ቦሌ የሚገኘው ግዙፍ ህንፃ ባለቤት ነኝ ህንፃውን ተዘረፍኩ የሚሉት ይህ ሰው ሰሚ እንዴት አጡ ? እውነታውስ ምንድን ነው ?
የሞቱት አሕዮች ጭንቅላት ተቀያይሮ ቢገጠምም…
በቅድስት ቤተ ክርስቲያችን ትልቅ ስራ ከሰሩና ትልቅ ተጋድሎ ካላቸው ቅዱሳን አባቶች አንዱ ቅዱስ ቶማስ ዘመራስ ነው፡፡ መራስ የትውልድ ሀገሩ ናትና በዚያው ይጠራል፡፡ ዲዮቅልጥያኖስና መክስሚያኖስ በክርስቲያኖች ላይ መከራ ባጸኑበት ዘመን ለ22 ዓመታት የተጋደለው ይህ ድንቅ ሰማዕትና ሐዋርያ ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ፣ ቀንና ሌሊትም በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖችም በመራራት ተጠምዶ የኖረ ነበር፡፡
በጨካኞቹ ነገስታት ዘመንም ለጣኦት እንዲሰግድ የደረሰበትን መከራ ታግሶ በክርስቶስ ፍቅር በመጽናቱ በ22 ዓመታት የመከራ ጊዜው ጨለማ ውስጥ ጥለውት አካሉን እየቆራረጡ ለጣዖታቸው ያጥኑ ስለነበር 2 እግሮቹ፣ 2 እጆቹ፣ 2 ጀሮዎቹ፣ አፍንጫውና ፪ ዐይኖቹ አልነበሩም፡፡ የተጣለበትን ስፍራ የምታውቅ አንዲት ሴትም በስውር እየገባች ትመግበው ነበር፡፡
እኛ በዘመናችን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፍቅር የትኛውን አካላችን እንድንሰዋ አልጠተየቅንም፤ ወይም በረሀብ አልተቀጣንም፡፡ ይልቁንም በነጻነት የምናመልክበት እድል እነዚህ ቅዱሳን አባቶቻችን መከራውን ታግሰው ባቆዩልን እምነት መጽናትና ቤተ ክርስቲያናችንን በተሰጠን ስጋዊና መንፈሳዊ ሃብት ማገዝ ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡
የቤተክርስቲያን የመከራ ዘመን አልፎ ንጉስ ቆስጠንጢኖስ ስልጣን ከ
“በጎዳናህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክትን ስላንተ ያዝዛቸዋል በእጃቸውም ይደግፉሃል፡፡” ይላል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት፡፡ ይልቁንም የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ በርካቶችን ሲጠብቅ በቅዱስ መጽሐፍ ተመልክተናል፡፡ በየዓመቱ በህዳር በ12 ቀን በዓለ ሲመቱ የሚከበረው ቅዱስ ሚካኤል የዋህ፣ ርህሩህ፣ አዛኝ፣ ለወዳጆቹ ቅርብ፣ የሰው ሁሉ ልጆችን ጠላት በእሳት ሰይፍ መትቶ የጣለው በክንፎቹ ረድኤት የሚጠብቀንም ነው፡፡ “በሰማይ ብርቱ ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላአክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም አልቻላቸውም። ከዚያም በኃላ በስማይ ቦታ አልተገኘለትም” ተብሎ በራዕይ 12÷7 እንደተጻፈ ዲያብሎስ በትዕቢቱ ከወደቀ በኋላ የመላዕክት ሁሉ አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
አምላካቻን እግዚአብሔር ወደር የማይገኝለት ኃያል፣ የሚመስለው የሌለ ብርቱ፣ ዘመን የማይቆጠርለት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ መላዕክቱን መንፈስ የሚላኩትን የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው ተብሎ እንደተጻፈ የኃይሉ መገለጫ ከሆኑት አንዱ ናቸው ቅዱሳን መላዕክት፡፡ ይልቁንም የስሙ ትርጓሜ “ማን እንደ አምላክ ማለት የሆነው ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በርካታ ድንቅ ስራ ሰርቷል፡፡ በበዓለ ሲመቱም በየዓመቱ ከሕዳር 12 እስከ የአእላፍ መላእ በዓል እስከሚከበርበት ሕዳር 13 ለሰው ልጆች ሁሉ ከአምላካችን ምሕረት ይለምናል፡፡ ስፍ
#የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኜ ወዳንተ መጥቻለሁ
“በጎዳናህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክትን ስላንተ ያዝዛቸዋል በእጃቸውም ይደግፉሃል፡፡” ይላል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት፡፡ ይልቁንም የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ በርካቶችን ሲጠብቅ በቅዱስ መጽሐፍ ተመልክተናል፡፡ በየዓመቱ በህዳር በ12 ቀን በዓለ ሲመቱ የሚከበረው ቅዱስ ሚካኤል የዋህ፣ ርህሩህ፣ አዛኝ፣ ለወዳጆቹ ቅርብ፣ የሰው ሁሉ ልጆችን ጠላት በእሳት ሰይፍ መትቶ የጣለው በክንፎቹ ረድኤት የሚጠብቀንም ነው፡፡ “በሰማይ ብርቱ ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላአክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም አልቻላቸውም። ከዚያም በኃላ በስማይ ቦታ አልተገኘለትም” ተብሎ በራዕይ 12÷7 እንደተጻፈ ዲያብሎስ በትዕቢቱ ከወደቀ በኋላ የመላዕክት ሁሉ አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
አምላካቻን እግዚአብሔር ወደር የማይገኝለት ኃያል፣ የሚመስለው የሌለ ብርቱ፣ ዘመን የማይቆጠርለት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ መላዕክቱን መንፈስ የሚላኩትን የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው ተብሎ እንደተጻፈ የኃይሉ መገለጫ ከሆኑት አንዱ ናቸው ቅዱሳን መላዕክት፡፡ ይልቁንም የስሙ ትርጓሜ “ማን እንደ አምላክ ማለት የሆነው ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በርካታ ድንቅ ስራ ሰርቷል፡፡ በበዓለ ሲመቱም በየዓመቱ ከሕዳር 12 እስከ የአእላፍ መላእ በዓል እስከሚከበርበት ሕዳር 13 ለ
ከዓይን ሲርቅ የሚደርቀው እንቁላል…
“ሐልዎተ እግዚአብሔር” የእግዚአብሔርን መኖር ከምናውቅባቸው ነገሮች አንዱ ፍጥረታትን መመልከት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን አባቶቻችን ያስተምሩናል፡፡
ይህ ሁሉ ስፍር ቁጥር የሌለው ፍጥረት አስገኚ፣ ፈጣሪ ባይኖረው ከዓለም ጅማሬ እስካለንበት ዘመንና እስከ ዓለም ፍጻሜ ስርዓቱን ጠብቆ ባልኖረም ነበር ይሉናል፡፡
ያውም ከድንቅ ተፈጥሯዊ ባሕርዩ ጋር፡፡ በዚህ ድንቅ ተፈጥሯዊ ባህርይ ከሚታወቁት ፍጥረታት አንዷ ግዡፏ የአእዋፋት ዝርያ ሰጎን ናት፡፡
ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እስኪፈለፈል ድረስ አይኗን ከእርሱ ላይ አታነሳም፡፡ ምግብ ፍለጋ ስትሔድም ወንዱን አስጠብቃ ነው፡፡ አይኗን አንስታ ረጅም ጊዜ ከቆየች ይደርቅና አይፈለፈልላትም፡፡
የመፈልፈያ ጊዜያቸው ሲደርስም ከውጪ ሆና ቅርፊቱን ታንኳኳለች፣ እነርሱም ከውስጥ ሆነው ያንኳኳሉ፡፡ ድምጽ ታሰማቸዋለች፣ እነርሱም መልሰው ድምጽ ያሰማሉ፡፡ ይህን ጊዜ እንቁላሉን ሰብራ ታወጣቸዋለች፡፡
ስታንኳኳ ካላንኳኩ፣ ድምጽ ስታሰማቸው ድምጽ ካላሰሙ ጊዜያቸው ገና ነው አሊያም ሞተዋል፣ ወይም እንቁላሉ ባዶ ነው ብላ ስለምታስብ ትታቸው ትሔድና በዚያው ይደርቃል፡፡
እኛም እንደ ጫጩቶቹ ነን፡፡ አባታችን እግዚአብሔርም የከከበበን የኃጢአት ቅርፊት ሰብሮ የሚያወጣን ዘወትር አይኖቹን ከኛ የማያነሳ ጠባቂያችን ነው፡፡
ይህ
እኔ እና ደጀኔ ....አሞናል😅 ....ቸግሮናል 😅
የጠየከውን አታገኝም?
ሰው መሆን በራሱ ወደ ላይ ማንጋጠጥ፣ አንዱ ጥያቄ ሲመለስ ሌላ መጠየቅ፣ አንዱ ፍላጎት ሲሟላ ሌላኛው ላይ ማተኮር ያለበት ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ እጅግ አጥብቀን ፈጣሪያችንን ጠይቀን የማናገኛቸው ነገሮች ያጋጥሙናል፡፡
ሌሎች በቀላሉ የሚያገኟቸው እኛ ግን ነጋ ጠባ ፈጣሪያችንን ወትውተን ያላገኘነው ነገር ይኖራል፡፡ አልፎ ተርፎም ይህ አጥብቀን የምንሻው ነገር ሊኖረን እንደሚገባ በበርካቶች ዘንድ የሚታመንበት፣ ጥቂት የማይባሉ ሰዎችም እርግጠኛ ሆነው እንዳለን የሚያስቡት ይሆናል፡፡
ታላቁ የቤተ ክርስቲያን ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በረከቱ ይደርብንና እንዲህ ይለናል፡፡ “እግዚአብሔርን ደጋግመህ ጠይቀኸው ያልሰጠህ ነገር ካለ፣ አንተን ደጋግመው ጠይቀውህ ያልሰጠሃቸው ሰዎች እንዳሉ አስብ፡፡” እግዚአብሔር “ፈታሒ በጽድቅ ኮናኒ በርትዕ“ ነውና እንደየስራችን ይከፍለናል፡፡
እገዛችንን ልንሰጣቸው እየቻልን አልፈናቸው የሔድን ስንቶች ናቸው? ጩኸታቸውን እንዳንሰማ መስኮታችንን የዘጋንባቸው፣ ወይም ዳንኪራችንን ከፍ አድርገን ጩኸታቸውን የዋጥንባቸው ስንቶች ናቸው?
የትኛውን ጥሪ ነው በአጽንኦት የሰማነው? ስለበደላችን በቀራንዮ አደባባይ “ኤሎሔ… ኤሎሔ… ላማ ሰበቅታኒ” አባት ሆይ ለምን ተውኸኝ ያለው ጥሪ የኛ አይደለምን? እርሱ የሁሉ ባለቤት ሲሆን “ተጠማሁ” ማለቱ የኛን መጠማት ለ
በኒውዚላንድ ዋና ከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ የአገሬው ተወላጆች ለተቃዉሞ ሰልፍ ወጡ
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በብሪቲሽ እና በአገሬው ተወላጆች ማኦሪ ህዝቦች መካከል የሀገሪቱን ምስረታ ስምምነት እንደገና በሚገልጽ አከራካሪ ህግ ላይ ወደ ኒውዚላንድ ዋና ከተማ የዘጠኝ ቀናት ተቃዉሞን ተቀላቅለዋል።የኒውዚላንድ ፖሊስ እንዳስታወቀዉ አርብ እለት 10,000 የሚጠጉ ሰዎች በሮቶሩዋ ከተማ ለተቃዉሞ የወጡት የስምምነት መርሆች በመቃወም የማኦሪ ባንዲራ በማውለብለብ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ማክሰኞ ይህዉ ተቃዉሞ ወደ ዌሊንግተን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ህጉ ሐሙስ ዕለት የመጀመሪያውን የፓርላማ ንባብ ካለፈ በኋላ ተሳታፊዎች በመላ ሀገሪቱ ከተሞች ሰልፎችን ይደረጋሉ።እርምጃው የማኦሪ ጎሳዎች መሬታቸውን እንዲይዙ እና ጥቅሞቻቸውን እንዲያስከብሩ ሰፊ መብት የሚሰጣቸውን የ184 አመቱ የዋይታንጊ ስምምነትን እንደገና ያሻሽላል።
በአስተዳደር የመሀል ቀኝ ጥምር መንግስት ጁኒየር አጋር የሆነው ኤሲቲ ኒውዚላንድ ፓርቲ ባለፈው አመት ምርጫ ወቅት ቃል የገባውን ረቂቅ ህግ ባለፈው ሳምንት ይፋ አድርጓል፣ እነዚህ መብቶች ተወላጅ ላልሆኑ ዜጎችም ሊተገበሩ ይገባል ሲል ተከራክሯል።
ሁለት አናብስት መቃብሩን ቆፈሩለትና ገንዞ ቀበረው
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስርዓተ ብሕትውናን የጀመረው አባ ጳውሊ ሲሆን አባ እንጦንስ ደግሞ ስርዓተ ምንኩስናን ጀምሯል፡፡
በምድራዊ ሃብት ባለጸጋ የነበረው የጳውሊ አባት ሲያርፍ ታላቅ ወንድሙ ጴጥሮስ የራሱንና ትንሽ ልጅ የነበረው የወንድሙ የጳውሊን ድርሻ ሰጠውና ወንድሙ አካላመጠን ሲደርስ እንዲያስረክበው አደራ አለው፡፡
ጳውሊ አካለ መጠን ደርሶ ድርሻዬን ስጠኝ ሲለው ገና ልጅ ነህ ታጠፋዋለህ ብሎ ከለከለው፡፡ እርሱ ግን በሀሳቡ አልተስማማም፡፡ ስለዚህም ጴጥሮስ ብዙውን አስቀርቶ ጥቂቱን፣ የማረባውን አስቀርቶ መናኛውን ሰጠው፡፡
ጳውሊ በሁኔታው ተበሳጭቶ ወደ ዳኛ ሲሔድ አንድ ሃብታም ሞቶ ሊቀብሩት ይዘውት ሲሔዱ አየ፡፡ ይህን ጊዜ አባቴ ባለጸጋ ነበር ሞተ፣ ይህ ሰውም ሃባታም ነበር ሞቶ እኔም ሃብት ቢኖረኝም እሞታለሁ አለና፣ ወደ ቤት ሔዶ ወንድሙ ጴጥሮስን ሀብቱን ሁሉ አንተ ውሰደው ይቅርብኝ ብሎ ትቶት ወደ አንድ መቃብር ቤት ገብቶ መጸለይ ጀመረ፡፡
ከሦስት ቀናት በኋላም ግማሽ ህብስት ከሰማይ ወረደለት፡፡ ይህን ሲያይም እዚህ ሆኜ ይህን ያሕል በረከት ካገኘሁ ከዓለም ብለይ ድንቅ ተአምር ይደረግልኛል በማለት በረሃ ገብቶ ብሕትውናን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡
የበረከት ስራ እንደንሰራበት የተሰጠን ሃብታችን ለስጋዊ መሻታችን ብቻ እያዋልን የምንኮራ ስንቶቻችን ነ
በኢየሩሳሌም መቅደስ ደጃፍ ላይ ስምንት ሙዳየ ምጽዋት ይቀመጥ ነበር። ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኔዓለም በሴቶች መግቢያ በኩል ባለው ሙዳየ ምጽዋት አጠገብ ቆሞ፣ ሁሉን በሚያውቅ ባህርይው ስጦታውንና ስጦታው የተሰጠበትን ልብ ያይ ነበር። አንዳንዶች ለዝና ሰጡ፣ ሌሎች ስጦታቸውን ኑሮአቸውን ሊያናጋ እንደማይችል በማሰብ ሰጡ።
አንዲት ድሃ መበለት ግን በቤትም በእጇም የነበራትን ሁለት ሳንቲም በሙሉ ሰጠች። ከእነዚህ ከሁለት ሳንቲሞች ውጪ በምድር ላይ ምንም ጥሪት ሀብት የላትም። በዚህ ጊዜ ጌታ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድሃ መበለት ከሁሉ አብልጣ ጣለች እነዚህ ሁሉ ከትርፋቸው ወደ እግዚአብሔር መዝገብ ጥለዋልና ይህች ግን ከጉድለቷ የነበራትን ትዳርዋን ሁሉ ጣለች" አለ፡፡
ይህ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 21፣1-4 የሰፈረው ይህ ቃል የመስጠትን ምንነት ጌታችን በሚገባ ያስረዳበት ነው፡፡ ሁሉ የእርሱ ሲሆን በቸርነትና በልግስና ከሰጠው ላይ ስጡኝ ብሎ ይለምናል፡፡
የዚህች መበለት በጌታችን የተደነቀ መስጠት ብዙ ይነግረናል፡፡ አለማስተዋል እንጂ እንኳን ገንዘባችን እኛ ራሳችን ዋጋ የተከፈለብን የእግዚአብሔር ገንዘቦች ነን።
አንዳንዶቻችን ከሰጠን የሚጎድልብን እየመሰለን እንሰስታለን፣ እግዚአብሔር ግን ስጡኝና ፈትኑኝ፣ የጎደለውን ባልሞላ በረከቱን ባላበዛ ታዘቡኝ ይለናል። ደግሞም ስጦታ ከጉድለት እንጂ ከትርፍ