GAMO TV

GAMO TV ይህ የጋሞ ቴሌቪዥን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው። ገፁን ላይክ ፣ ሼርና ኮሜንት በማድረግ ወቅታዊና እውነተኛ መረጃዎችን በየዕለቱ ይከታተሉ!
(1)

ማስታወቂያየጋሞ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን በቀን 10/10/16 ዓ/ም ቴሌቪዥን ጣቢያውን አስመርቆ መደበኛ ስርጭት እንደሚጀምር ማሳወቃችን ይታወሳል።ይሁንና በሀገራዊና ክልላዊ ኩነቶች መደራረብ ምክን...
17/06/2024

ማስታወቂያ
የጋሞ ማህበረሰብ ቴሌቪዥን በቀን 10/10/16 ዓ/ም ቴሌቪዥን ጣቢያውን አስመርቆ መደበኛ ስርጭት እንደሚጀምር ማሳወቃችን ይታወሳል።

ይሁንና በሀገራዊና ክልላዊ ኩነቶች መደራረብ ምክንያት ለጥቂት ጊዜ ያራዘምን መሆናችንን እናሳውቃለን።

የክረምት ወራት ልዩ ልዩ የስፖርት ፌስቲቫል በቆጎታ ወረዳ መካሄድ ጀመረ።አርባ ምንጭ፦ ሰኔ 9 | 2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን ) "ስፖርት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል የ2016 ዓ.ም የክረምት...
16/06/2024

የክረምት ወራት ልዩ ልዩ የስፖርት ፌስቲቫል በቆጎታ ወረዳ መካሄድ ጀመረ።

አርባ ምንጭ፦ ሰኔ 9 | 2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን ) "ስፖርት ለሁሉም" በሚል መሪ ቃል የ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት ከተማ አቀፍ የወጣቶች ስፖርት ውድድር በቆጎታ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በወንዶች እግር ኳስ የመክፈቻ ጨዋታ ኤዞ 01 ከቱላ ቀበሌ እግር ኳስ ቡድን ጋር ይጫወታሉ።

በ13 ቀበሌያት ተሳታፊነት የሚደረገው ይህ ውድድር በእግር ኳስ፣ በቮሊቦል፣ በገበጣ፣ በካራቴ፣ በዎርልድ ቴኳንዶ እንዲሁም በሌሎችም የስፖርት መስኮች ለቀጣይ ሦስት ወራት ይካሄዳል።

በውድድሩ መክፈቻ የጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ልዩ ልዩ የስፖርት ትጥቅና የቁሳቁስ ድጋፍ አበርክቷል።

ወጣቶች በእረፍት ጊዜያቸው በስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካልና አዕምሮአቸውን እንዲያዳብሩ ማድረግ፤ በመጪው ዘመን በስፖርቱ የላቀ ውጤት ማስመዝገብና ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት የውድድሩ ዋነኛ ዓላማ እንደሆነም ተጠቁሟል።

1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በአርባምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው።አርባምንጭ፦ ሰኔ 9/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)፦ በዓሉ በአርባምንጭ ጃሚ መስጊድ አከባቢ በድምቀት እ...
16/06/2024

1 ሺህ 445ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በአርባምንጭ ከተማ እየተከበረ ነው።

አርባምንጭ፦ ሰኔ 9/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)፦ በዓሉ በአርባምንጭ ጃሚ መስጊድ አከባቢ በድምቀት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ከማለዳ ጀምሮ በቦታው በመገኘት ሶላት በመስገድና ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በማካሄድ እያከበረ ይገኛል።

የጋሞ ቴሌቪዥን ድርጅት የድርጅቱን ሎጎ በአዲስ መልክ እያሠራ ነው። በዚህ ሥራ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፣ የጋሞ ቴሌቪዥን እና ሌሎችም ምሁራን እየተሳተፉበት ሲሆን በቀን 11/10/16 ዓ/ም ...
15/06/2024

የጋሞ ቴሌቪዥን ድርጅት የድርጅቱን ሎጎ በአዲስ መልክ እያሠራ ነው። በዚህ ሥራ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፣ የጋሞ ቴሌቪዥን እና ሌሎችም ምሁራን እየተሳተፉበት ሲሆን በቀን 11/10/16 ዓ/ም አዘጋጆች ገምጋሚዎች በተገኙበት በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ገለጻ ያደርጋሉ።
አስተያየትዎን በኮሜንት ያስቀምጡ።

የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ 1445ኛውን የዒድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለመላዉ የእስልምና እምነት...
15/06/2024

የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ 1445ኛውን የዒድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በማስመልከት ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት

ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል-አደሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ !

የኢድ አል አድሀ (አረፋ ) በዓል በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነዉ። በዒድ ዕለት የምንፈጽማቸው በጎ ተግባራት ሁሉ ከፈጣሪ ዘንድ በረከት የምናገኝበት በመሆኑ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት በዓሉን ከኛ እኩል ተደስተው እንዲውሉ ማድረግ ይገባል።

በዞናችን የወል ዕውነት ላይ በመመርኮዝ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጽናትና በመርህ የሚመራ ስርዓት ለመዘርጋት ግብ አስቀምጠን ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ መልኩ እየተጋን እንገኛለን ።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በዞናችን በሚገኙ አንዳንድ መዋቅሮች ገዥ እና አሰባሳቢ ያልሆኑ ትርክቶችን በመፍጠር ወቅት እየጠበቁ የአከባቢያችንን ገጽታ ለማበላሸት የሚሰሩ ቡድኖችን እየተመለከትን እንገኛለን።

ስለሆነም በህብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት መርህ የሚያምነው ሰላም ወዳዱ የዞናችን ህዝብ ሰላማችንን ለማደፍረስ የሚሰራጩ አጀንዳዎችን ባለመቀበልና እኩይ ተግባር ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላትን በማጋለጥ ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር ተቀራርቦ እንዲሰራ በዚህ አጋጣሚ አሳስባለው።

በዓሉ የመረዳዳትና የመተሳሰብ የቆየ ዕሴታችንን ከፍ አድርጋችሁ የምታሳዩበት፤ የእምነቱ አስተምህሮ በሚያዘው መሰረት አቅመ ደካሞችን የምታግዙበትና ማዕድ የምታጋሩበት እንደሚሆን አምናለሁ ።

ዒድ ሙባረክ !!
መልካም የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል !!

አቶ ሰብስቤ ቡናቤ
የጋሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ ለኢድ አል አደሃ(አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።አቶ አባይነህ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛ...
15/06/2024

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ ለኢድ አል አደሃ(አረፋ) በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ።

አቶ አባይነህ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አል አደሃ (ዓረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ ብለዋል።

ኢድ አል አደሃ አረፋ በዓልን የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ማሳለፍ ይገባልያሉት አቶ አባይነህ ሕዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል አድሃ( አረፋ) በዓልን ሲያከብር በሃይማኖቱ አስተምህሮ መሰረት የተቸገሩ ወገኖችን በማሰብና ያለውን በማካፈል መሆን አለበት ብለዋል።

የብዝሃነት ሀገር በሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ
ህዝበ ሙስሊሙ በሃይማኖት ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ኢድ አል አደሃ (ዓረፋ) በዓል ከሌሎች እምነት ተከታዮች ጋር አንድነቱንና ወንድማማችነቱን በሚያጠናክር መልክ በዓሉን ማሳለፍ እንዳለበት አቶ አባይነህ አሳስበዋል።

በዓሉ የሠላም ፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲሆን አቶ አባይነህ ተመኝተዋል።

በመንፈሳዊ ዘርፍ ሰልጥነው የሚመረቁ አገልጋዮች የሠላም እሴት ግንባታን በሚያጠናከር መልኩ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ሁለንተ...
15/06/2024

በመንፈሳዊ ዘርፍ ሰልጥነው የሚመረቁ አገልጋዮች የሠላም እሴት ግንባታን በሚያጠናከር መልኩ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ሁለንተናዊ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል አስታወቀ።

አርባምንጭ ፥ሰኔ 08/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን ) የአርባምንጭ መካነ ኢየሱስ ሁለንተናዊ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሴምነሪ ዘንድሮ ለ8ኛ ጊዜ በዲፕሎማ መርሃ-ግብር በቲዮሎጂ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ደቡብ ምዕራብ ሲኖዶስ ፕሬዚዳንትና የማዕከሉ ቦርድ ሰብሳቢ ቄስ ሚልክያስ ምታቸው በማዕከሉ የሰለጠኑ ምሩቃን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር የሰላም ሰባኪ በመሆን ማህበራዊ እሴት ከማጎልበት ረገድ የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ማዕከሉ በአምስት መምሪያዎች በመደራጀት በተለያዪ ዘርፎች ትምህርትና ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ የማዕከሉ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ወይኬ አስረድተዋል።

ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ 174 ወንጌላውያንን በማስመረቀ ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዳበቃም አክለዋል።

ማዕከሉ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በዲፕሎማ መረሃ-ግብር ያሰለጠናቸውን 16 ሰልጣኞችን ማስመረቁን የሴምነሪው ዲን መ/ት ሲሻሙሽ አያሌው ገልፅዋል።

የዕለቱ ተመራቂዎች ባገኙት ዕውቀት ለፈጣሪና ለህዝብ ታማኝ በመሆን ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር የህብረተሰቡን ማህበራዊ መሰተጋብር ለማጎልበት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በስልጠናው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ መንፈሳዊ ምሩቃን የማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

22ኛው አለም አቀፍ ዘላቂ የውሃ ሃብት ልማት ሲምፖዚየም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡በውሃ ሃብት አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ የሚደረጉ ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶችን ለምሁራን ...
14/06/2024

22ኛው አለም አቀፍ ዘላቂ የውሃ ሃብት ልማት ሲምፖዚየም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በውሃ ሃብት አጠቃቀምና አስተዳደር ላይ የሚደረጉ ሳይንሳዊ የምርምር ውጤቶችን ለምሁራን ማጋራት ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አርባ ምንጭ፦ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን) በሲምፖዚየሙ መልዕክት ያስላለፉት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ የውሃ ሀብት አጠቃቀምና ልማት ላይ የሚሰሩ የምርምር ሥራዎች ለአንድ ሀገር ዕድገት ወሳኝ በመሆናቸው ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ የውሃ ሃብታችንን በማልማት ለዜጎች ጥቅም እንድውል ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

አያይዘውም በዘርፉ የሚደረጉ ምርምሮች የውሃ ሃብት አጠቃቀምና ልማትን ለማሳደግ እና በመስኩ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘለቄታው ለመፍታት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ከሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሲምፖዚየሙ ተሳታፊ የሆኑት ዶክተር ተስፋለም አብርሃም በበኩላቸው በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ዙሪያ ከፍትሃዊነት ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮችን በዘለቄታው ለመፍታት የምርምር ሥራዎች ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡

የገቢ አሰባሰብን ከማጎለበት ባሻገር ኢኮኖሚዉ የሚያመነጨውን ሀብት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ  ክልል  ርዕሰ  መስተዳድር   አቶ ጥላሁን  ከበደ አሳሰቡ።አርባምንጭ፥ 06/...
13/06/2024

የገቢ አሰባሰብን ከማጎለበት ባሻገር ኢኮኖሚዉ የሚያመነጨውን ሀብት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ አሳሰቡ።

አርባምንጭ፥ 06/2016 ዓ/ም (ጋሞ ቴሌቪዥን) "ፀጋዎችን አሟጠን በመሰብሰብ አስተማማኝ የፋይናንስ አቅም እንፈጥራለን፤ የክልላችን ብልፅግና እናረጋግጣለን " በሚል መሪ ቃል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ዓ/ም ሀብት አስተዳደር እና አሰባሰብ ልዩ የንቅናቄ መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በንቅናቄው መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ልማትን ለማሳለጥ እና የመሰረት ልማት ተደራሽነት ችግርን ለመቅረፍ ገቢን አሟጦ መሰብሰብ ወሳኝ በመሆኑ፤ ባለድርሻ አካለት መረባረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በገቢ አሰባሰብ ሂደት የሚሰተዋሉ መሰረታዊ ችግሮችን በአፋጣኝ በመፍታት የገቢ መጠንን ለማሳደግና የሀብት ብክነትን ለማስቀረት ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ወቅቱን የጠበቀ ፍትሃዊ የሀብት አሰባሰብ እና የመንግስት ሀብት አሰተዳደር ቁጥጥር ሥርዓትን ለማጠናከር በአፅንኦት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በመንግስት ንብረት ግዢ አስተዳደር የሚታዩ ክፍተቶቸን ለመቅረፍ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

የአፈር ማዳበሪያ እዳ በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት ክልሉ ከፍተኛ ወለድ እንዲከፍል መገደዱን አስታወሰው፤ ሀብትን በቁጠባ የመጠቀም ልምድ ማዳበር ይገባል ብለዋል።

የኦዲት ግኝት አስተያየትን በጊዜ ተፈፃሚ በማድረግ ረገድ የሚታየውን ክፍተት መቀረፍ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ኢኮኖሚው በሚያመነጨው መጠን ገቢ አለመሰበሰቡን የገለፁት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ፤ የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ጨምሮ ከዕለታዊ የንግድ እንቅስቃሴ በተሻለ ሁኔታ ገቢን ለመሰብሰብ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በበጀት ዓመቱ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ገቢን አሟጦ ለመሰብሰብ ርብርብ ማጠናከር እንደሚገባ ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ የክልሉ ዋና አፌ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፀሐይ ወራርሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

"Gade zaari araddisoy bazzoteththanne kosha teqqanas" giza ayfe kaaran miththa tossa oothoy Gaammo zoonen Arba Minc'e ka...
12/06/2024

"Gade zaari araddisoy bazzoteththanne kosha teqqanas" giza ayfe kaaran miththa tossa oothoy Gaammo zoonen Arba Minc'e kataman oothettides.

Arba Minc'e: Hiisa 5/2016 M.L (Gaammo Telebizhine) Gaammo zoone ayson kaalo kawo gisha Daanna Mogosa Mokkonninay zoonen diza bula zumata miththa tokeththan c'ililison heera koshappenne bazzoteththappe naaganas bessizaysa yootida.

Heera bazzoteththappe teqqanas qopettidi oothettiza miththa tossa oothoy salo sa'a deththan 51-tho nne Tophphiyan 31-tho gididaysa Gaammo zoone goshsha kaaleththan heeranne wora naago mac'ara kaappo Daanna Moolla Gaashshahunay qonc'issida.

Miththa tokeththan heera c'ililisanas halchettidi oothettishe dizaysaka akeekisida.

Geeshsha c'arko demmanaasinne medheta naaganaas miththa tossas dhoqqa go'ay dizaysa Arba Minc'e yuusho worada goshsha xaafo keeththa kaappo Daanna Gazo Miilooney qonc'issida.

Tokettida miththay go'an pee'ana gakkanas heera asayinne kawo gishay dizayti kaaleteththi ooththana bessizaysa Arba Minc'e katama goshsha xaafo keeththa kaappo Daanna Pire Piqiruy akeekisida.

Zoonenne yuusho worada kawo kaappoti sohozan beettidi miththa tokkida.

"በጎነትን ባህል ማድረግ ይገባል"- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ጥላሁን ከበደአርባምንጭ፥ ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን) ርዕሰ መስተዳድሩ"በጎነት ለኢትዮጵያ" በ...
11/06/2024

"በጎነትን ባህል ማድረግ ይገባል"- የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ

አርባምንጭ፥ ሰኔ 04/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)
ርዕሰ መስተዳድሩ"በጎነት ለኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮ ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በአርባ ምንጭ ከተማ የአቅመ ደካማ ቤትን በማደስ አስጀምረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት መተጋገዝና መተሳሰብ የኢትዮጵያዊነት ዕሴት በመሆኑ በጎነትን ባህል ልናደርገዉ ይገባል ብለዋል።

በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወጣቶች በተቀናጀ መንገድ ተሳትፎ እንዲያደርጉም ጥሪ አስተላልፈዋል።

የከተማዋ ነዋሪዎች እና ባለሀብቶች አቅመ ደካሞችን በማገዝ የድርሻቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልገሎት በዞኑ ሁሉም መዋቅሮች የአረጋውያን እና የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ተግባር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ወላይቴ ቢቶ፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ፣ ከፍተኛ የክልል፣ የዞን እና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

Arba Minc'e: C'ooc'e 4/2016 M.L (Gaammo Telebizhine) Dugeha Tohphiya kilile ayfe ayso aawa Daanna kabbada xilahuney Arba...
11/06/2024

Arba Minc'e: C'ooc'e 4/2016 M.L (Gaammo Telebizhine) Dugeha Tohphiya kilile ayfe ayso aawa Daanna kabbada xilahuney Arba Minc'e kataman "Meeri joy" geetettiza kawos gidonta eqon wolqay bantayta maaddanas keexettiza keeththas 10 miiloone bira maado immida.

Kililenne zoone dhoqqa kawo aawateththay dizayti Arba Minc'e kataman "Meeri joy" geetettiza wolqay bandayta maaddiza kawos gidonta eqon keexettiza keeththa yuuyi xeellida.

Dugeha Tophphiya kilile ayfe ayso Daanna Kabbada Xilahuney lo'o oothon erettiza ha eqota galatidi ha laythaninne kaalliza laythan kumeththara 10 miiloone bira maado ooththanaas qaala gelida.

Dugeha Tophphiya kilile miishsha biiro kaappo Daanna Abaata Tafari wolqay bantayta shemposo demoy keehi boncho gididaysa akeekisidi koshshiza maado ooththanas qaala gelida.

Gaammo zoone ayfe ayso aawa Daanna Abara Abbayinney nuus dizaysappe bandayta maadoy lose gidanas bessizaysa qopisidi oothoy polo gakkanaashin kaaleteththi ooththana gida.

"Meeri joy" eqota doomisida M/riyo Zawude Zabidera 2006 M.L. doomettida wolqay bandaytas shemposo gidida ha keeththa polo gaththanaas daroti maado ooththishe dizaysa xomosisida.

Dumma dumma bessappe shiiqida keha dureti oothoy polon gakkanas bessiza maado ooththanas qaala gelidDaanna

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን  የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ  ፈተና በ2 ሺህ 872 የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ::ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ እ...
11/06/2024

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2016 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በ2 ሺህ 872 የፈተና ጣቢያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ::

ፈተናው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን እገዛ ማድረግ እንዳለባቸውም ቢሮው አሳስቧል።

አርባምንጭ፤ ሰኔ 4/2016 ዓ/ም (ጋሞ የቴሌቪዥን) በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ የመማር ማስተማርና የትምህርት ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢሳያስ እንድሪያስ በክልሉ ባሉ 12 ዞኖች በ2 ሺህ 872 የፈተና መስጫ ማዕከላት ከ134ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚቀበሉ ገልፀዋል።

ለዚህም የፈተና ቀሣቁስ ስርጭት በጊዜ መከናወኑን አስታውቀዋል ።

የፈተና ሂደቱ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል እንዲያደረጉ አሳስበዋል።

የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብርሃም አምሳሉ በዞኑ 32 ሺህ 600 ተማሪዎች በ136 መፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን እንደሚቀበሉ ተናግረዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቦጋለ ቦቼ ተማሪዎች ከኩረጃ በፀዳ መልኩ እንዲፈተኑ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ጠቁመዉ ፤ ተማሪዎች ይህንን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ም/ኢንስፔክተር ጋፋሮ ቶማስ የፈተና ሂደቱ በሠላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት ከሚመለከታቸው ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።

Gaammo zoonen Qoggota woradan 8-tho kifile derewa paac'ey saron imettishe dees.Arba Minc'e:C'ooc'e 4, 2016 M.L(Gaammo Te...
11/06/2024

Gaammo zoonen Qoggota woradan 8-tho kifile derewa paac'ey saron imettishe dees.

Arba Minc'e:C'ooc'e 4, 2016 M.L
(Gaammo Telebizhine)paac'e imoy wontappe nam'u saaten saro hanotan doomettides.

Ichchashu paac'e giddoththotan 345 addetinne 536 mac'cati kumeththan 881 tamaareti paac'e ekkishe dizaysa worada kaalo ayso aawanne timirte X/keeththa kaappo Daanna Taakkala Taaddasay qonc'issida.

በጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ የ8ኛ ክፍል  ክልላዊ ፈተና   እየተሰጠ ይገኛል።በ5 የፈተና ማዕከላት ወንድ 345 ፤ ሴት 536 በጥቅሉ 881 ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና እየተቀበሉ  እንደሚገኝ የወረዳ...
11/06/2024

በጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

በ5 የፈተና ማዕከላት ወንድ 345 ፤ ሴት 536 በጥቅሉ 881 ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና እየተቀበሉ እንደሚገኝ የወረዳው ም/ዋና አስተዳዳሪና ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ታከለ ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ ዘርፉን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ አርባምንጭ ፥ ሰኔ 3/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለክልሉ አምራ...
10/06/2024

የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ ዘርፉን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

አርባምንጭ ፥ ሰኔ 3/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች "የማምረት አቅም አጠቃቀም አመላካቾች እና አለካክ ስልቶች" ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መንግስቱ ተክሌ በመርሃ-ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በኢንዱስትሪዉ ዘርፍ የተሻለ ምርታማነት እንዲኖር አምራቾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

በቢሮዉ የምርምር፣ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማማከር ዳይሬክቴር አቶ ገለቱ ገነሞ በክልሉ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ለተከታታይ 6 ቀናት በሚቆየው የስልጠና መርሃ -ግብር ከጋሞ፣ወላይታ እና ጌዲኦ ዞኖች የኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ ፣ ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች እና ከከፍተኛ አምራች ኢንደስትሪዎች የተወጣጡ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ከተማ አቀፍ የክረምት ወራት ልዩ ልዩ የስፖርት ፌስቲቫል በጨንቻ ከተማ መካሄድ ጀመረ።አርባ ምንጭ፦ ሴነ 2/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን ) በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት ከተማ አቀፍ የወጣ...
09/06/2024

ከተማ አቀፍ የክረምት ወራት ልዩ ልዩ የስፖርት ፌስቲቫል በጨንቻ ከተማ መካሄድ ጀመረ።

አርባ ምንጭ፦ ሴነ 2/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን ) በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት ከተማ አቀፍ የወጣቶች ስፖርት ውድድር በዛሬው ዕለት በጨንቻ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

በስምንት ቀበሌያት ተሳታፊነት የሚደረገው ይህ ውድድር በእግር ኳስ፣ በቮሊቦል፣ በካራቴ፣ በዎርልድ ቴኳንዶ እንዲሁም በሌሎችም የስፖርት መስኮች ለቀጣይ ሦስት ወራት ይካሄዳል።

በውድድሩ መክፈቻ የጋሞ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ልዩ ልዩ የስፖርት ትጥቅና የቁሳቁስ ድጋፍ አበርክቷል።

ወጣቶች በእረፍት ጊዜያቸው በስፖርታዊ እንቅስቃሴ አካልና አዕምሮአቸውን እንዲያዳብሩ ማድረግ፤ በመጪው ዘመን በስፖርቱ የላቀ ውጤት ማስመዝገብና ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት የውድድሩ ዋነኛ ዓላማ እንደሆነም ተጠቁሟል።

ያሉንን  ፀጋዎች በመጠቀም ከተረጅነት ለመዉጣት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።አርባምንጭ፡ ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)"ተረጅነት የሀገርንና የህዝብን ክብር  ያዋርዳል...
08/06/2024

ያሉንን ፀጋዎች በመጠቀም ከተረጅነት ለመዉጣት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።

አርባምንጭ፡ ሰኔ 01/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)

"ተረጅነት የሀገርንና የህዝብን ክብር ያዋርዳል" ያሉት የፌደራል ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳዳት ነሻ ፤ የተረጅነት መነሻ ምክንያቶችን ለይቶ በመረባረብ ለብልፅግና መስራት ይገባል ብለዋል።

ኢኮኖሚዉ የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝባችንን ችግር መፍታትና ማደግ ይገባናል ያሉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ፤ በግብርና፣ በቱሪዝምና በማዕድን ዘርፍ ያሉ ፀጋዎችን በመረዳት ከተረጅነት ለመውጣት መስራት አለብን ብለዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በበኩላቸዉ፤ የተረጅነት ታሪክን ለመቀልበስ ተደጋግፎ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ በከተማዉ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት፣ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሪፌራል እና የዶክተር አመኑ መታሰቢያ ሆስፒታሎች፣ የአደባባይ ግንባታዎች፣ የውስጥ ለውስጥ የአስፓልትና የመንገድ ዳር ጌጠኛ ንጣፍ ስራዎች አበራታች መሆናቸው ተገልጿል።

የመደረኩ ተሳታፊዎች ከስራ ዕድል ፈጠራ፣ ከመልካም አስተዳደርና ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን አንስተዉ ምክክር ተካሂዷል።

በፌደራል ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰዓዳት ነሻ  የተመራ ልዑክ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎበኘ።አርባምንጭ፡ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)...
07/06/2024

በፌደራል ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰዓዳት ነሻ የተመራ ልዑክ የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታልን ጎበኘ።

አርባምንጭ፡ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ደስታ ገልቻ ሆስፒታሉ 600 ያህል የተኝቶ ህክምና አልጋዎችን እንደሚይዝ ገልፀዋል።

ሲቲ ስካንን ጨምሮ ከፍተኛ የህክምና መሳሪያዎች ገብተው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ፤ ሆስፒታሉ በቅርቡ ስራ እንደሚጀምርም አብራርተዋል።

ልዑኩ በከተማዋ ሌሎች ልማታዊ ተግባራትን የሚጎበኝ ሲሆን፤ በጉብኝቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ፣ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ፣ የጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ ፣ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛኸኝ ጋሞን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በጤና ተቋማት  ፅዱ አከባቢ በመፍጠር  የጤና አገልግሎቱን ዉጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት አስር ወራት ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል።አር...
06/06/2024

በጤና ተቋማት ፅዱ አከባቢ በመፍጠር የጤና አገልግሎቱን ዉጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።

የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የ2016 በጀት ዓመት አስር ወራት ዕቅድ አፈፃፀም እየገመገመ ይገኛል።

አርባምንጭ፡ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)

በጤና ተቋማት ፅዱ አከባቢ በመፍጠር የጤና አገልግሎቱን ዉጤታማ ማድረግ እንደሚገባ የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሰይፉ ዋናቃ ገልፀዋል።

የጤናዉ ሴክተር አመራርና ባለሙያዎች የፅዳት ጉዳይን ባህል አድርገዉ እንዲንቀሳቀሱም ኃላፊዉ አሳስበዋል።

የሴክተሩ አስር ወራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ዉይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በቀረበዉ የአፈፃፀም ሪፖርት ከ245 ሺህ በላይ የማዐጤመ አባላትን ማፍራት እንደተቻለ ተመላክቷል። ከአባላት ከ93 ሚሊዮን ብር በላይ እንደተሰበሰም ተገልጿል።

የወረርሽኝ ቁጥጥር፣ የእናቶች ማቆያ፣ የክትባት መጠነ ማቋረጥ ክትትል እና የወባ መከላከል ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባም አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመድረኩ የሴክተሩ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

Arba Minc'e katama dere zore keeththa nam'antho yuusho kaaleththo maaran 31-tho  moode duulatay  dumma dumma wudatas qof...
05/06/2024

Arba Minc'e katama dere zore keeththa nam'antho yuusho kaaleththo maaran 31-tho moode duulatay dumma dumma wudatas qofa qashoninne kawo kaappota sunthas eenoteththa imon kuuyettides.

Arba Minc'e: Hiisa 28, 2016 M.L. (Gaammo Telebizhine) duulatan 2016 bajete laytha uddupun aginata ootho poloy tishshateththan mixxi xeelettida gidishe beettiza pac'eta giigiso oge bolla wuday imettidi tobbe oothettides.

Arba Minc'e katama ayso aawa Daanna Gaammo Gazayinnay baaso dichcha, demisha shiishonne koronte go'a zambiso baggara gooba oothoy oothettidaysa erissida.

Seerappe kare ogen keeththa keexxo hanota teqoy, kaame oge ootho tishshisoyinne Arba Minc'e katama yegelthisoy mino polotappe malatetidayta gididaysa akeekisida.

Uddupun aginatan beettida issi issi pac'eta attida aginatan giigisanas kaalli xeelo hanotay minnidi bana bessizaysaka qofisida.

Mazegaja keeththata go'ateththara oyqettizaysan ooraththa enc'ereta gadeppe 6-tho deththay diza dhoqqateththan keexxanasinne katama bessata deththa laamo pilgeththa koshshateththa bolla tobbidi daro dere zore keeththa yarati ha qofa eenoteththan mintheththida.

Zore keeththay issi issi ootho keeththa kaappota laamera oyqettidi kuushsha koshshiza qopas eenoteththa bessiza maaran;

1. M/ro Bundo Emebeto; Arba
Minc'e katama kawo
kaalo gishiyo

2. Daanna Sayidde
Tamasgannay; Arba
Minc'e katama
zal'enne giya dichcha
X/keeththa kaappo

3. Daanna kaapite Bahiluy; Arba
Minc'e katama
interpirayzenne ootho qaada
medho X/keeththa kaappo ooththidi kumeththa dere zore keeththa kooshen doorettin duulatay kuuyettides.

Arba Minc'e katama dere zore keeththay nam'antho yuusho kaaleththo maaran 31-tho  moode duulata ooththishe dees.Arba Min...
05/06/2024

Arba Minc'e katama dere zore keeththay nam'antho yuusho kaaleththo maaran 31-tho moode duulata ooththishe dees.

Arba Minc'e: Hiisa 28, 2016 M.L. (Gaammo Telebizhine) Arba Minc'e katama dere zore keeththa duuniya M/riya Tasfaya Xurunasha Arba Minc'e katama giddon dumma dumma bessatan doommettida baaso dichchati anjettidi dereteththas go'a imo bolla pee'ana mala wuday imettizaysa qonc'issida.

Arba Minc'e katama geeshshateththa naagisanasinne doommettida baaso dichcha ootho polon gaththanas dere dendeteththay koyettizaysa gujjidi malatida.

Duulatan Arba Minc'e katama ayso aawa Daanna Gaammo Gazayinnera gujjidi Gaammo zoonenne Arba Minc'e katama kawo kaappoti, dere zore keeththa komiteti, zore keeththa yaratinne hara bana gelthizayti ubbay beettida.

Duulatan 2016 bajete laytha uddupun aginata ootho poloy, zore keeththa komiteta kaalli xeelo mintheththo qopayinne katama yegelthiso keeththa go'a imo hanota mixxi xeelo tobbey ooththettishe dees.

Woden woden heera  ashketeththanne zarumateththa mixxi xeeloy dere saroteththa naagisanas inje oge gididaysa Gaammo zoon...
01/06/2024

Woden woden heera ashketeththanne zarumateththa mixxi xeeloy dere saroteththa naagisanas inje oge gididaysa Gaammo zoone ayso aawa Daanna Abara Abbayinney erissida.

Arba Minc'e: Hiisa 24/2016 M.L.(Gaammo Telebizhine) Gaammo zoone saroteththa zore keeththa nam'antho yuusho moode duulatay oothettides.

Gaammo dubbusha woga era pulto gidida Gaammo c'imatan beettida saroteththa leemiso wodeppe woden xaphisanas bessizaysa Gaammo zoone ayfe ayso aawa Daanna Abara Abbayinney zorida.

C'ora turusteti shempi aadhdhiza zoone gidida gishas mac'ara dichchateththa qaaththa minthanas saroteththa bolla wudettidi ootho koshshizaysaka akeekisida.

Saroteththa giddoththo gidida Gaammo zoonen danoy medhettenna mala koyrottidi teqqanas issippeteththan ooththana bessizaysa Gaammo zoone saroteththa kaaleththo kaappo Daanna Dalc'o Daabberoy qopisida.

Kontirobande zal'ey, dereteththa miidiyata wogay banda ogen go'eteththinne dere haaro bolla qoha gatho malatiza zoone giddon saroteththa paac'c'iza issi issi bala loseti aadhdhi aadhdhi beettiza gishas giigo bessizaysi iripporten shiiqides

የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሚዩኒኬሽን በጋሞ ዞን ለሚገኙ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የዊልቸር ድጋፍ አደረገ።አርባምንጭ፤ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)"የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን መደገፍ ለሁ...
31/05/2024

የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሚዩኒኬሽን በጋሞ ዞን ለሚገኙ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የዊልቸር ድጋፍ አደረገ።

አርባምንጭ፤ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)
"የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን መደገፍ ለሁለንተናዊ አካታችነት እና ዘለቀታዊ ለውጥ" በሚል መሪ ቃል በጋሞ ዞን ውስጥ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች የሚሆን የዊልቸር ድጋፍ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን አርባምንጭ ቅርንጫፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ቴሌ ኮሚዩኒኬሽን የአካል ጉዳተኞችን ችግር ለመቀነስ በሀገር አቀፍ ደረጃ 9 ሚሊዮን ብር የፈጀ 500 ዊልቸሮችን ማሰራጨት ሲችል በጋሞ ዞን ውስጥ ለሚገኙ 15 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የሚሆን ዊልቸር ድጋፍ አድርጓል።

"Dere go'ateththasinne kumeththa dichchateththas  keesettiza polotika partetara issippe ooththana"-Dugeha Tophphiya kili...
31/05/2024

"Dere go'ateththasinne kumeththa dichchateththas keesettiza polotika partetara issippe ooththana"-Dugeha Tophphiya kilile ayso aawa bonchettida Kabbada Xilahuna

Dugeha Tophphiya kilile giddon diza keesettiza polotika partetara kilile kawoy zoreteththa duulata ooththides.

Arba Minc'e: Hiisa 23/2016M.L(Gaammo Telebizhine) Dugeha Tophphiya kilile ayso aawa Daanna Kabbada Xilahunay wogaanne seera naagida ogen polettiza maadoteththayinne keeseteththay minni baana koshshees gida.

Kililen diza anjota go'ettidi dere go'ateththa dichchanaas minnana bessizaysaka xomosisida.

Doomettida dichchateththa oothota minthanaas kawonne keesettiza polotika parteti issipeteththan ootho lose zambisanas bessizaysa Dugeha kilile polotika parteta issippeteththa zore keeththa shiishshizayti Daanna Asefa Taammiraatey qonc'isida.

Kilile kawo ayfe gishay Daanna Bawudi Alamaayoy dere dichchateththa wudan polotika parteti issippettidi ootho lose dichoy nuuppe nangettees gida.

Zoreteththa duulatay laappun qopa qasho c'achchata keson kuuyettides.

Keesettiza polotika parteti Geediyo,Wolaythanne Gaammo zoonetan yuuyi xeelota ooththidaysa gidishin Arba Minc'e kataman oothettiza "Dere asa kalo" pirojekite, Gaammo bayra xeera nam'antho deththa timirte keeththanne Gaammo dichcha maabaran oothettiza oothota xeellida.

Yuuyi xeeloppe millera puute tokeththa oothokka polida.

Goshsha mac'aran ha'i wode teknolojeta go’ettidi muruutanne murutateththa dichon dere koshsha kuntho oothoy koyettizaysi...
31/05/2024

Goshsha mac'aran ha'i wode teknolojeta go’ettidi muruutanne murutateththa dichon dere koshsha kuntho oothoy koyettizaysi qonc’ettides.

Arba Minc'e: Hiisa 23/2016 M.L.( Gaammo Telebizhine) Gaammo zoone issippeteththa ootho dichcha xaafo keeththay woradatanne katama ayso enc'eretan diza mac'ara oothonchatas biitta osha gishonne go'ateththa tishshiso loohiso Arba Minc’e kataman immishe dees.

Biitta osha gishonne go'ateththa baggara gooba loseta minthanasinne mac'aran beettiza pac'eta giigisanas wudettida loohiso gididaysikka malatettides.

"ለህዝብ ተጠቃሚነትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እንሰራለን"-  ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ...
31/05/2024

"ለህዝብ ተጠቃሚነትና ሁለንተናዊ ብልፅግና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በትብብር እንሰራለን"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የክልሉ መንግስት ውይይት አካሂዷል።

አርባምንጭ፤ ግንቦት 23/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ህግና ስርዓትን ባከበረ መልኩ የሚደረገው ሚዛኑን የጠበቀ ትብብርና ፉክክር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በክልሉ ያሉ ፀጋዎችን በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ መትጋት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ልማታዊ ስራዎችን ለማጠናከር በመንግስትና ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል በጋራ የመስራት ባህል ሊጎለብት እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ታምራት አሰፋ ገልፀዋል።

የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ባውዲ በበኩላቸው ፤ በሀገር ልማትና ዕድገት ዙሪያ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅንጅት የመስራት ልምድን ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የምክክር መድረኩ ባለ ሰባት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎቹ በጌድኦ፣ ወላይታና ጋሞ ዞን ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፤ በአርባምንጭ ከተማ የሚሰራውን የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት፣ የጋሞ ባይራ ሞዴል አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትንና የጋሞ ልማት ማህበር የሚያከናዉናቸዉን የልማት ስራዎችን ተመልክተዋል ።

ከጉብኝታቸዉ ጎን ለጎን የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አከናዉነዋል።

በጥናትና ምርምር ተለይተው የተሠሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል እንደሚገባ ተገለፀ።አርባምንጭ፤ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)የደቡብ ኢትዮጵያ ...
30/05/2024

በጥናትና ምርምር ተለይተው የተሠሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል እንደሚገባ ተገለፀ።

አርባምንጭ፤ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም (ጋሞ ቴሌቪዥን)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስ ኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለክልሉ ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ምክክር መድረክ በአርባምንጭ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ስርፀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘላለም ጳውሎስ በጥናትና ምርምር ተለይተው የተሠሩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል እንደሚገባ ገልፀዋል።

አክለውም ከባዮ ጋዝ ተክኖሎጂ በሚገኝ ተረፈ ምርትን በመጠቀም የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻልና የአካባቢ የአየር ብክለትን ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በቀጣይም የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት በማምረት ወደ ተጠቃሚው ሕብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ አቶ ዘላለም ጳውሎስ ጥሪ አቅርበዋል።

የዕለቱ የምርምር ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተር ዶ/ር ዳዊት ዳልጋ በበኩላቸው በጥናትና ምርምር የተለዩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት በማምረት አሁን ላይ በሀገራችን የሚታዩ የግብርና ማዳበሪያ እጥረቶችን ለመቅረፍ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

መድረኩ በዋናነት አማራጭ የሃይል ምንጭ/ባዮጋዝ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የአካባቢ አየር ብክለትን በመቀነስ ረገድና ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ ለክልሉ ህብረተሰብ ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።

በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የፌዴራል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የባዮ ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ልዩነትን አጥብቦ ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አካላት የላቀ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገለፀ።አርባምንጭ፤ ግንቦት፣ 21/2016 ዓ.ም(ጋሞ ቴሌቪዥን )፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ...
29/05/2024

ልዩነትን አጥብቦ ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አካላት የላቀ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ተገለፀ።

አርባምንጭ፤ ግንቦት፣ 21/2016 ዓ.ም(ጋሞ ቴሌቪዥን )፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ በክልሉ ለሚገኙ የሚዲያ ተቋማት እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች የክህሎት ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልእክት ሀገራችን የጀመረችውን ሁለንተናዊ የለውጥ ጉዞ ከግብ ለማድረስ ልዩነትን አጥብቦ ታላቋን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አካላት ሚናቸው የላቀ ነው ብለዋል።

የሚዲያ ባለሙያዎች በይበልጥ በንባብና በክህሎት ራሳቸውን በማብቃት ወቅታዊ፣ ተዓማኒና ግልፅ መረጃን ተደራሽ በማድረግ የማህበረሰቡን መረጃ የማግኘት ፍላጎት ለመሙላት እና ለፍትህ መስፈን እንዲተጉ አሳስበዋል።

አክለውም ስልጠናው የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች ለክልሉ ሰላምና እድገት ያላቸውን አበርክቶ ለማሳደግና የባለሙያውን እውቀትና ክህሎት ለማሻሻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው በህዝብ ግንኙነት ስራዎች፣ መርሆ፣ ስነምግባር፣ በማህበራዊ ሚዲያና በመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ስራዎች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

Address

Arba Mintch

Telephone

+251468812386

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GAMO TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GAMO TV:

Videos

Share