HOLY FIRE TV

HOLY FIRE TV Jesus is only the way of heaven
(1)

 #ትልልቅ ነገሮችን ማየት ካቃተህ፣ ካለህበት አከባቢ ውጣ!! #ከምትኖርበት ማህበረሰብ የተሻለ አስተሳሰብ እስከሌለህ ድርስ  #ተመሳስለህ ትኖራለህ እንጂ አትለወጥም!! #የከነዓንን ማርና ወተ...
05/04/2024

#ትልልቅ ነገሮችን ማየት ካቃተህ፣ ካለህበት አከባቢ ውጣ!!

#ከምትኖርበት ማህበረሰብ የተሻለ አስተሳሰብ እስከሌለህ ድርስ #ተመሳስለህ ትኖራለህ እንጂ አትለወጥም!!

#የከነዓንን ማርና ወተት እስካላየህ ድረስ #የግብጽ ሽንኩርት ይመችሃል!!

#አሁን ያለህበት ሸለቆ እንደሆነ የምትረደው ተራራ ለይ ከወጣህ ብቻ ነው!!

“ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ፤ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።”
— ኤርምያስ 33፥3

 #የምህረቱ ውጤት ነኝ!! #ከእኔ የምለው አንዳች የለኝም!!
31/03/2024

#የምህረቱ ውጤት ነኝ!!
#ከእኔ የምለው አንዳች የለኝም!!

 #ይህ የምታየው አሸዋ አይደለም ነገር ግን እንደ ምድር  አሸዋ የበዛ ሕዝብ ነው!! ገና ኢትየጽያን እንወርሳለን“ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቈጥር ዘንድ የሚ...
17/03/2024

#ይህ የምታየው አሸዋ አይደለም ነገር ግን እንደ ምድር አሸዋ የበዛ ሕዝብ ነው!!

ገና ኢትየጽያን እንወርሳለን

“ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቈጥር ዘንድ የሚችል ሰው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቈጠራል።”
— ዘፍጥረት 13፥16

አቤቱ ሕዝብህን አበዛህ!!
17/03/2024

አቤቱ ሕዝብህን አበዛህ!!

 ...🙏🙏🙏ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ከውብ መድረክ ጋር ተገጥሟል። ነገ አዲስ አበባ በፀሎት እና በዝማሬ ትሞላለች...
16/03/2024

...🙏🙏🙏
ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነው ዘመናዊ ሳውንድ ሲስተም ከውብ መድረክ ጋር ተገጥሟል።
ነገ አዲስ አበባ በፀሎት እና በዝማሬ ትሞላለች...

 ....የከተማዋ ውብ ገፅታ መገለጫዎች ከሆኑ ስፍራዎች ዋናው ነው መስቀል አደባባይ። እዚህ የከተማዋ እንብርት፣ የአዲስ አበባ ልብ የሆነው ስፍራ ላይ እግዚአብሔርን ልናመልክ ፣ ወንጌል ልንሰ...
06/03/2024

....
የከተማዋ ውብ ገፅታ መገለጫዎች ከሆኑ ስፍራዎች ዋናው ነው መስቀል አደባባይ። እዚህ የከተማዋ እንብርት፣ የአዲስ አበባ ልብ የሆነው ስፍራ ላይ እግዚአብሔርን ልናመልክ ፣ ወንጌል ልንሰብክ ጊዜው ደርሷል።
መጋቢት 8 ከ7:00 ሰዓት ጀምሮ
በመስቀል አደባባይ...

  በመስቀል አደባባይ የወንጌላውያን አማኞች በአንድነት ኢየሱስን የሚያከብሩበት ትልቅ ድግስ ተዘጋጅቷል ። እነሆ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በፍቅር እና በደስታ በሕብረት ንጉሱ ኢየሱስን ይከበራል ...
19/02/2024

በመስቀል አደባባይ የወንጌላውያን አማኞች በአንድነት ኢየሱስን የሚያከብሩበት ትልቅ ድግስ ተዘጋጅቷል ። እነሆ ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ በፍቅር እና በደስታ በሕብረት ንጉሱ ኢየሱስን ይከበራል ።
- ስለ ሀገራችን #ኢትዮጵያም ሁሉም በአንድነት ይፀልያል

ሰላም ለኢትዮጵያ-ሰላም ለምድራችን 🇪🇹

 #ክብር ለታላቁ ንጉስ  #ለኢየሱስ ይሁን!! አሜንፊልጵስዩስ 2¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹⁰ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥¹¹ መላስም ሁሉ ለእግዚ...
16/02/2024

#ክብር ለታላቁ ንጉስ #ለኢየሱስ ይሁን!!

አሜን

ፊልጵስዩስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥
¹¹ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።

" ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተስፋ ( HOPE ) ይባላል .. "......ይህ ናይጄሪያዊ ህጻን ተስፋ ይባላል .. ለባእድ አምልኮ እራሳቸውን ያስገዙት ቤተሰቦቹ ለሞት አሳልፈው ሊሰጡት ከቤት አውጥተ...
06/02/2024

" ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተስፋ ( HOPE ) ይባላል .. "......

ይህ ናይጄሪያዊ ህጻን ተስፋ ይባላል .. ለባእድ አምልኮ እራሳቸውን ያስገዙት ቤተሰቦቹ ለሞት አሳልፈው ሊሰጡት ከቤት አውጥተው በጭካኔ በጎዳና ላይ ሲወረውሩት ምንም አልመሰላቸውም ። ምክንያቱም ለነሱ ከዚህ ነብስ ከማያውቅ ምስኪን ህጻን ይልቅ .. የህጻኑን " ሟርተኛ " እና " መአት አምጭ " .. መሆን የተነበየላቸው ጠንቋይ ያስፈራቸዋል ። አውጥተው ከጎዳና ጣሉት .። ( በነገራችን ላይ በባእድ አምልኮ ምክንያት ህጻናትን አውጥቶ መጣል በናይጄሪያ የተለመደ ነው )

በዚህ ምክንያት ፡ የጭካኔ ውሳኔ ተወስኖበት ከሞቀ ቤት ወጥቶ የተጣለው ይህ ህጻን ቤተሰቦቹ እንዳሰቡት ቶሎ የሚሞት አልሆነም ......
ከናቱ እቅፍ ተነጥቆ እራሱን ባገኘበት አንዲት መንደር ውስጥ በትናንሽ እግሮቹ ከወዲያ ወዲህ እየባዘነ ያገኘውን ለቃቅሞ እየበላ .. በወደቀበት ተኝቶ እየተነሳ ከሩቅ የታሰበለትን በጎ ነገር ያወቀ ይመስል ሞትን እንቢ ብሎ ....የሌሊቱ ውርጭ እና የቀኑ ሃሩር እየተፈራረቀበት በጽናት ቢቆይም 8 ኛው ወር ላይ ግን ለሞት እጁን የሰጠ መሰለ ..
እነዛ ወዳላሰበበት እየመሩት ሰወች የሚወረውሩለትን ወደ አፉ እንዲያደርግ የሚረዱት እግሮቹ ረሃብ አዛላቸው ..እናም አንድ ሌሊት ከተኛበት ሜዳ ላይ መነሳት እንዳቃተው ቀረ .........

እናም በዚህ ቅጽበት ..Anja Ringgren በምትባል በጎ አድራጊ ተመስለው የፈጣሪ እጆች ወደሱ ቀረቡ በሆላንዳዊትዋ በጎ አድራጎት ሰራተኛ ከወደቀበት ቦታ ተገኝቶ ሲነሳ የጎድን አጥንቶቹ የሚቆጠሩ ከህይወት ይልቅ ለሞት የቀረበ በፓራሳይት የተጎዳ በረሃብ የደቀቀ ... እጅግ አሳዛኝ ህጻን ነበር . ይህች መልካም ሴት ከወደቀበት አንስታ አዲስ ህይወት እና አዲስ ስም ሰጠችው .
እናም ወደሞት አፋፍ ላይ ላይ ወዳለው ምስኪን ህጻን ተጠግታም...
" ከዛሬ ጀምሮ .ስምህ ተስፋ ( HOPE ) ይባላል " .. ስትል አንሾካሾከችለት ።.........

አሁን ያ ሁሉ አልፏል .. HOPE በአንድ ወቅት ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ የሚያውቅ አይመስልም .... በአካሉ በርትቶ ደስ የሚል ቆንጅዬ ልጅ ሆኖ በበጎ አድራጊዋ Anja Ringgren በሚመራው የበጎ አድራጎት ድርጅት ውስጥ ከሚያድጉ ህጻናት ጋር እየኖረ ነው .....
ከተስፋ በተጨማሪ ፡ በተመሳሳይ ሌሎች ህጻናትን ከወደቁበት አንስታ ያሳደገችው በጎ አድራጊዋ Anja Ringgren ፡ እነዚህ በወላጆቻቸው ተገፍተው የተጣሉ ህጻናት ከየት እንደመጡ ፡ ወላጆቻቸው እነማን እንደሆኑ ሊያውቁ ይገባል ብላ ታምናለችና. .. በቅርቡ በህጻንነት እድሜው አውጥተው የጣሉትን የተስፋን ወላጆች አፈላልጋ ነበር ።

በአንድነት ተስማምተው ልጃቸውን የጣሉት ባልና ሚስት ትዳራቸው ፈርሶ በመለያየታቸው ምክንያት እናትየውን ማግኘት ባይቻልም ። ከአባቱ ጋር እንዲገናኝ እና አባቱ እሱ መሆኑን እንዲያውቅ አድርጋው ፡ ነበር ።
HOPE አባቱን ካገኘና አብሮ ፎቶ ከተነሳ በኋላ ፡ ከወደቀበት ወዳነሳችው አሳዳጊ እናቱ ቤት ተመልሷል ።
እዚህ ላይ ግን በጭካኔ አውጥቶ የጣለው አባት ያለሀፍረት ልጁን ለማግኘት መፈለጉ ለብዙዎች አስገርሟል ።.....
ቅን ልብ እና ፡ መልካም አስተሳሰብ ካለ ተአምር መስራት ይቻላል ።

Tesfaye ብዕርህ አይንጠፍ ✍️

ከእለታት አንድ ቀን ወንጌላዊ አለምነህ ጀምበሩ የገጠር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ ትውልድ ስፍራው ጎጀም ለመመለስ ከባለቤቱ ጋር ሆኖ በመንግስት ትራንስፓርት ይሳፈራል።ጉዞም ይጀምራሉ።..ብዙ ከተ...
03/02/2024

ከእለታት አንድ ቀን ወንጌላዊ አለምነህ ጀምበሩ የገጠር አገልግሎቱን ጨርሶ ወደ ትውልድ ስፍራው ጎጀም ለመመለስ ከባለቤቱ ጋር ሆኖ በመንግስት ትራንስፓርት ይሳፈራል።ጉዞም ይጀምራሉ።
..ብዙ ከተሞችን በነፋስ ሽውታ እያለፉ ተጓዙ።አለምነህም በልቡ መፀለይ ጀመረ።ምን እየፀለየ እንዳለ ባለቤቱ ባታውቅም እየፀለየ እንደነበረ ግን አስተውላለች።ያው ልማዱ ነው ብላ ትታዋለች።
ከረጅም ጉዞ በኋላ አንድ ከተማ ደረሱ።

በዚህ ጊዜ አለምነህ ድንገት ወደ ባለቤቱ ዞሮ፦
" እዚህ መውረድ አለብን" ይላታል።

እሷም ግራ ተጋብታ " ለምን? ገና አልደረስንም እኮ!" ትለዋለች።

" አይ መንፈስ ቅዱስ እዚህ ውረዱ፤ የምታድሩትም እዚህ ከተማ ነው ብሎኛል" አላት በእርግጠኝነት መንፈስ ሆኖ።

የሱ ነገር ሁሌ እንግዳ ቢሆንባትም እግዚአብሔር ካለው እንደማይመለስ ስለምታውቅ "አይ አለምነህ! የምንወርድበትንስ ምክንያቱን ነግሮሃል?" አለችው።ለማወቅ በመፈለግ እና ትንሽም ግራ በመጋባት።

"አልነገረኝም።" አላት።
ታዘው ወረዱ።ወደ አንድ ሆቴል ሄደው አልጋ ያዙ።ሻንጣቸውን አስቀምጠው ወክ ለማድረግ ወደ ከተማ ወጡ።

አለምነህ ግን በልቡ መፀለዩን ቀጠለ።
" ጌታ ሆይ!ለምንድን ነው እዚህ ከተማ ውረዱ ያልከን?እዚህ ከተማ ምን አለ? እያለ የእግዚአብሔርን ሃሳብ ለማወቅ ጠየቀ።ባለቤቱም የሚሆነው ባይገባትም በእርምጃ እና በፀሎት ዝም ብላ ተከተለችው።

ትንሽ እንደተጓዙ አንድ መናፈሻ ያለው ሆቴል ጋር ደረሱ።
መንፈስ ቅዱስም አለምነህን፦"ወደ ውስጥ ግባና የምነግርህን ታደርጋለህ" አለው።ድምፁን ተከትሎ ወደ ውስጥ ገባ።

መናፈሻው ውስጥ ትልቅ ሰርግ እየተደገሰ ነበር።ህዝቡም ግጥም ብሏል።አለምነህ አሻግሮ ወደ መድረኩ ተመለከተ።ሙሽራውን ያውቀው ነበር።የሚያውቀው ሰው ነው።

መንፈስ ቅዱስ መናገሩን ቀጠለ።
" ወደ ፊት ሂድና ሰርጉን አስቁም! " አለው።

አለምነህ በጣም ደነገጠ።ያልጠበቀው ድምፅ ነበር።
"ለምን" አለ።ክው እንዳለ።

መንፈስ ቅዱስም አለው፦" ከእኔ አይደለም።እሷ(ሙሽራይቱ) ፈፅሞ አትወደውም።ከጥቂት ጊዜ በኋላ ልትለየው አቅዳ የገባችበት ህይወቱንም አጥፍታ፣ንብረቱንም ዘርፋ ለመሄድ በጠላት የቴሴረ ሴራ ነው።የልጄን ቅንነት አይቼ ለማዳን ነው፤ አንተን የላኩህ" አለው።

በዚህ ጊዜ አለምነህ ወደ ጋብቻው መድረክ ቀረበ፤ምንም ሳይናገር በሙሽራይቱ ላይ ያለው መንፈስ እራሱን ገልጦ መጮህ ጀመረ።

አገኝህኝ፣ አዋረድከኝ፣ ነቃህብኝ! እረ ኡኡኡ እያለ ወደቀ።
ሰርጉም ቀረ!። ነፃነት ሆነ።
(ይህን ምስክርነት ከእራሱ ከወንጌላዊ አለምነህ ጀምበሩ አንደበት የሰማሁት ሲሆን።በጊዜ ርዝመት ቦታዎችን እና ከተሞችን ማስታወስ ባለመቻሌ ሳልጠቅሳቸው አልፌአቸዋለው።በተረፈ ምስክርነቱን ለፁሁፍ እንዲመች ከማድረግ ውጪ የጨመርኩት ምንም ነገር የለም።ተባረኩ።)

ናትናኤል ገብረወልድ

Good news for SOUTH AFRICAall are invited.
22/01/2024

Good news for SOUTH AFRICA

all are invited.

 #አቤት ይህች ዓለም  #ራቁቱን የሚሄደውን አጨብጭባ ትቀበልና ወንጌል የሚሰብከውን አሳዳ  #ታንገላታለች!!  #ዋጋሽን ልሰጥ ኢየሱስ ይመጣል!!“እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ...
19/01/2024

#አቤት ይህች ዓለም #ራቁቱን የሚሄደውን አጨብጭባ ትቀበልና ወንጌል የሚሰብከውን አሳዳ #ታንገላታለች!!

#ዋጋሽን ልሰጥ ኢየሱስ ይመጣል!!

“እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።”
— ራእይ 22፥12

ታላቁ መጽሐፍ 📖📖5 ቢሊዮን ጊዜ የታተመ ብቸኛው መጽሐፍ ተብለው በዓለም ድንቃድንቅ❤በአንድ ሺ ስድስት መቶ አመታት ውስጥ በአርባ  ስዎች ተፅፎ አልቋል ። ከነዚህም ሰዎች መካከል  ሀኪሞች ፣...
16/01/2024

ታላቁ መጽሐፍ 📖📖
5 ቢሊዮን ጊዜ የታተመ ብቸኛው መጽሐፍ ተብለው በዓለም ድንቃድንቅ❤

በአንድ ሺ ስድስት መቶ አመታት ውስጥ በአርባ ስዎች ተፅፎ አልቋል ። ከነዚህም ሰዎች መካከል ሀኪሞች ፣አሳ አጥማጆች፣ነገስታት ፣ የጦር መሪ ወዘት ይገኙበታል።

በሁሉም አህጉራት እና በተለያዩት አካባቢዎች በበረሀ ፣ በእስር ቤት ፣ ቤተመንግሥት ፣ በእረኝነት ሜዳ ፣ ደሴት ላይም ፅፎታል ዮሀንስ ። ፀሀፊዎችም የነበሩበት ስሜት የተለያየ ነበር ። በደስታ ፣በሀዘን ፣ በስ,ቃይ እና ሰቆ'ቃ ፣ በፍቅር ፣ግራበመጋባት ውስጥ ሆነው ይህን መፅሐፍ ፅፈውታል።

ቋንቋዎቹም ተመሳሳይ አልነበሩም። በእብራይስጥ ፣ አርማዬክ ፣ በግሪክ ተፅፏል ። እንደዚህ በተለያየ ሰው ፣በተለያየ ስፍራ ፣በተለያየ ቋንቋና በተለያየ ስሜት ተፅፎ ግን አንዱ ከሌላው አይጣረስም።

በጣም ብዙ ተቃውሞ የደረሰበት መፅሐፍ ነው። በብዙ መሪዎች ድምጥማጡ እንዲጠፋ የተፈረደበት ይህ መፅሃፍ ይሄን ሁሉ ጫና ተቋቁሞ አመታትን ዘልቋል ብዛቱም እንደ ምድር አሸዋ ሆኗል። ለአብነት ጌድዮን ኢንተርናሽናልን እንኳ ብንወስድ 1899 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት ቢሊዮን ኮፒዎችን አሰራጭቷል። ዮናይትድ ባይብል ሶሳይቲ በበኩሉ ከ 2010 -2014 ብቻ 160 ሚሊየን ኮፒዎችን ለአለም አበርክቷል።

በየትኛውም አካባቢ በአንድ መንገድ አንድ ኮፒ የሆነ ሰው እጅ ላይ ይገኛል። በ 2014 ብቻ 428 ሚሊየን ኮፒዎች እንዳሰራጨ የአለም መፅሀፍ ቅዱስ ማህበር ይናገራል። የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ "አምስት ቢሊዮን ግዜ የታተመ ብቸኛው መፅሀፍ " ብሎ መዝግቦታል። ባሳደዱት ቁጥር እየበዛ አለምን ያጥለቀለቀ ድንቅ መፅሃፍ ነው።

ይህ መፅሐፍ ለመጀመሪያ ግዜ ወደ ኢንግሊዘኛ ቋንቋ ሲተረጎም ዊሊያም ተንደርሊ የተባለው ተርጓሚ በቁሙ በእሳት ተቃጥሎ እንዲሞ'ት ተደርጓል። (ይህ ሰው ሊቀጡት ሲወስዱት እንዲህ ብሎ ልክ እንደ እስጢፍኖስ "ጌታ ሆይ የኢንግላንድን ነገስታት አይን ክፈት " ፀሎቱም ፍሬ አፍርቶ ሙሉ አውሮፓን በክርስትና አጥለቀለቀ።) ብዙ ዋጋ ተከፍሎበት ነው ዛሬ እኔና እናተ እጅ እንዲገባ የተደረገው። ይህን የህይወት ምስክርነት ያለውን ሰዎች በእግዚአብሔር መንፈስ ተረድተው የፃፉትን የአምላካችንን የፍቅር ደብዳቤ ስንት ግዜ አንብበነዋል???

 #አዎ የከበረው ተስፋችን  #ኢየሱስ  #ይመጣል!!“ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።”  — ራእይ 22፥20
05/01/2024

#አዎ የከበረው ተስፋችን #ኢየሱስ #ይመጣል!!

“ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።”
— ራእይ 22፥20

"ኢየሱስ ይመጣል " በማለታቸው ከስራ ተባረዋል!በአሜሪካ ዶለር ላይ ግን" In god i trust " "በእግዚአብሔር እተማመናለሁ/ታምኛለሁ " ይላል..እኛ ጋር ግን....😎 በሲዳማ ክልል የሐ...
27/12/2023

"ኢየሱስ ይመጣል " በማለታቸው ከስራ ተባረዋል!

በአሜሪካ ዶለር ላይ ግን" In god i trust " "በእግዚአብሔር እተማመናለሁ/ታምኛለሁ " ይላል..እኛ ጋር ግን....😎

በሲዳማ ክልል የሐዋሳ ከተማ ትራፊክ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የነበሩ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ በአንድ ወዳጃቸው ቀብር ላይ በመንግሥት መኪና "ኢየሱስ ይመጣል " በማለታቸው ከስራ ተባረዋል።

እንደ እኔ አስተያየት ቢሆን ይህ ሰው በመንግሥት መኪና "ኢየሱስ ይመጣል " ማለታቸው እንደ ጥፋት ከተቆጠረ መደረግ ያለበት አስተዳደራዊ ቂጠት ነው እንጂ ከስራው ማባረር አግባብ ነው ብዬ አላምንም። ለማንኛውም ለእኝህ አባት ፈጣሪ ለመጥቀም የፈለገበት ሰበብም ልሆን ይችላል።

ወንጌልን በመስበክ እንኳን ከስራ መባረር ይቅርና መሞትም ያለ ነውና አዲስ ነገር አይደለም። ግን ክርስቲያኖች ለእኝህ አባት የሞራል ከሳ መተባበር እንዳለበት አስባለሁ።

@ፍፁም ተስፋዬ ( Erbeeto)

22/12/2023

#ጌታ በሥራ ለይ ነው!!

 #ሁለተኛውን ሞት እንዳትሞቱ  #ኢየሱስ  ሞቶላችሁሃል!!!“ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላ...
15/12/2023

#ሁለተኛውን ሞት እንዳትሞቱ #ኢየሱስ ሞቶላችሁሃል!!!

“ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
— ራእይ 21፥8

"በEBS ቴሌቪዥን ወንጌል ተሰበከ!!" "ዓለም ነቅቼብሻለሁ፤ ተጣልተናል። ከዚህ በኋላ ወዳጅነት የለንም ብዬ ጥዬ ወደ ኢየሱስ መጣሁ!!"ዘማሪት ዘሪቱ ከበደ ከእግዚአብሔር ጋር ፀበኛ የሆነ ዓ...
19/11/2023

"በEBS ቴሌቪዥን ወንጌል ተሰበከ!!"

"ዓለም ነቅቼብሻለሁ፤ ተጣልተናል። ከዚህ በኋላ ወዳጅነት የለንም ብዬ ጥዬ ወደ ኢየሱስ መጣሁ!!"
ዘማሪት ዘሪቱ ከበደ

ከእግዚአብሔር ጋር ፀበኛ የሆነ ዓለም አለ። ከዚያ ዓለም ጋር ደሞ ወዳጅነት ነበረኝ። ያ ወዳጅነት ደሞ ከእግዚአብሔር ጋር ወዳጅነት ስፈልግ መቀጠል አልቻለም።
ስለዚህ ያዉ ስነቃባት በእግዚአብሔር ብርኃን ዉስጥ ስትታየኝ ስብከቷን በተራዬ ላጋልጥባት ሆነ። ስብከቷ የሽቅድምድም፤ የስስት፤ የመጎምጀት፤ የትዕቢት፤ የቅናት.. ያ ሁሉ ጥበብ ነዉ ብላ የምትሰብከዉ ነገር አለ።
በሷ ጥበብ ፈንታ አዲሱን ጥበብ ገርነትን፤ የዋህነትን፤ ይቅርታን፤ ፍቅርን በመማር ያዉ ዓለም ነቅቼብሻለሁ፤ ተጣልተናል። ከዚህ በኋላ ወዳጅነት የለንም ብዬ ጥዬ ወደ ኢየሱስ መጣሁ!!

እናመሠግናለን EBS ቴሌቪዥን🙏🙏!!
ይልመድባችሁ!!

 #ለሕግ ባለሙያዎች የተደረገ ጥሪ...
17/11/2023

#ለሕግ ባለሙያዎች የተደረገ ጥሪ...

ከካውንስሉ የተላለፈ መልዕክት...
17/11/2023

ከካውንስሉ የተላለፈ መልዕክት...

ይድረስ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳበኦሮሚያ ክልል  በ ቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ሕገ መንግስታዊ የሐይማኖት ነጻነት የመብት ጥሰት የተፈጸመባቸው 1.የቢሾፍቱ...
17/11/2023

ይድረስ ለኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ
በኦሮሚያ ክልል በ ቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ ሕገ መንግስታዊ የሐይማኖት ነጻነት የመብት ጥሰት የተፈጸመባቸው
1.የቢሾፍቱ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያንና
2.የቢሾፍቱ የቃለ ሕይወት ማዕከል እንዲሁም
3.በሸገር ከተማ አስተዳደር የፈረሱ የጸሎት ቤቶች የአንድ ግለሰብ ወይም የአንድ ቤተ እምነት ጥያቄ ሳይሆን 35 ሚሊየን የሚሆነው የወንጌል አማኝ ጥያቄ በመሆኑ የእርስዎን ቁርጠኛ ምላሽ እንፈልጋለን ።

14/11/2023



የቢሾፍቱ ሙሉወንጌል ቤተክርስቲያን ንብረት የሆነዉ እና ለልዩ ልዩ አገልግሎት የምትጠቀምበት ቦታ ቤተክርስቲያኒቱ ህጋዊ የይዞታ ባለቤት ሆና ሳለ ቦታዉን ከቤተክርስቲያኒቱ ነጥቆ በአሁኑ ጊዜ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የጨለለቅ ክፍለ ከተማ ፅ/ቤ በሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ቅጥር ጊቢ ዉስጥ ከፍቶ ይገኛል።

በሶሻል ሚዲያ ለምትሰሩ ፌስ ቡከሮች፣ ዩቲዩበሮች እና ቲክቶከሮች ጥቅምት 29 ሐሙስ ጠዋት በዩጎ ሲቲ ቤተ ክርስቲያን ከ 3:00 ጀምሮ እንድትገኙ!የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያና...
03/11/2023

በሶሻል ሚዲያ ለምትሰሩ ፌስ ቡከሮች፣ ዩቲዩበሮች እና ቲክቶከሮች ጥቅምት 29 ሐሙስ ጠዋት በዩጎ ሲቲ ቤተ ክርስቲያን ከ 3:00 ጀምሮ እንድትገኙ!

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል

😭😭😭  ይህ የምታዩት ወንድማችን ነብይ አንዱአለም ጴጥሮስ ይባላል አሁን በዚህ ሰዓት በጣም በጠና ተመዋል ሰውነቱ ሶስት (3) ጊዜ ኦፕራስዮን ከመደረጉ የተነሳ አሁን ኮማ ውስጥ ይገኛል!! P...
01/11/2023

😭😭😭 ይህ የምታዩት ወንድማችን ነብይ አንዱአለም ጴጥሮስ ይባላል አሁን በዚህ ሰዓት በጣም በጠና ተመዋል ሰውነቱ ሶስት (3) ጊዜ ኦፕራስዮን ከመደረጉ የተነሳ አሁን ኮማ ውስጥ ይገኛል!! Please እንፀልይለት...
እባካችሁ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ወንድማችን እንድረስለት...
ይህ ከታች የምታዩት የባንክ አካውንት የሚስቱ አካውንት ነው። እባካችሁ የቻላችሁትን ተባበሩ...😭😭😭
Degenashi Temesegni 1000073209588 Ehitopa Nigid Banki

share share share share

 ...  #እንኳን ደስ አላችሁ!!የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኒ ዛሬ ከቸርች መሪዎች ጋር በነበረው ስብሰባ የድሬዳዋ መካነየሱስ ቤተክርስቲያንን እንደማያፈርስ ቃል ገብቷል። በከተማዋ ያሉ የወንጌላ...
30/10/2023

... #እንኳን ደስ አላችሁ!!
የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኒ ዛሬ ከቸርች መሪዎች ጋር በነበረው ስብሰባ የድሬዳዋ መካነየሱስ ቤተክርስቲያንን እንደማያፈርስ ቃል ገብቷል። በከተማዋ ያሉ የወንጌላውያን ቤተክርስቲያያናት ጥያቄዎችን እንደሚመልስም ተናግሯል።
እናመሰግናለን...

 !!የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች (ወንጌላውያኑ) ቤተክርስቲያናት ከቀደሙት መንግስታት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ፈጽሞ ሊቆም ያልቻለና የተለያዩ ጥቃቶችን እያስተናገች ያለች ቤተ እምነት ነች። ...
29/10/2023

!!

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች (ወንጌላውያኑ) ቤተክርስቲያናት ከቀደሙት መንግስታት ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ፈጽሞ ሊቆም ያልቻለና የተለያዩ ጥቃቶችን እያስተናገች ያለች ቤተ እምነት ነች።

የቤተክርስቲያን መወረስ ከደርግ ዘመን ጀምሮ የነበረ እስከ እስከ አሁንም የዘለቀ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ የቤተክርስቲያን ፈረሳና ወረሳ፣ የመቃብር ስፍራ ጭምር እየፈረሰ ይገኛል።

ከወንጌላውያኑ ውጪ ያሉ እምነቶች የእነርሱ አንድ የማምለኪያ ስፍራ ሲነካ ምን ያህል እንደሚሆኑ የታወቀ ነው። ለዚህም ነው እነርሱ ቤተ እምነታቸው የማይደፈረው። በሰላማዊ መንገድ እኛም ይህን ነገር ባህል ማድረግ አለብን። እኛ የወንጌል አማኞች መንግስትን የምናከብርና፣ ህገ መንግስቱ የምንታዘዝ ነን አሁንም ቢሆን የምናነሳው ህገ መንግስታዊ መብታችን አልተከበረልንም የሚል ጥያቄ ነው ያለን።

ቤተእምነት አይፈርስም፣ አይነካምም። አንድ ብር ያለው ሰው በልማት ስም ቤተክርስቲያን አፍርሶ ሆቴል ልገንባ አለ ሲባል እጅግ አሳፍሪ ጊዜ ላይ እንዳለን አመላካች ነው።

በሰበሰብነው መረጃ መሰረት እስከ ዛሬ በመንግሥት ተወርሰው ያልተመለሱ፣ የፈረሱ መልሰው እንዳይገነቡ የታገዱ፣ ሊወረሱ እየተሰራባቸው ያሉ ቤተክርስቲያን በአጠቃላይ 39 ሲሆኑ፣ በየስፍራው ያሉና በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እንግልት የሚደርስባቸውና ጫና ያለባቸው ቤተክርስቲያናት ቀላል አይደሉም።
ከሰላሳ ዘጠኙ መሐል በአሁን ሰአት ጥቂቶቹን እነሆ።

፨ በዚህ ወቅት በታችኛው የመንግስት መዋቅር ለመውረስ በመሞከር እየተጻጻፉባቸው ካሉት ውስጥ

1, የድሬዳዋ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን

2, የቢሾፍቱ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ንብረት (ቤተልሔም የሚጸለይበት ስፍራ) ብዙዎቻችን ስንጸልይበትና መንፈሳዊ ስራ ሲሰራበት የነበረ ስፍራ ለመወረስ ስራ እየተሰራባቸው ካሉት መሐል ነው።

3, የቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን / ቢሾፍቱ ማዕከል (ለብዙ ጊዜ ስንጸልይበት የነበረ የቢሾፍታ የቃለ ህይወት ገስት ሐውስ)

፨ ከዚህ ቀደም ሙሉ በመንግስት የተወረሱ

1 , የኦሎምፒያ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን

2, የኢትዮጵያ ብርሃነ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን (ቡልጋሪያ ያለው የቀድሞ የመጥምቃውያን አዳራሽ)

3, የኢትዮጵያ ወንጌላውዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ (ጉድ ሸፐርድ)

4, የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ አጥቢያ

5, ፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች

፨ ፈርሰው እንዳይሰሩ የተከለከሉ

1, የሐላባ ጋለቶ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን
2, የሐላባ ርኆቦት መካነየሱስ ቤተክርስቲያን

፨ ኮተቤ ሚሊኒየም የክርስቲያኖች መቃብር ስፍራ አጥር ፈርሶአል!!

እነዚህ የተወሰኑት ብቻ ናቸው። እኛ መንግስት ይህን አስቦ ይሰራል ብለን እናምንም ነገር ግን በውስጥ በመዋቅር ወደ ታች ያሉትን አመራሮች የክልል ከንቲባዎችና በስራቸው አመራሮችን ግን አትኩሮ መመልከት አለበት። ለድሬዳዋ፣ ለቢሾፍቱ፣ ለአዲስ አበባ፣ ለሃላባ ከንቲባዎችና የዞን አመራሮችንና የሚመለከታቸው አካላትን ጠርተው መጠየቅ አለባቸው።

የቤተክርስቲያን አመራሮች፣ ምዕመናን በሰላማዊ መንገድ መታገልና፣ ይህን ጉዳይ በሚዲያ ሼር በማድረግ ድምጽ በመሆን፣ ሊወረሱ ያሉ ቦታዎችን መታደግ ያስፈልጋል። በዚህ ጉዳይ አንድ ድምጽ፤ አንድ አቋም መያዝ አለብን።

Christian Media Association

Address

Addis Ababa

Telephone

+251989846989

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HOLY FIRE TV posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to HOLY FIRE TV:

Videos

Share

Category