ሰበር ዜና Ethiopian Breaking News

ሰበር ዜና Ethiopian Breaking News Connect with ሰበር ዜና to find daily breaking news as they happen in Ethiopia & around the globe all in one place by providing 24/7 coverage from all sources.

03 Aug Afternoon Rateዛሬ በግል ባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል።
08/03/2024

03 Aug Afternoon Rate

ዛሬ በግል ባንኮች ያለው የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ከላይ ተያይዟል።

August 03 Rateበትናንትናውና  በዛሬው  በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል።
08/03/2024

August 03 Rate

በትናንትናውና በዛሬው በሚውለው በዶላር ምዛሬ ዋጋ መግዣው ላይ የ12 ብር ልዩነት ፤ በመሸጫው ላይ የ15 ብር ልዩነት ታይቷል።

August 1 rate
08/01/2024

August 1 rate

07/10/2024

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/BreakingNewsEthiopiaa" የተሰረቀ ስልካችሁን ማስረጃ በማቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ " - ፖሊስየአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ ሞባይ...
05/13/2024

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

" የተሰረቀ ስልካችሁን ማስረጃ በማቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ " - ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን ከሌቦች የሚረከብ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ማሞ ድልድይ አካባቢ ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከማለዳ 12 ሰዓት ከ20 ላይ አንድ ግለሰብ ሞባይል ስልክ መቀማታቸውን ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ወንጀል ፈፃሚውን ለመያዝ ባደረገው ክትትል የተሰረቁ የሞባይል ስልኮችን ከሌቦቹ ላይ የሚረከብ " ታምራት ፍቅረማርያም " የተባለን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባደረገው ብርበራ በእለቱ የተሰረቀውን የሞባይል ስልክና በልዩ ልዩ ጊዚያት ከሌቦች የተረከባቸውን ፦
➡️ 61 ስማርት ሞባይል ስልኮችን ፣
➡️ 251 የታብሌት ስልክ ሽፋኖችን ፣
➡️ 2 ላፕቶፖችን እና በጥሬ 60 ሺ አንድ መቶ ብር ከሌባ ተቀባዩ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ መያዙን አስታውቋል፡፡

ግለሰቡ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን እና ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ከሌቦች ተቀብሎ የሚያስቀምጠው በተከራየው ቤት ውስጥ ነው ተብሏል።

ቤት የሚያከራዩ ግለሰቦች የተከራይን ማንነነት እና በምን ስራ ላይ እንደተሰማራ የማረጋገጥ ግዴታ እንደለባቸው ፖሊስ አሳስቧል።

" የሞባይል ስልክ ጠፍቶብኛል / ተሰርቂያለሁ " የሚል ማንኛውም ግለሰብ ገንደ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ ስልኩን በመለየትና አስፈላጊውን ማስረጃ በማቅረብ ንብረቱን መረከብ እንደሚችል ተገልጿል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/BreakingNewsEthiopiaaየቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ።የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 20...
05/09/2024

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ ከግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም ለሊት 6፡00 ሰዓት ጀምሮ በስራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ ፣ የኬሮሲን ፣ የአይሮፕላን ነዳጅ ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

- ነጭ ናፍጣ ➡ ብር 79.75 በሊትር
- ኬሮሲን ➡ ብር 79.75 በሊትር
- የአውሮፕላን ነዳጅ ➡ ብር 70.83 በሊትር
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 62.36 በሊትር
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ ➡ ብር 61.16 በሊትር ሆኖ ባለበት ይቀጥላል።

የቤንዚን ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጎ በሊትር 78 ብር 67 ሳንቲም ገብቷል።

 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/BreakingNewsEthiopiaaበኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።የአዲስ...
05/08/2024



የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐ ግብር ሊጀምር ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ መርሐግብር እንደሚጀምር አስታውቋል።

ዩኒቨርሲቲው በቅደመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ተመርቀው የስራ ዓለም ውስጥ ለሚገቡ ተመራቂዎች ራሱን የቻለ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ፕሮግራሙ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና የገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ነው ያለው ዩኒቨርሲቲው " ይህ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጥ ነው " ብሏል።

" የፕሮግራሙ መጀመር በሥራ ገበያው ውስጥ ብቁ ሙያተኞችን ለማግኘትና የዩኒቨርሲቲውን አቅምና ብቃት ያለው ባለሙያ የማፍራት ተልዕኮ የሚያሳካ ነው " ሲል ገልጿል።

የሙያ ብቃት ማረጋገጫው ላይ የሚሰጥ ሲሆን ይህ የሚመራበት አሰራር ይዘረጋል ተብሏል።

በትምህርት ስርዓት ውስጥ ያሉ #ተማሪዎችም ሆኑ በስራ ገበያ ያሉ ሰራተኞችና ምሁራን ለተማሩበት ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ወይም መውሰድ እንደሚችሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሳውቋል። #ኢዜአ

 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/BreakingNewsEthiopiaaሀሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘ...
05/08/2024



የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

ሀሙስ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ብቃት ምዘና ፈተና እንደሚሰጥ ተነግሯል።

ፈተናው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በጋራ በመሆን ነው የሚሰጡት ተብሏል።

ፈተናው በተመረጡ የመፈተኛ ጣቢያዎች በፈቃደኝነት ለተመዘገቡ 18 ሺህ 591 ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በፈተና ወቅት ተመዛኞች ስልክ ሆነ ማንኛውንም አይነት ኤሌክትሮኒክስ ግብአቶች ይዞ ፈተና ክፍል መግባት እንደማቻል ተገልጿል።

ተመዛኞች ፦

➡️ የታደሠ መታወቂያ ይዘው መገኘት እንደሚጠበቅባቸው ፣

➡️ ፈተናው ከመጀመሩ በፊት 1:00 ሠዓት ቀደም ብለው (1:30) ላይ የምዘና ፈተና መስጫ ቅጥር ግቢ ውስጥ መገኘት እንዳለባቸው እና አርፍዶ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ምንም እንኳን ፈተናው በፍቃደኝነት ለተመዘገቡ 18,491 መምህራን እና የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ቢገለጽም የምዘና ፈተና ለመውሰድ #ስላልተመዘገቡ ወይም ፍቃደኛ ስላልሆኑ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ምንም የተባለ ነገር የለም።

 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/BreakingNewsEthiopiaaታግታ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የተጠየቀባት ህጻን ተገኘች።የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳን...
05/07/2024



የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

ታግታ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የተጠየቀባት ህጻን ተገኘች።

የ2 ዓመት ከ8 ወር ዕድሜ ያላት አቢጊያ ዳንኤል የተባለች ህፃን ነዋሪነቷ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 " ሳርቤት ' አካባቢ ሲሆን ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስዳ ትታገታለች።

አጋቿ ቸርነት ጥላሁን የተባለው ግለሰብ ነው።

ግለሰቡ ከቤተሰቡ ጋር በነበረው ቅርበት ህፃን አቢጊያን በተለያዩ ቦታዎች እየወሰደ በማዝናናት እንደ ቤተሰቡ አባል ያጫውታት እንደነበረ እና ከ5 ወር በላይ ከቤተሰቡ ጋር በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የነበረው ቅርብ ወንጀሉን በቀላሉ ለመፈፀም ምቹ ሁኔታን እንደፈጠረለት የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል ገደማ ወደ ህፃኗ ወላጆች መኖሪያ ቤት በመሄድና "እናቷ አምጣት ብላኛለች "ብሎ ለቤት ሰራተኛዋ ከነገረ በሗላ ህፃን አቢጊያ ዳንኤልን ወስዶ በማገት ገንዘብ እንዲሰጠው ከወላጆቿ ጋር ሲደራደር ቆይቷል።

ተጠርጣሪው ግለሰብ 150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር እንዲሰጠው በመጠየቅ ገንዘቡን ማግኘት ካልቻለ ግን ህፃኗን በህይወት እንደማያገኟት ሲዝት ነበር።

የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ ህፃኗን ለማስመለስ እና ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

በተደረገው ክትትልም ዛሬ ሚያዚያ 28/ 2016 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አለም ሰላም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠርጣሪው ተከራይቶ በሚኖርበት መኖሪያ ቤት ውስጥ ለ3 ቀናት ያህል ታግታ የቆየችው ህፃን አቢጊያ ዳንኤል ልትገኝ መቻሏን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ምንም እንኳን ፖሊስ ህጿን መገኘቷን ቢገልጽም አጋቹ በቁጥጥር ስር ስለመዋሉ ያብራራው ነገር የለም።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉhttps://t.me/BreakingNewsEthiopiaaዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላ...
05/07/2024

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ ታይቷል።

ነገር ግን አውሮፕላኑ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ በተመደበለት የመንገደኞች ማስተናገጃ በር ያለ ምንም እክል መቆሙን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሳውቋል።

መንገዶኞቹም ከአውሮፕላን ላይ ደህንነታቸው እንደተጠበቀ መወርዳቸውን ገልጿል።

" በአሁኑ ሰአት የክስተቱ መንስኤ በመጣራት ላይ ይገኛል " ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት ደንበኞቹን ይቅርታ ይጠይቋል።

" ፍጹም ሀሰተኛ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርየትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል /Rapid Support Forces - RSF/ በሚባል የሚጠራው " የህ...
05/07/2024

" ፍጹም ሀሰተኛ ነው " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል /Rapid Support Forces - RSF/ በሚባል የሚጠራው " የህወሓት ታጣቂዎች ከሱዳን ወታደራዊ ሃይል /SUDANESE ARMED FORCES SAF/ ጋር በማበር እየወጉኝ ነው " በማለት ያወጣውን መግለጫ ፍጹም ሀሰተኛ እና መሰረተ ቢስ እንደሆነ ገለጸ።

ሱዳን በእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከገባች በርከታ ወራት ያለፉ ሲሆን በዚህም የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሹ ኃይል ደም አፋሳሽ ግጭት እያደረጉ ናቸው።

ታዲያ ፈጥኖ ደራሹ ኃይል " ህወሓት (TPLF) ከሱዳን ጦር ጋር ሆኖ ወግቶኛል " ብሏል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መግለጫ ለዘመናት የቆየውና በፅኑ መሰረት የቆመው የትግራይና የሱዳን ህዝቦች ወዳጅነት ከግምት ያላስገባ ነው ብሎታል።

" በሱዳን ያለው የአርስበርስ ግጭት ዓለምአቀፍ መልክ ለማስያዝና እርዳታ ለማግኘ ያለመ ነው " ሲልም ገልጿል።

ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በዚሁ የሺዎች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ያለውን የአገሪቱ የእርስ በርስ ጦርነት ላክ የህወሓት ሃይሎች ተሳትፈዋል የሚል ክስ ማቅረቡ " ሃሳባዊና መሬት ላይ መረጋገጥ የማይችል የለየለት ፈጠራ " ሲል አጣጥሎታል።

" በመሰረቱ ህወሓት የፓለቲካ ድርጅት እንጂ የሚያዘውና የሚያስተዳድረው ታጣቂ ሃይል የለውም " ያለው የጊዚያዊ አስተዳደሩ መግለጫ " የትግራይ ህዝብ ከወንድም የሱዳን ህዝብ የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነትና ጉርብትና አለው " ብሏል።

" ከዚህ አኳያ ትግራይ በሱዳን የውስጥ ጉዳይ ነገሮች በማጋጋል የምትገባበት ምክንያትና የምታገኘው ጥቅም የለም " ሲል አሳውቋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ በሱዳን የተፈጠረው አውዳሚ የአርስ በርስ ጦርነት የሚያስከትለው አደጋ በመረዳት የውጭ ሃይሎች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

ትላንት በአዲስ አበባ ፣ በቦሌ ክ/ከተማ " ስካይ ላይት ሆቴል " አካባቢ  #እግረኞች ላይ በደረሰ የትራራፊክ ግጭት 1 ሰው ሞቷል። አንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።በአቃቂ ቃሊቲ...
05/06/2024

ትላንት በአዲስ አበባ ፣ በቦሌ ክ/ከተማ " ስካይ ላይት ሆቴል " አካባቢ #እግረኞች ላይ በደረሰ የትራራፊክ ግጭት 1 ሰው ሞቷል። አንድ ሰዉ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶው " ቸራአሊያ " በሚባል አካባቢ #እግረኛ ላይ በደረሰ ግጭት ደግሞ አንድ ሰዉ ሞቷል።

ልደታ ክ/ከተማም በተመሳሳይ የአንድ ሰው በትራፊክ አደጋ ሞቷል።

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ደግሞ ቡና በመሸጥ ላይ የነበረችው ወጣት ወደ ኋላ እየሄደ በነበረ ኤፍኤሳር መኪና ተገጭታ ሞታለች።

የመረጃዎቹ ምንጮች የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት / የአዲስ አበባ ፖሊስ (ኢትዮ ኤፍ ኤም) ናቸው።

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/BreakingNewsEthiopiaa

12/11/2023

ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ

የተናገሩትንና የፃፉትን የመደመር እሳቤ አምኜ ተከተልኩዎት:: አሁን ግን በተናገሩት የማይኖሩ ብቻ ሳይሆን በሰዉ ደም የሚጫወቱ አረመኔ መሆንዎን ተረድቻለሁ:: እዉነት መስሎኝ በሀገር ህልውና ስም ሲያካሄዱ የነበረዉንና ኢትዮጵያውያንን ከማገዳደል አልፎ ሀገሪቷን ያደቀቃትን ከንቱ ጦርነት ሳዳምቅልዎ በነበረበት ወቅት ሲያወድሱኝ ነበር:: ዛሬ ነገሩ ገብቶኝ የወንድማማቾች መገዳደል ይቆም ዘንድ ለሰላም በመወገኔ ከስልጣን አነሱኝ:: ለወንበርና ለመኪና በመገዛት ኦሮሞን በኦሮሞ ለማጥፋትና ኦሮሞን ከወንድሞቹ ጋር ለማጣላት የሚጫወቱትን ቁማር እያየሁ ዝም ባለማለቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ:: ስለነበረን አጭር ቆይታ አመሰግናለሁ::

እስካለሁ ድረስ ለሰላምና ለህዝቦች ወንድማማችነት የማደርገዉ ትግል ይቀጥላል!

Kabajamoo Muummicha Ministeeraa Abiyyi Ahimadiif

Yaada Ida’amuu dubbattee fi barreessite amanee isin hordofe. Dhawaata garuu nama waan dubbatu hin jiraanne qofa otoo hin taane cubbamaa dhiiga namaatiin taphatu ta’uu keessanin hubadhe. Gaafan dhugaa sehee waraana bilaasha maqaa walabummaa biyyaatiin bantan, isa Itoophiyaanota wal-nyaachise, fi diinagdee biyyaa kuffise gegeessaa turtan deeggaretti na faarsaa turtan. Hardha gaafan dubbii argee gara nagaa goruun wal-ajjeechaan obboleeyyanii haa dhaabatu jennaan aangoo narraa fudhattan. Otoon shira Oromoo Oromoodhaan balleessuu fi obboleeyyan isaatiin walitti buusuuf kaatan argaa callisuu dhabuu kootii baayyeen gammada. Turtii waliin qabaannef galatoomaa!

Hagan jirutti qabsoon nagaa fi obbolummaa ummataatiif godhu itti fufa!

ጋዛ በከባድ ፍንዳታ እየተናጠች ባለበት የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት ዘመቻውን እያሰፋ ነው!አርብ ምሽት ጋዛ ሰርጥን ያናወጡ ከባድ ፍንዳታዎችን ተከትሎ የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት የሚያካሂደውን ...
10/27/2023

ጋዛ በከባድ ፍንዳታ እየተናጠች ባለበት የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት ዘመቻውን እያሰፋ ነው!

አርብ ምሽት ጋዛ ሰርጥን ያናወጡ ከባድ ፍንዳታዎችን ተከትሎ የእስራኤል እግረኛ ሠራዊት የሚያካሂደውን “ዘመቻ እያሰፋ” መሆኑን የጦሩ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ተናገሩ።

ለዚህ ጥቃት ምላሽ ነው በማለት ሐማስ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን መተኮሱን መግለጹን የፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤኤፍፒ ዘግቧል።በተጨማሪም የእስራኤል ሠራዊትን በጋዛ ላይ “ተከታታይ ጥቃቶችን” እየፈጸመ መሆኑ ለኤኤፍፒ ገልጿል።

ሠራዊቱ በጋዛ ላይ የሚያካሂደውን ወታደራዊ ዘመቻ እያስፋፋ መሆኑን መግለጹን ተከትሎ፣ የጋዛ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ የጋዛ ክፍል ለቀው እንዲወጡ አዟል።ረቡዕ ሌሊት የእስራኤል ታንኮች ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ክፍል ዘልቀው በመግባት የተመረጡ እርምጃዎችን ወስደው እንደወጡ መገለጹ ይታወቃል።

ይህም ጥቃት ሠራዊቱ በጋዛ ላይ ለሚያካሂደው የቀጣይ ምዕራፍ ዘመቻ አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የታለመ መሆኑን የእስራኤል ጦር ኃይሎች ባለሥልጣናት ተናግረዋል።ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈጸመውን ድንገተኛ ጥቃትን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ነገ ቅዳሜ ሦስተኛ ሳምነቱን የሚይዝ ሲሆን፣ እስራኤል እግረኛ ሠራዊቷን ወደ ጋዛ ለማስገባት እየተዘጋጀች መሆኑ ሲነገር ቀይቷል።

Via BBC

 #ትግራይየትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት " ኃላፊነት የጎደለው ነው " በማለት እንደማይቀበለው አስታወቀ።ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ " የ...
10/27/2023

#ትግራይ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት " ኃላፊነት የጎደለው ነው " በማለት እንደማይቀበለው አስታወቀ።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ፤ " የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ተፈናቃዮች አስመልክቶ ባወጣው ሁለተኛው ዘገባ የፌደራል መንግስት ባደረገው ጥረት በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ተጋሩ በብዛት ወደ ቄያቸው እንደተመለሱ፤ ሰብአዊ ድጋፍም እየቀረበላቸው እንደሆነ አስመስሎ ይፋዊ ዘገባ አውጥቷል " ሲል ገልጿል።

" በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጋሩ ከቄያቸው ተፈናቅለው በከፋ ሁኔታ በሚገኙበት ወቅት ፣ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ በማለት ሌተ ተቀን ቢወተውትም የወገኖቻችን መመለስ በሚመለከት አንዳች ተግባራዊ እንቅስቃሴ ባልተደረገበት ሁኔታ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ይህን መሰል ሃላፊነት የጎደለው ዘገባ ማውጣቱ ፤ ከአሁን በፊት በትግራይ ህዝብ ላይ ሲያደርስ የነበረውን በደል የሚያስቀጥል " ነው ብሏል።

ሪፖርቱ " በትግራይ ህዝብ ስቃይ መቀለድ ነው " ያለው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ሆን ብሎ የዓለም ማህበረሰብ ለማሳሳት ያዘጋጀው ቅጥፈት ስለሆነ ተቀባይነት የለውም " ሲል ገልጿል።

የፌደራል መንግስት ይህን መሰል ሃላፊነት የጎደላቸው ዘገባዎች ሆነ ተብሎ በመዋቅሩ ሲለቀቁ የሰላም ሂደቱ የሚያውኩ ፣ መተማመን የሚያጎድሉ መሆናቸው ከግምት ውስጥ በማስገባት ተገቢ እርምጃ ወስዶ እንዲያርም ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጥሪ ማቅረቡን በመቐለ የሚገኘው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከላይ ያለውን መግለጫ ካወጣው በኃላ አጭር መልዕክት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አሰራጭቷል።

ኮሚሽኑ " በተፈናቃዮች 2ኛ ዓመታዊ ሪፖርቱ ላይ እንደተገለጸው የጂኦግራፊ ወሰኑ ትግራይን አልሸፈነም ይህም በዝግጅቱ ወቅት ተደራሽ ስላልነበረ መሆኑን እናረጋግጣለን " ብሏል። ኮሚሽኑ የተሳሳተ መረጃን ለማረም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ (IRA) ጋር መተባበሩን እንደሚቀጥል አመልክቷል።

 በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል።CDCB (Center For Development &Capacity Building ) ባወጣው ሪፖርት የቡሳ ...
10/22/2023



በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

CDCB (Center For Development &Capacity Building ) ባወጣው ሪፖርት የቡሳ ጎኖፋን መረጃ ዋቢ አድርጎ በኦሮሚያ ክልል እስከ መስከረም ባለው ጊዜ 1.3 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ከተመዘገቡት ተፈናቃዮች ውስጥ 859,000 (66%) የሚሆኑት ከምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ወለጋ ብቻ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

በመግለጫው የተጠቀሱት ቁጥሮች ምን ያሳያሉ ?

- የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 1,292,323 መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 29 በመቶው ብቻ (374,448) ወደ መጠለያዎች መድረሳቸውን ያመለክታል። 71 በመቶ (916,606) የሚሆኑት በአካባቢው እና ራቅ ብለው በሚገኙ ማኅበረሰቦች ውስጥ ተበታትነው ይገኛሉ።

- 739 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል።

- ከ210,000 በላይ ህጻናት ከትምህርት ውጪ ሆነዋል።

- 1,117 መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎች ወደ ሥራቸው አልተመለሱም።

- 208 ጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ 788 በከፊል ወድመዋል። ( ከእነዚህ ውስጥ 13ቱ ሆስፒታሎች ሲሆኑ የተቀሩት ጤና ጣቢያዎች ናቸው)

በዚህ አጭር መግለጫ በምዕራብ ኦሮሚያ እና መካከለኛው አከባቢ በፌዴራል መንግስት እና በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ራሱን የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጭ ብሎ በሚጠራውና መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል የተፈጠረው ግጭት፣ እንዲሁም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ድንበር ላይ በአማራ ክልል በሚንቀሳቀሰው " ፋኖ " በመባል የሚታወቀው ታጣቂ ቡድን ጋር በሚፈጠሩ ግጭቶች ለችግሮቹ መንስዔ መሆናቸውን ይጠቅሳል።

በእነዚህ ግጭቶች በተለይ ሴቶች እና ህጻናት ለአደጋ የተጋለጡ ናቸው ያለው ይህ አጭር መግለጫ እናቶቻቸውን እና አባቶቻቸውን በድንገት የሚያጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው፤ ባል የሞቱባቸው ሴቶች ለዝርፊያ እና ለ አስገድዶ መድፈር (በፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት) እና አካላዊ ጥቃት እየተጋለጡ መሆናቸውን ያነሳል።

"በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ውስብስብ እና አሳሳቢ ሁኔታን ፈጥሯል። ይሄን ግጭት ለማስቆም ሁሉን አቀፍ ውይይት እና ሰላም ማስፈን ያስፈልጋል። በግጭቱ ወቅት ለተፈናቀሉ እና ችግር ውስጥ ላሉ ዜጎች አስቸኳይ የተቀናጀ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።" ሲል በCDCB የቀረበው የፓሊሲ ብሪፍ ጠይቋል።

" ... ሕገወጡ የድርጅቱ   ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " - አምባሳደር ሱሌማን ደደፎከሰሞኑ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክት...
10/21/2023

" ... ሕገወጡ የድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " - አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ

ከሰሞኑ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ ጨምሮ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛል።

#የግል አስተያየታቸውን ካጋሩት ውስጥ የቀድሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሱሌማን ደደፎ አንዱ ናቸው።

አምባሳደር ሱሌማን ፤ የተወሰደው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም የይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ይህ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

" እነዚህ ሰዎች ዘርግተው የሚጠቀሙበትና በበርካታ ደላሎች የሚሠራበት ሕገወጡ የድርጅቱ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " ብለዋል።

አምባደሩ ፤ " ዛሬም የኢትዮጵያ ፓስፖርት በበርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በደላሎች ሱቆች ውስጥ በይፋ በመቸብቸብ ላይ ይገኛል " ሲል ገልጸዋል።

" ዜጎቻችን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ እስከ 60,000 ብር የሚጠየቁበት፣ ከቪዛና ከፓስፓርት እድሳት እያንዳንዱ አገልግሎት ጠያቂ $100 ዶላር ላልታወቀ ግለሰብ ወይም ተቋም የሚከፍልበት አሠራር ዛሬም ስላለ በሥራ ላይ ያለው የኦንላይን ሲስተም scrap ተደርጎ በአዲስ መተካት ይኖርበታል። " ብለዋል።

ኦንላይን የቪዛ ጥያቄ አሁንም ሁለት ሦስት ጊዜ ካልተከፈለበት መልስ እንደማይሰጥ ይታወቃል ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፤ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ፤ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ብለዋል።

" ካሉን ቁልፍ የደህነት ተቋማት መካከል የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መ/ቤት ምን ዓይነት ውርደት/ውድቀት ውስጥ እንደከተተን አይተናል። " ያሉት አምባሳደሩ " ተቋሙ ብቻውን ለዚህ አልበቃም፤ የባሰም እንዳለ ምንም ጥርጥር የለውም፣ በየዕለቱ የምናየውና የምንሰማው ጉዳይ ስለሆነ። " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ በሕጋዊ መንገድ ለማደስ ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የሚጠየቅበት አገር ውስጥ መሆናችንን ስናስብ እጅግ በጣም እንደነግጣለን "ም ብለዋል።

" መንግሥት ብዙ ቅድሚያ የሚሰጣቸው (Priorities) ቢኖሩትም የሥልጣን ብልግናና የአስተዳደር በደሎች፣ በተለይም ሌብነት አሁን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች መካከል መሆን ይኖርባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ኢሚግሬሽን ብቻውን እንዳልበሰበሰ ታውቆ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበ

 ባለፉት ሁለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት ግን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።ምን የተቀረ ነገር ኖሮ ነው ? የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ...
10/15/2023



ባለፉት ሁለት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተፈትነው ያለፉት ግን እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው።

ምን የተቀረ ነገር ኖሮ ነው ? የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሰሞኑን በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው ማብራሪያ ሰጥታዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የፈተናው ክብደ እና ቅለት ከሆነ ምንም የተቀየረ ነገር የለም።

የፈተና አሰጣጥ እና ዝግጅት ሂደት አለ፤ እራሱን የቻለ ሳይንስ አለው በጣም እንዳይከብድም በጣም እንዳይቀልም።

እስከ ዛሬ ሲሰራ ከነበረው ምንም የተለየ ነገር የለም። የተለየው ፈተና አሰጣጡ ነው።

ፈተና አሰጣጡ ያመጣው ለውጥ ምንድነው ከተባለ ፤ ከዚህ በፊት ፈተናዎች በየትምህርት ቤት ነው የሚሰጡት ፈተና መታተም ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ ፣ ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ፈተናዎቹ ይሰረቃሉ።

ፈተና ሲሰረቅ የነበረው በተደራጀ መልክ ነው በክልሎች ፈታኞች በየክልሉ ሲሄዱ ትልቅ ግብዣ ተደርጎ ጉቦ ተሰጥቷቸው ተማሪዎቹ እንዲኮራረጁ ይደረጋል። ውጤቱ ትርጉም ያለው አልነበረም።

እኔ ትምህርት ሚኒስቴር የመጣሁ ጊዜ በሁለተኛው ሳምንት ፈተና ሰጥተን ነበር በድሮው አሰጣት ፎርማት ያኔ ነው የማለፊያ ውጤት 50 በመቶ ነው ብለን ፖሊሲ ያደረግነው ፣በወቅቱ ፈተና አሰጣጡን አልቀየርንም ነበር ያኔ ያለፈው 48% ነው። አንዳንድ ክልሎች 70-80 በመቶ አሳልፈዋል።

በምንም አይነት የተማሪዎቹ ችሎታና ብቃት አይደለም። ... መሰረቅ መኮረጁን ለማወቅ ዳታውን ከተታትሎ ማግኘት ይቻላል፤ ግልፅ ነው።

ፈተናው እራሱ የተማሪዎች ችሎታና ብቃት መለኪያ አልነበረም። ያንን ነው የቀየርነው። ከምንም በፊት የሰራነው በተማሪዎች ጭንቅላት ውስጥ በስርቆት፣ በማጭበርበር ፣ ሌላ ሰው በማስፈተን ፣ በመኮረጅ የሚገኝ ትምህርት የለም የሚል ነው። ይሄን አውቀው እንደ ችሎታቸው እንዲያጠኑ ነው ያደረግነው።

የዛ ውጤት፣ እንደ ሀገር ያለንበትን ልክ ነው ያሳወቀን። በዚህም ይሄ ነው የትምህርት ስርዓቱ ካልን በኃላ ሪፎርሞችን በተግባር አውለን አንድ ትውልድ ቢበላሽብን ቀጣዩን እንዴት እናድናለን ብለን ነው እየሰራን ያለነው። "

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ በ2014 እና በ2015 በድምሩ 1,741,619 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውስደዋል። ከነዚህ ውስጥ ያለፉት በድምሩ 57,301 ተፈታኞች ናቸው።

በዚህ ልክ ተፈታኝ ተማሪዎች መውደቃቸው ዜጎችን ያስደነገጠ ቢሆንም ከነዚህ ተማሪዎች በፊትም ፈተናው አሰጣጡ በዚህ መንገድ ቢሆን ውጤቱ ከዚህ እንደማይለይና የትምህርት ስርዓቱ ውድቀት ከታች ጀምሮ የመጣ እንደሆነ የሚገልጹ በርካቶች ናቸው።

ለዚህ ውድቀት ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነት እንዳለበትና ተማሪዎቹን ከሚያስተምሯቸው መምህራን ብቃት አንስቶ ፣ የትምህርት ቤቶች የጥራት ጉዳይ፣ የግብዓት አቅርቦት ሁሉ ሊፈተሽ የሚገባው እንደሆነ የሚያመላክት መሆኑ ይነሳል።

" የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ አይቻልም "- አዲስ አበባ ፖሊስየአዲስ አበባ ፖሊስ ለ  #ኤፍቢሲ በሰጠው ቃል ፤ የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ በፍጹም የተከለከለ መሆ...
09/25/2023

" የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ አይቻልም "- አዲስ አበባ ፖሊስ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለ #ኤፍቢሲ በሰጠው ቃል ፤ የመስቀል ደመራ በዓል ላይ ርችት መተኮስ በፍጹም የተከለከለ መሆኑን አሳውቋል።

ፖሊስ ምን አለ ?

- ህብረተሰቡ በመስቀል ደመራ በዓል ላይ የተከለከሉ ነገሮችን በፍጹም መያዝ አይገባውም። ለሚኖሩ ፍተሻዎችም መተባበር አለበት።

- በየአካባቢው በሚደመሩ ደመራዎች አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

- ከዚህ በፊት ደመራ ተደምሮባቸው የማያውቁ ቦታዎች እንዳይሆኑ የድሮዎቹን መጠቀም ይገባል።

- ርችት መተኮስ በፍጹም ክልል ነው። ክልከላው የተደረገው ርችትን ሽፋን በማድረግ ህገወጦች ህገወጥ የጦር መሳሪያቸውን የሚሞክሩበት ጊዜ በመሆኑ ነው። ርችት ሲተኩስ የተገኘ ግለሰብ ሆነ ተቋም በህግ አግባብ እርምጃ ይወሰድበታል።

 ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል።ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም...
09/09/2023



ኢትዮ ቴሌኮም 630 ሺ ደንበኞቹ ዛሬ ይፋ ያደረገውን የ5G ኔትወርኩን መጠቀም ይችላሉ ብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ በሙከራ ደረጃ በአዲስ አበባ እንዲሁም በአዳማ ከተሞ በሙከራ ደረጃ ሲያቀርብ ቆይቶ ዛሬ በይፋ በአዲስ አበባ አገልግሎት ማስጀመሩን አስታውቋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛውን ትውልድ (5G) የሞባይል ኔትወርክ ለመጀመሪያ ጊዜ የሞከው በአዲስ አበባ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ነበር። በቀጣይም በሙከራ ደረጃ በአዳማ ከተማ አገልግሎቱን ሲሰጥ ቆይቷል።

ይህ የ5G ኔትዎርክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ተደራሽነቱን አስፍቶ ለተጠቃሚዎች መቅረቡን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በነበረው ይፋዊ የማብሰሪያ መድረክ ላይ ተናግረዋል።

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ በኢትዮጵያ ይህንን አገልግሎት በአዲስ አበባ 145 ሳይቶች ላይ የ5G ኔትዎርክ ማስፋፊያ የተደረገ ሲሆን 630 ሺ ደንበኞቹ ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም የሚያስችል ቀፎ (Device) መኖሩን አስታውቀዋል።

ይህ አገልግሎት ከተዘረጋባቸው ቦታዎች መካከል ከመስቀል አደባባይ እስከ ቦሌ ኤርፖርት፤ ከመስቀል አደባባይ መገናኛ CMC እንዲሁም ወደ ሰሚት የሚወስደው መንገድ፤ ከመስቀል አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ድረስ፤ ከመስቀል አደባባይ ሜክሲኮ ሳር ቤት እንዲሁም ልደታ ከመስቀል አደባባይ ለገሀር ቸርቸል ጎዳና ይህ መሰረተ ልማት የተዘረጋላቸው አከባቢዎች ናቸው ተብሏል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ በመግለጫቸው ተቋሙ በቀን በአማካይ ወደ 2,087 GB የዳታ ትራፊክ መኖሩን የገለጹ ሲሆን ከዚህ ውስጥም የ4G አገልግሎቱ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ጠቁመዋል።

በአለማችን ወደ 110 ሀገረት በአፍሪካ ደግሞ 16 ሀገራት ይህንን አገልግሎት የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ 1.3 ቢሊዮን ተጠቃሚዎችን የ5G ኔትዎርክ ተጠቃሚ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጿል።

 የፕሪቶሪያ የ ' ሰላም ስምምነት ' ከተፈረመ በኋላ የ " ኤርትራ ወታደሮች " በትግራይ ወሲባዊ ባርነት ፣ ግድያዎችን እና ሌሎች ከባድ ጥሰቶች መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ባ...
09/05/2023



የፕሪቶሪያ የ ' ሰላም ስምምነት ' ከተፈረመ በኋላ የ " ኤርትራ ወታደሮች " በትግራይ ወሲባዊ ባርነት ፣ ግድያዎችን እና ሌሎች ከባድ ጥሰቶች መፈጸማቸውን አምነስቲ ኢንተርናሽናል አዲስ ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

- ከሰላም ስምምነቱ በኃላ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ምድር ወሲባዊ ባርነት፣ ግድያ፣ ከባድ ጥሰቶችን ፈፅመዋል።

- የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት መድፈር፣ ሴቶችን ለወራት ለወሲባዊ ባርነት መዳረግ፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ ዘረፋዎችን እየፈጸሙም እንደሆነ ተገልጿል።

- የተፈፀሙት ጥሰቶች የጦር ወንጀሎች እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ሊሆን ይችላል።

- ሸዊቶ በተሰኘች ወረዳ ቢያንስ 20 ነዋሪዎች በዋነኝነት ወንዶች ከጥቅምት15 - ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባለው ወቅት በኤርትራ መከላከያ ኃይል መገደላቸውን ገልጿል።

- የፕሪቶሪያው ስምምነት ከተፈረመ በኃላ የኤርትራ መከላከያ ኃይል ወታደሮች 24 ሰላማዊ ነዋሪዎችን በኮኮብ ጽባህ ወረዳ መግደላቸውን ሪፖርት ተደርጓል።

- አምነስቲ በኮከብ ጽባህ የተደፈሩ እና ለወሲባዊ ባርነት ተዳርገው የነበሩ 11 ሴቶችን አነጋግሯል። ከ40 በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎችም እንደተደፈሩ እና ለወሲባዊ ባርነት እንደተዳረጉ ለአካባቢው ለሚገኝ የሲቪል ማህበረሰብ መናገራቸውም ሪፖርቱ ላይ ሰፍሯል።

ሙሉ ሪፖርቱ በዚህ ይገኛል ፦ https://www.amnesty.org/en/latest/news/2023/09/eritrean-soldiers-committed-war-crimes-and-possible-crimes-against-humanity-in-the-tigray-region-after-signing-of-agreement-to-end-hostilities/

የሰራተኞች ጥያቄ ምንድነው ? ከሰሞኑን ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይት ምን ጥያቃ ተነሳ ምንስ ምላሽ ተሰጠ ?(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን - ፕሬዜዳንት ካሳሁን ፎሎ)ከኑሮ...
09/03/2023

የሰራተኞች ጥያቄ ምንድነው ? ከሰሞኑን ከጠ/ሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይት ምን ጥያቃ ተነሳ ምንስ ምላሽ ተሰጠ ?

(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን - ፕሬዜዳንት ካሳሁን ፎሎ)

ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ ደሞዝ ተከፋዩ ሰራተኛ ችግር ላይ ነው ያለው። በተለይ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የሆነው ሰራተኛ እጅግ የከፋ ችግር ውስጥ ይገኛል።

ለኑሮ ውድነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኮቪድ19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ከሩስያ እና ዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ የታየው የዋጋ ንረት፣ የነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያቶች ሲሆኑ #ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ጦርነቶች እና ግጭቶች ለኑሮ ውድነት አስተዋፅኦ አድርገዋል።

የኑሮ ውድነቱን ለማቅለል እየተጠየቀ ያለው ጥያቄ ፦

- ሰራተኛው በጣም ችግር ላይ ስለሆነ የስራ ግብር ይቀነስ።

- ዝቅተኛ ደመወዝ የሚከፈላቸው ጭራሽ መኖር ወደማይችሉበት ደረጃ ላይ ስለደረሱ የገበያው ሁኔታ ታይቶ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ይወሰን።

- ለሁለት ዓመት የተቋረጠው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አማካሪ ቦርድ ተመልሶ እንደገና ስራ እንዲጀምር። ይህ ቦርድ ከመንግሥት 5 ከሠራተኛ 5 ፣ ከአሰሪ 5 የሚሳተፉበት የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አፈፃፀምን እየተከታተለ አቅጣጫ የሚሰጥ ችግር ሲኖርም የሚፈታ ነው። ይህ ቦርድ ስራው በመቋረጡ የሠራተኞችን ጉዳይ ተጠያቂ የሚደረግበት ቦታ አልነበረም።

- 20/80 ተግባራዊ አልሆነም ተግባራዊ ይደረግ። ይህ ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ለሚቀጥሩት ሰራተኛ ይከፍላሉ ተብሎ የወጣ መመሪያ ነው። መመሪያው የሚለው ለሰራተኛው 80% ለአስተዳደራዊ ወጪ 20% ይውሰድ የሚልነው።

- በነፃ የመደራጀት እና የመደራደር መብት ይከበር። ሰራተኞች ለመደራጀት ሲሞክሩ / ሲደራጁ በአሰሪዎቻቸው እርምጃ ይወሰድባቸዋል ፣ እርምጃዎቹ ከቦታ ቦታ ማዘዋወር፣ ከድራ ዝቅ የማደረግ፣ ከስራ ማባረር ይጨምራሉ። ስለዚህ ህግ በሚፈቅደው የመደራጀት እና የመደራደር መብታቸው ይጠበቅ ይህጉ ይፈፀመ።

- በሀገሪቱ ባለው የፀጥታ ሁኔታ ሰራተኞች ላይም ጉዳት እያመጣ አንዳንድ ቦታዎች ሰራተኞች እንደሚታገቱ፣ እንደሚገደሉ፣ ስለሚታወቅ ያ ጉዳይ ተነስቶ መፍትሄ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ ምንድነው ?

በውይይቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዝቅተኛ ደመወዝ ወለል፣ ስራ ግብር ቅነሳ፣ ከአማካሪ ቦርድ ጋር በተያያዘ ሌሎችም ለተነሱ ጥያቄዎች ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ሰጥተዋል።

" ጥያቄዎቹ ትክክል አይደሉም " ፤ ወይም " አይፈፀሙም " የሚል ምላሽ አልተሰጠም። በጊዜ ሂደት ምላሽ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ምላሽ የሚሰጡት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በመሆኑ ይታያል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፤ አቅጣጫም አስቀምጠዋል።

ወዲያው መፈፀም ያለበት የአማካሪ ቦርድ መቀጠል ላይ ቅድመ ሁኔታ የማያስፈልገው ስለሆነ እሱ እንዲቀጥል ለሚመለከታቸው አካላት አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ሌሎችም ጥያቄዎች እንዲታዩ በሚል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

(የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን - ፕሬዜዳንት ካሳሁን ፎሎ)

 #ጅግጅጋ" እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ " - አባትበጅግጅጋ ከተማ የተደፈረችው ልጅ አባት ምን አሉ ?አባት ኡጋስ አረብ በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ልጃቸው በራሳቸ...
09/01/2023

#ጅግጅጋ

" እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ " - አባት

በጅግጅጋ ከተማ የተደፈረችው ልጅ አባት ምን አሉ ?

አባት ኡጋስ አረብ በጅግጅጋ ከተማ ወረዳ 13 ተብሎ በሚጠራው ቦታ ልጃቸው በራሳቸው ሰራተኞች ከተደፈረች በኃላ መገደሏን ገልጸዋል።

ለቢቢሲ ሶማሊ ክፍል አባት ኡጋስ አረብ ፦

" እኔ ተጎጂ ነኝ፤ ፍትሕ እፈልጋለሁ። እለኔ ልጅ ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም በዚህ መንገድ ሕይወታቸው ለጠፋ ሁሉ ፍትሕ እንዲሰፍን እጠይቃለሁ።

በወቅቱ መኝታ ቤቴ ውስጥ ተኝቼ ነበር። ቤት ውስጥም ከእኔ ውጭ ትልልቅ ሰዎች አልነበሩም።

ልጄ ጋር ሄጄ ሳያት እየተነፈሰች አልነበረም ደረቷንም በመጫን እንድትተነፍስ ለማድረግ ሞከርኩ።

አንገቷንም ሳየው ገመድ ተጠምጥሞባት ታንቃለች። ገመዱን ቆርጬ ወደ ሐኪም ወሰድኳት።

ለሕክምና ወደ ሆስፒታል አፋፍሰን ብንወስዳትም ሕይወቷ አልፏል።

በሞባይል ጥገና ሱቄ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ አራቱ ሠራተኞቼ በድርጊቱ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። አንደኛው ሠራተኛዬ ጠፍቷል። " ሲሉ ተናግረዋል።

Via BBC Somali

 የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ከአሁን በኋላ በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያለው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ....
08/27/2023



የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራን ከአሁን በኋላ በካድሬነት ሳይሆን በብቃታቸው ብቻ እንደሚመረጡ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ይህንን ያለው ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 30ኛውን ዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" የትምህርት ቤቶች አስተዳዳሪዎች ከአሁን በኋላ የሚመረጡት በካድሬነት ሳይሆን፣ ባላቸው ብቃትና ችሎታቸው ላይ መሠረት ተደርጎ ይሆናል።

በዚህ መሠረት በአገር አቀፍ ደረጃ በብቃታቸውና በችሎታቸው የተመዘኑ 1,600 የትምህርት አስተዳዳሪዎች ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል። ይህ ዓይነቱ አሠራር ቀጣይነት ይኖረዋል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሳደግ ሥራ በተጨማሪ የመምህራንና ርዕሳነ መምህራን ብቃትና ችሎታ ማጎልበት ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡

ትኩረት ካገኙ መሠረታዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤቶችን በግብዓትና በጥራት ከማሻሻል ባሻገር ክህሎት፣ ብቃትና ችሎታ ባላቸው ርዕሳነ መምህራን እንዲተዳደሩ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።

የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል በተጨማሪ በዕውቀት ተማሪዎቻቸውን ተወዳዳሪ ማድረግ የሚችሉ መምህራንን ማብቃት ከተያዙ ግቦች መካከል አንዱ ነው።

ባለፉት 30 ዓመታት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ጥራት ወርዷል ፤ በኑሮ ለተሻሉ ደግሞ የግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩበት ሥርዓት ተዘርግቷል።

ይህ ዓይነት አካሄድ በዜጎች መካከል በኑሮ ደረጃ ከተፈጠሩ ልዩነቶች አልፎ በትምህርት ዘርፍ ላይ መታየቱ ትልቅ ክስረት ነው። ይህ አካሄድ በአገር አቀፍ ደረጃ አደገኛ ሁኔታዎች የሚፈጥር ነው ፤ በየትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች በገንዘብ ዕጦት ሳቢያ የትምህርት ጥራት ሊጓደልባቸው አይገባም።

ትምህርት የአገር የሉዓላዊነት እሴት መለኪያ ነው ፤ በዚህ ጉዳይ ለዓመታት የተቀለደበት ዘርፍ ነው አሁን እርስ በርስ መነጋገር የማይቻልበት ሁኔታ ላይ መደረሱ የችግሩ ማሳያ ነው።

የትምህርት ዘርፍ መሠረታዊ መርሆዎች ሁለት ናቸው ፤ ዜጎች በብሔራቸውና በሃይማኖታቸው ሳይታዩ እኩል ጥራት ያለው ትምህርት የማግኘት መብታቸውን ማረጋገጥ አንደኛው ነው።

የትኛውም የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎች ከሁሉም እኩል ተወዳዳሪና ተፎካካሪ የሚሆኑበትን የትምህርት ሥርዓት በመዘርጋት፣ አሁን ያለውን የኢፍትሐዊነት ችግር በዘላቂነት መፍታት ይቻላል።

በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፉ ከአሥር ዓመታት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደ አሁኑ የፀብ (የረብሻ) መፍለቂያ ሳይሆኑ የመወዳደሪያና የብቃት ማጎልበቻ ይሆናሉ፡፡

ከዚህ በኋላ እንደ ከዚህ ቀደሙ ዲግሪ እንደ ከረሜላ የሚታደልበትን አሠራር አስቀርቶ፣ በብቃት እና በችሎታ ብቻ ዜጎች ማዕረግ የሚያገኙበት ሥርዓት በዘላቂነት ይዘረጋል። "

Via Reporter Newspaper

 ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀ።የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድ...
08/14/2023



ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፀደቀ።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የቀረበለትን የአስቸኳይ ጊዜ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በ12 ድምፅ ተአቅቦ በ16 ታቃውሞ በአብላጫ ድምፅ ነው የፀደቀው።

 #ኢትዮጵያ" ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ይቁሙ "በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚታዩ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ።ይህን ጥሪ ያቀረበው የኢት...
08/08/2023

#ኢትዮጵያ

" ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ይቁሙ "

በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚታዩ ደም አፋሳሽ ግጭቶች በአስቸኳይ ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲቆሙ ጥሪ ቀረበ።

ይህን ጥሪ ያቀረበው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነው።

ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች በንግግርና በምክክር መፍታት ሲገባ በተለያዩ አካባቢዎች እና በተለያዩ ወገኖች እየተወሰዱ ያሉ የኃይል እርምጃዎች የሀገራችን ኢትዮጵያን ደህንነትና ህልውና በመፈታተን ላይ መጥተዋል ሲል አሳውቋል።

ኮሚሽኑ " የተቋቋምኩበትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረኩ ባለሁበት በዚህ ወቅት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እየታዩ ያሉ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ሥራዬን አዳጋች እያደረጉት ይገኛሉ " ብሏል።

የኮሚሽኑ ምክር ቤት ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ/ም ባደረገው ልዩ ስብሰባ በመላው ሀገራችን የሚታዩ ግጭቶች በአስቸኳይ ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ ቆመው የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ አሉን የሚሏቸውን ልዩነቶች ወይም ጥያቄዎች በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠው በምክክር እንዲፈቱ አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ አቅርቧል።

ለዚህም ተግባራዊነት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባለድርሻ አካላትን በማቀራረብ፣ የልዩነት አጀንዳዎችን ሰብስቦ ለማወያየትና ለማመካከር አመቺ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን ያ
አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

 በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት 8 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት " የሰላም እና ዘላቂ መፍትሄ ጥሪ " መግለጫ አቀረ...
08/07/2023



በአማራ ክልል የተከሰተው ግጭትና አለመረጋጋት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲገኝለት 8 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በጋራ ባወጡት " የሰላም እና ዘላቂ መፍትሄ ጥሪ " መግለጫ አቀረቡ።

ጥሪውን ያቀረቡት ፦

👉 የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)
👉 የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል
👉 የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር
👉 የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት
👉 አዲስ ፓወርሀውስ
👉 የኢትዮጵያ ሴቶችና ሕፃናት ማኅበራት ኅብረት
👉 የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች
👉 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት
👉 ሴታዊት ንቅናቄ ናቸው።

ድርጅቶቹ በአማራ ክልል ውስጥ የተከሰተው ግጭት እጅግ አሳስቦናል ብለዋል።

በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት፦

- ግጭቶች በሰላማዊ ዘዴዎች የሚፈቱባቸውን መንገዶች ለማግኘት የሲቪል ማኅበራት ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የእምነት ተቋማት፣ መገናኛ ብዙኃንና የአገር ሽማግሌዎች የተከሰተው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የበኩላቸውን ግፊት እንዲያደርጉ ፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተጀመሩ የሰላም ጥረቶችና ሥምምነቶች በአማራ ክልልም በሚንቀሳቀሱ ወገኖች እና በፌዴራሉና የክልሉ መንግሥታት መካከል መደረግ የሚችልበት ዕድል እንዲፈለግ ፤

- ትጥቅን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች በሰብዓዊ መብቶች እና በሰብዓዊ ሕግጋት (humanitarian laws) እንዲመሩ እና የንፁኃን ደኅንነት እንዲጠበቅ፤ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች በተከሰቱ ግጭቶች የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፣ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ እና ሌሎችም ጉዳቶች በክልሉ እንዳይፈፀሙ ከፍተኛ የመከላከል ሥራዎች እንዲከናወኑና የተጠያቂነት ስርዓት እንዲዘረጋ ፤

- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም ወቅት የፀጥታ አካላት ያልተመጣጠነ ኃይል እንዳይጠቀሙ ፣ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ማግለሎች እና ጥቃቶች እንዳይስፋፉ እና የጅምላ እስሮች (indiscriminate mass arrests) እንዳይከናወኑ ፤

- የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ብዙኃን መገናኛዎች ግጭት አገናዛቢ አዘጋገብን እንዲተገብሩ፣ የሐሰተኛ እና የተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እንዲገቱ፣ እንዲሁም ሐቁን የሚያንፀባርቁ መረጃዎችን ብቻ ለዜጎች በማድረስ ከግጭት አባባሽነት እንዲቆጠቡ ፤

- ዝርዝር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማስፈጸም የሚወጡ መመሪያዎችና ደንቦች ለዜጎች ተዳራሽ በሆኑ አማራጮች በተከታታይ እንዲደርሱ ጥሪ አቅርበዋል።

   የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መምከራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።ውይይቱ የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ...
08/06/2023



የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ዛሬ ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መምከራቸውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ውይይቱ የነበረው በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ዙሪያ እንደነበር ተገልጿል።

አንቶኒ ብሊንከን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እና በጎራባቹ አፋር እና አማራ ክልሎች ያለውን ያልተገደበ የሰብአዊ ድጋፍ እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበረበት ለመመለስ እየሰራ ያለውን ጥረት እውቅና መስጠታቸው ተመላክቷል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ የውጭ ኃይሎችን ከትግራይ ምድር ማስወጣትና አብሮም የትግራይ ኃይሎችን ትጥቅ ማስፈታት የሚለው ጨምሮ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት በአስቸኳይ ተግባራዊ ማድረግን እንዳሰመሩበት ተሰምቷል።

ብሊንከን ፤ ሀገራቸው አሜሪካ የአፍሪካ ህብረት የስምምነት አፈፃፀም የክትትል እና ማረጋገጫ ዘዴን ጨምሮ በአጠቃላይ ህብረቱ የሚመራውን ሂደት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።

በደቡብ አፍሪካ ፤ ' ፕሪቶሪያ ' በዘላቂነት ግጭት እንዲቆም የተፈረመው ስምምነትን ለማስፈፀም በኬንያ ኖይሮቢ በተፈረመው ስነድ ፤ የትግራይ ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ትጥቅ አፈታት የውጭ ኃይሎችና ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት ጋር በአንድ ግዜ እንደሚፈፀም ይገልጻል።

" ከቅርብ ጊዜው ተሞከሯችን መማር አለመቻላችን እጅግ አሳዛኝ ነው " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት" ጦርነት መፍትሄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር፤ ችግሮችን በውይይት እን...
08/06/2023

" ከቅርብ ጊዜው ተሞከሯችን መማር አለመቻላችን እጅግ አሳዛኝ ነው " - የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

" ጦርነት መፍትሄ አይኾንም፤ ከትናንት እንማር፤ ችግሮችን በውይይት እንፍታ " ሲል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።

ምክር ቤቱ ባወጣው የ " ሰላም ጥሪ " መግለጫ ፤ በሃገራችን አንዳንድ አከባቢዎችና በተለይም በአማራ ክልል ከዕለት ወደ ዕለት ተባብሶ የቀጠለውን የፀጥታ መደፍረስ ሁኔታ በአንከሮ እየተከታተለው እንደሚገኝ ገልጿል።

" በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ጦርነት ካደረሰብን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ገና በቅጡ እንኳ ባላገገምንበት በዚህ ወቅት፣ ዳግም ወደ ሌላ መጠነ ሰፊ የእርስ በርስ ግጭት መግባት በሕዝባችን ላይ የሚያደርሰው ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ ልቡናዊ ጉዳት በእጅጉ የሚያሳስብ ነው " ብሏል።

ምክር ቤቱ ፤ " ጦርነት ከፍተኛ መጠን ያለው ሰብኣዊ እልቂትን እና ቁሳዊ ውድመትን ከማስከተል በቀር፣ ለችግሮቻችን መፍትኄ እንደማያስገኝ ከቅርብ ጊዜው ተሞከሯችን መማር አለመቻላችን እጅግ አሳዛኝ ነው " ሲል ገልጿል።

በሀገር ውስጥ የሚካሄድ ጦርነት የሀገር አንድነት ፀንቶ የቆመባቸውን የእሴት አምዶች በማፍረስ የሕዝባችንን እንድነት የሚንድ በመኾኑ፣ ሁሉም አካላት ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡና ወደ ውይይት መምጣት የሚቻልበትን መላ እንዲያፈላልጉ ምክር ቤቱ አጥብቆ አሳስቧል።

ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ እጅግ አውዳሚና አክሳሪ ከኾነው ጦርነት የችግር መፍትኄን ከመጠበቅ ይልቅ፣ በአስቸኳይ ወደ ውይይት እንዲመጡ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሰላም ጥሪ አቅርቧል።

ይህ እንዲሳካ ምከር ቤቱ አስፈላጊውን ለማድረግ ያለውን ዝግጁነት ገልጿል።

07/25/2023

በጉራጌ ዞን በታጠቁ ኃይሎች በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በምስራቅ መስቃን ወረዳ፤ ሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እና ዕሁድ ሐምሌ 16/2015 የታጠቁ ኃይሎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።በወረዳው በቼ እና ዲዳ በተባሉ የቀበሌ ከተሞች፤ ምሽት 3 ሰዓት ላይ ጥቃቱ እንደተሰነዘረ እና ግድያዎች እንደተፈጸሙ ምንጮች ከስፍራው ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል፡፡

ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከአካባቢው መሰወራቸው የተገለጸ ሲሆን፤ እስካሁን በቁጥጥር ሥር የዋለ አካል አለመኖሩ ተጠቅሷል።በተጠቀሰው ምሽት ላይ ሦሰት ሰዓት አካባቢ በቼ ቀበሌ ውስጥ በተሰነዘረ ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸው የታወቀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ዕሁድ ሐምሌ 17/2015 ምሽት ኹለት ሰዓት ገደማ አንድ አባውራ ከነባለቤታቸው እና ጎረቤታቸው ከሆኑ ግለሰብ ጋር መገደላቸውን አዲሰ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

በመስቃንና ማረቆ ብሔረሰብ መካከል ባለው የቆየ አለመግባባት በተደጋጋሚ የሚፈጸም ማንነት ተኮር ጥቃት መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ለአካባቢው ማህበረሰብ በነጻነት መንቀሳቀስ አስቸጋሪ መሆኑ ተመላክቷል።እንደ ነዋሪዎች ገለጻ፤ በአካባቢው ባለው የሰላም እጦት ሳቢያ አብዛኛውየመንግሥት ሠራተኞች ለደኅንነታቸው በመስጋት በሥራ ገበታቸው ላይ እንደማይገኙ እና ብዙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ዝግ መሆናቸውን ብሎም የተከፈቱትም አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ተነግሯል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ከሐሙስ ሐምሌ 13/2015 እስከ ሐምሌ 17/2015 ድረስ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት እንደደረሳቸው ጠቅሰው፤ “በቂ የጸጥታ አካላት ወደቦታው ልከናል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም፤ ግድያውን በሚመለከት ማንነትን መሰረት ያደረገ ነው ወይም አይደለም? የሚለውን ጉዳይ በሚመለከት በመጣራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በጊዜው ይፋ እንደሚደረግም አስታውቀዋል።

በዞኑ ኹለቱ ወረዳዎች መካከል ዓመታትን ያስቆጠረው ግጭት ዕልባት ሳያገኝ የቀጠለ ሲሆን፤ በተደጋጋሚ ሰላም ሚኒስቴርን ጨምሮ በርካታ አካላት ለችግሩ ዕልባት ለመስጠት ሙከራ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል። በዚህም መሰረት ከአራት ዓመታት በፊት ሰላም ሚኒስቴር ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን ሰፊ ሥራዎችን ይሰራ እንደነበር ነገር ግን ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት ባለመቻሉ ችግሮች ተባብሰው መቀጠላቸውን ለማወቅ ተችሏል።

Via Addis Maleda

Address

Ring Road
Washington D.C., DC
2005

Opening Hours

Monday 9am - 5pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 9am - 5pm
Thursday 9am - 5pm
Friday 9am - 5pm
Saturday 9am - 5pm
6pm - 7pm

Telephone

+16479780112

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሰበር ዜና Ethiopian Breaking News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሰበር ዜና Ethiopian Breaking News:

Videos

Share

Category