Atnawuz world አትናውዝ

Atnawuz world አትናውዝ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Atnawuz world አትናውዝ, TV Channel, Addis Ababa.

ለአማራው…!"…የማረከው ሬሽን ተመርዟል ሲልህ… የማረከውን ወታደር ቀድመህ አብላው። ውኃው ተመርዟል ሲልህም መራዡን አጠጥተህ ሞክርበት። ቅድሚያ ግን ፋኖ መቆጣጠር፣ መጠበቅ ያለበትን ይለይ። ...
05/08/2023

ለአማራው…!
"…የማረከው ሬሽን ተመርዟል ሲልህ… የማረከውን ወታደር ቀድመህ አብላው። ውኃው ተመርዟል ሲልህም መራዡን አጠጥተህ ሞክርበት። ቅድሚያ ግን ፋኖ መቆጣጠር፣ መጠበቅ ያለበትን ይለይ።

"…በሁለት ሦስት ቀን እንዲህ ከነቀነቅከው በቀጣዩ ቀናትማ የሚሆነውን አብሮ ማየት ነው። ይገባል አይወጣትም። ይኸው ነው።

https://t.me/atnawuz

05/08/2023
በቃን
04/08/2023

በቃን

https://youtu.be/5TgSV9GS6XU
03/08/2023

https://youtu.be/5TgSV9GS6XU

የአትናዉዝ ትኩስ እና ውቅታዊ ዜናዎችን ለማግኘት ስብስክራይብ ያድርጉ!atnawuzworld #አትናውዝ Gebremichael / # Amhara Regional state / / Ar...

ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች እየተደረጉ ያሉ እና በሌሎች አካባቢዎችም በአስቸኳይ መደረግ ያለባቸው ነገሮች፦ * ጊዜያዊ አስተዳደር ማዋቀር (የባለ አደራ መንግሥት) የፀጥታ መዋቅር መዘርጋት*...
03/08/2023

ፋኖ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች እየተደረጉ ያሉ እና በሌሎች አካባቢዎችም በአስቸኳይ መደረግ ያለባቸው ነገሮች፦

* ጊዜያዊ አስተዳደር ማዋቀር (የባለ አደራ መንግሥት) የፀጥታ መዋቅር መዘርጋት

* ህዝብ የመሠብሠብ፣ የማወያየትና የማሳመን ስራ መስራት

* የፋይናንስ ተቋማትንና መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን መምራት

* ኬላ በመዘርጋት፣ የደህንነት ፍተሻ ማድረግ

* እስር ቤቶችን ማስተዳደር የደህንነትና የመረጃ መስመር መዘርጋት

* አካባቢውን እንደ ነፃ ቀጠና በመጠቀም ሠራዊት መመልመል፣ ማሠልጠንና ማዝመት

* አጎራባች ከሚገኙ ሌሎች ፋኖዎች ጋር ቅንጂት በመፍጠር በመናበብ መታገል ከላይ የተጠቀሱት ጊዜ የማይሠጡ አስቸኳይ ተግባራት ናቸው። መደበኛ አደረጃጀት ቀጥሎ የሚታሠብ ነው።

አማራነት፤ አሸናፊነት!
ድል ለአማራ

https://youtu.be/_CKVjkX-YtE
20/07/2023

https://youtu.be/_CKVjkX-YtE

የአትናዉዝ ትኩስ እና ውቅታዊ ዜናዎችን ለማግኘት ስብስክራይብ ያድርጉ!atnawuzworld #አትናውዝ Gebremichael / # Amhara Regional state / / Ar...

እምዬ አገሬ ውድ አገሬ ኢትዮጵያ...እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ፣ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ፥ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ! በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶክ...
20/07/2023

እምዬ አገሬ ውድ አገሬ ኢትዮጵያ...እንዲሁም በጣም የምወዳችሁ፣ የማከብራችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ እና የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ፥ ሰላም ሰላም ሰላም ብያለሁ!
በአክብሮት የሰጣችሁኝን የአክብሮት ዶክትሬት በጣም በትልቅ ደስታ ነው የተቀበልኩት። በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
እኔ በጣም፣ በጣም ነው የገረመኝ........ ታጭቼ ብገኝ እንኳን የሚያስደንቀኝ ነበር፤ .......ተመርጬ ስለተነገረኝ በጣም ነው የማመሰግነው። በጣም እግዚአብሔር ያክብርልኝ።
ፍቅራችሁ እንዲሁ አክብሮታችሁ ስለሆነ፣ በእኔ እና በወገኖቼ ስም፤ እንዲሁም በዚህ ሁሉ ደስ በሚላቸው ኢትዮጵያውን ስም ከልቤ በጣም በጣም አመሰግናለሁ። እግዚአብሔር ሕይወታችሁን ይባርከው።
የኢትዮጵያ፥ ዛሬ ያሉትን ተማሪዎች፣ እንዲሁም የወደፊቱን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክ። አገራችንን መንፈስ ቅዱስ ይጠብቅልን።
ያስቸግራል ለመግለጽ ደስታዬን። በጣም አመሰግናለሁ። በጣም ክብራችሁ እና ፍቅራችሁ ከልክ ያለፈ ነው በቃ... ለእኔ የሚገባኝ አይደለም። ግን ይኽን ሁሉ ስላከበራችሁኝ በጣም እግዚአብሔር ይስጥልኝ። በጣም አመሰግናለሁ።
የኢትዮጵያን ሕዝብ እግዚአብሔር ይጠብቅልን። ምስጋናዬ በጣም ከፍ ያለ ነው።
በአካል ተገኝቼ አንድ ቀን እዚያ መጥቼ አያችኋለሁ። በሰላም ቆዩኝ። ይኽንን አጭር መልእክቴን ይቅር በሉኝ። ሌላ ጊዜ በደንብ አመሰግናችኋለሁ። (ሳቅ)
በጣም እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
እጅጋየሁ ነኝ። Thank You!


╔═╦╗╔╦╗╔═╦═╦╦╦╦╗╔═╗
║╚╣║║║╚╣╚╣╔╣╔╣║╚╣═╣
╠╗║╚╝║║╠╗║╚╣║║║║║═╣
╚═╩══╩═╩═╩═╩╝╚╩═╩═╝
----------------------------------------------------------------
Follow all of these
Facebook: https://www.facebook.com/atnawuzworld
Youtube: https://www.youtube.com/
Instagram: https://www.instagram.com/atnawuzworld
Tiktok: https://www.tiktok.com/
Telegram: https://t.me/atnawuzworld
-------------------------------------------------

14/07/2023

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) የወጣ መግለጫ!

በትናትናው እለት ራያ ቆቦ ከተማን ጨምሮ አራዱም ፣አሳመምቻ ፣ቀመሌ ተክለሃይማኖት ፣ጠዘጠዛ ፣ሮቢት እና ጎብዬ ዙርያ ባሉ አካባቢዎች በዋርካው ምሬ ወዳጆ በሚመራው የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ላይ በአገዛዙ የኦሮሙማ ስርአት የተከፈተው ጦርነት ባለፉት ሀያ ሰባት አመታታ በልዩነት አማራው ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈፅም የነበረውን የወያኔን ስርአት ፍላጎት ለማስፈፀም የሚደረግ የጦር ወንጀል ነው።

ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ባደረገው ማጣራት የገዥው ሰርዐት በኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም በፖርላማ በሽብር ብድን የተፈረጀውን እና ትላንት በአብዛኛው የኦሮሚያ ክልል ቦታዎች ላይ ለምሳሌ በወለጋ ፣ በጉትን፣ በሆሩ ጉድሩ፣ ወዘተ ላይ በሚኖሩ አማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀመውን የኦነግ ሰራዊት ወደ አማራ ክልል እያስገባ መሆኑን ደርሰንበታል ። በመሆኑም ትላንት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ላይ የዘመተው ሰራዎት የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የኦነግ ሰራዊት ጥምር ጦር እደሆነ ደርሰንበታል።

ባለፉት ወራት ውስጥ ህግ ለማስከበር በማለት አማራ ክልል ላይ በሁሉም አቅጣጫ የተከፈተው ጦርነት ከጅምሩ አሸባሪ ቡድንን ህግ አስከባሪ አድርጎ ማስገባት የስርዐቱን የዕለት ተዕለት ጨፍጫፊነት የሚያሳይ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በመላው ሀገሪቱ የሚጨፈጨፉ አማሮችን የደህንነት ከለላ ሳይሰጥ በአማራ ክልል ምንም የሰላም ችግር በሌለበት ሁኔታ ጦር ማዝመት የስርዐቱን አማራውን ሁለንተናዊ እረፍት ነስቶ በአፋጣኝ ህልውናውን ለመንጠቅ የሚደረግ ዘመቻ መሆኑን ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ለመላው የአማራ ህዝብ ለማስገንዘብ እንወዳለን።

በመጨረሻም ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር ( አተማ ) የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል።

▪️1) መንግስት ህግ ለማስከበር በሚል አማራ ክልል ላይ እየፈፀመው ያለውን የዘር ጭፍጨፋ በአፋጣይ እዲያቆም ጥሪ እናስተላልፋለን፣

▪️2) መንግስት በኢትዮጲያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ስም ወደ አማራ ክልል ያስገባውን የኦነግ ሰራዊት በአፋጣኝ እዲያስወጣ ጥሪ እናስተላልፋለን፣

▪️3) መንግስት ፋኖነት የአማራ አንዱ ባህላዊ ስርዐት ወይም መገለጫ መሆኑን ተገንዝቦ አሁን እያደረገው ያለውን ይህንን የአማራ ባህል የማጥፋት ወንጀል እዲያቆም ጥሪ እናደርጋለን፣

▪️4) መላው የአማራ ህዝብ የተከፈተበት ጦርነት ህልውናውን እስከ ወዲያኛው ለመንጠቅ የሚደረግ ጭፍጨፋ መሆኑን በልኩ ተገንዝቦ ህልውናውን በአንድነት በመቆም እዲያስጠብቅ ማህበራችን የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን። https://www.youtube.com/watch?v=yMUd-JIV7aA&t=329s&pp=ygUNYXRuYXd1eiB3b3JsZA%3D%3D

የአንድ ሳምንቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ የአዲስ አበባ ቆይታ ምን ይመስል ነበረ ?በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው ልዑካን ቡድን ከፌዴራል እና ከክ...
02/04/2023

የአንድ ሳምንቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑክ የአዲስ አበባ ቆይታ ምን ይመስል ነበረ ?

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተመራው ልዑካን ቡድን ከፌዴራል እና ከክልል አመራሮች ጋር ያደረገውን ምክክር አጠናቆ ዛሬ መቐለ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ለአንድ ሳምንት ያህል የተደረገው ምክክር የተጀመረው የሰላም ሂደት የተሟላ እንዲሆን በማድረግ አንፃር ስኬታማ ነበር ብሏል።

ምክክሩ የነበረው ፦
- የትግራይ ግዛታዊ አንድነትን ወደ ቦታው መመለስ፣
- በጀት እንዲለቀቅ ማድረግ፣
- ትግራይን መልሶ ማቋቋም እና መገንባት
- እስረኞች መፍታት የሚሉት ትኩረት ተሰጥቷቸው ውይይት ከተደረጉባቸው ጉዳዮች መካከል እንደሆኑ ተነግሯል።

ምክክሩን በተመለከተ የልዑካን ቡድኑ አባል ዶ/ር ሃጎስ ጎደፋይ ምን አሉ ?

" በወሳኝ ጉዳዮች ላይ እና በልማት ስራዎች ደጋፊ በሚሆኑበት ላይ በግልፅ እና በቅርበት መወያየት አስፈላጊ ስለነበር በተለይ በበጀት ጥያቄ፣ የግዛት አንድነት፣ እስረኞች መፍታት፣ ሰብዓዊ እርዳታ ሁሉም ጉዳዮች ላይ የፌዴራል መንግስት የድርሻውን እንዲያበረክት በሚያስችል መንገድ ሰፊ ውይይት አድርገናል ፤ በልዩ ሁኔታ በተለይ ከፌዴራል መንግስት ጋር ተነጋግረናል።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችም በአካል መጥተው የሚናጋገሩበትን መንገድ የሚጠርግ ነው ፤ መልካም ጅማሮም ታይቷል።

ካሳ፣ የደረሰ ውድመት እንዲሁም ማግኘት ስላለብን በጀት ወዘተ ተነጋግረናል፣ በፓርላማ የተወሰነው የ2015 በጀት እንዲለቀቅልን አሁን ተወስኗል። ሌላው በአስቸኳይ መፈታት ያሉባቸው ጉዳዮች በአፋጣኝ እንዲፈቱ ተነጋግረናል። "

በሌላ በኩል ፤ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ትግራይን መልሶ በማቋቋም ሂደት በሁሉም መስክ የበኩሉን እንደሚወጣ ዝግጅት ማጠናቀቁን የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ልዑካን ጋር የተወያዩ ሲሆን ውይይቱን ተከትሎ በሰጡት ቃል ተከታዩን ብለዋል ፦

" በትግራይ ባለፉት ዓመታት ከፍተኛ ጉዳት በህዝቡ ላይ ደርሷል፣ ብዙ ጥፋት ነው የተፈፀመው ያንን ከመሰረቱ በሚቀይር መንገድ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል።

የኦሮሚያ ክልል እዚህ ውስጥ ኃላፊነቱን በመወጣት ግዴታ አለበት፣ የትግራይ ህዝብ ህዝባችን ነው የራሳችን ነው ፤ ለዚህ ህዝባችን የሚያስፈልገውን ልክ ኦሮሚያ ክልል እንደምናደርገው ትኩረት አድርገን እዛ የሚሰሩትን ስራዎች መስራት መቀየር ያስፍልጋል።

ዘር በማቅረብ፣ ቴክኖሎጂ በማቅረብ፣ ችግኝ በማቅረብ፣ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በማገዝ ልክ እንደ አንድ ሀላፊነት ወስደን የክልላችን መንግስት ትኩረት አድርጎ በትግራይ ያሉ ስራዎች ላይ እንሳተፋለን ከኛ የሚጠበቀውን ሁሉ እናደርጋለን። "

Credit : TIGRAI TV


╔═╦╗╔╦╗╔═╦═╦╦╦╦╗╔═╗
║╚╣║║║╚╣╚╣╔╣╔╣║╚╣═╣
╠╗║╚╝║║╠╗║╚╣║║║║║═╣
╚═╩══╩═╩═╩═╩╝╚╩═╩═╝
----------------------------------------------------------------
Follow all of these
Facebook: https://www.facebook.com/atnawuzworld
Youtube: https://www.youtube/atnawuzworld
Instagram: https://www.instagram.com/atnawuzworld
Tiktok: https://www.tiktok.com/
Telegram: https://t.me/atnawuzworld

----------------------

 #መረጃ..!ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ  "ኢትዮጵያ ለገባችበት ችግር እርሶ ስልጣን በመልቀቅ የመፍትሄ አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ? ተብለው ከምክር ቤት አባል  በቀረበላቸው ጥያ...
02/04/2023

#መረጃ..!

ሰሞኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ "ኢትዮጵያ ለገባችበት ችግር እርሶ ስልጣን በመልቀቅ የመፍትሄ አካል ለመሆን አላሰቡም ወይ? ተብለው ከምክር ቤት አባል በቀረበላቸው ጥያቄ የተቆጡ የኦሮሚያ የክልል አመራሮች ነገ አቶ ክርስቲያን ታደለን የሚያወግዝ ሠልፍ ለማድረግ እስኪነጋ እየተጠበቀ ነው።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የአሰበ ተፈሪ ከተማ እና የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ነዋሪዎች ለአማራ ድምፅ እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ለመልቀቅ አላሰቡም ወይ ? ተብለው መጠየቃቸውን ምክንያት በማድረግ የዞን እና የወረዳ አመራሮች ብሔርን መሠረት ያደረገ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ማምሸታቸውን ነው የገለፁልን።

ነዋሪዎቹ እንደተናገሩት የነገው ሰልፍ የምክር ቤት አባል የሆኑትን አቶ ክርስቲያን ታደለን እና የወጡበትን ብሔር ከማውገዝ ባለፈ ወደ ፀብ እና ሁከት ሊያመራ ይችላል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው ለአማራ ድሞፅ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን የመጡበትን አምስተኛ አመት አስመልክቶ የሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ ነው ሲል አስታውቋል።

( ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ )

╔═╦╗╔╦╗╔═╦═╦╦╦╦╗╔═╗
║╚╣║║║╚╣╚╣╔╣╔╣║╚╣═╣
╠╗║╚╝║║╠╗║╚╣║║║║║═╣
╚═╩══╩═╩═╩═╩╝╚╩═╩═╝
----------------------------------------------------------------
Follow all of these
Facebook: https://www.facebook.com/atnawuzworld
Youtube: https://www.youtube/atnawuzworld
Instagram: https://www.instagram.com/atnawuzworld
Tiktok: https://www.tiktok.com/
Telegram: https://t.me/atnawuzworld

-------------------------------------------------

🧩 Contact us📞
📧: [email protected]


#መድረክ #ድንቅልጆች

02/04/2023

የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ለተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ምስጋና አቀረበ‼️

የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ፈቃዱ ተሰማ÷ ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል በክልሉ ዛሬ የተካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም÷በኦሮሚያ ክልል ሀሉም አካባቢዎች በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በነቂስ ወጥተው ለለውጡ ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን አንስተዋል፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ለነጻነት፣ ለእኩልነትና ለፍትህ ለተካሄደው ትግል እንዲሁም ከለውጡ በኋላ ለተመዘገቡት ድሎች እና ስኬቶች እውቅና ሰጥተዋል ነው ያሉት፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች በሰላማዊ መንገድ የመጣውን ለውጥ በሴራና በሃይል ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞች ሃይሎችን እንደሚታገሉ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋልም ብለዋል፡፡


╔═╦╗╔╦╗╔═╦═╦╦╦╦╗╔═╗
║╚╣║║║╚╣╚╣╔╣╔╣║╚╣═╣
╠╗║╚╝║║╠╗║╚╣║║║║║═╣
╚═╩══╩═╩═╩═╩╝╚╩═╩═╝
----------------------------------------------------------------
Follow all of these
Facebook: https://www.facebook.com/atnawuzworld
Youtube: https://www.youtube/atnawuzworld
Instagram: https://www.instagram.com/atnawuzworld
Tiktok: https://www.tiktok.com/
Telegram: https://t.me/atnawuzworld

-------------------------------------------------

🧩 Contact us📞
📧: [email protected]


#መድረክ #ድንቅልጆች

TV channel

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም !እኚ እናት ወ/ሮ ዘንባቤ ጫላ ይባላሉ ። ለበርካታ አመታት በመድኃኒት ፋብሪካ በመስራት ባጠራቀሙት ገንዘብ ከ11 አመት በፊት ቤት ሰርተው ትዳር መስርተው ይኖ...
02/04/2023

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም !

እኚ እናት ወ/ሮ ዘንባቤ ጫላ ይባላሉ ። ለበርካታ አመታት በመድኃኒት ፋብሪካ በመስራት ባጠራቀሙት ገንዘብ ከ11 አመት በፊት ቤት ሰርተው ትዳር መስርተው ይኖሩ ነበር ። ሆኖም ትዳራቸው ሰምሮ ከአጋራቸው ጋር አብሮ ለመኖር ልጅ መውለድ ባለመቻላቸው ምክንያት እና ባል ከሌላ ለሚወለዱ ልጆቹ ከጀርባ በኩል ያለው ቤት ይሰጣቸው በሚል አለመግባባት ወደ ፍቺ ያመራሉ ። ባል ያለፋበትን ፣ ያልደከመበትን እሳቸው ዘመናቸውን ሙሉ የደከሙበትን ከትዳር በፊት የሰሩትን ንብረት ይገባኛል ፤ ሲል ፍርድ ቤት ከሶ የድርሻውን በመውሰድ ቀሪውን ደግሞ በጉርብትና አልኖርም በማለት ወይዘሮ ዘንባቤ ሸጠው ሁለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ ቤት በመግዛት አንዱን በማከራየት በክራዩ ገቢ ኑሮቸውን ይደጉሙ ጀመር ።

ከለታት አንድ ቀን በሀይማኖት ከሚመስሎቸው ጓደኛቸው አንድ ሀሳብ መጣ ። ይህው "ቤት ውስጥ ብቻዎትን ከሚኖሩ ከጎን ያለችውን ሶስት በአራት የሆነችውን ክፍል ለምን አከራይተው አንድም ገቢ ያገኛሉ ሁለትም የሚያናግሮት ፣ የሚጫውቶት ሰው ያገኛሉ ። " ትልና ሀሳብ ታቀርባለች ። እውነት ነው ። ብለው በጓደኛቸው ሀሳብ የተስማሙት ወ/ሮ ዘንባቤ ተከራይ አግኝቼልሻለሁ በማለት ሀሳቡን ያቀረቡ ጓደኛቸው በቸርች የምታውቃትን ሴት እንድትከራይ ያደርጋሉ ።

ወ/ሮ ዘንባቤ ቸርች በመሄድ የአምልኮ ስርዓት ይፈፅሙ የነበረ ቢሆንም ተከራይታ የገባችው ሴት እኔ አገልጋይ ነኝ በማለት ቤት ውስጥ ታገለግላቸው ጀመረ ። ትፀልይላቸዋለች ፣ መልዕክት ታመጣላቸዋለች ፣ ዘይት ትቀባቸዋለች ፣ ትንቢት ትተነብይላቸው ጀመረ ። ወይዘሮ ዘንባቤ ሁሉን እውነት ብለው በመቀበል ቸርች መሄድን እርግፍ አድርገው በመተው በቤታቸው የሚሆነውን ነገር ለቤተሰቦቻቸው ሳያማክሩ ይቀጥላሉ ።

ወይዘሮ ዘንባቤ ከለታት በአንዱ ቀን እንዲህ ሲሉ ለምትፀልይላቸው ተከራያቸው ውስጣቸው ያለውን ሚስጥር ያካፍላሉ ። " ስሞት እሩቡን ለቤተክርስቲያን እንዲሰጥልኝ እፈልጋለሁ ። " ሲሉ ለቤተሰቦቻቸው ያልተናገሩትን የራስ ሚስጥርን በየዋህነት ላመኖት አገልጋይ ተከራይ ሀሳባቸውን ያካፍላሉ ።

አገልጋይ ነኝ ባዬ ይቺን ፍንጭ ትይዝና ዘወትር ምሽት ላይ "አንቺ ትሞቻለሽ ፣ የሞት ድምፅ እየሰማሁ ነው ። " በማለት ከጌታ የተሰጠ መልዕክ ነው ። በሚል በወይዘሮ ዘንባቤ ላይ የፍራቻ ፣ የድንጋጤ ስሜትን መዝራት ትጀምራለች ። እናም እንዲህ ትላቸዋለች ያው "እኔ የእግዚያብሔር አገልጋይ ነኝ ስለዚህ ስትሞቺ ለኔ ብትሰጪኝ ለቤተክርስቲያን እንደሰጠሽ ይቆጠራል ። " ትላቸዋለች ይሄኔ ሁሉን እውነት ነው ብለው የተቀበሉት እኚ ወይዘሮ አንዱን ቤት ሸጠው ለተከራያቸው ቅሊንጦ አካባቢ በለ አንድ ኮንዶሚኒየም በስሞ ይገዙላታል ። በተረፈው አምስት መቶ ሺ ብር ደግሞ ለእሳቸው ኮዬ ፈጬ እስቱዲዬ ይገዙና ያከራያሉ ።

በዚህ ያላበቃው የአገልጋያቸው ጉድ" ክራይ ለመቀበል ኮዬ ድረስ ከሚሄዱ ለኔ ሙሉ ውክልና ይስጡኝና እኔ ቤቱን አስተዳድረዋለሁ ።" ብላ ሙሉ ውክልና ትወስድና ቆዬ ፈጬ የገዙትን ቤት በ150 ሺ ብር እንደተሸጠ አድርጋ አካውንታቸው ላይ እንዲገባ ታደርጋለች ።

መልሳም መረጃና ማስረጃ እንዳይኖርባት ይሄንኑ 150 ሺ ብር በካሽ ሃምሳ ሃምሳ ሺ ብር እያወጡ በእጆ እንዲሰጦት ታደርግና ወደ ራሷ አካውንት ታስገባለች ።

የሰውን ለብ እና እንባ እንደ ተራ ነገር የቆጠረችው አገልጋይ ተብዬ ወይዘሮ ዘንባቤን ባዶዎቸውን ማስቀረቷ ሳያንስ አሁን ያሉበትን ቤት በስጦታ እንዲሰጦት በማድረግ ቤቱን በስሞ አስደርጋለች ።

በአሁን ሰዓት አገልጋይ ተብዬ ሶስት በአራት በሆነችው ቤት ውስጥ እየኖረች

የነገው  ውሎ
10/10/2022

የነገው ውሎ

እንግሊዛዊው ወጣት በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅረኛ ለማግኘት ሲል በቢልቦርድ ማስታወቂያ ማስለጠፉን ተከትሎ ስልኩ እረፍት እንደነሳው ተናገረ የ23 አመቱ እንግሊዛዊው ወጣት በህይወቱ የፍቅር ...
07/10/2022

እንግሊዛዊው ወጣት በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅረኛ ለማግኘት ሲል በቢልቦርድ ማስታወቂያ ማስለጠፉን ተከትሎ ስልኩ እረፍት እንደነሳው ተናገረ

የ23 አመቱ እንግሊዛዊው ወጣት በህይወቱ የፍቅር ጓደኝነት ለመጀመር በማሰብ በትውልድ ከተማው አቅራቢያ በሚገኝ ትልቅ ሀይዌይ ዳር ማስታወቂያ አስለጥፏል።

ኤድ ቻፕማን በጉርምስና ዕድሜው እና በ20ዎቹ መጀመሪያ ላይ በማህበራዊ ግንኙነት እና የፍቅር ጓደኛ ለማገናኘት በሚያስችሉ የሞባይል መተግበሪያዎችን በመጠቀም የሴት ጓደኛ ለማግኘት ቢያደርግ ሊሳካለት አልቻለም። በዩናይትድ ኪንግደም በሊድስ ከተማ የ23 ዓመቱ ቻፕማን ተስፋ ባለመቁረጥ በአውራ ጎዳና ላይ ትልቅ የማስታወቂያ ባነር በመከራየት ማስታወቂያ ያስለጥፋል።

ከማስታወቂያው በኃላ ከሴት ጓደኛ እንሁን በሚሉ መልእክት ብዛት መጨናነቁን በመግለፅ በህይወቴ በሙሉ ካገኘሁት ሁሉ የበለጠ ስኬት በማለት መደሰቱን ተናግሯል።

ላለፉት 23 ዓመታት ብቸኛ ቆይቻለሁ እናም አሁን ነገሮች የተቀየሩ ይመስላል ሲል ተናግሯል። የመጀመሪያው መልእክት የደረሰኝ የማስታወቂያ ሰሌዳው በተለጠፈበት እለት ሲሆን ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እድሜያቸው ከ18 እስከ 48 ዓመት የሆናቸው ሴቶች መልዕክት ልከውልኛል ሲል ቻፕማን ለካተርስ ኒውስ ተናግሯል።ይህ አዎንታዊ ነገር እንዳለ የሚያሳይ ምልክት ነው ሲል አክሏል።

በስምኦን ደረጄ

07/10/2022

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓጓዝ በነበረ የህዝብ ተሽከርካሪ ላይ የትራፊክ አደጋ ደረሰ!

የትራፊክ አደጋው የደረሰው መስከረም 26/2015 ዓ.ም በምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ወረዳ በአምቦ መስክ ቀበሌ እንደሆነ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

መነሻውን ከባህርዳር ወደ ማርቆስ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ተሸከርካሪ እና ከምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ተሸከርካሪ በመጋጨቱ ሲሆን በተሳፋሪዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

( ምንጭ መራዊ ኮሙኒኬሽን )

የቪዲዮ መረጃ ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን Subscribe ያድርጉ!

ለትግራይ ሕዝብ ያገባኛል የሚል እድሉ መጥቶለታል!        Atnawuz world አትናውዝ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለትግራይ ሕዝብ የሚላከውን እርዳታ አሸባሪው ትህነግ ተጠቀመበት ብለው ሲያዝ...
03/09/2022

ለትግራይ ሕዝብ ያገባኛል የሚል እድሉ መጥቶለታል!
Atnawuz world አትናውዝ

በርካታ ኢትዮጵያውያን ለትግራይ ሕዝብ የሚላከውን እርዳታ አሸባሪው ትህነግ ተጠቀመበት ብለው ሲያዝኑ ቆይተዋል። በዚህ ምክንያት ህፃናትና እናቶች ላይ የደረሰው የማያሳዝነው የለም። አሁን ግን ጥሩ አጋጣሚ እየተፈጠረ ይመስላል። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ለትግራይ ሕዝብ እርዳታ የሚደርስበት መንገድ ቀላል ይሆናል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሚቆጣጠራቸው አካባቢዎች እርዳታ ለማድረስ ቀላል ይሆናል። ስለሆነም ለትግራይ ህዝብ ያገባናል የሚሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ያላቸውን ማድረስ የሚችሉበት እድል ይኖራል ማለት ነው።

በተለይ ትህነግ በከፈተው ጦርነት ሌላውን ሰላም ፍጠር እያሉ የሚጨቃጨቁ፣ ትህነግ መንገድ ሲዘጋ ሌላው መንገድ ዘግቶ እርዳታ አላስገባም የሚል የሚመስላቸው በተግባር መገኘት የሚችሉ ከሆነ የሚታዩት አሁን ነው። ትህነግ እርዳታ እየዘረፈ፣ ሕዝቤ ተራበ ሲል ተሳስተውም ይሁን ሆን ብለው አብረው ሲጮሁ የነበሩት የሚፈተኑበት ወቅት አሁን ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ትህነግን ለመደገፍ ሲባል እርዳታን ፖለቲካ ያደረጉት የውጭ ኃይሎችንም ማሳፈር ያስፈልጋል። ኢትዮጵያውያንም ለራሳቸው ወገን እርዳታን ለፖለቲካ ሳይጠቀሙበት በስርዓት እንደሚያደርሱ ማሳየት ያስፈልጋል።

Via፦ #በጌታቸውሽፈራው

#አትናውዝ # #አሚማ

03/09/2022

የትህነግ የሽብር ቡድን በተከዜ ማይልሃም በኩል የጀመረው የወረራ ጦርነት በወገን ጦር ከፍ ያለ ዋጋ እያስከፈለው መሆኑ ታውቋል። በማይጋባው ግንባር በሽሬ መስመር ተከዜን ተሻግሮ እስከ ማይጣሳ እና ማይሀሽምን በማለፍ ወደ ደደቢት እየተጠጉ እንደሆነም ታውቋል።

ወራሪ ቡድኑ በተለይ ነሃሴ 26ለ27/2014 ሌሊቱን በቡድን መሳሪያ ሲዋጋ ቢያድርም ለመቀልበስ ያደረገው የጥቃት ሙከራ አልተሳካለትም ሲል አክሏል።

አሸባሪው ትሕነግ በዋግኽምራ በኩልም በጥሩ ሁኔታ እየተመታ ነው ተብሏል።

#አትናውዝ #አሚማ

ከትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) የተሰጠ መግመጫህወሐት ከማዕከላዊው መንግስት ስልጣኑ በህዝብ ዓመፅ ተወግዶ ወደ ትግራይ ከሸሸ በኃላ እንደገና በኃይል ወደ ስልጣን ለመመለስ ያልቆፈረው ጉ...
02/09/2022

ከትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) የተሰጠ መግመጫ

ህወሐት ከማዕከላዊው መንግስት ስልጣኑ በህዝብ ዓመፅ ተወግዶ ወደ ትግራይ ከሸሸ በኃላ እንደገና በኃይል ወደ ስልጣን ለመመለስ ያልቆፈረው ጉድጓድ ያልገለበጠው ድንጋይ የለም፡፡ የሃሰት ትርክቶችን በመፍጠር የትግራይን ህዝብ ከአጎራባች ክልል ወንድምና እህት ህዝቦችና ከመንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ ለማስገባት የጦርነት ነጋሪት ሲጎስም ኖረዋል፡፡

ልዩ ሃይልን በከፍተኛ ቁጥር በማሰልጠንና የእብሪት ወታደራዊ ትርክቶችን በማሳየት ጦርነትን አበክሮ ቀስቅሰዋል፡፡ ብሎም በመንግስት ይቀርብለት የነበረውን ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ በመግፋትና የአገራችንን መከላከያ ሃይል ከጀርባ በመውጋት ፀረ ሰላምነቱን ብቻ ሳይሆን የአገር ከሃዲነቱንም ጭምር ለመላው ዓለም ግልፅ በሆነ ሁኔታ አሳይተዋል፡፡

ትዴፓ ህወሐት ይሰብከው የነበረን ጦርነት እንዲያቆም፣ ጦርነት ሊያስከትለው የሚችለውን ቀውስና እልቂት እየጠቆመ ሲያስጠነቅቀው ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ይህ እብሪተኛ ቡድን በተለይም የሰሜኑን እዛችን ወግቶ ከፍተኛ መጠን ያለው ትጥቅ ከታጠቀ በኃላ በከፍተኛ ትዕቢት ተሞልቶ ከመላው የአገር መከላከያ ሃይላችን፣ ከአማራና መላው የአገራችን ልዩ ሃይሎች ጋር ውጊያውን ቀጥሎበታል፡፡

ሆኖም ይህ ራሱ የለኮሰው እሳት ራሱን በላውና ከ17 ቀናት ባልበለጠ ጊዜ እንዲንኮታኮት ሆነ፡፡ ነገር ግን ስናስጠነቅቅ እንደነበርነው የመጀመሪያው የጦርነቱ ሰለባ የትግራይ ህዝብ ሆነ፡፡ ህወሐት የትግራይን ህዝብ የበቀል ድግስ ሲያዘጋጅለት ማይካድራ ላይ ዘር የለየ ጭፍጨፋ ፈፀመ፡፡ቀጥሎም በተለመደው የጦርነት ባህርይ ለሆነው የሰው እልቂት፣የመሰረተ ልማት ውድመት መፈናቀል፣የሴቶች መደፈርና ለሃብት ዝርፍያ ዳረገው፡፡

መንግስት ለስድስት ወራት ያክል ትግራይን ለማሰተዳደርና ለማረጋጋት ቢሞክርም ጦርነቱ ግን ሊቆም ባለመቻሉ ለፅሞና ጊዜ ብሎ ሰኔ 21,2013 ለቆ በመውጣት ተከታታይ የሰላም ጥሪዎችን ለህወሐት አቀረበ፡፡ በዚህ ወቅት ትዴፓ ዳግም የተገኘው የሰላም ጥሪና ከመንግስት በኩል የቀረበውን ዕድል ህወሐት ይቀበል ዘንድ አበክሮ አሳስበዋል፡፡
ጦርነቱን ወደ ክልሎች ለማሰፋት ያደርገው የነበረን ሙከራ ሁሉ ከጅምሩ አውግዘዋል፡፡ህወሐት ከሰላም ጋር ያለው ግንኙነት ሆድና ጀርባ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በተለይም በጦርነቱ የበላይነት አግኝቻለሁ በሚል ስሜታዊነት ለሰላም ጥሪዎች ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ለ2ኛ ጊዜ አዲስ አበባን የመቆጣጠር ክተት አወጀ፡፡ ስልጣኑን ማስመለስ ካልቻለ ደግሞ አገራችንን ለመበታተን አልሞ የ13ና የ14 ዓመት ዕድሜ ህፃናትን ሳይቀር እያፈሰ አዘመተ፡፡

ይህ ከኃላው እየተገደለ የሚገፋው ታጣቂም ከፍተኛ የእውር ድንብር ጥፋቶችን እያደረሰ ደብረ ሲና ቢደርስም በደረሰበት አፀፋዊ እርምጃ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን ለሞት አስረክቦ ተመልሶ በትግራይ የክልል አጥር እንዲኮራመት ተደረገ፡፡በየሜዳው ወድቆ የአሞራ ሲሳይ ከሆነው ወጣትና ህፃን በላይ አካላ ጎዶሎ ሆኖ የገባው ቁጥር ቤቱ ይቁጠረው፡፡ ቁስሉ ሳይታከም በመቅረቱ ካለቀው ውጪ ድኖም የተረፈውን ሸሽቶ ማምለጥ የቻለውም ለከፍተኛ የሞራል ውድቀት ተዳርጎ አንገቱ የተሰበረ ሞራለ ቢስ ወጣት ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም እጅ ግን በደቀቀው የህወሐት አቅም ፊትም አልታጠፈም፡፡ከህወሐት አንፃር ግን አሁንም ከ500,000 በላይ ወጣት ጨርሶ፤ የቀረው ተዳክሞ ተስዶ ባለበት ሁኔታ፤ ህዝቡ በረሃብ፣ በመድሃኒት እጦት እያለቀ እያለ የሰላም ጥሪዎችን ገፍቶ በፀላኤ ሰላምነቱ በመቀጠል ለ3ኛ ዙር ጦርነት በስፋት ሲዘጋጅ መቆየቱን አይተናል፡፡

ህወሐት የትግራይን ህዘብ አሁንም በከፍተኛ የማሰገደድ ጫና እንዲዘምት፣ እንዲዋጋ ለማድረግ በሚተጋበት ጊዜ መንግስት ግን ለህዝቡ የተገኘውን ያህል ሰላም በመመኘት ያለ ቅድመ ሁኔታ ለመደራደር እንደሚፈልግ ለመላው ዓለም ግልፅ በሆነበት መልኩ ገልፀዋል፡፡ ብዙ ርቀትም ተጉዞ ከድርሻው በላይ ቀርበዋል፡፡ ህወሐት ግን የሰላም ጥሪዎችን ከደካማነት ቁጥር በመቁጠር የሰላም ጥሪውን በጉልበታችን ያመጣነው ነው ብሎ ሲያጣጥለው ተስተውለዋል። ተቀባይነት የማይኖራቸው ቅድመ ሁኔታዎችን በመደርደርም ሰላም እንዳይሳካ ከማድረጉ በላይ ጦርነትን በመለኮስም የሰላምን በር ፈፅሞ እንዲዘጋ ለማድረግ ሞክረዋል፡፡

ህወሐት ፀረ ሰላም መሆኑንና ለህዝብም ደንታ እንደሌለው፣ዘራፊና አሸባሪ ስለመሆኑም መላው ዓለም ተገንዝቦታል፡፡ስለዚህ ከህዝብና ከመላው የዓለም ማህበረሰብ እየተነጠለ መምጣቱ በግልፅ የሚታይ እውነት ነው፡፡
ጦርነቱን በጀመረ ዋዜማ በረሃብ ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ ያሉትን ረሃብተኞች ላይ ለመድረስ ከዓለም ማህበረሰብ የተሰጠውን ከ570,000 ሊትር በላይ የሆነ ነዳጅ ከሚያጣጥሩት ረሃብተኞች አፍ መንጠቁ ከፍተኛ ውግዘት ደርሶበታል።
ከዚህ በመነሳት ድርጅታችን የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ( #ትዴፓ)

• ህወሐት በህዝብና አገር ላይ የጀመረውን የሶስተኛ ጊዜ ጦርነት እጅግ ያወግዛል፣

• በዚህ ጦርነት ለሚደርሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂው ህወሐት እንደሆነ ያምናል፣

• መንግስት አገርንና የህዝብን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚወስደውን እረምጃ ሁሉ ይደግፋል፣

• የአገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ ዳግም ያረጋግጣል፣

• መላው ኢትዮጵያዊ ህዝብ በዚህ አገርን የማስከበርና የህዝብን ደህንነት የማረጋገጥ እርምጃ ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

በተለይም የትግራይ ህዝብ ህወሐት ጦርነትን እንዲያቆምና የሰላም ጥሪውን ተቀብሎ ከመንግስት ጋር እንዲደራደር ለማድረግ፣ የልጆቹን ደም ይገታ ዘንድ በህወሐት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ እምቢታ እንዲቀሰቅስ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

እንዲታጠቅ የተገደደውና ለግለሰቦች የስልጣንና የጥቅም ፍላጎት በማለቅ ላይ ያለው ወጣት ለወላጆቹ ሰላም፣ ለራሱም ነፃነት ጥቅምና እድገት በማሰብ በተመቸው መንገድ አፈሙዙን ወደ ጨቋኞቹ የህወሐት አመራሮች እንዲያዞር ወይም በሰላም እጁን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሃይል እንዲሰጥ ጥሪያችንን እናቀርበለን እንመክራለን፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ መስዋእትነት ፀንታ ትኖራለች!!
ነሐሴ 27/2014 ዓ.ም

ቤተክርስቲያን ውስጥ ምዕመናንን የገረፈው ነብይ በኡጋንዳ ፖሊስ ታሰረእራሱን ነብይ ነኝ ብሎ የሰየመው ኪንቱ ዴኒስ የተባለው ኡጋንዳዊ የ‘ሆይማ ኢምፓወርመንት’ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አባላ...
02/09/2022

ቤተክርስቲያን ውስጥ ምዕመናንን የገረፈው ነብይ በኡጋንዳ ፖሊስ ታሰረ

እራሱን ነብይ ነኝ ብሎ የሰየመው ኪንቱ ዴኒስ የተባለው ኡጋንዳዊ የ‘ሆይማ ኢምፓወርመንት’ ዓለም አቀፍ ቤተክርስቲያን አባላትን በበትር ሲገርፍ የሚያሳይ ቪዲዮ በኢንተርኔት ላይ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ በቀረበው አቤቱታ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋለው ነብይ ኪንቱ በምርመራ ወቅት እንደተናገረው፣ በተንቀሳቀቃሽ ምስሉ ላይ የሚታየው በበትር መገረፍ ትዕይንት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትን ምሳሌን መሠረት ያደረገ ነው ሲል ተከራክሯል።

ክሱን ተከትሎ ፖሊስ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ባደረገው ፍተሻ በቪዲዮው ላይ በምዕመናኑ ላይ በተፈጸመው ግርፋት ጥቅም ላይ የዋሉ ሳይሆኑ አይቀሩም የተባሉ ሦስት በትሮች መገኘታቸው ተነግሯል።

በተጨማሪም "ነብይ" ኪንቱ ዴኒስ በ18 ሰዎች የህገወጥ ዝውውር የተከሰሰ ሲሆን በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራው አስከሚጠናቀቅ ድረስ አስከ መጪው ሐሙስ ጳጉሜ 1 ድረስ በእስር ላይ እንደሚቆይ ተገልጿል።

በኡጋንዳ ውስጥ በርካታ የኢቫንጀሊካል አብያተክርስቲያናት በመላው አገሪቱ የሚገኙ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በሕግ ያልተመዘገቡ እና ብዙዎቹ ደግሞ እራሳቸውን የአግዚአብሔር ሰው አድርገው በሰየሙ ግለሰቦች የሚመሩ እንደሆነ ይነገራል። (BBC/ UPF)

ዳግም ጦርነት እንዲቆም አሜሪካ ልኡክን ወደ ኢትዮጵያ የላከች ሲሆን ጎረቤት ኤርትራ በትግራይ ሰሜናዊ ክልል ዳግም ወደ ግጭት መግባቷን አውግዛለች።የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመ...
02/09/2022

ዳግም ጦርነት እንዲቆም አሜሪካ ልኡክን ወደ ኢትዮጵያ የላከች ሲሆን ጎረቤት ኤርትራ በትግራይ ሰሜናዊ ክልል ዳግም ወደ ግጭት መግባቷን አውግዛለች።

የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በዚህ ቅዳሜና እሁድ ወደ ኢትዮጵያ ያቀናሉ እና "ሁሉም አካላት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን እንዲያቆሙ እና የሰላም ድርድር እንዲያደርጉ ያስተላልፋሉ" ሲሉ የዋይት ሀውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ዣን ፒየር ተናግረዋል ።

“ኤርትራ ዳግም ወደ ግጭት መግባቷን፣ ከትግራይ ውጭ የቀጠለውን የሕወሃት ጥቃት እና የኢትዮጵያ መንግስት የአየር ድብደባን እናወግዛለን” ስትል ለጋዜጠኞች ተናግራለች።

ባለፈው ሳምንት በሰሜናዊው ክልል ከአምስት ወራት ቆይታ በኋላ ዳግም የቀጠለው ጦርነት ለሁለት ዓመታት የሚጠጋውን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እና ትግራይ ለረሃብ የተጋለጠችበትን ሰብአዊ ቀውስ ለማስቆም የነበረው ተስፋ ጨልሟል።

"ለግጭቱ ምንም አይነት ወታደራዊ መፍትሄ የለም" ሲል ዣን ፒየር ተናግሯል።

"ሁሉም አካላት ራሳቸውን መቆጣጠር አለባቸው እና በሁሉም ተዋናዮች በተለይም ሰብአዊ እርዳታ እና ለተቸገሩ ወገኖች ሁሉ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንደገና እንዲጀመር እንጠይቃለን."

የኢትዮጵያ መንግስት እና አማፂው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሀት) የመጨረሻውን ዙር ጦርነት በመጀመራቸው ጥፋተኛ ሆነዋል።

በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ የበላይነት የነበረው ህወሓት፣ ታሪካዊቷ ተቀናቃኝ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር ባደረገው ከፍተኛ ጥቃት እንደገና ጦር ልኮ ነበር ሲል ሐሙስ እለት ከሰዋል።

ሸዋሮቢት !የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።አቶ ውብሽተ ለእረፍት ትላንት ማታ ከምሽቱ 3 ስዓት ገደማ አካባቢ ወደ ...
02/09/2022

ሸዋሮቢት !

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳውቋል።

አቶ ውብሽተ ለእረፍት ትላንት ማታ ከምሽቱ 3 ስዓት ገደማ አካባቢ ወደ ቤታቸው ከመኪና ላይ ወርደው ሊገቡ ሲሉ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በተተኮሰ ጥይት ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።

አቶ ውብሸት አያሌው ባለትዳር እና የአንድ ሴትና አንድ ወንድ አባት ነበሩ።

በሌላ በኩል ፤ በሸዋ ሮቢት ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብን ጨምሮ የተለያዩ ውሳኔዎች ከነሐሴ 26 ጀምሮ በከተማው የፀጥታ ምክር ቤት ተወስኗል።

ከክልከላዎች መካከልም ፦

- ማንኛውም ባጃጅ እና ሞተር ሳይክል ከምሽቱ 2 ሰአት በኃለ መንቀሳቀስ አይችልም።

- የሰው እንቅስቃሴ ገደብ ከምሽቱ አምስት ስዓት በኃላ ተገድቧል።

- መጠጥ ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች እንዲሁም ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተቋማት ከምሽት 4 ሰዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

- ከየትኛውም አካባቢ ተፈናቅለው በከተማዋ ተጠልለው የሚገኙ ወገኞች ከምሽቱ12 በኃላ መንቀሳቀስ አይችሉም የሚሉት ይገኙበታል።

ሰበር ዜና !"…ሸዋሮቤት ተኩስ አለ። ምንነቱ ባልታወቀው ተኩስ የተኩስም ልውውጥ የከተማው ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው መመታታቸውም እየተሰማ ነው። (ህይወታቸው አልፏል የሚሉም አሉ) ምንድነው...
01/09/2022

ሰበር ዜና !

"…ሸዋሮቤት ተኩስ አለ። ምንነቱ ባልታወቀው ተኩስ የተኩስም ልውውጥ የከተማው ከንቲባ አቶ ውብሸት አያሌው መመታታቸውም እየተሰማ ነው። (ህይወታቸው አልፏል የሚሉም አሉ) ምንድነው በሸዋሮቢት የተፈጠረው?

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ የአማራ ተወላጆችን መጨፍጨፉን ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጂዎች ተናገሩ። አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ የአማራ ተወላጆች ላይ በፈ...
04/07/2022

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ የአማራ ተወላጆችን መጨፍጨፉን ከጥቃቱ የተረፉ ተጎጂዎች ተናገሩ።

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በኦሮሚያ ክልል በቄለም ወለጋ የአማራ ተወላጆች ላይ በፈጸመው ጭፍጨፋ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ የበርካታ ንጹኀን ህይወት ማለፉን ከጥቃቱ የተረፋ ተጎጅዎች ተናግረዋል።
አሁን ላይ በአካባቢው የሀገር መከላከያ ሠራዊት መድረሱን ገልጸዋል። ጥቃት አድራሾችም ለጊዜው መሸሻቸውን የተናገሩት ተጎጅዎቹ በንጹኀን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ መንግሥት እንዲያስቆም ጠይቀዎል።

Atnawuz world አትናውዝ በንጹኀን ወገኖች ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ያለሁን ሁኔታ ተከታትሎ መረጃ ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Atnawuz world አትናውዝ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category



You may also like