
11/02/2024
( ማንም አሸነፈ ማን በማይመለከተን ) የአሜሪካን ምርጫ ቅስቀሳ ካማላ ሃሪስን ደግፎ በዚህ ካምፔን እየተሳተፈ ያለው ባራክ ኦባማ ፡. .. ዶናልድ ትራምፕ በአንዳንድ የሙስሊም ሀገራት ላይ የጉዞ እገዳ ማድረጋቸውን አውግዞ ሲናገር ተሰምቷል ።....
አስባችሁታል ? ኦባማ ኢራቅን በቦንብ ማረሱን ፡ ሶሪያ ላይ የቦንብ ውርጅብኝ ማዝነቡን ረስቶ. .. ታሊባንን በመምታት ሰበብ አፍጋኒስታን በቦንድ እንዳላጋያት ሁሉ. .....
ያችን የአረብ ምድር ገነት ተብላ የሚቀናባትን ሊቢያን ከተሞቿን በቦንብ አውድሞ ወደፍርስራሽነት የለወጠው ሶዬ. .. ....
ሰላማዊቷን የመንን አገር እስከማትመስል ድረስ ቦንብ እንዳላዘነበባት ፡ እዚህ ጎረቤት ሶማልያን ሳይቀር በጀት የደበደበ ፡ ይህ ርህራሄ የለሽ መሪ ። ....
ይህ ጨካኝ ፕሬዝደንት ፡ በስልጣን በቆየባቸው ስምንት አመታት ፡ በነዚህ የሙስሊም ሀገራት ላይ በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሃን በቦንብ እንዲገደሉ ያደረገ ሰው ፡ ይህንን ወንጀሉን ረስቶ ፡ ሙስሊሙን ለምርጫ ቅስቀሳ ሲያውል ፡ መስማት ያናድዳል ።
Via wasihun