ሲዳማ ብልፅግና ደጋፊዎች - Prosperity Fans

ሲዳማ ብልፅግና ደጋፊዎች - Prosperity Fans Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሲዳማ ብልፅግና ደጋፊዎች - Prosperity Fans, TV Channel, Addis Ababa.

14/09/2023

መልካም አዲስ አመት ለኢትዮጵያውያን 🇪🇹

እሱ የአዲስአበባ እሷ የሐዋሳየዛሬ አመት በሐዋሳ ገብርኤል ንግስ ተዋውቀዋል በዘንድሮው እዛው በቀኑ ተጋብተዋል።እንኳን ደስ አላችሁ
26/07/2023

እሱ የአዲስአበባ እሷ የሐዋሳ
የዛሬ አመት በሐዋሳ ገብርኤል ንግስ ተዋውቀዋል በዘንድሮው እዛው በቀኑ ተጋብተዋል።

እንኳን ደስ አላችሁ

Be Blessed
26/07/2023

Be Blessed

ለዘንድሮው ቴክሎጂ ውድድር በቂ ዝግጅት መደረጉ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ገለፀ።የውድድሩ ቴክኒክ ኮሚቴ የውድድሩ ዝግጅት ሥራ ያለበት ደረጃ ...
28/03/2023

ለዘንድሮው ቴክሎጂ ውድድር በቂ ዝግጅት መደረጉ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ገለፀ።

የውድድሩ ቴክኒክ ኮሚቴ የውድድሩ ዝግጅት ሥራ ያለበት ደረጃ ገምግሟል ።

በግምገማ ወቅት በሁሉም ኮሌጆች የዝግጅት ሥራ ያለበት ደረጃ በዝርዝር ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ስሆን በግምገማው ወቅትም ለውድድር የሚሆን በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል ።

ከዚህ መነሻ በተቋማት ደረጃ ከመጋቢት 20_23/2015 ዓ.ም ድረስ፤በክላስተሮች ደረጃ ከመጋቢት 28_30/2015 ዓ.ም ድረስና በክልል ደረጃ ከመያዝ 10_14/2015 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ይፋ ተደርጓል ።

25/03/2023
Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Loosu Dandootenna Interprayzootu Latishsh Biiro Manajimente Giddo Odiite Loosi Keeno Aa...
23/03/2023

Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Loosu Dandootenna Interprayzootu Latishsh Biiro Manajimente Giddo Odiite Loosi Keeno Aana Hasaawa Assitino.

Hasaawunnino Biirote Baajeettetenna Jajju Gashshootinni Biirote Hundaanni Noo Kolleejjuwara Assinoonni Qorqorshi Kaiminni Giddo Odiite Qorqorsha Safo Assine Hasaawanna Keeno Assinoonnita Xawinsoonni.

ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ 4252  ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የተመለመሉ ሰልጣኞችን እያሰለጠነ ይገኛል።በስልጠናው በመጀመሪያ ዙሪ ቅድምያ የተሰጣቸው 4252 ሰልጣ...
16/03/2023

ሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ 4252 ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የተመለመሉ ሰልጣኞችን እያሰለጠነ ይገኛል።

በስልጠናው በመጀመሪያ ዙሪ ቅድምያ የተሰጣቸው 4252 ሰልጣኖች የተሳተፉ ስሆን ከአጠቃላይ 551 ዲግሪ,1945 ዲፕሎማ,1544 ከ10_12ኛ ክፍል,23 ከሌሎች አረብ ሀገራት የተመለሱ,189 አሰልጥነውና ተመዝነው የተቀመጡ ናቸው።

ሰልጣኞቹ በአራት ኮሌጆች፦በሀዋሳ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፥በዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፥በይርጋለምና አለታ ወንዶ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ስልጠና እየተከታተሉ ይገኛሉ ።

ስልጠናው ከጀመረ ዛሬ 3ኛ ቀኑ ስሆን እስከ 15 ቀናት የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል ።

"በሥራ ዕድል ፈጠራ የዘርፉን መረጃ ማጥራት ፣ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ፍትሐዊ ማድረግ፣ የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብ ባህልን ማዳበር፣ ችግር ያለባቸውን መንግስታዊ...
14/03/2023

"በሥራ ዕድል ፈጠራ የዘርፉን መረጃ ማጥራት ፣ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ፍትሐዊ ማድረግ፣ የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብ ባህልን ማዳበር፣ ችግር ያለባቸውን መንግስታዊ ድጋፎች ለይቶ ማስተካከል እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ማጠናከር ትኩረት የምንሰጣቸው ጉዳዮች ናቸው"

ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ባለፉት ስምንት ወራት የሥራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ አፈፃፀም እና በቀሪ ወራት ቁልፍ ሥራዎች ላይ የሚያተኩር የውይይት መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

ከክልል እና ከዞን የዘርፉ አመራሮች የተጋበዙበትን መድርክ በንግግር የከፈቱት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ባለፉት ስምንት ወራት በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ የዕቅዱን 77 በመቶ ማከናወን መቻሉን ተናግረዋል ፡፡

ከሁለት ሚሊዮን ሰማኒያ አራት ሺህ በላይ ለሆኑ ዜጎች ሥራ ዕድል ተፈጥሯል ያሉት ክቡር አቶ ንጉሡ ይህም ካለፈው ስድስት ወር 39በመቶ ጭማሪ ማሳየቱንና ብዙ ዓለማቀፋዊ እና አካባቢያዊ ፈታኝ ችግሮች ቢኖሩም የሚበረታታ ሥራ የተሰራበት ነው ብለዋል፡፡

ክንውኑ 60 በመቶ ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀት እና 40 በመቶ በቅጥር የተፈፀመ ሥራን ያመለክታል ያሉ ሲሆን አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ ክልሎች እና አዲስ አበባ ከተማ የተሻለ አፈፃፀም የታየባቸው እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ዜጎች መብታቸው ተጠብቆ ለሥራ የሚሰማሩበትን ሥርዓት መዘርጋቱንንም ተናግረዋል፡፡

ሀገራዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረታችን ግብርናው ዘርፍ ላይ በተሻለ መጠን የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ ቢሆንም በአገልግሎት እና በኢንዱስትሪ ዘርፍ የተፈጠረው ብልጫ ስላለው ግብርና ላይ ትኩረት ሰጥተን ልንሰራበት ይገባል ያሉት ክቡር አቶ ንጉሡ ለሴቶች የተፈጠሩ የሥራ ዕድሎች 35 በመቶ ብቻ በመሆኑ አሁንም በስፋት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

መንግስታዊ ድጋፎችን መስጠት፣ የዘርፉን መረጃ የማጥራት ሥራ፣ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለውን የሥራ ዕድል ፈጠራ ፍትሐዊ ማድረግ፣ የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብ ባህልን ማዳበር፣ ችግር ያለባቸውን መንግስታዊ ድጋፎች፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ማጠናከር በውይይት መድረኩ በጥንካሬ የተሰሩ ሥራዎችን ለሌሎች ለማካፈል እና ድክመቶች ላይ በጥልቀት በመወያየት በቀጣይ ወራት የተሻለ ሥራ ለመሥራት የምንወያይበት ይሆናል ብለዋል፡፡

የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ከተማዋ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እና በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝ በመሆኗ ለብዙዎች ሥራ ዕድል እየተፈጠረባት መሆኑን አንስተው በቀጣይ ለመቶ ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ ፕሮጀክቶች በሂደት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

© የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡

Quchumate Loonsanni Projekituwanni Looso Looggino Wedellira Loosu Kaayyo Kalaqa Dandiinoonnita Xawinssi.~~~~~~~~~~~~~~~~...
10/03/2023

Quchumate Loonsanni Projekituwanni Looso Looggino Wedellira Loosu Kaayyo Kalaqa Dandiinoonnita Xawinssi.
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
Quchumu latishshira loonsanni projekituwanni looso hooggino wedellira loosu kaayyo kalaqa dandiinoonnita Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Quchumu Latishshinna konistirakishiinete Biiro xawissu.

Biiro maammaruni tantanne losu kaayyo
kalanqoonni wedelli ledo losu giddora eessate injo aana hasaawa assitino.

Biirote Layinki Sooreessinna Quchumu Safote Latishshi Handaari Sooreessi Kalaa Indashashawu Isiraeelihu sa'u yannara Quchumu latishshira 105 k/m ikkitanno doogo looso hooggino wedellira maamarunni tantanne loosu giddora e'anno gede assinoonnita coyrino.

Tayxe dirinni quchummate 75 carete doogo loosiisate yuniversitetenni roso gudde fulte loosu giddora e'inokki 400 wedella 59 maamarranni tantanne loosu giddora eessinoonni kulino.

Konni loosinni 30 quchumma horaameeyye assate hendoonnita kule, 20 ikkitanno quchummara bushshu looso gundoonnitano buuxisino.

Xaphooma loosu hajora 93 miiliyoone birra baajeette gaammoonnitanna; 11 loosoho ikkitanno maashine qixxeessinonnita huwachiishino.

Qaru illachi wedellu bobbakkino handaarinni loossanno gumaamma ikkite kaimu kapitaale kalaqidhe umonsa dandiite loossanno gede assa ikkinotano buuxisino.

Losu kaayyo kalanqoonninsa wedellino mootimma kalaqqino injoonni hagiirramma ikkansa kulte, loosinsanni gumaamma ikkite aantete umonsa dandiite loosate jawaattannota kayissino.

የEASTRIP ስኬት የሚወሰነው በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በአመራሩ ቁርጠኝነት እና ትኩረት ላይ ነው። ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኮሌጅ...
06/03/2023

የEASTRIP ስኬት የሚወሰነው በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በአመራሩ ቁርጠኝነት እና ትኩረት ላይ ነው።

ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኮሌጅ ዲኖች እና ከቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት አመራሮች ጋር ወርሃዊ የፕሮጀክት ክትትል ስብሰባውን ጀምሯል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እንደገለፁት፣ የEASTRIP ፕሮጀክት ወደ መጨረሻው ደረጃ እየተቃረበ በመሆኑ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ያስፈልገዋል።

የኘሮጀክቱ ስኬት የሚወሰነው በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በአመራሩ ቁርጠኝነት እና ትኩረት ላይ ነው ብለዋል።

በመድረኩ ፈጻሚ ተቋማትና አጋሮቹ በአፈፃፀም ሂደት ያገኙት ስኬት እና ተግዳሮቶችን ለይተው የተቀመጡ የቀጣይ አቅጣጫዎችን በትኩረት ለመተግበር ተስማምተዋል፡፡

©የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፡

በሲዳማ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸሐዋሳ (ኢዜአ) የካቲት 25 /2015  በሲዳማ ክልል በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወ...
05/03/2023

በሲዳማ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ከ30 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩ ተገለጸ

ሐዋሳ (ኢዜአ) የካቲት 25 /2015 በሲዳማ ክልል በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ሰባት ወራት ከ30 ሺ በላይ ወጣቶች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን የክልሉ ስራ፣ ክህሎት እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ከፍያለው ከበደ በበጀት ዓመቱ ከ58 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

በዚሀም በሰባት ወራት ውስጥ ለ30 ሺህ 260 ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል መፈጠሩንና ከዚህም ውስጥ ከ15 ሺህ የሚልቁት የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት/ዲግሪና ዲፕሎማ ምሩቃን ናቸው ብለዋል።

የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሆኑት ወጣቶቹ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በአገልግሎት እና በግብርና ዘርፍ መሰማራታቸውን አመልክተዋል።

ለግብርናው ዘርፍ የስራ እድል ፈጠራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ያሉት አቶ ከፍያለው በዘርፉ ለተሰማሩት 6 ሺህ 369 ለሚሆኑ ወጣቶች ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን ተናግረዋል።

በግብርና ዘርፍ የተሰማሩት ወጣቶች ከዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጆች፣ ከሆቴሎች እንዲሁም ከግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ሌሎች ተቋማት ምርታቸውን በቀጥታ እንዲያቀርቡ ትስስር መፈጠሩን ነው ምክትል ኃላፊው ያስረዱት።

በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ ለወጣቶቹ ለማበደር ከታቀደው 198 ሚሊዮን ብር እስካሁን 75 ሚሊዮን ብር መሰራጨቱንም ገልጸዋል።

የመነሻ ካፒታል፣ የመስሪያ እና መሸጫ ቦታ እንዲሁም የግንዛቤና ክትትል ስራዎች በማጠናከር ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ከአዲስ የስራ እድል ፈጠራ በተጨማሪም በነባር ኢንተርፕራይዞች ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ወጣቶችን የመደገፍ እና የማብቃት ስራ እንደሚከናወን በመጠቆም።

©ኢዜአ

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጫበ ጋንበልቶ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው  በበጋ ስንዴ ሥራ እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !
04/03/2023

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጫበ ጋንበልቶ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው በበጋ ስንዴ ሥራ እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !

የውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ማስታወቂያ !የኢትዮጵያ መንግሥት ተቋርጦ የነበረውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መጀመሩን ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በህ...
04/03/2023

የውጭ ሀገር ሥራ ዕድል ማስታወቂያ !

የኢትዮጵያ መንግሥት ተቋርጦ የነበረውን የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት መጀመሩን ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በህግ ማዕቀፍ ተደግፎ ሲካሄድና ሲሰራበት የቆየ የሥራ ዘርፍ ቢሆንም፤በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል ።አሁን ግን በኢትዮጵያ እና በሳውዲ አረቢያ መንግሥት መካከል በተደረገው ስምምነት መሠረት በቤት አያያዝ፥በምግብ ዝግጅትና በህጻናት እንክብካበ ሙያዎች ሠራተኞችን አሰልጥነው በህጋዊ መንገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመላክ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ስምምነቱም የዜጎቻችንን መብት፣ ደህንነትና ጥቅም ማስጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት የተደረገበት መሆኑን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ እየገለጸ የሰለጠኑና የበቁ ዜጎችን በአጭር ጊዜ አሰልጥነውና ብቃታቸውን መዝነው ወደ ሳውድ አረቢያ በህጋዊ መንገድ ለማሰማራት በሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ ይሠራል፡-
1.በመጀመሪያ ለዩኒቨርስቲ ምሩቃን እና ከዚህ በፊት በሙያና ቴክኒክ ኮሌጆች ገብተው በቤት አያያዝ እና በሌሎች ሙያዎች አጫጭር ሥልጠና ወስደው COC አልፈው የተቀመጡትን ቅድሚያ ሰጥቶ ማሰማራት ይፈልጋል
2.በተጨማሪም በክልላችን ውስጥ በሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ገብተው በመሰልጠን ሙያ ይዘው ለመሰማራት የሚፈልጉ ዜጎችን ተቀብሎ በማሰልጠን ለማሰማራት ቢሮአችን ዝግጁ መሆኑን እየገለጸ፤የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልግና መስፈርቱን የሚታሟሉ ዜጎች ከየካቲት 27_30/2015 ዓም በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሠራተኛና ማህበራዊ ጽ/ቤቶች ወይም መምሪያ ቀርባችሁ እንዲትመዘገቡ ቢሮ ጥሪውን ያቀርባል ።

ስልጠናው ከመጋቢት 1_16/2015 ዓም ጀምሮ በሀዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በይርጋለም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ በአለታ ወንዶ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እና ዳዬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሚሰጥ ስለሆነ ሰልጣኙ በተጠቀሱት ኮሌጆች ገብቶ ለመሰልጠን ራሱን ያዘጋጀ መሆን ይኖርበታል፡፡

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ስመጡ የታደሰ ቀበሌ መታወቂያ እና ተገቢውን የትህምርት ማስረጃ ይዞ መገኘት አለባቸው ።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ
ሲዳማ/ሀዋሳ
የካቲት 25/2015 ዓ.ም

Loosu kaayyo egensiishsha !Itiyophiyu mootimma taxxi yee keeshshinoha gobbate gobbayidi loosu bobbayishshi hanafamasi ba...
04/03/2023

Loosu kaayyo egensiishsha !
Itiyophiyu mootimma taxxi yee keeshshinoha gobbate gobbayidi loosu bobbayishshi hanafamasi bayiru hagiirrinni xawissano.
Gobbate gobbayidi loosu bobbayishshi 1990 M.D kayise seerunni irkinse harinsannanna loonsanna keeshshinoha loosu handaara ikkirono kalqete deerrinni tuncu yitinote koovidi - 19 fayya korkaatinni taxxi yee /murame/ keeshshinoti qangannite.
Xa kayiinni, Itiyophiyunna Sawudi Arebiyu mootimma mereero assinoonni sumuumme kaiminni mini amadooshshinni,sagalete qixaxawonna daaimu awuuto ogimmanni loosaasine Sawudi Arebiya bobbaasate sumuummete iillinoonni.
Assinoonni sumuumme qansootinke qoosso, keeraanchimmanna horo agarsiisa dandiissitanno qixxaawo assinoonnita ikkase xawissanni Sidaamu dagoomu qoqqowi mootimma loosu, dandootenna interpirayizootu latishshi biiro ikkadonna qajeelino qansoota harancho yannanni Sawudi Arebiya seeru doogonni bobbaasate aantino qara qara umma aana balaxishsha uyite loossanni afantanno.
1.Allidi rosunna qajeelshu uurrinshshuwanni/yuniverstetenni Maassantinoriranna konni albaanni ogimmatenna tekinikete kolleejjuwara e’e minu amadooshshi ogimmanni harancho qajeelsha adhite COC fonqolo sa’e ofolte noorira balaxishsha uyine bobbaasa
2. Ledotennino qoqqowinke giddo afantanno pooli tekinikete kolleejjuwa haaro e’e qajeelatenni ikkado ogimma amadde bobbahate hasidhanno qansoota haa’ne qajeelshatenni bobbaasate biironke qixxaabbinohura kaayyote horaameyye ikka hasidhannonna safaraancho wonshannohunna wonsh*tanoti Amajje 27-30 geeshsha woradatenna quchumu gashoottara loosaasinenna dagoomittete borro minnaranna biddishshuwate borreesantanno gede biiro egensiissanno.
3.Borreessamaanchu/o borreessamate dagganno woyte olluunnita ayimmate egensiishshi kaarde amadinohanna 10 kifile gudinohanna hakkunni aleenni rosinoha ikkiro hatte leelishshanno rosu taje shiqishira dandaannoha ikka noosi.
Qajeelshu Badheessa 01-16 /2015 M.D Sase lamalara Hawaasa pooli tekinikete kolleejjera, yirgaalamete rosunna ogimmate kolleejjera, Alatta wondo rosunna ogimmate kolleejjeranna Daayye poli tekinikete kolleejjera uyiinanniha ikkanno daafira qajeelaano qummi assinoonni kolleejjuwara e’e qajeelatenna ikkadimmate buuxo keeno keenante Badheessa 26 hanafe loosoho bobbakkannoha ikkanno.

Amme borreessame, qajjeelle tenne kaayyote horaameeyye ikke !!
Sidaamu dagoomu qoqqowi mootimma loosu, dandootenna interipirayizootu latishshi biiro
Sidaama/Hawaasa
Ammajje 25/2015 M.D

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአለታ ጩኮ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው  በበጋ ስንዴ ሥራ እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !
04/03/2023

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአለታ ጩኮ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው በበጋ ስንዴ ሥራ እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዳራ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው  የተለያዩ ሥራዎች እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !
01/03/2023

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዳራ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው የተለያዩ ሥራዎች እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዳሌ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው  የበጋ ስንዴ እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !
01/03/2023

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዳሌ ወረዳ በማህበር ተደራጅተው የበጋ ስንዴ እየሰሩ የሚገኙ ወጣቶች እንቅስቃሴ !

"በክልሉ የሚገኙ አማራጮችን በሙሉ በመጠቀም የስራ አጥነትን ለመቅረፍ ፓርቲያችን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።" አቶ አሸናፊ ኤልያስ በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃ...
01/03/2023

"በክልሉ የሚገኙ አማራጮችን በሙሉ በመጠቀም የስራ አጥነትን ለመቅረፍ ፓርቲያችን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።" አቶ አሸናፊ ኤልያስ በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

በክልሉ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ያሉበት ሁኔታ የኢንስፔክሽን ቡድን በማሰማራት የተደረገውን ምልከታ ግብረ-መልስ ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄዷል።

የውይይት መድረኩን የመሩት በብልፅግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ኤልያስ በክልሉ የሚገኙ አማራጮችን በሙሉ በመጠቀም የስራ አጥነትን ለመቅረፍ ፓርቲያችን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ በመግለጽ በክልሉ በበጀት ዓመቱ የስራ ዕድል ተፈጥሮላቸው የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከልየታ ፣ ከአደረጃጀት ፣ ከስምሪት እንዲሁም ከውጤታማነታቸው አንፃር ያሉበትን ሁኔታ የኢንስፔክሽን ቡድን በማሰማራት ድጋፋዊ ክትትል እና ምልከታ መደረጉን አንስተዋል።

የወጣቶች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የብልፅግና ፓርቲ ዋና መርህ እንደመሆኑ መጠን የወጣቶች ሥራ ዕድል ክልሉ ያሉ ምቹ አማራጮችን በመጠቅም ከተቀጣሪነት ይልቅ የተመቻቸላቸውን የስራ ዕድል በመጠቀም የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ያላቸውን ጥንካሬ በመለየት የሚጎላቸውን የግብዓት እጥረቶችን ኢንስፔክሽን ቡድኑ የለየ እንደነበር በማንሳት በቀጣይ የክልሉ መንግስት እና ፓርቲ የተጀመሩ ሥራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አሸናፊ ኤልያስ ገልጸዋል።

የኢንስፔክሽን ቡድኑ አባላትም በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ ኢንተርፕራይዞች ያሉበትን ሁኔታ ከአንድ ሳምንት በላይ ጊዜ በመውሰድ በማየት ፣ በመገምገም እና በማወያየት ምልከታ በማድረግ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች እና ጉድለቶችን በማቅረብ በቀጣይ መታረም በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

በኢንስፔክሽን ቡድኑ የታዩ ጉድለቶች ከክልል መዓከል እስከታችኛው መዋቅር ያሉ አመራሮች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ዝርዝር ውይይት እና የማስተካከያ እርምጃዎች እንደሚደረጉ በመድረኩ ተገልጿል።

ቴክኒክና ሙያ እውቀትና ክህሎት ያላቸውን እጀ ወርቅ የሆኑ ዜጎችን ማስተናገድ የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲ...
01/03/2023

ቴክኒክና ሙያ እውቀትና ክህሎት ያላቸውን እጀ ወርቅ የሆኑ ዜጎችን ማስተናገድ የሚያስችል ሥርዓት ነው፡፡

ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እና በ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንዳስታወቁት፤ ላለፉት 28 ዓመታት በሥራ ላይ የነበረው የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ወቅቱ የሚፈልገውን ብቁና በቂ የሰው ኃይል ማፍራት እንዲቻል በሚያስችል መልኩ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡

ይህም የትምህርት እና የሥልጠና ዘርፉን በደንብ አሰናስሎ ከማስኬድ አኳያ የነበሩ ክፍተቶችን የሚሞላና ከታችኛው የትመምህርት እርከን ጀምሮ በሙያ የተቃኘ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡

ፖሊሲው ከሙያ ስልጠና አኳያ ከአስተሳሰብ ጀምሮ ያሉ ዝንፈቶችን የሚያስተካከል እና የሥልጠና ጥራት፣ አግባብነት፣ ተደራሽነት እና ፍትሃዊነት የሚያስተናግድ ስርዓትን የሚዘረጋ ነው፡፡

የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት እውቀትና ክህሎት ያላቸውን እጀ ወርቅ የሆኑ ዜጎችን ማስተናገድ የሚያስችል እና ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ አምስት ድረስ ብቻ ተወስኖ የነበረው የሥልጠና ደረጃዎች ወደ ስምንት የሚያሳድግ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ የሥራ ገበያውን እና የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ የ2015 የሥልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት መቀበያ መቁረጫ ነጥብን እንዳዘጋጀም ነው የጠቆሙት፡፡

በዚህም መሰረት ከቴክኒክና ሙያ ውጪ ባሉ ማዕከላት የሚስተናገዱትን ሳይጨምር በሥልጠና ዘመኑ 608,666 የሚሆኑ ሰልጣኞች ወደ ቴክኒክና ሙያ ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ በበኩላቸው፤ በዚህ አመት የተዘጋጀው መቁረጨ ነጥብ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የተፈተኑ ተማሪዎችን ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ በመሆኑ የሚያገለግለውም ለ2015 ዓ.ም የስልጠና ዘመን ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በ2013/2014 የሥልጠና ዘመን በተለየየ ምክንያት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ያልገቡ ተማሪዎች ግን የሚስተናገዱት በ 2014 ዓ.ም በነበረው የመቁረጫ ነጥብ መሰረት ይሆናል ብለዋል፡፡

የ2015 የሥልጠና ዘመን ወደ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት መግቢያ ነጥብ ላይ የቀረበውን በየደረጃው የቀረበውን ማብራሪያ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተቀመጠ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

©የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

በየደረጃው ያሉ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን የሚያነቃቁና የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት ለሴቶች ተጠቃሚነት መሥራት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉ...
28/02/2023

በየደረጃው ያሉ ሴት ሥራ ፈጣሪዎችን የሚያነቃቁና የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በመስጠት ለሴቶች ተጠቃሚነት መሥራት እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ከሀገሪቱ ለተዉጣጡ ሴት ሞዴል ሥራ ፈጣሪዎች የኢንተርፕረነርሺፕ እና የንግድ ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ነቢሃ መሀመድ እንደገለፁት፤ ሴቶች ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ እና ከፍ ያለ የንግድ ክህሎት እንዲኖራቸዉ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እና መሰል የንግድ ክህሎትን የሚያሳድጉ ስልጠናዎች በተጠናከረ መልኩ ሊሰጥ ይገባል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለበርካታ አመራሮችና ባለሙያዎች የኢንተርፕረነርሺፕ እና የንግድ ክህሎት ስልጠና ሰጥቷል። የስልጠናው ተሳታፊዎችም በግል ንግድ የተሰማሩ ሞዴል ስራ ፈጣሪዎች በመሆናቸዉ ፋይዳዉ የጎላ ይሆናል ብለዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እርቅነሽ በበኩላቸው፣ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ሴቶችን፣ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችን እና አረጋዉያን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎች የእቅድ አካል በማድረግ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዉ ይህ ለሞዴል ሥራ ፈጣሪዎች የሚሰጠዉ ስልጠና የሴቶችን ኢኮነሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሀሰን ሁሴን በበኩላቸዉ ስልጠናዉ ለሴት ስራ ፈጣሪዎች መሰጠቱ አሁን እየሰሩት ያለዉን የንግድ ሥራ ትርጉም ባለዉ መልኩ እንዲያሳድጉ እድል ይፈጥርላቸዋል ብለዋል፡፡

©የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

Egennotenna Dandootenni Ikkado ikkino Qansicha kalaqate Rosunna Qajeelshu Uurrinshuwa Qeechi Luphiima Ikkasi Sidaamu Dag...
27/02/2023

Egennotenna Dandootenni Ikkado ikkino Qansicha kalaqate Rosunna Qajeelshu Uurrinshuwa Qeechi Luphiima Ikkasi Sidaamu Dagoomu Qoqqowi Mootimma Loosu Dandootenna Interprayizootu Latishshi Biiro Xawissu.

Biiro Tenne Xawissinohu Mootimmate Kolleejjuwa Tayixe Diro Balaxote Qixxaawo Jeefisse Rosaano Adhate Hajo Aana Xawishsha Uyitu Yannaraati.
~~~~~~~~~~~~~~~~~~
Hajote aana xawishsha uyinohu Sidaamu dagoomu qoqqowi mootimma loosu dandootenna interprayizootu latishshi biiro sooreette riqiwamaanchi kalaa Tewodrosi Gawiiwihu rosunna qajeelshu kolleejjuwa egennotenna dandootenni hettisamaancho qansicha kalaqate jawu qeechi noonsata kule,balanxe qoqqowu giddo afantanno 11 mootimmate rosunna qajeelshu uurrinshuwara rosaano haa’ne qajeelshate qixxaawo assinoonnita xawisino.

Kalaa Tewodrosi ledeno xaa geeshshsa qajeelaano haa’noonnikkihu 12 kifile gobboomu fonqoli gumanna yuniversite e’anno rosaano baxxita geeshsha ikkinota kule, xa kayinni kolleejjuwa rosaano adhite qajeelsate qixxaabbinohura rosaano shiqqe borreessamatenni kaayyote horaameeyye ikkitanno gede qaagiissino. Rosaanote maatenna haja la’annonsari tennera qeechansa fultanno gedeno ledatenni.
Konni kaiminni Hawaasinna Daayye poly rosunna qajeelshu kolleejjuwara deerra 1_5 geeshshanna gattino kolleejjuwara deerra1_ 4 geeshsha qajeelsha uyinannita raga worroonnita kalaa Tewodrosi xawishshisinni coyirino.

Qajeelaanote uyinanni qajeelshi albi gede mittu daniha ikkikkinni qooxeessu qooxeessunkunni dikkote aana hasamamanno qajeelshuwa ikkansanna haroo 18 roortanno ogimmate danna qajeelshaho shiqinshoonnitano xawisino.

Konnira qajeelaano afidhino 12 kifile rosu gumi garinni deerra 1-5 rossannota huwachishino.

ኢጋድ በሰላም፣ ደህንነት፣ ኢኮኖሚ ልማት፣ አስተማማኝና ምቹ የሥራ ሁኔታ፣ መደበኛ የጉልበት ፍልሰት እና ክልላዊ ውህደትን ለመፍጠር ያለው ቁርጠኝነት የሚበረታታ ነው። ክቡር አቶ አሠግድ ጌታቸ...
27/02/2023

ኢጋድ በሰላም፣ ደህንነት፣ ኢኮኖሚ ልማት፣ አስተማማኝና ምቹ የሥራ ሁኔታ፣ መደበኛ የጉልበት ፍልሰት እና ክልላዊ ውህደትን ለመፍጠር ያለው ቁርጠኝነት የሚበረታታ ነው።

ክቡር አቶ አሠግድ ጌታቸው
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የባለሙያዎች መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

መድረኩ የሰራተኞች፣ የቅጥር እና የጉልበት ፍልሰት ላይ ያተኮረ ሲሆን ዓላማውም በቀጠናው የፍልሰት አስተዳደርን በመዘርጋት የሚስተዋለውን የሥራ አጥነት ችግር መቀነስ ነው፡፡

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አሰግድ ጌታቸው በመድረኩ ላይ እንደገለፁት፤ የኮቪድ ወረርሽኝ፣ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ሁኔታ እንዲሁም ቀጠናውን በተደጋጋሚ የሚጎበኘው ድርቅ የአባል ሀገራቱን የኢኮኖሚ እድገት ከማቀዛቀዙ ባሻገር የሥራ አጥነት ችግር በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር አድርጎታል፡፡

በቀጠናው የሚገኙ ሀገራት በየዓመቱ ወደ ስራ ገበያው የሚቀላቀለውን የሰው ሀይል በመደበኛው ስርዓትና በተናጠል ለማስተናገድ የሚቸገሩበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡

በዚህም ኢጋድ እና የዓለም የስራ ድርጅት አባል ሀገራት በመስኩ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታታ ጥረት እያደረጉ ነው።

በተለይም ኢጋድ በሰላምና ለደህንነት፣ በኢኮኖሚ ልማት፣ አስተማማኝና ምቹ የሥራ ሁኔታ፣ መደበኛ የጉልበት ፍልሰት እና ክልላዊ ውህደትን ለመፍጠር ያለው ቁርጠኝነት የሚበረታታ ብለዋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሰራተኞች መብት እንዲጠበቅና የሰራተኞች ፍልሰት እና በስደት ወደ ኢትዮጵያ የሚሰሩ ከሚመለከታቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች፣አጋሮች እና የልማት ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ ነው ብለዋል።

ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ መንግስት መንግስት የሰራተኞች ፍልሰት እና የፍልሰጠኞች መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ ከሚመለከታቸው ሚኒስትር መስሪያ ቤቶች፣ ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሆነም ነው ክቡር ሚኒስትሩ የጠቆሙት።

የሰራተኞች ፍልሰት በአግባቡ ከተያዘ ከስደተኞቹ ባለፈ ተቀባዩን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የገለፁት ክቡር አቶ አሰግድ በዘርፉ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን ለመከላከል አገር አቀፍ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ትብብር እና የተግባር እርምጃ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡

ዘገባው የሚኒስቴር መስሪያቤት ነው

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ የትምህርትና ስልና ረቂቅ ፖሊሲ እና በከፍተኛ ትምህርት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ በምርምር ተቋማት እና በኢንዱስትሪ ትስስር...
27/02/2023

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ የትምህርትና ስልና ረቂቅ ፖሊሲ እና በከፍተኛ ትምህርት ቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ በምርምር ተቋማት እና በኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 17ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፈዋል ።

ም/ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በትምህርትና ስልጠና ረቂቅ ፖሊሲ ላይ ሲሆን በስራ ላይ ያለው ፖሊሲ ላለፉት 28 ዓታት ማሻሻያ
ሳይደረግበት የቆየ በመሆኑ ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ከማፍራት፤ የቴhኖሎጂና የፈጠራ ሥራዎችን ከማበረታታት ፣ እንዲሁም ሀገር በቀል ዕውቀቶችን ዘንቱ ሀገራዊ ተጢታሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ሰፊ ከፍተቶች ነበሩበት በመሆኑ ለሁሉም ህጻናትና ወጣቶች ጥራት ያለው ትምህርት ማዳረስ፤ ትውልዱን ባለብዙ ልሳን እና ተወዳዳሪ በማድረግ ረገድ ጉህ አስተዋጽኦ የሚያበረከት፣ ብቁ የሰው ሃይል ለማፍራት የሚያስችል የዘርፉን ዓለም አቀፋዊ ለውች መሠረት ባደረገ መልኩ የኢትዮጵያን የትምህርት ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ ግብ ያደረገ ረቂቅ ፖሊሲ ተጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምከር ቤት ቀርቧል ።ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ከጸደቀበት ከዛሬ ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል።

በተጨማሪም ምከር ቤቱ የተወያየው በከፍተኛ ትምህርት ቴhኒከና ሙያ ስልጠና፣ በምርምር ተቋማት እና በኢንዱስትሪ ትስስር ረቂቅ
አዋጅ ላይ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪዎች ጋር በመተባበር የሰለጠነና ገበያው የሚፈልገውን የሰው ሃይል ለማፍራት ያደረጓቸው ጥረቶች በተግዳሮቶች የታጠሩ እና የሚጠበቀውን ጤት ያላሳኩ በመሆኑ ይህንን ትስስር በህግ ማእቀፍ ከፍ በማድረግ hኢንዱስትሪው ጋር የሚመሰረተው ትስስር የዕውቀት ሽግግርን መሰረት ያደረገ እንዲሆን፣ ለብዝሃ ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ እንዲያበረhቱ የሚያስችል ከሆኑም በላይ ችግር ፈቺ ምርምር እንዲያከናውኑ፣ ኣስተማማኝ የገቢ ምንጭ
እንዲኖራቸውና ተወዳዳሪ ሆነው አንዲገኙ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት መብትና ግዴታዎች መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ አዋጁ
ተጋጅቶ ቀርቧል።ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፈው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች
ምከር ቤት እንዲተላለፍ በመሉ ድምጽ ወስኗል።

በግል ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሀገር ውስጥ የስራ ስምሪት አገልግሎት መመሪያ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው  የግል ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሀገር ውስጥ የስራ ስምሪት አ...
27/02/2023

በግል ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሀገር ውስጥ የስራ ስምሪት አገልግሎት መመሪያ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

የግል ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የሀገር ውስጥ የስራ ስምሪት አገልግሎት ስለሚሰጡበት ሁኔታ ለመወሰን በወጣው መመሪያ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በውይይቱ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴዔታ ንጉሱ ጥላሁን እና ከተለያዩ የኤጀንሲ ተወካዮች የተውጣጡ ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በውይይቱ አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንደገለጹት÷ የግሉ ዘርፍ ለስራ ዕድል ፈጠራ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።

የስራ ዕድል በቅጥርና በራስ እንደሚፈጠር ጠቅሰው÷ መንግስት ለግሉ ዘርፍ የስራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሰሪና ሰራተኞች መብታቸው እንዲጠበቅና ግዴታቸውንም እንዲወጡ የሁለቱ ግንኙነቶች የተሳካ እንዲሆን ምቹ ሁኔታንም መፍጠር ያስፈልጋልም ነው ያሉት፡፡

ሁኔታዎች ባልተመቻቹበት ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት አይቻልም ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው÷ የአሰሪና ሰራተኛው ጥቅሞቹ መብቱና ደህንነቱ ሊጠበቅለት ይገባዋል ብለዋል ።

ከአሰሪዎች ጋር በቅርበት መስራት ተጠቃሚነቱን ከፍ እንደሚያደርገው ገልጸው÷ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍም የዛሬው ውይይት ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን አመላክተዋል።

ውይይቱ በቀጣይ የሀገር ውስጥ የስራ ስምሪቶች ላይ ምን መደረግ አለበት ከሚለው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከመግባባት ለመድረስ የሚደረግ ነውም ተብሏል፡፡

አሁን ላይ ያለውን የስራ አጥ ቁጥር ችግር ለመፍታት ኤጀንሲዎችን ጭምር በማስተባበር እስከ 2017 ዓ.ም ለ14 ሚሊየን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የድርጊት መርሐ ግብሩ እስከ 2022 ዓ.ም 20 ሚሊየን ዜጎችን የስራ ባለቤት የሚያደርግ ነው ተብሏል።

ዘገባው የFBC ነው

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሲዳማ ብልፅግና ደጋፊዎች - Prosperity Fans posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category

Nearby media companies