Protests against abiy ahmed

Protests against abiy ahmed no medemer

28/09/2021
21/09/2021

"ነፋሪት ከም ዝመፀት ምስ ስማዕና፣ ከም ኩሉ ግዘ ብሰላም እትሓልፍ እዩ መሲሉና ነይሩ።" ህፃን ገነት ፀጋይ ግዳይ ደብደብ ነፋሪት ፋሽስቲ ኣብዪ ኣሕመድ

ህፃን ገነት ፀጋይ ትበሃል። ነባሪት ከተማ ቶጎጋ እያ።ነፋሪት ፋሽሽት ኣብይ ኣሕመድ ፣ኣብቲ ከተማ ኣብ ልዕሊ ንዕዳጋ ተኣኪቦም ዝነበሩ ሰላማዉያን ሰባት ዳግማይ ሓዉዜን ጨፍጫፍ ኣብ ዘካየደሉ እዋን ግዳይ እቲ ደብዳብ ዝኮነት ህፃን እያ።

ንሳ፦ ምስ መሳርሕትና መብራት ንጉስ ክተዋግዕ ከላ "እታ ነፋሪት ከም ኩሉ ግዘ ስኽ ኢላ እትሓልፍ ናይ ሰላም ነፋሪት መሲሉና ነይሩ "ትብል። "ኩሉ ግዘ ነፈርቲ መፅየን ክሓልፋ ኢና ንርኢ። ከምዘን ናይ ወትሩ እዩ መሲሉና ነይሩ። ካብኡ ጠብ ጠብ ኣቢላ ሓሊፋ ክትከይድ ሪኢናያ።"ብምባል ንደብዳብ እታ ነፋሪት ትዝክሮ።

ድሕሪ እዚ ህፃን ገነት ፀጋይ ኢዳ ከም ዝተቆረፀት ትዛረብ። ፋሽሽት ኣብይ ኣሕመድ ኮነ ኢሉ ኣብ ልዕሊ ንዕዳጋ ዝተኣከበ ሰላማዊ ሰብ ጨፍጫፍ ምስ ፈፀመ ግዳያት እቲ ጨፍጫፍ ግልጋሎት ሕክምና ከይረክቡ ከም ዝተከልከለ ይፍለጥ።
"ድሕሪ እዚ"ትብል ህፃን ገነት ፀጋይ፣ ኢደይ ምስ ተቆረፀት ማለታ እዩ። "ኣምቡላንስ መፅየን ናብ ሕክምና እናከድና ከለና ወታደራት ኣብይ ከልኪሎምናስ ገዛና ተመሊስና።" ብምባል ነቲ አሰቃቒ ኩነት ትዝክሮ።

ህፃን ገነት ፀጋይ ኣብ ሐዚ ኮይና ንቅድሚት እንትተቋምት 2014 ዓ/ም ወርሒ መስከረም ትምህርቲ ክጅምር እየ ብምባል፤ ነቲ ዝበፀሓ ግፍዒ ሰራዊት ትግራይ ሕነ ከም ዝፈደየላ ትዛረብ። "ሳላ እቲ ጅግና ሰራዊት ትግራይ ሓራ ወፂና ኣለና። ትግራይ ትስዕር።" ድማ ትብል ብሕራነ።

ኣብቲ 15 ሰነ 2013 ዓ/ም ኣብ ከተማ ቶጎጋ ዳግማይ ጨፍጫፍ ደርጊ ዝበፀሖም ተጋሩ ሓንቲ እየን ወ/ሮ ርግበ ኣለሙ። ዝውንንኦ ቤት-ምግብን መስተን ኣለወን። በቲ ጨፍጫፍ ኣብ ገዝኣ ልዕሊ 10 ሰባት አስከሬኖም ከም ዝወፀ፣ ንሳን ኣሕዋታን ሓዊሱ በዓል ገዝኣ፣ ወላዲኣን ገለ ተገልገልትን ግዳይ እቲ ጨፍጫፍ ከም ዝኾኑ እውን ይዛረባ። "ካብ ደገ ዝመፀ ሰብ እዩ ፍሒሩ ኣዉፂኡና" ይብላ ወ/ሮ ርግበ። ንሰን ኣብ ርእሰንን ሑቐአንን ዝተሃሰያ ኾይነን ካልኦት ኣርባዓተ ስድርአን ከምዝተወቅዑ ይገልፃ።

ኣብቲ እዋን ካብ ህፃን ክሳብ ሽማግለ ከም ዝሞቱን ሬሰኦም እካ ብስርዓት ክርከብ ዘይተከኣለ ግዳያት ከም ዝነበሩን ብምግላፅ እቲ ዳግማይ ሓዉዜን ዝኮነ ጨፍጫፍ ነፋሪት ኣብይ ኣሕመድ መግለፂ ከም ዘይብሉ ፤ብፍላይ ግዳያት እቲ ጨፍጫፍ ዝኮኑ ሰባት ግልጋሎት ሕክምና ከይረክቡ ብወታደራት እቲ ፋሽሽት ብምክልካሉ ህይወቶም ከም ዝሓለፈ ትገልፅ።

15 ሰነ 1980 ዓ/ም ኣብ ልዕሊ ኣብ ዕዳጋ ዝነበረ ህዝቢ ከተማ ሓዉዜን ነፈርቲ ደርጊ ብዝፈፀመኦ ጨፍጫፍ፤ ኣብ ሓንቲ ፀሓይ ልዕሊ 2500 ተጋሩ ብግፍዒ ተቐቲሎም። እዚ ዕለት 15 ሰነ መዓልቲ ሰማእታት ኮይኑ ብመንግስቲ ትግራይ ዝክበር መዓልቲ ሰማእታት እንትኸዉን፤ በቲ ዕለት 15 ሰነ 2013 ዓ/ም ኣብ ከተማ ቶጎጋ ኣብ ልዕሊ ኣብ ከተማ ተኣኪቡ ዝነበረ ሰላማዊ ሰብ ዝበፀሐ መስካሕክሒ ጨፍጫፍ ልዕሊ 64 ሰባት ብምቕታሎምን ኣስታት 200 ሰባት ብምቑሳሎምን እቲ ተግባር ዳግማይ ሓዉዜን እናተበሃለ ይግለፅ።
#ድወት

05/09/2021

ቴሌቪዥን ትግራይ Subscribe ይግበሩ!©Copyright: Tigrai Tv Any unauthorised use, copying or distribution is strictly prohibited...........................................

05/09/2021

ብሩኽ ቀዳመ-ሰንበት
------------------------
Have a great weekend, everyone!

05/07/2021

KMN:- July 04/2021
==================
ክቡራን የኩሽ ሚዲያ ኔትዎርክ ተከታታዮች ዛሬ 1:00 pm በዲሲ ሰዓት አቆጣጠር ከአሉላ ሰለሞን ጋር ስለ ትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ባጠቃላይ የሀገሪቱ ፖለቲካ ዙሪያ በቀጥታ ስርጭት ቆይታ ይኖረናል። ጠብቁን።

27/06/2021

ንፁሃን ዜጎች ላይ የሚፈፀመው ጭካኔ የረዥም ግዜ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ወይስ የጊዚያዊ ስልጠና ውጤት?

18/06/2021

ዝኸበርኩም ተመልከቲና:-
ቴሌቪዥን ትግራይ ሚዲያ ሃውስ ኣብ ሳተላይት ዲሽ ንምክትታል ዝስዕብ ኣድራሻ (ፍሪኮንሲ) ተጠቐሙ::
Dear viewers,
Please use the following frequencies to watch TMH tv on satellite 📡
TMH is back on satellite on the following numbers. Please share & let our people know about it.

Satellite: ABS 3A at 3.0°West
Frequency: 10972
Polarity: vertical
Symbol rate: 30000
FEC: Auto

Satellite: Intelsat 20 at 68.5°East
Frequency: 12562
Polarity: Horizontal
Symbol rate: 30000
FEC: Auto

Satellite: Arabsat at 26°East
Frequency: 12073
Symbol rate: 27500
Polarity: Horizontal
FEC: 3/4

TMH

03/11/2020

ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ

በግፍ በተገደሉ ንፁሃን ዜጎች ደም፣ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘች መሯሯጥ፣ በግፍ ላይ ግፍ መፈፀም ብቻ ሳይሆን፣ እንደተለመደው እውነታውን ለማድበስበስ የሚደረግ ኣደገኛ ፀረ-ህዝብ ሴራ ነው፡፡

ከሁሉ በማስቀደም፣ የትግራይ ህዝብና የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ጥቅምት 22/2013 ዓ/ም በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ቃንቃ ጋዋ ቀበሌ፣ በንፁሃን ኢትዮጵያውያን ወገኖች የደረሰው የግፍ ጭፍጨፋ የተሰማቸው ጥልቅ ሃዘን ይገልፃሉ፡፡ በየትኛውም ስፍራም ሆነ ጊዜ፣ ብሄር ተኮር ጥቃት የትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጥብቅ ያወግዛሉ፡፡
ስለሆነም በንፁሃን ወገኖቻችኝ ላይ በተፈፀመው ግፍ ልባቸው ለተሰበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም የግፍ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች የትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መፅናናት ይመኛሉ፡፡

የትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል፣ በኣሃዳዊ ኣምባገነኑን ቡዱንና ጋሽ ኣሻግሬዎቹ የደረሰባቸው ስፍር ቁጥር የሌለው ብሄር ተኮር ጥቃት በማንኛውም የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰብና ህዝብ ላይ ሊፈፀም ቀርቶ ሊታሰብ እንደማይገባው፣ ዕድሜ ልካቸው ሲታገሉለት የኖሩት እውነታ ነው።
ነገር ግን ትናንት በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ በንፁሃን ወገኖቻችን የተፈፀመው እጅግ ዘግናኝና ኣሳዛኝ ጭፍጨፋ፣ በማን እንደተፈፀመ በትክክል ሳይጣራ፣ በሕገ ወጡ ኣሃዳዊ ኣምባገነናዊ ቡዱን እውነታውን ለማድበስበስ ሲባል እንደተለመደው ጉዳዩን ወደ ሦስተኛ ወገን ማለትም የፈረደባቸው ህወሓትና የትግራይ ህዝብ ወንጅሏል፡፡ ይኸው ህገ ወጡ ኣሃዳዊ ኣምባገነናዊ ቡዱን መሪዎች የጥቃቱ ድርጊት የፈፀመ ኣካል ኦነግ ሸኔ እንደሆነ፣ ህወሓትም ከጀርባው በመሆን እየደገፈው ነው በማለት እንዳሻቸው በሚያሽከራክራቸው ሚዲያዎች፣ ሓሰተኛ የያዙኝ ልቀቁኝ አዛኝ ቅቤ ኣንጓች ቧልት ያለ ምንም ይሉኝታ በማን ኣለብኝነት እየተቀባበሉ፣ በማስተጋባት ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም ይህ የኣዞ እምባ ጭሆት፣ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች፣ ላእላዊነት ኣስደፍሮ ሀገር የካደ ኣሃዳዊ ኣምባገነናዊ ቡዱን ከሻዕቢያ መሪ በመመሳጠር የትግራይ ህዝብና መንግስት በሐይል ለማንበርከክ እያደረጉት ያሉት ዝግጅት ለማቀላጠፍ እንደ እሳት ማቀጣጠያ ቤንዚን ሊጠቀሙበት የከጀሉት ስለመሆናቸው የሚያሳይ ኣደገኛ ፀረ-ህዝብ ሴራ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

በመጨረሻም፣ በግፍ ለተገደሉት ንፁሃን ደም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መሯሯጥ፣ በግፍ ላይ ግፍ መፈፀም ብቻ ሳይሆን፣ እንደተለመደው እውነታውን ለማድበስበስ የሚደረገው ኣደገኛ ፀረ-ህዝብ ሴራ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ ስለዚህ በዋናነት ትናንት በምዕራብ ወለጋ ዞን እንዲሁም ከዚህ በፊት በየቦታው በተለያዩ ኣከባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውና ብሄር ተኮር የጅምላና የግፍ ጭፍጨፋዎች በገለልተኛ ወገን ተጣርተው እውነታው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች እንዲሁም የዓለም ኣቀፍ ማህበረሰብ እንዲያውቀው እንዲደረግ፣ የትግራይ ህዝብና ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጥሪያቸውን ያቀርባሉ፡፡ ስለዚህ ማንኛውም የሰብአዊ መብት ተማጓች ተቋም፣ እንዲሁም የአለም አቀፍ ማህበረሰብ፣ ጊዜው ሳያልፍ እና ነገሮች እንዳይደበቁ፣ በአስቸካይ የማጣራት ሥራቸውን በማከናወን ሀላፊነታቸው ሊወጡ ይገባል፡፡

የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
ጥቅምት 23/2013 ዓ/ም
መቐለ

11/09/2020

Tigray National Anthem.
-----------------------------
Our people and our principles are our true power!

መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና !!

ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና ወይከ ኣይንሰዓርን፤

ሃሩር ፀሓይ ነዳድ ህቦብላ ማይ በረድ
ማይ ማይ ትበል ነብሲ ኣብ ጀቕጀቕ ንረግረግ
ደንጎላ ንተርኣስ በዓቲ ይኹን ቤትና
ለይትን ቀትርን ጉዕዞ ንድከም ይጥመየና
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና
ወይከ ኣይንሰዓርን፤

ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና
ወይከ ኣይንሰዓርን፤

ንከበብ በዛብእ መሬት ትፅበበና
ኣብ ስጋና ይቀርቀር አስናን ፀላእትና
ስጋና ንኣሞራ ደምና ውሕጅ ይኹን
አዕፅምትና ይድቀቕ ሑሩጭ ኮይኑ ይበተን
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና ወይከ ኣይንሰዓርን፤

ዘይንድይቦ ጎቦ ዘይንሰግሮ ሩባ ፍፁም ወይከ የለን
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና
ወይከ ኣይንሰዓርን፤

ናፓልም ምስ መርዛም ጋዝ ፋሽሽታዊ ነዳድ
ሚልዮን ቁምብላታት ኣብ ቅድሜና ይንጎድ
መስዋእትን መቑሰልትን ኪሳራታት ንኽፈል
ዝኸፍአ መከራ ውዲታት ይፍተልተል
መስመር እዩ ሓይልና ህዝቢ እዩ ሓይልና
ትዓወትቲ ኢና (3)

08/09/2020

ትግራይ ትመርፅ!

መረፃና፣ መረፃ መሰል ዓርሰ ውሳነ እዩ!! መረፃና፣ መረፃ ዓርሰ ምሕደራ እዩ! መረፃና፣ መረፃ ምዕቃብ መንነት፣ ድሕንነት ሃለዋትን ህዝብና እዩ!

መረፃና፣ መረፃ ምብራኽ ባህግታት ህዝብና እዩ! ትግራይ ብቓልሳ ዘረጋገፀቶ ዓወት ጨቢጣ ግድን ናብቲ እትሓልሞ ብራኸ ክትግስግስ እያ!!

መስመርና ኣፅኒዕና ንመኸተ!!

ዘለኣለማዊ ክብርን ሞገስን ንስውኣትና!!

08/09/2020
05/09/2020

የትግራይን ምርጫ ለማስቆም ወይም ለማደናቀፍ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚወስደው ማናቸውም ውሳኔ እንደጦርነት አዋጅ ይቆጠራል። በዚህ ምክንያት ለሚፈጠር ችግር ተጠያቂው የፌዴሬሽን ምክር ቤትና ጠቅላይ ሚኒስትሩ መሆናቸውን ወዳጅም ጠላትም ሊያውቅ ይገባል።

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ካቢኔ

26/06/2020
26/06/2020
19/06/2020

Tigrai Independence Party is a political party in Tigrai fighting to create an in… ገብረሚካኤል ገ. ዘርኣፅዮን needs your support for Support Tigrai Independence Party

26/05/2020

“ከመጋረጃ በስተጀርባ በተፈበረከ ሐሰተኛ፣ የበሬ ወለደ ወሬ የሚደናገር ህዝብ ፈፅሞ ኣይኖርም”! የትግራይ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ ግንቦት 17/2012 ዓ/ም (ቴሌቭዥን ትግራይ)

ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ የተቀነባበረ፣ ሓሰተኛ ዴኮሜንታሪ ፊልም ሰርቶ በማሰራጨት፣ በትግራይ ህዝብና መንግስት ላይ ሲሰነዘር የነበረው ብሄር ተኮር ጥቃት፣ ኣገርሽቶቦት፣ ትላንት ግንቦት 16/2012 ዓ/ም፣ በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት፣ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል፣ በብልፅግና ፓርቲ ፌስቡክ ፔጅ፣ በኣዲስ ኣበባ ብልፅግና ፓርቲ ፌስቡክ ፔጅ፣ በኣማራ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ከግል ሚዲያዎች፣ ማለትም በኢሳት፣ በኣባይ ሚዲያ፣ በዘሀበሻ ወዘተ የሚባሉ እንዲሁም መረጃ ዶት ኮም እና ኣዲስ ፋክት በተባሉ ማህበራዊ የሚዲያ ኣውታሮች የበሬ ወለደ ትርክታቸውን ኣሰራጭቷል፡፡

እነዚህ በአንድ ሳምባ የሚተነፍሱ ሚዲያዎች በትግራይ ክልል የተለያዩ ኣከባቢዎች የፀጥታ መደፍረስ መፈጠሩ ተገለፀ፣ በተለያዩ ኣከባቢዎች ማለትም በሽረ እንዳስላሰ እና ኣከባቢዎች፣ እንዲሁም በዋጅራትና ኣከባቢው ሰለማዊ ሰልፎች ተካሄዱ፣ ፍትህ መጓደል ኣለ ወዘተ፣ ስለዚህ ይህ ችግር ወደ ከፋ ደረጀ ከመሸጋገሩ በፊት የፌደራል መንግስት ጣልቃ እንዲገባ ጠየቁ በማለት፣ እንዲሆንላቸው የሚመኙትን ቅዠት፣ ራሳቸው ፈብርከው ሐሰተኛ፣ የበሬ ወለደ ወሬ ኣሰራጭቷል፡፡

በኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት የሚተዳደሩት እነዚህ የሚበዙት ሚዲያዎች ትላንት ያሰራጩት ሐሰተኛ ወሬ ባለፉት ሁለት ዓመታት የፌዴራል መንግስት እያሰተዳደረ ላለው ኣካል እና ለእነዚህ የሚዲያ ኣውታሮች፣ ትልቅ ራስ ምታት የሆነባቸውን በትግራይ ህዝብና መንግስት ያለው እንደ ብረት የጠነከረ ግንኙነት፣ ክፍተት ይፈጥርልናል ብሎው፣ ትላንት ሐሰተኛ ወሬ ማሰራጨታቸው ከንቱ ልፋት ከመሆኑ በዘለለ “ከመጋረጃ በስተጀርባ በተፈበረከ ሐሰተኛ፣ የበሬ ወለደ ወሬ የሚደናገር ህዝብ ፈፅሞ ኣይኖርም”! ይልቁንም የእነዚህ ሚዲያዎች ኣጎብዳጅ ባህሪ ፍንቱው ኣርጎ በማሳየት እርቃናቸው ያስቀረ ቅሌት ውስጥ መግባታቸውን ነው፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል በየትኛውም ኣከባቢ፣ የተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ የተፈጠረ የሰላም መደፍረስና ግርግር ፈፅሞ ያልተሰማ እና መሬት ላይ የሌለ መሆኑን ለወዳጅም ለጠላትም ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ እውነታውም ይሄው ነው፡፡

ስለዚህ፣ ሐሰተኛ ወሬ በማሰራጨት፣ የተጠመዱት እነዚህ ሚዲያዎች፣ በኣጠቃላይ በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ላይ በየዕለቱ እያሳዩ ያሉት፣ ንቀትና ቧልት፣ እንዲሁም በትግራይ ህዝብና መንግስት ላይ እየሰነዘሩት ያሉት ብሄር ተኮር ጥቃት ኣደብ እንዲገዙ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንም፣ ግንቦት 16/2012 ዓ/ም ከላይ ስማቸው በተጠቀሱት እና ለጊዜው ስማቸው ባልተጠቀሱት ሚዲያዎች የተሰራጨውን ሐሰተኛ የበሬ ወለደ ወሬ አጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡

የትግራይ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

15/05/2020
13/05/2020
12/05/2020

ዶር አብይ ሌላ ቦታ እንዳደረገው ትግራይ ወስጥ ለመግባት ባይሞክር ይሻለዋል፣ ትግራይን ከነካ total war / ሙሉ ጦርነት ነው የሚሆነው፤ እኛ ብዙ ጦርነትን አይተናል፣ ጦርነትን የሚያውቅ ይፈራል፣ አይተነኩስም፣ ስለዚህ እኛ ጦርነት እንፈራለን፣ አንፈልግም።

ጦርነት ሲመጣብን ደሞ እንዴት እንደምናሸንፍ እናውቅበታለን፤ ጉራ አይደለም ደጋግመን ያደረግነው ነው። ኮሮችን ደምስሰን ኮሮችን ገንብተናል፣ መካናይዝድ ሐይል ደምስሰን መካናይዝድ ገንብተናል፣ ወታደራዊ መንግስት አፍርሰን፣ ህዝባዊ መንግስት ገንብተናል።

ታጋይ ስየ ኣብርሃ
ከወራት በፊት ከትግራይ ሚድያ ሃውስ ጋር ከነበረው ቃለ መጠየቅ የተወሰደ

07/05/2020
07/05/2020
07/05/2020

"...ገንፎ ኣለሁኝ ለማለት ትተነፍሳለች..." ነው ጨዋታው ፦

በመጨረሻው ሰዓት እንዲህ ማቅራራት ለጓድ መሽሬ ቀርቶ ለጓድ መንጌም ሞቱን ከማቀላጠፍ በቀር የፈየደው ነገር የለም። ኣብዪ ኣሕመድ በትግራይ ህዝብ ላይ ያላዘነበው ተደጋጋሚ የስድብ እና የስም ማጥፋት ትንኮሳ የለም። ከ9 ግዜ በላይ ያደረገውን ሴራዊ ወታደራዊ ጠባጫሪነት በትግራይ ህዝብ ቃሪያ ጥፊ ተጩሎ መመለሱን ያውቃል። ካሁን በኋላ እሚጠብቀው ግን ጥፊ ሳይሆን ዱላ ይሆናል። ዱላው ደግሞ እሳት እሚተፋ ብረት ነው። ያኔ ታድያ ባጣናቸው ጀግኖቻችን ልክ ዕዳውን እምናወራርድበት መልካም ዕድል ይፈጠርልናል። ለትግራይ ህዝብ ጦርነት ገጥሞ በድል ስኬት ማጠናቀቅ ታሪክ ያልመዘገበው የገዛ ባህሉ ነው። እንኳን የትግራይ ሰው የትግራይ ኮረብታዎችም ተዋጊ ናቸው። ባሁኑ ሰዓት የትግራይ ህዝብ 5 ሰባራ ጥይቶችን ያነገቡ 11 ሰዎች ኣይደለም። ይንን ሃቅ እያወቁ ለመፈርጠጥ የግማሽ ሰዓት ቀረርቶ ባላስፈለገ ፤ ዳሩ ኣንበሳ ባለበት የበርካቶች እንስሳት የብሄራዊ ፓርክ ኣሁንም ታላቁ እንስሳ ኣንበሳ መሆኑን ያኔ የኣንበሳ ጭራ በነካኩ ቅፅበት ዳግም ይገነዘባሉ። በቁርጡ ሰዓት የኣብዪ ኣሕመድና ተደማሪ ጀሌዎቹ ምርጫ ያባቶቻቸውን ታሪክ መድገም ብቻ ይሆናል።

➽ ወይ እንደቀደመው ኣባቱ ኣገር ጥሎ መፈርጠጥ ፥

➽ ኣልያም ደግሞ መማረክ ይሆናል። ምናልባት ከዚሁ ታሪክ የሚለው እንደካሁን ቀደም ማርኮ መልቀቅ ህልም ነው 😎

07/05/2020

ምርጫ ካልፈለግክ በእርግጫ ትወጣታለህ!!!
(By Tsegaye Ararssa)
=========================
ክልሎች፣ በፌደራሉ ሕገ-መንግሥትም፣ በክልሎች ውስጥ የበላይ ህግ በሆኑት የክልል ሕገ-መንግሥታትም፣ ምርጫ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ፣ ምርጫ መደረግ በሚገባው ቦታ ሁሉ፣ ምርጫ የማስፈጸም ግዴታ አለበት። ለወገንተኛ ፖለቲካ አጎብድዶ፣ የሕግ የበላይነትንና ሕገ-መንግሥታዊነትን ማክበር አቅቶት፣ ወይም ጠልቶ፣ ይሄን ምርጫ የማስፈጸም ግዴታውን ካልተወጣ፣ የሕግና የታሪክ ተጠያቂነቱን ተሸክሞ ወደ ፍፃሜው ይወርዳል።

በክልሎች የሚካሄድን ሕገ-መንግሥታዊ ምርጫ ማስቀረት ወይም ማስተጓጎል ግን በፍጹም አይችልም።

ምርጫ ቦርድ፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ102 መሠረት ምርጫ የማስፈጸም ሥልጣንና ኃላፊነት ተሰጠው እንጂ፣ ምርጫ የማገድ፣ የማስተጓጎል፣ ወይም የማራዘም፣ መብት አልተሰጠውም።

ምርጫ የማድረግ ግዴታ የተጣለበት ተቋም ነው ማለት፣ ምርጫ እንዳይደረግ ብሎ የመከልከል ሥልጣን ያለው ተቋም ነው ማለት አይደለም።

ይሄ ተቋም ምርጫ የማስፈጸም ግዴታ አለበት ማለት፣ ሌላ ተቋም ምርጫ ማስፈጸም አይችልም ማለት አይደለም። ምርጫ ቦርድ ግዴታ አለበት ማለት፣ ምርጫ ለማካሄድ (በተለይ ደግሞ ለመከልከል) የብቻ መብት (exclusive right) ያለው ብቸኛ ተቋም ነው ማለት አይደለም።

በምርጫ ቦርድ ስንፍና ወይም ፖለቲካዊ አሻጥር ምክንያት የሕዝቦች ድምፅ አይታፈንም። ምርጫ ይካሄዳል። ሊካሄድም ይገባዋል። ይሄ የሕግም፣ የሞራልም፣ የዴሞክራሲያዊ ፖለቲካም ግዴታ ነው።

ምርጫ ቦርድ ምርጫ አላስፈፅምም ካለ፣ ክልሎች፣ ጊዜያዊ (ወይም ቋሚ) የምርጫ አስፈፃሚ ተቋማትን በማቋቋም (ወይም ሌሎች ተቋማት በጊዜያዊነት ምርጫን እንዲያስፈጽሙ መልሶ በማደራጀት)፣ በክልሎቻቸው ውስጥ ምርጫን የማካሄድ መብትም፣ ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታም አላቸው። ይሄን አለመቀበል፣ እንደ እኔ በግድ ሕገ-ወጥ ካልሆናችሁ ብሎ መፎከር ነው። ይሄን አለመቀበል፣ ሕጋዊነትን በሕገወጦች ለማስፈራራት መሞከር ነው። ይሄን አለመቀበል፣ አላስፈላጊ ግጭትን የሚቀሰቅስ ትንኮሳ ነው።

በተረፈ፣ በዚህ ትንኮሳ ለሚፈጠረው የለየለት ፖለቲካዊ (እና ወታደራዊ) ቀውስ፣ ብቸኛው ተጠያቂ፣ "ሕገ-መንግሥቱ ያስቀመጠውን ድንጋጌ ተከትላችሁ ምርጫ ካደረጋችሁ የኃይል እርምጃ እወስዳለሁ" እያለ የሚዝተው፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን የሚከለክል "ዴሞክራት መሪ" በመሆን ቀዳሚ ሆኖ የተመዘገበው፣ አብይ አህመድ፣ ይሆናል።

!
!

07/05/2020

ፐigray

07/05/2020

ለ ኮለኔል አብይ የተሰጠ መልስ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚፈራላቸው ካገኙ ዛሬ ደርዘን ማስፈራርያ ለቀዋል። አንድ መሪ ህግ ኣክብሮ ሌሎችም ህግ እንዲያከብሩ ማድረግ አለበት እንጂ የጦርነት ነጋሪት ሞግሰም የለበትም። ይህ ግልፅ ሽብር መንዛት ነው። ይቅር የማይባል ትልቅ ወንጀል ነው። ህዝብ ተረጋግቶ የእለት ተለት ኑሮውን እንዳይመራ ከዛሬ ነገ ጦርነት ይነሳል ብሎ እንዲፈራ የሚያደርግ አገራዊ ሽብር ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመስከረም በሁዋላ በስልጣን ላይ ለመቀጠል ካላቸው ሰማይ ጥግ የሚደርስ ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ ህጋዊ ጥያቄ በተነሳ ቁጡር ደማቸው እየፈላ በጣም እየተቸገሩ ነው። ከልክ ያለፈ የስልጣን ጥማት ህሊናን እውር ያደርጋል። ከመስከረም በሁዋላ ያለ ምርጫ የኮሮና አምባገነንነት ለመጫን ነው ያ ሁሉ ዛቻቸው። ዛሬ በተለቭዥን መስኮት ብቅ ብለው እስከ መጪው ምርጫ እኔ ነው የምመራው ብለው በግላጭ የነገሩን የኮሮና ዲክታተርሽብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለመትከል ነው። ሀገሮች ከ30 ዓመት በላይም ያለ ምርጫ የቆዩ አሉ ብለው የውስጣቸውን ፍላጎት በአደባባይ ቆመው እንደዋዛ የነገሩን ሰውየ ከመስከረም በሁዋላ ከኔ ውጪ ማንም አይመራም ማለታቸው የሚደንቅ አይደለም። የኢሳያስ መንገድ የሙጡኝ ብለው ተያይዞውታል። ዛሬ ከረፋዱ ተነስተው ይህ የኢሳያስ መንገድ የሚቃረን ሁሉ አልታገስም ብለውናል። ትግራይ ምርጫ ታደርጋለች የሚል ውሳኔ የጭን ቁስል እንደሆነባቸው ብቻ ሳይሆን የኢሳያስ መንገድ ህልማቸው በእንጭጩ የሚቀጭ ሆኖ አግኝተውታል። እሳቸው እንደ አገር መሪ ሀላፊነት የሚሰማቸው ቢሆኑ ኖሮ ትግራይ የምታደርገውን ምርጫ አድንቀው የአገሪቱ ቦርድ ልከው ፍታሃዊና ተቀባይነት ያለው እንዲሆን እንደ መንግስት ማገዝ ይኖርባቸው ነበር። ያም ሆነ ይህ ህዝባችን በዚህ ተልካሻና ምክንያት የሌለው ዛቻ ሊፈራ ይቅርና አንድነቱ ይበልጥ እያጠበቀ ዳግም ወርቃማ ታሪክ ወደ መስራት እንደ ሚሳኤል ይምዘገዘጋል። የትግራይ ክልል መንግስት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛቻ በዋዛ ሊያልፈው አይገባም። ግልፅ ምላሽ ሊሰጥ ይገባል።
ዓባይ ትግራይ!
1. ምርጫ የማድረግ
2. የራስዋን እድል በራስዋን የመወሰን
ሙሉ መብቷ ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታና ያለ ምንም መሸራረፍ መከበር አለበት።
ዓወት ንዓባይ ትግራይ!

06/05/2020

#ጋዜጠኛ: በትግራይ ደረጃ ምርጫ ማካሄድ ምርጫ ቦርድ ባይፈቅድስ?

: ምርጫ ቦርድ እኮ ወረቀት የሚያድል ተቋም ነው። ምርጫ ቦርድ የመምረጥ መብት የሚያረጋግጥ ተቋም ኣይደለም።
ኣቶ ጌታቸው ረዳ

Address

Mekelle
Mekelle
0970950970

Telephone

0951076763

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Protests against abiy ahmed posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category


Other Newspapers in Mekelle

Show All