Hanaze media ሀናዜ ሚዲያ

Hanaze media ሀናዜ ሚዲያ ይህ የኢትዮጺያ

 የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም !" ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራ...
07/07/2022



የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም !

" ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር አይቻልም " - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል ድረስ የኪራይ ዋጋ መጨመር የማይቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ለቤት ኪራይ የወጣው ደንብ እስከሚሻሻል የቤት ኪራይ መጨመር አይቻልም ብለዋል።

ከንቲባዋ በመግለጫቸው የከተማ አስተዳደሩ በየ3 ወሩ የሚታደስ መመሪያ እንደነበረው አስታውሰዋል።

በከተማዋ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት በመኖሩ በዜጎች ላይ ጫና እያስከተለ በመሆኑ የቤት ኪራይ መጨመር መከልከሉን አስረድተዋል።

በመሆኑም የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ሁኔታ አይቶ ደንቡ እስካልተሻሻለ ድረስ ምንም አይነተ የቤት ኪራይ ጭማሪ ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

#አከራዮችም ሆኑ #ተከራዮች ይህንኑ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመው ክልከላውን ተላልፈው በሚገኙ ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ አሳስበዋል።

በዚህ ዙሪያ ዜጎች መብት እና ግዴታቸውን በቅጡ ተገንዝበው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።



t.me//hanazemedia

29/06/2022

Follow our tiktok page

tiktok.com/

18/04/2022

Intro of hanaze media

09/03/2022



በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ያሉ ተፈናቃዮች የከፋ ችግር ላይ መውደቃቸው ተገልጿል።

አስተዳደሩ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት " ዋግ ከችግር ቆፈን ላይ ወድቃለች፤ የመከራ ቃፊር እየናጣት ነው የሚደርስላት ትሻለች " ብሏል።

አሁን ላይ ከአበርገሌ፣ ከጻግብጂ፣ ከዝቋላ፣ ከሰቆጣ ዙሪያ፣ ዛታ፣ ወፍላና ኮረም በጦርነት ምክንያት በየቀኑ ከ2000 ሰው በላይ የተፈናቀለ ወለህ ሜዳ ላይ ሰፍሯል እንዲሁም በሰቆጣ ከተማ ከተለያዩ ቦታዎች የሰፈረው ከ52,000 (ከሀምሳ ሁለት ሺህ ) በላይ ህዝብ መሆኑ ተገልጿል

ቤት ንብረቱን ጥሎ በመጠለያ የሚኖረው ማህበረሰብ የማይቻል ችግር ተሸክሟል ተብሏል።

አዛውንቶች፣ እናቶች፣ ህጻናት በአስቸጋሪ ሆኔታ ላይ የሚገኙ ሰሆን ከእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸው እርሀባቸውን እንዳይችሉ በበሽታ ተቆራምደዋል ተብሏል።

አዛውንቶች፣ ጧሪ የሌላቸው ሽማግሌዎች በሽታው፣ እርጅናው እና ረሀቡ እየተፈራረቀባቸው ሞታቸውን እየናፈቁ ነው።

" ዋግ ላይ መቋጫ የሌለው ችግር ፣ እፎይታ የሌለው መከራ፣ እየተፈራረቀ ነው " ያለው አስተዳደሩ " የሰው ልጅ እንደዘበት ሜዳ ላይ ወድቋል ፤ በዋግ ህዝብ ላይ የመከራ ጅራፍ አልለይ ብሏል፤ የችግር ድምጽ በህጻናት አእምሮ ሰፍሮ የሳቅ አንደበታቸው ተዘግቷል " ሲል አስተድቷል።

በዋግ ያሉ ተፈናቃዮች በየጊዜው የሚመጣው የነፍስ ማቆያ እርዳታ ለጥቂት ጊዜ እንቆይ ይሆናል እንጂ ችግራችን በመሰረታዊነት ሊቀርፍልን አይችልም ያሉ ሲሆን ፤ በዋናነት ችግሩ የሚቀረፈው አከባቢያቸው ነጻ ሆኖ ወደቀያችን ሲመለሱ መሆኑን ገልፀዋል።

መንግስት ለአከባቢው #ትኩረት ሰጥቶ ማህበረሰቡን ሊታደግ ይገባል ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ከዋግኽምራ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Tikivah news

 የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ወደ ትግራይ የሚደረጉት የእርዳታ በረራዎች መጨመራቸውን አሳውቀዋል።ከታህሳስ ወር ጀምሮ 210 ሜትሪክ ቶ...
09/03/2022



የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ወደ ትግራይ የሚደረጉት የእርዳታ በረራዎች መጨመራቸውን አሳውቀዋል።

ከታህሳስ ወር ጀምሮ 210 ሜትሪክ ቶን የህክምና እንዲሁም ስነምግብ አቅርቦቶች ትግራይ ክልል መድረሳቸውን ፓወር አመልክተዋል።

ነገር ግን ብቸኛው የተቸገሩትን ሁሉ ለመድረስ የሚያስችለው ፤ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚሄዱበት መንገድ እንደተዘጋ ነው ብለዋል።

700 ሺህ ሰዎች የረሃብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ያሉት ሳማንታ ፓወር " የኢትዮጵያ መንግስት ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦትን ማመቻቸት አለበት " ብለዋል።

Tikivah news

የየካቲት ወር የዋጋ ግሽበት 📈የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የየካቲት ወር 2014 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር...
09/03/2022

የየካቲት ወር የዋጋ ግሽበት 📈

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሽበት መረጃ የየካቲት ወር 2014 ዓ.ም አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ33.6 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

የምግብ ዋጋ ግሽበት የየካቲት ወር 2014 ዓ/ም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

በያዝነው ወር በአብዛኛው በእህሎች ዋጋ ጭማሪ የታየ ሲሆን በአንፃሩ የአትክልት ዋጋ ላይ ቅናሽ ታይቷል፡፡

ምንጭ፦ ካፒታል ጋዜጣ

TTikivah newsnTikivah news

 #ይፈለጋልየኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በምስሉ ላይ ያለውን ግለሰብ በወንጀል እንደሚፈልገው አሳውቋል።ግለሰቡ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣትና በመጠቀም ከተለያዩ ባንኮች ብር አጭ...
09/03/2022

#ይፈለጋል

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከላይ በምስሉ ላይ ያለውን ግለሰብ በወንጀል እንደሚፈልገው አሳውቋል።

ግለሰቡ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎችን በማውጣትና በመጠቀም ከተለያዩ ባንኮች ብር አጭበርብሮ በማውጣት ወንጀል እንደሚፈለግ ነው ፖሊስ የገለፀው።

ፌዴራል ፖሊስ ተጠርጣሪውን የሚመለከት ማንኛውም መረጃ ካልዎት እንዲያሳውቁ ጥሪ ያቀረበ ሰሆን ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጠይቋል።

ስልክ ፡ 0115309139 (ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2:30-11:30)
ስልክ : 0111119475 / 0111711012 (በማንኛውም ሰዓት)
ነፃ የስልክ መስመር 861

Tikivah news

09/03/2022



የዩክሬን መንግሥት ስንዴ፣ አጃ እና መሰል የእህል ምርቶች ከሀገር ውጭ ለገበያ እንዳይቀርቡ ማገዱ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

የግብር እና ምርቶችን የሚመለከተው አዲሱ ሕግ ዩክሬን ውስጥ የተደነገገው በዚህ ሳምንት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

በአሁን ሰዓት ከሩስያ ጋር በጦርነት ላይ የምትገኘው ዩክሬን የምድራችን ከፍተኛ የስንዴ አምራች ሀገር ናት።

በተጨማሪ ዓለማችን ግማሹን የሱፍ አበባ እና ከዚህ ሰብል የሚገኙት ዘይትና ሌሎች ምርቶችን የምታገኘው በአሁን ሰዓት ጦርነት ላይ ካሉት 2ቱ ሀገራት ነው።

ዩክሬን በበቆሎ ምርቷም በዓለማችን የምትታወቅ ሀገር ናት።

Tikivah news

09/03/2022

" የምግብ ዋጋ ጣራ እየነካ ነው "

የዓለም አቀፉ ምግብ ፕሮግራም ኃላፊ ዴቪድ ባስሌይ የዩክሬን ጦርነት የምግብ ዋጋን እንደሚያንረውና ያላደጉ አገራትን ምጣኔ ሃብት ሊያደቅ እንደሚችል አስጠነቀቁ።

ዩክሬንና ሩሲያ የምግብ ምርቶችን በገፍ ከሚያመርቱ የዓለማችን አገራት መካከል ናቸው።

ኃላፊው እንደሚሉት ጦርነቱ አንዳንድ አገራትን ወደከፋ ረሃብ ሊገፋቸው ይችላል።

"ምድራችን ላይ ያለው የከፋ ሁኔታ ወደ ባሰ ሁኔታ አይሸጋገርም ብለን ተስፋ ብናደርግም እነሆ ይሄ ተፈጠረ" ብለዋል ኃላፊው።

ሩሲያና ዩክሬን በአንድ ወቅት የአውሮፓ የዳቦ ቅርጫት ይባሉ ነበር። የምድራችንን ሩብ የስንዴ ምርት አምራች አገራት ነበሩ።

በተጨማሪ ዓለማችን ግማሹን የሱፍ አበባና ከዚህ ሰብል የሚገኙት ዘይትና ሌሎች ምርቶችን የምታገኘው ከ2ቱ ሀገራት ነው።

ሩሲያ በነዳጇ ዩክሬን በበቆሎ ምርቷ የዓለማችን ትሩፋቶች ናቸው።

ዴቪድ ባስሌይ በዓለማችን የረሃብ ስጋት ተደቅኖባቸዋል የሚባሉ ሰዎች ቁጥር ከ80 ሚሊዮን ወደ 276 ሚሊዮን ማሻቀቡን ገልፀዋል። ይህ የሆነው የአየር ንብረት ለውጥና የኮሮና ወረርሽኝ ላይ ሩሲያ በዩክሬን ያወጀችው ጦርነት ሲታከልበት ነው ብለዋል።

ኃላፊው አንዳንድ አገራት አሁን ባጋጠመው ቀውስ ሳቢያ የከፋ አደጋ ፊታቸው ተደቅኗል ብለዋል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ እኚህ አገራት ከፍተኛውን ጥራጥሬ የሚያስመጡት ከጥቁር ባሕር አካባቢ በመሆኑ ነው።

ባስሌይ ፤ "ሊባኖስ ለምሳሌ 50 በመቶ ጥራጥሬ የምታስመጣው ከዩክሬን ነው። የመን፣ ሶሪያ፣ ቱኒዚያ እና ሌሎች በርካታ አገራትን መጥራት እችላለሁ፤ ከዩክሬን በሚያስመጡት እህል ላይ ጥገኛ ናቸው" ያሉ ሲሆን "ነገር ግን አሁን የዳቦ ቅርጫት ከመሆን ወደ ዳቦ ጠባቂነት ስትለወጥ በጣም የሚያስገርም የእውነት መመሰቃቀል ነው" ብለዋል።

Tikivah news

09/03/2022

የተመድ ኢሜል ውዝግብ ፈጠረ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለሰራተስኞቹ በላከው የኢሜል መልዕክት የዩክሬንን ሁኔታ " ጦርነት " ወይም " ወረራ " ብለው እንዳይጠሩ መልዕክት ማስተላለፉን አይሪሽ ታይምስ አስነብቧል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞቹ በዩክሬን ላለው ሁኔታ " ግጭት " ወይም " ወታደራዊ ጥቃት " የሚሉትን ቃላት እንዲጠቀሙ መመሪያ እንደሰጣቸው ገልጿል።

የተመድ ኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት ለሰራተኞች በላከው የኢሜል መልዕክት ሰራተኞች በዩክሬን ላለው ሁኔታ " ጦርነት " ወይም " ወረራ " እያሉ እንዳይጠቀሙ ከመግለፁ በተጨማሪ የዩክሬንን ባንዲራ በግል ወይም ይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ወይም ድረገጾች ላይ እንዳያካትቱ መመሪያ ሰጥቷል።

ይህ ዘገባ ከወጣ ብዙም ሳይቆይ የተመድ ቃልአቀባይ (የትዊተር ገፅ) ዘገባውን በሰራችው የአይሪሽ ታይምስ የአውሮፓ ዘጋቢ ናኦሚ ኦሊሪ የትዊተር ገፅ በመግባት የወጣውን ዘገባ አስተባብሏል ፤ ሀሰተኛ ነው ፤ እንደዛ አልተባለም ሲል ነው ተመድ ዘገባውን ያጣጣለው።

ድርጅቱ ብዙም ሳይቆይ ትዊቱን አጥፍቶታል።

አይሪሽ ታይምስ ተመድ ለሰራተኞቹ የላከውን መልዕክት ሊክደው እንደማይችል እና ማስረጃውም በእጁ ላይ እንዳለ ገልጿል።

በሌላ በኩል የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ በትዊተር ገፃቸው ላይ ክሬምሊን ሩስያ ላይ " ጦርነት " እና " ወረራ " የሚሉትን ቃላት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ እንዳገደችው ሁሉ ተመድም ይህን ያደርጋል ብሎ ማመን እንደከበዳቸው ገለፀው ፤ እንደዚህ ያሉ ዘገባዎች ውሸት ከሆኑ በፍጥነት ውድቅ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

በዚሁ ትዊት ስር የተመድን ኮሚኒኬሽን እመራለሁ ያሉት ሜሊሳ ፍሌሚንግ ፤ አንዳድን ቃላቶችን አትጠቀሙ በሚል ለዓለም አቀፍ ሰራተኞች የተላለፈ ይፋዊ መልዕክት የለም ብለዋል።

Tikivah news

 አሜሪካ በአፋር እና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 250 ሜትሪክ ቶን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።አሜሪካ ድጋፉን ያደረገችው በUSAID በኩል ነው።ለክልሎቹ  የተደ...
09/03/2022



አሜሪካ በአፋር እና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 250 ሜትሪክ ቶን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች።

አሜሪካ ድጋፉን ያደረገችው በUSAID በኩል ነው።

ለክልሎቹ የተደረገው ድጋፍ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ግምት ያለው ምግብ ነክ ያልሆነ ቁሳቁስ ነው፡፡

ድጋፉ በአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽንና በዓለም ስደተኞች ድርጅት (IOM) በኩል ለተጎጂዎች ይደርሳል ተብሏል፡፡

Tikivah news

" የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት አልተፈፀመም " - ገንዘብ ሚኒስቴርየተከሰተውን የምግብ ዘይት መጥፋትና የዋጋ መናር ችግሮችን ለመፍታት የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት  ...
09/03/2022

" የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት አልተፈፀመም " - ገንዘብ ሚኒስቴር

የተከሰተውን የምግብ ዘይት መጥፋትና የዋጋ መናር ችግሮችን ለመፍታት የ40 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ግዥ ስምምነት #አለመፈጸሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ንግድ ቢሮዎች ጋር በመሆን ሰኞ በሰጠው መግለጫ በአገሪቱ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተው የምግብ ዘይት ዋጋ መናር ለመፍታት የሚያግዝ 40 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት በቅርቡ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ አስታውቀው ነበር።

የሚኒስቴሩ የንግድ ዕቃዎች ዋጋ ጥናት፣ ክትትልና ቁጥጥር ዳይሬክተር ወ/ሮ መስከረም ባህሩ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት እያንዳንዳቸው 20 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በልዩ ሁኔታ እንዲያስገቡ አቅጣጫ መቀመጡን ተናግረው ነበር፡፡

ዳይሬክተሯ መበደበኛ የግዥ ሒደቶችን መከተል ወራትን ሊወስድ ስለሚችል በልዩ ሁኔታ የሳዑዲ ዓረቢያ አስመጪ ድርጅት መመረጡንና ሰኞ የካቲት 28/2014 ዓ.ም. ስምምነት መፈጸሙን ተናግረዋል፡፡

ገንዘብ ሚኒስቴር ግን የተፈፀመ ስምምነት የለም ብሏል።

" ዘይት ለማቅረብ የተመረጠም ሆነ ከመንግሥት ጋር ስምምነት ያደረገ አቅራቢ የለም " ያለው ሚኒስቴሩ መንግሥት ሊያስገባ ያሰበው የዘይት መጠንን በተመለከተም፣ ውሳኔ ላይ እንዳልተደረሰና ጉዳዩ በጥናት ላይ ያለ መሆኑን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ዘይት ምን ያህል ነው የሚለውን እየተጠና መሆኑና ጥናቱ ደግሞ በሚቀጥለው ሳምንት ነው እንደሚያልቅ ነው ያሳወቀው።

የሚገባው ዘይት መጠን የሚታወቀው ከጥናቱ በኋላ መሆኑን ገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሪፖርተር : Ethio media center

Tikivah news

 የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ከሩስያ ወደ ሀገራቸው በሚገባ ነዳጅ እና ጋዝ ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቀዋል።አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ የመጣል ውሳኔ ካሳለፈች ሩሲያ ለአውሮጳ...
09/03/2022



የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ከሩስያ ወደ ሀገራቸው በሚገባ ነዳጅ እና ጋዝ ላይ እገዳ መጣሉን አስታውቀዋል።

አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ ማዕቀብ የመጣል ውሳኔ ካሳለፈች ሩሲያ ለአውሮጳ የምታቀብለውን የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦቷን እንደምታቋርጥ መዛቷ ይታወቃል።

ሩስያ የነዳጅ ማዕቀብ ውጤቱ እጅግ የከፋ እንደሚሆን እና ዳፋውም ለዓለም እንደሚተርፍ ማስጠንቀቋ አይዘነጋም።

የምዕራባውያን መንግስታት ከሩስያ በሚገባው የነዳጅ አቅርቦት ላይ ክልከላ ከጣሉ የነዳጅ ዋጋ 300 ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ሩስያ መግለጿ ይታወሳል።

በአሁን ሰዓት በዓለም ገበያ ላይ የ1 በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 140 ዶላር ደርሷል።

Tikivah news

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባህርና አየር የተቀናጀ ትራንስፖርት አገልግሎት (sea-air multimodal transportation) ለመስጠት የሚያስችለውን የጋራ ስምምነት ከጅቡቲ አለም አቀ...
09/03/2022



የኢትዮጵያ አየር መንገድ የባህርና አየር የተቀናጀ ትራንስፖርት አገልግሎት (sea-air multimodal transportation) ለመስጠት የሚያስችለውን የጋራ ስምምነት ከጅቡቲ አለም አቀፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አገልግሎት (IDIPO) እና ከጅቡቲ ኤር ጋር ተፈራረመ።

ስምምነቱ ከቻይና በባህር ወደ ጅቡቲ የሚመጡ ጭነቶችን የአየር መንገዱን ሰፊና ዘመናዊ የካርጎ ጭነት አገልግሎት አቅም በመጠቀም ከጅቡቲ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በአየር ለማጓጓዝ የሚያስችል ነው።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ

Tikivah news

09/03/2022

📍

በቡድን በመደራጀት እና በተናጠል ተሽከርካሪዎችን ሲሰርቁ እና ሲተባበሩ የነበሩ 21 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ፡፡

የተሰረቁ ተሽከርካሪዎችን ማስመለሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው በሶስት ቡድን የተደራጁ 16 ተጠርጣሪዎችን እና በተናጠል የመኪና ስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 5 ግለሰቦችን ነው።

ከሰረቁ ተሽከርካሪዎች መካከል ጥቅምት 17 ቀን 2014 ዓ/ም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አዲሱ ሚካኤል ገነሜ ት/ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የተሰረቀ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-31876 ኦሮ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ሙሉ ለሙሉ ተበታትኖ የተለያዩ አካሎች ለተለያዩ ግለሰቦች እንደተሸጡ ተረጋግጧል።

የተመለሱ ተሽከርካሪዎች የትኞቹ ናቸው ?

• ታህሳስ 7 / 2014 ዓ/ም ለሊት ላይ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ህብረት ኢንሹራንስ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የተሰረቀ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 90972 ኢት የሆነ ሲኖትራክ ተሽከርካሪን ቁጥሩ ኮድ 3A-06160 ኢት የሆነ ሌላ ሰሌዳ ተለጥፎበት ከጅማ ከተማ ከተደበቀበት ማስመለስ ተችሏል።

• ጥር 20 ቀን 2014 ዓ/ም ለሊት ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ላፍቶ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የተሰረቀ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 14623 ደህ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ቁጥሩ ኮድ 3B-31202 አ.አ የሆነ ሌላ ሰሌዳ ተለጥፎበት ከዱከም ከተማ ከተደበቀበት ተመልሷል።

• ጥር 30 ቀን 2014 ዓ/ም ለሊት ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ 1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የተሰረቀ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 08100 ደህ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ሃዋሳ ከተማ ተገኝቷል።

• ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ጎፋ ገብርኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የተሰረቀ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2- 11595 ኦሮ የሆነ ዶልፊን ተሽከርካሪ አዳማ ከተማ ተፈኝቷል።

• በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ቀጨኔ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥር 22 እና ጥር 26 ቀን 2014 ዓ/ም የተሰረቁ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2A- 57471 አ.አ እና ኮድ 1-36397 አ.አ ተሽከርካሪዎች ተመልሰዋል።

• የካቲት 5 ቀን 2014 ዓ/ም ከአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 አባኮራን ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የተሰረቀ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 34574 ኦሮ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ሞተሩን ጨምሮ ሌሎች የተሽከርካሪው የውስጥ አካላት ተፈታተው ከተሸጡ በኋላ የውጪ አካሉ (ቦዲ) በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ሙሉ ወንጌል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግለሰብ መኖሪያ ግቢ ውስጥ እየተቆራረጠ ለሽያጭ ሲዘጋጅ ከህዝብ በደረሰ ጥቆማ ተይዟል፤ የተሸጡ የተሽከርካሪው ሞተርና ሌሎች የውስጥ አካላት ከተሸጡበት በምሪት ተመልሰዋል፡፡

• ከለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ለሚኩራ ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ/ም የተሰረቀ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-12136 ኢት የሆነ ካቻማሊ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ለባለ ንብረቱ ተመልሳል።

በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎቹ ላይ በተደረገው ምርመራ እና ክትትል 9 ተሽከርካሪዎችን መስረቃቸውን በማረጋገጥና ከያሉበት በማስመለስ በአስር (10) መዝገቦች ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

TTikivah newsnTikivah news

07/03/2022

Address

Adama
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hanaze media ሀናዜ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hanaze media ሀናዜ ሚዲያ:

Videos

Share