Surafel bitaw

Surafel bitaw ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት

ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛከሊቦኖስ ድንግል ነይ ወደኛእንኳን አደረሳችሁ
09/05/2024

ምስራቀ ምስራቃት የአምላክ መገኛ
ከሊቦኖስ ድንግል ነይ ወደኛ

እንኳን አደረሳችሁ

ሕይወትን የሰራውን ከበደለኞች ጋር ሰቀሉትእንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም ከደረሳችሁ
03/05/2024

ሕይወትን የሰራውን ከበደለኞች ጋር ሰቀሉት

እንኳን ለጌታችን ለአምላካችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም ከደረሳችሁ

Today is my birthday Happy birthday to me 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉
17/04/2024

Today is my birthday

Happy birthday to me 🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት… ሱራፌልም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጨሁ ነበር፡፡...
15/02/2024

ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በልዑል ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ አየሁት… ሱራፌልም ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያሉ ይጨሁ ነበር፡፡» ኢሳ.6.1-8 አሜን አሜን አሜን

ጥምቀት በኮተቤ በፎቶ
21/01/2024

ጥምቀት በኮተቤ በፎቶ

የኮተቤ ደ/ል/ዳ/ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤልና ኆህተ ሰማይ ቅድስት ድንግል ማርያም ታቦታት እንዲህ በማረ መልኩ በሰላም ገብተዋል እግዚአብሔር ይመስገን
20/01/2024

የኮተቤ ደ/ል/ዳ/ቁልቢ ቅዱስ ገብርኤልና ኆህተ ሰማይ ቅድስት ድንግል ማርያም ታቦታት እንዲህ በማረ መልኩ በሰላም ገብተዋል እግዚአብሔር ይመስገን

ከተራ በኮተቤ ገብርኤል ታቦታቱ ወጥተው እየባረኩን ነው2016 ዓ.ም
19/01/2024

ከተራ በኮተቤ ገብርኤል ታቦታቱ ወጥተው እየባረኩን ነው
2016 ዓ.ም

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴጥር ፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ምአጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በ...
16/01/2024

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ

ጥር ፮ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡

የኖኅ የትውልድ ነገዶች ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።እግዚአብሔርም አለ።‹‹ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።››እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ከተማይቱንም መሥራት ተው።ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ።እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። (ዘፍ.፲፩፥፩-፱)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹ኑ እንውረድ›› ባሉት መሠረት ሥላሴ በስም በአካል በግብር ሦስት መሆናቸው እንረዳለን፤ የስም ሦስትነታቸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ የግብር ሦስትነታቸውስ ደግሞ አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ የመሆኑ ምሥጢር ነው፤ የአካል ሦስትነታቸው ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ስላላቸው ነው፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመሆኑ የሥላሴ ገጽ አካል ፊት እንደ ሰው ነውን? የሚል ጥይቄ የተነሣ እንደሆነ መልሱ‹‹አዎ፤ እንደ ሰው ነው›› ይሆናል፤ ነገር ግን የሰው ውሱን ጠባብ ፈራሽና በስባሽ ነው፤ የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ በሰማይና በምድር፣ በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ሕያው ባሕርይ ነው፡፡‹‹ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው? ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው››እንዲል፤ (ኢሳ.፹፮፥፩-፪) የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ ወዘተ በመሳሰሉት ነው።

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!

ወንድማችን መልካሙ ጋዜጠኛ አርፎዋልአምላክ ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጎን ይደምርልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን ለልጁ እና ለመላው ወዳጄች ቤተሰቡ መጽናናትን ያድልልን አሜን😥
14/01/2024

ወንድማችን መልካሙ ጋዜጠኛ አርፎዋል

አምላክ ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጎን ይደምርልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን ለልጁ እና ለመላው ወዳጄች ቤተሰቡ መጽናናትን ያድልልን አሜን😥

 #የሚዲያ ጥቆማ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2016 ዓ.ም የጌታችን የአምላካችን የመ...
02/01/2024

#የሚዲያ ጥቆማ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2016 ዓ.ም የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርርቶስ የልደት በዓልን በማስመልከት ሐሙስ ታኅሣሥ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልእክት ያስተላልፋሉ።

ስለሆነም በደብዳቤው ላይ የተቋማችሁ ስም የተገለጸው የሚዲያ ተቋማት በሰዓቱና በቦታው በመገኘት መግለጫውን ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንድታደርሱ ጥሪ ቀርቧል።

ከአዲስ አበባና አካባቢው  #በምሽት ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እንዳትጓዙ ገዳሙ አሳወቀ። የፊታችን ረቡዕ የሚከበረውን ዓመታዊ የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል በማስመልከት የደብረ...
02/01/2024

ከአዲስ አበባና አካባቢው #በምሽት ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እንዳትጓዙ ገዳሙ አሳወቀ።

የፊታችን ረቡዕ የሚከበረውን ዓመታዊ የአባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል በማስመልከት የደብረ ሊባኖስ አባቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሙሉ መልዕክቱ.....

ከደብረ ሊባኖስ ገዳም አባቶች የተላለፈ መልዕክት

የተከበራችሁ እንግዶቻችን

በመጀመሪያ ይህን መልእክት ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱልን።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የልደት በዓልን ለማክበር ወደ ገዳማችን የምትመጡ ምዕመናንና ምዕመናት ክብረ በዓሉን በማስመልከት በገዳሙ ከዋዜማው ጀምሮ የሚተላለፉ የተለያዩ መርሐ ግብሮች ስላሉን ወደ ገዳማች በዋዜማው ( ማክሰኞ ታኅሣሥ 23 ቀን) ከቀኑ 9:30 እስከ10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ እንድትደርሱ እያሳሰብን፤ በተለይ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት የማትደርሱ ከሆነ አምሽታችሁ መንገድ ከምትጀምሩ ጉዟችሁን በጠዋት አድርጋችሁ ለታቦተ ንግሥ እንድትደርሱ ስንል በጻድቁ ስም እናሳስባለን።

አምላከ ተክለ ሃይማኖት ከፊት ይምራችሁ ከኋላ ይጠብቃችሁ አሜን!

" ጌታችን ኢየሱስም መልሶ። ቀኑ አሥራ ሁለት ሰዓት አይደለምን? በቀን የሚመላለስ ቢኖር የዚህን ዓለም ብርሃን ያያልና አይሰናከልም፤ በሌሊት የሚመላለስ ቢኖር ግን ብርሃን በእርሱ ስለ ሌለ ይሰናከላል አላቸው።"
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1፥9-10)

እንኳን ለብስራተ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
01/01/2024

እንኳን ለብስራተ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የመላኩ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በኮተቤ ገብርኤል እንዲህ በደመቀ መልኩ ተከብሩ አልፏልያአመት ሰው ይበለን
30/12/2023

የመላኩ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በኮተቤ ገብርኤል እንዲህ በደመቀ መልኩ ተከብሩ አልፏል

ያአመት ሰው ይበለን

የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ዋዜማ በኮተቤ ገብርኤል
28/12/2023

የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ዋዜማ በኮተቤ ገብርኤል

subscrib በማድርግ የyou tube ቻናላችንን ይቀላቀሉ
05/12/2023

subscrib በማድርግ የyou tube ቻናላችንን ይቀላቀሉ

Share your videos with friends, family, and the world

እንኳን ለፅዮን ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
01/12/2023

እንኳን ለፅዮን ማርያም ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
17/11/2023

እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ህዳር 6በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤ ከግብጽ ሲመለ...
15/11/2023

ህዳር 6

በዚህች ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ አንዲሁም ከዮሴፍና ሶሎሜ ጋር 3 ዓመት ከ 6 ወር በስደት ከተንገላታች በኋላ ወደ አገራቸው የተመለሱበት ቀን ነው፤ ከግብጽ ሲመለሱ ጌታችን በእመቤታችን ጀረባ ላይ ሆኖ እነዚያ እውራንን ባበሩ ጣቶቹ ወደ ኢትዮጵያ ይጠቁም ያመለክት ነበር፤ እመቤታችንም ልጄ ሆይ ለምንድነው ጣትህን የምታመለክተው ብትለው "ያቺ የተባረከች አገር ናት እኔን የሚያመልኩ አንቺን የሚማልዱ በፍቅርሽ የነደዱ ቅዱሳን መነኮሳት የሚፈልቁባት አገር ናት፤ ያንቺ ዘመዶች ሰቅለው ይገድሉኛል በዚህች አገር ያሉ ግን ሳይዩኝ ያመኑኛል፤ አስራት በኩራትሽ ትሁን ብሎ ሰጥቷታል፡፡ በኪደተ እግራቸውም ጣና ሐይቅን፤ ዋልድባንና ሌሎችንም ቦታዎች ዞረው እንደባረኩ ድርሳነ ኡራኤልና ተአምረ ማርያም ላይ በስፋት ተጽፏል፡፡ እመቤታችንን ከሐና ማህጸን ፈጥሮ ከፍጥረተ ዓለም ለይቶ ከሁሉ አልቆ የእናት አማላጅ ትሁናችሁ ብሎ የሰጠን እግዚአብሔር ይመስገን። ዳግመኛም በዛሬዋ ቀን በኢትዮጵያ ምድር ታላቅ አምድ ወደቀ ይህም የመናገሻው ባህታዊ አባ ኤልያስ ነው፤ በ 400 ዓመት እድሜው ህዳር 6 1874 ዓ/ም አረፈ፤ በአጼ ምኒሊክ ዘመነ መንግስት ማለት ነው፤ የቅርብ ጊዜ ነው፤ ይህ አባት በግራኝ መሐመድ ወረራ ጊዜ የነበረ ነው፤ በዚያን ጊዜ በተለይ ኦሮሞዎች "አያና ውቃቢ" እያሉ በጣም ያከብሩት ነበር፤ ከመናገሻ እንጦጦ ኪዳነምሕረት እየተመላለሰ ሱባኤ እየገባ ጸሎት ያደርግ ነበር፤ በዛሬዋ ቀን ይህ አባት ሲሞት በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ከዋክብት ሲበታተኑ ሲራወጡ ታየ የተጉለቱ አባ በላይነህም ይህንን ምልክት አይቶ የአባ ኤልያስን መሞት ተረዱ ወደ መናገሻ ቢመጡ ሞቶ ተቀብሮ አገኙት፤ጎንደር ላይም በተመሳሳይ ከዋክብት ሲበታተኑ እነ አለቃ ወልደ ቂርቆስ በአይኔ አየሁ ሲሉ መስክረዋል ይላል መርስሄ ሐዘን ''ትዝታዬ ስለራሴ የማስታውሰው" በሚለው መጽሐፋቸው የከተቡልን። የሚገርመው ይህ አባት ከቤተመንግስት ወገን ሲሆን ተድላ ደስታን ንቆ 400 ዓመት በቅድስና በተጋድሎ የኖረ መናገሻንና እንጦጦ ኪደነምሕረትን በጸሎቱ የባረከ ይህንን የመሰለ ቅዱስ አለመዘከሩ ታሪኩ አለመጻፉ የታሪክ ጸሐፍት ወዴት አሉ ሊቃውንቱስ ወዴት ተደበቁ ያሰኛል፤ ከእመቤታችንንና ከመናገሻው አባ ኤልያስ በረከት ያሳትፈን። አሜን !!!

(መዝ ፳፩፥፲፮)¶እንኳን ለቸሩ መዳኃኒዓለም የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
06/11/2023

(መዝ ፳፩፥፲፮)¶
እንኳን ለቸሩ መዳኃኒዓለም የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰንቅዱስ ጊዮርጊስ በአማላጅነቱ ሁላችንንም ይጠብቀን አሜን
03/11/2023

እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአማላጅነቱ ሁላችንንም ይጠብቀን አሜን

እንኳን ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን እግዚአብሔር ዘላለማዊ ኃይሉንና አምላክነቱን ለዓለም ከገለጸበት ታላቅ ሥራ መካከል በእመቤታችን በቅድስት ...
01/11/2023

እንኳን ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ወርሃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

እግዚአብሔር ዘላለማዊ ኃይሉንና አምላክነቱን ለዓለም ከገለጸበት ታላቅ ሥራ መካከል በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም የገለጸው ድንቅ ሥራው በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ይህንን ኹኔታ ድንግል ማርያም ‹‹ብርቱ የኾነ እርሱ ታላቅ ሥራን በእኔ አድርጓል፤ ስለዚህም ፍጥረት ኹሉ ያመሰግኑኛል›› /ሉቃ.፩፥፵፱/ በማለት ገለጸችው፡፡

ቅድስት ኤልሳቤጥም ‹‹የጌታዬ እናት›› አለቻት /ሉቃ.፩፥፵፫/፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ‹‹ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ›› አላት /ሉቃ.፩፥፳፰/፡፡ ቅዱስ ዳዊት ደግሞ ‹‹ልጄ›› ይላታል /መዝ.፵፬፥፱/፡፡ ሰሎሞንም ‹‹እኅቴ›› ይላታል /መኃ.፭፥፩/፡፡ ለወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም እናት ኾና ተሰጥታዋለች /ዮሐ.፲፱፥፳፮/፡፡ ይህን ድንቅ ምሥጢር ውስንና ደካማ የኾነ አእምሮ ሊገነዘበው ከሚችለው በላይ ነው፡፡

ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በጻፈው መልእክቱ እንደገለጸው ‹‹የቅድስት ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና፤ አማኑኤልን መውለዷና የማይሞተው ጌታ መሞቱ›› እነዚህ ሦስቱ ከዚህ ዓለም ጥበበኞችና ገዢዎች የተሰወሩ ምሥጢራት ናቸው፡፡ ቅዱስ አግናጥዮስ ‹‹እነዚህ ድንቅ ምሥጢራት በራሳቸው ከንግግርና ከቋንቋዎች ኹሉ በላይ ኾነው የሚነገሩ በእግዚአብሔር የዝምታ መጐናጸፊያ የተጠቀለሉ ድብቅና ጣፋጭ ምሥጢሮች ናቸው›› ይላል፡፡

የእመቤታችን ምስጋናዋ የበዛለት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊም ‹‹አቤቱ መሰንቆ ልቡናዬን አነቃቃ፤ የልቤንም እንዚራ፡፡ ድምፁን ከፍ አድርጎ የዳዊት ልጅ የኾነችውን፣ የጌታውን እናት ድንግል ማርያምን ያመሰግናት ዘንድ፤ ለዓለም ሕይወት የሚሰጠውን የወለደች እናቱ የኾነች እርሷን ከፍ ከፍ ያደርጋት ዘንድ›› ብሏል፡፡ በሌላም አንቀጽ ደግሞ ‹‹ከሕሊናት ኹሉ በላይ ለኾነ ለዚህ ነገር አንክሮ ይገባል፡፡ ምድራዊት ሴት ፈጣሪዋን ወለደችው፤ እርሱም እናቱን ፈጠረ›› አለ፡፡ ስለእነዚህ ነገሮች ኹሉ ምን ማለትን እንችላለን? እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ስለ ድንግል ማርያም ያልተናገረበት ጊዜ፤ ያላናገረው ቅዱስ እንደሌለ እንመለከታለን፡፡

‹‹በእግዚአብሔር፣ በመላእክትና በሰው ፊት የከበረ ሰው መታሰቢያው ለዘለዓለም ነው፡፡ በቤቱ በቅጥሩ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምን ይቀበላልና›› /ኢሳ.፶፭፥፫/፡፡ ይህንን ታላቅ በረከት እንደሚሰጣቸው የተናገረው የማይዋሸው ቅዱስ እግዚአብሔር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ወልድ እናት ከድንግል ማርያም የበለጠ በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ማንን ልንጠራ እንችላለን? እንደ እርሷስ ሊታሰብ፣ ሊከበርም የሚችል በቅድስና ሕይወት ያለፈ ማን ይኖራል?
ቅዱስ እግዚአብሔር ፍጥረቱንና ዓለሙን ለማዳን የወሰነው ጊዜ በደረሰ ጊዜ ከድንግል ማርያም በድንግልና ተወለደ፡፡ አስቀድሞ በመልአኩ አፍ እንዳናገረ ክብሩ በእርሷ ላይ ታየ /ኢሳ.፷፥፪/፡፡ ማኅፀኗን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በእርስዋ አደረ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በእመቤታችን ላይ የማደሩ ምሥጢር ያነጻቸው፤ ይቀድሳቸው፤ በሥጋም በነፍስም መርቶ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ያገባቸው ዘንድ በነቢያት፣ በሐዋርያት ላይ እንዳደረው ዓይነት አይደለም፡፡ ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ (ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ) ከሥጋዋ ሥጋን፣ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ ፍጹም ሰው፣ ፍጹም አምላክ ኾነ እንጂ፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ይህን ዘለዓለማዊ እውነት ‹‹መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል ኃይልም ይጸልልሻል፡፡ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል›› በማለት ገልጾታል /ሉቃ.፩፥፵፭/፡፡

ኢትዮጵያዊው ሊቅ ደራሲና ገጣሚ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ‹‹የእስራኤል ንጉሥ በእስራኤል ልጅ አደረ፤ የዳዊት አምላክ ከዳዊት ልጅ ሥጋን ለበሰ፡፡ የዕብራውያን ጌታ በዕብራውያን ልጅ ማኅፀን ተወሰነ፡፡ ለአብርሃም የዕብራይስጥ ልሳን ያስተማረው ከቀድሞም ያልሰማውን ልሳን እንዲናገር አፉን ጆሮውን የከፈተለት ከዕብራዊት ድንግል ተወለደ፤ በድንግልና ወተት ጥቂት ጥቂት እያለ አደገ፡፡ የሕፃናትን ሥርዓት እንዳያጎድል አፉን የሚፈታባት ዘመን እስኪፈጸም ጥቂት ጥቂት እያለ በዕብራይስጥ ልሳን ሲናገር ኖረ፡፡ ለሙሴ በዕብራይስጥ ልሳን በጣቶቹ የተጻፉትን ዐሠርቱ ቃላትን የሰጠ የዕብራይስጥ ፊደል ለመማር ከመምህር እግር በታች ተቀመጠ፡፡ የባቢሎን አውራጃ በምትኾን ሰናዖርም የፍጥረትን ሁሉ ቋንቋ የበተነ እርሱ የአሕዛብን ቋንቋ እንደማያውቅ ኹሉ እናቱ አፍ በፈታችበት ልሳን በዕብራይስጥ ልሳን ሲናገር ኖረ፡፡ ጆሮ ይህንን ነገር ከመስማት የተነሣ የሚለመልምበት ይህ ነገር ዕፁብ ድንቅ ነው፡፡ ለዚህ አንክሮ ይገባል›› አለ፡፡ ይህ በሰው ጥበብ በብራናና በቀለም የተጻፈ እውነት ሳይኾን ለድኅነት በተጠሩ ሰዎች ሁሉ ልቡና በአምላክ ጥበብ የተጻፈ እውነት ነው፡፡

የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ይደርብን፤ የልጇ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክረስቶስ ጸጋ ይብዛልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹...
30/10/2023

እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)
የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

ቅዱስ ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት እና ሰው መሆን ለመናገር ተልኮ የምሥራች ዜናን ያበሠረ፤ በዲያቢሎስ የተንኮል ወጥመድ ገብተው ለተሰናከሉት ፈጥኖ ለርዳታ የሚደርስ፣ በጨለማ እና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የብርሃን ፋና ያበራ፣ ሰብአ ሰገልን የመራ መልአክ ነው፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ስለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ ‹‹ይወርዳል ይወለዳል›› በማለት በየወገናቸው እና በየዘመናቸው የተናገሩትን የነቢያትን ትንቢት ያስፈጸመና የምሥራችን ቃል የተናገር፣ የጨለማ አበጋዝ በሆነ በሰይጣን ተንኮል ከእፉኝት መርዝ የከፋ በሰው ልቦና ውስጥ አድሮ የነበረውን የኀዘን ስሜት ያጠፋ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል እና ክብሩ

ቅዱስ ሉቃስ እንደጻፈው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሁል ጊዜም ለደስታና ለምሥራች የሚላክ መልአክ ነው፤ በተለይም ስለ ልደተ ክርስቶስ ለድንግል ማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የምስጋና እና የክብር ሰላምታ ያበሠረ በመሆኑ ‹‹አብሳሬ ትስብእት (መልአከ ብሥራት) መጋቤ ሐዲስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ መላእክት ከተፈጠሩ በኋላ አምላካቸውን ለማወቅ ‹‹መኑ ፈጠረነ›› እያሉ ሲባዝኑ ሳጥናኤል ‹‹እኔ ፈጠርኳችሁ›› ሲል ቅዱስ ገብርኤል ግን የፈጠረንን አምላክ እስክናውቅ ድረስ በያለንበት እንቁም እንጽና፤ ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ አምላክነ›› በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡ (አክሲማሮስ. ገጽ.፴፭) በዚህም አባቶቻችን እንደሚሉት መልአኩን የመጀመሪያው የተዋሕዶ ሰባኪ ነው፡፡ ምክንያቱም ከፍጥረታት አስቀድሞ አምላኩን ዐውቆ ስብከት የጀመረ መልአክ ነውና፡፡ በዚህም ምክንያት ጌታ ‹‹ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም፤ድንግል ማርያምን ያበስር ዘንድ የተገባው ሆነ›› እንዲል፤ ነገረ ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበሥር አድሎታል፤ ከዚህ በኋላም ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክት እና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ካህናት አባቶች እንደሚሉት ስእለት ሰሚ እንዲሁም ፈጥኖ ደራሽ መልአክ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መልአክ ነው፡፡ ስለዚህም ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይባላል፡፡ በሀገራችንም ክብረ በዓሉ በቁልቢ ገብርኤል እና በተለያዩ ቦታዎች እጅግ በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ይከበራል፡፡

የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደ ምትወደው በድርሳነ ገብርኤል ላይ ተጽፏል፤ ‹‹ርእዩኬ አኃዊነ ዘከመ ታፈቅሮ እግዝእትነ ማርያም ለቅዱስ ገብርኤል እምኲሎሙ መላእክት እስመ አብሠራ ልደተ ወልድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ወውእቱ ከመ ያፈቅራ ወይረድኣ በጊዜ ምንዳቤሃ ለነኒ ይርድአነ በጊዜ ምንዳቤነ፣ ወንድሞቻችን ሆይ፥ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና›› እንዲል፡፡ (ድርሳነ ገብርኤል ዘኅዳር ምዕራፍ ፪፥ ቁጥር ፲፫)

ቅዱስ ገብርኤል ብርሃናዊ መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ በራእዩ እንዲህ በማለት ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡›› (ራእ.፲፰፥፩)

ነቢዩ ዳዊት ‹‹መላእክቱን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ›› እንዳለው ቅዱስ ገብርኤል ነበልባላዊ መልአክ ነው፡፡ (መዝ.፻፫፥፬)

ቅዱስ ገብርኤል ኃያል መልአክ ነው፤ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹ብርቱ መልአክ ደመና ተጎናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፤ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዐምዶች ነበሩ፤ የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ፤ ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሳም አንበሳ በታላቅ ድምጽ ጮኸ›› በማለት መስክሯል፡፡ (ራእ.፲፥፩)

ቅዱስ ገብርኤል የመላእክት አለቃ ነው፤ በራማ በሠፈሩት ዐሥሩ የነገድ ሠራዊት ላይ የአርባብ አለቃ ነው፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ‹‹በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው›› ይላል፡፡ በዚህም ምክንያት የራማው መልአክ ተብሎ ይጠራል፡፡ (ሄኖክ.፲፥፲፬)

ቅዱስ ገብርኤል ፈጣን መልአክ ነው፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚሉት በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሥነ ስቅለት ጊዜ በመስቀል ላይ የደረሰበትን መከራ አይቶ አላስችለው ቢል ሰይፍ ወርውሯል፤ ‹‹ዓለምም የሚያልፈው ቅዱስ ገብርኤል የወረወረው ሰይፍ ሲያርፍ ነው›› ይላሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ መልኩም ሰይፍ እንደወረወረ ከዚህ በታች በተጻፈው መልኩ እንገነዘባለን ይኸውም፡-

ሰላም ለሰኰናከ ወለመከየድከ ክልኤ

ታሕተ ዐውደ መስቀል ዘቆማ በዕለተ ድልቅልቅ መውዋዔ

ሰይፈ ቁጥዓ ገብርኤል ዘመላኅከ ቅድመ ጉባኤ

አንስትሰ ሶበ ሰምዓ ቃለ ዚኣከ በቋዔ

ኀበ ሐዋርያት ሖራ ይንግራ ትንሣኤ

ትርጉም፡- ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ›› እንዲል፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ገብርኤል ከዓለም በፊት አምላኩን ያወቀ ዓለም ልታልፍ ስትልም የወረወረው ሰይፍ እንደሚያርፍ ሊቃውንቱ ያስረዳሉ፡፡

በሀገራችን በተለምዶም ‹‹ሚካኤል እንደአየህ ገብርኤል እንዳያይህ›› የሚባል አባባል አለ፤ ይኸውም የመልአኩ ተራዳኢነት እንዳለ ሁኖ ተነግሮ ለማይሰማ አካል ግን መልአኩ ፈጣን እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የቅዱስ ገብርኤልን ቁጣ የምንሰማ እና የምናይ ሲሆን ለምሳሌም ካህኑ ዘካርያስ የመልአኩን ቃል ባለመስማቱ (ባለመቀበሉ) ዲዳ ሁኗል፡፡በተጨማሪም በኢ-አማንያንም ዘንድ ሳይቀር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይፈራል፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፩)

ቅዱስ ገብርኤል እና ተራዳኢነቱ

ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳን ሰማዕታትን ገድላቸውን እንዲፈጽሙ እሳቱንና ስለቱን ተሳቀው ወደኋላ እንዳይመለሱ ተጋድሏቸውን እንዲጨርሱ ይረዳቸዋል፡፡ (ዳን.፫፥፳፭) ክርስቶስ በስደት ሲሰደድም ሲመለስም እንዲናገር የተላከ መልአክ ነው፡፡ (ማቴ.፪፥፲፱፣ሉቃ.፪፥፰)

ቅዱስ ገብርኤል የእግዚአብሔር ባለሟል ነው፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነኝ›› እንዲል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ማለቱ ለእግዚአብሔር የተወሰነ ፊት ኖሮት ማለትም እንደ ንጉሥ ወታደር በእግዚአብሔር ፊት ተገትሮ የሚቆም መሆኑን ለመግለጽ አይደለም፡፡ ምንጊዜም ከእግዚአብሔር የማይለይ መሆኑን እና አማላጅነቱን ለመግለጽ ነው እንጅ፡፡ (ሉቃ.፩፥፲፱)

ቅዱስ ገብርኤል ምእመናንን የሚጠብቅ ጠባቂ መልአክ ነው፤ ስለዚህም ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንመልከት፤ ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለአንተ ያዛቸዋል፤እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል››እንዲል (መዝ.፺፩፥፲፩)፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል››(መዝ.፴፬፥፩)፤ ‹‹በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ፡፡››(ዘጸ.፳፫፥፳)

የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን

እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰንሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስየስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊ...
28/10/2023

እንኳን ለቅዱስ እስጢፋኖስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ሲመቱ ለሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕታት ቅዱስ እስጢፋኖስ

የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት›› ከመባሉ በፊትም በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነበር፤ ከዚያም ዲያቆን ሆኖ ተሾሟል፤ ይህም ጥቅምት ፲፯ ቀን ነው፡፡

በሐዋርያት ሥራ ላይ እንደተጠቀሰው ይህ ቅዱስ በመጀመሪያ ገማልያል በተባለ መምህር ትውፊትን፣ ኦሪትንና ነቢያቱን ተምሯል፡፡ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ስብከት ወቅትም እርሱ በዋለበት እየዋለ ባደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ፤ ደቀ መዝሙሩም ሆነ፤ ጌታችንም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ አደረገው፤ አጋንንትም ተገዙለት፡፡ (የሐዋ.፭፥፴፬፣፮፥፭-፲)

በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ሁለቱ አርድእት መካከል የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነትም ወንግልን ሰብኳል፡፡ በቤተ ክርስቲያንም ፈተና ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ሰባት ዲያቆናት ሲመርጡ አንዱ እርሱ ነበር፡፡ የስድስቱ ዲያቆናት አለቃና የስምንት ሺህ ማኅበር መሪ ሆኗል፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህውን ማኅበረ እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት እየጠፋች ወንጌል ደግሞ እየሰፋች ሄደች፡፡ (የሐዋ.፮፥፬)

ቅዱስ እስጢፋኖስም የእግዚአብሔር ጸጋና ኃይል ያደረበትና ታላቅ እንዲሁም ድንቅ ታምራትን የሚያደርግ ሰው ስለነበር በዚያን ጊዜ አይሁድ በምቀኝነት ተነሡበት፤ ከእርሱ ጋርም ክርክር ገጠሙ፤ ነገር ግን ሊያሸንፉት አልቻሉም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ አድሮበታልና በፈጣሪ ኃይል አሸነፋቸው፡፡

ከዚህም በኋላ በሐሰት ምስክር ‹‹ይህን ሰው በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› በማለት ወነጀሉት፤ እርሱ ግን ስለ እውነት መሰከረ እንጂ በጀ አላላቸውም፤ ሊቀ ካህናቱም በጠየቁት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር አምላኩ መሰከረ፤ በመጨረሻም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ፡፡ አባቶቻችሁ ከነቢያት ያሳደዱት ማን አለ? ዛሬም እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና የገደላችሁትን የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን ገደሉአቸው፡፡ በመላእክትም ሥርዐት ኦሪትን ተቀብላችሁ አልጠበቃችሁም፡፡›› በዚህም ተበሳጭተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ በዚህም ምስክሩን ፈጽሞ የሰማዕታት አክሊልን በጥር ፩ ቀን ተቀዳጅቷል፤ በዚህም ቀዳሜ ሰማዕታት ይባላል፡፡(የሐዋ. ፯፥፶፩-፶፫)

አይሁድ ቅዱስ እስጢፋኖስን ለማጥፋት ቀንተው ሲገድሉት ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ክርስትናን ለማጥፋት እነርሱን ሰበብ አድርጎ ለሞቱም ተጠያቂ እንዲሆኑ አድርጎአቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ክርስትናን ለማጥፋት ጠላት በሰዎች ላይ እያደረ ክርስቲያኖችን ያስገድላል፤ ያስጨፈጭፋል፤ እንዲሁም ያሳድዳል፡፡ በየጊዜውም በተለያዩ ክፍለ ሀገራት በጅምላ የሚጨፈጨፉት ሕፃናት፣ አረጋዊያን እንዲሁም ወጣቶች ምንም በማያውቁት ምክንያት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመናገራቸው ሳቢያ፣ ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓላትን በማክበራቸውና ባህላቸውን ለማስጠበቅ በመፈለጋው ብቻ ነው፡፡ እነዚህ እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የጠላት ተገዢ ከመሆናቸው ባሻገር ለራሳቸውና ለሌሎች ጥፋት መንሥኤ በመሆናቸው እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሐሰተኞችን በመቃወም ለእውነት መመስከር ይገባናል፡፡ ለዚህም በሃይማኖት ጸንቶ መኖር ይጠበቃልና እንጽና!

የቅዱስ እስጢፋኖስ አማላጅነትና ተረዳ

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ‹‹ኪዳን›› የሚለው ቃል ‹‹ተካየደ – ተዋዋለ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ፤ ተማማለ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን፣ ...
27/10/2023

እንኳን ለእናታችን ለቅድስት ኪዳነ ምህረት ወርሃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

‹‹ኪዳን›› የሚለው ቃል ‹‹ተካየደ – ተዋዋለ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ፤ ተማማለ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን፣ ትርጕሙም ኪዳን፣ ውል፣ መሐላ፣ ቃል ኪዳን፣ የውል ቃል ማለት ነው /ዘዳ.፳፱፥፩፤ ኤር.፴፩፥፴፩-፴፫፤ መዝ.፹፰፥፫/፡፡ በሌላ በኩል ኪዳን የጸሎት ስም ሲኾን፣ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ፣ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት ያስተማራቸው ጸሎት ኪዳን ይባላል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳን (ውል፣ ስምምነት) የተቀበለችበት ዕለት (የክብረ በዓል ስም) ደግሞ ኪዳነ ምሕረት ይባላል፡፡

በየዓመቱ የካቲት ፲፮ ቀን የምናከብረው ይህ በዓል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ በልጇ በመቃብር ላይ ኾና ‹‹ኦ ወልድየ ወፍቁርየ እስእለከ በእንተ ዘተሰባእከ እምኔየ ወበማኅፀንየ ዘጾረተከ፤ ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፤ ከአንተ ጋር ከአገር ወደ አገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ›› እያለች ስትጸልይ ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደእርሷ መጥቶ ‹‹ሰላም ለኪ ማርያም እምየ፤ እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?›› አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእመቤታችንና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሰየሙትን ዅሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡ጌታችንም ‹‹ይህን ዅሉ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ›› ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው ‹‹… ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፤ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርያችን መመኪያ ናት፡፡ አንተ ‹መታሰቢያሽን ያደረገ፣ ስምሽንም የጠራ፣ የዘለዓለም ድኅነትን ይድናል› ብለሃታልና …፤›› በማለት የሚማጸነው፡፡

በተአምረ ማርያም መጽሐፍ እንደተመዘገበው በዚህ ዕለት የሚታሰቡ ሁለት ተአምራት አሉ፤ ከእነዚህም አንደኛው የስምዖን ታሪክ ነው፡፡ ስምዖን የሚባል እንግዳ ተቀባይ ደግ ሰው ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያፍርምና ከዕለታት አንድ ቀን በእንግድነት ከቤቱ ገብቶ ‹‹ልጅህን አርደህ ካላበላኸኝ ሌላ ምግብ አልበላም›› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ስምዖን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆየና ‹‹አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው›› በማለት፣ ‹‹የእግዚአብሔርን እንግዳ›› ላለማሳዘን ሲል ልጁን አርዶ አቀረበለት፡፡ እንግዳ መሰሉ ሰይጣንም ሥጋውን ቅመስልኝ ብሎ ግድ አለው፡፡ ስምዖንም (በላዔ ሰብእ) አርዶ ያዘጋጀውን የልጁን ሥጋ በቀምሰ ጊዜ ሰይጣን ስላደረበት (ስለተዋሐደው) ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ቤተሰቦቹን፣ ጎረቤቶቹንና መንገደኛውን ዅሉ ይበላ ጀመር፡፡ በአጠቃላይ ፸፰ ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ በቍስል የተመታ ሰው አገኘና ሊበላው ሲል ‹‹ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ በሥላሴ፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም ለመነው፤ እርሱም ዝም አለው፡፡በመጨረሻም ‹‹በድንግል ማርያም ስም›› አለው፡፡ ስምዖን የእመቤታችንን ስም በሰማ ጊዜም ወደ ልቡናው ተመልሶ ‹‹እስኪ ቃሉን ድገመው›› አለው፤ በሽተኛውም መልሶ ‹‹ስለ ድንግል ማርያም ውኃ አጠጣኝ›› ብሎ ለመነው፡፡ ያን ጊዜ ‹‹ይህችስ እንደምታስምር በልጅነቴ ሰምቻለሁ›› ብሎ ጥቂት ውኃ ሰጠው፤ ውኃው ጕሮሮውን እንኳን ሳያርስለት ‹‹ጨረስህብኝ›› ብሎ ነጥቆት ሔደ፡፡ በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አግኝቶ ሊበላ ሲል ገበሬው ‹‹በላዔ ሰብ የምትባል አንተ ነህ?›› ባለው ጊዜ ‹‹ለካስ አመሌን ሰው ዅሉ አውቆብኛል›› ብሎ ዋሻ ገብቶ በመጸጸት በዚያው ሞተ፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ጽልመት መጥተው ሲወስዷት እመቤታችን ‹‹ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?›› አለችው፡፡ ጌታችንም ‹‹ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋ፣ ፈጣሪውን የካደ ሰው ይማራልን?›› አላት፡፡ እመቤታችንም ‹‹በስሜ የተጠማውን ውኃ አጥጥቶ የለምን?›› ብላ ስምዖንን (በላዔ ሰብእን) አስምራዋለች፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ብርሃን መጥተው ወደ ገነት አስገብተዋታል፡፡

ሁለተኛው ተአምር ደግሞ ከብሮ ከኖረ በኋላ ለድህነት በተጋለጠ አንድ ምእመን ላይ የተደረገ ነው፤ ከክርስቲያን ወገን የኾነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ‹‹ከብሬ በኖርኹበት አገር ተዋርጄ አልኖርም›› ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ከአገሩ ወጥቶ ሲሔድ ሰይጣን ያዘነ ሰው መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ ‹‹ሥላሴን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትንን፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን ወርቅ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡ ዅሉንም ካደለትና ወርቁን ተቀብሎ ዞር ሲል ‹‹ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም ‹የአምላክ እናት አይደለችም› ብለህ ካድልኝ›› አለው፡፡ ሰወየውም ‹‹እርሷንስ አልክድም›› ስላው በደንጊያ ቀጥቅጦ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት የሟቹን ነፍስ ሊወስዱ ሲሉ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ፡፡ እመቤታችንም ጌታችንን ‹‹ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ከልብኑ ይትመሐር እምየ፤ እናቴ፣ ውሻ ይማራልን?›› አላት፡፡ እመቤታችንም፡- ‹‹‹ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ› ያልኸው ቃል ይታበላልን?›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ‹‹ምሬልሻለሁ›› አላት፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ‹‹ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ›› ባለው መሠረት ከቅዱሳን ጋር ያደረጋቸው ቃል ኪዳኖች ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ከላይ በተአምራቱ እንደተመለከትነው አንዱ ለእመቤታችን የሰጠው የአማላጅነት ኪዳን ነው፡፡ ማማለድ ማለት ስለሌላው መጸለይ፣ መለመን፣ የደረሰውን ችግር እንዲወገድ ማድረግ፣ ማስማር (ይቅርታ ማሰጠት) ማለት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ከእግዚአብሔር በታች ከቅዱሳን ዅሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት የማማለድ ሥልጣን ‹‹ሰአሊ ለነ ቅድስት፤ ቅድስት ሆይ ለምኚልን›› እያሉ ለሚለምኗት ዅሉ ከእግዚአብሔር እያማለደችና እየለመነች ምሕረትን እንደምታሰጥ ቀናውንና የተመሰገነውን ሃይማኖት የምንከተል ምእመናን ዅሉ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ እንደመኾኗ ከዅሉም ቅዱሳን በበለጠ ለእግዚአብሔር ቅርብ ናትና፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም ኾነ በሰው ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘት ወይም ቅርብ መኾን ደግሞ አንድን ጉዳይ በቀላሉ ለማስፈጸም ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ፡-
መልአኩ ቅዱስ ገብርአል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ባለሟል በመኾኑ የድኅነትን ምሥጢር አብሣሪ ኾኗል /ሉቃ. ፩፥፲፱-፳፮/፡፡

አስቴር የንጉሡ አርጤክስስ ሚስት በመኾኗ በወገኖቿ አይሁድ የታወጀውን የሞት አዋጅ አስለውጣለች /መጽሐፈ አስቴር ፫፥፲/፡፡

ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟል በመኾኑ ‹‹ይህንን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ?›› በማለት ለእስራኤላውያን ምሕረትን አሰጥቷል /ዘፀ.፴፪፥፲፬/፡፡

ስለዚህ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትም እንደ ፀሐይ የበራ ሐቅ ነው፡፡ ይህንን እውነት ቅዱስ ያሬድ ሲመሰክር፡- ‹‹ወታስተሠርዪ ኀጢአተ ሕዝብኪ ተበውሀ ለኪ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለሕዝብሽ፣ ለወገኖችሽ የኃጢአት ይቅርታን ታሰጪ ዘንድ፤ ዘለዓለማዊ ሕይወትንም ለሚወርሱ ዅሉ መሸጋገሪያ ድልድይ ትኾኚ ዘንድ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ሥልጣን አግኝተሻል›› በማለት አመስግኗታል /አንቀጸ ብርሃን/፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው፡- ‹‹ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ፤ የድኅነት ምክንያት ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት፣ መርገም (ኀጢአት) ባጠፋን ነበር›› ብለዋል፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡– ‹‹ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፡፡ መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፡፡ ለጻድቃን ያይደለ ለኀጥአን አሳስቢ፡፡ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሶስቢ፤›› ሲሉ ይማጸኗታል /ቅዳሴ ማርያም ቍ.፻፷፭-፻፸፩/፡፡

ስለዚህም ዘወትር በሥርዓተ ቅደሴአችን፡- ‹‹ድኅነትን የምንለምንሽ ክብርን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ዅል ጊዜ ድንግል የምትኾኚ አምላክን የወለድነሽ የክርስቶስ እናት ሆይ ኀጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ወደ ላይ ጸሎታችንን አሰርጊልን፡፡ በእውነት የጽድቅ ብርሃን የሚሆን አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን ንጽሕት ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ንጽሕት ድንግል ሆይ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግ ዘንድ፤ ኀጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ጌታችን ለምኚልን

25/10/2023

እንኳን ለአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ክፍል 2

ወደ ደቡብ በሄደም ጊዜ የመን ከሠራዊቱ ጋር ዘምተው አሸንፈው ተመለሱ። የአፄ ካሌብ ልጅ ገብረ መስቀል ቤተ ክርስቲያን ሠራላቸው። በውስጡም በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች በእመቤታችን በድንግል ማርያም ስም የተሰየመች በወርቅና በብር ያጌጠች ታቦት አስገባ፡፡ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ከተራራው ላይ ሲወርድ ለቤተክርስቲያኑ ማሠሪያ የሆነውን መወጣጫ መሰላል ‹ላፍርሰው› ብሎ አባታችንን ጠየቀ፤ አባታችንም ‹‹አዎ! አፍርሰው፤ አትትወው፤ ነገር ግን ስለዘንዶው ጅራት ፈንታ ሰዎች ይወጡበት ዘንድ ገመድ አብጅ›› አለው፡፡ ንጉሡም አባታችን አቡነ አረጋዊ እንዳዘዘው አደረገ፤ያም ቦታ ደብረ ደኃምሞ ተብሎ ተሰየመ።

ከዚህ በኋላም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ‹‹ከድካም ወደ ዕረፍት፣ ከኃዘን ደስታ ወዳለበት፣ ከኀሣር ወደ ክብር ቦታ በታላቅ ደስታ እወስድህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ፡፡ የሞት ጥላ አያርፍብህም፤ መልአከ ሞትም ሊያስደነግጥህ አይችልም፤ እንደ ነቢያት ኤልያስና ሄኖክ ትሰወራለህ›› ብሎ ቃል ኪዳን ሰጥቷቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ አረገ፡፡

አባታችን አቡነ አረጋዊ ማትያስ ለተባለው ደቀ መዛሙር ጌታችን ተገልጦ የሰጣቸውን ቃል ኪዳንና ይህ መጽሐፍ ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነገሩት፤ (መዝ ፻፲፩/፻፲፪፥፮) ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቶቹ በተሰበስቡበትም ሁሉንም ከአስተማሩ በኋላ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም›› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም በመሪር ኃዘን እግራቸው ሥር ወድቀው አለቀሱ፤ አባታችን አቡነ አረጋዊም አጽኗኗቸው፡፡ ጥቅምት ፲፬ ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በ፺፱ ዓመታቸው ተሰወሩ፤ በዚያም ከመቋሚያና ከመስቀል በስተቀር ምንም የተገኘ የለም፡፡

ወስብሃት ለእግዚአብሔር

እንኳን ለአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰንክፍል 1አባታችን አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ናቸው። ትውልዳቸውም ከሮም ነገሥታት ወገን ሲሆን አባታቸው...
25/10/2023

እንኳን ለአቡነ አረጋዊ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን

ክፍል 1

አባታችን አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ናቸው። ትውልዳቸውም ከሮም ነገሥታት ወገን ሲሆን አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበር፤ እናታቸው እድና ትባላለች፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ የተባረከ ልጅም ወለዱ፤ በሕገ እግዚአብሔርና ቅዱሳት መጻሕፍትን እያነበበ አደጉ፡፡ ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ሚስት ቢታጭላቸውም ከነበራቸው የክርስቶስ ፍቅር የተነሳ ትዳር መመሥረትን ትተው ደውናስ ወደ ምትባል ገዳም ሔዱ፤ በዚያም አባ ጳኩሚስ ይኖሩ ነበር።
አበምኔቱ አባ ጳኩሚስን ልበሰ ምንኩስናን እንዲያለብሳቸው ጠየቁት። አባ ጳኩሚስም ‹ልጄ ሆይ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኩሰህ ለመኖር ይቻልሃልን?› አለው፡፡ ቅዱስ አባታችንም ‹‹አባቴ ሆይ የምድር መንግሥት ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ነገር ግን የማታልፈውንና የማትጠፋውን ዘለዓለማዊት መንግሥት እወርስ ዘንድ እፈልጋለሁ›› አለው፡፡ እናም በ፲፬ ዓመታቸው በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናውን ልብስ ለበሱ፤ በገዳሙም እየተጉ ኖሩ፡፡ከዚህ በኋላ የጻድቁ ዜና በሀገራቸው ሮም ውስጥ እንዲሁም በመላው ቦታ ተሰማ፡፡ በዚህም የተማረኩት ሰባት ቅዱሳን፤ አባ ሊቃኖስ ከቁስጥንጥንያ፣ አባ ይምአታ ከቆስያ፣ አባ ጽሕማ ከአንጾኪያ፣ አባ ጉባ ከቂልቅያ፣ አባ አፍፄ ከእስያ፣ አባ ጰንጠሌዎን ከሮም፣ አባ አሌፍ ከቂሳርያ እርሱ ወዳለበት ገዳም መጡ። አባ ጳኩሚስ ለብዙ ዓመታት ምንኩስናን ሥርዓተ ማኅበርን አስተማራቸው። እናቱ ንግሥት እድና የልጅዋን ዜና ሰምታ እርሱ ወዳለበት መጥታ መነኮሰች፡፡ በሴቶችም ገዳም ገብታ መኖር ጀመረች፡፡ መነኮሳቱም አባ ዘሚካኤልን መሪያቸው አደረጉት፤ በአካለ ሥጋ ሕፃን ሆኖ ሳለ የአእምሮውን ብስለት ዐይተው የሕይወት መንገድ ስለመራህን አቡነ አረጋዊ መባል ይገባሃል አሉት፤ በዚህም አቡነ አረጋዊ ተብለው ተጠሩ፤ ብልህ አዋቂ ማለትም ነው፡፡በገዳመ ዳውናስ ሰባት ዓመት ከቆዩ በኋላ ይስሐቅን (በኋላ አባ ገሪማን) ለመጠየቅ እና የሀገሩን ሰዎች ለማስተማር በአንድነት ሆነው ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ በዘመናቸው የካቶሊክ ሃይማኖት እንዲቀበሉ ጫና ቢደረግባቸውም… ‹‹እውነቱን እውነት፣ ሐሰቱን ሐሰት ማለት ተገቢ ነውና ክርስቶስ ከተዋሕዶ በኋላ ሁለት ባሕርይ ነው ብሎ ማስተማር ክሕደት ነው››…. ብለው በድፍረት መቃወም ጀመሩ፡፡ ይሁን እንጂ በኃይል እና በገንዘብ ብዛት የምትመካው የሮማ ቫቲካን ቤተክርስቲያን ቅዱሱን ማሳደድ ጀመረች:: ቅዱሱ አባታችን አቡነ አረጋዊም ‹‹በአንዱ ቦታ መከራ ቢያጸኑባቸው ወደ ሌላው ሽሹ…›› የሚለውን የወንጌል ቃል አብነት በማድረግ እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኢትዮጵያን ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም የዐስራት ሀገር እንዲሆናት በቃል ኪዳን እንደሰጣት ከቅዱሳት መጻሕፍት በማንበቡ በኢትዮጵያ ፍቅር ተያዘ፤ ወደዚያውም መሄድ ፈለገ፡፡ ይህንንም ሁለት ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ለማንም ሳያሳውቅ ቅዱስ ሚካኤል እየመራው ንጉሡና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሰ፡፡እዚያም ጥቂት ቀን ተቀምጦ ወደ ሮም ተመለሰ፡፡ ስለኢትዮጵያ በዐይኑ የተመለከተውን በጆሮ የሰማውን ሁሉ ለወንድሞቹ ነገራቸው፡፡ እነርሱም ‹‹እኛም ወደዚህች ሀገር መሄድ አለብን›› ተባባሉ፡፡ ያላቸውን የመገልገያ ዕቃ ይዘው ከታቦቶቻቸውና ከካህናቶቻቸው ጋር ንዋየ ቅድሳትና መጻሕፍችን ይዘው ከመሰል ወገኖቻቸው ጋር አባታችን ዘሚካኤል (በአቡነ አረጋዊ) እየመራቸው በአልዓሜዳ አምስተኛ የንግሥና ዓመት በ፬፻፹ ዓ.ም ንጉሡና ጳጳሱ ካሉበት አክሱም ከተማ ደረሱ፤ ስምንቱ ቅዱሳንም መጡ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ዘጠነኛው አቡነ ይስሓቅ (አቡነ ገሪማ) በሮም ከነገሠ ከሰባት ዓመት በኋላ መንግሥቱን ትቶ ወደ አክሱም መጣ፤ በዚያን ጊዜ እንደነሱ አመነኮሱት፤ ቍጥራቸውም ዘጠኝ ሆነ።ለሁሉም አንድ የተለየ ማረፊያ ቦታ ቤተ ቀጢን የተባለው ተሰጥቷቸው በጸሎት ተጠምደው ይኖሩ ነበር፤ በአንዲት የጸሎት ቤት በአንድነት ሆነው ለጸሎት ፈጣሪያቸውን እየለመኑ፤ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረጉም ቆዩ፡፡ መላእክት ዘወትር ባለመለየት ያጽኗኗቸው፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር ይገለጽላቸው ነበር፡፡ በእያንዳንዳቸውም ብዙ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ከእነርሱ መካከልም ተራራ ያፈለሱ፣ ባሕሩን ከፍለው ደረቅ መንገድ ያደረጉ፣ ስንዴ ዘርተው በቅጽበት ለዘጠኝ ሰዓት መሥዋዕተ ቁርባን ያደረሱ አሉ፡፡ የኢትዮጵያ ምድር በእነዚህ የቅዱሳን ኪደተ እግር ተቀደሰች፡፡በኋላም ንጉሥ አልዓሜዳ ከሞተ በኋላ በነገሠው በታዜና ስድስተኛ ‹‹የንግሥና ዓመት ላይ ተለያይተን እናስተምር›› ብለው ወስነው ተለያዩ። አቡነ ሊቃኖስ ደብረ ቆናጽል፣ አባ ጰንጠሌዎን ከእዚሁ ሁለት ምዕራፍ እልፍ ብሎ ከሚገኝ ኮረብታ፣ አቡነ ይስሐቅ መደራ፣ አቡነ ጉባ በእዚሁ በመደራ ትይዩ ሦስት ምዕራፍ እልፍ ብሎ፣ አባ ጽሕማ፣ አባ ይምዓታ ገርዓልታ፣ አባ አሌፍ አሕስዓ ብሕዛ በተባለችው፣ አባ አፍጼ ይሐ ተሠማሩ።አባታችንም እናታቸው እና ማትያስ የተባለ ደቀ መዝሙራቸውን ይዘው ከሁሉም ርቀው ወደ መረጡት ቦታ ሲሄዱ ከዛፍ ጥላ ሥር አረፉ፤ እርስዋም እስከ ዛሬ ድረስ የቅዱሳን ማረፊያ ሆና ትገኛለች፡፡ አባታችንም ቅድስት ቦታ ዳሞን ባያት ጊዜ ሦስት ጊዜ ሰገደ፡፡ በተራራዋ ሥር ለመኖርም ወደደ፡፡ ነገር ግን ወደ ተራራዋ መውጫ አላገኘም፡፡ ተመልሶ ወደ ሌላ ተራራ ሄዶ አማረጠ፤ ሆኖም እንደ ደብረ ዳሞ የበረከት ቦታ ባላገኘ ጊዜ ተመልሰ፡፡ በዚያም የምንጭ ውኃ አገኘ፡፡ ውኃውን እየተንከባከበች የሴት መነኮሳቶችን ታስተዳድር ዘንድ እናቱ ቅድስት እድናን አስቀመጣት፤ ይህችንም ደብረ በአተልሞ አላት፤ ትርጓሜውም የእናቴ ማረፊያ ቤት ማለት ነው፡፡ከዚያም ሲሄድ ጠፍጣፋ ድንጋይ አገኘና ከዚያ ላይ ትንሽ ምንጣፍ አነጠፈና ተቀመጠ፡፡ በትሩንም በድንጋይዋ ላይ አቆመ፡፡ በተነሳም ጊዜ ደቀ መዝሙሩ ማትያስ በትሩንና ምንጣፉን ሲያነሳው ያች ድንጋይ ቁመቷም ጎኗም ልክ በዚያች ምንጣፍ አይነት ቅርጽ አወጣች፡፡ የቀድሞ መልኳ ነጭ ሲሆን አሁን ግን የማይፋቅና የማይላጥ ቀይ ቀለም ሆኗል፡፡ ስለአባታችን አቡነ አረጋዊ ታላቅነቱና ስለክብሩ ከዚያ የደረሱ ሁሉ ይሳለሟታል፡፡ከዕለታት በአንደኛው ቀን መንገድ ሲሄድ ውሎ ከተራራ አጠገብ ወደ ታች የተንዠረገገች ሐረግ/ገመድ/ አገኘና በሥሯ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት ሲጸልይ ከቆየ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦ ‹‹እግዚአብሔር ያከበረህ ቅዱስ ሆይ ምን ያስጨንቅሃል?›› አለው፡፡ አባታችንም ‹‹ከዚህ ተራራ ላይ ወጥቼ ስለኃጢአቴ ይቅርታን እጠይቅህ ዘንድ እወዳለሁ›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹ወደ ተራራው የምትወጣበትን እግዚአብሔር እስኪልክልህ ድረስ ጥቂት ጊዜ ታገስ›› አለው፡፡ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ለተራራው ፍቅር አደረባቸው፤ አለቀሱም፡፡ በዚህም ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ዳግመኛ መጥቶ ‹‹አረጋዊ ሆይ አይዞህ! አትፍራ ስልጣን ተሰጥቶሃልና፡፡ በሐረጓ በስተቀኝ በኩል ባለችው ቦታ ተቀመጥ፤ ወደ ተራራው ጫፍ ያወጣህ ዘንድ በገመድ ፋንታ ቁመቱ ስድሳ ክንድ የሆነ ታላቅ ዘንዶ እግዚአብሔር ይልክልሃል›› አለው፡፡ ከዚያም በጾም በጸሎት ሁለት ሱባኤ ይዘው ፲፬ ቀን በዚያ ተቀመጡ፡፡ የታዘዘውም ዘንዶ በሦስት ሰዓት መጣ፤ በዘንዶው ጅራት ላይ ወጥቶ በቅጽበት ከተቀደሰው ተራራ ጫፍ ላይ ደረሰ፤ እንደደረሰም ሦስት ጊዜ ሰገደ። ወዲያው ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ›› እያለ አመሰገነ፡፡ ስለዚህም ቦታው ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሎ ተሠየመ፡፡ በመሸም ጊዜ አነስተኛ ዳቦ አንስቶ ባርኮ መብላት ጀመረ፡፡ ዳቦዋ ግማሽ ስትሆን ስለጠገበ የዳቦውን ግማሽ አምሳል ለኋለኛው ትውልድ ምልክት ትሆን ዘንድ እንጨት ጠርቦ/ቀርጾ/ አስቀመጠ፤ ይህች ምልክት እስከዛሬ ድረስ አለች፡፡ደቀ መዛሙርቱም ከታች ወደ ላይ የሚወጡበትን መሰላል በሠሩ አባታችን አቡነ አረጋዊ ደግሞ መጠነኛ ቤት ሠራና ይዞት የመጣውን ታቦት በውስጡ አስገባ፡፡ እግዚአብሔርንም ስለቁርባኑ ወይም ስለመሥዋዕቱ ለመኑ፡፡ እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ መላእክት ከሰማይ ይዘውላቸው ወረዱ፡፡ ለመኖሪያቸውም ትንሽ በአት አገኙ፡፡ ያለምንም መኝታ በጸሎትና በስግደት በመትጋት ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ተአምራትን አደረጉ፤ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዘው የሚሠቃዩትን በጸሎታቸው ኃይል ፈወሷቸው፤ ያላመኑትን ደግሞ እያስተማሩ አሳመኗቸው፤ ለዚያችም ሀገር ብርሃን አበሩላት።አፄ ካሌብም ‹‹አባቴ ሆይ! በጸሎትህ አስበኝ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለች፤ ኃይልም ታሰጣለች፤ በጠላት ላይም ድልን ታቀዳጃለች›› ብሎ አቡነ አረጋዊን ለመኗቸው፤

ቅዱስ ሚካኤልቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመአምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤልየሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ - የሚለ...
23/10/2023

ቅዱስ ሚካኤል

ቅዱስ ማለት ልዩ፥ ክቡር ማለት ነው፤ ሚካኤል ማለት ደግሞ «መኑ ከመ

አምላክ፥ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?» ማለት ነው። ሚካኤል

የሚለው ስም ቃሉ የዕብራይስጥ ነው፤ ሚ - የሚለው «መኑ» ማለት

ነው፥ ካ - የሚለው «ከመ» ማለት ሲሆን፥ ኤል - ማለት ደግሞ

«አምላክ» ማለት ነው።

ይህን ማለትም የቅዱስ ሚካኤልን ስም በጠራን ቊጥር የምንመሰክረው

ስለ እግዚአብሔር ነው፤ በመሆኑም እግዚአብሔርን በባሕርይ

የሚመስለው፥ በሥልጣንም የሚተካከለው፥ በምድርም በሰማይም

እንደሌለ የሚናገር ልዩ፥ ክቡር ስም ነው። የነቢያት አለቃ ሙሴ ባሕረ

ኤርትራን ለሁለት ከፍሎ ሕዝቡን ያሻገረለትንና ፈርዖንን ከነሠራዊቱ

ያሰጠመለትን አምላክ እግዚአብሔርን በመዝሙር ሲያመሰግን፥ «አቤቱ ፩፥፩፦ «ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?» መሳ ፲፫፥፲፯ የእስራኤል

ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ በመሥራታቸው፥ እግዚአብሔር

በፍልስጥኤማውያን እጅ ለአርባ ዓመት አሳልፎ ሰጥቷቸው ነበር.። በዚህ

ዘመን ከዳን ወገን ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፥ ሚስቱም መካን

ስለነበረች ልጅ አልወለደችም ነበር።

የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ እንደምትፀንስ፥ ወንድ ልጅም

እንደምትወልድ፥ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ

ናዝራዊ እንደሚሆን ነገራት። የሚያሰክር መጠጥ እንዳትጠጣ፥ የረከሰም

ነገር እንዳትበላ፥ በልጁም ራስ ላይ ምላጭ እንዳይደርስ (ፀጉሩን

እንዳትላጨው) አስጠነቀቃት። እርሷም ተመልሳ የሆነውን ሁሉ ለባሏ

ነገረችው፤ «የእግዚአብሔር ሰው ወደ እኔ መጣ፥ መልኩም እንደ

እግዚአብሔር መልአክ እጅግ የሚያስደነግጥ ነበረ፤ ከወዴትም እንደመጣ

ጠየቅሁት፥ እርሱም ስሙን አልነገረኝም፤» አለችው።

ማኑሄም፥ «ጌታ ሆይ፥ ወደ እኛ የላክኸው የእግዚአብሔር ሰው እባክህ

እንደገና ወደ እኛ ይምጣ፤ ለሚወለደውም ልጅ ምን እንደምናደርግ

ያስገንዝበን፤» ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን

ቃል ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በእርሻ ውስጥ ሳለች እንደገና ወደ

ሴቲቱ መጣ፥ እርሷም ፈጥና ባሏን ጠራችው፥ «እነሆ፥ አስቀድሞ ወደ እኔ

የመጣው ያ ሰው ደግሞ ተገለጠልኝ፤» ብላ ነገረችው። እርሱም፦

«ከሚስቴ ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን?» ብሎ ቢጠይቀው «እኔ ነኝ፤»

ሲል

መለሰለት። ማኑሄም፦ «እነሆ ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ነገር፥ ግብሩስ

ምንድነው?» ብሎ ዳግመኛ ጠየቀ። መልአኩም ለሴቲቱ ነግሯት

የነበረውን

ሁሉ መልሶ ነገረው። ማኑሄ ለመልአኩ የፍየል ጠቦት ለማዘጋጀት

ቢፈልግም፦ «አንተ የግድ ብትለኝ እህልህን አልበላም፥ የሚቃጠለውንም

መሥዋዕት ብታደርግ ለእግዚአብሔር አቅርብ፤» አለው። ምክንያቱም

ቅዱሳን መላእክት ቅድሚያ የሚሰጡት ለእግዚአብሔር ክብር ነው።

እነርሱን ግን እግዚአብሔር ራሱ እንደሚያከብራቸውእንደሚያስከብራቸውም

ያውቃሉ።

ማኑሄ የተገለጠላቸው የእግዚአብሔር መልአክ እንደሆነ አላወቀም፥ ሚስቱም አላወቀችም። በመሆኑም፦ «ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ

ስምህ ማን ነው?» በማለት ጠየቀው።

የእግዚአብሔርም መልአክ፥ «ስሜ ድንቅ ነው፥ ለምን ትጠይቃለህ?»

ብሎታል። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቊርባን በድንጋይ ላይ

ለእግዚአብሔር አቀረበ። መልአኩም ተአምራት አደረገ፥ ማኑሄና ሚስቱም

ይመለከቱ ነበር። ነበልባሉም ከመሠዊያው ላይ ወደ ሰማይ በወጣ ጊዜ

የእግዚአብሔር መልአክ በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፥

ማኑሄና ሚስቱም ተመለከቱ፥ በምድርም በግንባራቸው ወደቁ።

(ሰገዱለት)። ይህ መልካም የምሥራችን የተናገረ፥ የተለያዩ ተአምራትን ያደረገ፥ መሥዋዕታቸውንም ወደ ሰማይ ያሳረገ፥ የእግዚአብሔር መልአክ

ቅዱስ ሚካኤል ነው። ሚካኤል ማለት በሁለተኛ ትርጉሙ «የእግዚአብሔር

ነገሩ ዕፁብ ድንቅ ነው፤» ማለት ነውና። መሳ ፲፫፥፩-፳። በዚህም የስሙ

ትርጓሜ ነገረ እግዚአብሔር መሆኑን እንረዳለን።

፩፥፪፦ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፤ ኢያ ፭፥፲፬

ከነቢያት አለቃ ከሙሴ በኋላ በእርሱ እግር ተተክቶ የእግዚአብሔርን ሕዝብ

የመራው ኢያሱ ነው። የመረጠውም ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ነው።

እግዚአብሔርም፦ «በሕይወትህ ዘመን ሁሉ የሚቋቋምህ የለም፤ ከሙሴ

ጋር እንደነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ አልጥልህም፥ ቸልም

አልልህም፤» ብሎታል። ኢያ ፩፥፭። ይህ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሆነለት

ታላቅ ሰው ኢያሱ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት አስፈልጐታል።

ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ለመሆኑ ምልክቱ ቅዱሳን መላእክት

ናቸውና። እግዚአብሔር ባለበት ቅዱሳን መላእክት አሉ፥ ቅዱሳን

መላእክትም ባሉበት እግዚአብሔር አለ። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን

ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደባት ሌሊት የምሥራቹን «እነሆ፥ ለእናንተና

ለሕዝቡ ሁሉ ደሰታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤

እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ

ክርስቶስ ነው።» በማለት ለእረኞች የነገሯቸው ቅዱሳን መላእክት ናቸው።

እረኞቹም፦ «እስከ ቤተልሔም እንሂድ፥ እግዚአብሔርም የገለጠልንን

ይህን

ነገር እንወቅ፥ አሉ።» ሉቃ ፪፥፮-፲፭። በዚህም ቅዱሳን መላእክት

የገለጡላቸውን ምሥጢር እግዚአብሔር ገለጠልን ብለዋል።

ኢያሱ ወልደ ነዌ፥ ሕዝቡን እየመራ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዐይኑን አንሥቶ

ቢመለከት እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ አየ። ወደ

እርሱም ቀርቦ «ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻ

ችን ወገን ነህን?» አለው።

እርሱም «እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ነኝ፤ አሁንም ወደ አንተ

መጥቻለሁ፤» ብሎታል። ኢያ ፭፥፲፫-፲፭። የእግዚአብሔር ሠራዊት

የሚባሉት

ቅዱሳን መላእክት ናቸው። «ያዕቆብም መንገዱን ሄደ፥ በዓይኖቹም

የእግዚአብሔርን ሠራዊት ከትመው አየ፥ የእግዚአብሔር መላእክትም

ተገናኙት። ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ እነዚህ የእግዚአብሔር ሠራዊት ናቸው

አለ፤» ይላል። ዘፍ ፴፪፥፩-፪። ቅዱስ ዳዊትም፦ «ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን

የሚያደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል፤» ብሏል። መዝ

፩፻፪፥፳፩። የእነዚህም (የእግዚአብሔር ሠራዊት) አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል

ነው። ይኽንንም ሐዋርያው ቅዱስ ይሁዳ «የመላእክት አለቃ ሚካኤል»

በማለት መስክሮለታል። ይሁዳ ፩፥፲፪።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

ተፈጸመ የከበረች በረከታችሁ ይደርብን። የብጹዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የባላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ...
01/10/2023

ተፈጸመ
የከበረች በረከታችሁ ይደርብን። የብጹዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት ባዕታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የባላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ። መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ) አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሃሌሉያ ...
29/09/2023

ብፁዕ አቡነ ሰላማ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/ አዲስ አበባ)

አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ሰላማ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአዲስ አበባ ሃሌሉያ ሆስፒታል በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

የብፁዕነታቸውን ሽኝት መርሐ ግብር በተመለከተ በቋሚ ሲኖዶስ እንደተወሰነ ዝርዝሩን የምናሳውቅ ይሆናል።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን

እርጅና ያልገታው ዝለት ያላገኘው አገልግሎትአንተን ማመስገን ... መቆም ዙፋኑ ፊት
28/09/2023

እርጅና ያልገታው ዝለት ያላገኘው አገልግሎት
አንተን ማመስገን ... መቆም ዙፋኑ ፊት

Address

ኮተቤ ካራ
Addis Ababa

Telephone

+251967879122

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Surafel bitaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Surafel bitaw:

Videos

Share

Category



You may also like