WE Ethiopians

WE Ethiopians የመንግስት ዋነኛው ተግባር የዜጎች ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ነው !!
ይህንን ተግባር የማያከናውን መንግስት እንደ መንግስት አይቆጠርም !!

government's primary duties are maintaining peace and security for the citizens
If the government is not provide the above activities it is fragile government .

03/20/2025

የደብረፅዮን ህወሓት VS ብልፅግና

03/17/2025
03/17/2025

ቡና በነፃ ሳልክፍል ጠጣሁኝ እንዴት
እንደሚመስል አብረን እንመልከት
STARBUCKS !!
Washington DC !!

03/11/2025

የትግራይ ህዝብ ድምፁን እያሰማ ነው

ሰበር ዜና ሻዕቢያ አድግራት ላይ መታየቱን መረጃዎች እየወጡ ነው
03/11/2025

ሰበር ዜና

ሻዕቢያ አድግራት ላይ መታየቱን መረጃዎች እየወጡ ነው

አድግራት ከተማ ውስጥ የሻዕቢያ  ስላዮች  መግባታቸው ታውቀዋል መንግስት ልብ በል ??
03/11/2025

አድግራት ከተማ ውስጥ የሻዕቢያ ስላዮች
መግባታቸው ታውቀዋል

መንግስት ልብ በል ??

ኤርትራ በኡትዩጵያ  ስር  VS በኢሳያስ ስር
03/09/2025

ኤርትራ በኡትዩጵያ ስር VS በኢሳያስ ስር

ኢትዮጵያ 5  Generation የተባሉ ድሮኖች መታጠቅዋ ታውቀዋል
03/08/2025

ኢትዮጵያ 5 Generation የተባሉ ድሮኖች መታጠቅዋ ታውቀዋል

03/07/2025

ሰሜናዊቷ ኮከብ መቐለ ከተማ ያለ አስተዳደር ያለ ከንቲባ ሶስት ወራትን አሳልፋለች። ህዝቡ አገልግሎት ማግኘት ፈፅሞ አልቻለም ከጄኖሳይድ የተረፈን ህዝብ ታግሎና የማይተካ ውድ ህይወቱን ገብሮ የፖለቲካ መሪዎቹን ያተረፈ ህዝብ በፖለቲከኞቹ እየተሰቃየ ይገኛል።
:
ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ሰላም አግኝቼ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ተመልሶ የተፈናቀሉ ወገኖቼ ወደ መኖሪያቸው ተሰባስበው በክልሉ ሰላም ሰፍኖ መደበኛ ህይወታችንን እንጀምራለን ብሎ ሲመኝ ነበረ ህዝብ ተስፋው ተሞጧ ካፒቶኖቹ በፈጠሩት ወዥንበር ህዝቡ መሀል ባህር ላይ ቆሞ ማዕበል እንዲያናውዘው እያደረጉት ይገኛል።
:
የትግራይ ህዝብ ይህ አይገባውም በህብረቱና በአንድነቱ ከመጣበት ሰደድ እሳት እንደተረፈው ሁሉ አሁንም ከማዕበሉ የሚወጣበትን መንገድ በህብረቱና በዲሞክራሲያዊ ትግሉ ሊያረጋግጥ ይገባል።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የቀድሞ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ተናገሩ። የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት (ጆቤ)፣ የኢትዮጵያና ...
03/07/2025

ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የቀድሞ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ተናገሩ።

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አበበ ተክለ ሃይማኖት (ጆቤ)፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ግንኙነት መጀመሪያውንም ያልተቀደሰ ግንኙነት እንደነበር ጠቁመው፣ ወደ ግጭት ሊያመሩ እንደሚችሉ የሚያመላክቱ ፍንጮች እንዳሉ ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ የወደብ ተጠቃሚ መሆን የምትችልባቸውን ሁኔታዎች በተመለከተ ከሦስት ዓመታት በፊት የሠሩትን ጥናታዊ ጽሑፍ አስታውሰው፣ ጥያቄው ግን በጉልበት መመለስ የለበትም ብለዋል፡፡

በአገሮቹ መካከል ጦርነት ቢቀሰቀስ አቅጣጫው ምን ይሆናል የሚለው ጉዳይ የሚታወቀው የጦርነቱ ዓላማ ሲታወቅ እንደሆነ ጠቅሰው፣ ‹‹ጦርነቱ አንድም አሰብን መያዝ፣ ሁለተኛው ደግሞ ሻዕቢያን ማስወገድ ሊሆን ይችላል፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የጦርነቱ ዓላማ አሰብን መያዝ ከሆነ የሁለቱን አገሮች የመሣሪያና የቴክኖሎጂ አቅም መገምገም እንደሚገባ ጠቅሰው፣ የሻዕቢያን መንግሥት የመጣል ዓላማ ካለ ደግሞ፣ የኤርትራ ዕጣ ፈንታ የሚያሳስባቸው እንደ አሜሪካ ያሉ አገሮች ጣልቃ ገብነት የሚጠበቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

‹‹እነ አሜሪካ፣ ቻይናና ሩሲያ ጉዳዩን እንዴት ያዩታል? ግብፅስ ለማን ትወግናለች? የሚለውም ሌላኛው ጉዳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አሰብን ልያዝ ብትል፣ የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ ቢደግፏት፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ግን ደስተኛ ላትሆን ትችላለች፡፡

እንዲህ ዓይነት ቀውስ ግብፅንም መጋበዙ አይቀርም፡፡ የሶማሊያና የሶማሌላንድን ፍላጎት የቱርክ አሸማጋይ ሆኖ በቀጣናው ውስጥ መገኘት፣ እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕን ወደ ሥልጣን መምጣትን ማመዛዘን ያስፈልጋል፡፡

የቀጣናው አሠላለፍ ይቀየር ቢባል እንኳን፣ አሠላለፉን በቀይ ባህር ብቻ መቀየር አይቻልም፡፡

አሰብን መያዝ የኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ መገንዘብ ይገባል፤›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ከ28 ዓመታት በፊት በተካሄደው የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ሻዕቢያን የመደምሰስ አቅም የነበረ ቢሆንም ይህ አለመደረጉ ትልቅ ስህተት እንደነበር የገለጹት የቀድሞው የአየር ኃይል ዋና አዛዥ፣ ከዚያ በኋላ በነበሩት 18 ዓመታት የተሠራው ጠላትን በዝምታ የማቆየት ትልቅ ስህተት ከባድ ዋጋ ማስከፈሉን ተናግረዋል፡፡

በተለይም በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የትግራይ ሕዝብ ዋጋ እንዲከፍል ምክንያት ሆኗል ብለው፣ አሁንም ጦርነት ከተቀሰቀሰ የትግራይ ክልል የጦርነት ዓውድማ ሊሆን የሚችልበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የፌዴራሉ መንግሥት ሠራዊት ቲዲኤፍ ከሚባለው የክልሉ ሠራዊት ጋር ሳይስማማ ወደ ትግራይ መግባት ይችላል ወይ? የሚለው ጉዳይ አጠያያቂ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ከ28 ዓመታት በፊት ‹‹ኢትዮጵያ በፌደራሊዝም ሥርዓት ተሳስራለች፡፡

የአየር ኃይልም የላትም በሚል ሻዕቢያ ወረራ ፈጽሟል፤›› ያሉት ሜጀር ጄኔራል አበበ፣ በወቅቱ የመከላከያ ሠራዊቱ የማዕከላዊ ኮማንድ አባል እንደነበሩና ሻዕቢያን አስመራ ድረስ ገብቶ የመደምሰስ ውሳኔ ላይ ተደርሶ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

ይሁንና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ውሳኔ መሠረት፣ ‹‹ኤርትራን ማዳከም በቂ ነው›› ተብሎ እንዲመለሱ መታዘዛቸውን ያስታወሱት ጄኔራሉ፣ በወቅቱ የተሠራው ስህተት ‹‹ዛሬ እንደ አገር ዋጋ እያስከፈለን ነው፡፡

በእኛ ጥፋት ምክንያት ሻዕቢያ ነፍስ ዘርቷል፤›› ሲሉም ኣክለዋል።

ethiopian reporter.

Address

Washington D.C., DC
22145

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WE Ethiopians posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to WE Ethiopians:

Videos

Share