St mary's University Accounting Department 2004 - 2006 batch

St mary's University Accounting Department 2004 - 2006 batch Every Things happen in Accounting Stay in Accounting

06/12/2022

የገና_ጾም_የንስሐ_እና_የቄደር_ጥምቀት_ጥሪ



❤ !

"ጥሩ ውኃንም እረጭባችኃለሁ እናንተም ትጠራላችሁ" ሕዝቅ 36፥25

"የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም"

❤ ?

❤ ?

❤ ?

የነፍስ ጉዳይ ነውና ሳትቸኩሉ በደንብ አንብቡት!

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት ለጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።" 1ኛ ጴጥ 4፥3

ቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

!

ተወዳጆች ሆይ እሑድ ህዳር 25 ጠዋት 2 ሰዓት በወይን አምባ ማርያም ቤተ ክርስትያን የቄደር ጥምቀት እና ንስሐ የመስጠት አገልግሎት ስላለ መጥታችሁ ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ። እባካችሁ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ኑ። በተቻለ መጠን ደጇ ሁለት ሰዓት ድረሱ!

የጸሎት መርሃ ግብሩ ካለቀ በኃላ ብትጠመቁ ዋጋ የለውም። ምክንያቱም ለምሳሌ የጸሎቱ መርሃ ግብር ላይ አቡነ ዘበሰማያት 41 ጊዜ ካርያላይሶን 41 ጊዜ እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ ወዘተ እንድትጸልዩ ስለሚሰጣችሁ እነዚህን ጸሎቶች ሳትካፈሉ ሰዓት አርፍዳችሁ ብትመጡ መጠመቅ አይቻልም። ስለዚህ የነፍስ ጉዳይ ነውና ሰዓት ይከበር።

❤ ?

ቀደር ለመጠመቅ የሚያበቁን ኃጢአቶች ለምሳሌ ረቡዕ ብና አርብ የፍስክ ከበላን፣ ውርጃ ከፈጸምን፣ ከሃይማኖታችን ውጪ ካሉ ሰዎች ጋር ሩካቤ ሥጋ ከፈጸምን፣ በልጅነት እና ካደግን በኃላ ግብረ ሰዶም ከፈጸምን፣ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ካደረግን፣ በልጅነት መሬትን ካወሰብን፣

ከሥጋ ዘመድ ጋር ግንኙነት ከፈጸምን፣ ቅዱስ ቁርባን ተቀብለን በዝሙት ከወደቅን፣ በቅዱስ ቁርባን አግብተን ባል በሚስት ላይ ሚስት በባል ላይ ከዘሞተች፣ ኢ- ሩካቤ ከፈጸምን ማለት ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ ግንኙነቶችን ከፈጸምን፣ የአሕዛብን ምግብ ከበላን፣ ኦርቶዶክስ ሆነን ወደ ሌላ እምነት ገብተን ከተመለስን፣

ለዛር ለጨሌ ለአቴቴ ከገበርን፣ የተገበረውን መስዋዕት ከበላን፣ ጠንቋይ ቤት ከሄድን፣ ዛር አንጋሽ ጋር ከሄድን፣ ግለ ወሲብን ከፈጸምን፣ ሴት የወር አበባዋን ሳትጨርስ ግንኙነት ካደረገች፣ ወንድም የወር አበባ ካልጨረሰች ሴት ጋር ግንኙነት ካደረገ፣ ጫት ሲጋራ ከተጠቀምን ወዘተ ቄደር የግድ መጠመቅ አለብን።

ወዳጆቼ ልብስ በሳሙና ይታጠባል በመጨረሻ በኦሞ ተዘፍዝፎ ይለቀለቃል። በዚህም ጸዐዳ ይመስላል። ንስሐ ኃጢአታችንን የምናጥብበት ሳሙና ነው። ቄደር ደግሞ ኦሞ ነው ያነጻናል።

በተለይ ንስሐ ገብታችሁ ቅዱስ ቁርባን ለመቀበል ያሰባችሁ ቄደር ተጠምቃችሁ ብትቀበሉ መልካም ነው። በንስሐ ያላካተትነው ኃጢአት በቄደር ይነጻልና። እንዲሁም በቄደር ነጽተን ቅዱስ ቁርባን ብንቀበል ይሰምርልናል።

ሌላው ንስሐ ለመግባት አስባችሁ የንስሐ እድሉን ያላገኛችሁ እና ንስሐ አባት የሌላችሁ እሑድ ህዳር 25 ቀን ጠዋት 2 ሰዓት መጥታች በደብሩ ካህናት ንስሐ መግባት ትችላላችሁ።

የእናንተን ችግር የሚረዱ በተለይ ለካህናት መናገር የምትጨነቁበትንና የምታፍሩበትን ለምሳሌ ግለ ወሲብንና የወሲብ ፊልምን የተመለከቱ ወዘተ ዘመን አመጣሽ ኃጢአትን የሚረዱ ካህናትን ስላዘጋጀን መጥታችሁ በነፃ ንስሐ ግቡ፣ የኃጢአት ሸክምን በእናታችሁ ቤት አራግፉ።

የወለላይቱ እመቤት ልጆች የትኛውንም ኃጢአት ብንሠራ ሁሉም ኃጢአተቶች ከንስሐ በታች ናቸው። ከንስሐ በላይ የሆነ ኃጢአት የለም። የእኛ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ቸርነት በላይ አይደለም።

የእኛ ኃጢአት የደም ጠብታ ነው። የእግዚአብሔር ቸርነት ደግሞ ውቅያኖስ ነው። ስለዚህ የደም ጠብታ የውቅያኖስን ውሃ እንደማያደፈርስ ሁሉ የትኛውም የእኛ ኃጢአት የእግዚአብሔርን ቸርነት አይበልጥም። ንስሐ ግቡ ቄደር ተጠመቁ።

ስለዚህ እሑድ ህዳር 25 ቀን ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ወይን አምባ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስትያን ኑ። ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ጸሎቱ ይጀመራል መጥታችሁ ተጠመቁ።

❤ ፦

ከየትኛውም አቅጣጫ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርዳችሁ፣ ሠፈራ ብላችሁ በባጃጃ ተሳፍራችሁ፣ ድልድዩን እንደተሻገራችሁ አስፓልቱ ጫፍ ላይ ቤተ ክርስትያኗ ትገኛለች።

ከመገናኛ ቀጥታ ወይን አምባ ማርያም የሚል ታክሲ አለ ቤተ ኮርስቲያኑ በር ላይ ያወርዷቹኃል።

ከመገናኛ በቀጥታ ጎሮ ብለው ተሳፍረው፣ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ከዚያ ባጃጅ ተሳፍረው፣ ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ላይ ስትወርዱ ትገኛለች፡፡

ከሲ አምሲ፣ ከአያት፣ ከሰሚት የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው፣ ባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ጫፍ ወርደው ትገኛለች፡፡

ከቃሊቲ፣ ከቱሉ፣ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጩ የምትመጡ ጎሮ አደባባይ ወርደው ከዚያ በባጃጅ ተሳፍረው ሠፈራ ድልድይ ወርደው ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡

አርብ ህዳር 23-3-15 ዓ.ም
አዲስ አበባ

16/08/2020
20/02/2020

Amole is a Mobile Payment and Commerce Platform.

18/02/2020
18/02/2020
18/02/2020

Address

Addis Ababa
251

Telephone

+251920753463

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when St mary's University Accounting Department 2004 - 2006 batch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category


Other Music Awards in Addis Ababa

Show All