14/02/2024
እዉነተኛ ደስታ የት ይገኛል❓
የህንዱ ቢሊኒየር ራታነጂ ታታ በሬዲዮ አቅራቢ እንዲህ ተብሎ ተጠየቀ፡-
‹ጌታዬ… ምንድነው የሚያስታውሱት በህይወቶ ደስታን ልክ ሲያገኙ…?› ቢሊኒየረር ራታኒጂ ታታ እንዲህ አለ፡-
‹እኔ በህይወቴ አራት ደረጃ አልፌያለሁ ለደስታ… እና በመጨረሻ ትክክለኛውን የደስታ ጣዕም ነው ያገኘሁት
የመጀመሪያው ደረጃ ገንዘብ እና የሀብት ምንጮችን መሰብሰብ ነበር፡፡ ግን በዚህ ደረጃ እኔ የምፈልገውን ደስታ ላገኝ አልቻልኩም፡፡
ከዛም ወደ ሁለተኛው ደረጃ ቀጠልኩኝ… ውድ የሆኑ ዕቃዎችና ነገሮችን መሰብሰብ… ግን አሁንም የገባኝ ይሄን ጊዜያዊ ስሜት እንደሆነ ነበር… ለውድ ነገሮች የሚመጣ ፍቅር ዘላቂ አልነበረም፡፡›
ቀጥዬ ወደ ሶስተኛ ሂደት ገባሁኝ… ትልቅ ፕሮጀክት በእጅ ማስገባት ነበር፡፡ ይሄ ማለት 95% የነዳጅ ገበያ በህንድና በአፍሪካ መያዝ ነበር፡፡ እሱ ብቻ አልነበረም እኔ በጣም ትልቅ የብረት ፋብሪካ በእሲያ እና በኢንድ ያለ ባለቤት ነበርኩኝ፡፡ ግን እንደአልምንኩት የሚሆን ደስታን ማግኘት አልቻልኩም፡፡
አራተኛው ደረጃ የእኔ ጓደኛ የሆነ የጠየቀኝ ነገር ነበር … መራመድ ለማይችሉ ለተወሰኑ ልጆች ዊልቸር እንድገዛ ነበር፡፡ ወደ 200 ዊልቸር ይሆናል የገዛሁት… በጓደኛዬ ትዕዛዝ ዊል ቸሮችን በፍጥነት ገዛሁኝ፡፡
ግን ጓደኛዬ በጣም አልቅህም አለኝ… ዊልቸሮችን አብረን ሄደን ለልጆችሁ እንድንሰጥ፡፡ እኔም በመዘጋጀት ከእሱ ጋር ለመሄድ ተስማማው፡፡
እዛ በመሄድ ለልጆቹ በእጄ ዊልቸሮቹን ሰጠሁኝ፡፡ በልጆቹ ላይ የሚገርም የሚበራ ደስታ አየሁኝ፡፡ ሁሉም ዊልቸሩ ላይ በመቀመጥ በደስታ እየዞሩ ሲደሰቱ ተመለከትኩኝ፡፡ እነሱ ከፍተኛ የደስታ ጫፍ ደርሰው ነበር… በጋራ ያሸነፉበት ስጦታ እየተደሰቱ ነበር፡፡
እኔም ልክ ለመሄድ ስነሳ… አንድ ህፃን ልጅ እግሬ ያዘኝ፡፡ በቀስታ ለማስለቀቅ እግሬን ለማስለቀቅ ስሞክር ግን ልጁ ፊቴ በቅርበት እያየ እግሬን ይበልጥ ወደ ራሱ በማስጠጋት ያዘኝ፡፡ እኔ ወደ እሱ ጠጋ ዝቅ በማለት ምን እንደሚፍልግ ጠየኩት…
ልጁ የመለሰልኝ መልስ እኔም ማስገርም ብቻ አልነበረም ያደረገው ህይወትን የምመለከትበትን መንገድ ሙሉ በሙሉ ቀየረብኝ እንጂ… ልጁም እንዲህ አለኝ፡-
‹ፊትህን ላስታውሰው እፈልጋለሁ… እኔ በገነት ሳገኝ ለይቼክ በድጋሚ ላመሰግን እፈልጋለሁ›
#ምንጭ፧ ከፌስቡክ
➜ ከተመቻችሁ ደስታን ፍለጋ ላይ ታች ለሚሉ እህት/ወንድሞች ያድርጉ፣