12/03/2024
ሰበር ዜና
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ማክሰኞ መጋቢት 03 ቀን 2016 ዓ.ም
፨ በደቡብ ጎንደር ደራ ሀሙሲት ወረዳ በተደረገ ውጊያ የአገዛዙ ወታደር ከባድ ኪሳራ ማስተናገዱ ተሰማ!
በአሁን ሰዓት የወረዳው ዋና መቀመጫ የሆነችው አምበሳሜ ከተማን ጨምሮ በርካታ የወረዳው አከባቢዎች በፋኖ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙ ታዉቋል።
፨ በጎንደር ዕዝ ጉና ክ/ጦር በእስቴ ደንሳ ብርጌድ የጣና ገላውዲዮስ ሻለቃ ፋኖዎች በደራ ወረዳ አርብ ገበያ፣ ሰኔ ማርያም እና ጎኋፂዮን በተባሉ አከባቢዎች ትናንት መጋቢት 02/2016 ዓ/ም አመሻሹን ጀምረው እስከ ዛሬ ረፋድ በወሰዱት እርምጃ በርካታ የጠላት ተላላኪ ወታደሮች ሲደመሰሱ ከ15 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መማረካቸው ታዉቋል።
በተጨማሪም በቁጥር 19 ነፍስ ወከፍ ክላሽንኮቭ መሣሲያ እንዲሁም ሁለት ስናይፐር እና አንድ ብሬን በፋኖ እጅ መግባቱም ተገልጿል።በተመሣሣይ በአሁን ሰዓት በእስቴ ወረዳ ግንዳጠመም በተባለ አከባቢ ክባድ ትንቅንቅ እየተካሄደ ይገኛል።
ካለፉት ቀናት ጀምሮ በጋይንት ወረዳ ሳሊ፣ ጎብጎብ፣ በታች ጋይንት ወረዳ ደግሞ አርብ ገበያና አጋት እንዲሁም በእብናትና በአንዳቤት ወረዳ በተደረገ ትንቅንቅ አናብስቱ የጎንደር ፋኖዎች ታላቅ ድል መቀዳጀታቸውንም ተገልጿል።
ድል ለአማራ ህዝብ
ድል ለአማራ ፋኖ
ይቀላቀሉ👇
https://www.youtube.com/