የኒው ኦርሊንስ ሽብር ተጠርጣሪ እስላማዊ መንግሥትን መቀላቀሉን ተናግሯል
በአውሮፓውያኑ የዘመን መለወጫ፣ ሰዎች በሞቱበት የኒው ኦርሊንሱ ሽብር ጥቃት ተጠርጣሪ፣ ድርጊቱን በእስላማዊ መንግሥት አሸባሪ ቡድን ተነሳስቶ ብቻውን የፈጸመው ይመስላል ሲል፣ ኤፍ ቢ አይ ትላንት ሐሙስ አስታወቀ። ተጠርጣሪው የጦር ሠራዊት አባል ነበር። መርማሪዎች ላስ ቬጋስ ውስጥ በአሜሪካ ወታደር ይሸከረከር ከነበረው ሌላ የተሽከርካሪ ጥቃት ጋራ፣ የጥቃቶቹ መነሻ ምክንያትና ተያያዥ ሊሆኑ ይችላሉ በሚባሉ ነገሮች ዙሪያ ምርመራዎችን ቀጥለዋል፡፡
የዋይት ሀውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክስዋራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
▶ ኢትዮጵያ በሶማሊያ ከሚሰማራው አዲስ ተልዕኮ ጋራ እንደምትተባበር አስታወቀች
በሶማሊያ አዲሱ የአፍሪካ ኅብረት የሰላም ተልዕኮ ከአል ሻባብ ጋራ ለሚያደርገው ፍልሚያ እንደምትተባበር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡ በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የድጋፍና የማረጋጋት ተልዕኮ በቅርቡ ወደ ሶማሊያ እንደሚሰማራ በመጠበቅ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋራ የፈጸመቸው የባሕር በር አቅርቦትን የተመለከተ የመግባቢያ ስምምነት በፈጠረው ውጥረት ምክንያት፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች ተሳተፎ እንደማይኖራቸው ሶማሊያ ስታስታውቅ ብትሰነብትም፣ቱርክ ላይ በተፈጸመው የሰላም ስምምነት ውጥረቱ ሊረግብ ችሏል።
የኢትዮጵያው መከላከያ ሚኒስትር አይሻ ሞሃመድ ትላንት ሐሙስ በሶማሊያ ጉብኝት በማድረግ ከሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼኽ ሞሃሙድ ጋራ ተወያይተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክት ማድረሳቸውን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአወጣው መግለጫ አስታውቋል።
“ውይይቱ በሶማሊያ እና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ሁለቱ ሀገራት በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ቁርጠኝነት ደግመው ያረጋገጡበት ነው” ሲል የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በአወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
👉 የአሜሪካ ድምፅ የቀጥታ ሥርጭት ታኅሣሥ 25 ቀን 2017 ዓ.ም.
ጋቢና ቪኦኤ
🎙 ጋቢና ቪኦኤ የአዲሱ ትውልድ ድምፅ በአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ክፍል ተዘጋጅቶ የሚቀርብ የወጣቶች መርኃግብር ነው፡፡
▶ የአኝዋክን ታሪክ ሰናጅ ወጣት
በጋምቤላ የሚነገሩ ተረቶችን እና አፈታሪኮችን ለመጀመሪያ ግዜ በአኝዋክ ቋንቋ ፅፎ በመፅሃፍ መልክ በማሳተም ጋምቤላ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች በነፃ ያከፋፈለው የጋምቤላ ተወላጅ ወጣት ጄኮፕ ኦሞድ፣ አሁን ደግሞ "ሉዎ ኦፍ ዌስተርን ኢትዮጵያ" ወይም "በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው የሉዎ ማህበረሰብ" የተሰኘ የታሪክ መፅሃፍ ፅፎ ለገበያ ቅርቧል። በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ ነዋሪ የሆነው እና በኒውሮ ሳይንስ የህክምና ዘርፍ የተሰማራው ጄኮፕ በመፅሃፉ የጋምቤላ ማህበረሰብ በታሪክ ያሳለፈውን ውጣ ወረድ እና ፅናቱን እንዲሁም የነገ ተስፋውን እንደሚያስቃኝ ገልጿል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪድዮ ፋይል ያገኛሉ)
በኒው ኦርሊንስ በመኪና የተፈጸመው ጥቃት እንደ ሽብር ጥቃት በመመርመር ላይ ነው
⚫ የሟቾች ቁጥር 15 ደርሷል
በአሜሪካ ሉኢዚያና ግዛት፣ ኒው ኦርሊንስ ከተማ ውስጥ ዐዲሱን ዓመት ለማክበር ተሰባስበው በነበሩ ሰዎች ላይ አንድ አሽከርካሪ መኪናውን በፍጥነት በመንዳት 15 ሰዎችን የገደለበትና ቢያንስ 35 ሰዎችን የጎዳበት ድርጊት እንደ ሽብር ተግባር ተቆጥሮ በመመርመር ላይ መኾኑን የፌዴራል ምርመራ ቢሮው (ኤፍ ቢ አይ) አስታውቋል።
አሽከርካሪው ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ መኪናውን አቁሞ ከፖሊሶች ጋራ ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ሊገደል ችሏል። በቴክሳስ ግዛት የተወለደው የ42 ዓመቱ ሻምሱድ-ዲን ጃባር የሠራዊት ዓባል የነበረና ከ10 ዓመታት በፊት የተሰናበት መሆኑ ታውቋል።
ተከራይቶት በነበረው ክፍት ወይም ፒክ አፕ መኪና የኋላ መጎተቻ ላይ የእስላማዊ መንግሥት ወይም አይሲስ ባንዲራን እያውለበለበ ‘በርበን ስትሪት’ ተብሎ በሚጠራውና በበዓላት ብቻ ሳይሆን፣ በአዘቦቱም ቀን ሞቅ ደመቅ በሚለው መንገድ ላይ ዐዲሱን ዓመት ለመቀበል ተሰባስበው በነበሩ ሰዎች ላይ መኪናውን በፍጥነት አሽከርክሮ ቢያንስ 15 ሰዎችን ገድሎ 35 የሚሆኑት ላይ ጉዳት አድርሷል።
https://amharic.voanews.com/a/us-new-orleans-casualties/7922320.html
ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
👉 የአሜሪካ ድምፅ የቀጥታ ሥርጭት ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም.
▶ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲከፈት የሚጠይቅ ሰልፍ በከተማው ተካሔደ
ዛሬ ታኅሣሥ 23 ቀን 2017 ዓ.ም በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መቐለ ከተማ ላይ በአካሔዱት ሰላማዊ ሰልፍ፣ በህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) አመራሮች መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ምክኒያት ለአድን ወር ተዘግቶ የቆየው የከተማው ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንዲከፈት ጥሪ አቅርበዋል።
በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች፣ ሁለት ከንቲባ የተሾመለት፣ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተዘግቶ “ታሽጓል” የሚል ጹሑፍ ከተለጠፈበትና በፖሊስ መጠበቅ ከጀመረ አንድ ወር ኾኖቷል።
ሰለፈኞቹ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት ከንቲባ ሥራ እንዲጀምሩም ጠይቀዋል። ሲያወዛግብ በቆየው የህወሓት ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር ኾነው የተመረጡት አቶ አማኑኤል አሰፋ፣ “የከተማ ከንቲባ በምክር ቤት እንጂ በግርግር እና በሰልፍ አይሾምም” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።
ከምሽቱ 3:00 የአማርኛ ዜና
👉 የአሜሪካ ድምፅ የቀጥታ ሥርጭት ታኅሣሥ 23 ቀን 2017 ዓ.ም.