Amazing Grace Tv Channel

Amazing Grace Tv Channel Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amazing Grace Tv Channel, TV Channel, Zinabusonofjesus@gmail. com, Addis Ababa.

፨ መከራ ወይም ቻላጅ በውስጣችን የተሸከመናውን ያክላል።     ፨  ዛሬም በውስጣቹ የተሸከማቹት ራዕይ ዋጋ  የምያስከፍላቹ የእኔ ነገር ከስው የተለየ ነው እንዴ ? ልክ እንዴ ርብቃ ይህ ለኔ...
06/04/2024

፨ መከራ ወይም ቻላጅ በውስጣችን የተሸከመናውን ያክላል።
፨ ዛሬም በውስጣቹ የተሸከማቹት ራዕይ ዋጋ የምያስከፍላቹ የእኔ ነገር ከስው የተለየ ነው እንዴ ? ልክ እንዴ ርብቃ ይህ ለኔ ምኔ ነው ያላቹ አይዙአቹ ያሽከማቹ እርሱ እግዚአብሔር ይረዳቹዋል። ዘፍጥረት 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ ይስሐቅም ስለሚስቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ መካን ነበረችና እግዚአብሔርም ተለመነው፥ ርብቃም ሚስቱ ፀነሰች።
²² ልጆችም በሆድዋ ውስጥ ይገፋፉ ነበር፤ እርስዋም፦ እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔ ምኔ ነው? አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች።
²³ እግዚአብሔርም አላት፦ ሁለት ወገኖች በማኅፀንሽ ናቸው፥ ሁለቱም ሕዝብ ከሆድሽ ይከፈላሉ፤ ሕዝብም ከሕዝብ ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል።
²⁴ ትወልድ ዘንድ ዘመንዋ በተፈጸመ ጊዜም፥ እነሆ፥ በማኅፀንዋ መንታ ነበሩ።
²⁵ በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ ሁለንተናውም ጠጕር ለብሶ ነበር፤ ስሙም ዔሳው ተባለ።
²⁶ ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።

Ma blessed isaac happy happy birth day lv u so much.
01/05/2023

Ma blessed isaac happy happy birth day lv u so much.

Happy birth day ma bigger of ur brothers Love u so much happy happy birth day again & again.
01/05/2023

Happy birth day ma bigger of ur brothers Love u so much happy happy birth day again & again.

30/03/2023

(ኦሪት ዘጸአት ምዕ. 33)
----------
13፤ አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ አውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ መንገድህን እባክህ አሳየኝ፤ ይህም ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ተመልከት አለው።

14፤ እግዚአብሔርም። እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፥ አሳርፍህማለሁ አለው።

15፤ እርሱም። አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህስ፥ ከዚህ አታውጣን።

16፤ በምድርም ፊት ካለው ሕዝብ ሁሉ እኔና ሕዝብህ የተለየን እንሆን ዘንድ አንተ ከእኛ ጋር ካልወጣህ፥ እኔና ሕዝብህ በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘታችን በምን ይታወቃል? አለው።

17/02/2023

(የሐዋርያት ሥራ ምዕ. 12)
----------
1፤ በዚያም ዘመን ንጉሡ ሄሮድስ መከራ ያጸናባቸው ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ በአንዳንዶቹ ላይ እጁን ጫነባቸው።

2፤ የዮሐንስንም ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።

3፤ አይሁድንም ደስ እንዳሰኛቸው አይቶ ጨምሮ ጴጥሮስን ደግሞ ያዘው። የቂጣ በዓልም ወራት ነበረ።

4፤ በያዘውም ጊዜ ወደ ወኅኒ አገባው ከፋሲካም በኋላ ወደ ሕዝብ ያወጣው ዘንድ አስቦ እያንዳንዱ አራት ወታደሮች ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍራ ክፍል አሳልፎ ሰጠው።

5፤ ጴጥሮስም በወኅኒ ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ስለ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ጸሎት አጥብቆ ይደረግ ነበር።

6፤ ሄሮድስም ሊያወጣው ባሰበ ጊዜ፥ በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር።

7፤ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።

16/02/2023
06/02/2023

0912654914

16/11/2022

" ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:11)

**** ሰለ ው/ዊ ቦንኬ ያነበቡኩትን ላካፋላቹ ፡ ገና በማለዳው ካረፈበት ሆቴል የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ አንድ መናፈሻ ገብቶ አረፍ አለ።አጠገቡ አንድ በሀያዎቹ የሚገመት አንድ ወጣት ፀሐይ...
10/11/2022

**** ሰለ ው/ዊ ቦንኬ ያነበቡኩትን ላካፋላቹ ፡ ገና በማለዳው ካረፈበት ሆቴል የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ አንድ መናፈሻ ገብቶ አረፍ አለ።አጠገቡ አንድ በሀያዎቹ የሚገመት አንድ ወጣት ፀሐይ ሲሞቅ አየ። ረዘም ያለውን ዝምታ የሰበረ ንግግር ተናገርኩኝ ሁልጊዜም እንደማደርገው ይህን አጋጣሚ የወንጌሉን የምስራች ለመናገር ስለፈለኩኝ "የማለዳው ፀሐይ እንዴት ናት? ብዬ ዝምታውን ሰበርኩኝ።
ወጣቱ ልጅ:" ቆንጆ ነው በጣም ደስ ይላል" አለኝ

ቦንኬ: "ይህን ውብ ፀሐይ በነፃ የሰጠን ማን እንደሆነ ታውቃለህ? አልኩት

ወጣቱ ልጅ: " አላውቅም" አለ

ቦንኬ: "መጽሐፍ ቅዱስ ታነባለህ? "አልኩት
ወጣቱ ልጅ: " ፊቱን ጭፍግግ አድርጎ አላነብም ለምን አነባለሁ መጽሐፍ ቅዱስ እኮ ያረጀ መጽሐፍ ነው። እንደምታየኝ እኔ ወጣት ነኝ። የ21 ክፍለ ዘመን ሰው ነኝ ወጣት ነኝ ለእኔ የሚመጥኑ አዳዲስ ፍልስፍናዎችን ያየዙ መጽሐፍትን አነባለሁ እንጂ ያረጀ እና ዘመን ያለፈበትን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ሊያደርግልኝ አነባለሁ" አለኝ

ቦንኬ: ጥቂት ሰኮንዶች ዝም ካልኩኝ በኋላ የውይይቱን አቅጣጫ የቀረኩኝ በማስመሰል " አሁን እዚህ ምን ትሰራለህ" አልኩት
*ወጣቱ ልጅ:ዘና ብሎ እንደምታየው ፀሐይ እየሞኩኝ ነው አለኝ:
ቦንኬ:ቆፍጠን ብዬ ፀሐይ ለምን ትሞቃለህ እንደ አንተ አይነቱ የ21 ክፍለ ዘመን ወጣት ይህችን አሮጌ ፀሐይ መሞቅ አልነበረበትም።የፀሐይ እድሜ ብዙ ሚለየን አመት እንደሆነች ከሳይንስ እንደተማከርክ እርግጠኛ ነኝ።ስለዚህ እንደ አንተ አይነቱ ወጣት አዲስ ነገር መፈለግ ይኖርበታል እንጂ አሮጌ ነገር መፈልግ አይኖርበትም በማለት በማፌዝ ተናገርኩት። ወጣቱ ግራ በመጋባት ማዳመጥ ጀመረ። ቦንኬም በመቀጠል "አየህ ፀሐይ እድሜዋ ረዥም ቢሆንም ዛሬም ብርህን ትሰጣለች ፣ ሙቋቷ አልቀነሰም ፣ ድምቀቷ አልቀነሰም።ዘር፣ ቀለም ፣ሃይማኖት ሳትለይ ለሁሉ ታበራለች።መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ነው።ዛሬም ለሰው ዘር ሁሉ ያበራል ፣ ነፃ ያወጣል ፣ ይለውጣል ።የፀሐይ ብርሃን ወደ አንተ የመጣው ከ93 ሚሊየን ማይልስ ርቀት ነው።አንተ ግን ወደ ፀሐይ ለመድረስ ብዙ አልተጓዝክም።ሲነጋ ለፀሐይ በርህን ከፍተህ አሁን ደግሞ ወጥተህ በፀሐይ ፊት ተቀምጠህ ሁለተናህን ለፀሐይ ብርሃኗ እና ለሙቀቷ ሰጠህ። የእግዚአብሔርም ቃል ከአንተ የሚጠበቀው ይሄ ነው። ልብህን ለቃሉ እና ለኃይሉ ብርሃን ክፈት በውስጡ ላለው እውነቱ ራስህን ስጥ "
ወጣቱም ልጅ: ፊቱ በርቶ ደስ ብሎት መስማት ቀጠለ
የእግዚአብሔር ቃል አያረጅም ዛሬም ይሰራል ፣ ለዘላለም ህያው ነው። ከቃሉ የሚመነጨው ብርሃን በውስጥ የተዳፈነውን እምነት እና ተስፋ ቀስቅሶ ወደ ዘላለም ህይወት ይመራል። መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ነው። የህይወታችን መመሪያችን እንዲሆን ሁልጊዜም ከምንም ነገር በላይ ጊዜ ሰጥተን ልናጠናው፣ ልናሰላስልው ይገባል።

"....እኔ ዛሬ የማዝህን እነዚህን ትእዛዛት በልብህ ያዝ፤
በልጆችህም ውስጥ ቅረጻቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድ ላይ ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሳ ስለ እነሱ ተናገር..." ዘዳግም 6:6-7
" ኢየሱስ ክርሰቶሰ ያድናል "

09/11/2022

" ሥራህን አውቃለሁ፤ እነሆ፥ በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼአለሁ ማንምም ሊዘጋው አይችልም፤ ኃይልህ ምንም ትንሽ ቢሆን ቃሌን ጠብቀሃልና፥ ስሜንም አልካድህምና።"
(የዮሐንስ ራእይ 3:8)

(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 1)----------1፤ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።2፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋ...
08/11/2022

(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 1)
----------
1፤ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።

2፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።

3፤ እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።

ከተማሩ ሰዎች ይልቅ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ #አልማዝ የሚሆነው የድንጋይ  #ከሰል ነው !አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል P...
08/11/2022

ከተማሩ ሰዎች ይልቅ በመከራ ያለፉ ሰዎችን አከብራለሁ

#አልማዝ የሚሆነው የድንጋይ #ከሰል ነው !

አልማዝ በተፈጥሮ መንገድ እንዴት እንደሚሰራ ልንገራችሁ። አልማዝ የሚሰራው HPHT በሚባል Process ነው። HPHT ማለት High Pressure High Temperature ማለት ነው። አንድ አልማዝ አልማዝ ከመሆኑ በፊት አራት ደራጃዎችን ማለፍ ይኖርበታል። አንደኛ ከምድር በታች ከ300 እስከ 600 ኪሎ ሜትር ዝቅ ብሎ መቀመጥ። ሁለተኛ ከፍተኛ ሙቀት መታደል፣ ከ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ቃጠሎ ውስጥ መቀመጥ። ሶስተኛ ከፍተኛ ጭነት ማግኘት። አራተኛ ለረዥም ጊዜ ውስጥ በነዚህ ሁኔታ ውስጥ መቆየት ! እንግዲህ አንድን የድንጋይ ከሰል ወስዳችሁ ከምድር በታች 600 ኪሎ ሜትር ብታወርዱት፣ 1200 ዲግሬ ስንቲ ግሬት ቃጦሎ ውስጥ ብታኖሩት፣ በከፍተኛ ፕሬዠር ውስጥ ብታስቀምጡት እና ለረዥም ጊዚያት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብትተዉት። ከሱሉ አልማዝ ይሆናል ! ከሰሉ ወደ ዳይመንድ ይለወጣል።

አንዳንዶቻችሁ በህይወታችሁ ግራ ይገባችኋል፣ በጣም የሚወዳችሁ አምላካችሁ ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር አውርዷችሁ ይሆናል። በማይገባችሁ ፈተና 1200 degree cent great ቃጠሎ ውስጥ አስቀምጧችሁ ፤ በማጣት፣ በመገለል፣ በመገፋት ለረዥም ጊዚያት እየፈተናችሁ "ምንድነው እየተካሄደ ያለው" ብላችሁ እስክትጠይቁ ድረስ ለአምስት አመት፣ ለአስር አመት ከሰው፣ ከወዳጅ፣ ከዘመድ፣ ከጓደኛ ዝቅ አድርጓችሁ ይሆናል። ....

"ምን ማለት ነው የሚወደኝ አምላክ ይሄን የሚፈቅደው" ስትሉ .... አልማዝ አድርጎ ሊሰራችሁ፣ ውብ አድርጎ፣ ሊሰራችሁ፣ የምታበሩ አድርጎ ሊያበጃችሁ፣ እንቁ፣ ዳይመንድ፣ አልማዝ ሊያደርጋችሁ ስላሰበ ነው !

አልማዝ ሰባት ባህሪዎች አሉት።

#አንደኛ ጠንካራ ነው። ወስዳችሁ በድንጋይ ቀጥቅጡት አይሰበርም። በሰይፍ ምቱት አይሰነጠቅም። በመጋዝ ገዝግዙት አይቆረጥም። በአልመዝ ግን ብረት ይቆረጣል፣ በአልማዝ ግን ሰይፍ ይቆረጣል። በአልማዝ ግን ድንጋይ ይፈርሳል። አልማዝ የሚቆረጠው በሌላ አልማዝ ነው።

#ሁለተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። ከፍተኛ የማንጸባረቅ ባህሪ አለው። refractive index ይባላል። የተቀበለውን ብርሃን መልሶ የማብራት ባህሪ አለው። ያንጸባርቃል።

#ሶስተኛው የአልማዝ ባህሪ የተቀበለውን የጸሐይ ብርሃን፣ ነጩን ብርሃን ወደ ተለያዩ በርካታ ቀለማት የመበተን ችሎታ አለው።

#አራተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። እጅግ በጣም ንጹህ ነው። አልማዝ የሚታወቀው በነጹህነቱ ነው።

#አምስተኛ የአልማዝ ባህሪ ልንገራችሁ። አልማዝ በእሳት አይቃጠልም። አንድ ቤት ውስጥ አልማዝ አለ እንበል ያ አልማዝ ያለበት ቤት ሙሉ ለሙሉ ቢቃጠል አልማዙ ምንም አይሆንም። ምንም። በነበረው ቅርጹ፣ በነበረው ንጽህናው እናገኘዋለን።

የሚያስገርመኝን #ስድስተኛውን የአልማዝን ባህሪ ልንገራችሁ። ወርቅ ላይ አሲድ ድፉበት ወርቁ ይበላሻል። አልማዝ ላይ አሲድ አፍስሱበት ምንም አይሆንም። አይበላሽም።

የመጨረሻው እና #ሰባተኛው የአልማዝ ባህሪ በጣም ውድ ነው። በጣም ውድ ነው። የአውራጣትህን ራስ የምታክል ዳይመንድ አንድ ትልቅ ፎቅ ይገዛል። በጣም ውድ ነው።

ከጓደኞቻችሁ በታች 600 ኪሎ ሜትር ወርዳችሁ ፣ በ1200 ዲግሪ ሴንቲ ግሬት ስቃይ ውስጥ ያለፋችሁ፣ በፕሬዠር ውስጥ ለበርካታ አመታት ያለፋችሁ እናንተ አልማዝ ሁናችሁ የተሰራችሁ ሰዎች ናችሁ። ሰዎች ጠጠር ብትመስሏቸውም አልማዞች ናችሁ። ዋጋችሁ በጣም ውድ ነው። ...

07/11/2022

" በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ። በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና።"
(2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:6)

07/11/2022

" ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም ጣዖትን የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት የለውም።"
(ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:5)

ኢሳይያስ 53¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋ...
22/04/2022

ኢሳይያስ 53
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
⁵ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

31/08/2021

JESUS JESUS

Kibere ale gena . Jesus is Lord
14/03/2021

Kibere ale gena . Jesus is Lord

07/06/2020

Jesus is Lord

Address

Zinabusonofjesus@gmail. Com
Addis Ababa
11111222

Telephone

0912654914

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amazing Grace Tv Channel posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amazing Grace Tv Channel:

Videos

Share

Category



You may also like