
01/29/2025
አይሞሎ!
ለፈንዞ ጌታ ለጥርኝ ጌታ ይድረሰ ሰላምታ!
እንኳን ለ85ኛ የአገው ፈረሰኞች ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!
ዓመቱን ጠብቆ ብቅ የሚለውን ያሸበረቀ፣ የደመቀ ፣ አስደማሚ እና ለአይን ማራኪ የሆነውን ዓመታዊ በዓልን ፣ የፈረሰ ትርኢቱን ፣ የወንዶችን እና የሴቶችን ሽምጥ ግልቢያ ከባለ ታሪኩ ከደጋግ የአዊ ህዝብ ጋር በእንጅባራ ከተማ ተገኝቶ ማሳለፍ ምን ያህል ደስታ እንደሚሰጥ ያየሰው ይመስክር!
በበዓሉ ለመታደም እድሉ የገጠማችሁ እንግዶች፣ ምንኛ ታድላችሗል!
በፈጣሪ ፈቃድ ለከርሞ በሰላም ያገናኘን።
መልካም በዓል ይሁንላችሁ!
ይሁኔ በላይ