ANWAR MEDIA —አንዋር ሚዲያ

ANWAR MEDIA —አንዋር ሚዲያ ከፌስቡክ እና ዩቲዩብ በተጨማሪ ለናንተ መረጃዎችን ለማድረስ ቴሌግራም ከፍተናል�ጆይን ፣ ሼር ማድረግዎትን አይርሱ�
http://t.me/AnwarMedia
http://t.me/AnwarMedia

12/16/2024

∝ ☞የልጃገረድ "ክብሯን "ለክብረ ቢስ ጎረምሳ በአንድ ምሳ አስረክባ ከዚያ ግን ወዲህ ዞራ በወግ በማዕረግ በሊሞዚን በመንዙማ ስትል ትንሽ አይሰቀጥጣትም.........? እንደው ትንሽ? Shame on you በተለይ ባሎች! ፑ! አሁን ካንተ ጋር ነው እንግሊዝን የምንገጥመው?

ወንድሜ ☆ክብሯን ካስረከበች★ በአንድ ጥብስ ብቻ ደግስ:: ክብሯ ካለማ ማህር ▶V8◀ ጀባት:: ለካ የቻይናም አለ:: በምን ይለይ ይሆን? ኤጭ! በቃ ተዋቸውና ኸልዋ ግባ:: ወይም በክብር የተፋታችዋን አግባ::

12/16/2024

↠"ሰርግ አልፈልግም:: ኒካህ ብቻ" ካለችህ ቀኝ ሗላ አዙረህ ንካው:: ዕውነቷን ከሆነ የፊታችን እሁድ ብላ መወሰን አለባት:: ካልሆነ ግን ልክ 3 ሳምንት ሲቀረው ያለምንም ዝግጅት የሰርግ ጦር ሜዳ ይዛህ ነው የምትገባው:: ሁሉንም ነገር አስገዝታህ በቃ አሁን የጣትና የአንገት ይቀራል ትልሃለች:: ከዚያ ገዝተህ ከጨረስክ በሗላ ውዴ ቬሎው ምን ዐይነት ከለር ይመችሃል? እያለች የማያልቅ የወጪ ግድብ ውስጥ ገብተህ በቦንድ ሽያጭ የማያልቅ እዳ ተሸክመህ ... በረካ የሌለው ትዳር ጀምረህ ... እዳውን ሳትጨርስ ልትለያይ ትችላለህ:: አንዳንዷ ምንም እንደሌለህ እያወቀች adventure film 🎞️ ትጫወታለች:: አንደኛውኑ እሷም የሰርጉ ማለትም የእቅዱ አካል ሆና ፍላጎቷን እቅጩን ነግራህ የመ-ሸበት አለ ማደር ነው:: (እና እሁድ ይሁን ወይ?)

...................2ኛ ሚስት ትክክለኛ ቦታው ባሏን ለማታከብርና ለወሬኛ ሚስት ነው:: ሌላ መድኃኒት የላትም:: አርፋ ቤቷ ቁጭ ነው የምትለው:: አንዳንድ ጣልቃ-ገብ ዘመዶቿም ትን...
12/10/2024

...................2ኛ ሚስት ትክክለኛ ቦታው ባሏን ለማታከብርና ለወሬኛ ሚስት ነው:: ሌላ መድኃኒት የላትም:: አርፋ ቤቷ ቁጭ ነው የምትለው:: አንዳንድ ጣልቃ-ገብ ዘመዶቿም ትንሽ ጨፍረው ... ልክ ወስደው እንደማያገቡዋት ሲያስታውሱ ሥርዓት ይይዛሉ::

ሳይወዳት ላገባት ባል ደግሞ መልኳ ሳይበላሽ በጊዜ መለያየቷ ጥሩ ነው:: ሆኖም ግን በደንብ ሳትዘጋጅ ዝም ብላ መለያየቷ ጥሩ አይደለም:: ሥራ ሳታገኝ ሥራ ከፈታህ አጎትህም አያበድርህም:: በትዳር እያለች እንዴት ትዘጋጅ? ለሚለው ጥንቃቄ ይፈልጋል:: ሁሉም ትዳር ችግሮች አሉበት:: የማይሻሻል ዓይነት ከሆነ ነው መለያየት እንጂ በሰበብ ባስባቡማ የትም አይገኝም::

-> የሚወድሽን አግቢ:: አንቺ ደግሞ የምታከብሪው ዓይነት ይሁን:: እንደማታከብሪው ከገመትሽ ይቅርብሽ:: አንዳንድ ሚስቱን የሚወድ ባል አለ .. ግን የሚጨቁን:: ይህ ወዳጅ ሳይሆን ለራሱ ብቻ የሚኖር ስግብግብ ሰው ነው:: ሰው እንደሆነች, አካሏ ሥጋ, አጥንት, ደም እንዳለው ይዘነጋል:: መውደድ ከማክበር ጋር:: መውደድ ካበቃ በማዘን, ማዘንም ካበቃ መለያየት::

መውጫ:- ሴት ልጅ የወር አበባና ወሊድን የሚያክል ነገር ተሸክማ ከወንድ እኩል ዲግሪ መሰጠት የለበትም:: ወንድ ቢኤ ሲይዝ ለሴት ማስተርስ መሆን ነበረበት:: ወሊድን የሚተካ ዲግሪ ይኖር ይሆን? የምታጠናው በወር አበባ ድብርት መሃል እንዲሁም በወሊድና በማጥባት distracted እየሆነች መልሶ ከወንድ እኩል ተወዳደሪ ማለት አግባብ አይደለም:: ሴቶች ግን እንዴት ያሉ ጠንካሮች ናቸው በአላህ::

12/09/2024

☞☞ምላስ እና ጥርስ☜☜
»℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡℡
≈ምርጥ ጎረቤት ምርጥ ጓደኛ⇚
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

ምላስ የሚተብተው ገራሚ ጎረቤቶችና ጓደኞች ስላሉት ነው:: የሆነ ተንኮል ከሠራ ላጥ ብሎ ይገባና ያደፍጣል:: ጓደኛው ጥርስ በሩን ይዘጋና አስፈላጊ ከሆነ ስቆ ይሸውድለታል:: የሚመታው ደግሞ ምላስ ሳይሆን ወይ ግንባር በቴስታ ወይ መቀመጫ በካልቾ ነው የሚረገጠው:: ጥርስ ተሳስቶ ምላስን ቢያደማ እንኳ ምላስ ጓደኛና ጎረቤቱን አይቀየምም:: ውለታ ጠባቂ ነው:: እንደውም ቆስሎ እንኳ ጥርስ እንዳይቆሽሽ ደሙን ይጠርጋል:: ጥርስ ውስጥ ባዕድ ነገር ከገባ ምላስ አያርፍም:: አንጎልን እረፍት ይነሳል:: እጅ ሥራ ይበዛበታል:: ጥርስ ውስጥ የገባውን በአስቸኳይ ማስወገድ አለበት:: ከወጣም በሗላ አያምንም ሁላ:: እየመጠጠ ቼክ ያደርጋል:: በዚህ መተሳሰብ ለዕድሜ ልክ ይኖራሉ:: ባልና ሚስት, ጎረቤታሞችና ጓደኛማቾች ከምላስና ከጥርስ ሊማሩ ይገባል::

12/08/2024

"Emotional intelligence"


Dignity

12/07/2024

......................ብዙ ሰው ካልተጨናነቀና ካልተከለከለ ያመነ አይመስለውም:: ያንተ መቸገርን የፈጣሪ የድሎት ምንጭ, ያንተ መራብ የፈጣሪ የጥጋብ በጀቱ አድርገህ ማየትህን ካልተውክ ኃይማኖትህ ቀርቶ ተራ ኑሮህ እራሱ የጤነኛ አይሆንም:: ኃይማኖት ማለት መልካም ኑሮ የመኖሪያ መስመር እንጂ የሆነ መንገድ ላይ ≪ danger ⚠️ ≫ ገመድ አስረህ ዘለልኩ/አልዘለልኩ obsession አይደለም:: የጾም ዓላማ ፈጣሪን ለማጥገብ ሳይሆን ስሜትህን ለመግራት እንዲሁም የሶላት ዓላማ ፈጣሪህን፣ ለማስታወስ, ፣መልካምነትን ለመላበስ እና disciplined የፕሮግራም ሰው ለመሆን ነው:: ≪እየሰገድክ ዲሲፕሊን ከሌለህ እርሳው≫ ::!

12/02/2024

.....አዲስ የተጋባችሁ ሰዎች ፌስቡክ ላይ ባትፎጋገሩ ጥሩ ነው :: የአንድ ኦሎምፒክ ዕድሜ (4 ዓመት) ይሁነው:: መጋባት በእናንተ አልተጀመረም:: በእናንተም አይቋጭም:: "የኔ" እያላችሁ ፐሮፍይል ያደረጋችሁትን፣ የፖሰታችሁትን ወደሗላ ሄዳችሁ "ወይኔ" እያላችሁ ከመደለትና only me ከማድረግ ትድኑ ዘንድ::

12/02/2024

☞☞ልትሠሩት ቀርቶ ልታስቡት በማትችሉት ነገር ሰው ጋር ልትጠሉም ልትጣሉም ትችላላችሁ:: እናንተ የማታውቁት ግን ስለናንተ የተወሩ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ:: የአንዳንዶቹ ቅንብር.... AI ያቀናበረው የሚመስል ሊሆን ይችላል:: AI ማለት Automated Iblees ማለት ይሆን? የኢብሊስ ቅንብሮች የወዳጆቻችሁን ልብ የመመረዝ ኃይል አላቸው:: የሩሕ ወዳጅ ግን ባልሆነው ቀርቶ በሆነውም ጭምር ልቡ ያልተበላሸው ነው:: ውዴታው ከልብም በላይ ሩሕ ላይ ስለሆነ:: ሌላው እንኳ እከክልኝ ልከክልህ የሚባል የእከካም ፍቅር ነው::

☞ጋብቻ በኢስላም☜⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄ ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት ከቸራቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አንዱ ነው .÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት...
11/10/2024

☞ጋብቻ በኢስላም☜
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት ከቸራቸው ማህበራዊ ጉዳዮች አንዱ ነው .
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
ጋብቻ ኢስላም ልዩ ትኩረት ከቸራቸውና ካበረታታቸው ማህበራዊ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ የነብያት ፈለግም ነው፡፡ (ገጽ፣ 196 ተመልከት)

ኢስላም ለጋብቻ ዝርዝር ድንጋጌና ስርዓትን በመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶታል፡፡ የባለ ትዳሮች መብት መከበር የጋብቻው ግንኙነት እንዲጎለብትና እንዲረጋ ያደርጋል፡፡ በመንፈስ የተረጋጋ፣ በእምነቱ የጸና፣ በሁሉም የማሕበራዊ ጉዳዮች ላይ የመጠቀ፣ ሕፃናት በውስጡ የሚያድጉበት የሆነን ስኬታማ ቤተሰብ ለመመስረት ያስችላል፡፡

ከነኚህ ኢስላማዊ ድንጋጌዎች መካከል፡

ኢስላም ለአንድ ጋብቻ ትክክለኛነት በባልም ሆነ በሚስት በኩል የግድ ሊሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶችን አስቀምጧል፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ኢስላም ለሚስትነት ያስቀመጣቸው መስፈርቶች፡
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
ሙስሊም፣ ወይም የመጽሐፍት ባለቤት ማለትም አይሁድ ወይም ክርስቲያን መሆን አለባት፡፡ ይሁን እንጂ ኢስላም ከሙስሊሟም ቢሆን በሃይማኖቷ ጠንካራዋን እንድንመርጥ ይመክራል፡፡ ምክንያቱም ወደፊት ለልጆችህ እናትና ተንከባካቢ፣ ለአንተ ደግሞ በመልካም ነገር ላይ የምታግዝህና የምታጸናህ እሷ በመሆኗ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ባለ ሃይማኖቷን ምረጥ አለያ እጅህ አመድ አፋሽ ትሆናለች›› (አል ቡኻሪ 4802 / ሙስሊም 1466)

ጥብቅና ጨዋ መሆን አለባት፡፡ በዝሙትና በእንዝላልነት የምትታወቅ ሴትን ማግባት ክልክል ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከምእመናት ጥብቆቹም ከነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም (ተፈቀዱላችሁ)›› (አል ማኢዳ 5)

ለዘላለሙ ሊያገባቸው እርም ከተደረጉ መሐሪሞቹ መካከል መሆን የለባትም፡፡ የዚህን ዝርዝር ማብራሪያ ከዚህ በፊት አሳልፈናል፡፡ በጋብቻው አንዲት ሴትን ከእህቷ ወይም ከአክስቶቿ ማለትም ከአባቷ እህት ወይም ከእናቷ እህት ጋር በአንድ ላይ ማግባት አይፈቀድለትም፡፡ (ገጽ፣ 200 ተመልከት)

ኢስላም ለባልነት ያስቀመጣቸው መስፈርቶች፡
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
ባል ሙስሊም መሆን አለበት፡፡ በኢስላም፣ ሙስሊም ሴትን ሃይማኖቱ የመጽሐፍ ተከታይ (አህለል ኪታብ) ወይም መጽሐፍ የለሽ ቢሆንም ለካሃዲ መዳር የተከለከለ ነው፡፡ ኢስላም አንድን ወንድ በባልነት ለመቀበል ወንዱ ሁለት ባህሪዎችን የተላበሰ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡

በሃይማኖቱ ጽኑ መሆኑና

መልካም ስነ ምግባር የተላበሰ በሆኑ ናቸው፡፡

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሃይማኖቱንና ስነምግባሩን የምትወዱለት ልጃችሁን ከጠያቃችሁ አጋቡት፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1084 / ኢብኑ ማጃህ 1967)

☞የባልና የሚስት መብቶች
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
አላህ (ሱ.ወ) በባልም በሚስትም ላይ ሊጠብቁት የሚገባ የሆነ መብት ሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም የጋብቻን ሕይወት የሚያሳምሩና የሚጠብቁ ነገሮችን በሙሉ እንዲፈፅሙ አነሳስቷል፡፡ እነኚህን ጉዳዮች የመጠበቅ ኃላፊነት በሁለቱም ወገን ላይ የተጣለ ነው፡፡ ባልም ሆነ ሚስት አንዳቸው ከሌላኛው የማይቻልን ነገር እንዲፈፅም መጠየቅ የለባቸውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ለነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኗኗር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው፡፡›› (አል በቀራ 228) የሕይወት ጉዞ ቀጣይነት እንዲኖረው አና የተከበረው ቤተሰብ እንዲጸና ነገርን ማግራራትና ጉድለትን ማለፍ እንዲሁም መለገስ ያስፈልጋል፡፡

☞የሚስት መብቶች

ቀለብና መጠለያ

አንድ ሰው በአካባቢው ተለምዶ መሰረት የባለቤቱንና የልጆቹን ወጪ የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡

ሚስት ባለ ሃብት ብትሆንም እንኳ፣ ባል ለሚስቱ የምግቧን፣ የመጠጧን፣ የልብሷንና የአስፈላጊ ጉዳዮች ወጪዋን የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡ እንዲሁም ለርሷ ተመጣጣኝ የሆነን መኖሪያ ወይም ማረፊያም ሊያዘጋጅላት ይገባል፡፡

የወጪ መጠን፡ ወጪ የሚለካው እንደ ባልየው የገቢ መጠንና እንደየ አገሩ የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን፣ ማባከንም ሆነ መጨናነቅ የሌለበት ሊሆን ይገባል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የችሎታ ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ፤ በርሱም ላይ ሲሳዩ የተጠበበት ሰው፣ አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጅ አያስገድዳትም፡፡›› (አል ጠላቅ 7)

ይህን ወጪ ሲሸፍን መመጻደቅ፣ እንዲሁም በመጨናነቅ እሷንም ሆነ እራሱን ማዋረድ የለበትም፡፡ ገንዘብ ሲያወጣ፣ አላህ (ሱ.ወ) በገለጸው መልኩ በመልካም እሳቤ ሊሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህ ሚስት በባሏ ላይ ያላት መብት እንጂ እርሱ በቸርነቱ የለገሳት አይደለም፤ እናም መብቷን በአግባቡ ሊጠብቅላትና ሊሰጣት ይገባል፡፡

በኢስላም፣ በሚስትና በቤተሰብ ላይ የሚወጣ ወጪ ከባድ ምንዳን ያጎናጽፋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ሙስሊም ከአላህ እመነዳበታለሁ በሚል እሳቤ በሚስቱ ላይ ወጪ ሲያወጣ ለርሱ ምጽዋት ይሆንለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 5036 /ሙስሊም 1002) በሌላም ዘገባ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በርሷ ብትመነዳባት እንጂ አንተ የአላህን ፊት ከጃይ ሆነህ አንድም ወጪን አታወጣም፤ በሚስት አፍ ውስጥ የምታስቀምጣት ጉርሻ እንኳን ብትሆን፡፡›› (አል ቡኻሪ 56 /ሙስሊም 1628) ወጪ አልሰጥም ያለ ሰው፣ ወይም እየቻለ ማውጣት ካለበት የቀነሰ ሰው፣ በርግጥ ከባድ ወንጀል ውስጥ ተዘፍቋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ለአንድ ሰው ወንጀለኛነት፣ የሚያስተዳድረውን ሰው ማንገላታቱ ይበቃዋል፡፡›› (አቡ ዳውድ 1692)

መልካም አኗኗር ወይም ግንኙነት

መልካም አኗኗር በሚለው የተፈለገው መልዕክት መልካም ስነ ምግባር የሚለው ነው፡፡ ልበ ለስላሳነት፤ ለብ ያለ ንግግርን መናገር፤ አንድም የሰው ልጅ ሊርቃቸው የማይችሉ ስህተቶችንና ድክመቶችን ችሎ ማለፍና የመሳሰሉትን ነው፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፤ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ)፤ አንዳችን ነገር ልትጠሉ፣ አላህም በርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡›› (አል ኒሳእ 19)

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከሙእሚኖች መካከል የተሟላው ሙእሚን በስነ ምግባሩ በላጭ የሆነው ነው፤ በላጮቻችሁ ለሚስቶቻቸው በስነ ምግባራቸው ጥሩዎቹ ናቸው፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1162)

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህም ብለዋል፡- ‹‹ከሙእሚኖች መካከል የተሟላው ሙእሚን በስነ ምግባሩ ጥሩውና ለሚስቱ ገራገር የሆነው ነው፡፡››

(አል ቲርሙዚ 2612 / አህመድ 24677)

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በላጫችሁ ለቤተቡ ጥሩዋችሁ ነው፤ እኔ ለቤተሰቤ ጥሩዋችሁ ነኝ፡፡›› (አል ቲርሚዚ 3895) አንድ ሠሐቢይ፣ ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ)፡- «አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ የአንዳችን ሚስት በሱ ላይ ያላት መብት ምንድን ነው?» በማለት ጠየቃቸው፤ እሳቸውም፡ ‹‹ስትበላ ልታበላት፤ ስትለብስም ልታለብሳት፤ ፊቷን ላትመታት፤ ላታዋርዳት፤ በቤትህ ውስጥ እንጂ ላታኮርፋት ነው፡፡›› አሉት፡፡ (አቡ ዳውድ 2142)

☞መቻቻል

የሴቶች ተፈጥሯዊ ባህሪ ከወንዶች ጋር ይለያያል፤ በመሆኑም ይህን የሚለዩባቸውን ባህሪያት ወንዱ ሊላመደውና አቅልሎ ሊመለከተው ይገባል፡፡ የጋብቻን ሕይወት ከብዙ አቅጣጫ ለማየት ጥረት ማድረግ አለበት፡፡ ማንም ከስህተት ነፃ አይደለም፤ እናም ስህተት ሲከሰት ትዕግስት ማድረግና ከስህተቱ ባሻገር ያሉትን መልካም ጎኖች መመልከት ያስፈልጋል፡፡ አላህ (ሱ.ወ)፣ ባልንም ሚስትንም፣ አንዱ የሌላኛውን መልካም ወይም ጠንካራ ጎን እንዲመለከቱ ያሳስባል፡፡ እንዲህ ይላል፡- ‹‹በመካከላችሁም ችሮታን አትርሱ፡፡›› (አል በቀራ 237)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣ ለሴቶች ልዩ ትኩረት እንዲሰጣቸውና ወንዶች በመልካም እንዲኗኗሯቸው አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም የሴቶች መንፈሳዊና ስጋዊ ባህሪያቸው ከወንዶች ጋር እንደሚለያይ ተናግረዋል፡፡ ይህ የባህሪ ልዩነት ለአንድ ቤተሰብ መደጋገፊያና ውበት መሆኑንም አስተምረዋል፡፡ እናም ይህ የባህሪ ልዩነት የመለያየትና የፍቺ መንስኤ ሊሆን አይገባም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሴት የተፈጠረችው ከጎን አጥንት ነው፤ በምንም ጉዳይ ላይ ላንተ አትስተካከልልህም፤ በሷ ልትጠቀም ከፈለግህ ከነጉብጠቷ ልትጠቀምባት ትችላለህ፤ ለማቃናት ከሞከርክ ግን ትሰብራታለህ፤ ስብራቷም መፈታቷ ነው፡፡›› (አል ቡኻሪ 3153 / ሙስሊም 1468)

ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም

አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም፡፡ ቢያንስ በአራት ቀናት አንዴ ይህንን ሊፈፅም ይገባል፡፡ ከአንድ በላይ ያገባ ከሆነም የሳምንቱ ቀናቶችን በእኩልነት በሚስቶቹ መካከል ሊከፋፍል ይገባል፡፡

ክብርህና ሞገስህ ስለሆነች ልትከላከላት ይገባል፡፡

አንድ ሰው ሲያገባ፣ ያገባት ሴት የእርሱ ክብሩ ነች፡፡ ስለሆነም ለሞት የሚዳርገው ቢሆንም እንኳን ይህን ክብሩን ሊከላከልና ሊሟገትለት ይገባል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ስለ ሚስቱ የተገደለ ሰው ሰማዕት ነው፡፡›› (አል ቲርሚዚ 1421/ አቡ ዳውድ 4772)

የሚስትን ሚስጥር አለማባከን

አንድ ሙስሊም፣ የሚስቱን ልዩ ባህሪያትና፣ በርሱና በርሷ መካከል ስለ ተፈፀመ የአልጋ ላይ ሚስጥር ለሰዎች ሊያወራ አይፈቀድለትም፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹የትንሳኤ ቀን ከሰዎች ሁሉ ከደረጃ በኩል የከፋ ሰው ማለት፣ እርሱ ለሚስቱ ተገላልጦ፣ ሚስቱም ለርሱ ከተገላለጠች በኋላ የሷን ሚስጥር አውጥቶ የሚበትን ሰው ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ (ሙስሊም 1437)

በሴት ላይ ድንበር ማለፍ አይፈቀድም

ኢስላም ለሚፈጠሩ ችግሮች በርካታ መፍትሄዎችን አስቀምጧል፡፡ ከነዚህም መካከል፡

ስህተቶች በመወያየት፣ በመመካከርና በተግሳጽ ሊታረሙ ይገባል፡፡

ከሦስት ቀናት ላልበለጠ ጊዜ አለማናገር ወይም ማኩረፍ ከዚያም ከቤት ሳይወጣ በመኝታና በግብረ ስጋ ግንኙነት ማኩረፍ ይፈቀድለታል፡፡

እመት ዓኢሻ እንዲህ ብለዋል፡- ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአላህ መንገድ ላይ ሲዋጉ ካልሆነ በስተቀር አንዲትንም ሴት ሆነ ባሪያ መራቅ አያውቁም፡፡

ማስተማርና መምከር

ሰውየው ሚስቱን በመልካም ሊያዛትና ከመጥፎ ሊከለክላት ይገባል፡፡ ወደ ጀነት ጸጋ የሚያዳርሳቸውን፣ ከእሳት ቅጣት የሚያርቃቸውን ነገሮች በማመቻቸትና በሱም ላይ በማበረታታት፣ እንዲሁም እርም ነገሮችን በመከልከልና እንዲጠሉ በማድረግ ልዩ ትኩረት መስጠት አለበት፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ሚስትም ባሏን በመምከር፣ ወደ መልካም ነገር በመገፋፋትና በመጠቆም፣ ልጆችን በጥሩ ስነ ምግባር ኮትኩቶ በማሳደግ ላይ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ፡፡›› (አል ተህሪም 6) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሰውየው በሚስቱ ላይ ጠባቂ ነው፣ ስለጠበቀው ነገር ይጠየቃል፡፡›› (አል ቡኻሪ 2416 /ሙስሊም 1829)

ሚስቱ ያስገባችውን ቃል መጠበቅ

ባል በጋብቻ ውል ላይ የተጠቀሱ ቅድመ መስፈርቶችን የመጠበቅና የመሙላት ግዴታ አለበት፡፡

ጋብቻው በሚፈፀምበት ጊዜ፣ ሚስት ለምሳሌ፣ ይዘቱ ለየት ያለ ቤትን ሊገዛላት ወይም ሊሰራላት ዓይነት የተፈቀዱ ነገሮችን እንዲፈፅምላት ቃል ካስገባችው፣ ቃሉን የመጠበቅና የመሙላት ግዴታ አለበት፡፡ ምክንያቱም የጋብቻ ውል ከቃልኪዳኖች ሁሉ ትልቁና ከባዱ በመሆኑ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ከመስፈርቶች ሁሉ እጅግ በርሱ ልትሞሉ የሚገባው ብልትን የተፈቀደ ያደረጋችሁበት ቃል ኪዳን ወይም መስፈርት ነው፡፡›› (አል ቡኻሪ 4856 /ሙስሊም 1418)

የባል መብቶች

በመልካም ነገር ላይ እሱን የመታዘዝ ግዴታ አለባት

አላህ (ሱ.ወ) ወንድን በሴት ላይ የበላይ አስተዳዳሪ አድርጎታል፡፡ ይኸውም ልክ የአገር መሪዎችና አስተዳዳሪዎች ለሕዝብ እንደሚያገለግሉት፣ ጉዳይዋን የሚያስፈፅምላት፣ መስመር የሚያስይዝላትና የሚከታተልላት እሱ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው አላህ (ሱ.ወ) ለወንድ ልዩ መገላጫዎችን የሰጠው በመሆኑና በንብረት የማስተዳደር ኃላፊነት በሱ ላይ የተጣለ በመሆኑ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፤ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘባቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡›› (አል ኒሳእ 34)

ባሏ እንዲረካባት መዘገጃጀት ወይም መመቻቸት

ባል በሚስቱ ላይ ካለው መብቶች አንዱ፣ እርሱ ግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲፈፅም እራሷን ማመቻቸትና እንዲረካባት ማድረግ ነው፡፡ በመሆኑም ሆን ብላ ለርሱ መቆነጃጀትና መዘገጃጀት ይወደድላታል፡፡ የወር አበባ ደም ላይ መሆን፣ ወይም የግዳጅ ጾም ላይ መሆን፣ ወይም በህመምና በመሳሰሉት ሸሪዓዊ ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር፣ ሚስት ባሏ ሊገናኛት እየፈለገ ወይም ሲጠራት ፈቃደኛ ካልሆነች እጅግ በጣም ትወገዛለች፤ ከባድ ወንጀልንም ትሸከማለች፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ሰው ሚሰቱን ወደ ፍራሹ ሲጠራት እንቢተኛ ከሆነችና ተቆጥቶባት ወይም ተከፍቶባት ካደረች እስኪነጋ ድረስ መላእክት ይረግሟታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 3065 /ሙስሊም 1436)

ባል ወደቤቱ እንዲገቡ የማይፈልጋቸውን ሰዎች እንዲገቡ አለመፍቀድ

ባል በሚስቱ ላይ ካለው መብቶች መካከል ሚስት እርሱ ከሚጠላቸው ሰዎች አንዱንም አለማስገባት ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንዲት ሴት በርሱ ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር ባሏ እያለ ልትጾም አይፈቀድላትም፤ በሱ ፍቃድ ካልሆነ በስተቀር በቤቱ ውስጥ ሰው እንዲገባ መፍቀድ የለባትም፡፡›› (አል ቡኻሪ 4899)

በባል ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር ከቤት አለመውጣት

ባል በሚስት ላይ ካሉት መብቶች አንዱ ያለርሱ ፍቃድ ከቤት አለመውጣት ነው፡፡ ልዩ ቦታ ለመሄድ መውጣቷም ይሁን ለስራ ጉዳይ መውጣቷ ሁለቱም አንድ ነው፡፡ ያለ ባል ፈቃድ አይሆንም፡፡

ሚስት ባሏን መንከባከብ

ሚስት ባሏን በሀገሬው ተለምዶ መሰረት ምግብ በማዘጋጀትና መሰል በሆኑ በቤት ውስጥ ጉዳዮች ልትንከባከበው ይገባል፡፡

11/10/2024

☞☞ኢስላማዊ ጋብቻና ጥቅሞቹ☜☜
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::;::::::::
እንደሚታወቀው ጋብቻ አሏህ ለኛ ለሰው ልጆች ከሰጠን ኒእማዎች መካከል አንዱ ነው። ትዳር የሰው ልጅ ከመጀመሪያው ሲፈጠር በትዳር የተረጋጋና ደስተኛ ህይወትን ይመራበት ዘንድ አሏህ ያስቀመጠው የስነ-ፍጥረት ህግ ነው፡፡
================================
ኢስላም እያንዳንዱ ግለሰብ ፣ ማህበረሰብ ባጠቃላይ የሰው ልጅ የትዳርን ጥቅም እንዲያገኙ ሁሌም ወደ ትዳር አለም ጥሪ ያደርጋል።
================================
ትዳር የህይወታችን ወሳኝ ክፍል እንደመሆኑ በኢስላም ልዩ ስፋራ አለው። የኢማናችን ግማሽ እንደሆነም ተገፃል።

▼☞የትዳር ጥቅሞች☜
⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄
☞ኢማንን ሙሉ ያደርጋል

☞ደስተኛና ፅኑ የቤተሰብ ፍቅር መስርቶ ለመኖር ያስችላል

☞የማህበራዊ ህይወት ቀጣይነት እንዲኖረው ያደርጋል

☞ፍቅርን እና አጋርነትን ያስገኛል

☞የሰው ልጅ የዘር ሃረግ እንዳይቋረጥ ልዩ ሚና ይጫወታል

☞የአሏህን ውዴታ ያስገኛል

☞የአሏህ ባሪያ ፣ ሷሊህ የሆኑና ኢስላምን የሚያገለግሉ ልጆችን በኢስላማዊ አደብ ኮትኩቶ ለማሳደግ ይረዳል

☞የረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ኡመት ከሌሎች ነብያቶች ኡመት በላይ ከፍ ያደርጋል

☞ከሃራም ነገር ይጠብቃል

☞የአሏህን ህግጋት ከመጣስ ያድናል

☞ዘርን ያስገኛል

☞የአእምሮ ሰላምን ፣ ደስታና ምቾትን ያጎናፅፋል

☞ቀልብ የሰከነች እንድትሆን ሲያደርግ ወደ ስኬትም ያመራል

☞ከሸይጧን ወጥምድ ይጠብቃል

☞ቀላል የሆነ የአኗኗር ዘይቤ እንዲኖረን ያደርጋል

11/05/2024

«ኢትዮጲያም አበደረች » አሜሪካ ከዓለም 50 ትሪሊዮን በላይ ተበድራለች ይባላል:: ከእኛው የተበደረችውን አትርፋ ታበድረናለች:: ኢትዮጵያም ከአይ ኤም ኤፍ ተበድራ አበደረች:: ብልጠት እንዲህ ነው:: ቻይና መንገድ የምትሠራልን ብዙውን ከራሷ አምጥታ ሳይሆን ለአፍሪካ የሚመጡ የሆኑ ፈንዶች አሉ:: ባለፈንዶቹ ውጤቱን ይፈልጋሉ:: ብድሩ በእኛ ስም ቢመጣም ዓለም አቀፍ ተቋራጭና ተቃራጭ ሆነው ይመጣሉ:: ፈንዱን አየር ላይ አቅጣጫ አስቀይሰው ይጠልዙታል:: ኢትዮጵያ ማበደርን በ«ደቡብ ሱዳን »እየተለማመደች ነው:: አትርፈን ማበደራችን ሳይሆን «ለማበደር» መውጣታችን እራሱ ትርፍ ነው:: ለደቡብ ሱዳን ፊያት ሰጥተን በወርቅ መቀበል እንዳይዘነጋ:: አደራ:: ሌላም እንደዚህ ጠቆር፣ ጠቆር ያሉትን እየፈለግን አበድረን ተለማምደን ከዚያ ወደ ጠይሞቹ ከዚያ ወደ ብጫዎቹ እንሄድና በመጨረሻም ለራሰ በራዎች እናበድራለን:: ይህም መሆኑ አይቀርም ።

11/02/2024

"ጥሩ ሰው ምን አይነት ነው?
"""""""""""""""""''""""""""""“""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት ይችላሉ ወይስ ሁሉም ሰው ሊያጠቃዎት እንደሆነ ያስባሉ? ከሰዎች ጋር በሚያደርጉት ንግግር ሁሌም ግልጽ ነዎት ወይስ ሁሉንም ነገር አስልተውና ተጠንቅቀው ነው የሚናገሩት?

ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሽ በዕለት ተዕለት የህይወት ዘይቤዎ በቀላል አገላለጽ "ቅዱስ" የሚባሉ አይነት ሰው ስለመሆንዎ እና አለመሆንዎ የመናገር አቅም አላቸው። በቅርቡ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች ባወጡት መዘርዝር መሰረት ሰዎችን ጥሩ የሚያስብሏቸው ምን አይነት ባህሪያት እንደሆኑና መጥፎም የሚያስብሏቸው የትኞቹ እንደሆነ አስቀምጠዋል።

• ጓደኛ ለማፍራት ማወቅ ያለብን ጠቃሚ ነጥቦች

ከሁለት አስርታት በፊት የወቅቱ የሥነ አእምሮ ባለሙያዎች የሰው ልጅን ጥሩም ሆነ መጥፎ ባህሪያትን ለመረዳት በማሰብ ሦስት ዋና ዋና መገለጫዎችን ለይተው ነበር። የመጀመሪያው ከእራስ ጋር በፍቅር መውደቅ ወይም 'ናርሲሲዝም' ተብሎ የሚታወቀው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የራስን ጥቅም ለማስጠበቅ የትኛውንም ነገር ለማድረግ ዝግጁ መሆንን የተመለከተ ነው። የመጨረሻው መገለጫ ደግሞ ከባድ የሥነ ልቦና ችግር ማስተናገድ ነው።

ከዚህ ግኝት በኋላ የዘመኑ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች እነዚህን መገለጫዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ሰዎች በሥራ ቦታ እንዴት ስኬታማ እንደሚሆኑ፣ ግንኙነቶች እንዴት እንደሚመሰረቱና እንደሚፈርሱ እንዲሁም ውስጣዊ እርካታ እንዴት እንደሚገኝ ለማጥናት ሞክረዋል።

በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ባለሙያና መምህር የሆኑት ስኮት ቤሪ ኮፍማን እንደሚሉት ሰዎች ብዙ ጊዜ ከጥሩው ባህሪያቸውና ማንነታቸው ይልቅ ወደ መጥፎውና በመጠራጠር የተሞላውን ውስጣዊ ስሜት እንደሚመርጡ ይናገራሉ።

"ልናበረታታውና ሁሌም ልንንከባከበው የሚገባንን ባህሪ ለምን ገሸሽ እንደምናደረገው አይገ

ስኮት ቤሪ ኮፍማን ከጓደኞቻቸው ጋር በመሆን በሰሩት ጥናት መሰረት ደግሞ ሰዎች ጥሩ ባህሪ እንዳላቸው ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ መገለጫዎችን አስቀምተዋል። በዚህም መሰረት በጥናቱ የተሳተፉት ሰዎች፤ የሰዎችን ጥሩ ጎን በቀላሉ ማየት እና ይቅር ባይነት፣ የሌሎችን ስኬት ማድነቅ እንዲሁም ሰዎችን ያለፍላጎታቸው አንድ ነገር እንዲያደርጉ ከማስገደድ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ምልክቶችን አሳይተዋል።

የመጀመሪያው መገለጫ 'ሂዩማኒዝም' ወይም ሰብአዊነት ነው። ይህም የሰዎችን ክብርና ሙሉ አቅም በቀላሉ መረዳት መቻል ነው። ሁለተኛው 'ካንቲያኒዝም' የሚባል ሲሆን ስያሜው ኢማኑኤል ካንት ከተባለው ፈላስፋ የመጣ ሲሆን ሰዎችን ከእራሳችን መነጽር ብቻ መመልከት እንደሌለብን የሚያትት ነው።

ሦስተኛው ደግሞ 'ፌዝ ኢን ሂዩማኒቲ' በሰው ልጆች እምነት መጣል እንደ ማለት ሲሆን በዚህኛው መገለጫ ሰዎች ሁሌም ጥሩ ናቸው ብሎ መረዳትና የትኛውም ሰው ማንንም ለመጉዳት አያስብም ብሎ ማሰብን ያካትታል።

የሥነ ልቦና ባለሙያው ዊሊያም ፍሊሰን እንደሚለው የሰው ልጆች በባህሪያቸው ጥሩ ናቸው ብሎ ማሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነው። እሱ እንደሚለው ሰዎች በአጠቃላይ ጥሩ ናቸው ብለን ባሰብን ቁጥር እራሳችንን ከሰዎች መከላከል አለብን የሚለው ተፈጥሮአዊ ስሜት እየቀነሰ ይመጣል።

ስለዚህም መጥፎ ነገር እንኳን ቢፈጽሙ ለመቅጣት ወይም ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ ከማሰብ ይልቅ ይቅርታ ማድረግ ቀላል ይሆናል ማለት ነው።

ስኮት ቤሪ ኮፍማን አረጋግጫለሁ እንደሚሉት በሄዱበት ሁሉ ለሰዎች ደግነትንና ጥሩነትን የሚያሳዩ ሰዎች በህይወታቸው ደስታና የእርካታ ስሜትን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። ከዚህም ባለፈ ከፍ ያለ የራስ መተማመንና በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ይስተዋልባቸዋል።

ነገር ግን የጥሩ ሰዎች መገለጫዎች ምንድናቸው? ፍቅር፣ ደግነት፣ የቡድን ሥራ፣ ይቅር ባይነት፣ አመስጋኝነት፣ በሰዎች ስኬት አለመቅናት፣ አሳቢነት ወይስ ለብዙዎች ጥቅም መቆም?

መርካቶ አንድ  አብዱል መሊክ ከሚባል ወንድሜ ጋ ደውዬ ነበር:: መኖሪያውም መስሪያውም እዚያው ነው:: በቅርበት ቢሆኑም እነርሱ ቤት አልደረሰም:: ሁኔታው ሲያስረዳኝ አንዱ አንዱን መርዳት እ...
10/22/2024

መርካቶ አንድ አብዱል መሊክ ከሚባል ወንድሜ ጋ ደውዬ ነበር:: መኖሪያውም መስሪያውም እዚያው ነው:: በቅርበት ቢሆኑም እነርሱ ቤት አልደረሰም:: ሁኔታው ሲያስረዳኝ አንዱ አንዱን መርዳት እንዳይችል እንኳ ከአንድ ቤት የአራት ወንድማማቾች ሱቅ ወድሟል:: እንደማያድኑት ሲያውቁ የጓደኞቻቸውን ንብረት ወደ ማዳን ገቡ:: እኛ ግቢ የብዙ ጓደኞቻችንን እቃ አሳድረን አሁን ለየባለቤቶቹ አድለን ጨረስን:: እጃችን መድማቱን ያየነው ሲነጋ ነው:: የእሳት አደጋ ኃላፊውም ጭምር እዚሁ ነው ያነጉት:: በዚሁ ሁኔታ ግን አብረውን ሲበሉ የነበሩ "አስቀምጥ እንጂ" እያልን ሲዘርፉ የነበሩ ነበሩ:: ያለንበት ግብረገባዊ ደረጃችን ያሳዝናል:: ከዚህም ሌላ የሚያሳዝነው እሳቱ ከስር እየነደደ ፎቁ ላይ የነበሩ ወጣቶች ዘና ብለው በሞባይላቸው እየቀረጹ ነበር:: እሳቱ ሲባባስ እንዴት እንደወረዱ አላውቅም:: በጭስ ታፍነው ሆስፒታል የገቡ እንዳሉ ሰምቻለሁ:: ወንድም ወንድሙን እንዳያቋቁም በመደዳ የወደመባቸው በጣም ያሳዝናሉ:: የአንዳንድ ሰው ጥንካሬ የራሱ እንደወደመት ሲያረጋግጥ የሌላ ሰው ንብረት ወደማዳን የሚሮጥ እና ከውድመቱ መኃል ለዘረፋ የሚሯሯጥ አይተናል:: እዚያው እንደተፋዘዝን ነን:: (አሁንም ቢሆን ድንጋጤው አለ ፣አለቀቀንም

10/20/2024

#ዝምተኛ እና #ትግስተኛ ------------------------------------------------------------------ ዝምተኛና ትእግስተኛ የተለያዩ ናቸው::ትእግስት ከቃሉ ትርጉም መከራን፣ችግርን፣ እና የትኛውንም ውጣ ውረድያለምንም መሰላቸት እና መበሳጨት የመቀበል ብቃት ነው ። ነገሮችን ንቀን እናልፋለን እንላለን እንጂ አልናቅናቸውም:: ውስጣችን ሌላ ሥራ እየሠራ ነው:: ቆሽታችን እያረረ, ጨጓራችን እየተጎዳ, ጉበታችን እየከሰለ ይሆናል:: ትእግስት ማለት ውስጥ ከቶ ከድኖ በዝምታ ማለፍ ማለት አይደለም:: እንደውም ከድኖ ከሚያበስለው ለፍላፊውና አልቃሻዋ ይሻላሉ:: ይወጣላቸዋል:: ትእግስት ማለት ክፉ ለዋለብን ደግ መዋል, ይቅርታ መጠየቅና ምንም እንዳልተፈጠረ መውሰድ ነው:: ለአላህ ሰጥቸዋለሁ ብሎ መቀመጥም ስህተት ነው:: ብንሰጠው ባንሰጠው እርሱ እንደሆን ያውቀዋል:: እንደውም ይቅርታ ስንል ነው ለእርሱ የሰጠነው:: ጥሩ ስንሆን ሰራዊቱ ሁሉ በዙሪያችን ያሰልፋል:: ጊንጥና እባቡም ጭምር ተባባሪ ይሆናሉ:: ፊታችን ከፓውዛ መዓዛችን ከሽቶ ይጠነክርልናል::

10/06/2024

_ዛሬ ምሽት ላይ መሃል አዲስ አበባ የመሬት፣መንቀጥቀጥ አለ ሲባል ሰምቸ ለአንድ ለምወደው ጓደኛየ ደወልኩ እውነት ነው በመሃል አዲስ አበባ የመሬት መንቀጠቀጥ ተከስቷል ሲባል ሰማሁ እውነት ነው አልኩት አዎ አለኝ:: ፎቅ ላይ የሚኖሩ ዘመዶች ሲደውሉ ነው ያወቅኩት አለኝ:: እኔም «አይሰው ከመሬት ያለ ሰው② ደርሶበት ያላየው መፍረድ የቀለለው አይ መሬት ያለ ሰው» አልኩት!:: ለማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተደጋገመ ስለሆነ ስልኮቻችንና ኢንቦክሶቻችንን ካላስፈላጊ ወሬ እንዲሁም በዋናነት ነፍሶቻችንንም ፣ በተውበት ወይም በንስሃ እናጽዳ:: የዛሬው 4.9( earthquake strikes) ደረጃ ስለሆነ ተርፈናል እንጂ በሰከንዶች ውስጥ ባለንበት ቦታ ነው አጉል የምንሆነው:: ብልግና ቤት እየባለገ አስከሬኑ የሚገኝ ብዙ ሰው ይኖራል:: ለሁለቱም አለም አሳፋሪ ሆኖ ከመሞት አላህ ይጠብቀን::

10/06/2024

~~"በሀገራችን አነስተኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል።መሬት መንቀጥቀጥ አላህ ባሮቹን ከሚያስፈራራበት እና ከሚያስጠነቅቅበት ክስተቶች መካከል አንዱ ነው::"



በእኛ እግር ዘወትር የምትረገጠው መሬት በጌታዋ ትዕዛዝ ትንቀጠቀጣለች:: ህዝቦች በወንጀል ሲዘፈቁ፣ ሽርክ እና ጥፋት ሲንሰራፋ፣ በምድራችን ብክለት ሲስፋፋ ጌታችን አላህ ሰዎች ከጥፋታቸው ታርመው ወደሱ ይመለሱ ዘንድ ማስጠንቀቂያዎችን ይልካል:: ከነዚህ ማስጠንቀቂያዎች አንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ ነው::

ይህ ማስጠንቀቂያ ካለንበት የወንጀል አረንቋ በመውጣት ወደ አላህ እንድንመለስ የማንቂያ ደውል ነው::

በሀገራችን የተከሰተው መሬት መንቀጥቀጥ በትንሹ ተከስቶ ያለፈ ቢሆንም ከበድ ያለ ሆኖ ቢከሰት ባለንበት የወንጀል አረንቋ እንደተዘፈቅን ወደ ጌታችን ፊት የምንቀርብበት ሁኔታ ይፈጠር ነበር::

ይህ ከመሆኑ በፊት አሁን ላይ እድል አግኝተናል:: ወደ አላህ እንመለስ:: ጌታችንን አብዝተን ምህረትን እንለምን:: አላህ እንዲታረቀን ፣በእዝነቱ እንዲያየን በዱኣ ልንበረታ ይገባል ።

10/01/2024

~~ከስድስት አመትበፊት ተጎራብተን እንኖር ነበር። በስልኬ ተደዎለ፣ቁጥሩ አዲስ ቁጥር ስለነበር አላወኩትም ፣አነሳሁት ሃሎ ስል ከአመታት በፊት የተጎራበትኳቸው፣የበፊት ጎረቤቶቸ ናቸው።አንዷ በጎን ፣አንዷ ደግሞ ፊት ለፊት ይኖሩ ነበር።ሰላም ናችሁ ሁላችሁም ብየ ጠየኩ?ሰላም ነን አሉኝ ፣መሻ አላህ ሁልጊዜ ሰላማችሁን ያብዛላችሁ አልኳቸው! በጎኔ በኩል ትኖር የነበረችው ጎረቤቴ « ባሌ ለኔ ጊዜ የለውም:: ረስቶኛል:: ጠዋት ሥራ ነው:: ማታ ሥራ ነው:: አሁንስ መፋታት ነው የምፈልገው » ስትለኝ ከፊትለፊት የነበረችው ሴት ደግሞ «ለባለቤቴ ሥራ ፈልግለት:: በጣም ተጨናነኩ የት ሂጀ ልጥፋ፣እያለ ነው:: እራሱን እንዳያጠፋ ሁሉ ሰጋሁ:: ተኝቶ ነው የሚውለው:: እንደው፣ ከእነ እንትና ጋር ዘበኝነት እንኳን ቢሆን ጠይቅልኝ» አለችኝ:: የሰው ፍላጎት መለያየት፣ያንዳንዱ ደግሞ አለማመስገን እየገረመኝ ያው ጎረቤቴን አንድ ስራ አናግሬለት ዘበኝነት ላስገባው አስቤ ነበር:: ባስገባው ሁለቱም ሴቶች እረፍት ያገኙ ነበር:: ሥራ ያጣው ወዲህ ባሏ በሥራ ቢዚ የሆነባት ጋር ዘበኝነት ባስገባው እያልኩ ነው:: ችግሩ ከውል ውጭ( over time) እያሠራች የጉልበት ብዝበዛ እንዳታካሂድበትና ክፍተቷን እንዳትሞላበት ፈራሁ:: If you know. እ ደግሞ "የአፋታኝ" ጭቅጭቋንም ጠላሁ:: መፋታታቸውም አይቀሬ ይመስላል:: አንዱ ቤት በጥጋብ አንዱ ቤት በረሃብ ሊበተን ነው:: በእነሱ ቦታ ብትሆኑ ምን ታደርጉ ነበር? ምንስ ልትመክሯቸው ትችላላችሁ ?እስኪ ኮሜንት ላይ ምክርና አስተያየታችሁን አስቀምጡልኝ።

09/27/2024

⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄⇄÷⇄⇄ ♨♨♨♨♨♨♨♨♨♨♨♨ ♨♨ አንቺን የመሰለች ምርጥ ሚስት የሰጠኝ አላህን……… ብሎ ሳይጨርስ ዘላ አፉን ያዘችው:: ካመሰገነ እንዳይጨመርለት ነው እኮ:: ከጎድን ተፈጥራ እንዲህ ከሆነች፣ ከአከርካሪ ብትሆን ኖሮ እንዴት ልትሆን ነበር ?

Address

Washington D.C., DC

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANWAR MEDIA —አንዋር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share