ZumraTube ዙምራቲዩብ

ZumraTube  ዙምራቲዩብ ZumraTube is the best Ethio-Canadian infotainment media. We provide with multidimensional access to the information and entertainment that matters to you.

ZumraTube is a world media sharing site. Get up to date Tv shows, Dramas, Music clips, Movies and News from ZumraTube.

 አህያው ዛፍ ስር ታስሮ ነበር። በአጋጣሚ ሰይጣን መጣና አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ለቀቀው። አህያውም ወደ ማሳው እየሮጠ ገብቶ ሰብሉን ማውደም ጀመረ። ይህን ያየችው የገበሬው ሚስት አህያውን ...
12/08/2024



አህያው ዛፍ ስር ታስሮ ነበር። በአጋጣሚ ሰይጣን መጣና አህያውን ከታሰረበት ፈቶ ለቀቀው። አህያውም ወደ ማሳው እየሮጠ ገብቶ ሰብሉን ማውደም ጀመረ።

ይህን ያየችው የገበሬው ሚስት አህያውን በጥይት መታችው። የአህያው ባልተቤት ተበሳጨና የገበሬውን ሚስት ገደላት። ገበሬው መጣና ሲያይ ሚስቱ ሙታለች። ወዲያው አጸፋውን መለሰና የአህያውን ባለቤት ተኩሶ ገደለው።

የአህያው ባልተቤት ሚስት ልጆቿን ጠራችና የገበሬውን ቤት እንዲያቃጥሉ አዘዘቻቸው። ልጆቹም አመሻሹ ላይ እናታቸው ያዘዘቻቸውን ለመፈጸም ገበሬውም በውስጥ ሲቃጠል እያሰቡ በደስታ ሄዱ። ወዲያውም ቤቱን አቃጥለው ተመለሱ። እንዳጋጣሚ በሚያሳዝን ሁኔታ ገበሬው እቤት አልነበረምና ተመልሶ መጥቶ የአህያውን ባልተቤት ሚስትና ልጆቹን ገድሎ ተመለሰ።

ሲመለስ ግን ሰይጣንን መንገድ ላይ ያገኘዋል። ገበሬው ትንሺ ሰከን ሲል የሆነውን አስታውሶ ነበርና ሰይጣንን ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ይጠይቀዋል? ሰይጣንም እንዲህ አለ፦ እኔ ምንም አልሰራሁም። አህያውን ብቻ ነው የፈታሁት። ግን ሁላችሁም የውስጣችሁን ሰይጣን ፈታችሁት። ሁሉንም ነገር ያደረጋችሁት እራሳችሁ ናችሁ።

ሌላ ጊዜ ለምንም ነገር ምላሺ ከመስጠታችን ፣ ውሳኔወችን ከማሳለፋችን በፊት ለአፍታ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል። ብዙጊዜ ሰይጣን የሚያደርገው ውስጣችን ያለውን አህያ መልቀቅ ነው። "በአለም ላይ ትልቁ ባለስልጣን እራሱን የሚቆጣጠር ነው!"

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ!በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ ...
12/08/2024



ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ!

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።

ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታውቋል።

:- አዲስ አበባ ፖሊስ

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 የዌስትሃም አጥቂ ሚሼል አንቶኒዮ ከባድ የመኪና  አደጋ አጋጥሞታል። አደጋው ሲደርስ ቤተሰቦቹ መኪና ውስጥ ነበሩ። ተጫዋቹ እና ቤተሰቦቹ ያሉበት ሁኔታ ከባድ በመሆኑ ሁሉም ፀሎት እንዲያደርግ...
12/08/2024



የዌስትሃም አጥቂ ሚሼል አንቶኒዮ ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሞታል። አደጋው ሲደርስ ቤተሰቦቹ መኪና ውስጥ ነበሩ።

ተጫዋቹ እና ቤተሰቦቹ ያሉበት ሁኔታ ከባድ በመሆኑ ሁሉም ፀሎት እንዲያደርግለት ክለቡ ዌስትሀም ጥሪውን አቅርቧል።

:- እጅግ አስተማሪ ታሪኮችና ጽዕሁፎች ፔጅ

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ስፔናዊው የባርሴሎና አጥቂ ላሚኒ ያማል ስለቤተሰባዊ ህይወቱ ሲናገር ...ህልሜን እየኖርኩ ነው የወደፊቱ እንዳለ ሆኖ በዚህ በ17 አመቴ ከመቶ ሚሊየን ዶላር በላይ ማግኘት ያስቻለ የእግር ኳ...
12/06/2024



ስፔናዊው የባርሴሎና አጥቂ ላሚኒ ያማል ስለቤተሰባዊ ህይወቱ ሲናገር ...

ህልሜን እየኖርኩ ነው የወደፊቱ እንዳለ ሆኖ በዚህ በ17 አመቴ ከመቶ ሚሊየን ዶላር በላይ ማግኘት ያስቻለ የእግር ኳስ ጥበብ እሱን ተከትሎም ታዋቂነትንና ዝናን እንዲሁም ተወዳጅነትን በማትረፌ ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ ሰወች ከኔ ጋር ፎቶ ሊነሱ በቪዲዮ ሊቀርፁኝ ሌላው ቀርቶ በአካል ቀርበው እኔን ሰላም ማለት ሁሉ ይፈልጋሉ።

ይህ ነገር ሲበዛ ምቾት የሚነሳ ነገር ቢሆንም ሰወች ለእኔና ለምጫወትበት ክለብ ለባርሳ ካላቸው ፍቅር የተነሳ መሆኑን ስለምረዳ ብዙም አልከፋም።

ይህ እንግዲህ ከቤት ውጭ ያለ ታሪኬ ነው ።

ቤት ውስጥስ? 😄
ቤት ውስጥማ እኔ ምንም ነኝ ከቤት ውጭ ያ ሁላ ሰው ከኔ ጋር ፎቶ ለመነሳትና እኔን ለማስፈረም የሚሯሯጥልኝ እኔ ላሚኒ ያማል ቤት ስደርስ ልብሴን ቀያይሬ የበላንበትን ሰሀኖች ማጠብ ክፍሌን ማፅዳት ሁሉ ይጠበቅብኛል።
.. ይልና ፈገግታ በተሞላበት ሁኔታ ንግግሩን ሲቀጥል ...

ይህንን የቤት ስራዬን ከጨረስኩ ነው የምወደውን የኳስ ጌም እንድጫወት የሚፈቀድልኝ። እዚህ ላይም ብዙ ሰአት ጌም ላይ ከቆየሁ እናቴ መጥታ ትጮህብኛለች። የኔ ዝናና ታዋቂነት ከቤት ውጭ ነው።

በማለት ነበር ለሚወዳት እናቱ እስካሁንም ድረስ ያላንዳች ማንገራገር ታዛዥ እንደሆነ የተናገረው።

:- Wasihune Tesfaye

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ለጉልበት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚያስፈልገውን 3 ሚሊየን ብር አገኘ ትናንት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ በተዘጋጀው ”ነፃነ...
12/06/2024



ሠዓሊ ብሩክ የሺጥላ ለጉልበት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚያስፈልገውን 3 ሚሊየን ብር አገኘ

ትናንት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በሸራተን አዲስ ሆቴል ላሊበላ አዳራሽ በተዘጋጀው ”ነፃነት“ የስዕል አውደርዕይና ጨረታ ሽያጭ ለህክምና የሚያስፈልገውን ወጪ ሙሉ በሙሉ ማግኘት መቻሉን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

በኹነቱ ላይ ጓደኞቹ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በብሩክ የሺጥላ የቀረቡ የእጅ ስራ የጥበብ ውጤቶችን በጨረታና በመደበኛ ግዢ በመፈፃም ወጪው እንዲሳካ ማድረጋቸው ታውቋል።

በተለይ አንድ ማንነታቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ደግ ልብ ያላቸው ግለሰብ ከፍ ያለ ድጋፍ በማድረግ ብሩክንም ሆነ በአዳራሹ የታደሙ እንግዶችን አስደስተዋል፡፡

ሰዓሊ ብሩክ የሺጥላ በበኩሉ ህክምናው እንዲሳካ ላደረጉት ሁሉ ምስጋናውን አቅርቦ አጠቃላይ ዝግጅቱ የተሳካ በመሆኑ መደሰቱን አስታውቋል፡፡

የህክምና ወጪው እንዲሳካ በማድረግ እገዛ ላደረጉለት ተቋማትና ግለሰብ የምስጋና ስጦታ አበርክቷል፡፡

በጨረታ ከቀረቡት የስዕል ስራዎቹ መካከል
ይቅርታ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ ምስጋና፣ ሰኔ 30 እና ጦርነትን ማብቃትና ሌሎችም ተጠቃሽ ናቸው፡፡

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ''ከባለሀብቶችና ኤምባሲዎች ጋር በመነጋገር  ገቢ አመጣለው'' ተዋናይነት ማስተዋልአዲሷ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ማስተዋል ወንደሰን ከምርጫው በኋላ ለአዲስ ሚዲ...
12/06/2024



''ከባለሀብቶችና ኤምባሲዎች ጋር በመነጋገር ገቢ አመጣለው'' ተዋናይነት ማስተዋል

አዲሷ የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ማስተዋል ወንደሰን ከምርጫው በኋላ ለአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋዜጠኛ ዮናስ ሞላ ሀሳቧን ሰጥታለች።

በጣም ደስ ብሎኛል አልጠበኩም ነበር ያለችው ተዋናይነት ማስተዋል አዲስ አበባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መስራች እንደመሆኗ አሁን ያለችበት ሁኔታ ደስ አይልም ብላለች።

ዋና ከተማ ላይ በርካታ ኤምባሲዎች አሉ እኔ ከነሱና ባለሀብቶች ጋር በመነጋገር ጥሩ ገቢ በመነጋገር ለማምጣት እጥራለው ስትል ተደምጣለች።

በአለም ላይ ከ4 ቢሊዮን በላይ ተከታታይ ያለው የስፖርት አይነት በመሆኑ ሁሉም ይደግፈኛል ሁላችንም ይወክላል ፣ሴቶችንም እናበረታታለን ይደግፉናል ስትል ከምርጫው በኋላ አስተያየት ሰጥታለች።

:- AMN

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ሁለቱ እውቅ አርቲስቶች በእግር ኳስ አመራርነት ተመረጡ።የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን ዛሬ አዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጧል። በፕሬዝዳንትነት የቀድሞውን አልቢትር ኢንጂነር ሀይለየሱስ ፍሰ...
12/05/2024



ሁለቱ እውቅ አርቲስቶች በእግር ኳስ አመራርነት ተመረጡ።

የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን ዛሬ አዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጧል።

በፕሬዝዳንትነት የቀድሞውን አልቢትር ኢንጂነር ሀይለየሱስ ፍሰሃን መርጧል። ለፕሬዚዳንትነት ከድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የባንኮች ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ከነበረው አንተነህ ፈለቀ ብርቱ ፏክክር እንደገጠማቸው ተነግሯል።

9 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያካተተው ምርጫው በምክትል ፕረዚዳንትነት ተዋናይነት ማስተዋል ወንደሰንን መርጧል።

አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ደግሞ በአቃቤ ነዋይነት መመረጧን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል።

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ

:- Maraki Sport Ethiopia



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

አረ ባክህ..... 🤣
12/04/2024

አረ ባክህ..... 🤣

 የጉድ ሀገር !! የወሲብ ንግድ በአደባባይ እንደስራ መታየት ጀምሯል ! ቤልጂየም በሰኔ ወር 2024 የወሲብ ንግድን እንደ ማንኛውም የስራ ዘርፍ በህጋዊ መንገድ መስራት እንዲቻል ፈቅዳለች፡፡...
12/04/2024



የጉድ ሀገር !!

የወሲብ ንግድ በአደባባይ እንደስራ መታየት ጀምሯል !

ቤልጂየም በሰኔ ወር 2024 የወሲብ ንግድን እንደ ማንኛውም የስራ ዘርፍ በህጋዊ መንገድ መስራት እንዲቻል ፈቅዳለች፡፡

ሀገሪቱ ዜጎች ወደ ወሲብ ንግድ ለመግባት ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ መያዝን እንደ መስፈርት ያስቀመጠች ሲሆን ህጉ መጽደቁ በድብቅ ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦችና ተቋማትን ማስደሰቱ ተገልጿል።

በዚህ ህግ በወሲብ ንግድ የተሰማሩ ሰዎች አገልግሎቱን ለደንበኞቻቸው ለመስጠት ከተቋቋሙ ድርጅቶች እና ፈላጊዎች ጋር መዋዋል እንዲችሉ ተፈቅዶላቸዋል፡፡

ብራሰልስ አሁን ደግሞ በዚህ ስራ የተሰማሩ ዜጎች እንደ ማንኛውም ሰራተኛ የጡረታ፣ የጤና ደህንነት ክፍያ፣ ዓመታዊ እረፍት፣ የህመም እና የወሊድ ፈቃድ ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዳለች፡፡



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 በቅርቡ ከኦሮሚያ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙትየኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከፍተኛ አባላቶች ፒያሳ የሚገኘው የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ጎበኙ። ለተጨማሪ መረጃ 👇https://t.me/...
12/04/2024



በቅርቡ ከኦሮሚያ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የተፈራረሙት

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከፍተኛ አባላቶች ፒያሳ የሚገኘው የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ጎበኙ።



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ሴት በመምሰል የወሲብ ንግድ ከሚሰሩ ሴቶች  ጋር በመሆን እየዘረፈ ሲሰወር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለበደብረ ማርቆስ ከተማ መኳንት ናጋ የተባለው የ18 ዓመት ወጣት  የወሲብ ንግድ ...
12/03/2024



ሴት በመምሰል የወሲብ ንግድ ከሚሰሩ ሴቶች ጋር በመሆን እየዘረፈ ሲሰወር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በደብረ ማርቆስ ከተማ መኳንት ናጋ የተባለው የ18 ዓመት ወጣት የወሲብ ንግድ ከሚሰሩ ሴቶች ጋር በመመሳሰል ሲዘርፍ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ።

ግለሰቡ ቀበሌ 08 በአብማ አካባቢ ሴት በመምስል ማታ የወሲብ ንግድ ከሚሰሩ ሴቶች ጋር አብሮ በመሆን ገንዘብ በመቀበል ከአካባቢው በመጥፍት በተደጋጋሚ የወንጀል ድርጊት ሲፈጽም የነበረው ግለሰብ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር መዋሉን ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ሴት ይመስላል ግን? ወይስ ከጨለመ ወንዱም ሴት መስሎ ይታያቸዋል?



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ይህ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት የሊቨርፑል ደጋፊ ከሞላ ጎደል ሁሉም የአንፊልድ ጨዋታዎች አያመልጡትም ታዲያ የሚያስገርመው ጨዋታዎቹን መከታተሉ ሳይሆን ማየት የተሳነው መሆኑ ነው ነገር ግን አ...
12/02/2024



ይህ ምስሉ ላይ የምትመለከቱት የሊቨርፑል ደጋፊ ከሞላ ጎደል ሁሉም የአንፊልድ ጨዋታዎች አያመልጡትም ታዲያ የሚያስገርመው ጨዋታዎቹን መከታተሉ ሳይሆን ማየት የተሳነው መሆኑ ነው ነገር ግን አይኑ የሚደረገውን ማየት ባይችልም አብሮት ሜዳ የሚገኘው ጓደኛው ምን እየተፈጠረ እንዳለ በድምፅ ፍንትው አድርጎ ይነግረዋል።

ድንቅ የክለብ ፍቅር ድንቅ ጓደኛ❤️👏

:- እግር ኳስ አለም



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 አቶ ታዬ ደንደአ በ20 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ!የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል የካቢኔ አባል አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ መወሰኑን ባለቤታቸው ሲንትያ አ...
12/02/2024



አቶ ታዬ ደንደአ በ20 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ!

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል የካቢኔ አባል አቶ ታዬ ደንደአ በዋስ እንዲለቀቁ መወሰኑን ባለቤታቸው ሲንትያ አለማየሁ ለቢቢሲ ተናገሩ።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔውን ያሳለፈው ዛሬ ሰኞ፣ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በነበረው ችሎት ነው።

:- BBC AMHARIC



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ "የፕሪቶሪያው ስምምነት ኤርትራን አይመለከታትም" አሉየኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2024 ዓ.ም ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፣...
12/01/2024



ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ "የፕሪቶሪያው ስምምነት ኤርትራን አይመለከታትም" አሉ

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2024 ዓ.ም ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ደም አፋሳሹ የሰሜኑን ኢትዮጵያ ጦርነት ለማስቆም የተደረሰው የፕሪቶሪያዉ ስምምነት አገራቸውን እንደማይመለከት ነው የተናገሩት።

ፕሬዚዳንቱ ኤርትራ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ከሚሰሩ አገራት ጋር ትሰራለች መባሉንም አስተባብለዋል።

:- ባላገሩ ቴሌቪዥን



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ ሆኗል።የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ በመሆን ልዩ ዋንጫ ፣ አንድ ሚ...
12/01/2024



የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ ሆኗል።

የኢትዮጵያ አይዶል የዓመቱ ኮከብ የፍፃሜ ውድድር አሸናፊ ዮሐንስ አምደወርቅ በመሆን ልዩ ዋንጫ ፣ አንድ ሚሊዮን ብር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ነፃ የትምህርት እድል አሸናፊ ሆኗል።

2ኛ ሚኪያስ ጌቱ

3ኛ ማቲያስ አንበርብር

4ኛ ብዙአየሁ ሰለሞን

ውጤቱ የ2 ዙር የዳኞች ውጤት እና ተመልካቾች በ8600 በፅሁፍ መልእክት የሰጡት ድምፅ ተደምሮ ነው አሸናፊው የተለየው።



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

 ስፔናዊው የባርሴሎና አጥቂ ላሚኒ ያማል ስለቤተሰባዊ ህይወቱ ሲናገር ....ህልሜን እየኖርኩ ነው የወደፊቱ እንዳለ ሆኖ በዚህ በ17 አመቴ ከመቶ ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ማግኘት ያስቻለ የእግር...
12/01/2024



ስፔናዊው የባርሴሎና አጥቂ ላሚኒ ያማል ስለቤተሰባዊ ህይወቱ ሲናገር ....

ህልሜን እየኖርኩ ነው የወደፊቱ እንዳለ ሆኖ በዚህ በ17 አመቴ ከመቶ ሚሊየን ዶላር ገንዘብ ማግኘት ያስቻለ የእግር ኳስ ጥበብ እሱን ተከትሎም ታዋቂነትንና ዝናን እንዲሁም ተወዳጅነትን በማትረፌ ባለፍኩበት መንገድ ሁሉ ሰወች ከኔ ጋር ፎቶ ሊነሱ በቪዲዮ ሊቀርፁኝ ሌላው ቀርቶ በአካል ቀርበው እኔን ሰላም ማለት ሁሉ ይፈልጋሉ።

ይህ ነገር ሲበዛ ምቾት የሚነሳ ነገር ቢሆንም ሰወች ለእኔና ለምጫወትበት ክለብ ለባርሳ ካላቸው ፍቅር የተነሳ መሆኑን ስለምረዳ ብዙም አልከፋም።

ይህ እንግዲህ ከቤት ውጭ ያለ ታሪኬ ነው።

ቤት ውስጥስ 😄 ቤት ውስጥማ እኔ ምንም ነኝ ከቤት ውጭ ያ ሁላ ሰው ከኔ ጋር ፎቶ ለመነሳትና እኔን ለማስፈረም የሚሯሯጥልኝ እኔ ላሚኒ ያማል ቤት ስደርስ ልብሴን ቀያይሬ የበላንበትን ሰሀኖች ማጠብ ክፍሌን ማፅዳት ሁሉ ይጠበቅብኛል።
..ይልና ... ፈገግታ በተሞላበት ሁኔታ ንግግሩን ሲቀጥል

ይህንን የቤት ስራዬን ከጨረስኩ ነው የምወደውን የኳስ ጌም እንድጫወት የሚፈቀድልኝ። እዚህ ላይም ብዙ ሰአት ጌም ላይ ከቆየሁ እናቴ መጥታ ትጮህብኛለች። የኔ ዝናና ታዋቂነት ከቤት ውጭ ነው።

በማለት ነበር ለሚወዳት እናቱ እስካሁንም ድረስ ያላንዳች ማንገራገር ታዛዥ እንደሆነ የተናገረው።

:- Wasihune Tesfaye



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

  ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ። አንደኛው ማየት አይችልም። እናትና አባቶቻቸው ከሞቱባቸው ሰነባብተዋል። ቤት ውስጥ የሚኖሩት ሁለታቸው ብቻ ናቸው። ዓይኑ የሚያየው ልጅ በወንድሙ ይማረራል እስከመ...
11/30/2024





ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ። አንደኛው ማየት አይችልም። እናትና አባቶቻቸው ከሞቱባቸው ሰነባብተዋል። ቤት ውስጥ የሚኖሩት ሁለታቸው ብቻ ናቸው። ዓይኑ የሚያየው ልጅ በወንድሙ ይማረራል እስከመቸ ነው አንተን እየመራሁ የምኖረው ት/ት ቤት ስትሄድ መፀዳጃ ቤት ስትሄድ... እስከመቸ እያለ ያማርራል።

እሱም ተው እንጂ ወንድሜ እንደዚህ አትበል ማየት የማትችለው አንተ ብትሆንስ! ይሄ የፈጣሪ ፍቃድ ነው እኔ ፈቅጄ አላደረኩትም ይለዋል። እንደዚህ ስላለው ይበሳጭና ይገፈትረው እና ይወድቃል። እንዲህ እዲህ እያለ ብዙ ዘመናትን ኖሩ፡፡ ከእለታት በአንዱ ቀን ካሁን ብኋላ ይበቃኛል ራቅ ወዳለ ቦታ ጥየው እመጣለሁ እንጂ ከሱ ጋር ... ብሎ ያስባል።

እንዳሰበውም አልቀረም አንድ ቀን ወንድሜ አለው ማየት የማይችለው በጣም ደስ አለው ምክንያቱም ወንድሜ ብሎ ጠርቶት ስለማያውቅ። ሰውን ለመጉዳት አንዳንድ ሰወች ደግ ይሆኑ የለም ወንድሜ አለው። ደስ የሚል ቦታ እወስድሀለሁ አለው ያልገባው እሱም እሸ አለው፡፡

ራቅ ወዳለ ቦታ ይዞት ሄደና ከዛፍ ስር አስቀምጦት መጣሁ ብሎት ይሄዳል። ማንንም በማያውቅበት በዚያን ቦታ ተቀምጦ እራሱን እያወዛወዘ ወንድሙን ይጠብቃል። ብዙ ስዓት ተቀመጠ ግን አልመጣም። ተጨነቀ ወንድሜ ምን ሆኖ ይሆን እያለ ማልቀስ ጀመረ። አከባቢውን በሚረብሽ ድምፅም ወንድሜ ወንድሜ ... እያለ ይጣራል ግን ከቦታው የለም።

ክፋተኛው ወንድሙ ኡፍ ተገላገልኩ እያለ በደስታ ወደ ቤቱ ይመለሳል። ቤት እንደደረሰ በሩን ከፍቶ ሲገባ ሌቦች ያገኙትና ይገድሉታል። ወንድሙን የጎዳ ቢመስለውም ግን ወንድሙን ከሞት አድኖታል። ክፋት ምንጊዜም ለራስ ነው። እንዲሁም ደግነትም ለራስ ነው።

👉 ፔጁን ሼር ላይክ በማድርግ ቤተሰብ ይሁኑ

:- እጅግ አስተማሪ ታሪኮችና ጽዕሁፎች ፔጅ



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

  ?? ወንድሙ ተጨንቋል‼️ይህ ወጣት   ይባላል! አባት ያለ እናት በመከራ አሳድጎትና አስተምሮት ከ5ዓመታት የሀረማያ ዩንቨርስቲ ቆይታው በኋላ በFood Engineering ከፍተኛ ውጤት አም...
11/29/2024



?? ወንድሙ ተጨንቋል‼️

ይህ ወጣት ይባላል! አባት ያለ እናት በመከራ አሳድጎትና አስተምሮት ከ5ዓመታት የሀረማያ ዩንቨርስቲ ቆይታው በኋላ በFood Engineering ከፍተኛ ውጤት አምጥቶ በ2014ዓ.ም ተመረቀ!!

የደከመለት አባቱን ለመካስ ጓጉቶ ስራ ፍለጋ በብዙ ቢንከራተትም የሚቀጥረው ድርጅት ስላላገኘ ኑሮ ለማሸነፍ ምዕራብ ሀረርጌ በዴሳ ላይ ፑል ማጫወት ይጀምራል! ግን አልሆነለትም! አልተሳካለትም!!

ጎበዙ ንዋይ ብስጭት፣ ድብርትና ጭንቀት ሲጫጫነው ወደ አዲስአበባ ታላቅ ወንድሙ ጋር ለማረፍና ያገኘውን ስራ ለመሞከር መጥቶ ብዙ CV አስገብቷል! በየቀኑ በጠዋት እየወጣ የተለያዩ ቦታዎች ደጅ ይጠናል!!

ህዳር13 እንደተለመደው አለምባንክ አንፎ ድልድይ አካባቢ ከሚገኘው ወንድሙ ቤት በጠዋት ይወጣል!

በየሰዓቱ እየደወለ ቼክ የሚያደርገው ታላቅ ወንድሙ መብራቴ ወደ ሞባይሉ ሲደውል"የደወሉላቸው ደንበኛ ቴሌፎን ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም"የሚል መልዕክት ሲሰማ ፈራ፣ ደነገጠ "ያለወትሮ ልቤ ተረበሸ" አለ! ደጋግሞ ቢደውልም መልስ አጣ!

ወደ ቤት ሲመለስም እንደፈራው ታናሽ ወንድሙን አጣው! ቁልፉን ብቻ አገኘው!ያለፉትን 8ቀናትም ወንድም መብራቴ ለፍለጋ በለቅሶና በመንከራተት ላይ ይገኛል!! "እባካችሁን ወንድሜን አፋልጉኝ" ይለናል!!

የሚያሳዝነው ኢንጅነር ንዋይ ምን ሆኖ ነው? #ሼር በማድረግ እንፈልገው🙏

ስልክ:- 0948127084

"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
:- ባይሽ ኮልፌ በጎ አድራጎት



ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://t.me/zumra_tube

Address

West

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ZumraTube ዙምራቲዩብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ZumraTube ዙምራቲዩብ:

Share

zumratube

"የሴት ሥራ በመስራቴ የተቀየረው መሃይምነቴ እንጂ ወንድነቴ አይደለም"

እኝህን ያለጊዜያቸው የተፈጠሩ ሊቅ አለማድነቅ አይከብድም?

Nearby media companies