Population Media Center Ethiopia

Population Media Center Ethiopia PMC-Ethiopia began working in Ethiopia in 2001. The annual population growth rate is 2.55 percent.

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ፳፻፲፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሠላም፣ የደስታ እንዲሁም የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን!  ፖ...
19/01/2024

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ፳፻፲፮ ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሠላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሠላም፣ የደስታ እንዲሁም የአብሮነት እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን!

ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ።

Warm greetings to all our cherished followers celebrating the Epiphany festival in 2024! May this joyous occasion be filled with peace, happiness, and prosperity for each and every one of you. On behalf of the Population Media Center Ethiopia, we extend our heartfelt wishes for a blessed and memorable holiday season. May the spirit of Epiphany bring forth moments of reflection, enlightenment, and unity in your lives. Cheers to a festive and meaningful celebration!

🌟🙏 #ጥምቀት

ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን ያማከለ የውሃ፣ ሳኒቴሽን እና ኃይጂን (’ዋሽ’) መተግበሪያና ማስፈጸሚያ ሰነዶች ዝግጅት ለማሕበረሰብ ጤናማ ሕይወት እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች ሴቶች...
09/01/2024

ሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን ያማከለ የውሃ፣ ሳኒቴሽን እና ኃይጂን (’ዋሽ’) መተግበሪያና ማስፈጸሚያ ሰነዶች ዝግጅት ለማሕበረሰብ ጤናማ ሕይወት
እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያሉ ሀገሮች ሴቶችና ወጣት ልጃገረዶች የተለያዩ የቤት ውስጥ ሥራዎችን በኃላፊነት ተረክበው የሚሰሩ ሲሆን፤ በአብዛኛው ጊዜ ምግብ ከማብሰል ጀምሮ፣ የቤት ንጽህናን መጠበቅ እንዲሁም ሕፃናትን የማሳደግ ኃላፊነት ይጣልባቸዋል። በገጠራማ አካባቢዎች ደግሞ ረጅም መንገድ በመጓዝ ውሃ የመቅዳት፣ ለማብሰያ የሚውል ማገዶ የመሰብሰብ፣ ከብቶችን የማገድ፣ የእርሻ ሥራዎችን የመሥራት እና የመሳሰሉት ላይ ይሳተፋሉ። በመሆኑም እነዚህ እገዛቸው በቤተሰብ ጤናማ የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የጎላ አስተዋጽኦ አላቸው። በተለይም የንጹህ ውሃ አቅርቦት ከፍተኛ ሚና ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።
የአካባቢ ንጽህና እንዲሁም የንጽህ ውሃ አቅርቦት ጉዳይ በአካል ጉዳተኞች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በተለይ የዚህ ችግር ሰለባ የሆኑ ወገኖችን በገጠር አካባቢ በመኖራቸው መሠረታዊ የሆኑ ግልጋሎቶችን በቀላሉ ማግኘት ባለማቻላቸው ችግሩ የተወሳሰበ እንዲሆን አድርጎታል።
ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ጋር በመተባበር የ’ዋሽ’ (WASH) ሥራዎችን ላለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በጋምቤላ፣ በቢኒሻንጉል ጉሙዝ፣ እና በአፋር ክልሎች በርካታ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። ከዚህም ጋር በተያያዘ የተለያዩ የተግባር መመሪያ አዘጋጅቶ በማጠናቀቅ ላይ ነው። ከእነዚህም መተግበሪያና ማስፈጸሚያ ሰነዶች መካከል 1. ሥርዓተ ፆታ እና ‘ዋሽ‘ 2. አካል ጉዳተኞች እና ‘ዋሽ’፣ እንዲሁም 3. የወር አበባ፣ ጤና እና የንፅህና አጠባበቅ ዋሽ ይገኙበታል።
ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግር ለመፍታት ከክልሎቹ እስከ ወረዳ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ጋር በመሆን ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በራዲዮ ቶክ ሾው እና ድራማዎች፣ እንዲሁም ማሕበረሰቡን ያሳተፈ የንቅናቄ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም የ’ዋሽ’ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ በሆነባቸው ወረዳዎች ለውጥ መታየት መጀመሩን ተቋሙ በወረዳዎቹ ባደረጋቸው የመስክ ምልከታ እና ግምገማዎች ማረጋገጥ ችሏል። ለውጡም በወረዳ ደረጃ ብቻ እንዳይቀር እና እንደ ሀገርም መንግሥት በዘርፉ የሚያከናውናቸው ሥራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው፣ እንዲሁም በተደራጀና በተቀላጠፈ መልኩ እንዲተገበሩ ይረዳ ዘንድ ከዩኒሴፍ በተገኘ ድጋፍ ሰባት የሚደርሱ ሥርዓተ ፆታ እና አካል ጉዳተኞችን ያካተተ የውሃ ሳኒቴሽን እና ኃይጂን እንዲሁም የወር አበባ ጤናና ንጽህና አጠባበቅ መሠረት ያደረጉ የትግበራ መርጃ ሰነዶችን አዘጋጅቷል።
ሰነዶቹም 1. የሃይማኖት መሪዎች የ’ዋሽ’ መርጃ ሰነድ፣ 2. የጋዜጠኞችና የሚዲያ ፈፃሚዎች የ’ዋሽ’ መርጃ ሰነድ፣ 3. የትምህርት ቤት ‘ዋሽ’ የማሕበራዊ የባሕሪ ለውጥ የትግበራ መመሪያ ሰነድ፣ 4. የሥርዓተ-ፆታ ምላሽ ሰጪ እና አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ‘ዋሽ’ የትግበራ መመሪያ ሰነድ፣ 5. አካታች የወር አበባ ጤና እና ንፅህና አጠባበው መመሪያ ሰነድ፣ 6. ሁሉን አቀፍ የማሕበረሰብ ግብረመልስ እና ምላሽ ሰጪ ዘዴ የ‘ዋሽ’ አገልግሎቶች መመሪያ ሰነድ፣ 7. የወር አበባ ጤና እና ንፅህና አጠበበቅ ደህንነቱ የተጠበቀ ነፃ የማረፊያ ሥፍራ መመሪያ ናቸው።
እነዚህ ሰነዶች በፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ አስተባባሪነትና ድጋፍ ሰጪነት ከዩኒሴፍ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጁ ይሁኑ እንጂ፣ ከይዘት ዝግጅት ጀምሮ እስከ ግብዓት አሰባሰብ፣ ብሎም እስከ ማጠናቀቂያው እና ጉዳዩ በሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እስከ ማጸደቅ እንዲሁም ሥልጠናዎችን እስከ መስጠት ድረስ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማሕበራት ፌዴሬሽን፣ ከብሔራዊ የዋን ዋሽ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት፣ ከሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች፣ ከሚዲያ ተቋማት የተውጣጡ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የጎላ ሚና ተጫውተዋል። ዶኩመንቶቹ በመንግሥት ደረጃ ያለውን ሥርዓት ጤና ለማጠንከር እና ለአቅም ግንባታ ሥራዎች እንደሚረዱ ይታመናል።
የማስፈጸሚያ ሰነዶቹ ወደ ትግበራው በሚለወጥበት ወቅት በተለይ የጤናው፣ የትምህርት፣ የማሕበራዊው፣ የውሃና ሥርዓተ ፆታ መስክ የ’ዋሽ’ ሥራዎችን በተደራጀና በተቀላጠፈ መልኩ እንዲተገብሩ ይረዳል። ሰነዶቹ በተለይ በአገር አቀፍ እና በክልሎች ደረጃ የሥራ ድግግሞሽ እንዳይፈጠር ከማስቻላቸውም ባለፈ ወጥነትና ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲተገበሩም ይረዳል። መመሪያዎቹ በሚዘጋጁበት ወቅት ሥርዓተ ፆታና አካል ጉዳተኝነትን ያካተቱ መሆናቸው በቀጣይ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ይህንኑ መሠረት ያደረጉ እንዲሆኑም ያስችላሉ። መተግበሪያዎቹ የሕብረተስቡን ተሳትፎ የሚያሳድጉ ከማድረጉም በተጨማሪ ግልጽነት፣ ኃላፊነት እና የተጠያቂነት አሰራሮች እንዲኖሩ ያግዛሉ። ሰነዶቹ እንደ ሀገር የውሃ ሳኒቴሽንና ኃይጂን/ ’ዋሽ’ እና በወር አበባ ጤናና ንጽህና አያያዝ ላይ የታዩ ክፍተቶች እንዳይኖሩም ያግዛሉ ተብሎም ይታመናል።
በዶኩመንቶቹ ላይ ከፌዴራል ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የመንግሥት ለሚንስቴር መሥሪያ ቤት ተወካዮች፣ ሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች፣ የቢሮ ተወካዮች፣ ጋዜጠኞችና የሚዲያ ፈጻሚ አካላት በተለያዩ ዙሮች የተለያዩ ሥልጠናዎች የተሰጡ ተሰጥቷል። በሥልጠናዎቹ ወቅት ክልሎቹ ለአተገባበሩ እቅዶቻቸውን በማዘጋጀት ወደ ተግባር ለመግባት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
እነዚህን ጠቃሚ ሰነዶች ለማዘጋጀት ከሁለት ዓመታት በላይ የፈጀ ሲሆን፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በሚገባ የተሳተፉበት በመሆኑ አፈጻጸሙ ውጤታማ እንደሚሆን ይታመናል። ሰነዶቹን ሥራ ላይ ለማዋል የማስተባበር ሥራው በጤና ሚኒስቴር፣ በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ በትምህርት ሚኒስቴር፣ በሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር፣ በብሔራዊ የዋን ዋሽ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት እና ዩኒሴፍ የሚሰራ ይሆናል።

09/01/2024

Have you heard about the incredible initiatives led by Population Media Center Ethiopia? 🌱💙 Population Media Center Ethiopia is making waves by harnessing the power of storytelling to tackle social issues and drive positive change. 🎥🌟

Through captivating narratives and compelling media, they're shedding light on crucial topics such as reproductive health, gender equality, and environmental sustainability. 🌏🌿 Witnessing the impact of storytelling in inspiring informed choices and building a brighter future together is truly remarkable. 🤝🌈

Join the movement for positive change and become an integral part of this inspiring story. 📚🎬 🇪🇹🌟

Learn More: https://pmcethiopia.org/

በሀገር ውስጥ እንዲሁም በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለ2016 ዓ.ም የገና በዓል በሠላም፣ በጤና አደረሰሳችሁ። በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እንዲሁም የአብሮነት እ...
06/01/2024

በሀገር ውስጥ እንዲሁም በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለ2016 ዓ.ም የገና በዓል በሠላም፣ በጤና አደረሰሳችሁ። በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር እንዲሁም የአብሮነት እንዲሆን ልባዊ ምኞታችንን እንገልጻለን! ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ

As the joyous season of Christmas envelops us, PMC-E extends heartfelt greetings to our cherished Christian community in Ethiopia and around the world.

May this festive season overflow with moments of love, peace, and joy. Let the spirit of Christmas ignite kindness and compassion in your hearts, fostering unity and understanding among all.

Wishing you and your loved ones a Merry Christmas filled with warmth, laughter, and the company of those dear to you.

With gratitude for your unwavering support and commitment to positive change,

Population Media Center Ethiopia

🎄 !

Population Media Center Ethiopia (PMC-E) & Save the Children Project Impact in Eliminating FGM and Child Marriage in Afa...
05/01/2024

Population Media Center Ethiopia (PMC-E) & Save the Children Project Impact in Eliminating FGM and Child Marriage in Afar and Somali Regional States
Explore the profound impact of the collaborative efforts between Population Media Center Ethiopia (PMC-E) and Save the Children Project in the quest to eliminate Female Ge***al Mutilation (FGM) and Child Marriage in the Afar and Somali regional states. In this captivating video, witness the transformative initiatives that have been undertaken to address these deeply rooted cultural practices affecting vulnerable populations.
Dive into the heart of Ethiopia's Afar and Somali regions, where PMC-E and Save the Children, Project have been working tirelessly to raise awareness, educate communities, and empower individuals to eradicate FGM and Child Marriage. Through compelling storytelling, this video sheds light on the stories of resilience, courage, and change among the affected communities.
Discover the innovative strategies employed by PMC-E and Save the Children Project to engage local communities, challenge societal norms, and foster sustainable solutions. From educational programs to community outreach and advocacy, witness the multifaceted approach taken to create a lasting impact on the lives of individuals affected by these harmful practices.
Join us in celebrating the successes and milestones achieved through this collaborative endeavor. Together, we strive towards a future where every individual, regardless of gender or background, can live free from the shackles of FGM and Child Marriage. This video serves as a testament to the power of collective action and the potential for positive change in even the most challenging environments.

Population Media Center Ethiopia (PMC-E) & the Children Project Impact in Eliminating FGM and Child Marriage in Afar and Somali Regional StatesExplore the pr...

Wishing a transformative and joyous New Year 2024 to our incredible donors, partners, and the global community celebrati...
01/01/2024

Wishing a transformative and joyous New Year 2024 to our incredible donors, partners, and the global community celebrating the Gregorian Calendar New Year! As we step into this new chapter, let's wholeheartedly embrace the tapestry of cultures and traditions that make our world vibrant and interconnected. May this year bring unprecedented unity, understanding, and collective prosperity. Here's to a year filled with shared dreams, impactful collaborations, and boundless possibilities. Cheers to a truly inspiring journey ahead!

!

Transformative CFM Workshop Unveils Path to Inclusive WASH ServicesDecember 27, 2023 - Addis Ababa, EthiopiaIn a groundb...
27/12/2023

Transformative CFM Workshop Unveils Path to Inclusive WASH Services
December 27, 2023 - Addis Ababa, Ethiopia
In a groundbreaking two-day event starting on December 26 and concluding on December 27, 2023, Population Media Center Ethiopia (PMC-E) partnered with UNICEF to host a transformative Familiarization Workshop in Addis Ababa, Ethiopia. The workshop served as a catalyst for government stakeholders and WASH program actors to come together and understand the significance of the Community Feedback Mechanism (CFM) framework.
Opening Remarks by Mr. Najat Akbar, UNICEF Ethiopia Chief of WASH
Mr. Najat Akbar, the UNICEF Ethiopia Chief of WASH, welcomed participants and highlighted the workshop's importance in successfully implementing WASH activities at national and regional levels. The event provided a unique platform for participants to share their experiences and challenges encountered in their respective regions.
Insights from WASH Social and Behavioral Change Specialist, Kalkidan Gugsa
Kalkidan Gugsa, WASH Social and Behavioral Change Specialist associated with UNICEF Ethiopia, extended a warm welcome, emphasizing the profound significance of CFM. She underscored its pivotal role in influencing communities and healthcare outcomes, urging collective exploration and appreciation for its transformative impact on community engagement and healthcare practices.
Two-Day Familiarization Training Workshop Highlights
Dr. Eshetu Girma, MPH, PhD, presented various WASH topics, including pretests, introductions, setting norms, community feedback importance, common WASH problems, community sensitization, and gender and disability inclusiveness for WASH. Group discussions and reflections were integral to the event, covering communication skills, public speaking, feedback dynamics, conflict resolution, and confidentiality.
Equipping Participants for Change
The workshop equipped participants with essential skills related to CFM, including communication, public speaking, feedback management, conflict resolution, and confidentiality. It concluded with the formation of CFM establishment or revitalization teams, entrusted with managing CFM, analyzing feedback, and strategizing responses.
Promoting Gender and Inclusiveness in WASH Initiatives
In-depth discussions emphasized gender and inclusiveness in WASH initiatives, recognizing the importance of equitable access and participation. Representatives from diverse ministries and regions participated, marking a monumental step towards empowering communities and ensuring every community member's voice is heard, valued, and acted upon.
A Monumental Step Towards Positive Change
Hosted collaboratively by PMC-E and UNICEF, the CFM Familiarization Training Workshop stands as a watershed moment in Ethiopia's healthcare narrative. It delves deep into the essence of the Community Feedback Mechanism and its far-reaching implications, promising re-engineering and complexity adaptive, transparent, accountable, and sustainable WASH program delivery, and community engagement in Ethiopia.

Regional Workshop on Inclusive Menstrual Health and Hygiene (MHH) Toolkit in Humanitarian SettingsAddis Ababa, Dec. 08, ...
09/12/2023

Regional Workshop on Inclusive Menstrual Health and Hygiene (MHH) Toolkit in Humanitarian Settings
Addis Ababa, Dec. 08, 2023: PMC-E hosts a Regional Familiarization Workshop on Inclusive Menstrual Health and Hygiene (MHH) Toolkit in Humanitarian Settings, generously supported by UNICEF. Dr. Hailegnaw Eshete, Country Director of Population Media Center Ethiopia (PMC-E), inaugurated the event, extending a warm welcome to participants and expressing gratitude for their invaluable presence.
Dr. Hailegnaw highlighted PMC-E& #39;s extensive 20-year commitment to pivotal issues such as reproductive health, girls& #39; education, and environmental sustainability. The organization, in collaboration with UNICEF, UNFPA, and Save the Children, aims to address critical concerns like WASH, nutrition, and harmful practices. PMC-E utilizes entertainment-education and various mass media to foster positive behavioral change, emphasizing the need for healthier and more prosperous lives in Ethiopia. & quot; This MHH workshop is a critical initiative, especially in the context of displacements, humanitarian crises, and refugees. Your active participation is essential to prioritize and cascade this workshop in your respective regions. MHH
is not just an individual concern but a societal issue. We are delighted to have you discuss and share your experiences and concerns regarding MHH,& quot; Dr.Hailegnaw emphasized.
Feleke Kibret, PMC-E/UNICEF WASH and Nutrition Project Coordinator underlined the importance of Training of Trainers (TOT) and national training cascade plans. He stressed the development of action plans to ensure the widespread implementation of
MHH training across regions. Birhanu Tezera, Managing Director of Grace Consultancy, delivered a comprehensive presentation on the menstrual health and hygiene toolkit in humanitarian settings. He covered inclusive MHH programming, need assessment, program planning, implementation procedures, materials and supplies, infrastructure, waste management, safeguarding, and monitoring and evaluation protocols.
Throughout the two-day workshop, participants engaged in lively discussions on existing practices, best practices, challenges, and opportunities related to MHH. Topics ranged from space availability and logistics to community engagement and education.
Participants addressed both successful practices, such as community mobilization activities and the establishment of MHH clubs, and challenges like the shortage of MHH room services and weak coordination in urban schools. Challenges included limited MHH services in humanitarian settings, coordination issues, weak male engagement, and the absence of standardized guidelines. The participants also formulated regional cascading operational plans for future implementation.
Representatives from Health Bureaus across Tigray, Amhara, Oromia, Benishagul Gumuz, Gambella, Southwest Ethiopia, Central Ethiopia, South Ethiopia, Dire Dewa, Harari, and Sidama regions actively participated in the workshop. Their commitment and collaborative spirit will undoubtedly contribute to advancing inclusive menstrual health and hygiene initiatives across the country. Thank you to all participants for their valuable insights and dedication.

“መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!” ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ ሕዝብ ፈንድ(ዩኤንኤፍፒኤ)፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ...
06/12/2023

“መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!”
ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ ሕዝብ ፈንድ(ዩኤንኤፍፒኤ)፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሕፃናት ፈንድ(ዩኒሴፍ)፣ ከዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት(ሴቭ ዘ ቺልድረን) እና ከሌሎች አጋሮች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ እነዚህ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የተለያዩ ትምህርታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቷል። በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም በጎጂ ድርጊቶች ላይ የተዛባ አመለካከቶች ያሉ በመሆኑ፤ የችግሩን አሳሳቢነት ከሥሩ ለመፍታት የሚያስችል ሥልቶችን በመንደፍ በመሥራት ላይ ይገኛል። ችግሮቹንም ለመፍታት ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ እየሠራቸው ካሉ ተግባራት መካከል በጉዳዩ ላይ ያተኮሩ የራዲዮ ፕሮግራሞች፣ የተለያዩ የንቅናቄ ሥራዎች፣ የተለያዩ የተግባቦት ሕትመቶች ማሳተም እና ማሰራጨት፣ የትምህርት ቤት ሚኒ ሚዲያዎችን በመጠቀም ቁልፍ መልዕክቶችን ማስተላለፍ፤ የሬዲዮ አድማጭ ቡድኖችን በማቋቋም በጉዳዩ ላይ የተዘጋጁ የሬዲዮ ድራማ እና የውይይት ፕሮግራሞችን እንዲከታተሉ እና ግንዛቤ እንዲይዙ ሁኔታዎችን የማመቻቸት እና የመሳሰሉት በጥቂቱ ይገኙበታል። በሚሠሩ ሥራዎች የአመለካከት ለውጥ ከማምጣት በተጨማሪ፤ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የጾታ ጥቃት እንዳይፈፀም፣ ተፈጽሞም ሲገኝ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በማስቻሉም ረገድ ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር በመሥራት ላይ ይገኛል። ስለሆነም በሀገራችን በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱትን አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወሲባዊ ጥቃትም ሆነ ፆታን መሰረት ያደረገ አድልዎን በጋራ መከላከል ‘የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል’ የወሩ የፖፕሌሽኝ ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ መልዕክት ነው። በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ማውገዝ፣ ተጠቂዎችን መርዳትና መንከባከብ፣ የተቀናጀና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠትና ጥቃት የሚፈፅሙትንም በማጋለጥ ለፍትህ ማቅረብ ከሁሉም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው። የፍትህ አካላት፣ ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትና አፋጣኝ ውሳኔ በማስተላለፍ ወንጀለኞች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው። በያዝነው ሕዳር ለሁለት ሳምንታት በመካሄድ ላይ ያለው እንቅስቃሴ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈፀመውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል የታለመ ነው። “መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!”

Unveiling the Power of Media: Journalists Ignite WASH Advocacy in Bishoftu WorkshopBishoftu, Ethiopia - November 30, 202...
01/12/2023

Unveiling the Power of Media: Journalists Ignite WASH Advocacy in Bishoftu Workshop

Bishoftu, Ethiopia - November 30, 2023: In a groundbreaking move, PMC-E spearheaded a dynamic two-day Journalist and Media Practitioners WASH Toolkit Familiarization Workshop, setting ablaze the path to transformative media initiatives.

Kalkidan Gugsa, the compelling UNICEF SBC Specialist, illuminated the often-overlooked realm of Water, Sanitation, and Hygiene (WASH) during this immersive event. Collaboratively crafted over two years with government ministries and funded by UNICEF in collaboration with Population Media Center Ethiopia (PMC-E), the toolkit took center stage, captivating an eager audience. Recognizing the myriad contributors, Kalkidan stressed the vital need for continuous journalist input to amplify the toolkit's impact.

"As media practitioners, you play a pivotal role in prioritizing WASH issues daily," emphasized Kalkidan. "Shift your perspective from mere business promotion to embracing the social, economic, and health dimensions. Let's elevate the WASH narrative together."

Alemu Kejela from the Ministry of Health underscored the global WASH crisis, connecting water sanitation and hygiene to diseases like cholera. He passionately urged journalists to utilize their platforms to address and combat these pressing challenges.

Yimenu Adane of UNICEF/Ministry of Health delved into Ethiopia's WASH situation, providing a compelling overview that justified the toolkit's background. Chala Gari, representing the Ministry of Health, unfolded the indispensable role of media, including social media, in health communication and promotion, offering invaluable insights into effective WASH communication strategies.

The workshop struck a resonant chord with participants who acknowledged the historic oversight of WASH in media coverage. Empowered with newfound awareness, media practitioners pledged to champion WASH issues, emphasizing the urgent need for enhanced collaboration among organizations.

In addressing the workshop's pivotal role, participants engaged in discussions about inclusive WASH planning and media strategy, highlighting the significance of setting the WASH agenda. The event fostered networking among diverse participants, including representatives from regional health bureaus, MoH, MoWE, MoE, MoWS, the Federation of Persons with Disabilities, journalists, public relations experts, and WASH promotion and education professionals.

In conclusion, the workshop laid the bedrock for a media-driven WASH advocacy movement, empowering journalists to sculpt public discourse, influence decision-makers, and assume a pivotal role in propelling water, sanitation, and hygiene initiatives nationwide.

“መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!”እ.ኤ.አ በ2016 በኢትዮጵያ በተካሄደው የሥነ ሕዝብ እና የጤና የዳሰሳ ጥናት (EDHS) እንደሚያሳየው 33 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜ...
29/11/2023

“መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!”
እ.ኤ.አ በ2016 በኢትዮጵያ በተካሄደው የሥነ ሕዝብ እና የጤና የዳሰሳ ጥናት (EDHS) እንደሚያሳየው 33 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ15-49 የሆኑ ሴቶች ወሲባዊ ወይም አካላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። ጥናቱ እንደሚያሳየው፣ በዚሁ ዕድሜ ክልል ውስጥ ካሉ ሴቶች ውስጥ 10 በመቶ የሚሆኑት ወሲባዊ ጥቃት ሲፈጸምባቸው፤ 23 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ካላዊ ጥቃትን አስተናግደዋል። በተመሳሳይ ከአራት ሴቶች ውስጥ አንዷ ከ15 ዓመቷ ጀምሮ ጾታዊ ጥቃት ያጋጥማታል።
ዓለም አቀፍ የ16 ቀናት እንቅስቃሴ፣ በሥርዓተ-ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን ለመከላከልና ለማስቀረት በዓለም አቀፍ ደራጃ ለ32ኛ ጊዜ “በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል ኢንቨስት ያድርጉ!” በኢትዮጵያ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ ‘መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!”’ በሚል መሪ ኃሳብ ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት መከበር ጀምሯል። ዘመቻው በሴቶችና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም ጥሪ ለማቅረብ የታለመ ሲሆን፤ ከሕዳር 18 እስከ ታኅሳሣሥ 1 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።
ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች በማሕበረሰቡ ውስጥ ያለውን የተዛባ ፆታዊ የግንኙነት ሁናቴ መገለጫ ነው። ይህ ድርጊት ቀዳሚና ዋንኛው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲሆን፤ የትም ይከሰት የትም ፆታዊ ጥቃት ለፆታዊ እኩልነት መረጋገጥ፤ ለሕብረተሰብ ጤና፣ በሀገር ልማትና እድገትም ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚጥል እና ቀጣይነት ያለው የልማት፣ የኢኮኖሚ፣ የሠላም እና የእድገት እንቅፋት ነው። ሴቶችና ልጃገረዶች ደህንነት የማይሰማቸው ከሆነ በማሕበረሰባቸው ልማትና እድገት ላይም ሙሉ ተሳትፎ አይኖራቸውም። በኢትዮጵያ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ትኩረት የሚሹ ዋንኛ ጉዳዮች ናቸው። የትዳር አጋሮች ጥቃት፣ ወሲባዊ ትንኮሳና ጥቃት፣ የሴት ልጅ ግርዛት፤ በጠለፋ የሚደረግ ጋብቻ፤ አስገድዶ መድፈር እና ያለዕድሜ ጋብቻ በብዛት ከሚታዩ የፆታዊ ጥቃት ዓይነቶች ናቸው። በሴቶች ላይ የሚደርሱ እነዚህን መሰል ጥቃቶች በግለሰብ ደረጃ የሚደረጉ ፆታዊ ጥቃቶች ሲሆኑ፤ የሀገሪቱን ማሕበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበላሹ ድርጊቶች ናቸው። በዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ስምምነቶች ፆታዊ ጥቃት መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት ጥሰት መሆኑ ተደንግጓል። በሴቶች ላይ የሚደረግ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሴቶች መብቶቻቸውን እንዳይጠቀሙ ያግዳቸዋልድ። በሴቶች ላይ የሚፈፀም ጥቃት በተለምዶ በወንዶች የሚፈጸም ነው። በሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት በወንዶች ካልተመጣጠነ የበላይነት (ሥልጣን) ግንኙነት ይመነጫል። የተለያዩ ዓይነት የበላይነቶች አሉ፤ እንደ ኢኮኖሚ የበላይነት (ገንዘብ እና ሌሎች ምንጮችን መቆጣጠር) እና አካላዊ የበላይነት (የአካል ጥንካሬ ወይም መሣሪያ መጠቀም) ጥቂቶቹ ናቸው። በማሕበረሰቡ ዘንድ ሴቶች ከወንዶች ይልቅ የበታች ናቸው። የበታች የሆኑ ሴቶች ደግሞ በብዙ መልኩ ለጥቃት ተጋላጮች ናቸው።
የፆታ እኩልነት የሚረጋገጠው ሁሉም የሰው ልጆች እኩል መብት ሲያገኙ መልካም የሕይወት አጋጣሚ ሲፈጠርላቸውና የአኗኗር ዘይቤያቸውን ለማስተካከል ሙሉ መብት የተሰጣቸው ከሆነና ለማሕበረሰቡ አስተዋጽኦ ማድረግ ሲችሉ ነው። ከዚህ በተቃራኒው የፆታ እኩልነት አለመከበር ደግሞ ያልተመጣጠነ የኃይል ሚዛንና ፆታን መሠረት ያደረገ ማግለል የፆታዊ ጥቃት ናቸው። ይህ ደግሞ የፆታዊ እኩልነት መረጋገጥ ዋንኛ እንቅፋት ሲሆን፤ ያልተመጣጠነ የኃይል ሚዛን ደግሞ ጾታን መሠረት አድርገው የሚመጡ ናቸው።
ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ ሕዝብ ፈንድ (ዩኤንኤፍፒኤ)፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፍ የሕፃናት ፈንድ (ዩኒሴፍ)፣ ከዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ቺልድረን፣ እና ከሌሎች አጋሮች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ እነዚህ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል የተለያዩ ትምህርታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ሲሰራ ቆይቷል። በሀገሪቱ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም በጎጂ ድርጊቶች ላይ የተዛባ አመለካከቶች ያሉ በመሆኑ፤ የችግሩን አሳሳቢነት ከሥሩ ለመፍታት የሚያስችል ሥልቶችን በመንደፍ በመሥራት ላይ ይገኛል። ችግሮቹንም ለመፍታት ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ እየሰራቸው ካሉ ተግባራት መካከል በጉዳዩ ላይ ያተኮሩ የራዲዮ ፕሮግራሞች፣ የተለያዩ የንቅናቄ ሥራዎች፣ የተለያዩ የተግባቦት ሕትመቶች ማሳተም እና ማሰራጨት፣ የትምህር ቤት ሚኒ ሚዲያዎችን በመጠቀም ቁልፍ መልዕክቶችን ማስተላለፍ፤ የራዲዮ አድማጭ ቡድኖችን በማቋቋም በጉዳዩ ላይ የተዘጋጁ የራዲዮ ድራማ እና የውይይቶት ፕሮግራሞችን እንዲከታተሉ እና ግንዛቤ እንዲይዙ ሁኔታዎችን የማመቻቸት እና የመሳሰሉት በጥቂቱ ይገኙበታል። በሚሰሩ ሥራዎች የአመለካከት ለውጥ ከማምጣት በተጨማሪ፤ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የጾታ ጥቃት እንዳይፈፀም፣ ተፈጽሞም ሲገኝ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በማስቻሉም ረገድ ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር በመሥራት ላይ ይገኛል።
ስለሆነም በሀገራችን በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱትን አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወሲባዊ ጥቃትም ሆነ ፆታን መሰረት ያደረገ አድልዎን በጋራ መከላከል ‘የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል’ የወሩ የፖፕሌሽኝ ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ መልዕክት ነው። በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ማውገዝ፣ ተጠቂዎችን መርዳትና መንከባከብ ፣ የተቀናጀና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠትና ጥቃት የሚፈፅሙትንም በማጋለጥ ለፍትህ ማቅረብ ከኹሉም የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው። የፍትህ አካላት፣ ማሕበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠትና አፋጣኝ ውሳኔ በማስተላለፍ ወንጀለኞች ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የኹሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት።
በያዝነው ሕዳር ለሁለት ሳምንታት በመካሄድ ላይ ያለው እንቅስቃሴ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚፈፀመውን ፆታዊ ጥቃት ለመከላከል የታለመ ነው። “መቼም፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ፆታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!”

Breaking Ground in School WASH SBC! Addis Ababa Workshop Unveils Game-Changing Strategies for National WASH Behavioral C...
24/11/2023

Breaking Ground in School WASH SBC! Addis Ababa Workshop Unveils Game-Changing Strategies for National WASH Behavioral Change!

Addis Ababa, November 24, 2023: The PMC-E/UNICEF collaboration took a giant leap forward with a two-day Regional Familiarization Workshop in Addis Ababa, dedicated to propelling the National School WASH Social Behavioral Change (SBC) Guide. This event, from November 23 to 24, marks a game-changing milestone in advancing water, sanitation, and hygiene (WASH) practices in Ethiopian schools.

Revolutionizing School Hygiene: Recognizing the urgent need for enhanced WASH conditions in schools, PMC-E and UNICEF are actively driving social and behavioral change within school settings. This initiative aligns seamlessly with broader national and global efforts to uplift student well-being through comprehensive WASH behavior change.

Dynamic Discussions: The workshop served as a vibrant platform, fostering engaging discussions, thoughtful reflections, and the strategic development of action plans tailored for regional implementation. Divided into three groups, participants passionately delved into the challenges and opportunities surrounding School WASH SBC in their respective areas.

Key Moments: A pivotal highlight was a comprehensive presentation on School WASH behaviors, shedding light on key aspects of behavioral change strategies. The session emphasized the significance of effectively planning and implementing Social Behavioral Change (SBC) techniques.

Holistic Approach: In-depth discussions on SBC monitoring and evaluation took center stage, focusing on understanding roles and responsibilities in implementing the National School WASH Social Behavioral Change Guide. This ensures that the transformative strategies outlined in the guide are actively put into practice.

Collaborative Insights: Notably, participants from various institutions, including the Tigray Water and Energy Bureau, Oromia Region Health and Education Bureaus, Zone, Woreda, Central Ethiopia Region Health and Education Bureaus, and Southern Ethiopia Region Health and Education Bureau, collaborated to share insights, fostering a healthier and more conducive learning environment.

Culmination: The workshop concluded with a thorough review of the National School WASH Social Behavioral Change Guide document, providing participants with a comprehensive understanding of the guide's principles and strategies.

Looking Ahead: The momentum generated by this event is set to propel the effective implementation of the National School WASH Social Behavioral Change Guide across regions, creating a positive impact on the well-being of students throughout Ethiopia. Together, let's revolutionize school hygiene and pave the way for a brighter, healthier future!

“በእሷ እና በወደፊት ሕይወቷ መካከል ያሉትን መሰናክሎች እናስወግድ!”እ.ኤ.አ በ1954 በወጣውና በ1959 በፀደቀው ዓለም አቀፍ የወጣት ሴቶች መብቶች ድንጋጌ ላይ ለሕፃናት ልዩ እንክብካቤና...
16/11/2023

“በእሷ እና በወደፊት ሕይወቷ መካከል ያሉትን መሰናክሎች እናስወግድ!”
እ.ኤ.አ በ1954 በወጣውና በ1959 በፀደቀው ዓለም አቀፍ የወጣት ሴቶች መብቶች ድንጋጌ ላይ ለሕፃናት ልዩ እንክብካቤና እርዳታ ማድረግ የቤተሰብም የማሕበረሰብም ግዴታ መሆኑ በግልፅ ተቀምጧል፡፡ ኦክቶበር 11 የዓለም ወጣት ሴቶች ቀን ሆኖ እ.ኤ.አ ከ2012 ጀምሮ እንዲከበር የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በዓሉ በመከበር ላይ የሚገኝ ታላቅ ዓለም አቀፍ ኩነት
ሲሆን፤ ዘንድሮም በዓለም አቀፍ ደረጃ `Invest in Girls& #39; Rights: Our Leadership, Our Well- being` “በወጣት ሴቶች መብት ላይ መስራት ጥቅሙ የጋራ ነው፤ አመራራችን ለሁለንተናዊ ደህንነት” በሚል መሪ ቃል በዓሉ ተከብሮ ውሏል። ታዳጊ ሕፃናት በጾታቸው ምክንያት ከሚደርስባቸው መድሎና መገለል፣ ከኃይል ጥቃት፣ በታዳጊነት ከሚፈጸም ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ከመሳሰሉ ጎጂ ድርጊቶች እንዲጠበቁ እንዲሁም የጤና፣ ትምህርትና ሌሎች አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ተገቢ ነው። ሴት ሕፃናት ከቤተሰብ ጀምሮ፣ በማሕበረሰብና በሀገር ደረጃ አቅማቸውን ያገናዘቡ ተሳትፎዎችን ማድረግና ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ ይታመናል። ይህ ዕለት መከበሩ ሕፃናት ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸውና መብቶቻቸው እንዲከበርላቸው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማሰማት የሚችሉበትን መልካም አጋጣሚ ፈጥሯል። ሆኖም እያንዳንዷ ወጣት ልጅ የትም ብትሆን ስለ መብቷ በደንብ ጠንቅቃ በማወቅ፣ ትምህርቷን በአግባቡ እንድትከታተል ፣ የጤና እንክብካቤ እንድታገኝ፣ ያለምንም ጥቃት እንድታድግ መሥራት የሁሉም አካል ድርሻ ነው። በጾታዊ እና በሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን መሠረት ያደረጉ ኢንቨስትመንቶች መጨመር እና በአፍላነት ዕድሜ ላይ ያሉ ልጃገረዶች ስለ ሰውነታቸው እና ሕይወታቸው በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስኑ እንዲሁም የለውጥ አራማጆች እና የወደፊት መሪዎች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በኢትዮጵያ የወጣት ሴቶች ዝውውር አንዱና ዋነኛው የማህበራዊ ችግር ነው። ይህ ችግር በድህነት መስፋፋት እና በህገወጥ አዘዋዋሪዎች ሕጻናትንና ታዳጊ ወጣቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በመጉዳት ላይ ይገኛል። በተጨማሪም በህገወጥ መንገድ የሚዘዋወሩ ህፃናት አካላዊ እና ስሜታዊ ጥቃቶች እንደሚደርስባቸው ይታወቃል - መደፈር፣ ረሃብ፣ አካላዊ ጥቃት፣ አካል መጉደል፣ የጤና መታወክ እና ይብስ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል።
ብዙ ጊዜ ወጣት ሴቶችን ለጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች ድህነት በቀዳሚነት ተጠቃሽ ነው። ብዙ ደሃ ቤተሰቦች ኑሯቸውን ለመደጎም ሲሉ ለስራ ያልደረሱ ወጣት ሴቶችን የተለያዩ ስራዎችን እንዲያከናዉኑና ለቤተሰቡ ተጨማሪ ገቢ እንዲያስገኙላቸዉ ይጥራሉ። ወጣት ሴቶችን ለጉልበት ብዝበዛ የሚያጋልጣቸው ሌላው ምክንያት ከባህላችንና ከልምዳችን ጋር የተያያዘ ነው። አብዛኛው ሰው ወጣት ሴቶችን በለጋ ዕድሜያቸው የተለያዩ ዕውቀቶችና ክህሎቶች እንዲኖራቸው በማሰብ በስራ ላይ እንዲሰማሩ ይደግፋሉ ይገፋፋሉም። የትምህርት ዕድል ያለመኖርም፣ የወላጆች ሞት፣ በቂ የገቢ ምንጭ አለመኖር፣ የወላጆች የትምህርት ደረጃ ማነስ፣ የቤተሰብ መፍረስ፣ ግጭትና የቤት ውስጥ ጥቃቶች የመሳሰሉትም በመንስኤነት ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ወጣት ሴቶች ጉልበት ብዝበዛ በህፃናቱ ላይ ከሚያሰከትለው ከፍተኛ የአካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ማህበራዊና የመሳሰሉት ጉዳቶች ባለፈ በህብረተሰብና በሀገር ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው። የብዝበዛው ሰለባ የሆኑ አፍላ ሴቶች ከቀላል የአካል ጉዳት እስከ ሞት ለሚደርስ ጉዳት ይጋለጣሉ ወይም ለዕድሜ ልክ ለማይሽር አካላዊም ሆነ አእምሯዊ ጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ። የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ የሀገር ኢኮኖሚ ላይም አሉታዊ ተፅእኖ ያስከትላል። ከድህነት ጋር በተያያዙና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በሀገር ውስጥም ሆነ ወደ ውጭ በሚደረገው የህገወጥ የሕፃናት ዝውውር የወደፊት ሀገር ተረካቢ ሊሆን የሚችለውን በርካታ አምራችና ብቁ የሰው ኃይል ማጣትን ሊያስከትል ይችላል። ፖሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ በተለያዩ የሀገሪቷ ክልሎች የሴት ልጆች ጤናማና ብሩህ የወደፊት ሕይወት ለመፍጠር ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል። ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥነ ሕዝብ ፈንድ (ዩኤንኤፍፒኤ) ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት ፈንድ (ዩኒሴፍ) እና ከዓለም አቀፍ የሕፃናት አድን ድርጅት (ሴቭ ዘ ቺልድረን) ጋር ጾታዊ ጥቃትን፣ በታዳጊነት የሚፈጸም ጋብቻን እና የሴት ልጅ ግርዛትን ለማስቆም፣ ለሴቶች ልጆች የሕይወት ክህሎት ሥልጠና በመሥጠት፣ የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን በማስትዋወቅ፣ የሕጻናት ዝውውር እና ጉልበት ብዝበዛ እና ሌሎች ሰብዓዊ መብትን የሚጋፉ/የሚጥሱ ድርጊቶችን በመቃወም ህብረተሰቡን የሚያስተምሩና የሚያነቃቁ በራድዮ የሚተላለፉ በርካታ ተከታታይ ድራማዎችንና የሬድዮ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት፣ የህትመት ወጤቶችን በማሰራጨት፣ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ ለሕጻናትና ወጣት ሴቶች የተለያዩ ደጋፎችን በማድረግ እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በርካታ የሃገራችን ክልሎች ላይ እየሰራ ይገኛል።
በታዳጊነት የሚፈጸም ጋብቻንና የሴት ልጅ ግርዛትን ማስቀረት፣ ጥቅሙ ጤናን እና ሰብአዊ መብቶችንከማስጠበቅ ያለፈ ነው። የተሻሉ የትምህርት ፖሊሲዎች እና ውጤቶች ወጣት ሴቶች በመደበኛው ኢኮኖሚ ውስጥ ሥራ እንዲያገኙ እና ለቤተሰቦቻቸው የበለጠ ውጤታማ የሆነ አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ዕድል ይሰጣቸዋል። የ2030 ለዘላቂ ልማት ግቦች ቀነ ገደብ በመቃረቡ እያንዳንዷ በአፍላ ዕድሜ ላይ የምትገኝ ልጃገረድ በሁሉም ልዩነት ውስጥ መብቷን እና ምርጫዋን እንድትጠቀም፤ አቅሟንም ሙሉ በሙሉ እንድትገነዘብ እንዲሁም ለራሷ የምታስበውን የወደፊት ጊዜ እንድትገነባ የበኩላችንን እንወጣ። ከማሕበረሰብ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያላቸውን ወጣት ሴቶች በመፍጠር ጤናማ የሆነ ዜጋን ከማፍራት አኳያ ተቋማችንም ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ ይገኛል። በመሆኑም “የአንድ ልጅ መደገፍ የሀገር መደገፍ” መሆኑን ተገንዝበን ሁላችንም የበኩላችንን ኃላፊነት እንድንወጣ አደራ ለማለት እንወዳለን፡፡
“በእሷ እና በወደፊት ሕይወቷ መካከል ያሉትን መሰናክሎች እናስወግድ!” የፖፑሌሽን ሚዲያ ሴንተር ኢትዮጵያ የወሩ መልዕክት ነው!

National Workshop Champions Inclusive Menstrual Health and Hygiene (MHH) Toolkit in Humanitarian Settings(Addis Ababa, E...
10/11/2023

National Workshop Champions Inclusive Menstrual Health and Hygiene (MHH) Toolkit in Humanitarian Settings
(Addis Ababa, Ethiopia, 10 November 2023, PMC-E): Embarking on a transformative journey, the Population Media Center Ethiopia (PMC-E) orchestrated two-day National Familiarization Workshop on the Inclusive Menstrual Health and Hygiene (MHH) Toolkit in Humanitarian Settings. This monumental event, held on November 8-9, 2023, dedicated itself to elevating the well-being, dignity, and empowerment of persons with disability, women and girls grappling with crisis situations.
Unveiling Neglected Realities:
The workshop brought to light the often-overlooked challenges surrounding menstrual health and hygiene in humanitarian settings. Persons with disability, women and girls facing crises navigate obstacles, including limited access to sanitary products and inadequate safe spaces for hygiene. The implementation and enforcement of an inclusive MHH toolkit emerged as a pivotal catalyst in drawing attention to these pressing issues.
Insights from UNICEF Ethiopia:
Laura Anquez, UNICEF Ethiopia's WASH Cluster Coordinator, passionately highlighted the natural essence of menstruation. Stressing the importance of dignified menstrual hygiene management for the overall well-being of persons with disability, women and girls in humanitarian settings, Laura accentuated the role of the inclusive MHH toolkit in providing essential resources. She emphasized its capacity to reduce infection risks and promote better health outcomes, enabling persons with disability, women, and girls to fully participate in their daily activities.
A Unified Call for Collaboration:
Laura Anquez urged collaboration and robust coordination among government ministries and workshop participants for the seamless implementation of the toolkit. Participants were actively encouraged to voice concerns and contribute recommendations for the ongoing development and future steps of the MHH toolkit implementation. Laura stressed how best address and serve the people in disaster, outbreaks, emergency, and humanitarian situations. Emergency increase in complexity, scale and duration and need coordinated and integrated responses.

Championing Gender Equality and Mental Well-being:
Kalkidan Gugsa, WASH Social and Behavioral Change Specialist at UNICEF Ethiopia, underscored the toolkit's pivotal role in advancing gender equality. She passionately asserted that the implementation of an inclusive MHH toolkit breaks down gender-related barriers, creating an environment that prioritizes the needs of every individual. Kalkidan also shed light on the mental health impact of menstrual health challenges, emphasizing the toolkit's comprehensive support as a positive influence. She also highlighted the development process of the toolkit, and engaging federal ministries, Gender and Disability emergency WASH Cluster, and partners who are engaging on humanitarian settings. She obliged the MHH Toolkit will serve in emergency MHH programming implementation.
PMC-E's Gratitude and Participant Reflections:
PMC-E expressed heartfelt gratitude to all attendees, recognizing their pivotal role in shaping the outcomes of the toolkit for persons with disability, women, and girls in humanitarian settings. Participants engaged in open dialogue, reflecting on the significance of the Inclusive MHH Toolkit and sharing their concerns.
Global Standards and Dignity Commitment:
Numerous participants highlighted the alignment of including menstrual health and hygiene in humanitarian response with international standards for gender-responsive humanitarian action. This commitment reflects a dedication to upholding the rights and dignity of all individuals, irrespective of gender.
In conclusion, the implementation of the Inclusive Menstrual Health and Hygiene Toolkit in humanitarian settings is not just imperative but transformative. This initiative spearheads a comprehensive and inclusive approach to humanitarian response, addressing a critical aspect of reproductive health that has long been overlooked.
Collaborative Effort for Lasting Change:
The National Familiarization Workshop on Inclusive Menstrual Health and Hygiene Toolkit in humanitarian settings was a harmonious collaboration, hosted by PMC-E in partnership with UNICEF. The diverse assembly, including representatives from key ministries and stakeholders, actively engaged in spirited discussions and reflections, paving the way for the integration of the toolkit into WASH programs.

Address

Jomo Keneyatta Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 17:00

Telephone

+251115520990

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Population Media Center Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Population Media Center Ethiopia:

Videos

Share

Nearby media companies