም የሁሉም የአማራ ክልል ሕዝብ እምነትና ስ...
04/04/2024

" ከመንግሥት ጋር ተቀናጅተን በወረዳችን ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፍን እንሠራለን" -የሰከላ ወረዳ ነዋሪዎች

ይህ የሰከላ ወረዳ ሕዝብ አቋም የሁሉም የአማራ ክልል ሕዝብ እምነትና ስሜት ነው። የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች መንግሥትን በሃይል አፍርሰን እንመልሳለን ያሉ ሃይሎች ለሃገሬ ገበሬ የአፈር ማዳበሪያ አያቀርቡለትም። ምርጥ ዘር አይሰጡትም፤ የመስኖ ልማቱን አይደግፉለትም። የመሰረተ ልማት ጥያቄውን አይፈቱለትም። ከህመሙ ማገገሚያ መድኀኒት አያቀርቡለትም።

እነዚህን ሰዎች አበጥረው የሚያውቋቸው ዘመዶቼ ሁልጊዜም የተሻለውን ስለሚያውቁ ከጎናቸው አይቆሙም። የአማራን ሕዝብ ጥያቄ እንፈታለን ብለው የተሰባሰቡት ሰዎች ማኅበራዊ ሃላፊነት የሚባለው ደረጃ ቀርቶ ኪስ በማውለቅ፣ ማጅራት በመምታት፣ ትግልን በመክዳት፣ ታላላቆችን በመናቅ፣ ሥራ በመፍጠር ሳይሆን የፈጠሩትን በመዝረፍ የሚታወቁ መሆናቸውን አበጥሮ የሚያውቀው ሕዝባችን ፈጽሞ አይከተላቸውም። የሆነውና እየሆነ ያለውም ይኸው ነው።

ይህ ሕዝብ ትናንትም፣ ዛሬም ነገም የሚፈልገው (የሚጠይቀው) ዘላቂ ሰላም፣ ፍትሃዊ ልማት እና ማንነቱ ተከብሮ መሥራትና መለወጥን ነው።

🕊ሰላም ለሕዝባችን❗️

ውሾቹ ይጮኻሉ፤ ግመሎቹ ጉዟቸውን ቀጥለዋል🇪🇹በ   ከተማ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞ የሚገነባው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ላንድፊልድ ፕሮጀክት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው።ዘመና...
03/04/2024

ውሾቹ ይጮኻሉ፤ ግመሎቹ ጉዟቸውን ቀጥለዋል🇪🇹
በ ከተማ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞ የሚገነባው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ላንድፊልድ ፕሮጀክት በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው።

ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ለከተማው አገልግሎት መስጠት ሲጀምር የከተማውን የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በማዘመን ደብረ ብርሃንን ለነዋሪዎች ምቹ ከተማ ከማድረጉ በተጨማሪ ቀላል የማይባል የሥራ ዕድልም ይፈጥራል።

"አማራ ክልል በርካታ የልማት ጥያቄዎች የሚነሳበት ክልል ነው። ይህንን የሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ ደግሞ  ኢኮኖሚያችን በሚያመነጨው ልክ  ተመጣጣኝ ገቢ  መሰብሰብ ይጠበቅብናል። የአማራ ክልል በ...
02/04/2024

"አማራ ክልል በርካታ የልማት ጥያቄዎች የሚነሳበት ክልል ነው። ይህንን የሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ ደግሞ ኢኮኖሚያችን በሚያመነጨው ልክ ተመጣጣኝ ገቢ መሰብሰብ ይጠበቅብናል።

የአማራ ክልል በቆዳ ስፋትም ሆነ በሕዝብ ብዛት ታላቅ የሚባል ብቻ ሳይሆን ለሃገራችን ኢኮኖሚ የሚያበረክተው አስተዋጽኦም በእጅጉ ሰፊ ነው። ሁኖም ግን ክልሉ በሚያመነጨዉ ሃብት ልክ ገቢ በአግባቡ እየተሰበሰበ አለመሆኑ የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት እያቀጨጨው ይገኛል።

ስለሆነም ከላይ እስከ ታች ያለው የክልሉ አመራር ለበጀት ምደባ የሚጓጓውን ያክል ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብና ገቢን በማስተዳደር የሕዝብን የመልማት ጥያቄ ለመፍታት መሥራት ይጠበቅበታል።

ከደሃ ሕዝብ የመልማት ጥያቄ ላይ ቁመው ግብር የሚሰውሩ፣ ግብር ለሚሰውሩ ወገኖች የሚተባበሩ፣ ግብር ከፋዮችን ዘመናዊ በሆነ ጥራት ያለው አገልግሎት የማያስተናግዱ አካላት እየሠሩት ያለው ሥራ የሕዝብ ጠላትነት መሆኑ መታወቅ አለበት። ይህንን አይነት ሕገወጥነት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማረም የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን ማዘመን ከሁላችንም ይጠበቃል።

በክልላችን ውስጥ የሚገኙ የውሃ፣ የትምህርት ቤት፣ የመድኀኒት አቅርቦት፣ የመስኖ፣ የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ሁሉ ከግብር ከፋዩ ሕዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚሠሩ መሆናቸውን የማይረዳ የክልላችን ነዋሪ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።

ስለሆነም ይህንን እያወቁ የሕዝብን ሃብት የሚመዘብሩ ሙሰኞች፣ ግብር የሚሰውሩ የሕዝብ ጠላቶችም ሆነ ሃቀኛውን ግብር ከፋይ ምቹና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዳያገኝ የሚያደርጉ አሠራሮች ሁሉ ተያይዘን እንድንወድቅ የሚያደርጉ በመሆናቸው መስተካከል የሚገባቸው ናቸው።

በዚህ ወቅት ከሕዝብ ጎን በመቆም ከድሃ ሕዝብ ላይ ግብር በመሰወር አንከብርም፤ ታማኝነታችን በሰላምና በደስታ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በመከራ ጊዜም ሕያው ነው ነብላችሁ በሃቀኝነት የጸናችሁ ታማኝ ግብር ከፋዮች ክብር ይገባችኋል።"

ክቡር አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ "ግብር ለሀገር ክብር" በሚል መሪ መልእክት ምስጉን ግብር ከፋዮችንና ታታሪ ሠራተኞችን ለማበረታታት ባዘጋጀው የንቅናቄ መድረክ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደz

ከጠላት ጋር የሚወግን ሁሉ ጠላት ነው❗️ግርማ ካሳ የተሰኝ የጽንፈኛው ቡድን አፈቀላጤ ከሰሞኑ ህወሃት በራያና በዋግ ኽምራ ሕዝብ ላይ የጀመረችውን ትንኮሳ መነሻ በማድረግ የራያና የአገው ሕዝብ...
02/04/2024

ከጠላት ጋር የሚወግን ሁሉ ጠላት ነው❗️

ግርማ ካሳ የተሰኝ የጽንፈኛው ቡድን አፈቀላጤ ከሰሞኑ ህወሃት በራያና በዋግ ኽምራ ሕዝብ ላይ የጀመረችውን ትንኮሳ መነሻ በማድረግ የራያና የአገው ሕዝብ ለምን ሰላማዊ ሰልፍ አደረገ ብሎ "ለራያ ወገኖች ትኩረቱ መቀሌ ሳይሆን አራት ኪሎ ይሁን" ብሎ ጽፏል።

ስለዚህ እንዲህ ከሆነ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪዎች ነን የሚሉት ፋኖ ተብየ ጽንፈኞቹ ከህወሃት ጋር ምን አስተሳሰራቸው የሚለው ጥያቄ የወቅቱ ዐቢይ ጉዳይ ነው።

የትኛውም አንባቢ እንደሚረዳው ህወሃትን ጠላት ለማለት የተገደድነው ህወሃት በአማራ ሕዝብ ፍትሃዊ ፍላጎቶችና መብቶች ላይ የጭቆና ቀንበርን ጭኖ የኖረና ለሠራው ግፍም ይቅርታ ያልጠየቀ እንዲሁም የአማራን ሕዝብ ሃብቱንና መሬቱን ዘርፎ የኖረ፣ ማንነቱን የቀማ፣ የአማራ ሕዝብ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠላት ተደርጎ እንዲታይ በፖሊሲ፣ በሕግና በተቋማት ግንባታ ውስጥ አካቶ የሠራ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመ ድርጅት በመሆኑ ነው።

ይህም ብቻ ሳይሆን ዛሬም ከዚህ ስህተት ሳይመለስ የፌዴራል መንግሥቱ ለዘላቂ ሰላም በሚበጅና የሕዝብን ድምጽ መሰረት ባደረገ አሠራር ችግሩን ለመፍታት እየሄደበት ያለውን መንገድ ለማደናቀፍ የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመና ትንኮሳውንም እያደረገ ያለ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ይህንን ሃይል ነው እንግዲህ እነ ግርማ ካሳ " እጃችሁን አጣጥፋችሁ ዝም ብላችሁ ተወረሩ።ለምን ወደ መቀሌ ትጮሃላችሁ። ትክክለኛው ጠላታችሁ እኮ ህወሃት ሳይሆን ብልጽግና ነው" እያሉ ያሉት።

በዚህ ስሌት እነሱ ብልጦች እኛ ጅሎች መሆናችን ነው። ብልጽግና የአማራና የትግራይ ሕዝብ ጦርነት ውስጥ በመግባታቸው የሚያተርፍ ድርጅት አይደለም። መሪ ድርጅት እንደመሆኑ መንግሥቱን አጽንቶ፣ በአቻ መንግሥታት ሁሉ ተከብሮ፣ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቦ፣ ...የተሻለ ተወዳጅና የለውጥ መንግሥት ሁኖ መኖርና ለቀጣይ ምርጫ በሕዝብ ዘንድ ተመራጭ ሁኖ የሚቀጥለው ሃገር ሰላም ሲሆን ብቻ ነው። ይህ ስብከት ጅሎችን ለማነቃነቅ የሚጠቅም የጅል ዘፈን ብቻ ነው።

ሌላው ሃቅ ግን የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን አካሄድ ለማደናቀፍ የሚሠራው ፤ ሕዝበ ውሳኔ አንቀበልም ያለው፤ የራያ፣ የዋግ ኽምራ፣ የወልቃይት ጠገዴና ጠለምትን በሃይል ወርሬ እይዛለሁ እያለ የሚዝተውና የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመና ግጭትም እየጀመረ ያለው ሃይል በምን መስፈርት የአማራ ሕዝብ በጥተኛ ጠላተሰ እንደማይሆን እነ ግርማ ሊያስረዱን አልቻሉም።

በዚህ እውነተኛ መነጽር ስንመለከተው ለዘላቂ መፍትሔ እየሠራ ያለው ብልጽግና ፤ የአማራን ሕዝብ ጥያቄ ለማዳፈንና ማንነቱንና መልክዐ ምድሩን ለማዘረፍ ሽፋን እየሰጠ ያለው ደግሞ ጽንፈኛው ቡድን ነው።

ስለሆነም የአማራ ሕዝብ እውነቱን ይረዳዋልና ከወሮበላው ቡድን ጋር አይቆምም። ባለመቆሙም የተበሳጩት እነ ግርማ የራያ ሕዝብ ለምን ኮከብ ያለው ባንዲራ ይዞ ሰላማዊ ሰልፍ ወጣ ብለው በሕዝባችን ላይ የስድብ አፋቸውን አንስተዋል፤ ተበሳጭተዋልም😂

ጽንፈኞች ሆይ ስንት ጥያቄ ነው ያላችሁ ... ብሔራዊ ተቀባይነት የሌለው፣ ዓለም አቀፋዊ እውቅና የሌለው፣ ኮከብ ባለመኖሩ ዳቦ የማይሆንና ፖለቲካዊ ፋይዳ የሌለው የባንዲራ ጥያቄ ደግሞ ምንድን ነው?? በስንቱ እንሳቅ😂

ጉዳዩ ሲጠቃለል ከጠላት ጋር የሚወግን ሁሉ ጠላት መሆኑ ይታወቅ። የራያና የአገው ሕዝብ የሕዝባችን ጥያቄ በዘላቂነት ይፈታ ዘንድ የክልሉም ሆነ የፌዴራል መንግሥቱ እየሄደበት ያለው ከደም አፋሳሽና ከጠላትነትን ነጻ የሚያደርግ እንዲሁም የሕዝብን ድምጽ የሚያከብር ዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዳይደናቀፍ በሰለጠነ መንገድ ያቀረበው ጥያቄ የሚበረታታ ነው።

ሰላም ለሕዝባችን ❗️

የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእርግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ ሆነው በመሾምዎ የ Ethio Press ዝግጅት ክፍል እንኳን ደስ አለዎት እ...
01/04/2024

የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእርግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ ሆነው በመሾምዎ የ Ethio Press ዝግጅት ክፍል እንኳን ደስ አለዎት እያለ መልካም የሥራ ጊዜ ይሁንልዎት ዘንድ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።

"ኀብረት ሥራ ማኅበራት በተለያዩ የዓለም ሀገራት ልማትን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር እና የልማት ማነቆዎችን በመፍታት መተኪያ የሌላቸው ተቋሞች ናቸው። በዚህም የኢኮኖሚ ቀውስን የመቅረፍ ሚናቸ...
01/04/2024

"ኀብረት ሥራ ማኅበራት በተለያዩ የዓለም ሀገራት ልማትን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር እና የልማት ማነቆዎችን በመፍታት መተኪያ የሌላቸው ተቋሞች ናቸው። በዚህም የኢኮኖሚ ቀውስን የመቅረፍ ሚናቸው ከፍተኛ ነው።

ኅብረት ሥራ ማኅበራት በሚሰጡት ተቋማዊ አመራርና አደረጃጀትም ዴሞክራሲያዊ አሠራር በተግባር የሚገለጽባቸው ተቋማት ናቸው።

ማኅበራቱ በኢትዮጵያ የሥራ እድል ከመፍጠር እና የአባላቱን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባለፈ የሀገርን የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ልማት የማፋጠን ሚናቸው የጎላ ነው።

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ገበያን በማረጋጋት እና የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅማቸው እየተሻሻለ መጥቷል።

ማኅበራቱ በሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ ሳይወሰኑ የአባሎቻቸውን ምርቶች ወደ ውጭ በመላክ የክልሉን ምርቶች ለመላው ዓለም እያስተዋወቁ ይገኛሉ። የግብይት ተሳትፏቸውም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል።

ስለሆነም የኅብረት ሥራ ማኅበራት በሂደት የውጭ ባለሃብቶችን የሚተኩበት አልያም የሚያግዙበት ደረጃ ላይ እንዲደርሱ ዘመኑ የሚጠይቀውን ሪፎርሙ ማካሄድና ከተለያዩ ሴክተሮች ጋር በቅንጅት መሥራት ይገባቸዋል።"

የተከበሩ አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር

 ****ታላቅ ሕዝብ ሁነህ ትንሽ መሆን አትችልም። ቤት የተባለች ሃገር የምትቆምበት መሰሶ ሁነህ ሳለ፤ አንዷን የክዳን እሳር ልሁን ማለት አትችልም። እንደ ታላቅ ሕዝብ ታላቅ ለመሆን ሕዝቡ የ...
01/04/2024


****
ታላቅ ሕዝብ ሁነህ ትንሽ መሆን አትችልም። ቤት የተባለች ሃገር የምትቆምበት መሰሶ ሁነህ ሳለ፤ አንዷን የክዳን እሳር ልሁን ማለት አትችልም። እንደ ታላቅ ሕዝብ ታላቅ ለመሆን ሕዝቡ የሚያስበው የሃሳብ ልዕልና ላይ መድረስ ያስፈልጋል።

"ዐቢይ አህመድን ታውቀዋለህ?" ብለኸው "አላውቀውም" የሚል ገበሬ/ነጋዴ፣... ልጅ ሁነህ ፤ "ኢትዮጵያን ትሞትላታለህ?" ስትለው "ሃገሬ እኮ ናት ፤ እንዴት አልሞትላትም!?" የሚል አባት ልጅ ከሆንክ የአባትህ የአእምሮ ልዕልና ላይ ለመድረስ መጣር ይኖርብሃል።

አዎ ... ያላወቀው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥን ነው። ሁኖም ግን ጠቅላዩ የሚጨነቁላትን እናት ሃገር ለመጠበቅ ለሕይወቱ የማይሳሳ ልዕልና ላይ የደረሰ በመሆኑ ልትኮራ ይገባሃል።

የሕዝብ ወይንም የሰው ታላቅነት መሰረቱ የሃሳብ ልዕልና መሆኑን መርሳት የለብንም። "የአጵሎስ፤ የጳውሎስ" መባልም፤ "ግሪካዊ፤ ሮማዊ" መባልም ፤ "የአብርሃም ዘር" መባልም፤ "የክርስቶስ ወገን ነህ" እንደማያሰኝ ሁሉ "ታላቅ ሕዝብ" ወይም "ታላቅ ኢትዮጵያዊ" መባልም የሆነ ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ጎጥ በመጥራት አይመጣም። ታላቅ የሚያስብለን የሃሳብ ልዕልና መሆኑን መወቅ አለብን።

ስለሆነም ታላቁ ማንነታችን 1) ኢትዮጵያዊነታችን ነው። በዚህ ውስጥ ያለን ንዑስ ማንነት ሁሉ ለኢትዮጵያዊነት ማወፈሪያ የሚሆን ጭማሬ እንጂ በራሱ የሚያቆመን ማንነት እንዳልሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።

2) ታላቁ ማንነታችን የሃሳብ ልዕልናችን ነው። የመንደር ሃሳብ ነው ያለኝ ወይስ ሰው ሁሉ የሚቀበለውና ለመላው ዓለም የሚያገለግል ሃሳብ ነው የሚለው አንዱ የታላቅ ማንነት መለኪያ ነው። ቶማስ ኤዲሰን፣ ቴስላ ወይም ሌሎች ለምድራችን እድገት አበርክቶ ያላቸው ተመራማሪዎች የአሜሪካ፣ የክሮሺያ፣ የጀርመን ወይም የሌላ ሳይሆኑ የመላው ዓለም ኩራትና ሃብት እንደሆኑት ሁሉ የሃሳብ ልዕልና እንዲሁ ገዥ ማንነት ነው።

ስለሆነም ዘመኑ የደረሰበት ልዕልና ላይ መገኘት ይጠበቅብናል። የዚህ ማንነት መገለጫ ደግሞ ብሔራዊነት ነው። ምንም እንኳን ከኢትዮጵያዊነት በሚያንስ ማንነት እንድንጠራና እንድንኮራ በሚሠራ የፖለቲካ ማንነት ውስጥ ብንኖርም እውነቱ ግን ❗️የማለው ነው።

"የአማራ ሕዝብ ሰቆቃ በአጭር ጊዜ ይቋጭ ዘንድ ጠንካራ ድርጅት መገንባትና ብቃት ያላቸው፣ በዓላማ የጸኑ አባላትን ማፍራት አስፈላጊ ነው።አሁን ላለንበት ችግር መፍትሔ መሆን ብቻ ሳይሆን የሕዝ...
31/03/2024

"የአማራ ሕዝብ ሰቆቃ በአጭር ጊዜ ይቋጭ ዘንድ ጠንካራ ድርጅት መገንባትና ብቃት ያላቸው፣ በዓላማ የጸኑ አባላትን ማፍራት አስፈላጊ ነው።

አሁን ላለንበት ችግር መፍትሔ መሆን ብቻ ሳይሆን የሕዝባችንን ጥያቄዎች ከመመለስ ባሻገር የሕዝባችንን ነገ አስቦ የሚሠራ ሃይል ባለቤት መሆን የምንችለው ጠንካራ ፓርቲ ሲኖረን ነው።"

አረጋ ከበደ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር

  ሕዝባችን  ሰውን ያለ ልዩነት በማክበር፣ ሥራውንና ሃላፊነቱን በታታሪነት በመወጣት፣ በሃገር ወዳድነት ፀንቶ የኖረ ሕዝብ ነው። ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ጽንፈኛ/ጎጠኛ ቡድን በሚሰፋለት ስልቻ ው...
30/03/2024


ሕዝባችን ሰውን ያለ ልዩነት በማክበር፣ ሥራውንና ሃላፊነቱን በታታሪነት በመወጣት፣ በሃገር ወዳድነት ፀንቶ የኖረ ሕዝብ ነው። ፀረ ኢትዮጵያ የሆነ ጽንፈኛ/ጎጠኛ ቡድን በሚሰፋለት ስልቻ ውስጥ ሊኖር አይችልም።

አማራ ታታሪና ሠራተኛ፤ ሰው አክባሪ ማንነት ነው። ከዚህ ውጭ መድከም ሂደቱን አሰልች፤ ውጤቱንም ከንቱ ያደርገዋል። በአክራሪ ብሔርተኞች ገመድ ተጠልፎ የሚወድቅ አማራ ካለም ሃሳቡ በብዙኀኑ ውድቅ የተደረገና የሞተ ነው የሚሆነው።

አማራ በማንነቱ የሚኮራ ብቻ ሳይሆን በኅብረ ብሔራዊ አንድነት የሚያምን ሕዝብ ነው። ከጥንት ጀምሮ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተከባብሮ በአንድነት የመኖሩ ምስጢርም ይኸው ነው።

የብልጽግና ፓርቲ በእድገት ፖሊሲው ውስጥ የያዛቸው የትኩረት መስኮች ዓለም አቀፍ ሁኔታውን በመረዳት የኢኮኖሚ እድገትና የሥራ እድል ፈጠራን ለማስፋት ወደር የማይገኝላቸው ናቸው።ከትኩረት መስኮ...
30/03/2024

የብልጽግና ፓርቲ በእድገት ፖሊሲው ውስጥ የያዛቸው የትኩረት መስኮች ዓለም አቀፍ ሁኔታውን በመረዳት የኢኮኖሚ እድገትና የሥራ እድል ፈጠራን ለማስፋት ወደር የማይገኝላቸው ናቸው።

ከትኩረት መስኮቹ ውስጥ ቴክኖሎጂ፣ ቱሪዝምና የማዕድን ሃብት ልማት ይገኙበታል። ትልቁ መሰረታዊ ነገር የምጣኔ ሃብት ማሳደጊያ ምልከታችንን መቀየር አስፈላጊ ነው የሚለው ነው።

ሃብት መፍጠር የሚቻለው፤ የሥራ ፈጠራን ማስገኘትም ሆነ የሥራ ዕድል የሚሰፉው የግድ የፍጆታ ሸቀጦችን በመቸርቸር አልያም ምግብና መጠጥ በመሸጥ አለመሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

በእነዚህ ዘርፎች እጅግ ለመቁጠር የሚያዳግቱ የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች ባለቤት መሆንም የሥራ ዕድል ማስገኘትም ይቻላል። ሁኖም ወጣቶቻችን ንቁዎችና አዳዲስ የሃብት ማፍሪያና የምጣኔ ሃብት ዕድገት ማስመዝገቢያ ዕድሎችን ለመልመድ ዝግጁዎች መሆን አለባቸው።

ከዚህ አንጻር የመጀመሪያው ችግር የሚመነጨው ቴክኖሎጂው በዓለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን እድገት ካለመረዳት ነው።

ስለሆነም ቴክኖሎጂን በመላመድ፣ በመፍጠር፣ በአግባቡ በመጠቀምና በማስተዳደር ኋላቀርነት እንደ ማኅበረሰብ በተለይ በተማረው ወጣት ዘንድ ሥር ሰዷል። ይህን ከመሰረቱ መቀየር ያስፈልጋል።

ከቴክኖሎጂ አንጻር የእኛ ክልል በሁለት ጉዳዮች ተጠፍንጎ የተያዘ ይመስላል። በእርግጥ እነዚህ ጉዳዮች ለአማራ ክልል ወጣቶች ብቻ የተሰጡ አይደሉም። በሁሉም አካባቢዎች የሚስተዋሉ ናቸው። ከእነዚህ ሁለት ጉዳዮች የመጀመሪያው ኋላቀርነት ነው።

ቴክኖሎጂን መረዳትና ለችግሮቻችን የመውጫ መንገድ አድርጎ በማሰብ መሥራት ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ አይደለም። የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ባለቤት ሁኖ እንኳን ኮምፒውተር ለመንካት የሚፈራው ወጣት ቁጥር የትየሌሌ ነው። የያዘውን ስማርት ስልክ ለማነጀቢያነት የሚጠቀመው ወጣት ለመቁጠር ያዳግታል ሳይሆን ሁላችንም ያው ነን። በሌላው ዓለም ግን ያ ስማርት ስልክ ቢሮ ነው፤ የገቢ ምንጭም ነው። የሥራ ዕድል ማግኛ መሣሪያም ነው። ቴክኖሎጂን ተላምዶ በአግባቡ በመጠቀምና የኢኮኖሚ ምንጭ ማድረግ መቻል በመንግሥትም በወጣቱም ዘንድ በትኩረት ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ ነው።

ሌላው የገጠመን ችግር ዘመናዊ "አጓጉልነት" ነው። "የተማርኩ ነኝ" ይልሃል። ሰልጥኛለሁ ባይ ነው። በየንግግሩ እንግሊዝኛ እየቀላቀለም ያወራል። ሁሌም እርሱ ጎበዝና የተሻለ አሳቢ ሌላው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሰነፍና ማሰብ የጎደለው ነው። በመማሩና አዋቂ በመሆኑ ምክንያት ግን አንዳች ጠብ የሚል ጥናት ወይም አእምሯዊ የፈጠራ ውጤት የለውም፤ ተግባራዊ ልምምድ የለውም። ያለው ብቸኛ ነገር በአሉታዊ አስተሳሰብ የተሞላ ትችት፣ ጎጠኝነትና እንጨት እንጨት የሚል ንግግርና አላዋቂነት ብቻ ነው።

ለእንደዚህ አይነቱ ወጣት ምክንያታዊነት ከንቱ ነገር ነው። ቴክኖሎጂን መረዳትና ማወቅ ማለት በፌስቡክ ላይ ስድብ ሲጽፉ መዋል ነው። ሌላው ቀርቶ ፖለቲካ ማለት "ያዘው ልቀቀው" ሲሉ መዋልና "ገዳይ ገዳይ" የሚል የ 16ኛ ክፍለ ዘመን መንፈስ የተላበሰ ዘፈን ሲዘፍኑ መዋል ነው። ይህ ሁኔታ በአስቸኳይ ካልተቀየረ እንደማኅበረሰብ እንበሰብሳለን፤ ተወዳዳሪ ወጣቶችን ማግኘትም አንችልም።

ስለዚህ እነዚህ የኢኮኖሚ ፖሊሲ አማራጮችን ተቀብሎ ከወዲሁ መሥራት ጊዜ የማይሰጠው እና የግለሰቦችም የመንግሥትም ትኩረት ሊሆን የሚገባው ጉዳይ ነው።

''እውነተኛ መሪዎች የሚለዩት በያዙት የስልጣን ደረጃ ሳይሆን በፈተና ወቅት ባለቸው የዓላማ ፅናትና ሕዝብን መርቶ በማሻገር ብቃታቸው ነው!"ክቡር አቶ አረጋ ከበደየአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግ...
29/03/2024

''እውነተኛ መሪዎች የሚለዩት በያዙት የስልጣን ደረጃ ሳይሆን በፈተና ወቅት ባለቸው የዓላማ ፅናትና ሕዝብን መርቶ በማሻገር ብቃታቸው ነው!"

ክቡር አቶ አረጋ ከበደ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር

በሰው ልጅ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ምድራችን ከጋርዮሽ ስርዓት ጀምሮ እስከ አሁኑ የዘመናዊ ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት ድረስ በየዘመናቱ የተለያዩ መሪዎችን አስተናግዳለች።

በረጅሙ የዓለም ሕዝብ ታሪክ ውስጥ ስልጣን በሃይልም ሆነ በምርጫ ይዘው የመሪነት ዙፋኑን የተቆናጠጡት መሪዎች እልፍ ናቸው። ነገር ግን የሚመሩትን አገርና ሕዝብ ከነበረበት ውስብስብ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ቀውስ መንጥቀው በማውጣት ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም፣ ልማት፣ ዴሞክራሲ ወዘተ ባለቤትና ተጠቃሚ በማድረግ ከራሳቸውም አልፈው ለዓለም ሕዝብ ቱርፋታቸው የደረሰ በታሪክ የሚታወሱ እጅግ ጥቂቶች ናቸው።

መሪዎች የስኬት ማማን መቆናጠጥ የሚችሉት በምኞትና መሪ በመሆን ህልማቸው ሳይሆን ለስኬት የሚያበቃ ርዕይ፣ ጥራት ያለው እቅድ፣ ፈተናን ወደ እድል የመለወጥና የመጠቀም አቅም፣ መልካም ዲሲፕሊን፣ ዓለምን፣ አገርንና አካባቢን የመረዳትና የመተንተን ብቃት፣ ሀይል የሚያሰባስብ የአመራር ባህል፣ ሕዝብን ያሳተፈና ያማከለ ገቢራዊነት ሲኖራቸው ነው።

ብዙዎቹ የዓለማችን መሪዎች ታይተው እንደ ጤዛ ከመጥፋት ባለፈ ዓለም ሊያወሳው የሚችል አሻራ ለምን ማስቀመጥ አልቻሉም ብለን ከጠየቅን ምክንያቱ የዓላማ ፅናትና ለሕዝብ መሰጠት ቀዳሚውን ረድፍ ይወስዳል። በፈተና ጊዜ የማይፀናና ራሱን ለሕዝብ መስዋዕትነት ያላዘጋጀ መሪ የስኬትን ቁልፍ ሊያገኝ አይችልም።

እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ አገላለፅ ሁሉ መሪ ማለት በሰላም ጊዜ የሕዝብን ደስታ የሚፈጥር፣ በፈተና ወቅት ደግሞ የሕዝቡን መከራ የሚጋራ፣ በክፉ ቀን ጥሎ የማይሸሽና የማይለዋወጥ አቋም የሚወስድ፣ ሀላፊነትና ወገንተኝነት የሚሰማው ነው።

መሪዎች ለሕዝቡ የልማት፣ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍትሕ፣ የመልካም አስተዳደርና ምቹ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የልብ መሻቱ ጥያቄ ሁሉ ምላሾች ናቸው።

መሪዎች በፈተና ጊዜ በዓላማ ፅናት፣ በሕዝባዊ ወገንተኝነት፣ ራስን በመስጠት ሕዝብን ማደራጀት፣ ማንቃት፣ መምራትና ማሻገር እንዲሁም በሰላም ጊዜ በፍቅርና በምስጋና ፍሬው የሚታጨድባቸው ማሳዎች ናቸው።

ክቡር ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት ፈተናና የቁርጥ ቀን እንደ ወርቅ ተፈትነው ነጥረው የወጡ የሕዝብ ልጆችን እንድንለይ ያደርገናል ሲባል አቅማቸውን ሁሉ የሰውን ልጅ ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና ለማምጣት የኖሩትን እንጂ ለሞት፣ ለእንግልት፣ ለሃብትና ንብረት ውድመት እየዳረጉ "እኔ የሕዝብ ልጅ ነኝ" በማለት የሚምሉና የሚገዘቱትን አለመሆኑ ግልጽ ነው።

ስለሆነም ለሕዝብ ጥቅምና መብት መከበር ሲሉ በፅናት የሚታገሉና እራሳቸውን የሰጡ መሪዎችን አመስጋኝና አክባሪ እንሁን። በውጤትና የሰውን ሕይወት ለመቀየር በመቆሙ ሰውን የምንመዝን መሆን አለብን። ምክንያቱም እነዚህ መሪዎች የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ፣ ክብሩ፣ ታሪኩ፣ መብቱና ጥቅሙ ተከብሮ ይኖር ዘንድ ህልውናችን እንዲለመልምና ፍሬ እንዲያፈራ አትክልት ስፍራውን የሚኮተኩቱ ድንቅ አትክልተኞች ናቸው።

ስለሆነም ትናንት በአድዋ የታየው ጀግንነታችን፣ በአክሱም፣ በላሊበላና በጎንደር ዘመን የተገኘው ብሔራዊ ድላችን፤ አጀብ ያሰኘው ጥበባችን፣ በኢትዮጵያዊነት አጋምዶና አዋህዶ ያኖረን ድንቅ እሴታችን ዛሬ እርስበእርስ በመደማመጥ፣ በመከባበር፣ በመደጋገፍ፣ አንድነታችንንና ሰላማችንን በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ አቅም አድርገን ልንጠቀምበት ይገባል።

የዚህ የፈተና ወቅት

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share