Ebc1 daily ethio news news

09/11/2022
በቅርብ ቀን የስርጭት አገልግሎት ይጀምራል ********
26/10/2022

በቅርብ ቀን የስርጭት አገልግሎት ይጀምራል ********

26/10/2022

የወንድ የዘር ፈሳሽን ቶሎ ማፍሰስ
=======
ብዙ ጊዜ ይህ ክስተት የሚፈጠረው በግላዊ አልያም በጋራ ጭንቀት ውስጥ በሚገኙ ወንዶች ላይ ነው ይላሉ ጉዳዩ የሚገባውን ጥናት አድርገናል የሚሉ ባለሙያዎች፡፡ ቶሎ የዘር ፈሳሽን ማፍሰስ እውቅና ያለው የጤና ችግርም ነው፡፡ ነገር ግን በህክምና ቋንቋ የተሰጠው ፍቺ ግልጽ ያልሆነ፣ አሻሚ እና ተጨባጭ የቁጥር መስፈርቶች የጎደለው ነው፡፡ ይህ ደግሞ የህክምና ባለሙያዎች ጉዳዩን መርምረው አግባብና ትክክለኛ ነው ብለው የሚያምኑበትን የህክምና መንገድ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጉዞ እጅግ ፈታኝና ግራ አጋቢ እንዳደረገባቸው ይናገራሉ፡፡

እንግዲህ አንድ ወንድ በወሲባዊ ግንኙነት ወቅት የዘር ፈሳሹን ቶሎ የማፍሰስ ችግር በተደጋጋሚ ካጋጠመው ጭንቀት ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ምክንያቱም በወሲብ ደስታን አለማግኘት ዞሮ ዞሮ የጋራ የሆነውን ግንኙነት መጉዳቱና አደጋ ላይ መጣሉ አይቀርምና፡፡

ምን ተሻለ?
=====
በዚህ የጤና ችግር እየተፈተኑ ከሆነ በቅድሚያ ወደ ጤና ባለሙያ መሄድ የሚያስፈልግ ሲሆን እስከዚያው ድረስ ግን ከስር የተቀመጡትን ነገሮች በቤት ውስጥ በማድረግ ወሲባዊ ህይወትዎ ላይ የተሻለ ለውጥ ማየት ይችላሉ፡፡

አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ
=====
መደበኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የዘር ፈሳሽን ቶሎ የማፍሰስ ችግርን ለመቅረፍ ምርጡ ዘዴ ነው፡፡ ውሃ ዋና፣ ሩጫ፣ የኳስ ጨዋታ፣ ጂምናስቲክ ወ.ዘ.ተ እንደመፍትሄ የቀረቡ ሲሆን መደበኛ የሆነ እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ዮጋ መሞከር ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

አመጋገብን ማስተካከል
=====
አንዳንድ የጤና ችግሮችን በምግብ ማከም እየቻልን ለምን ብለን መድሃኒት እንወስዳለን? ይህን ቀድሞ የዘር ፈሳሽንም ለማከም ወሲባዊ መነቃቃትን የሚያስከትሉ እንደ እንቁላል፣ የበግ ስጋ፣ ጥቁር ባቄላ የመሳሰሉ በአቅራቢያችን በቀላሉ የምናገኛቸውን ምግቦች መመገብ ይቻላል፡፡

ስነልቦናዊ መፍትሄዎች
=======
ባለሙያዎቹ እንደሚሉት ከሆነ ብዙ ጊዜ ይህ በወንዶች ላይ የሚከሰተው ያለጊዜ የዘር ፍሳሽን የማፍሰስ ችግር በአእምሮ ጭንቀትና ውጥረትም ሊከሰት ይችላል፡፡ አሉታዊ ሀሳቦችን ከአእምሮው ያስወግዱ የተረጋጋ የአእምሮ ሁኔታን ይፍጠሩ፡፡ ብሩህ የሆነ አመለካከት ይኑርዎት ለጭንቀት ቦታ አይስጡ፡፡ እንዲያ ካደረጉ ወሲባዊ ህይወትዎ ላይ የተሻለ ለውጥ ማየት ይችላሉ፡

https://am.sewasew.com/p/%E1%8B%A8%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8B%B5-%E1%8B%A8%E1%8B%98%E1%88%AD-%E1%8D%88%E1%88%B3%E1%88%BD%E1%8A%95-%E1%89%B6%E1%88%8E-%E1%88%9B%E1%8D%8D%E1%88%B0%E1%88%B5

Address

Afar
Addis Ababa

Telephone

+251921536674

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ebc1 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category