እናት ፍቅርናት like አድርጉት

እናት ፍቅርናት like አድርጉት እውነተኛ ፍቅር የምትሰጥ እናት ብቻ ነች

ፍትህ ለጉራጌጉራጌ  በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች የማዳከም እንቅስቃሴ ይቁምየጉራጌ ማህበረሰብ ውብ መልካምድር አቀማመጥላይ ላይ ያለ ብዙ ባህሎች ያሉት  በብዙ የሚቆጠሩ በአላቶች ያሉት ከበአላቶ...
20/09/2023

ፍትህ ለጉራጌ
ጉራጌ በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች የማዳከም እንቅስቃሴ ይቁም
የጉራጌ ማህበረሰብ ውብ መልካምድር አቀማመጥላይ ላይ ያለ ብዙ ባህሎች ያሉት በብዙ የሚቆጠሩ በአላቶች ያሉት ከበአላቶቹ አንዱ በዮኔስኮ የተመዘገበ የመስቀል በአል ነው
የመስቀል በአል አከባበር ሲከበር የተለያዩ የውጭ ሀገራት ዜጎችእና በሀገር ውስጥም የሚገኙ የተለያዩ ብሔርብሔረሰቦች ወደ ዉቢታ ጉራጌክልል ያቀናል ዜጎች
በአሉ ለማክበር በሚሔዱበት ጊዜ መንገድ ትራንስፖርት ካወጣው ታሪፍ ውጪ 3 እጥፍነው ሚያስከፍሉት ትራንስፖርት ታሪፉ 340 ሲሆን በበአሉ ምክንያት በማድረ የአንድሰው መሔጃጉዞ ብቻ1000ብር እስከ 1300 ብር ነው ሚጠይቁት በኪሎሜትር ሲተመን ከአዲስ አበባ 220 k.M ይሔ ህገወጥ ተግባር ሊቀረፍ ይገባል ብዙ ኢትዮጲያዊ የመስቀል በአል ሔዶ ማክበር ይፈልጋል በትራንስፖርት ምክንያት ሳያከብር ይቀራል መንግስት ባለበት ሀገር ይህ አሳፋሪ ተግባር ሲደረግ ማየት ያሳፍራል
እንደሌላ ክልል ትራንስፖርት መንግስት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢሶች ሊመድ ይገባል ሁላቹም ሼር ሼር አድርጉት Bini Kassa Ze Atirfo

13/09/2023

ያለ እግዚያብሔር ፍቃድ አንዳችነገር አይሆንም

11/09/2023
14/08/2022

የፊታችን 🔥🔥💯

ብዙ በሚሰሩበት በወጣትነት ዘመናቸው ካጣናቸው:ዘመን አይሽሬ ስራን ከሰሩ:ለጥበብ ከለፉ እንዲሁም አሁን ላሉት ወጣት ጥበበኞች የጥበብን መንገዱን ከጠረጉ ተወዳጅ ድምፃውያን መካከል አንዱ ተወዳጁ አርቲስት ነው።
ልጆች የወላጆቻቸውን ፈለግ ሲከተሉ ማየቱ እጅግ ደስ ይላል። የአርቲስት ልጅ የሆነው አርብ ማታ አማካኝነት የተሰኘ ሙዚቃ ወደእናንተ ያደርሳል።

Stay Connected!!

07/08/2022
01/07/2022

Awtar Tv - መክብብ ዘሪሁን | Mekbb Zerihun - Suguyo | ስጉዮ - New Ethiopian Music Video 2022 is the first-ever Ethiopian...

30/06/2022
11/06/2022
07/06/2022
Enasitewil
07/06/2022

Enasitewil

🔯 #ስማኝማ🔯

✅ስለ ገንዘብ - በድሃ ፊት አትናገር!
✅ስለ ጤንነትህ - ህመምተኛ ፊት አታውራ!
✅ስለ ጥንካሬህ - ደካሞች ፊት አትናገር!
🌀ስለ ደስታህ - በተከፋ ሰው ፊር አታውራ!
✴ስለ ነጻነትህ - እስረኞች ፊት አትናገር!
✴ስለ ልጆችህ - መሃን ፊት አታውራ!
✴ስለ እናት እና አባትህ - ወላጅ አልባ ሰዎች ፊት አትናገር!

ምክንያቱም ቁስሎቻቸውን ከበፊቱ በበለጠ እንዲቆስል እና እንዲደማ ምክንያት ትሆናለህና።

✳ለምትሰጠው ነገር ሁሉ ትንሽ ፈገግ በል ከልብህም ደስታን
ጨምርበት
✳ለማንኛውም ሰው ጆሮ ስጥ ግን ድምጽህን ቀንስ
✳ሁሉንም ውደድ ጥቂቶቹን እመን ማንንም ግን አትበድል
✳የውሸት ጓደኛ እና ጥላ አንድ ናቸው ሁለቱም የሚቆዩት ጸሃይ እስክትጠልቅ ድረስ ብቻ ነው
✳መልካም ሰው ከሰው ልጅ የመንፈስ ምግብ ነው
✳የማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑ የሚታወቀው ተፈትኖ ካለፈ ወይም ከወደቀ ብቻ ነው።

ሼር፣

ይነበብ
31/05/2022

ይነበብ

Yinebeb
30/05/2022

Yinebeb

✅🚺 🚺✅

✴ ከሚያናግርሽ ወንድ ሁሉ ጋር አትሳቂ! አንዳንዴ መኮሳተር ጥሩ ነዉ! ድንበር የሌለዉ ፈገግታና ሳቅ ከመንገድሽ ያዘገይሻል!

✴ በወንጌል ጉዳይ አትደራደሪ! ምክንያቱም, ክርስቶስ ስለአንቺ መከራን ሲቀበል አልተደራደረብሽም! ሞቶልሻል!

✴ ጠራ ኮራ ብለሽ ሂጂ! ባለሽ ዘንጪ! ኩርምት አትበይ! ግን ከባህልሽና ከእምነትሽ ያፈነገጠ አለባበስንና እስታይልን ቻዉ በይ! ክርስቲያን ሰማያዊ እንጂ ዘመናዊ አይደለም!

✴ ዝሙትንና መዳራትን ከሚጋብዙ ዘፈኖችና እንቅስቃሴዎች, ማሬ ነግሬሻለሁ ባለሽ አቅም ሁሉ ሽሺ!

✴ በቦርሳሽ ዉስጥ ኮስሞቲክስና መስታዉት ብቻ ይዘሽ አትዙሪ! መፅሀፍ ቅዱስሽንም መያዙን አትርሺ! ቦርሳሽ ዉበት የሚኖራት ያኔ ነዉ!

✳ ድንግልናሽን ጠብቂዉ! ለምታገቢዉ ብቻ አስቀምጪ!
እግዚአብሔር ቅዱስ ነዉና! በክርስቶስ ሲቀድስሽ የቅድስናን ሕይወት እንድትኖሪ ነዉ!

✳ በእግዚአብሔር ዘንድ ከወንድ እኩል ተቀባይነት እንዳለሽ አትርሺ!
ክርስቶስም በስጋ ከሴት(ከድንግል ማርያም) ነዉ የተወለደዉ!
ስለዚህ እግዚአብሔር በክርስቶስ ተቀብሎሻለ! ማን ይቃወምሻል?!

✳ አንቺኮ ምርጥ ነሽ! ወንድ ሁሉ ይፈልግሻል! ያሚያገባሽ እንዴት ታድሏል! ተፈላጊ መሆንሽን አትርሺ! ግን ለሚያገባሽ እንጂ ለሚፈልግሽ ሁሉ አትገኚ!

✳ ዘጠነኛዉ ይሄ ፈገግ የሚያደርግ ነዉ ግን የግሞ ትክክል ነዉ!
"ወንድ ከልቡ አፍቅሮሽ ሲያለቅስ, ዝም ብለሽዉ ሮጠሽ አትለፊ!" ቢያንስ እንባዉን እስኪጠርግ ቆመሽ ተመልከቺ! አትመፃደቂ!

✳ የመጨረሻዉ መልዕክቴ; "ክርስቶስን ባገኘሽዉ አጋጣሚ ሁሉ ስበኪ! ያኔ ዉበትሽ ይደምቃል! ፀጋ ይብዛላችሁ! መልዕክቱ አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት

ሼርርርር

29/05/2022

በእርግዝና ወቅት ጸበል መጠመቅ ይቻላል?

በእውኑ ጸበል መጠጣት እና መጠመቅ ጽንስ ያጨናግፋልን?

ጸበል በመጠመቃችን እና በመጠጣታችን ጽንሱ ይጎዳልን?

በእርግዝና ወቅት እስከ መቼ ወራት ነው ጸበል መጠመቅ እና መጠጣት የሚቻለው?

በእግርዝና ወቅት ጸበል ብንጠመቅ ብንጠጣ ምን ጥቅም እናገኛለን?

ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያዳርሱ ለጥያቄያቸው መልስ ይሁኑ!

[በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም]

ተወዳጆች ሆይ ሰሞኑን ‹‹በእርግዝና ወቅት መቁረብ ይቻላልን›› የሚለውን ትምህርት ሳስተላልፉ የትምህርቱን አውድ ተከትሎ አብዛኞቻችሁ ከላይ ርዕስ ያደርኩዋቸውን ጥያቄዎች ጠይቃችኃል፡፡ ደግሞም አግባብ ነው ምክያቱም የብዙዎች ጥያቄ ስለሆነ፡፡ ስለዚህ በተቻለኝ አቅም ለመመለስ እሞክራለሁ፡፡

በእርግዝና ወቅት ጸበል መጠመቅ ይቻላል?

ወዳጆቼ በሚገርም ሁኔታ ብዙዎቻችን በእርግዝና ወቅት ጸበል መጠመቅ እና መጠጣት የሚቻል አይመስለንም፡፡ ለዚህም ነው በየጸበል ቦታ ነፍሰ ጡሮች ሲጠመቁ የማናየው፡፡ አንዲት ሴት ካረገዘችበት ጊዜ ጀምሮ ስለ ጽንሱ እና ስለ ራስዋ ጤንነት በየወሩ የሕክምና ክትትል እንደምደርገው ሁሉ ቢያን በወር አንድ ሦስት አንድ ቀን ይህ ባይሆንላት በወር አንድ ቀን ጸበል ብትጠመቅ በተለይም የፈታሔ ማኅፀን የቅዱስ ሩፋኤልን ጸበል ብትጠመቅ ስንሱ መልአካዊ ጥበቃ ያገኛል ተባርኮም ከክፉ ነገር ተጠብቆ ይወለዳል፡፡

እኛ ኦርቶዶክሶች ምድራዊ እና ሥጋዊ ሐኪም እንደሚያስፈልገን ሁሉ ጽንሱን በማኅፀን የፈጠረና የጠቀለለ ልዑል እግዚአብሔር በመለኮታዊ ጥበቃው ጠብቆ ጤነኛ እና የተባረከ ልጅ እንዲሰጠን የጸበል ሕክምና ያስፈልገናል፡፡ ለጽንሱ በጸበል መንፈሳዊ ክትትል ልናደርግለት ይገባል፡፡ አንዳንዶች ነፍሱ ጡር ሴት ጸበል መጠመቅ የለባትም የሚሉት ትምህርት ሳይሆን ከፍርሃት የመጣ ሟርት ነው፡፡ ጸበል አዳኝ እንጂ ገዳይ አይደለም፡፡ በጸበሉ ላይ ያደረው ቅዱስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ ጽንሱ ችግር ካለበት የሚፈውስ እንጂ የሚያጨናግፍ አይደለም፡፡ ስለዚህ ሴት ልጅ በእርግዝናዋ ወቅት ጸበል መጠመቅ ትችላለች፡፡

በእውኑ ጸበል መጠመቅ እና መጠጣት ጽንስ ያጨናግፋልን?

የሚገርመው አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ድራፍት፣ቢራ፣ወይን፣ጠላ ስትጠጣ ያልተጨናገፈ ጽንስ አዳኝ እና ፈዋሽ የሆነ ጸበል ብትጠጣ ጽንሱ እንዴት ይጨናገፋል? መጠመቅስ እንዴት ጽንስን ሊያስወርድ ይችላል? ይህ እኛ የቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ለምዕመናኑ ባለማስተማራችን የፈጠርነው ክፍተት እንጂ የምዕመናኑ ችግር አይደለም፡፡

እኔ እስከማውቀው ጸበል ተጠምቃ ጠጥታ ጽንሱ የረጋላት፣በጽንሱ ምክንያት ከሚፈጠር ሕመም የዳነች እንጂ ጸበል ተጠምቃ ጠጥታ የጽንስ መጨናገፍ የደረሰባት ሴት አላውቅም፡፡ እንደውን ለጽንስ መጨናገፍ አንዱ ምክንያት ጸበል አለመጠመቅ እና አለመጠጣታችን ነው፡፡ ምክንያቱም የአያቶቻችን፣የእናት አባቶቻችን ዛር፣የራሳችን ዓይነ ጥላ እና በምቀኝነት የተደረገብን መተት ኖሮብን ብናረግዝ ጸበል ባለመጠጣታችን እና በማለመጠመቃችን የተነሳ በእነዚህ መናፍስት ክፉ ሴራ ጽንሱ ሊጨናገፍ እና በደም ተመትቶ ደም ሆኖ ሊፈስ ይችላል፡፡ ይህን ባለማድረጋችን ሳናውቀው አጋንንት ስንት ጽንስ አጨናግፎብናል፣ስንት ልጅ አሳጥቶናል፡፡

በእርግጥ አንዳንድ አባቶች ነፍሰ ጡር ሴት ጸበል አብዝታ እንዳትጠጣ ይመክራሉ፡፡ ይህም የሚሆነው ጸበል ውኃ ቢሆንም የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበት እና የተቀደሰ ስለሆነ ለጽንሱ እንዳይከብደው በማለት አንድ ሁለት ሦስት ኩባያ ጸበል እንዲጠጡ ይመክራሉ፡፡ ቅድም እንዳልኳችሁ ከፍተኛ የሆነ የአልኮል ይዞታ ያለውን መጠጥ እየጠጡ ጽንስ ያልጠጨናገፈ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለበትን ጸበል ጠጥተው ጽንሱ በፍጹም አይጨናገፍም፡፡

ጸበል በመጠመቃችን እና በመጠጣታችን ጽንሱ ይጎዳልን?

አንዳንድ የዋሆች ጸበል በመጠመቃቸው እና በመጠጣታቸው ጽንሱ የሚጎዳ የሚመስላቸው አሉ፡፡ እንደውም በእርግዝና ወቅታቸው ጸበል ባለመጠመቃቸው እና ባለመጠጣታቸው ነው ጽንሱ የሥጋም የመናፍስትም ጉዳት የሚደርስበት፡፡ ስለዚህ የትኛውንም ጸበል ብንጠጣ ጽንሱ አይጎዳም እኛ በማናውቀው ጽንሱ ከተጎዳ እግዚአብሔር ባወቀ ጸበል በመጠመቃችን እና በመጠጣታችን ጤናውም ሁሉም ነገሩ ይስተካከላል፡፡ ለዚህም እኔው ምስክር ነኝ፡፡ ከዛሬ አንድ ወር በፊት አንድ የማላውቃት ልጅ ስልክ ደውላልኝ በሚያሳዝኑ ሁኔታ እያለቀሰች ‹‹በግል የጽንስ ክትትል የማደርግበት የግል ሆስፒታል አለ፡፡ ዛሬ እዛ ሄጄ ዶክተሯ ጽንሱ ጭንቅላቱ ላይ ውኃ ቋጥሯል ስለዚህ ዛሬውኑ ካልወጣ ችግር ይፈጥርብሻል፣እወልዳለሁ ብትይ እንኳን ከምታስቢው በላይ ችግር ያለበት ልጅ ነው የምትወልጅው፡፡ ስለዚህ ኪዝሽ በድንገተኛ ይታይ እና ጽንሱ ይቋረጥ በዛ የአምስት ወር ጽንስ ነኝ ምን ላድረግ›› አለች፡፡ እዚህ ላይ እኔት ትታችሁ የኃያሉ የመድኃኔ ዓለምን ተአምር ልብ በሉ፡፡

እኔም ሲቃ እና ትንቅንቅ ያለውን በእንባ የታጀበውን ድምጿን ስሰማ ሰውነቴን አንዳንች ነገር ወረረኝ፡፡ በእግርዝና ወቅት የሚፈጠረውን ጭንቀት በባለቤቴ ስለማውቀው ጭንቀቷ ውስጤ ገብቶ እጅጉን ረበሸኝ፡፡ እኔም ‹‹ባለቤትሽን አማክረሽው ምን አለሽ›› ስላት እሷም ‹‹ባለቤቴን እስካማክር ጊዜ አልሰጠችኝም በድንገተኛ ገብተሸ ቶሎ ይሠራልሽ ነው ያለችኝ›› አለችኝ፡፡ እኔም ‹‹በይ ጽንስን የሚፈጥር በማኅፀን ጠቅልሎ በመኮታዊ ጥበቃው ጠብቆ ወደዚህ ምድር የሚያመጣው እግዚአብሔር ስለሆነ ለአንድ ሳምንት የማስብበት እና ወስኜ የምመጣበት ጊዜ ስጪኝ በይና እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አጠምቅሻለሁ ቅብዓ ቅዱስም እቀባሻለሁ ከዛ በኃላ የኃያሉ የመድኃኔ ዓለምን ተአምር እናያለን›› አልኳት፡፡ እሷም ስትጠይቃት ዶክተሯ ጭራሽ ተቆጥታ ‹‹አንድ ሳምንት ብለሽ ሌላ ችግር ልትፈጥሪ ነው! በፍጹም አይሆንም! ባለ ቤትሽን ጥሪውና ተነጋግራችሁ ወስኑ›› አለቻቸው፡፡ እኔም ‹‹በይ ነይ ብያት›› መጥታ ለሰባት ቀን እየተጠመቀች ቅብዓ ቅዱስ እየተቀባች ጸበል እየጠጣች ቆይታ ካበቃች በኃላ ሌላ ሆስፒታል ሄዳ ቀድሞ በሌላ ዶክተር የተባለችውን ሳትናገር ሙሉ ምርመራ አደረገች፡፡ ጽንሱ በጥሩ ጤንነት እንዳለ ተነገራት፡፡ ደስ ስላላት በሌላ ዶክተር ስለ ጽንሱ የሰማችው መርዶ ለመረመራት ዶክተር ስትናገር ተገርሞ እርግጠኛ እንድትሆን በድጋሚ መርምሯት አሁንም ጽንሱ ከአቀማመጡ፣ከልብ ምቱ እስከ ጤንነቱ ያለውን መልካምነት ደግሞ ነገራት፡፡ ይህንን የምሥራች ለእኔም ነግራኝ ደስታውን ተካፈልን፡፡

ወዳጆቼ ይህን ያነሳሁላችሁ ስንቶች አሉ በአንድ የአልትራ ሳውንድ እይታ ጽንሱ እንዲህ ሆኗል፤በጽንሱ ላይ ይህ ተፈጥሯል ስለዚህ ጽንሱ ይቋረጥ እያሉ ነገ በጥሩ ጤንነት ተወልደው የሞቦርቁ፣ትዳር የሚያደምቁ ልጆች እንደዋዛ እየተጨናገፉ ደመ ከልብ ሆነው የቀሩ፡፡
እኛ እምነታችን ጎዶሎ ሆኖ እና ሐኪም የነገረን እግዚአብሔር የነገር እስኪመስለን ስለደረስን እንጂ በጽንስ ላይ አንድ ነገር ተፈጥሯል ሲባል ያንን ሰምተን ተደናግጠን በጽንሱ ላይ ውርጇን ከመወሰናችን በፊት ጸበል ሄደን ብንጠመቅ፣ቅብዓ ቅዱስ ብንቀባ፣ለምንወደው ታቦት ብንሳል፣በጸሎት ብንማጸን ጽንሱን ከመጨናገፍ እናተርፍ ነበር፡፡ እኛም ወልደን እንስም ነበር፡፡ ግን ብዙዎቻችን በእርግዝና ወቅት ጸበል መጠመቅ እና መጠጣት አይቻልም የሚለውን የተሳሳተ ትምህርት ይዘን ክፍያ የማይጠይቀውን በእጃችን ያለውን መድኃኒት የሆነውን ጸበል ሳንጠቀምበት ቀረን፡፡

በእርግዝና ወቅት እስከ መቼ ወራት ነው ጸበል መጠመቅ እና መጠጣት የሚቻለው?

ተወዳጆች ሆይ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት አቅሟ እስከቻው ድካም እስካልተጫናትና ጸበል ሄዳ ለመጠመቅ አቅም እስካላጣች ጊዜ ሄዳ ቀስ ብላ በጥንቃቄ መጠመቅ ትችላለች፡፡ እዚህ ላይ እህቶቼ ልትጠነቀቁ የሚገባው ጸበል ስትጠመቁ ምናልባት እናንተ የማታውቁት እግዚአብሔር የሚያውቀው ክፉ መንፈስ ከተጋለጠ ሊጥላችሁ ይችላል፡፡ በዚህም ጉዳት ደርሶባችሁ እድናለሁ ብዬ እንዲህ ሆንኩ ብላችሁ ፈጣሪ ላይ እንዳታማርሩ ቢቻል ከባለቤታችሁ ጋር ካልሆነ ከአንድ ሰው ጋር ሆናችሁ ብትጠመቁ ይመረጣል፡፡

እህቶቼ በተለይ ዘጠን ወራችሁ ገብቶ ወደ መውለጃችሁ ከተቃረባችሁ የፈታሔ ማኅፀን የቅዱስ ሩፋኤልን ጸብል ጠዋት ጠዋት አንድ ኩባያ እየጠጣችሁ ሆዳችሁን ተዳበሱበት፡፡ እንዲሁም መልክአ ቅዱስ ሩፋኤል ጠዋት አልያም ማታ እየጸለያችሁ መልአኩን ተማጸኑት፡፡ ምናልባት የቅዱስ ሩፋኤልን ጸበል ካጣችሁ፣ካላገኛችሁ ንጹህ ውኃ አቅርባችሁ ውኃው ላይ መልክአ ቅዱስ ሩፋኤልን እያነበባችሁበት በውኃ ላይ እፍ ያላችሁበት እሱን መጠጣት፣ሆዳችሁን መደባበስ፡፡ ይህንን ብታደርጉ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ጽንሱን በረድኤቱ እና በጸሎቱ ይጠብቅላችኃል፣እናንተንም ያለ ጭንቅ በሰላም እንድትገላገሉ ይራዳችኃል፡፡ አንዲት ነፍሰ ጡር ሴት ከቤቷ ጸበል መጥፋት የለበትም፡፡ ስለዚህ እርጉዝ ሴት መውለጇዋ ሲቃረብ ለመጠመቅ ቢከብዳትም እስከምትወልድበት ቀን ድረስ ጸበል መጠጣት ይገባታል፡፡

በእግርዝና ወቅት ጸበል ብንጠመቅ ብንጠጣ ምን ጥቅም እናገኛለን?

በእርግዝና ወቅት ጸበል ብንጠመቅ እና ብንጠጣ ብዙ ጥቅሞች እናገኛለን የሚለውን እናያለን፡፡ አንደኛ ጸንሱን ከማኅፀን ጀምሮ በጸበሉ ላይ ባለው ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር መንፈስ እናስባርከዋለን፡፡ ሁለተኛ በአያቶቻችን በእናት አባቶቻችን በኩል በውርስ ከሚተላለፍ እና ከሚመጣ ዛር፣የዛር ውላጅ እና ከማኅፀን ጀምሮ አብሮ ተጸንሶ ከልጁ ጋር ከሚወለድ ዓይነ ጥላ መንፈስ ይጠበቃል፡፡ ሦስተኛ በዛር እና በዓይነ ጥላና በሌሎችም ክፉ መናፍስት በሚመጣ ውርጃ መጨናገፍ ይጠበቃሉ፡፡ አራተኛ ጽንሱ ከየትኛውም የማናፍስት ውጊያ እና ጥቃት ተጠብቆ በሰላም እንዲወለዱ ይረዳቸዋል፡፡ አምስተኛ እናቱ ያለ ምጥ እና ያለ ጭኝቅ በሰላም ትወልዳለች፡፡

ወዳጆቼ ዛሬ ዛሬ ኦርቶዶክስ ሆነን ግን በያዘንው እምነት የምናገኘውን ሰማያዊ ጥቅም ትተን በሳንይሱ መንገድ ብቻ ተጉዘን ጽንሳችን በተደጋጋሚ እየተጨናገፈ፣ጤና ያጡ ከተፈጥሮ ያፈነገጡ ልጆች ለመውለድ ተገደናል፡፡ ስለዚህ በማኅፀን ያለውን ጽንሳችንን በቅዱስ ቁርባን ብቻ ሳይሆን በጸበሉም ማስባረክ እና ጤንነታቸውን ማስጠበቅ ስለምንችል በአቅራቢያችን ካለው ጸበል ቢያንስ እየሔድን እንጠመቅ፡፡ መቼም በወር አንዴ ለቼክ አፕ ሆስፒታል እንደምንሄደው ሁሉ ቢያንስ በወር አንዴ ቤተ ክርስትያን እየሔድ በእግዚአብሔር ጸበል ቼክ አፕ ብናስደርግ ጥቅሙ ብዙ ነው፡፡

16/05/2022
06/05/2022

......የቅንጦት ኑሮ የምወድ ሰው አይደለሁም፡፡ ገንዘብ አለኝ ብዬ ቅንጦት ውስጥ አልገባም፡፡ ...ከእኔ ያነሰ ገንዘብ ያላቸው፣ ነገር ግን የሰላሳ ሺ ብር የእጅ ሰዓት የሚያደርጉ ሰዎች አውቃለሁ፡፡ ....እኔ ግን ርካሽ ዋጋ የሚያወጣ ተራ ሰዓት እንኳን የለኝም፡፡ ....የምጠቀምበት የሞባይል ቀፎም ማንኛውም ሰው ከሚይዘው የተለየ አይደለም፡፡ ....ገንዘብ አለኝ ብዬ መኪና አላማርጥም፡፡ ያገኘሁትን መኪና ነው የምይዘው፡፡ ከአመታት በፊት በሰላሳ ሺህ ብር የተገዛች አሮጌ ቶዮታ ነበር፣ እስከ ቅርብ ጊዜ የነበረው፡፡

ዘመናዊ ቪላ ለመግዛት የሚሆን አቅም እያለኝ፣ ለአራት አመታት በእናቴ ቤት አንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ ነው የኖርኩት፡፡ በእኔ ኩባንያ ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ብዙ ሰራተኞች የራሳቸው የሆነ የግል ቪላ አላቸው፡፡ እኔ ግን አሁንም ድረስ በአንዲት የኪራይ ቤት ውስጥ ነው የምኖረው፡፡ መኝታ ቤቴ ከአንድ አልጋ ውጪ የመያዝ አቅም ስለሌላት ልብሶቼን ሌላ ክፍል ውስጥ ነው የማስቀምጠው፡፡ ከእኔ ያነሰ ገቢ ያለው ተራ ነጋዴ እንኳን፣ ከእኔ ቤት እጅግ ያማረ ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡

አሜሪካ እያለሁ ታዋቂ ሚሊየነሮች የሚኖሩበት እጅግ ዘመናዊ ሰፈር ውስጥ በሚገኝ ስምንት ሺ ሜት ካሬ ግቢ ያለው ዘመናዊ ቪላ ውስጥ ኖሬያለሁ፡፡ አሉ የተባሉ ሆቴሎችን፣ ሬስቶራንትንና መዝናኛ ቦታዎችን አዳርሻለሁ፣ ቅንጦትን በሚገባ ቀምሼ አጣጥሜዋለሁ፡፡ አሁን ግን ስሜት አይሰጠኝም፡፡ የቅንጦት መኪናና ቤት እኔን አይገልፅኝም፣ ቀለል ያለ ኑሮ ነው የሚመቸኝ፡፡ ገንዘብ ሲኖረኝ፣ ከምንም ነገር በላይ ሰውን መርዳ ነው የሚስደስተኝ፡፡

በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዬ ለግል ጉዳዬ ብዙ ገንዘብ አላወጣም፡፡ የቅንጦት ኑሮ ስለማልወድ ይሄን ያህል ብዙ ገንዘብ የሚስወጣኝ ነገር የለም፡፡ እርግጥ ለሌሎች ሰዎች ብዙ ገንዘብ አወጣለሁ፡፡ የተቸገረ ሰው ገንዘብ ሲጠይቀኝ የቻልኩትን ያህል ለመስጠት አላመነታም፡፡ ገንዘቡ የግለሰቡን ችግር በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሊቀርፍለት እየቻለ፣ በእኔ ኪስ መቀመጡ ዋጋ የለውም ብዬ አስባለሁ፡፡ ያለመሰሰት ገንዘቤን ስሰጥ የሚያዩኝ አንዳንድ ሰዎች፣ ኤርሚስ ገንዘብ አባካኝ ነው ሲሉ እሰማለሁ፡፡ እኔ ግን መስጠትን እንደ ማባከን አይደለም የማየው፡፡ ስለሰጠሁ አይጎድልብኝም፣ ምናልባትም ይጨምርልኛል፡፡

ምንጭ፡ የማይሰበረው ኤርሚስ አመልጋ

06/05/2022

🚹የሠርግ ማታ ባል ለሚስቱ የሰጠው ምክር🚹

✅የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ
በእኔ እና ባንቺ መሃል ከእንግዲህ ምንም አይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም።

የኔ ውድ በፊት እኔ ትልቅ ልጅ ነበርኩ አሁን ግን በድጋሚ ህፃን እሆናለሁ፣
ትዝ ይለኛል ህፃን እያለሁ ምግብ ባልቼ እንደሆነ ወይንም እርቦኝ እንደሆነ የምታውቃኝ እናቴ ነበራች
ጥዋት ከእንቅልፍ የምትቀሰቅሰኝ እናቴ ነበራች
ከቤት ከመውጣቴ በፊት መስተካከል ያለበትን ነገሮች አስተከክለ የምትሸናኝ እናቴ ነበራች

ከእንግዲህ ግን እናቴ አንቺ ነሽ
ከእንግዲህ የኔን ደካማ ጎን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም
ከእንግዲህ ጥማቴን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም
አየሽ ፍቅር ልጅ እያለሁ የሆንኩትን ነገር ሁሉ ለእናቴ ነበረ መጥቼ የምናግራት እሷም ምስጢሬን ለማንም ነግራ አታውቅም
አሁን ግን እናቴ አንቺ ነሽ ምስጢሬን የምነግርሽ ላንቺ ብቻ ነው
ለማንም ምስጢሬን አሳልፈሽ አትስጪ

ልጅ እያለሁ ብዙ ጥፋቶችን አጠፋ ነበረ እናቴም ለጊዜው በጣም ትቆጠኝ ነበረ ግን ቁጣዋ ብዙም አይቆይም ወዲያውኑ ተመልሳ መሳቅ ትጀምራለች
የኔ ፍቅር ምናልባት አንቺንም ሊያስከፋሽ እችላለሁ እባክሽን ግን ቂም አትያዥብኝ ጥፍቴን ግን አይተሽ ዝም አትበይ ምክር ስጪኝ እቀበላለሁ

የኔ ማር ወደ ጣፋጭ የአልጋ ጨዋታ ከመሄደችን በፊት ደግሜ የምነግርሽ ነገር ለሰዎች ወሬ በፍጹም ጆሮ አትስጪ
ከእንግዲህ ወዲህ ላንቺ ከእኔ የሚቀርብ ማንም ሊኖር አይችልም መኖር የለበትም።

የኔ ፍቅር የብዙ ሰዎች ትዳር መፍረስ ምክንያት ጎሮቤት አልያም የጓደኛ ብዛት ነው ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከልክ በላይ አታቅርቢ

በፈጣሪ ፊት ቃል እገባለሁ እኔም ምርጡ አባትሽ ሁሌም ከጎንሽ መቆም የምችል ከማንም አስቀድሜ ለልጄ ለሚስቴ የሚል መልካም ባል እሆንልሻለሁ!!

👉የባል ምክር የተመቻው ብቻ ሼር ያድርግ

Address

ሳሪስ
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እናት ፍቅርናት like አድርጉት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category


Other Music Awards in Addis Ababa

Show All

You may also like