አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia

አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia የዚህ ፔጅ የተቋቋመበት አላማ በየቦታው በግፍ እየተሰቃየ ላለው የአማራ ህዝብ እንዲሁም ድምፅ ሚሆናቸው ላጡ ኢትዮጵያዊያን ድምፅ ለመሆን ነው

የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገው ምድር  የአዲሱ  ትውልድ መሪዎች።          1 አርበኛ ስለሺ ከበደ            2 ፋኖ የቆየ ሞላ            3 መቶ አለቃ ማርቆስ አምኜ ...
07/10/2024

የአማራ ፋኖ በጎጃም የጎጃም አገው ምድር የአዲሱ ትውልድ መሪዎች።
1 አርበኛ ስለሺ ከበደ
2 ፋኖ የቆየ ሞላ
3 መቶ አለቃ ማርቆስ አምኜ
4 ፋኖ አዲሱ ፈጠነ
5 ፋኖ ዘመን ተሻለ
6 ሻለቃ አሌ ባይህ
ይህ ዘምን ትግል አብሪ ኮከቦች ናቸው።

አማራ ያሸንፋል በርቱልኝ ወንድሞቼ

በመለስ ዜናዊ ፎርሙላ አማራን የመበታተን እድል ተዘግቷል!"""""""""''''የአገው የክልልነት ጥያቄ ተሰፋ ቢስ ምኞት ነዉ  !!!!"""""""""""""""'""""""'""""''""'"'''...
02/10/2024

በመለስ ዜናዊ ፎርሙላ አማራን የመበታተን እድል ተዘግቷል!
"""""""""''''
የአገው የክልልነት ጥያቄ ተሰፋ ቢስ ምኞት ነዉ !!!!
"""""""""""""""'""""""'""""''""'"'''''''''''''''''''"""""""""'""'''
አርበኛ ስለሽ ከበደ

በህውሃት ተዘርቶ ሊበቅልና ፍሬ ሊያፈራ እንዲሁም ተቦክቶና ተጋግሮ ሊበላ ሲል ከሽፎ አሁን ደግሞ በደቀ መዝሙሩ ኦሮሙማ እንደገና ለመጋገርና ለመበላት የተዘጋጀውን ፕሮጀክት እራሳችሁን በሆዳችሁ የሸጣችሁ የአገው ሸንጎ ተብየዎች እንዳትሞክሩት እንመክራለን።

በዛሬው እለት መስከረም 22-23 ቀን 2017 ዓ. ም በእንጅባራ ከተማ የፌደራል እና የክልል ባለስልጣናት በተገኙበት የአገውን ህዝብ የክልልነት ጥያቄ ህዝቡ ያቀረበ ለማስመሰል ማህበረሰብን በሀይል በመሰብሰብ ለማወያየት እየተሞከረ ነው።

የአገውን ህዝብ ክብርና ታሪክን እንዲሁም ማንነት በማይመጥን አጀንዳ ተጠልፋችሁ ከዚህ በፊት ለመሰሪው ህውሃት አሁን ደግሞ ለስግብግቡ ኦሮሙማ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆናችሁ የምትንቀሳቀሱ እና አሁን ደግሞ እንደ አዲስ በእጅ አዙር ለከርሳችሁ በተመደበላችሁ በጀት ተገዝታችሁ በዚህ ታሪካዊ የትውልድ የዘር መጥፋት አዋጅ ታውጆ ለመትረፍ ትንቅንቅ እየተደረገ ባለበት ወሳኝ ወቅት በሚያሳፍርና ምንም ምክንያታዊ ባልሆነ ወቅት የጠላትን ከፋፋይ አጀንዳ ይዞ ለመንቀሳቀስ መሞከር ከታወቀውና በአደባባይ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ከሚገኘው ጠላት በላይ ሆናችሁ ታሪካዊ ባንደነትን እየፈፀማችሁ እንደምትገኙ ህዝብ እየታዘባችሁ ነው።

አስትዋዩ የአገው ህዝብ በከፍተኛ ስሜት እየታዘባችሁና እያዘነባችሁ እንደሆነ የራሳችሁ ህሌና እየወቀሳችሁ እንደሚገኝ እርገጠኞች ነን። አጀንዳው ከየት እንደተነሳ፤ ለማስፈፀሚያ የሚውለው የበጀት ምንጭና የባንዳነት እንቅስቃሲያችሁ ለእናንተ ምስጢር ቢመስላችሁም እያንዳንዷ እንቅስቃሴ የከዳችሁት ህዝብ ከዘር መጥፋት ጥቃት ሲተርፍ ነገ በታሪክ አደባባይ የሚፋረዳችሁ ይሆናል።

የአገው ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ ላይ የማይደራደር : የታሪክ ጥያቄ ውስጥ እንግባ ከተባለም የኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የቀዳሚነቱን ድርሻ የሚወስድ ነው:: የአማራ እና የአገው ህዝብ ለፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን በሀቅ እና በታሪክ ፊት የሚገለፅ አንድነት እና ሁለትነት ያለው ህዝብ ነው:: የምታተርፉት ትዝብትን ብቻ ነው:: ሁለቱን ህዝብ መለዬት ፀጉር የመሰንጠቅ ያህክል ከባድ ነው:: እንጭጩ አብይ አህመድ ከዚህ የተሻለ ማሰብ ስለማይችል እንጅ የፋኖ ትግል መነሻው የአገውም የአማራውም የህልውና ጥያቄ ነው:: መፍትሔውም ጥያቄውን መመለስ ብቻ ነው::

ትግላችን ትእግስትን፤ ትህትናን፤ ቂም አልባነትን፤ ንስሃን ቅድሚያ ሰጥቶ በሆደ ሰፊነት አጥፊዎችን በትናን ጥፋት የሚፋረድ ባለመሆኑ በአሁኑ ሰአት መላው ህዝባችን እራሱን ከመጥፋት ለማትረፍ እልህ አስጨራሽ ትግል እያደረገ ባለበት ታሪካዊ የህልውና ትግል ዋጋ አልባና ጭራሽ አሁን ካለንበት ነባራዊና ህልውናዊ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም የጠላት አጀንዳ አስፈፃሚ ፊት አውራሪ ሆኖ መገኘት በስዋዊ ብቻ ሳይሆን በመንፈሳዊው አለምም ከተጠያቂነት አታመልጡም።

ትናንት ጠፍጥፎ ከፈጠራችሁ ህወሃት ትምህርት ሳትወስዱ በዚህ እጅግ ወሳኝ በሆነ የህልውና ትግል ወቅት ለስጋ ህይወታችሁና ለጥፋት በተመደበላችሁ ማታ ተበልቶ ለጧት ቁርስ በማይተርፍ ፍርፋሪ ጥቅም ህሌናን ሽጦ ለሆድ አድሮ የባንዳነት ተልእኮ ላይ ከመሳተፍ በላይ ምን ውርደት ይኖራል?

ስለሆነም አጀንዳው ከየት እና ለምን እንደተሰጣችሁ፤ ለዚሁ የጥፋት አጀንዳ ማስፈፀሚያ የሚውለው የበጀት ምንጭና በምን መልኩ እየተለቀቀላችሁ እንደሆነ እንዲሁም ለህልውናው ሲል መስእዋትነት እየከፈለ የሚገኘውን ጀግና እና አርቆ አሳቢ የሆነውን ህዝብ ለማታለል የተለያዬ ካባ ለብሳችሁ የተለያዬ አጀረጃጀትና ስልት ቀይሳችሁ እየተንቀሳቀሳችሁ እንደሆነ በትኩረት ስንከታተላችሁ ቆይተናል።

ከአሁን በኃላ ድርጊታችሁ እንደተነቃበት አውቃችሁ ሙሉ በሙሉ ከባንዳነት ተግባራችሁ ተመልሳችሁ ከገባችሁበት ሆድ አደር እኩይ እንቅስቃሴያችሁ ወጥታችሁ በጥልቀት እየታዘባችሁ የሚገኘውን ህዝብ ይቅርታ ጠይቃችሁ ከስህተታችሁ እንድትመለሱ የመጨረሻ ጥሪያችንን ስናቀርብላችሁ ለመላው ህዝባችን ያለንን ክብር በመጠበቅ ነው። ሆዳችሁ ሸፍኗችሁ፤የተመደበላችሁ በጀት አስጎምጅቷችሁ ህዝባችሁን ለእኩይ አላማ ከመሸጥና የባንዳነት ተግባራችሁ ካልተመለሳችሁ ከዚህ በፊት በተግባር እንዳደረግነው ከጠላት በላይ ጠላት እንደሆናችሁ ተቆጥሮ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆናችንን እንገልፃለን!!!
አዲስ ትውልድ!
አዲስ አስተሳሰብ!
አዲስ ተስፋ !!።

ደረሰ 25_08_2024
16/08/2024

ደረሰ 25_08_2024

ጋዜጠኛ መላኩ

የሽምቅ ውጊያን አስመልክቶ በትግል ሜዳ በተግባር የተፈተነ በልምድና በእድሜም የበሰለ ሰው የጻፈው እንጂ አንድ ጀማሪ ወጣት የጻፈው አይመስልም። መጽሐፉን ኤዲት እንዳደርገው ደራሲው ሲሰጠኝ አሰልቺ መስሎኝ ፈጣሪ ሆይ ትዕግስቱን ስጠኝ ብዬ ገጽ አንድ ሁለት እያልኩ ማርተዕ ስጀምር ባስገራሚ ሁኔታ ሌሊቱን ቁጭ አስብሎ የሚያሳድር መሳጭ መጽሐፍ ሁኖ አግኝቼዋለሁ። ሙያየ ስለሚያስገድደኝም ጭምር ብዙ አርቲክሎችን እንዲሁም መፅሐፍትን በየግዜው አገላብጣለሁ ይሄ መፅሐፍ ግን ከረጅም ግዜ በዃላ በይዘቱ ለየት ያለ መፅሐፍ ግሩም የሆነ ሂወት ያለው መፅሀፍ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ደራሲ ወጣት የፖለቲካ ተንታኝ ያሬድ ብርሀኑን ሳላደንቅ አላልፍም።

መልካም ንባብ

25_08_2024 ሁላችሁንም ወዳጅ ዘመድ  መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በክብር ተጋብዛችኋል ።
12/08/2024

25_08_2024 ሁላችሁንም ወዳጅ ዘመድ መላው አማራ እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በክብር ተጋብዛችኋል ።

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች ፩ አስረስ ማር ዳምጤ የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢና የፓለቲካ ዘርፍ መምሪያ ኃላፌ፪ ፋኖ እሸቱ ጌትነት የአማራ ፋኖ በጎጃም የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ...
09/08/2024

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች

፩ አስረስ ማር ዳምጤ የአማራ ፋኖ በጎጃም ም/ሰብሳቢና የፓለቲካ ዘርፍ መምሪያ ኃላፌ፪ ፋኖ እሸቱ ጌትነት የአማራ ፋኖ በጎጃም የአደረጃጀት መምሪያ ኃላፊ ፫አርበኛ ፋኖ ስለሺ ከበደ የአደርጃጀት ም/ኃላፊ

07/08/2024

የተከበራችሁ ውድ አማራዊያን እና እውነተኛ ኢትዮጵያዊያን፣
ትንሳኤ ናፋቂው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሚል ርዕስ በሊቀመንበራችን አቶ ያሬድ ብርሀኑ (ያያ) ተፅፎ ግሩም ተደርጎ የአለምን ታሪክ ከሽምቅ ትግል እስከ ሰላማዊ ትግል እንዲሁም ሀገረ መንግስት ምስረታን በድንቅ አለማቀፍ እውነቶችን ከወቅታዊው የአማራ ህዝብ ትግል ጋር ተጣቅሶ ትውልድ እንዲማርበት እንዲሁም አንድ ንፁህ ሀገር ሁሉን እኩል የምታይ ሀገርን መገንባት ለሚሻ ኢትዮጵያዊ ሁሉ የሚሆን ፍንትው ያለ መውጫ መንገዱንም ከአለም ታሪክ በመማር በተለያየ ግዜ የተደረጉ ሁነቶችን በመገምገም አሳምሮ ይዞልን ቀርቧል።

ይሔ መፅሀፍ በ ኦገስት 25_08_2024 ኬሲንግቶን በሚገኘው 160 langerman Dri. Kensington.
Church of Scientology አዳራሽ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ከተለያየ ቦታ በስካፕ በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል።

ሁላችሁንም በአክብሮት የጋበዝን መሆኑን በትህትና እንገልፃለን ።

ጋባዥ አዘጋጅ ኮሚቴው

አማራማ መሪ አለው ወዳጀ ጎጀ መለኛው
03/08/2024

አማራማ መሪ አለው ወዳጀ
ጎጀ መለኛው

03/08/2024

የአማራ ህዝብ አብዩት የጀመረበት ዝክረ ሰማእታት የ1ኛ ክፍለ ጦር የኮረኔል ታደስ ብርጌድ ዝክረ በዓል

የአማራ ፋኖ በጎጃም

Address

Johannesburg

Telephone

+27781380526

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አማራ ታሪኩን በልጆቹ ይፅፋል _Ethiopia:

Videos

Share