30/10/2022
የወዳጅነት ፓርክ ሁለተኛው ምዕራፍ ዛሬ ተከፍቷል። ስፖርትን፣ ጨዋታንና ማኅበራዊ መስተጋብርን ያቀናጀ ነው። ልጆች እየተጫወቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ይለማመዳሉ። ወጣቶች ያነብባሉ፣ ደግሞም ስፖርት ይሠራሉ። ወላጆችና አያቶች ከልጆቻቸው ጋር መጥተው ማኅበራዊ ልምዳቸውን ይለዋወጣሉ። አዲስ ተጋቢዎች በሠርግ ዐጸዱ ጋብቻቸውን ይመሠርታሉ። የነገዋ ኢትዮጵያ የተሻለች እንድትሆን የተሻለ ትውልድ እያፈራን እንቀጥላለን።
The second phase of Friendship Park opened today. It combines sports, games, and social interaction. Children learn about science and technology while playing. Young people read and engage in sports. Parents and grandparents bring their children with them to share social experiences. Newlyweds exchange vows in the wedding garden. We will continue to raise better generations for the sake of the future Ethiopia.