Nigat Media

Nigat Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nigat Media, TV Channel, Addis Ababa.

  ስር ውለዋል‼️ሆቴልና አልጋ ቤቶች እንግዳ እየመሰሉ የሚሰርቁ ግለሰቦች ከሆቴሉ ሰርቀው ስወጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለከተማ ቡርቅቶ ሆቴል ውስጥ አልጋ ተከራይተው በ...
10/04/2024

ስር ውለዋል‼️
ሆቴልና አልጋ ቤቶች እንግዳ እየመሰሉ የሚሰርቁ ግለሰቦች ከሆቴሉ ሰርቀው ስወጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

በሀዋሳ ከተማ ታቦር ክፍለከተማ ቡርቅቶ ሆቴል ውስጥ አልጋ ተከራይተው በሆቴሉ ከሚያድሩ ተጫዋቾች እስማርት አይፎኖችንና ዕቃዎቻቸውን እየሰረቁ ባሉበት በእጃቸው በያዙት ለስርቆት ከሚጠቀሙት 240 በላይ ማስተር ቁልፎች ፣ የአሜሪካ ዶላሮች ፣ የባንክ ቼክ ከሰረቁት 7 ስልኮች ጋር በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተይዘው ወደ ሌቦች ማረፊያ ተወስደዋል።

የውቧ ሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ፊቼ ጫንባላላ በዓልን ከቤተሰቦቹና ከስራ ባልደረቦቹ በቤታቸው ስያከብሩ።አይዴ ጫንባላላ
08/04/2024

የውቧ ሀዋሳ ከተማ ከንቲባ የተከበሩ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ፊቼ ጫንባላላ በዓልን ከቤተሰቦቹና ከስራ ባልደረቦቹ በቤታቸው ስያከብሩ።

አይዴ ጫንባላላ

“ቡርሳሜ”፦*********መጋቢት 27፣ 2016ዓ.ም //ሀዋሳ//ለፍቼ በዓል የሚቀርበው የምግብ ዓይነት ከእንስት የተዘጋጀ በቅቤ የራሰ ቆጮ ነው። በሲዳምኛ ቋንቋ አጠራር “ቡርሳሜ” ይባላል። ...
05/04/2024

“ቡርሳሜ”፦
*********

መጋቢት 27፣ 2016ዓ.ም
//ሀዋሳ//

ለፍቼ በዓል የሚቀርበው የምግብ ዓይነት ከእንስት የተዘጋጀ በቅቤ የራሰ ቆጮ ነው።

በሲዳምኛ ቋንቋ አጠራር “ቡርሳሜ” ይባላል። ቡርሳሜ የሚቀርበው ከሸክላ በተሠራ ባህላዊ ገበታ (ሻፌታ) ከወተት ጋር ነው።

የአመጋገብ ስርዓቱም በዕድሜ ታላቅ ከሆነው ሰው ቤት ይጀመርና እንደ እድሜ ቅደም ተከተል አብሮ የመመገብ ሥርዓቱ ይከናወናል።

በሲዳማ ብሔር አሮጌውን ዓመት መሰናበት ለአዲስ ዓመት ብስራት ነው፡፡ የዘመኑን መለወጥ ተከትሎ ሁሉም በደስታና በፌሽታ «አይዴ ጫምበላላ» እየተባባለ ይጠያየቃል።

ሁሉም አዲሱ ዓመት የሰላም የፀጋና የብልፅግና እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ይገላለፃሉ “ቡርሳሜ” በ“ሻፌታ” ቀርቦ በወተት በጋራ የመመገብ ሥርዓት የሚጀምረው ገበታው ከቀረበ በኋላ በአባቶች ቡራኬ ነው። ይሄኔ ሁሉም እጁን በገበታው ትይዩ በመዘርጋት “ፍቼ ከዘመን ዘመን አድርሽን” በማለት የአባቶችን ቡራኬ ቃል በጋራ እያስተጋቡ ይመገባሉ።

በፍቼ ቀን በጋራ በተበላበት “ሻፌታ” (ባህላዊ ገበታ) ውሃ ተሞልቶ ጠዋት ላይ አባወራውና ቤተሰቡ በውሃው ፊታቸውን በማስነካትና ከዚሁ ጋር የቀረበውን ቅቤ አባወራው እየቆነጠረ የራሱንና የቤተሰቡን አናት በማስነካት ወደ አዲሱ ዘመን የመሸጋገር ተምሳሌት
ይከናወናል፡፡

ልጆች ፊታቸውን ታጥበው ቅቤ ይቀባሉ። ጫምበላላ በሚከበርበት በዚህ ቀን አባወራው ከብቶቹን “ካሎ” (የግጦሽ ሳር) ውስጥ አሰማርቶ በሳሩ ላይ ቦሌ ነስንሶ በሚገባ እንዲመገቡ ያደርጋል፡፡

ለመላ ኢትዮጵያውያን እንኳን ለሲዳማ ብሔር የዘመን
መለወጫ ፊቼ-ጫምባላላ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!

የፍቼ ጫምባላላ በዓል ፍቅር፣ ሠላም፣ መደጋገፍ፣ መተሳሰብ፣ አብሮነትና አንድነት በተግባር የሚገለፁበት  ነው፡- ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ-መስ...
05/04/2024

የፍቼ ጫምባላላ በዓል ፍቅር፣ ሠላም፣ መደጋገፍ፣ መተሳሰብ፣ አብሮነትና አንድነት በተግባር የሚገለፁበት ነው፡- ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ለሆነው ፊቼ ጫምባላላ በዓል የአንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ለመላው የሲዳማ ክልልና የሀገራችን ህዝቦች አስተላልፈዋል፡፡

በሀገራችን ከሚገኙ በርካታ አኩሪ ባህሎችና ትውፊቶች ውስጥ የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ ጫምባላላ አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ-መስተዳድሩ በዓሉ ዘመድ አዝማድ የሚጠያየቅበት፣ የተጣሉት የሚታረቁበት፣ ፍቅር፣ ሠላም፣ መተሳሰብ፣ አብሮነትና አንድነት በተግባር የሚገለፁበት፣ ሰዎች ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት እንዲሁም ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣ ውብ ባህላዊ ዕሴቶችና ትውፊቶች፣ የአከባቢ አጠባበቅ ጥበብና የሥነ-ምህዳር ዕውቀቶች ለወጣቱ ትውልድ ከሚተላለፍባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡

ርዕሰ- መስተዳድሩ አክለው ፍቼ ጫምባላላ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በማይዳሰስ ቅርስነት ከተመዘገቡ ብርቅዬ የሀገራችን ቅርሶች ውስጥ አንዱ መሆኑን አንስተው የፍቅርና የአንድነት በዓል በሆነው የፊቼ ጫምባላላ አከባበር ላይ አባቶች በ"ቄጣላ"፣ ሴቶችና ልጃገረዶች በ"ሆሬ"፣ ወጣት ልጆች በ"ፋሮ" የሚያደምቁበትና በርካታ ቀልብ ሳቢ ባህላዊ ክንዋኔዎች የሚታዩበት በዓል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ርዕሰ-መስተዳድሩ በዓሉ ለመላው የሲዳማ ክልልና የሀገራችን ህዝቦች የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ከአሮጌው ዘመን ቂም በቀል እና ቁርሾ ይዘን ልንሻገር አይገባም - አቶ ደስታ ሌዳሞ*************************የፍቼ ጫምባላላ በዓል እሴቶችን በተግባር ልንኖርባቸው ይገባል ሲሉ የ...
05/04/2024

ከአሮጌው ዘመን ቂም በቀል እና ቁርሾ ይዘን ልንሻገር አይገባም - አቶ ደስታ ሌዳሞ
*************************

የፍቼ ጫምባላላ በዓል እሴቶችን በተግባር ልንኖርባቸው ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ተናግረዋል፡፡

የሲዳማ የዘመን መለወጫ ፍቼ ጫምባላላ የዋዜማ ክብረ በዓል "ፊጣራ " በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ፍቼ ጫምባላላ በውስጡ በርካታ ማህበረሰባዊ ጠቀሜታ ያላቸው እሴቶችን መያዙን አውስተዋል፡፡

በዓሉ ከአሮጌው ዘመን ይዘናቸው ልንሻገር የማይገቡ ቂም በቀል፣ ቁርሾ እና ሌሎች እኩይ ነገሮችን አስወግደን "ሁሉቃ"ን በማለት የምንታደስበት ነው ብለዋል።

"ሁሉቃ" በሲዳማዎች አጠራር ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት መሸጋገርን የሚያመላክት ሲሆን ህዝቡም ከእርጥብ እንጨት በተሰራ ማለፊያ እየሾለከ ከዘመን ዘመን መሸጋገሩን በትውፊት እንደሚያሳይ የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል፡፡

Hawaasi Quchumi gashshooti kantiiwi Kalaa Makuri Maarshayehu baalante dagara Fichee-Cambalaallate ayyaana lainohunni haw...
05/04/2024

Hawaasi Quchumi gashshooti kantiiwi Kalaa Makuri Maarshayehu baalante dagara Fichee-Cambalaallate ayyaana lainohunni hawalle iillishi'ne /iillishinke yitanno sokko saysino.

Baalunku balaxisiise xaphoomu dagara hawalle Sidaamu diru soorro Fichee-Cambalaallate ayyaanira keerunni illishinke/iillishi'ne yaa baxeemmo.

Baalunku affininte gede Sidaamu daga diru soorro hundi annuwinke baalante daga ledo mittimmatenni halante ayyirrissanni keeshsh*tino ayyanaati. wole ragaannino Sidaamu daga hanqafaanchimmate nna muccite Itoophiyu ayimmanni ayyirrissaniiti afamannohu.

Kunni Sidaamu dagara ayyimmate xawishsha ikke keeshshino ayyaana qangeemmo woyte wole ragaanni Sidaamu kaliiqa waajjannohanna manchi beeti daafira nna kalaqamu baalu gatikkini baxxino baychi noonsa daga ikkassiniiti.

Konnirano daga akkala diro gudde haaro diro sa'anno woyte giwammohu ledo araaramatenni keeru daafira baxxino baychi noosiha ikkana baxxinohunni fixoori barra maatesi nna olliisi gatikkinni mittimmate ajuujanni ayyirrissano umise hornyuba afidhino.

Kunni togoo hereenna konni ayyaani barra jajjabu annuwi shaafeeta mittimmatenni saga'litanno.kuni leellishannohu budu sagalenke daga mageeshsha mittimmatenni baalante daga ledo miteenni heedhannohuraati.

Konne hegeraamo ikkino hornya baalanti daga mitteenni sufisiissannoha ikkasinni konnirano Sidaamu daga gede noonke hornyuba baxxino garinni kalqete affanonke gede huwachishate widoonni baalunku halamme xa'mitanno.

Sidaamu mitte daga gede sa''u dirrara wolootta daganna dagoomi ledo ikkatenni dimokiraasetenna qansootu qoosso ayyirinyira qeechasi fulinoho.konnirano techo gobbankera afantino xawaabba soorro maareekantanno gede assinoonni sharro huwata dandiinanni.

Tennera hoodeteno jireenyu yannara daganke umisenni umose gashshate qoosso afidhinoha ikkana konnirano dagoomitette ikko miinjunni hattono poletiku handaarinni jawaachinshanni soorro maarekisiisa dandiinoonni.

Hawaasi Quchumi gede maarekantino soorro xawisate geeshshira ikko Quchummate sai aganira wolayita sooddote Quchumira assinoonni 9ki Itoophiyu Quchummate foremera 2ki deerra amade qeelino Quchuma ikka dandiino.

Kuni Quchuminke giddo baxxinohunni xaa yannara keeraancho gobba heeratenna investmentete hattono gangalatu mereersha ikkase qummeessannoha ikkasinni roore dagganno yannarra soojjaati afirikira heewisamaanchonna gumullosi leellishshanno ikkado harinshsho aana afantanno gede dhuka kalaqinoho.

Konnira Quchumu gashshooti hanafantinno projekitubba jeefisate Quchuma latisate dhukanna teessaanonnita latishshu xa'mo gumullate yanna yannante kaajjado wo'naalshsha assate aana afamanno.

Kone lainohunni sau dirrara Quchumu gede loosamino looso leellishannoha ikkana konni ragaani Quchumu noosiha 3.5 biilone birra duunamino baatooshshe gudate gashshootu baxxino illachinni loosanni afamanno.

Konne Quchumunnita rahote lopho aantete luphi yino deerra iilishshate
baxxinohunni wo'munku Quchumu teessaano eote dhuka lossate ragaani darasanyu nookiha assinani dikko effiratenni Quchuminke ajuuja reekate qeechasi fula noosi yino.

Konni ikka dandaanna mittimmatenni xuma turisitete nna invetimentete hattono heerate injiitino Quchuma ijaarsa dandiineemmo yaanni ayyaanu keerunniha,mittimmankeranna baxxillunniha ikkankera halcheemmo.

Dancha Ayyaana!!

Hawalle Sidaamu daga diru soorro Fichee cambalaallate Ayyaanira keerunni iillitini iillinnoomo.Ayyaanu Hawaasi teessanor...
05/04/2024

Hawalle Sidaamu daga diru soorro Fichee cambalaallate Ayyaanira keerunni iillitini iillinnoomo.
Ayyaanu Hawaasi teessanoranna massagaanote, sidaami dagara massagaanote, tophiyu dagararanna massagaanote hattono kalqete dagara keerunniha baxillunniha,mittimmannihanna baxxino garinni sidaamu qoqqowi mootimma daga soorrate amaddino mixo jeefo gantannohanna jireenya buuxisiinseemmoha ikkanno gede halcheemm.

Dancha hagiirru Ayyaana baalunkura.

አይዴ ጫምበላላእንኳን ለሲዳማ ዘመን መለወጫ ለሆነው የፍቼ ጫምባላላ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!በዓሉ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን አጠናክረን በጋራ በመቆም የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ...
05/04/2024

አይዴ ጫምበላላ
እንኳን ለሲዳማ ዘመን መለወጫ ለሆነው የፍቼ ጫምባላላ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

በዓሉ ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን አጠናክረን በጋራ በመቆም የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዳግም ቃል የምንገባበት እንዲሆንልን እመኛለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

Ayide Cambalaalaa

Baga bara haaraa Sidaamaa kan ta'e Fiichee Cambalaalaa geessan, geenye!

Ayyaanichi tokkummaa sabdaneessummaa keenya cimsinee waliin dhaabbachuun fayyadamummaa uummata keenyaa mirkaneessuuf irra deebiin kan waadaa itti seennu akka nuuf ta'un hawwa.

Waaqni Itoophiyaa fi uummata ishee haa eebbisu

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ለወንድም ሲዳማ ህዝቦች እንኳን "ለፊቼ-ጫምባላላ" በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ ዋና አስተዳዳሪው ለወንድም ሲዳማ ህዝቦች እንኳ...
05/04/2024

የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ለወንድም ሲዳማ ህዝቦች እንኳን "ለፊቼ-ጫምባላላ" በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ዋና አስተዳዳሪው ለወንድም ሲዳማ ህዝቦች እንኳን ለብሔሩ የዘመን መለወጫ የሆነው "ፊቼ-ጫምባላላ" በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን ብለዋል።

የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል ፍቼ ጨምበላላ ከጥንት ጀምሮ በትውልድ ቅብብሎሽ ከነሙሉ ክብሩ ዛሬ ላይ የደረሰ ደማቅና የኩራታችን ምንጭ የሆነ ባህላዊ ዕሴታችን ነው ያሉት፡፡

ዛሬ ላይ በዓሉ የሲዳማ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያውያን ከዚያም አልፎ የዓለም ህዝቦች ሁሉ ሃብት ሆኖ ይገኛልም ብለዋል፡፡

ይህ በዓል ከዘመን መለወጫ በዓልነቱ ባሻገር የሲዳማ ህዝብ ጥልቅ የሆነ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ እሴቶች መገለጫም ጭምር እንደሆነም ገልጸዋል።

የወላይታና የሲዳማ ህዝብ ታሪካዊና የተጠናከረ ትስስር ያላቸው ህዝቦች መሆናቸውን አስታውሰዋል።

የወላይታና የሲዳማ ህዝብ የቆየ ታርካዊ ትስስር፣ ባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ኃይማኖታዊና ኢትዮጵያዊ ትስስር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

ልዩነቶቻችን የዉበት ምንጭ፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችን ደግሞ የጥንካሬ መሠረት ናቸዉና ብዝሃነታችንን ተቀብለን በማስተናገድ የኢትዮጵያ ብልጽግና በጋራ ጥረት አጠናክረን የምንቀጥልበት ወቅት ላይ እንገኛለን ነው ያሉት።

በደም ተሳስረው ለዘመናት አብረው የኖሩት ወንድም ህዝቦች በዘላቂነት ለማስቀጠል እኛ ታሪካዊ ግደታ አለብንም ብለዋል።

ፊቼ-ጫምባላላ በዓል በሰላም፣ በፍቅርና በወንድማማችነት በጋራ የሚከበር የህዝብ በዓል እንደሆነ የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው በዓሉ የሰላም፣ የይቅርታና የመተሳሰብ እንድሆን መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል።

Ayiidee Chaamballaala
አይዴ ጫምባላላ!
እንኳን አደረሳችሁ! አደረሰን!
መልካም በዓል!

ሳሙኤል ፎላ
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

07/03/2024

#በጉጉት የሚጠበቀው አፊኒ ለእይታ ቀርቧል 🙏

በትራፊክ አደጋ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ህይወት አለፈ😭በወላይታ ዞን በድጉና ፋንጎ ወረዳ በተከሰተው ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ አሸከርካሪውን ጭምሮ የ 8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በ13 ሰዎች ...
25/02/2024

በትራፊክ አደጋ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ህይወት አለፈ😭

በወላይታ ዞን በድጉና ፋንጎ ወረዳ በተከሰተው ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ አሸከርካሪውን ጭምሮ የ 8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በ13 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ዛሬ 12 :30 ገደማ መነሻውን ከአርባምንጭ ከተማ ወደ ሀዋሰ ከተማ በመጓዝ ላይ ያሉ ለግል ጤንነታቸው በማለት ከተለያዩ ከመንግሥት ሰራተኞች ፣ ከባለሀብት የተወጣጡ ስፖርተኞች በድንገተኛ የመኪና አደጋ ፋንጎ ኮይሻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዞንጋ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ሕይወታቸው አልፏል ።

በአደጋው በሰው ህይወትና ንብረት ላይ አደጋ ደርሷል እስካሁን ባለው መረጃ የሟቾችና የተጎጂዎቹ ቁጥር ታውቋል።

አደጋው የተፈጠረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 A 01784 ሲሆን አጠቃላይ ተሳፋሪ ብዛት 27 ሲሆኑ የሞቱ 8 ሰዎች በህይወት የተረፉ 19 ከባድ ጉዳት 13 ቀላል የአካል ጉዳት 6 መሆናቸው ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል!!

ሀዋሳ በኢትዮጵያ ከተሞች ውድድር 2ኛ ሆናለች።በውበትና ንፅህና በመዝናኛ ማዕከልነት የሚታወቀው ሀዋሳ በወላይታ እየተደረገ ባለው ከተሞች ውድድር አሸናፊ መሆኗን መረጃዎች ወጥተዋል። እንኳን ደ...
21/02/2024

ሀዋሳ በኢትዮጵያ ከተሞች ውድድር 2ኛ ሆናለች።

በውበትና ንፅህና በመዝናኛ ማዕከልነት የሚታወቀው ሀዋሳ በወላይታ እየተደረገ ባለው ከተሞች ውድድር አሸናፊ መሆኗን መረጃዎች ወጥተዋል። እንኳን ደስ አለሽ ሀዋሳ

26/01/2024

በሐዋሳ ፍቅር ተይዟል

10/01/2024

Nappy በሀዋሳ በሌላኛው በሀዋሳው Nappy😂😂

09/01/2024

Napp በሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ያልተጠበቀ ክስተት 😂😂

"ማርያም ታማልዳለች ማለት የኢየሱስን ደም ከንቱ ለማድረግ የመፈለግ የድፍረት ኃጢአት ነዉ። አማላጅም፤ አዳኝም ኢየሱስ ብቻ ነዉ!!"ማክዳ ኃይሌሌ
08/01/2024

"ማርያም ታማልዳለች ማለት የኢየሱስን ደም ከንቱ ለማድረግ የመፈለግ የድፍረት ኃጢአት ነዉ። አማላጅም፤ አዳኝም ኢየሱስ ብቻ ነዉ!!"
ማክዳ ኃይሌሌ

የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ ወታደራዊ አመራሮች ውይይት አደረጉ።ዛሬ በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ የተመራ ልዑክ በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪ...
08/01/2024

የኢትዮጵያ እና የሶማሌላንድ ወታደራዊ አመራሮች ውይይት አደረጉ።

ዛሬ በራስ ገዟ ሶማሌላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ የተመራ ልዑክ በሀገር መከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተገኝቶ ውይይት አድርጎ ነበር።

በውይይቱም የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በአወዛጋቢና አዝናኝ ትዕይንቶቹ የሚታወቀው ናይጄሪያዊ ቲክ ታከር ጆሴ ኤንጂል ናፒ ሐዋሳ ገብቷልከ2.2 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው ናፒ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ቆይታ አድርጎ ነው ሰሞኑን ሐ...
08/01/2024

በአወዛጋቢና አዝናኝ ትዕይንቶቹ የሚታወቀው ናይጄሪያዊ ቲክ ታከር ጆሴ ኤንጂል ናፒ ሐዋሳ ገብቷል

ከ2.2 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ያለው ናፒ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ ቆይታ አድርጎ ነው ሰሞኑን ሐዋሳ የተከሰተው።

የጆሴ ኤንጂል ናፒ ወደ ከተማችን መምጣት ሐዋሳን ከማስተዋወቅ አንፃር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይገመታል።

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ወቅታዊ ጉብኝት ነዉ ለተባለዉ የስራ ጉዳይ ኤርትራ መግባታቸው ተነገረየሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ ረፋድ ላይ አስመራ ገብተዋል...
08/01/2024

የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ወቅታዊ ጉብኝት ነዉ ለተባለዉ የስራ ጉዳይ ኤርትራ መግባታቸው ተነገረ

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ዛሬ ረፋድ ላይ አስመራ ገብተዋል። ፕሬዝዳንቱ እና ልዑካቸው አስመራ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዝዳንት ኢሳያስ ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተዘግቧል።

የኤርትራዉ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረመስቀል በ X ገፃቸዉ እንዳሰፈሩት ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የሃገራቸዉን የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እንዲሁም አህጉራዊ እና አለም አቀፍ የጋራ ጉዳዮች ላይ በዚህ ወቅታዊ ጉብኝት ላይ ይወያያሉ" ብለዋል።

ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ከራስ ገዟ ሱማሌላንድ ጋር የወደብና የባህር ኃይል ሰፈር ለመመስረት የመግባቢያ ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ ተቃዉሞ ያሰማችዉ ሱማሊያ በፕሬዚዳንቱ አማካኝነት ስምምነቱን ዉድቅ ያደርጋል ያሉትን ህግ መፈረማቸዉ ይታወቃል።

 #አሳዛኝ መረጃ ከሲዳማ ጭሬ ወረዳ😭በሲዳማ ክልል በምስራቅ ዞን በጭሬ ወረዳ አባይታካ በምባል ቀበሌ ከሥር በፎቶ ላይ የምትመለክቱት ወጣት የአንድ ቤተሰብን ቤት ከፍትም ከኃላም በሩን በውጭ ...
09/12/2023

#አሳዛኝ መረጃ ከሲዳማ ጭሬ ወረዳ😭
በሲዳማ ክልል በምስራቅ ዞን በጭሬ ወረዳ አባይታካ በምባል ቀበሌ ከሥር በፎቶ ላይ የምትመለክቱት ወጣት የአንድ ቤተሰብን ቤት ከፍትም ከኃላም በሩን በውጭ ቆልፎ በቀን 24/03/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 7:00 አከባቢ በጭካኔ ቤቱ ላይ ብንዝን በማርከፍከፍ እሳት በመለኮስ በፎቶ የተመለከታቿቸውን ጨቅላ ህፃናትን ጨምሮ የሶስት ሰዎች ህወይት እንዲያልፍ አድርጓል።

ደግሞ ቤት የምገኙ ንብረት እና ሶስት ከብቶች ከቤት ጋር ተቋጥሏል።

ቤቱን በማቃጠል የሰዉ ህይወት እንድጠፋ ያደረገዉ ወጣት በፖሊስ ቁጥጥር ሰር ዉሏል።

በሶማሌ ክልል በመከበር ላይ የነበረው የብሔረሰቦች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከብሮ በሰላም ተጠናቀቀ።
09/12/2023

በሶማሌ ክልል በመከበር ላይ የነበረው የብሔረሰቦች ቀን በታላቅ ድምቀት ተከብሮ በሰላም ተጠናቀቀ።

የብሔርና ብሔረሰቦች አከባበር በጅግጅጋ!
09/12/2023

የብሔርና ብሔረሰቦች አከባበር በጅግጅጋ!

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ለዳሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ለሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ሙስጠፌ አስረክበዋል
09/12/2023

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ለዳሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ለሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ሙስጠፌ አስረክበዋል

155 ሸኔ አባላት ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸው ተገለጸ የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ከምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ከኢቱ ጎሳ ማኅበረሰብ ጋር በፀጥታ ጉዳይ ላይ ባደረገው ውይይት 155 የአሸ...
29/11/2023

155 ሸኔ አባላት ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸው ተገለጸ

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ከምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ከኢቱ ጎሳ ማኅበረሰብ ጋር በፀጥታ ጉዳይ ላይ ባደረገው ውይይት 155 የአሸባሪው ሸኔ ቡድን አባላት ወደ ሰላማዊ ሕይወት መመለሳቸው ተገልጿል፡፡

በኅብረተሰቡ ውስጥ መሽገው በህቡዕ በመንቀሳቀስ ራሳቸውን የገንዘብና ሃብት አሰባሳቢ ቡድን፣ የሰብዓዊ መረጃ ቡድን፣ የቅስቀሳና ፕሮፖጋንዳ ክንፍ፣ የአፈናና ስወራ ቡድን አባላት ብለው በማደራጀት በተለያየ ወቅት የተለያየ የሽብር ተግባራትን በመፈፀም የአካባቢውን ሰላም ሲያውኩ መቆየታቸው ተጠቅሷል፡፡

በሐይማኖት አባቶች፣ በሀገር ሽማግሌዎችና በአካባቢው ማኅበረሰብ በጎ ተፅዕኖ ምክንያት ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው የተመለሱት የሽብር ቡድኑ አባላት ለሽብር ተግባር ሲጠቀሙባቸው የነበሩትን የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችና ሞተር ሳይክሎች ለሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል ማሥረከባቸውን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ገልፀዋል፡፡

የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል አሕመድ ኢሚ ኅብረተሰቡ የራሱ የሰላም ዘብ መሆን በመጀመሩና ከሰራዊታችን ጋር በትብብር በመስራቱ የአካባቢው የፀጥታ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ መረጋጋት እየታየበት ነው ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኅብረተሰቡ ሲያነሳቸው የነበሩ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተደረገ ያለው ጥረት እንዲሳካ ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በቅንጅት የፀጥታ ማስከበር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል እንቅፋት የሚሆኑ አመራሮችን ማጋለጥ እንደሚገባ ተመለከተበኮንትሮባንድ እቃዎች ዝውውር የሚሳተፉ የመንግሥት አመራሮችን የማጋለጥና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደ...
28/11/2023

የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል እንቅፋት የሚሆኑ አመራሮችን ማጋለጥ እንደሚገባ ተመለከተ

በኮንትሮባንድ እቃዎች ዝውውር የሚሳተፉ የመንግሥት አመራሮችን የማጋለጥና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ገለጹ።

የኮሚሽኑ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሚኒስትር ዴኤታዎችና የተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል።

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ ባለፉት ወራት ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከል በተሰራው ሰፊ ስራ 3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር የሚገመቱ የወጪና ገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውን ገልጸዋል።

የኮንትሮባንድ የመከላከልና የቁጥጥር ስራዎች በተከታታይ እየተሰሩ ቢሆንም ችግሩ አሁንም በዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ላይ ተፅዕኖ መደቀኑን ጠቅሰዋል።

በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እንዳይውሉ መረጃ አሳልፈው የሚሰጡ፣ በቁጥጥር ስር የዋሉትም እንዲለቀቁ የሚያደርጉና በህግ እንዳይጠየቁ የሚሰሩ አመራሮች እንዳሉም ገልጸዋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ለኮንትሮባንድ ዝውውር እጀባ የሚሰጡ አካላት ስለመኖራቸውም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በየአካበቢው ያሉ ኬላዎች የምርት ዝውውርን እያስተጓጎሉና ኮንትሮባንድን እያባባሱ በመሆናቸው እንዲነሱ የተሰጠው አቅጣጫ አለመተግበሩንም ነው ያነሱት።

በየኬላው ችግር የሚፈጥሩ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በማጥራት እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም ኮንትሮባንድን መከላከልና መቆጣጠር የሁሉንም ጥረት በመጠየቁ በተፈለገው ደረጃ ውጤት ያለመገኘቱን ገልጸዋል።

በወልቂጤ ከተማ የሚስ ጉራጌ የቁንጅና ውድድር ተካሄደማያ ፋሽን ከብራና ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ህዳር 16 በወልቂጤ ከተማ የ miss gurage የቁንጅና ውድድር ተካሂዷል። በቅርቡ ተ...
28/11/2023

በወልቂጤ ከተማ የሚስ ጉራጌ የቁንጅና ውድድር ተካሄደ

ማያ ፋሽን ከብራና ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር ህዳር 16 በወልቂጤ ከተማ የ miss gurage የቁንጅና ውድድር ተካሂዷል።

በቅርቡ ተመርቆ ወደ ስራ በገባው ዮናስ ሆቴል በተካሄደውና ብዙ እንግዶች በታደሙበት የቁንጅና ውድድር ወይዘሪት ማርያማዊት ሠይፈ አሸናፊ ሆናለች።

 #ያሳዝናል 😭😭😭ህዳር 15-2016ዓም በዕለተ ቅዳሜ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ለምለም መልካሙ በሲዳማ ክልል አለታ ወንዶ ከተማ የምትኖር ከአራተኛ ፎቅ ላይ በመወርወር ራሷን አጥፍታለች:...
28/11/2023

#ያሳዝናል 😭😭😭
ህዳር 15-2016ዓም በዕለተ ቅዳሜ የ10ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ለምለም መልካሙ በሲዳማ ክልል አለታ ወንዶ ከተማ የምትኖር ከአራተኛ ፎቅ ላይ በመወርወር ራሷን አጥፍታለች::

እራሷን ለማጥፋት ምክንያት ከፍቅረኛዋ ጋር ስለተጣላችና ቀጥራው ብዙ ሰዓት ስትጠብቀው ስላልመጣ ራሷ ላይ ይሄን እርምጃ ወስዳለች እየተባለ ነው::

NigNigat Mediaተሰቦቿ ለወዳጅ ዘመዶቿ መጽናናትን ይመኛል!!

  |በኦሮሚያ ክልል ተልታሌ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አለፈከሟቾች በተጨማሪም በአደጋው ምክንያት በ18 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ14  ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድ...
28/11/2023

|በኦሮሚያ ክልል ተልታሌ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አለፈ

ከሟቾች በተጨማሪም በአደጋው ምክንያት በ18 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ14 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

አደጋው የደረሰው የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሚላሚ ከተማ ወደ ዋዩ ሲጓዝ መንገድ ስቶ በመገልበጡ መሆኑ ተገልጿል ።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው በተልታሌና ወላይታ ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ መላካቸው ተገልጿል።

ለኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ዞን አስተዳደር ስጦታ አበረከቱለት።ስጦታው የንጉስ ካዎ ጦና እና በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የሆነው የአጆራ መንትያ ፏፏት ሲሆን ስጦታውን የወላይታ ዞን ዋና አስተ...
28/11/2023

ለኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የወላይታ ዞን አስተዳደር ስጦታ አበረከቱለት።

ስጦታው የንጉስ ካዎ ጦና እና በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የሆነው የአጆራ መንትያ ፏፏት ሲሆን ስጦታውን የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሳምነው አይዛን ጨምሮ የሀገር ሽማግሌዎች በወላይታ ህዝብ ስም አበርክተዋል።

ለተደረገው ደማቅ አቀባበልና ለተወዳጁ ስጦታ ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወላይታ ሶዶ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታ ከዕዳ ወደ ምንዳ የመንግስት አመራሮች ስልጠና ላይ በመገኘት የዕለቱን ማጠቃለያ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሲዳማ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሂደት - አፊኒ*********************የሲዳማ ህዝብ እንደማኅበረሰብና እንደ ትውልድ ለዘመናት ጠብቆና ተንከባክቦ ያቆየው የራሱ የሆነ ባህላዊ የግጭት ...
27/11/2023

የሲዳማ ባህላዊ የግጭት አፈታት ሂደት - አፊኒ
*********************

የሲዳማ ህዝብ እንደማኅበረሰብና እንደ ትውልድ ለዘመናት ጠብቆና ተንከባክቦ ያቆየው የራሱ የሆነ ባህላዊ የግጭት አፈታት ዘዴ አለው። ይህ የግጭት አፈታት "አፊኒ" ይባላል። አፊኒ ቀጥተኛ የአማርኛ ትርጉሙ "ሰማችሁ ወይ" እንደማለት ነው።

አፊኒ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ግለሰቦች ወይም አካሎች በሸንጎ ውስጥ በውይይት ወይም በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት እንዲሳተፉ ዕድል የሚሰጥ መንገድ ነው። ሀሳብን ለማንሸራሸርና ለማሰባሰብ ጊዜ ለማግኘት ጭምር የሚረዳ የንግግር መሳሪያም ነው ማለት ይቻላል።

አፊኒ የሚቀርበው፤ የቀረበውን ሀሳብ አቅጣጫ ተረድቶ እየተከታተለ ያለው ወገን እንዲረዳውና ሀሳቡን ለተሰብሳቢው ያደረሰው ወገን ጊዜ ወስዶ በማጤን እውነትን በመግለጥ ሙግቱን ለመርታት ወሳኝ የሆኑ ቁልፍ መከራከሪያ ምክንያቶችን ለማሰባሰቢያ ነው።

እንዲሁም የሀሳቡ ደጋፊዎች ጉዳዩን በአፅንኦት እንዲከታተሉ እና ደጋፊ ሀሳብ እንዲያመነጩ ለማጠናከር ጭምር ነው። ይህም ለመጨረሻ ውሳኔ አቅጣጫ ደጋፊዎቹን ለማስማማት ያለመ ነው። የሚቃወም ካለም "እዚህ ጋር የተለየ ሀሳብ አለኝ" ብሎ የመቃወሚያ ሀሳቡን እንዲያቀርብ የአፊኒ ስርዓት ዕድሉን ይሰጣል።

በሲዳማ ባህል ሰዎች ሲናገሩ "አፊኒ" ሳይባል ጣልቃ አይገባም። በሌላ መልኩ አንድ የተበደለ ሰው ማንኛውም አይነት እርምጃ ከመወሰዱ በፊት በአጠገቡ ላሉት ወይም ለታላላቆቹ "አፊኒ" በማለት ማሳወቅ ባህላዊ ግዴታው ነው። ይህንን ሳያደርግ በግብታዊነት እርምጃ የወሰደ እንደሆነ ቅጣት ይጣልበታል።

አጥፊው ቅጣቱ በማኅበረሰቡ ዘንድ ያለውን ተቀባይነት እንዲያጣ ስለሚያደርገው ከባድ ይሆንበታል፡፡ ከቅጣቶቹ ውስጥ እድር፣ እቁብ ወይም ሌሎች ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ያለውን ሥልጣንና ተሳትፎ እንዲያጣ፣ እንዳይሸጥ እና እንዳይገበይ፣ ልጆቹን እንዳይድር የሚከለክሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

አፊኒ እውነትን ከማፈላለግና ከፍትሕ አሰጣጥ ጋር በእጅጉ ይተሳሰራል። እውነትን በማጣራትና በማረጋገጥ ወደሚቀጥለው እርምጃ ለመራመድ አፊኒ ወሳኝ መንገድ ነው። ይህም የሚሆነው አፊኒ በጉዳዩ ላይ እውቀት ያለው ማንኛውም ሰው መረጃ እንዲሰጥ ሰፊ እድል ስለሚሰጥ ነው።

በመሬት፣ በድንበር፣ በትዳር፣ በጠለፋ፣ የሰው ሀቅ በመብላት እና በተለያዩ ወንጀሎች … ስሞታ የቀረበባቸው ጉዳዮች ወደ ሕግ ከማምራታቸው በፊት በሲዳማ ባህል በአፊኒ ስርዓት ይዳኛሉ።

ቅኝተ ኢትዮጵያ ህዳር 16/2016 ዓ.ም

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nigat Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category