25/11/2023
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማቋቋም የቀረበለትን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 15/2016 (ኢዜአ) ፦ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማዋን አስፈጻሚ አካላት መልሶ ለማቋቋም የቀረበለትን አዋጅ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ አዋጁን ያጸደቀው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው።
በዚሁ መሰረት መልሰው የተቋቋሙት ተቋማት፡-
1- የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ
2- የስራ እና ክህሎት ቢሮ
3- የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ
4- የፕላን እና ልማት ቢሮ
5- የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን
6- የህብረት ስራ ኮሚሽን
7- የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን
8- የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን
9- የሲቪል ምዝገባ እና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ
10- የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ
11- የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ናቸው፡፡
ተቋማቱን መልሶ ማቋቋም ያስፈለገው የኑሮ ውድነቱን ለመቀነስ፤ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እና የነዋሪውን ጥያቄ ለመመለስ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ይጠቁማል፡፡