18/12/2023
የባስኬቶ ዞን አስተዳደር ከፋን ኢትዮጵያ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር "ሾልአ_ካሻ" በዓልን ምክንያት በማድረግ 8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ልካሄድ ነው።
ላስካ ታህሳስ 8/2016 ዓ.ም (ባስኬቶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የባስኬቶ ዞን አስተዳደር ከፋን ኢትዮጵያ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር የባስኬት ብሔረሰብ ምስጋና በዓል ለሆነው "ሾልአ_ካሻ" በዓልን ምክንያት በማድረግ 8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ይካሄዳል።
የፋን_ኢትዮጵያ መስራችና ስራአስኪያጅ አትሌት ወ/ሪት ፋንቱ ሜግሶ በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ ተገኝተው ከባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳደሪ ኢንጂነር ፍሬው ፍሻለው ጋር ውይይት አድርገዋል።
የባስኬቶ ዞን አስተዳደሪ ኢንጂነር ፍሬው ወደ አከባቢያችን ለመምጣት የመንገዱ ችግር አሳሳቢ ብሆንም ይህ የህዝቡ ችግር የእኔ ችግር ነው ብለው ብዙ ያልተዘመረለትና ያልተዘፈነለት አከባቢን ለማስተዋወቅ እስከዚህ ድረስ በመምጣታቸው በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የፋን ኢትዮጵያ መስራችና ስራአስኪያጅ አትሌት ወ/ሪት ፋንቱ ሜግሶ የእኛ ዋና ዓላማችን ብዙ ያልተዘመረላቸውና ያልተዘፈነላቸው አከባቢዎችን የማስተዋወቅ በመሆኑ እስከዚህ ድረስ በመምጣቴ ልዩ ደስታ ይሰማኛል ብለዋል።
አትሌት ወሪት ፋንቱ የፋን ኢትዮጵያ መስራችና ስራአስኪያጅ የእኛ ዋና ዓላማ "ትንሽ ጥላቻ ትልቁን ፍቅር አያጠፋም፣ ለኢትዮጵያ ለውጥ አብረን እንሩጥ" በሚል በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የተደረገና በባስኬቶ ዞን የባስኬት ብሔረሰብ የምስጋና በዓል የሆነው "ሾልኣ ካሻ" ምክንያት በማድረግ ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ የታለመ መሆኑን ገልጸዋል።
በዕለቱ ለሚደረገው 8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫና ለባስኬት ብሔረሰብ የምስጋና በዓል "ሾልኣ ካሻ" ድምቀት የሚሆኑ ትሸርቶች ከ10,000 በላይ የተዘጋጀ ስሆን የአንዱ ዋጋ 350 ብር መሆኑ ታውቋል።
የጎዳና ላይ ሩጫና ለባስኬት ብሔረሰብ የምስጋና በዓል "ሾልኣ ካሻ" በዓልን ለዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅ በዕለቱ ከ12 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ሚድያዎች ይገኛሉ።
በመጨረሻም የባስኬቶ ዞን አስተዳደር ከፋን ኢትዮጵያ መስራችና ስራአስኪያጅ አትሌት ወ/ሪት ፋንቱ ሜግሶ ጋር ከፋን ኢትዮጵያ ትሬዲንግ በመተባበር "ሾልአ_ካሻ" በዓልን ምክንያት በማድረግ 8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በጋራ ለማስኬድ የተዘጋጀ የውል ሰነድ ተፈራርመዋል።
እንኳን የባስኬት ብሔረሰብ የምስጋና በዓል ለሆነው "ለሾልአ ካሻ" ዋዜማ አደረሳችሁ አደረሰን!!