08/05/2024
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ለመደበኛ ሰራዊት አባልነት ፣ ለጤና ሙተኞች ፣ ለኢንጂነሪንግ ፣ እንዲሁም በሳይበር የሙያ ዘርፎች መስፈርቱን ለሚያሟሉ ሁሉ ለመመልመል ማስታወቂያ አውጥቷል ፡፡
በዚህም መሰረት አጠቃላይ እና ዝርዝር መስፈርቶቹ ከዚህ በታች እንደሚከተለው የተዘረዘረ ሲሆን መስፈርቱን የምታሟሉ ሁሉ መጥታችሁ እንድትወዳደሩ እና እንድትሳተፉ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽ/ቤት እና ሚሊሻ ፅ/ቤት ያስታውቃል ፡፡
#አጠቃላይ #የምልመላ #መስፈርቶች
1.1. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት የተቀበሉ፣ በህዝቦች ሉአላዊነትና አንድነት የሚያምኑና አገራቸውን ለማገልገል ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑ፣
1.2. ከማንኛውም የፓለቲካ ድርጅቶች ወገንተኝነት ነፃ የሆኑ፣
1.3.ከአሁን በፊት የመከላከያ፣ የፖሊስ እና የክልል ልዩ ሃይል አባል ያልነበሩ፣
1.4. አሁን ካለው ወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ በመነሳት የጽንፈኞቹ ፋኖና ሸኔ አባልና ደጋፊ ያልሆኑ፣
1.5. በትግራይ ክልል በተደረገው ውጊያ ያልተሳተፈ፣
1.6. በወንጀል ይሁን በፍታብሄር ተከሶ የፍርድ ቤት ክርክር የሌለባቸው፣
1.7. ዜግነት ኢትዮጵያዊ፣
1.8. መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና ወስዶ ከተመረቁ በኋላ ለ7 ዓመት ለማገልገል ውል ለመፈፀም ፍቃደኛ የሆኑ፣
1.9. በመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መብትና ግዴታቸውን አውቀው በተመደቡበት ቦታ ሁሉ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ፣
1.10.በተቋሙ የሚሰጣቸውን ስልጠናዎች ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆኑ፣ ከየትኛውም አጉል ሱሶች ከሲጋራ፣ ከጫት፣ ከሀሽሽ እና ከሌሎች ሱሶች ነፃ የሆኑ፣
1.11. በአካባቢው ማህበረሰብ የተመሰገነ ባህሪ እና ስነ-ምግባር ያላቸው፣
1.12. ከሚኖሩበት አካባቢ ከተለያዩ ወንጀሎችና ፀረ-ህዝብ ተግባር ነፃ ስለመሆናቸው ከአስተዳደር አካላትና ከፖሊስ የጽሁፍ ማስረጃ እና የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ ማቅረብ የሚችሉ፣
1.13.በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ተመልምለው የሚገቡ በተማሩበት ሙያ እጥፍ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ፣
1.14.ሙሉ ጤንነት ያላቸውና ስልጠናው የሚጠይቀውን የህክምና ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆኑና በምርመራው ማለፍ የሚችሉ፣
1.15.ትዳር ያልመሰረቱ ልጅ ያልወለዱ፣
1.16.ዕድሜ ለወንድም ለሴትም ተመልማዮች ከ18 እስከ 24 ዓመት የሆኑ፣
II. #አካላዊ #መስፈርት
2.1.የተስተካከለ ቁመና የእግር፣ የእጅ፣ የአንገት፣ የወገብ መሰበር እና ሌሎችም ችግሮች የሌለባቸው፣
2.2.የአይን፣ የአፍንጫ፣የጆሮ፣ የጥርስ እና የከንፈር መሰንጠቅ ችግር የሌለባቸው፣
2.3. ከቲቪ፣ ከሚጥል በሽታ፣ ከስኳር፣ ከደም ግፊት፣ ከኪንታሮት እና ከእንቅርት በሽታዎች ነፃ የሆኑ፣
2.4.ቁመት ለወንድ 1.60 ለሴት 1.55 ሜትር እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
2.5.ክብደት ለወንድ ከ50-70 ለሴት ከ45-60 ኪ/ግራም የሆኑ፣
III. #ለመደበኛ #ሰራዊት #የአካዳሚክ #መስፈርት
· ለወንድ ተመልማዮች 8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ እና ከዚያ በላይ የሆኑ
· ለሴት ተመልማዮች እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም ዲፕሎማ ወይም በሌቭል ያጠናቀቁና የብቃት ማረጋገጫ(COC) ያላቸው እና ከዚያ በላይ የሆኑ የ8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ካርድ ማቅረብ የሚችሉ
· ሁሉም ተመልማዮች ኦርጅናል ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
IV. #በመከላከያ #ዩኒቨርስቲ #ለኢንጂነሪንግና #ጤና #ሳይንስ #ትምህርት #የሚገቡ #ተመልማዮች #የመመልመያ #መስፈርት
· በተፈጥሮ ሳይንስ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስዶ/ወስዳ በ2011፣2012 ዓ.ም እና በ2013፣በ2014 ወይም በ2015ዓ.ም የዩኒቨር
· በ2011 የትምህርት ዘመን ለተፈተኑ ለወንድም ለሴትም 140 እና ከዚያ በላይ
· በ2013 የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዙር ለተፈተኑ ለወንድም ለሴትም 330 (የሲቪክስ ውጤት አይያዝም)
·በ2013 የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ዙር ለተፈተኑ ለወንድም ለሴትም 350 እና ከዚያ በላይ
· በ2014/2015 የትምህርት ዘመን ለተፈተኑ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው
·የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ለተፈጥሮ ሳይንስ በኢንግሊዘኛ፤ በሂሳብ፤ በፊዚክስና በኬሚስትሪ ከማዕከላዊ ነጥብ ከፍ ያለ (C) እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
V. #በመከላከያ #ዩኒቨርስቲ #ለሪሶርስ #ማኔጅመንት #ትምህርት የሚገቡ ተመልማዮች የመመልመያ #መስፈርት
· በማህበራዊ ወይም በተፈጥሮ ሳይንስ በ2011፣ 2012፣ 2013፣ 2014 እና 2015 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ፣
·በ2011 የትምህርት ዘመን ለተፈተኑ ለወንድም ለሴትም 140 እና ከዚያ በላይ
· በ2012 የትምህርት ዘመን ለተፈተኑ ለወንዶች 330 ለሴቶች 320 እና ከዚያ በላይ
·በ2013 የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዙር ለተፈተኑ ለወንድም ለሴትም 250 እና ከዚያ በላይ (የሲቪክስ ውጤት አይያዝም)
· በ2013 የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ዙር ለተፈተኑ ለወንድም ለሴትም 300 እና ከዚያ በላይ
·በ2014 የትምህርት ዘመን ለተፈተኑ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው
·የ2015 የትምህርት ዘመን ለተፈተኑ የትምህርት ሚኒስተር የሚያውጣውን የዩንቨርሰቲ መግቢያ ነጥብ የሚያሟሉ
የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ለማህበራዊ ሳይንስ በጆግራፊ እና በሂስትሪ /ታሪክ/ ከማዕከላዊ ነጥብ ከፍ ያለ (C) ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
· በምልመላ ወቅት የ8ኛ ክፍል፣ ከ9ኛ እስከ 10ኛ እና 11ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ወይም እስከ መሰናዶ ትምህርት ድረስ ያለውን የትምህርት ድረስ ያለውን የትምህርት ውጤት /ትራንስክርቢት /ማቅረብ የሚችሉ
· በስራ ፈጠራ ወይም በልዩ ችሎታ እና ትምህርት የላቀ ውጤት ያላቸው ይበረታታሉ
·በቴክኒክና ሙያ ፕሮግራም በደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ ያጠናቀቀና የብቃት ማረጋገጫ (COC) ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ (COC) ካገኙ በኋላ በሙያ 02 ዓመትና ከዚያ በላይ የሰሩ
·ዩኒቨርሲቲው ከሚያስተምርባቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ውጭ በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሮአቸው በኢንጂነሪንግ፤ በጤና ሳይንስ፤ በሀብት አስተዳደር፤ እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ ለመማር የሚፈልጉ
· በተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በመደበኛ የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርት በመከታተል ላይ የሚገኙና የየሴሚስተሩን የትምህርት ውጤት ሪፖርት ማቅረብ የሚችሉ
· ለጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከኢንጂነሪንግ መስክ ውጭ በሳይንስና ተዛማጅ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁና ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ማቅረብ የሚችሉ
VI. #ለሳይበር #ሙያተኛ #የመመልመያ #መስፈርት
የትምህርት ሁኔታ
· በኮምፒዩውተር ሳይንስ፣ በኮምፒዩውተር ኢንጂነርንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በኮምፒዩውተር ኔትወርክና ሃርድ ዌር፣ በኢንፎርሜሽን ሲስተም በሳይበር ደህንነት በኮምፒዩውተር ኔትወርክና ሴኩሪቲ በሶፍት ዌር ኢንጂነሪግ፣ በማቲማቲክስ፣ ሳይኮሎጂ፣ በኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪግ፣ በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪግ፣ በኤሌክትሮኒክስ ዋርፈር የተመረቁ የመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው፡፡
- የጤንነት ሁኔታ ሙሉ ጤንነቱ በሃኪም የተረጋገጠ
- የዕጩ መኮንን ኮርስ ወስዶ ወይም ወስዳ ለመስራት ፍላጎት ያለው/ያላት
-ወደ መከላከያ ሳይበር ገብቶ /ገብታ ለመስራት ፍላጎት ያለው/ያላት
- የሳይበር ሙያ የሚጠይቀውን ሙያዊ ድስፒሊን የሚያሟላ/የምታሟላ
NB፦ ሁሉም ተመልማዮች በተራ ቁጥር 1 ከላይ የተዘረዘሩ አጠቃላይ የምልመላ መስፈርቶችን ማሟላት ይኖርባቸዋል።እንዲሁም በምዝገባ ወቅት ኦሪጅናልና ኮፒ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
የምዝገባ ቦታና ጊዜ
Ø ተመዝጋቢዎች በምስራቅ መስቃን ወረዳ ስር በሚገኙ የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች፣ የምስራቅ መስቃን ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የምዝገባው ጊዜ ከሚያዝያ 15/08/2016 ዓ.ም እስከ ግንቦት 09 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይሆናል ፡፡
በሁሉም ቀበሌዎቻችን ዝርዝር የመመልመያ መስፈርቶች ተለጥፎ የሚገኙ መሆኑን እንገልፃለን።
የአገር መከላከያ ሚኒስቴር
ሚያዝያ 2016 ዓ.ም
እንሴኖ
ቴሌግራም፦ t.me/misrakmeskanworedacommunication
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/mesrakmeskan/
ኢ-ሜይል፦[email protected]
ዩትዩብ፦https://youtube.com/channel/UCH3dI7vy2ULtrlosd_GtqcQ