ኡማ ቲቪ /omah tv /ﻗﻨﺎﺓ ﺃﻣﺔ ﺍﻟﻔﻀﺈﻳﺔ

ኡማ ቲቪ /omah tv /ﻗﻨﺎﺓ ﺃﻣﺔ ﺍﻟﻔﻀﺈﻳﺔ Muselim voice

ሳዑዲ ዐረቢያ የዑምራ ተጓዥ ምዕመናን ሀገሪቱን ለቅቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠችለ1445ኛው ዓ.ሂ ዓመታዊው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ዝግጅት ላይ የምትገኘው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ የዑምራ ተጓዦች...
22/04/2024

ሳዑዲ ዐረቢያ የዑምራ ተጓዥ ምዕመናን ሀገሪቱን ለቅቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች

ለ1445ኛው ዓ.ሂ ዓመታዊው የሐጅ ሥነ ሥርዐት ዝግጅት ላይ የምትገኘው ሳዑዲ ዐረቢያ፣ የዑምራ ተጓዦች ሀገሪቱን ለቅቀው የሚወጡበትን ቀነ ገደብ አስቀመጠች። ሳዑዲ ከሌሎች የዓለም ሀገራት ለዑምራ ወደ ሀገሯ የሚያመሩ ተጓዦች ለቅቀው የሚወጡበት የመጨረሻ ቀን ዙል ቃዒዳህ 29/1445 (ግንቦት 29/2016) እንደሚሆን አስታውቃለች።

ሳዑዲ ዐረቢያ ከዚህ በተጨማሪም የዑምራ ቪዛ የሚያገኙ ምዕመናን ወደ ሀገሪቱ መግባት የሚችሉበት የመጨረሻ ቀን ግንቦት 15/2016 መሆኑን ቀድማ ገልጻ ነበር። ቀነ ገደቡ የተቀመጠው ወደ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ምዕመናን ይስተናገዱበታል ተብሎ የሚጠበቀውን የሐጅ ሥነ ሥርዐት ቅድመ ዝግጅት የተሻለ ለማድረግ መሆኑንም የሐጅ እና ዑምራ ባለሥልጣን መረጃ ያመለክታል።

የዘንድሮው ዓመት የሐጅ ሥነ ሥርዐት ሰኔ 7/2014 ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል። ምዕመናን ሥነ ሥርዐቱን ለመፈፀም ከግንቦት 1/2016 ጀምሮ ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ መግባት እንደሚጀምሩ የሀገሪቱ ጋዜጦች ጽፈዋል።

ሳዑዲ ለዑምራ ተጓዥ ምዕመናን ቀነ ገደብ ባስቀመጠችበት መግለጫ፣ ከዚህ ቀደም ከዑምራ ቪዛ ጋር በተገናኘ የነበሩ አሠራሮች ላይ ማስተካከያ መደረጉንም ይፋ አድርጋለች። ማስተካከያ ከተደረገባቸው ውስጥ የዑምራ ቪዛ የአገልግሎት ጊዜ ይገኝበታል።

ቀድሞ በነበረው አሠራር ለሦስት ወር የሚቆየው የዑምራ ቪዛ የአገልግሎት ጊዜ የሚሰላው ምዕመኑ የሳዑዲን መሬት ከረገጠበት ሰዓት አንስቶ የነበረ ቢሆንም በአዲሱ አሠራር ቪዛው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ይታሰባል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

በፍልስጤም በጋዛ 100 የቁርኣን ሀፊዞች ተመረቁ!በአስቸጋሪ የኑሮ አከባቢ እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆኑም አሁንም በፍልስጤም ጋዛ 100 የአላህን ቃል የቁርዓን ሀፊዞችን ተመረቁ።… ይ...
21/04/2024

በፍልስጤም በጋዛ 100 የቁርኣን ሀፊዞች ተመረቁ!

በአስቸጋሪ የኑሮ አከባቢ እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆኑም አሁንም በፍልስጤም ጋዛ 100 የአላህን ቃል የቁርዓን ሀፊዞችን ተመረቁ።

ይህ ከጋዛ በስተ-ምዕራብ ባለው የባህር ዳርቻ ካምፕ ውስጥ ከሚገኙት መጠለያዎች አንዱ ነው ።ይህ ትምህርት ቤት 100 የአላህን ቃል ቁርኣንን የሀፈዙ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከቀናት በፊትም 500 ሀፊዞችን ከጋዛ ከተማ በስተምስራቅ በሚገኘው አል ጡፋህ ሰፈር ከሚገኙት መጠለያዎች በአንዱ አስመርቋል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

ሊቢያዊው አባት ልጁ መሉ ቀርዓን በመሸምደዱ የተሰማውን ስሜት የገለጸበት መንገድ፤ አቤት የወላጅ ደስታ❤👌ያ አላህ ልጆቻችንን  በበእምነታቸው የፀኑ፤ በስነምግባር የታነጹ አድርጋቸው።🤲❤መረጃወ...
21/04/2024

ሊቢያዊው አባት ልጁ መሉ ቀርዓን በመሸምደዱ የተሰማውን ስሜት የገለጸበት መንገድ፤ አቤት የወላጅ ደስታ❤👌
ያ አላህ ልጆቻችንን በበእምነታቸው የፀኑ፤ በስነምግባር የታነጹ አድርጋቸው።🤲❤
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን!ሼክ ኢስማኢል አል-ዘይም አቡ አል-ሳባእ ወደ አኼራ ሄዱ! …ሼክ ኢስማኢል አል-ዘይም አቡ አል-ሳባእ በሳዑዲ አረብያ በበጎ አድራጎት ስራቸው የሚታወቁ ሲሆን ...
17/04/2024

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን!

ሼክ ኢስማኢል አል-ዘይም አቡ አል-ሳባእ ወደ አኼራ ሄዱ!

ሼክ ኢስማኢል አል-ዘይም አቡ አል-ሳባእ በሳዑዲ አረብያ በበጎ አድራጎት ስራቸው የሚታወቁ ሲሆን ሻይ፣ ቡና እና ቴምር በየቀኑ ለሀጃጆች እና ለኡምራ ተካፋዮች በነጻ በማደል በመዲና ከ40 አመታት በላይ ማገልገላቸው ተገልጿል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

በቅርቡ እስልምና የተቀበለው ወንድማችን በኢስላም / ዳውድ ኪም Daud Kim   በደቡብ ኮሪያ ኢንቼዮን ከተማ መስጅድ ለመገንባት የቦታ ውል ተፈራረመ ይህ ቦታ በቅርቡ መስጂድም ይሆናል።ዴቪድ...
11/04/2024

በቅርቡ እስልምና የተቀበለው ወንድማችን በኢስላም / ዳውድ ኪም Daud Kim በደቡብ ኮሪያ ኢንቼዮን ከተማ መስጅድ ለመገንባት የቦታ ውል ተፈራረመ ይህ ቦታ በቅርቡ መስጂድም ይሆናል።

ዴቪድ ኪም ይለናል

"የዛሬን ቀን ማመን አልችልም...
ኮሪያውያንን ለመጋበዝ የመስገጃ ቦታ እና ኢስላማዊ ፖድካስት ስቱዲዮ ለመገንባት እያሰብኩ ነው።

ብዙ አስቸጋሪ ነገሮች ይኖራሉ ግን እንደምችል አምናለሁ

የኮሪያ ጎዳናዎች ሁሉ በሚያምር የአዛን ድምፅ እስኪሞላ ድረስ
የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።"

"አላህን ፅናቱንና ስኬቱን እንጠይቀዋለን"
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

06/04/2024

27ኛ ለሊት ሼክ አብዱረህማን አል ሱደይስ ስል ፊሊስጢን ወንድሞቻችን ያደረጉት ዱዓ 🤲🤲

አንድ ቱርካዊ ዜጋ ቤቱን ሸጦ ያገኘውን ገንዘብ  ለተጎዱ የጋዛ ህዝብ በመለገስ 150 የፍልስጤም ቤተሰቦችን ማስተናገድ የሚችል 150 ድንኳን በጋዛ ሰርጥ ወረራ ቤታቸው ለፈረሰባቸው የሚውል ነ...
03/04/2024

አንድ ቱርካዊ ዜጋ ቤቱን ሸጦ ያገኘውን ገንዘብ ለተጎዱ የጋዛ ህዝብ በመለገስ 150 የፍልስጤም ቤተሰቦችን ማስተናገድ የሚችል 150 ድንኳን በጋዛ ሰርጥ ወረራ ቤታቸው ለፈረሰባቸው የሚውል ነው ። ግለሰብም አሁን የሚኖረው በኪራይ ነው።

“አቡ አል-ዳህዳህ” በታላቁ ሰሃባ ስም ራሱን ሰይሞል እስከ አሁን ትክክለኛ ማንነቱ አልታወቀም ።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

03/04/2024

የሕዝብ በዓላት ረቂቅ አዋጅ ውይይት ላይ የጊዜ ቀመር አጠቃቀምን አስመልክቶ የተነሳ ሐሳብ

#ሼር በማድረግ መልዕክቱን አዳርሱ!!

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!   በአርሲ የአሳሳ ከተማ የዲን ታጋይና በከይር ስራ ላይ በማስተባበር ጎልተው የሚታዩ ፣የሀገር ሽማግሌና የዳዕዋ አንቀሳቃሽ ሞተር የነበሩት ሀጂ ሙሐመድ ሀጂ...
02/04/2024

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!

በአርሲ የአሳሳ ከተማ የዲን ታጋይና በከይር ስራ ላይ በማስተባበር ጎልተው የሚታዩ ፣የሀገር ሽማግሌና የዳዕዋ አንቀሳቃሽ ሞተር የነበሩት ሀጂ ሙሐመድ ሀጂ ሰኢድ ጂሎ ለዑምራ ወደ ሳውዲ ዐረቢያ ባቀኑበት በትናንትናው እለት በመካ ቀጣዩ ዓለም ወደ አኪራ ተሸጋግረዋል።

ሐጂ ሙሐመድ እያንዳንዱ መስጊድ ከልመና ወጥተው ራሳቸው መቻል አለባቸው በሚል ራዕያቸው በአርሲ አሳሳ ከተማ ላሉ 51 መስጂዶች የገቢ ምንጭ እንዲሆናቸው ለእያንዳንዳቸው ወፍጪ ቤትና የግብርና ትራክተር እንዲሁም በጋራ ደግሞ የዱቄት ፋብሪካ የከፈቱ፣በራሳቸው ወፍጮ ቤት ደግሞ ዓሊሞች፣ዱዓቶችና ችግረኞችን በነፃ ያገለግሉ ነበሩ።አላህ መልካም ሥራቸውን ይቀበላቸው።

አላህ በጀነት ይመንዳቸው።ዛሬ ምሽት ከኢሻ ሰላት በኋላ በመካ በሀረም ሰላቱል ጀናዛ ተሰግቦቸው በዚያው ይቀበራሉ።አላህ ለቤተሰባቸውና ለአሳሳ ከተማ ህዝበ ሙስሊም መጽናናትን ይለግሳችሁ።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!!  ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ ዳግም ለሀገራቸው በቅተዋል!! ሸይኻችን በጥሩ ጤንነት ላይም መሆናቸውን ተሰምቷል!!መረጃወችን ለወዳጄ ዘ...
31/03/2024

እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!!

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ ዳግም ለሀገራቸው በቅተዋል!!
ሸይኻችን በጥሩ ጤንነት ላይም መሆናቸውን ተሰምቷል!!
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

በቦሌ ክፍለከተማ የሚገኘው አሚር መስጂድ በወረዳው ደንብ አስከባሪ እና ፖሊሶች በሀይል መፍረሱ ተገልጿል።በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ጉጂ  አካባቢ የሚገኘውን አሚር መስጂድ የፀጥታ...
28/03/2024

በቦሌ ክፍለከተማ የሚገኘው አሚር መስጂድ በወረዳው ደንብ አስከባሪ እና ፖሊሶች በሀይል መፍረሱ ተገልጿል።በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ጉጂ አካባቢ የሚገኘውን አሚር መስጂድ የፀጥታ አካላት በሀይል ማፍረሳቸውን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የአካባቢው ነዎሪዎች እንደገለፁት መስጂዱ ህገወጥ ነው በሚል ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የክፍለከተማው የፀጥታ አካላት ማፍረሳቸውንና የአካባቢው ሙስሊም ነዋሪዎችን በመደብደብ ከፊሉን ደሞ ማሰራቸው ታውቋል።

መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

 😢😢 ከስር የምትመለከቱት ወጣት ለፆመኞች ማፍጠሪያ እያደለ እያለ ድንገት መኪና ገጭቶት ወዲያው ህይወቱ አልፏል።በኽይር ስራ ላይ ፆመኛ ሆኖ ጌታውን ተገናኝቷል አላህ ይዘንለት🤲መረጃወችን ለወ...
28/03/2024

😢😢
ከስር የምትመለከቱት ወጣት ለፆመኞች ማፍጠሪያ እያደለ እያለ ድንገት መኪና ገጭቶት ወዲያው ህይወቱ አልፏል።
በኽይር ስራ ላይ ፆመኛ ሆኖ ጌታውን ተገናኝቷል
አላህ ይዘንለት🤲
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

አንድ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች በመስጅደል አል አቅሳ ሰገዱ!በፍልስጤም አል አቅሳ መስጂድ 120,000 ምዕመናን የኢሻ እና የተራዊህ ሰላት ሰግደዋል።…
28/03/2024

አንድ መቶ ሀያ ሺህ ሰዎች በመስጅደል አል አቅሳ ሰገዱ!

በፍልስጤም አል አቅሳ መስጂድ 120,000 ምዕመናን የኢሻ እና የተራዊህ ሰላት ሰግደዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ የሞሪታኒያ ሰዎች በዚህ አመት ለኡምራ መሄዳቸውን ትተው በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ወንድሞቻቸውን ለመደገፍ ገንዘብ ሰብስበዋል ።
28/03/2024

በሺዎች የሚቆጠሩ የሞሪታኒያ ሰዎች በዚህ አመት ለኡምራ መሄዳቸውን ትተው በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ወንድሞቻቸውን ለመደገፍ ገንዘብ ሰብስበዋል ።

ይህ የእግር ኳስ ግጥሚያ አይደለም በታንዛኒያ የቁርዓን ውድድር ነው በቢንያም ማካፓ ስታዲየም ዳሬሰላም.... ማሻአላህመረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይ...
28/03/2024

ይህ የእግር ኳስ ግጥሚያ አይደለም በታንዛኒያ የቁርዓን ውድድር ነው በቢንያም ማካፓ ስታዲየም ዳሬሰላም.... ማሻአላህ
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

ሩሲያ ግብረሰዶማውያንን በሽብር ወንጀል እንደምትከስ ገለጸች። ማንኛውም የግብረሰዶም እንቀስቃሴን ሕገወጥ እና ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴን የ...
26/03/2024

ሩሲያ ግብረሰዶማውያንን በሽብር ወንጀል እንደምትከስ ገለጸች።

ማንኛውም የግብረሰዶም እንቀስቃሴን ሕገወጥ እና ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረ ሰዶም እንቅስቃሴን የአክራሪነት እና የሽብር ድርጊት ነው ስትል ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።

በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።

ውሳኔው የተደረሰው የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች አክራሪ እና አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።

በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት ሠራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዚያው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወስኗል።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር። በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)
° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ መጠጥ ቤቶች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።

በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና የለውም።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

25/03/2024

አላሁ አክበር
በትናንትናው እለት በመጅመዕ አተ ተቅዋ መስጅድ ከተራዊህ ሰላት ብኋላ አንድ ወንድም በሸይኽ አሊዘይን መሀመድ ሸሀዳን ይዞ ወደ እስልምና ገብቶል ።
اللهم أعز الإسلام والمسلمين
اللهم أرفع رأية الإسلام عالية
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

ለመጅመዕ አተ-ተቅዋ መስጅድ 40 ሚሊየን 204 ሺ ብር ቃል ተገብቷል። ዛሬ ቅድመ ምረቃ በተካሄደለት መጅመዕ አተ-ተቅዋ መስጅድ ለቀሪ ሥራዎች ከተፈለገው 125 ሚሊየን ብር መካከል 40ሚሊየን...
24/03/2024

ለመጅመዕ አተ-ተቅዋ መስጅድ 40 ሚሊየን 204 ሺ ብር ቃል ተገብቷል።

ዛሬ ቅድመ ምረቃ በተካሄደለት መጅመዕ አተ-ተቅዋ መስጅድ ለቀሪ ሥራዎች ከተፈለገው 125 ሚሊየን ብር መካከል 40ሚሊየን 204 ሺ ብር ቃል የተገባ ሲሆን አራት ሚሊዮኑ ወዲያው ተሰጥቷል።

የመስጅዱ ዋና አስተዳዳሪና ኢማም ዑስታዝ ካሚል ሸምሱ መስጅዱ ዛሬ የደረሰበት እንዲደርስ ከጎናቸው የነበሩትን ወንድም ኑረዲን ነጋሽ፣ ወንድም ነስሩ መሐመድ፣ ወንድም እስማኢል ሐሰን በአስተዳደር ኮሚቴ ውስጥ በገንዘብ ማሰባሰብ ደግሞ ወንድሙ መቃሙ ሐሰን፣ ሙሐመድ ሸረፋ፣ አብዱ ሙሐመድ፣ ሰኢድ አሕመድ ገርባ፣ አብዱሽኩር ሻፊ እና ሌሎችም እንደነበሩ ገልጸዋል።

ሐጂ ሱልጣን አማን ኤባ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ባደረጉት ንግግር "አንድ ከሆንን ተዓምር እንሠራለን። ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ ይህ መስጅድ ተሠርቷል። አንድ ከሆንን ከዚህም በላይ እንሠራለን። እርስበርስ መለያየት ይብቃን ወንድማማችነትን እናጠናክር። ለውጡ ከመጣ በኋላ ተቋማችንን ለማሳደግ ብዙ ሠርተናል። ትናንት አንሳር መስጅድ ቦሌ ቡልቡላ 14ሺ ካሬሜትር ቦታ ወስደን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል። አንድ ከሆንን ከዚህም በላይ እንሠራለን። በየሚዲያው በሃሰት ስም ማጥፋት እናቁም። ወንድማችን ካሚል ሸምሱና በዚህ ሥራ የተሳተፋችሁ አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ። የፊታችን ረቡዕ የጎዳና ኢፍጣር ስለሚኖር እዚያ እንገናኝ።" ብለዋል።

ሸኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ በበኩላቸው "ቃል የገባችሁ ወንድሞች ረመዳን ሳይወጣ ቃላችሁን እንድትፈጽሙ አደራ እላችኋለሁ። እነ ዑስታዝ ካሚል ሸምሱ የጀመሩት ሥራ ጅምር እንጂ ፍጻሜ አይደለም። አንድነታችን አጠናክረን እንቀጥል" ብለዋል። ዑስታዝ አቡበከር አሕመድና ሸኽ አብዱልከሪም ሸህ በድረዲን ንግግር አድርዋል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

የሙጅመዓ አት- ተቅዋ መስጂድ ምረቃ እየተካሄደ ነው።በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተል ሰፈር አካባቢ ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ በቅርቡ የተሰጠው የሙጀመዕ አት - ተቅዋ መስጅድ የምረቃ...
24/03/2024

የሙጅመዓ አት- ተቅዋ መስጂድ ምረቃ እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተል ሰፈር አካባቢ ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ በቅርቡ የተሰጠው የሙጀመዕ አት - ተቅዋ መስጅድ የምረቃ ሥነሥርዓት እየተከናወነ ይገኛል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

ሸይኽ አልዘይዘን ሙሀመድ አህመድ አልሱዳኒዛሬ ሰላተ አተራዊህ በአዲሱ በሙጀመዕ አተቅዋ ቤተል ያሰግዳሉ ።ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!የቴሌግራም ቻናላችን ከስር ...
24/03/2024

ሸይኽ አልዘይዘን ሙሀመድ አህመድ አልሱዳኒ
ዛሬ ሰላተ አተራዊህ በአዲሱ በሙጀመዕ አተቅዋ ቤተል ያሰግዳሉ ።ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በሚገኘው አል-ሳቢን አደባባይ የረመዳን ወር ሁለተኛ ጁምአ "የእኛ ስራ ይቀጥላል ... ወረራህን አቁም!!" በሚል መሪ ቃል ሁለት ሚሊዮን ሰዎች የተሳተፉበት ሰልፍ ተ...
23/03/2024

በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በሚገኘው አል-ሳቢን አደባባይ የረመዳን ወር ሁለተኛ ጁምአ "የእኛ ስራ ይቀጥላል ... ወረራህን አቁም!!" በሚል መሪ ቃል ሁለት ሚሊዮን ሰዎች የተሳተፉበት ሰልፍ ተደርጓል!!

መሃማዱ ዲዋራየ19 አመቱ የሊዮን አማካኝተጫዋች መሃመዱ ከፈረንሳይ  ከ19 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከጨዋታ ውጪ ሆኗል በአለም አቀፍ የጨወታ እረፍት ጊዜ የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ ...
22/03/2024

መሃማዱ ዲዋራ

የ19 አመቱ የሊዮን አማካኝ
ተጫዋች መሃመዱ
ከፈረንሳይ ከ19 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከጨዋታ ውጪ ሆኗል

በአለም አቀፍ የጨወታ እረፍት ጊዜ የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ 8 ቀናት ተጫዋቾች እንዳይፆሙ የተወሰነውን ውሳኔ እንዲያከብሩ አልያም ከቡድኑ እንደሚባረሩ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ለማክበር ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው ከቡድኑ እንዱሰናበት የተደረገው

የተቀደሰውን ወር ረመዳን ከምንም ነገር ጋር ለድርድር ማቅረብ ተገቢ እንዳልሆነ እንዲሁም ረመዳንን መምረጡ ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ ተናግሯል

የፈረንሳይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔ ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል

አንቶኒዮ ሩዲገር፡ ጀርመናዊው ፣ የሪያል ማድሪድ ዕውቅ ተጫዋች በረመዳን ወቅት ታላላቅ ጨወታዎችን ለጀርመን ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም ለማድሪድ ሻምፕዮን ሊግ ፣ ላሊጋ የመሳሰሉትን መጫወት አይከ...
22/03/2024

አንቶኒዮ ሩዲገር፡

ጀርመናዊው ፣ የሪያል ማድሪድ ዕውቅ ተጫዋች

በረመዳን ወቅት ታላላቅ ጨወታዎችን ለጀርመን ብሄራዊ ቡድን እንዲሁም ለማድሪድ ሻምፕዮን ሊግ ፣ ላሊጋ የመሳሰሉትን መጫወት አይከብድም? ብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ

ለእኔ በጭራሽ አይከብደኝም ለምጄዋለሁ

ምንም አልበላም አልጠጣም ረመዳንን አጥብቄ አከብራለሁ

በእርግጥ ቀላል አይደለም ነገር ግን ተለማምጀዋለሁ

በአካልም ሆነ በስነ ልቦና ተዘጋጅቼ ረመዳንን ስለምቀበል ምንም አልቸገርም

ደግሞም ለፈጣሪ ብዬ የማደርገው ስለሆነ አላህ ብርታት እና ፅናቱን ይሰጣል

21/03/2024

የምናባዊ ደብዳቤ ……… ለተወዳጁ ለኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ
እባካችሁን እስከመጨረሻው ያዳምጡ!! ሼር ሼር ያድርጉ

አልሀምዱሊላህ 🤲🤲🤲 ታላቁ አሊም ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ ቀዶ ጥገናቸውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሰዋል!!!ይሁን እንጂ አሁንም በሰላም ተመልሰው ወደ ሀገራችን እስኪመለሱ ድርስ ሁላችንም በዱአች...
28/02/2024

አልሀምዱሊላህ 🤲🤲🤲 ታላቁ አሊም ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ ቀዶ ጥገናቸውን በተሳካ ሁኔታ ጨርሰዋል!!!

ይሁን እንጂ አሁንም በሰላም ተመልሰው ወደ ሀገራችን እስኪመለሱ ድርስ ሁላችንም በዱአችን አንርሳቸው

ታላቁ አሊም ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል ገቡ!!የተፍሲሩ ሊቅ!! የሀገራችን ብርሀን 🌥ታላቁ አሊማችን ሼይኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ በድጋሚ ለህክምና ወደ ቱርክ ከተጓዙ ቡ...
28/02/2024

ታላቁ አሊም ሸይኽ ሰዒድ አህመድ ሙስጠፋ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል ገቡ!!

የተፍሲሩ ሊቅ!! የሀገራችን ብርሀን 🌥

ታላቁ አሊማችን ሼይኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ በድጋሚ ለህክምና ወደ ቱርክ ከተጓዙ ቡሃላ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል ገብተዋል !

ሀገራችን ካፈራቻቸው እውቅ አሊሞች መካከል አንዱ የሆኑት ሼይኽ ሰኢድ አህመድ ሙስጠፋ ባጋጠማቸው ህመም በድጋሚ ለህክምና ወደ ቱርክ በድጋሜ ከተጓዙ ሳምንት የሞላቸው ሲሆን በዱአቹህ አትርሷቸው።

ሼይኽ ሰዒድ ጠና ያለ ህመም ያጋጠማቸው በመሆኑ የተሳካ ህክምና አድርገው በሙሉ አፊያ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ የሁላችንም ዱዓ ያስፈልጋቸዋል::

አሊሞቻችን ለምድራችን የኢልም ብርሀን ናቸው:: እነሱን ማጣት የኢልም ብርሀን እንደማጣት ነው::

ለሼይኽ ሰዒድ ሁላችንም ከልብ ዱዓ እንድናደርግላቸው ጥሪዬን ለማቅረብ እወዳለሁ

አላህ ሆይ ታላቁ አሊማችንን ከሙሉ ጤንነት ጋር ለሀገራቸው ታበቃቸው ዘንድ እንማፀንሀለን🤲🤲🤲
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

አሮን ቡሽኒል የ25 አመቱ ወጣት የአሜሪካን አየር ኃይል አባል ከሰአታት በፊት ዋሽንግተን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ደጃፍ ላይ እራሱን በእሳት አቃጥሏል እራሱን የማቃጠል ሂደት በቀጥታ ባስ...
26/02/2024

አሮን ቡሽኒል

የ25 አመቱ ወጣት የአሜሪካን አየር ኃይል አባል ከሰአታት በፊት ዋሽንግተን በሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ደጃፍ ላይ እራሱን በእሳት አቃጥሏል

እራሱን የማቃጠል ሂደት
በቀጥታ ባስተላለፈው ቪዲዮ ላይ እንዲህ ነበር ያለው

" ከዚህ በኋላ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተባባሪ አልሆንም
እጅግ አደገኛ የሆነ የተቃውሞ ድርጊት ልፈፅም ነው
ነገር ግን በፍልስጤም ንፁሃን ላይ በቅኝ ገዥዎች እያጋጠሟቸው ካለው ግፍ ጋር ሲነጻጸር ብዙም አይደለም

እራስን ማቃጠል አሰቃቂ ነገር ነው ነገር ግን በጋዛ እየሆነ ያለውን ያህል አስፈሪ አይደለም
ፍሪ ፓሊስታይን "

እሳቱን አጥፍተው ወደ ሆስፒታል ቢወስዱትም ህይወቱ ልትተርፍ አልቻለችም

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ሀገራችን ታላቅ አሊም አጥታለች።የባዩሽ መስጂድ ኢማም የሆኑ ሼኽ አብዱልሰላም አባት ሼኽ አንዋር (የጃረሞ ሼኽ) ወደ አኼራ ሄደዋል።አላህ ይዘንላቸው ለቤተሰቦ...
26/02/2024

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ሀገራችን ታላቅ አሊም አጥታለች።የባዩሽ መስጂድ ኢማም የሆኑ ሼኽ አብዱልሰላም አባት ሼኽ አንዋር (የጃረሞ ሼኽ) ወደ አኼራ ሄደዋል።

አላህ ይዘንላቸው ለቤተሰቦቻቸውም ሷብርን ይወፍቅ።
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

800 ሚሊዮን ዶላር የፈጀው በአፍሪካ ትልቁ መስጂድ በአልጄሪያ ተመረቀ!..የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የአልጀርሱን ታላቁ መስጂድ እሁድ እለት በይፋ ከ...
26/02/2024

800 ሚሊዮን ዶላር የፈጀው በአፍሪካ ትልቁ መስጂድ በአልጄሪያ ተመረቀ!..
የአልጄሪያው ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡኔ በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የአልጀርሱን ታላቁ መስጂድ እሁድ እለት በይፋ ከፍተዋል። በሳውዲ አረቢያ እስላማዊ ቅዱስ ከተሞች መካ እና መዲና ከሚገኙት መስጊዶች በመቀጠል በአለም ሶስተኛው ትልቁ መስጊድ ያደርገዋል፡፡ ግዙፉ መስጊድ በ70 ሄክታር ላይ የተገነባ ሲሆን በአንድ ጊዜ እስከ 120ሺ ሰጋጆችን መያዝ ይችላል።..
በተጨማሪም የአለማችን ረጅሙ ሚናር ያለዉ ሲሆን የጸሎት ጥሪ ለማስተላለፍ የሚያገለግል ግንብ ነው። የመስጊዱ ግንባታ ከሰባት አመታት በላይ የጠየቀ ሲሆን ከ800 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ተደርጎበታል፡፡..
ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚጀምረዉ የረመዳን ወር ኃይማኖታዊ ስነስርዓቶችን ያስተናግዳል ተብሎ ይጠበቃል።..

የሰብዓዊነት ጥግ ያንግ ጊ በካናዳ ኦትዋ ስመ ጥር ዶክተር ነው እስራኤል በጋዛ ሆስፒታሎች ላይ በምታደርሰው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅጉን የተከፋ በቲውተር ገፁ ላይ የእስራኤልን ጭካኔ አሰፈረ "...
24/02/2024

የሰብዓዊነት ጥግ

ያንግ ጊ
በካናዳ ኦትዋ ስመ ጥር ዶክተር ነው
እስራኤል በጋዛ ሆስፒታሎች ላይ በምታደርሰው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት እጅጉን የተከፋ
በቲውተር ገፁ ላይ
የእስራኤልን ጭካኔ አሰፈረ
" በመድሃኒት እጦት ህፃናት ያለ ማደንዘዣ እግር እና እጃቸው ሲቆረጥ እናቶች ያለ ማደንዘዣ በኦፕራሲዮን እንዲወልዱ ማስገደድ የጦር ወንጀል ነው "

እንደ ህክምና ባለሞያነቱ የሰጠው አስተያየት ነበር

ነገርግን
ከእስራኤል ጋር እጅ እና ጓንት የሆኑት ምዕራባውያን የዶ/ር ያንግ ንግግር አልተዋጠላቸውም
ከስራ እንዲባረር አደረጉት

ዶ/ር ያንግ
ስራ ፈትቶ ከቤት መዋል አልፈቀደም
መንፈሱን የረበሸው እና እንቅልፍ የነሳውን የጋዛ ንፁሃን ለመታደግ በሙያው የበኩሉን ድርሻ ለማበርከት ከውሳኔ ደረሰ

ወደ ግብፅ በረራ አደረገ

ሱፐር ማርኬት እንዲሁም ፋርማሲ በመግባት አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን በመግዛት
በግብፅ ራፋህ በኩል አቋርጦ ጋዛ ደረሰ

ዶ/ር ያንግ ሲናገር
የወሰድኩት እርምጃ አደገኛ እንደሆነ አውቃለሁ ህይወቴን ሊያሳጣኝም ይችላል ነገርግን የእኔ ህይወት እዚህ ከሚገኙ ንፁሃን የተለየ አይደለም

ለሙያዬ ቃል በገባሁት መሰረት የህክምና እርዳታ የሚፈልጉ ንፁሃንን እያገለገልኩ ብሞት ደስተኛ ነኝ

በመሆኑም በሙያዬ ንፁሃንን እየረዳሁ እቆያለሁ "
መረጃወችን ለወዳጄ ዘመድ ሼር ያርጉ!
የቴሌግራም ቻናላችን ከስር በሊንኩ ይቀላቀሉ👇
https://t.me/+UAKV32q7U2HKzEMf

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኡማ ቲቪ /omah tv /ﻗﻨﺎﺓ ﺃﻣﺔ ﺍﻟﻔﻀﺈﻳﺔ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category