21/06/2024
የሃጂ ጉዞ ካደረጉ እስልምና እምነት ተከታዮች ብያንስ 577 ሰዎች መሞታቸው ታወቀ
************************************************
በዘንድሮው ሃጂ ጉዞ ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተካታዮች የተሳተፉበት ብሆንም በሳውዲ አረቢያ መካ ከተማ ባጋጠመው አየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ብያንስ 577 ሰዎች ሞተዋል።
መካ ከተማ መጠኑ 51.8 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የሆነ ሙቀት መከሰቱም የታወቀም ስሆን፣ በዚሁ ሳቢያ ከሞቱት ውስጥ ቢያንስ 323ቱ ግብጻውያን መሆናቸውንም የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል።
ከመጠን በላይ የሆነው ሙቀት ባስከተለው ጉዳት፣ ብዙን ቁጥር ከያዙ ግብፃዋውያን ሟቾች በተጨማሪ፣ 23 የቱኒዚያ ዜጎች እና አምስት የሞሮኮ ዘጎች ህይወትም አልፏል።
እንዲሁም ሶስት የሴነጋል ዜጎች እና ሁለት ናይጄሪያውያንም በዚሁ ሙቀት ምክንያት መሞታቸውን የዘገበው ዜና ወኪሉ፣ ከ577 ሟቾች ውስጥ በስኳር ህመም እና በደም ግፊት የመሳሰሉ ሥር በሰደዱ በሽታዎች የተጠቁ መኖራቸውንና ይህም ከሙቀቱ ጋር ተጨምሮ ለሕልፈት እንደዳረጋቸውም ታውቋል።
የዘንድሮው ሃጂ ጉዞው ፍጻሜውን ያገኘው ባለፈው ሰኞ ስሆን በታሪኩ ያልታየው መቁት የገጠመውና ብዙዎችን ለሕልፈት የዳረገው በዚሁ ዓመት ነው።
mail.com