01/01/2025
ብልፅግና እንደ ቀልድ ስድስት ዓመት ሞላው። ምድሪቱ በደም አበላ ከጨቀየች እነሆ አምስት የአኬልዳማ ዓመታት!
ድርጅቱ እስከ አንገቱ በደም ተነክሮ ፈታ ዘና ብሎ እንደ ትላንቱ በውብ የቃላት ጋጋታ እና ዲኮር ታጅቦ አምስተኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አክብረዋል። በዓሉን ትተን ብልፅግና በኢኮኖሚ ደረጃ ባይኖርም በድርጅት ደረጃስ አለ ወይ ብለን እንጠይቅ....
ብልፅግና የምር አባል አለው..? ርዕዮተ-ዓለም አለው..? ሀሳብስ አለው..? ለሀሳቡ እና ርዕዮተ-ዓለሙ የሚታገል..የሚሰዋ አመራርስ አፍርቷል..? ውግንናውስ ለማነው..?
ድርጅቱ በኦሮሚያ ብቻ 5 ሚሊየን አባለት አሉኝ ይላል። እኔ ግን በፊት አንድ አባል ነበረው...አሁን ግን ምንም የለውም እላለሁ። ያ ብቸኛው ለማስመሳል ሳይሆን የምሩን ለሕዝብ ተጠቃሚነት የቆመ፣ የውስጠ ድርጅት ትግል እንዲኖር የጣረ፣ ብቻውን ብዙ ሆዳሞችን ሲታገል የቆየው የኩዩው ጥቁር አለት ዛሬ ከርቸሌ ነው።
አሁን ድርጅት ውስጥ ሀሳብ የለም። የውስጠ ድርጅት ትግል የለም። የዓላማ አንድነት የለም። ዓላማ እራሱ የለም። ጠንካራ ድርጅታዊ አደረጃጀት የለም። ስጋ መቁረጥ እንጂ የስራ ቁርጠኝነት የለም። ከሆድ ውጭ ሌላ የጋራ አጀንዳ የለም። በውሸት ሪፖርት ይሸላለማሉ። ውሸትነቱን እያወቁ በውሸትነቱ ይረካሉ። የጠራ መስመር..የጠራ አይዲዮሎጂ...ብሎ ነገር የለም። የአይዲዮሎጂን መስመር ሳይሆን የሆድን መስመር ይዞ ይነጉዳሉ...ልክ እንደዛ ሳሩን ብቻ እያየ እንደሚሄደው በሬ...ይህ ደግሞ በሬውን ብቻ ከገደል አፋፍ አያደርስም...ሙሉውን የሆድ ለስራ ስብስብን ከነ ድርጅቱ ገደል ልጨምር ይችላል...