Faf Media/ፋፍ ሚዲያ

Faf  Media/ፋፍ ሚዲያ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኪነ-ጥበብዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ፣ መልካም ተሞክሮዎች፣ አስተማሪና አዝናኝ መረጃዎች ይተላለፋሉ። የFaf media-ፋፍ ሚዲያ ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን!
(7)

አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ !ጋሞ ልማት ማህበር በጎፋ ለተጎዱ ወንድም ህዝቦች ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚውል ልዩ የሀብት አሰባሰብ ዘመቻ አወጀ!በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደ...
07/23/2024

አስቸኳይ የድጋፍ ጥሪ !

ጋሞ ልማት ማህበር በጎፋ ለተጎዱ ወንድም ህዝቦች ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚውል ልዩ የሀብት አሰባሰብ ዘመቻ አወጀ!

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ እስካሁን የሟቾች ቀጥር ከ157 በላይ መድረሱ የተገለጸ ሲሆን የአስክሬን ፍለጋው አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል:: የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ማወቅ ችለናል፡፡

የጋሞ ህዝብ ከወንድም ጎፋ ህዝብ ጋር አብሮ የደስታና ፈተና ጊዜያትን በመረዳዳት እና በመደጋገፍ የማለፍ የቆዬ ባህል እና ልምድ አለው:: በመሆኑም የምናካሂዳቸው ድጋፎች በአይነትና በገንዘብ የሚሰበሰብ ሲሆን በአካል በተለያዩ ስፍራዎች በመዘዋወር እንዲሁም በኦንላይን(Online) የሚደረግ ይሆናል::

በአካል በመዘዘዋወር በአ/ምንጭ ከተማ በሚገኙ
👉በገበያ፣
👉በሁሉም መንደሮች
👉የግል፣የመንግስት እና ማህበረሰብ አቀፍ ተቋማት በጎ ፈቃደኞቻችንን በመጠቀም ድጋፍ ያሰባስባል፡፡

በድጋፉ በዓይነት የሚፈለጉ የፍጆታ ዕቃዎች
______________________
👉ፉርኖ ዱቄት፣ የበቆሎ ዱቄት፣ ዘይት፣ ፋስታ፣መኮሮኒ እና ወዘተ… አልባሳት እና የተለያዩ ቁሳቁሶች::

በኦንላይን(online)
_____________
👉ከዚያ ውጭ በገንዘብ መደገፍ ለሚፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000021467174 ገቢ በማድረግ የድጋፉ አካል እንዲሆኑ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ማሳሰቢያ:- በኦንላይ(online)ገንዘብ ስትልኩ ማረጋገጫ ስክሪን ሻት(screenshot) በማድረግ በፌስቡክ(fb) ገጻችን አሊያም በቴሌግራም ገጻችን ላይ እንድትልኩልን እናሳውቃለን::

ለወገን ደራሽ ወገን ነው!

በአደጋው ምክንያት የተጎዱና የተፈናቀሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስትና ፓርቲ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አቶ ዓለማየሁ ባውዲ አረጋገጡ  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተ...
07/23/2024

በአደጋው ምክንያት የተጎዱና የተፈናቀሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ለማቋቋም የክልሉ መንግስትና ፓርቲ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አቶ ዓለማየሁ ባውዲ አረጋገጡ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ በአቶ አለማየሁ ባውዲ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የናዳ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን አጽናንቷል።

በአደጋው እስካሁን ባለው መረጃ ወንድ 148 እና ሴት 81 በድምሩ 229 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ተገልጿል።

አቶ ዓለማየሁ ባውዲ በተከሰተው ድንገተኛ አደጋ በጠፋው የሰው ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በራሳቸውና በክልሉ መንግስት ስም ገልጸው፣ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖችም መፅናናትን ተመኝተዋል።

አቶ ዓለማየሁ በመልዕክታቸው የአየር ንብረት ለውጥ እያስከተለ ያለውን ጉዳት በመገንዘብ በተፋሰሶች አካባቢ የሚኖሩ የህብረተሰቡን ክፍሎች ከጉዳት ለመከላከል ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

በአደጋው ምክንያት የተጎዱና የተፈናቀሉ የሕብረተሰብ ክፍሎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግስትና ፓርቲ ድጋፍና የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያደርግ አቶ ዓለማየሁ አረጋግጠዋል።

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በድንገተኛ አደጋው በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውንና ለነብስ አድን ሥራ ቀድመው በስፍራው የተገኙ የቀበሌውን አስተዳዳሪ ጨምሮ መምህራን፣ የጤና እና የግብርና ባለሞያዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በአሁኑ ሰአት ለተጎጂዎች የመጠለያ እና ምግብ በማቅረብ በርብርብ ላይ እንደሚገኙ ሲሉ ገልፀዋል።

የገዜ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ በበኩላቸው በድንገተኛ አደጋው እስካሁን ከ229 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ እና ከአጎራባች ክልሎች እና ዞኖች የተወጣጡ ባለሞያዎች በሥፍራው በመገኘት ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

 #በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትላንት ረፋድ አካባቢ የተከሰተው የመሬት ናዳ እስሁን ባለው መረጃ ከ200 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል። የጎፋ...
07/23/2024

#በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ ትላንት ረፋድ አካባቢ የተከሰተው የመሬት ናዳ እስሁን ባለው መረጃ ከ200 በላይ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳግማዊ አየለ ለሚዲያዎች እንደገለፁት በመሬት ናዳው በአንድ የቤተሰብ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ እነሱን ለማትረፍ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለነብስ አድን ሥራ ወደ ስፍራው ባቀኑ ሰዎች ላይ ተጨማሪ አደጋ በመድረሱ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ችሏል።

በአደጋው ለነብስ አድን ሥራ ቀድመው በስፍራው የተገኙ የቀበሌውን አስተዳዳሪ ጨምሮ መምህራን፣ የጤና ባለሞያዎች እና የግብርና ባለሞያወች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል።

በዞኑ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ አደጋ ያጋጥም የነበር በመሆኑ ነዋሪዎችን የአደጋ ስጋት ካለባቸው አካባቢዎች የማሸሽ ስራ ቢሰራም ተመሳሳይ አደጋ ይደርስበታል ተብሎ ባልታሰበ ሌላ ቀበሌ አደጋው ማጋጠሙ ሁኔታውን ይበልጥ አሳዛኝ አድርጎታል ብለዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ በአሁኑ ሰአት የተጎዱ ሰዎችን ነብስ ለማዳን እና ለተጎጂዎች የመጠለያ እና ምግብ በማቅረብ በርብርብ ላይ ይገኛል ሲሉ አቶ ዳግማዊ ገልፀዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት አመራር ቢሮ እና ከአጎራባች ክልሎች እና ዞኖች የተወጣጡ ባለሞያዎች በሥፍራው በመገኘት ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።

እስካሁን 5 ሰዎች ከናዳው ውስጥ በሕይወት መውጣት መቻላቸውን እና በሕህክምና ተቋማት የጤና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝም የዞኑ አስተዳዳሪ ጠቁመዋል።

በስፍራው የነብስ አድን ስራ እየተከናወነ የሚገኘው በሰው ኃይል ብቻ መሆኑን የጠቆሙት የዞኑ አስተዳዳሪ ለተጨማሪ የነብስ አድን ስራ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም አይነት ድጋፍ እና ትኩረት ወደ ዞኑ እንዲሆን ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተቋማት እየዘገቡ ይገኛሉ።

ጎፋ Tassa Tassa Tassa በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ትላንት በደረሰው የመሬት ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 157 በላይ ደርሷል። እተወጡ ያሉ መረጃዎች ቁጥሩ ከዚህ...
07/23/2024

ጎፋ Tassa Tassa Tassa

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ትላንት በደረሰው የመሬት ናዳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 157 በላይ ደርሷል። እተወጡ ያሉ መረጃዎች ቁጥሩ ከዚህ ልበልጥ እንደሚችል ነው የሚያሳዩት። ማሽን መግባት የማይችልበት ተዳፋት ቦታ ስለሆነ በሰው ኃይል ነው ቁፋሮ ተደርጎ እየተፈለገ ያለው።

07/21/2024

ጦራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአዋቂዎች ጽኑ ህሙማን ህክምናን አገልግሎት አስጀመረ።

ይህ ክፍል በተለያዩ ምክኒያቶች (በአደጋ ወይም በተለያዩ ህመሞች) የተነሳ በራሳቸው መተንፈስ የማይችሉና የግድ በማሽን መተንፈስ ያለባቸው ታማሚዎች የሚተኙበት ነውም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ጥብቅ የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች እንደአስፈላጊነቱ ተኝተው ይታከሙበታል፡፡ ይህም ሪፈራልና አገልግሎቱን ማግኘት እያለባቸው በርቀት ምክንያት የሚሞቱትን ታማሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል፡፡
ክፍሉ ሶስት ሜካኒካል ቬንትሌተሮችና አራት አልጋዎች ያሉት ሲሆን ክፍሉን ለማደራጀት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች (ወራቤ ኮ/ስ ሆስፒታል ፣ ጤና ሚኒስትርና AMIN General Hospital ድጋፎችን ያገኘን ሲሆን በጥቅሉ 10.4 ሚልየን የሚገመት ወጪ ተደርጓል።
በማለት ዶ/ር አብደላ ኡመር የጦራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ሜድካል ዳይሬክተር ለጎብኚዎች አብራርተዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ 46 ሺ በላይ ተማሪ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነዋል።==================-የማህበራዊ ክላስተር የሳምንቱ ዋና ዋና ዜናዎችርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው...
07/21/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ 46 ሺ በላይ ተማሪ የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈትነዋል።
==================-

የማህበራዊ ክላስተር የሳምንቱ ዋና ዋና ዜናዎች

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው የዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሠጣጥ ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቀረቡ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በማህበራዊ ትስስር ገጻተው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት የዋቻሞ ፣ የወልቂጤ እና የወራቤ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የትምህርት ሴክተሩ የየደረጃዉ አመራሮች፣የፀጥታ አካላት ፣ የትራንስፖርት ባለንብረቶች፣ የትምህርት ማህበረሰቡ ፣ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ወላጆችና ሌሎችም አካላት የዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሠጣጥ ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ በክልሉ መንግስት እና በራሴ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ዉጤት እየተመኘሁ ፣ በክረምት ቆይታችሁ በተደራጀ መንገድ በማህበራዊ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራት በመሳተፍ የአቅም ዉስንነት ላለባቸዉ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ እና በሌሎችም ማህበራዊ አገልግሎቶች ንቁ ተሳትፎ ከማድረግ ባሻገር የራሳችሁን አካላዊና አእምሯዊ አቅም በተለያዩ መንገዶች በማጎልበት የመደመር ትዉልድ ስብዕናን ለመጎናፀፍ እንድትተጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል። ።

በዘንድሮ ዓመት በኦንላይን የተሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በቀጣይ ጥቂት ዓመታት ሀገር-አቀፍ ፈተናን ሙሉ ለሙሉ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት መሠረት ያጣለ ነው- አቶ አንተነህ ፈቃዱ

አቶ አንተነህ ፈቃዱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በሁለት ዙር ለማህበራዊ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው የ2016 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል አገር-አቀፍ ፈተና በሠላም በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አላችሁ! አንኳን ደስ አለን ብለዋል።

በዋቸሞ፣ በወልቂጤ፣ በወራቤ እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲዎች የክልሉ 46 ሺ በላይ ተማሪዎች በሠላም ፈተናቸውን አጠናቀው ወደ ቀዬአቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል።

ዘንድሮ ከወትሮ በተለየ ሁኔታ በኦንላይን ጭምር 1,480 ተማሪዎች ተፈትነዋል ያሉት አቶ አንተነህ ይሄም እንደ አገር አገር-አቀፍ ፈተናን በቀጣይ ጥቂት ዓመታት ሙሉ ለሙሉ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረት መሠረት ያጣለ እንደሆነ አረጋግጠናል ነው ያሉት።

የክልላችን ተማሪዎች በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች በሠላም ተፈትነው ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ባለድርሻ አካላት ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።

የወባ በሽታ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የበዛባቸውን አከባቢዎችን በመለየት የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎች ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የወባ በሽታ የማህበረሰብ ስጋት ወደ ማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ የጤና አደጋ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል /PHEOC/ አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ አስታውቋል።

ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣው የወባ በሽታ የማህበረሰቡ የጤና ስጋት ሆኖ እንዳይቀጥል እና የወረርሽኙን ስርጭት ለመቀልበስ እንዲሁም እንደ ክልል እስከ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ድረስ የወባ በሽታ ስርጭትን በ70% ለመቀነስ የተያዘው ዕቅድ ለማሳካት የክልሉ ጤና ቢሮ ግብረ ሀይል የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችል ተቋማዊ አቅም ለመፍጠር በትኩረት እየሠራ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ።

ቢሮዉ የጨቅላ ሕጻናትና ሕጻናት ጤናን በተመለከተ የ2016 በጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ለመገምገም ያዘጋጀዉ መድረክ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ የቢሮዉ ምክትልና የበሽታ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ እንደተናገሩት የጤና አገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ቢሮዉ የመፈጸምና ማስፈጸም አቅም ግንባታ ሥራዎችን በትኩረት እየሠራ ነዉ።

ጥናትን መሠረት ያደረጉና የመፈጸምና ማስፈጸም ክፍተትን የሚሞሉ የአቅም ግንባታ ተግባራት በቀጣይም ታቅደዉ እንደሚፈጸሙ አቶ አሸናፊ ጠቁመዋል።

የጆንጎ ልማት ማህበር ያስገነባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ!በስልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የወሮ ጤና ጣቢያ ግንባታን ጨምሮ ከ40 ሚሊዮን ብር በሚልቅ ወጪ የጆንጎ ልማት ማህ...
07/21/2024

የጆንጎ ልማት ማህበር ያስገነባቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ!

በስልጤ ዞን ምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የወሮ ጤና ጣቢያ ግንባታን ጨምሮ ከ40 ሚሊዮን ብር በሚልቅ ወጪ የጆንጎ ልማት ማህበር ያከናወናቸው ልዩ ልዩ የልማት ፕሮጀክቶች የክልል የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቀዋል።

የምረቃ መርሃ ግብሩን በይፋ የከፈቱት የስልጤ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት መህዲያ ቡሴር በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የአከባቢው ተወላጆች የጆንጎ ልማት ማህበር በሚል ጥላ የማህበረሰባቸውን ችግር ለመፍታት እያከናወኑ ላለው ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ህዝባዊ የልማት ማህበሮች የመንግስትን ጉድለት በመሙላት በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን በማንሳት በዚህ ረገድ የጆንጎ ልማት ማህበር ስራ በመልካም አርዓያነት የሚጠቀስ ዘመን ተሻጋሪ ስራ መሆኑን ወ/ሮ መህዲያ ገልጸዋል።

የእለቱ የክብር እንግዳና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘይኔ ብልካ የጆንጎ ልማት ማህበር የማህበረሰብ ቁልፍ ጉዳይ በሆኑት በትምህርትና ጤና አቅርቦት መስራታቸው ለማህበረሰብ ለውጥ ያላቸውን ተነሳሽነት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።

የተቋማት ግንባታ ብቻውን ግብ እንዳልሆነ ያስታወሱት አቶ ዘይኔ ማህበረሰቡ ተቋማቱን ከመጠበቅ ባሻገር በትምህርቱ ዘርፍ ያለውን የብቃትና የተሳትፎ ችግር መፍታት ላይ ጠንክሮ እንዲሰራ መክረዋል።

በከተሞች የሚኖሩ የአከባቢው ተወላጆች እያደረጉ ያለው ተሳትፎ አመርቂ መሆኑን በመግለጽም በቀበሌዎች የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራዎች ላይ እንዲበረቱ አሳስበዋል።

የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከይረዲን ሀቢብ በበኩላቸው የጆንጎ ልማት ማህበር የወረዳውን ማህበረሰብ መሰረታዊ የልማት ክፍተቶች በመድፈን በኩል ገንቢ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን ገልጸዋል።

የጆንጎ ልማትና በጎ አድራጎት ማህበር የጀመራቸውን የልማት እንቅስቃሴዎች በሁሉም ዘርፎች አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁት አቶ ከይረዲን በወረዳው መንግስት በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግና ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር በአብሮነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የጆንጎ ልማት ማህበር አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ባስተላለፉት መልዕክት ሁለንተናዊ አቅማቸውን በማቀናጀት ወልዶ ላሳደጋቸው ማህበረሰብ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ እንደሚሰሩ ተናግረው ማህበረሰቡ ተቋማቱን በመጠበቅ፣ ልጆቹን በማስተማርና የሞራል እገዛ በማድረግ ከጎናቸው እንዲቆም ጠይቀዋል።

በዛሬው መርሃ ግብር ላይ የመሃል ጆንጎ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ፣ የወሮ ጤና ጣቢያና የሪም የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች የተመረቁ ሲሆን ለግንባታዎች ወደ 42 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ በልማት ማህበሩና በልማት ማህበሩ ውስጥ ባለ በጎ ፍቃደኛ ባለሀብት ፈንድ መደረጉ ተመላክቷል።

በዝግጅቱ ላይ ለተመረቁት የልማት ስራዎች ስኬታማነት አስተዋጽኦ ለነበራቸው ግለሰቦች ተቋምትና ማህበራት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ ስነ ስርዓትም ተከናውኗል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የስልጤ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መህዲያ ቡሴርን ጨምሮ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘይኔ ብልካ፣ የስልጤ ዞን ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ሙሃባ ሙስጠፋ፣ የጆንጎ ልማት ማህበር የበላይ ጠባቂ ሀጂ ሀቢብ ጀማል፣ የልማት ማህበሩ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ባህረዲን አህመድ፣ የልማት ማህበሩ ስራ አስኪያጅ ሽኩር ሸረፋ፣ የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከይረዲን ሀቢብ፣ የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አብዱሰመድ መሐመድ እና ሌሎች የዞንና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘገባው የዞኑ ኮሚኒኬሽን ነው።

07/20/2024

የቀድሞው የደቡብ ብሄር ብሄር ሰቦችና ህዝቦች ክልል በመባል ይታወቅ የነበረው ክልል ከለውጡ ወዲህ እንደሚታወቀው በአራት አዳዲስ ክልሎች መካለሉ ይታወቃል።
ክልሉ 56 ብሄር ብሄረሰቦችን በአንድ አቅፎ በነበረባቸው 30 የሚጠጉ አመታት በጋራ ያፈራቸውን ቋሚና ተንቀሳቃሽ ሀብትን በፍትሀዊነት ለአራቱም አዳድስ ክልሎች እንዳከፋፈለ ተገልጿል።

የሰላም ተምሳሌትና የአብሮነት መናገሽ የጦራ ከተማ አሰተዳደር እንግዶቿን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች..! የጦራ ከተማ አሰተዳደር የተለያዩ ብ...
07/20/2024

የሰላም ተምሳሌትና የአብሮነት መናገሽ የጦራ ከተማ አሰተዳደር እንግዶቿን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አጠናቃ እንግዶቿን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች..!

የጦራ ከተማ አሰተዳደር የተለያዩ ብሔር ብሄረሰቦች ተዋደው እና ተከባብረው የሚኖሩባት የፍቅርና የመቻቻል ከተማ መሆኗ ይታወቃል።

ታላቅ የምረቃት ፕሮግራም ነገ ዕለት እሁድ ሀምሌ 14/2016 የማይቀርበት ቀጠሮ!!

ህጋዊ ዕውቅና አግኝታ ወደ ስራ የገባችው አሸም-ባዴ ታሪክ መስራትዋን ቀጥላላች። በስልጤ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ እድገት ጉልህ አሻራ ለማሳረፍ ትልቅ አለማን አንግባ የተቋቋመችው አሸም-ባዴ ከእ...
07/20/2024

ህጋዊ ዕውቅና አግኝታ ወደ ስራ የገባችው አሸም-ባዴ ታሪክ መስራትዋን ቀጥላላች።

በስልጤ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ እድገት ጉልህ አሻራ ለማሳረፍ ትልቅ አለማን አንግባ የተቋቋመችው አሸም-ባዴ ከእድሜዋ የገዘፉ በርካታ እቅዶችን ነድፋ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች ።
በተለይም በማህበረሰባችን ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ላይ ትኩረት ሰጥታ ለመስራት ዕሩቅ አልማ ተነስታለች።
ይህንን ስራዋን ''ሀ'' ብላ ጀምራለች አሸም-ባዴ። ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎችን በመደገፍ ስራዋን የጀመረችው አሸም-ባዴ ከለጋነት እድሜዋ በላይ የሆነ ትልቅ በጎ አሻራዋን በማሃበረሰቡ ላይ ማሳረፍ ጀምሯለች። አሸም-ባዴ!! በማህበረሰባችን ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ዕሩቅ አልማ የተነሳችው አሸም-ባዴ የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅት ሰሞኑን በአንድ ትልቅ ስራ የማሃበረሰቡ ባህል ቋንቋ እና ታሪክ እሴት ለመጠበቅ እና ለማሳደግ በወንድማችን የተዘጋጀው ''የቀልብ እሴቼ'' በሚል ርዕስ የተዘጋጀችውን መፅሀፍ ለማሳተም እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል። በርካታ ቅን-ልቦች፣ የማህበረሰበብ ተቆርቋሪዎች፣ የጥበብ አፍቃሪዎች የበኩላቸውን ርብርብ እየደረጉም ይገኛል።
አሸም-ባዴ እንደ ተቋም ይመለከተኛል በሚል የዚህን መፅሀፍ 2,000 ኮፒ እና የማሃበረሰቡን ባህል ቋንቋ ታሪክ እሴት ለመደገፍ እንደ ተቋም የራስዋን አሻራ ለማኖር ቃል ገብታለች!!



!!!

ከታች ባሉት የአሽም ባዴ የማሃበራዊ ሚድያ አማራጭ ቤተሰብ ይሁኑ👇
✍የአሸም ባዴ የተለያዩ የማህበራዊ ድረገጾች ሼር ኮፒ በማድረግ ለስልጤ ወዳጅ ዘማድ ቤተሰብ ጥሪ አድርጉ ወደ እዚህ ማህበራዊ ድረገጾች ጋብዙልን
⤵️⤵️⤵️⤵️
ቴሌግራም አድራሻችን ⤵️⤵️⤵️⤵️
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭ https://t.me/+NYUpiF6wrOFiNjY0
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
የፌስቡክ አድራሻችን⤵️⤵️⤵️⤵️
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
https://www.facebook.com/Ashembade1
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
የዋትስአፕ አድራሻችን⤵️⤵️⤵️⤵️
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭
https://chat.whatsapp.com/Dz2YDRyOnDZ2UefZ5bbFVe
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭

ፍልስጤም በፓሪስ ኦሎምፒክ በስምንት አትሌቶች ትወከላለችየፍልስጤም ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪሱን አለማቀፍ መድረክ ፍልስጤማውያን የአይበገሬነት ማሳያ መሆናቸውን እናሳይበታለን ብሏልበ1996ቱ የአት...
07/20/2024

ፍልስጤም በፓሪስ ኦሎምፒክ በስምንት አትሌቶች ትወከላለች

የፍልስጤም ኦሎምፒክ ኮሚቴ የፓሪሱን አለማቀፍ መድረክ ፍልስጤማውያን የአይበገሬነት ማሳያ መሆናቸውን እናሳይበታለን ብሏል

በ1996ቱ የአትላንታ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ፍልስጤም በኦሎምፒክ መድረክ ስምንተኛ ተሳትፎዋን ታደርጋለች!

ከስድስት ቀናት በኋላ በሚጀመረው የፓሪስ ኦሎምፒክ ስምንት ፍልስጤማውያን አትሌቶች እንደሚሳተፉ ተገለጸ።
በቶኪዮው ኦሎምፒክ አምስት አትሌቶችን ያሳተፈችው ፍልስጤም ዘጠኝ ወራት በተሻገረው የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ምክንያት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ባትችልም ስምንት አትሌቶችን ወደ ፓሪስ ትልካለች ተብሏል።

በ1996ቱ የአትላንታ ኦሎምፒክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችው ፍልስጤም በፓሪስ ስምንተኛ የኦሎምፒክ ተሳትፎዋን ታደርጋለች።
በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት 400 የሚጠጉ አትሌቶችና የስፖርት ሰራተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል ወይም ቆስለዋል ያለው የፍልስጤም ኦሎምፒክ ኮሚቴ፥ በዚህ ፈታኝ ወቅት በፓሪስ ኦሎምፒክ አትሌቶቻችን መሳተፋቸው አለም አይበገሬነታችን እንዲመለከት ያደርጋል ብሏል።

በጦርነቱ ምክንያት በኦሎምፒክ ለመሳተፍ ሚኒማ ማሟላት ያልቻሉ በርካታ አትሌቶች በመኖራቸው የአለማቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለሰባት የፍልስጤም አትሌቶች ልዩ ግብዣ አድርጓል።
የቴኳንዶ አትሌቱ ኦማር ኢስማኤል ብቻ ነው በቻይና ታያን ሚኒማ አሟልቶ በፓሪስ የሚሳተፈው።
ለይላ አል ማስሪ እና ሞሀመድ ደውዳር በ800 ሜትር የሚወዳደሩ ሲሆን፥ የ20 አመቱ ዋሰም አቡ ሳል በኦሎምፒክ መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍልስጤምን በቦክስ ውድድር ይወክላል።

ፍልስጤማውያኑ አትሌቶች የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ ሜዳልያ ለማጥለቅና የጽናት ተምሳሌትነታቸውን ለማሳየት የፓሪስ ኦሎምፒክ መጀመርን እየተጠባበቁ ነው።

የፍልስጤም የኦሎምፒክ ኮሚቴ ቴክኒካል ዳይሬክተር ናደር ጃዩሲ የኦሎምፒክ ተሳትፎው በራሱ ድል ቢሆንም “እንደሀገር ምን ማድረግ እንደምንችል ለአለም ለማሳየት ተዘጋጅተናል” ብለዋል።

ፍልስጤም በፈረንጆቹ 1995 የአለም ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል መሆኗን የፍራንስ 24 ዘገባ አውስቷል።

አል-ዓይን አማርኛ እንደዘገበው!

አላሁ አክበር! እነሆ የምስራች!==============አሸም ባዴ የበጎ አድራጎት ማህበር ==============አሸም-ባዴ!አሸም-ባዴ በጎ አድራጎት ድርጅት በስልጤ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ እድገ...
07/20/2024

አላሁ አክበር! እነሆ የምስራች!
==============
አሸም ባዴ የበጎ አድራጎት ማህበር
==============
አሸም-ባዴ!

አሸም-ባዴ በጎ አድራጎት ድርጅት በስልጤ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ እድገት በጎ ተፅዕኖ ለማሳረፍ ትልቅ አለማን አንግቦ የተቋቋመ ሀገር-በቀል ድርጅት ነው። ምንም እንኳን ከተመሠረተ ቅርብ ጊዜ ቢሆንም በርካታ ንድፎች ነድፎ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በተለይም በማ/ሰባችን ባህል፣ ቋንቋና ታሪክ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት እሩቅ አልሞ ተነስቷል። ይህንን ስራውን ''ሀ'' ብሎ ጀምሯል። ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎችን በመደገፍ ጀምሯል። ከለጋነት እድሜው በላይ የሆነ ትልቅ አሻራውን ማሳረፍ ጀምሯል።

በምን አትሉም? ሰሞኑን ''የቀልብ እሴች'' በሚል ርዕስ በሙባረክ ላሉ የተዘጋጀችውን መፅሀፍ ለማሳተም እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል። በርካታ ቅን-ልቦች፣ የማ/ሰብ ተቆርቋሪዎች፣ የጥበብ አፍቃሪዎች የበኩላቸውን እርብርብ እየደረጉም ይገኛል። እኔም እንደ ተቋም ይመለከተኛል በሚል ቃል-በተግባር በማለት የዚህን መፅሀፍ #2000 ኮፒ ለማሳተም ቃል ገብቷል።

አላሁ አክበር!!!

ይህ ነው የመደራጀት ፈይዳው!!

አሻም-ባዴ🙏

https://www.facebook.com/Ashembade1?mibextid=ZbWKwL

ALHAMDULILAH,                                   in this historic day  we have signed and finalized bilateral cotractual ...
07/19/2024

ALHAMDULILAH,
in this historic day we have
signed and finalized bilateral cotractual agreement of Amin general hospital's expantion complex project Arctectural and complete construction design with my bro.Archtect Abdi the general manager of ATM CONSULTANCY, this is a new ste to our hospital which is targetting to be the best international hospital.

Mosmige M***a

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስልጤ ዞንየጦራ_ከተማ_አስተዳደር_የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ያስመርቃል💟ዕሁድ ሐምሌ 14/ 2016 በዚህ ታላቅ የምረቃ ፕሮግራም በክብር ተጋብዘዋልና እንዳይቀሩ 🥰🥰
07/19/2024

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስልጤ ዞን
የጦራ_ከተማ_አስተዳደር_የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ያስመርቃል💟ዕሁድ ሐምሌ 14/ 2016

በዚህ ታላቅ የምረቃ ፕሮግራም በክብር ተጋብዘዋልና እንዳይቀሩ 🥰🥰

አሁን በፖሰትኩት የሀረሸይጣን ፎቶ የተሰጠ አስተያየት እንዲህ ይላል፦  Jemale ✍️ #የፍረኪመ የዳሪ ፋሪስ የስልጤ ባለ ሀብት ሞኝ ነው የሰው ሀገር ያለማል ያበጃል ከዛ ሌባ ተብሎ አጋጣሚ...
07/19/2024

አሁን በፖሰትኩት የሀረሸይጣን ፎቶ የተሰጠ አስተያየት እንዲህ ይላል፦ Jemale ✍️
#የፍረኪመ የዳሪ ፋሪስ
የስልጤ ባለ ሀብት ሞኝ ነው የሰው ሀገር ያለማል ያበጃል ከዛ ሌባ ተብሎ አጋጣሚ ሲመቻቸው ግርግር ሲፈጠር ንብረቱን ያወድሙበታል ይዘርፉበታል በሪል እስቴት የተሰማሩ ባለ ሀብት ስልጤዎች አሉ በሀብት የተንበሸበሹ ባለ ፀጋዎች አሉ ግን ሸቀጥ ላይ ፋብሪካ ላይ ወዘተ ይሰማራሉ የሆቴል ኢዱስትሪ ላይ ቢሰማሩ ይበልጥ ተመራጭ ነበር በዚህ ዙርያ ያለ ለሪዞልት አመቺ ነው አየሩ ተስማሚ ነው ዙርያው ሆቴሎች ሬስቶራንቶች ካፌዎች እንዲሁም የሀገር ባል ማስጎብኛ እና መሸጫ መደብሮች መስኪዶች ተገንብቶ ለጎብኚ ክፍት ቢሆን ለሀገር ተጨማሪ የውጪ ምንዛሬ ምንጭ ነ ው ለክልሉ ውበት እና ለብዙ ወጣቶች የስራ እድል ነው ሚድያ ተጠቃሚ የሆኑ ታዋቂ ስልጤዎች እና ስልጤ ወዳጆች በአጭር ግዜ በማስተዋወቅ የቱሪስት መነሀርያ መሰባሰብያ ማረግ ይቻላል በተለያየ ክልል ያሉ ስልጤዎች ብቻ ይሞሉታል ሌላም ሳይመጣ ግን ተአምረኛ ወንዝ ስለሆነ አለም አቀፍ ዩኔስኮ ላይ አስመዝግቦ አለም አቀፍ ጎብኚዎችን ተቀብሎ ማስተናገድ ይቻላል ጥሩ ውጤት ካስመዘገበ አየር ማረፍያ እራሱ ማስገንባት ይቻላል ጎበዝ ከተሆነ ነቃ እንበል ።

 #ኢትዮጵያዊነት
07/18/2024

#ኢትዮጵያዊነት

የደረሱበትን አንድም አየሁ የሚል ካልተገኘላቸው የስልጤ ዞን ፕሮጀክቶች አዱ አረፋ አደባባይ
07/18/2024

የደረሱበትን አንድም አየሁ የሚል ካልተገኘላቸው የስልጤ ዞን ፕሮጀክቶች አዱ አረፋ አደባባይ

07/18/2024

ኑሪያ ሀሰን
ድምጸ መረዋዋ
ተወዳጅ የስልጤ አርቲስት

የመዲናዋ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል በዚህ መሰረት ፦1. አቶ ያብባል አዲስ - የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ 2. ወ/ሮ ቅድስት ወልደ-ጊዮርጊስ - የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላ...
07/18/2024

የመዲናዋ ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል
በዚህ መሰረት ፦
1. አቶ ያብባል አዲስ - የትራንስፖርት ቢሮ ሀላፊ
2. ወ/ሮ ቅድስት ወልደ-ጊዮርጊስ - የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ
3. ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ - የአረንጓዴና ውበት ቢሮ
4. አቶ ማሾ ኦላና - በምክርቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ
5. ወ/ሮ አንድነት ብዙ ሰው እና አቶ ሁሴለታ ዋቅጅራ - የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ዋና ኦዲተሮች ሆነው ተሹመዋል።5.
ለተሿሚዎች የስኬት ዘመን ይሆንላቸው ዘንድ ልባዊ ምኞት አከልን

ለማለት ከፍ
ማን እንደ ፋፍ!?

 #መስራት  #ይችሉበታል በርቱ አለህ ያግዛችሁ!ማህበረሰቡና የማህበረሰቡ መንግስት በሚገባ ይናበባሉ፤ ይጠቃቀማሉ፤ ይጠባበቃሉ🙏  በሀላባ የሚገነባው አለም አቀፍ ስታድየም በሀላባ ማህበረሰብ ን...
07/17/2024

#መስራት #ይችሉበታል በርቱ አለህ ያግዛችሁ!

ማህበረሰቡና የማህበረሰቡ መንግስት በሚገባ ይናበባሉ፤ ይጠቃቀማሉ፤ ይጠባበቃሉ🙏

በሀላባ የሚገነባው አለም አቀፍ ስታድየም በሀላባ ማህበረሰብ ንቅናቄ ብቻ የተገደበ አይደለምና ለሀገር የሚጠቅምና በስፖርት የበለጸገ ትውልድ ማፍራት ሰው የሆነ ሁሉ የሚመለከት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

በጀርመን አስተናጋጅነት የተካሄደው 17ተኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሙሉ በሙሉ በጫወታ አያልነት ስፔን ዋንጫውን ከፍ አድርጋለች።
07/14/2024

በጀርመን አስተናጋጅነት የተካሄደው 17ተኛው የአውሮፓ ዋንጫ ሙሉ በሙሉ በጫወታ አያልነት ስፔን ዋንጫውን ከፍ አድርጋለች።

የዌሴ እንሰት አይነቶች፣ የእድገት ደረጃዎች፣ የምግብ አይነቶች፣ ባህልን ለመጠበቅ ያለው ጥቅም በርካታ ነው።የስልጤ ማህበረሰብ በአፍሪካ ድንቃድንቅ ያዝመዘገበውን አተካኖ ጨምሮ በርካታ የእንሰ...
07/14/2024

የዌሴ እንሰት አይነቶች፣ የእድገት ደረጃዎች፣ የምግብ አይነቶች፣ ባህልን ለመጠበቅ ያለው ጥቅም በርካታ ነው።

የስልጤ ማህበረሰብ በአፍሪካ ድንቃድንቅ ያዝመዘገበውን አተካኖ ጨምሮ በርካታ የእንሰት ውጤት ምግቦች አሉ።

በጣና ዳርቻ በኢትዮጲያ ጠቅላይ ምንስተር የተሰራው ሌላኛው የገበታ ለሀገር የጎርጎራ ርዞርት ተመርቆ ለህዝብ ይፋ ካዳር ዳር ከሚጮሁት እንቁራሪቶች በላይ በባህር መሀል የሚኖሩ አሳዎች ዝም ብለ...
07/14/2024

በጣና ዳርቻ በኢትዮጲያ ጠቅላይ ምንስተር የተሰራው ሌላኛው የገበታ ለሀገር የጎርጎራ ርዞርት ተመርቆ ለህዝብ ይፋ ካዳር ዳር ከሚጮሁት እንቁራሪቶች በላይ በባህር መሀል የሚኖሩ አሳዎች ዝም ብለው ለአላማቸው ይኖራሉ።

ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ዋንጫውን ለ7ኛ ጊዜ ሲያነሳ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የነበረው ድባብ
07/14/2024

ሻምፒዮኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን ዋንጫውን ለ7ኛ ጊዜ ሲያነሳ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም የነበረው ድባብ

07/14/2024

ትራምፕ ከሞት መትረፋቸው ተገለጸ

Coming soon ✍️✍️✍️
07/13/2024

Coming soon ✍️✍️✍️

07/11/2024

የስልጤ ቡና ቸኮሌትና ጣፋጭ ጣዕም እንዳለው ተረጋገጠ

በኢትዮጱያ ተወዳጅነት ያተረፈው ቡና በማህበረሰቡ ቋንቋ "ቃወ" እንደሚባል ነው መረጃ ካደረሱን አካላት የተረዳነው።

የፌዴራል ቡናና ሻይ ባለስልጣን የጥራት ደረጃና ጣዕም ይፋ ባደረገው መሰረት በስልጤ አፈር የሚበቅለው ቡና ቸኮሌት ጣፋጭ መሆኑን አሳውቋል

በስልጤ አፈር ስንል ከዘረኝነት የምታያይዙ የበሽ**ታው ተ*ጠቂ*ዎች* አላችሁና አታያይዙት። በስልጤም ውስጥ ሆኖ ሁሉአካባቢ ቡና አያበቅልም፣ ብያበቅልም የተለያየ ነው።

የስልጤ ማህበረሰብና መንግስት ትኩረቱን የበለጠ በምን ላይ ማድረግ እንዳለብን አመላካች ነው። ስለሆነም "ግብርናው ላይ ማትኮር እንዳለበት መገንዘብ ያስፈልጋል።

የቡና ግብይት ሰንሰለት በማሳጠር የገበሬውን ተጠቃሚነት ሙሉ በሙሉ ለማስጠበቅ በትኩረት መስራት ይገባል።

ከዚህ ቀደም #በቻይና #ገበያ #የኢትዮጵያ ቡና ተፈላጊነት እየጨመረ በመምጣቱ አገሪቱ የተሻለ ገቢ ከቡና የምታገኝበት እድል መፈጠሩ ተነግሮ ነበር።

በሌሎችም የአለም ሀገራት ሀገራዊ ጥናት በማድረግ ሀገራዊ ተጠቃሚነትን ማስጠበቅ ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።

ከዚህ ቀደም በሮዝመሪ እውቅና እንዳተረፈ ይታወሳል። "ባል ሮዝመሪውን ሽጦ ለሌላ አላማ እያዋለው የቤተሰብ የምግብ እጥረት ስለምያጋጥም የባልና ምስት የንትርክ ርዕስ ሆነ" ለሚለው አሉባልታ ተገንዝበን ማስገንዘብ ላይ ቢተኮር።

እውቀት ዕድል ሲታከልበት ጥቅሙ ይጎላልና #አቶ #ሙርሰል #አማን የስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊና ምክትል አስተዳደር ከቀድሞ በላይ በርታ ስንል ከምስጋና ጋር ነው!!!

ለማለት ከፍ
ማን እንደ ፋፍ
የፋፍ ሚዲያ ቤተሰብ ስለሆኑ እናመሰግናለን!

@ስልጤ ዞን ግብርና መምሪያ

Address

American Fork, UT

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Faf Media/ፋፍ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Nearby media companies


Other Media/News Companies in American Fork

Show All

You may also like