Christian ዜማ Tube

  • Home
  • Christian ዜማ Tube

Christian ዜማ Tube Christian media There is no such thing.”
“Aim at heaven and you will get earth thrown in. The only thing it cannot be is moderately important.”
(1)

“We must show our Christian colors if we are to be true to Jesus Christ.”
“God cannot give us a happiness and peace apart from Himself, because it is not there. Aim at earth and you get neither.”

“Christianity, if false, is of no importance, and if true, of infinite importance.

23/12/2024

!! #ኢየሱስ!!

 #ተለቀቀ
23/12/2024

#ተለቀቀ

  ‼️‼️🔥ልዩ የትምህርት እና የአምልኮ ኮንፈረንስ   ጀምሮ ባሉት    አይቀርም!!  #ሼር!!
23/12/2024

‼️‼️🔥
ልዩ የትምህርት እና የአምልኮ ኮንፈረንስ ጀምሮ ባሉት አይቀርም!! #ሼር!!

 !                                    ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ/ም                                   ድሬዳዋ፣ ኢትዮጵያየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማ...
23/12/2024

!

ታህሳስ 12 ቀን 2017 ዓ/ም
ድሬዳዋ፣ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከድሬዳዋ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር “ሃይማኖት ለሰላም፣ ለአንድነት እና ለመከባበር” በሚል መሪ ቃል ሲያካሂደው የነበረው አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተጠናቋል!

በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያደረጉት የድሬዳዋ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሼኸ ኢብራሂም ኢማም የመድረኩን ታዳሚዎችን እንኳን የሰላም እና የብሄር ብሄረሰብ ከተማ ወደሆነችው ድሬደዋ በሰላም መጣችሁ በማለት ለእንግዶች የድሬዳዋ ቆይታቸው ያማራ እንዲሆን መልካም ምኖታቸውን በአክብሮት አቅርበዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሃር በበኩላቸው ድሬደዋ ሰው ከየት መጣህ፣ እምነትህ ምንድነው ተብሎ ሳይጠየቅ ሁሉም በፍቅር የሚኖርባት ከተማ መሆንዋን በመግለጽ ድሬዳዋ በሰላሟ እና ሁሉም በዕኩልነት የሚኖርባት ለሌሎች ከተሞች ምሳሌ እንደምትሆን ታምኖበት የመጀመርያውን አገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረስ እንድታዘጋጅ ስለተመረጠች የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትሪያርክ ርእሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት እና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ፍሊጶስ በበኩላቸው ሰውነት የአብሮነት መሰረት እንደሆነ፣ አብሮነት ደግሞ የሰውነት መገለጫ መሆኑን በመግለፅ እግዚአብሄር ሰዎችን ሲፈጥር በአንድነት በሰላም እንዲኖሩ በመሆኑ ሁሉም ለሰላም ተገቢወን ዋጋ እንዲሰጥ እና እንዲሰራ የአደራ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ሸኽ ሐጂ ኢብራሒም ቱፋ (የክቡር ዶ/ር) የአትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ሁላችንም በሰላም ለመኖር ከፈለግን፣ ሁላችንም በሰላም እና በአንድነት ሊያኖረን የሚችል ተግባርን ሁል ጊዜ መፈጸም አለብን በማለት ተናግረዋል፡፡

አክለውም እኛ የሃይማኖት አባቶች አስታራቂዎች መሆን አለብን፤ በሌላ በኩል ደግሞ በግጭት ውስጥ ያሉ ወገኖች ለሰላማዊ ንግግር እና ድርድር ፈቃደኛ በመሆን ሰላማዊ ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል በማለት ሁሉም ለሰላም እንዲናሳ እና እንዲተባበር የአደራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የብፅዑ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ተወካይ አባ ሐይለ ገብራኤል መልቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው ድሬዳዋ ለኑሮ ምቹ የሆነች የሰላም ከተማ መሆንዋን በማስታወስ ይቺን የሰላም እና የፍቅር ተምሳሌት የሆነች ከተማ ሌሎች የሃገራችን ከተሞች እንደሞዴል በመውሰድ በሰላም እና በፍቅር ሕዝባባችንን ሊያገለግሉ ይገባል በማለት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝዳንት የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ፓሰተር ፃድቁ አብዶ በበኩላቸው መጽሐፍ ቅዱስ “ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ ሰላምንም ተከተል” እንደሚል በመጥቀስ ሰላም በሁላችን ዘንድ እንዲኖር ከተፈለገ ሁላችንንም ክፉ ከሆነ ማንኛውም ነገር መሸሽ ይገባናል በማለት አብራርተዋ፡፡

አክለውም ሰላምን ለማስፈን የሌላውን ቁስል እንድ እራሳችን ቁስል በመመልከት ሕመሙ ሊሰማን፣ እንዲሁም እውነተኛ መከባበር እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ በመከባበር መኖር ይጠበቅብናል በማለት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት እና የኢሃተጉ የበላይ ጠባቂ ቄስ ዮናስ ይገዙ በበኩላቸው አብሮነት የሰላም መንገድ እንደሆነ፤ ሰላም ደግሞ ዋጋ የሚያስከፍል በመሆኑ የእኔ ከምንለው ይልቅ የእኛ በምንለው ነገር ላይ ትኩረት አድርገን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ፕሬዝዳንትና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ የጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) ተወካይ ወንድሙ አበበ (ዶ/ር) በአንተ እንዲደረግብህ የማትፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ የሚለውን አምላካዊ መመርያ ሁላችንም በመጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከቻልን ሰላም በምድራችን ይሰፍናልና ሁላችንም ይህን ወርቃማ ሕግ ልንጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ባስተላለፉት መልዕክት የሃይማኖት ተቋማት ከመንፈሳዊ አግልግሎታቸው ጎን ለጎን በሀገር ሰላምና ልማት ሂደት ውስጥ ጉልህ ተሳትፎና ተጨባጭ ውጤት ያላቸው አጋሮች መሆናቸው አስታውሰው፤ የድሬዳዋ አስተዳደርም ከሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች ጋር በትብብርና በአጋርነት ብቻ ሳይሆን በአክብሮት ጭምር አብሮ በመስራት ከተማዋ ከጥቂት ዓመታት በፊት ትገለጽበት የነበረውን መካረርና ስጋት ወደ መተማመን መመለስ ችሏል በማለት አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም በየደረጃው ያሉት የመንግስት አካላት ተወካዮች ይህንን ተጨባጭ ተሞክሮ ወስዳችሁ በየክልሎቻችሁ ትተገብሩት ዘንድ በታላቅ አክሮት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻም በተለያዩ አካባቢዎች የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ ወገኖች ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄአቸው እንዲመለስላቸው መስራት ይገባቸዋል በማለት የሰላም ጥሪ በድጋሜ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ፡ +251-115-52-58-11
Website: www.ircethiopia.et
Facebook: www.facebook.com/irce7

 #ልዩ   ከታህሳስ 23-27ከረቡዕ እስከ ቅዳሜ ከ 11:00 ጀምሮ እሁድ ቀን ሙሉ!!  !!
23/12/2024

#ልዩ ከታህሳስ 23-27
ከረቡዕ እስከ ቅዳሜ ከ 11:00 ጀምሮ እሁድ ቀን ሙሉ!! !!

   ታህሳስ 14 - 20👉 የወንጌል ዘመቻ - 14 - 19 - በከተማይቱ አራቱም አቅጣጫዎች 👉 ሩጫ - 19 - ጠዋት 12:00 ጀምሮ እስታዲየም 👉 ደም ልገሳ - 19 - 2:00 ጀምሮ - እስ...
23/12/2024


ታህሳስ 14 - 20
👉 የወንጌል ዘመቻ - 14 - 19 - በከተማይቱ አራቱም አቅጣጫዎች
👉 ሩጫ - 19 - ጠዋት 12:00 ጀምሮ እስታዲየም
👉 ደም ልገሳ - 19 - 2:00 ጀምሮ - እስታድየም
👉 የጎዳና ላይ ህክምና - 17 እና 18 ሙሉ ቀን - እስታድየም
👉 ኮንፍረንስ - 17 - 20 - ከሰአት 9:00 ጀምሮ ቀበሌ 05 መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
👉 የአከባቢ ጽዳት - 19 - ጠዋት 12:00 ጀምሮ
👉 የህብረቱ የ 30 አመታት በላይ ጉዞ ምስጋና - በ 20 - እሁድ ከ 9:00 ጀምሮ
👉 ቲሸርቶች ለማግኘት ፦
0923443840
0912834708
0933864620
0931272425
#ዝግጁ ናችሁ
#ልዩ ሳምንት ነው

በቡታጅራ አካባቢ ላለ ለሚመለከተው የመንግስት አካላት ይድረስልን  !!የቡታጅራ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን የተሰጣት ቦታ ላይ ያለ አግባብ በመግባት መሪውን በመደብደብ ጭምር፣ የቤተክርስቲያን ን...
23/12/2024

በቡታጅራ አካባቢ ላለ ለሚመለከተው የመንግስት አካላት ይድረስልን !!

የቡታጅራ መካነየሱስ ቤተክርስቲያን የተሰጣት ቦታ ላይ ያለ አግባብ በመግባት መሪውን በመደብደብ ጭምር፣ የቤተክርስቲያን ንብረት የሆኑ ነገሮችን በማፈራረሰ የልጆች መማሪያ ስፍራዎችን በማፈራረስ፣ እንደ ደረሰን መረጃ ህጋዊ ያልሆነ የመሬት ወረራ ተደርጎባታል። የቤተክርስቲያን ንብረት የህዝብ ንብረት ነው። ህጋዊ ባልሆነ የሚደረግን በቤተክርስቲያን ላይ የሚደረግን ጥቃት እንቃወማለን። የሚመለከተው አካል ተገቢውን ምላሽ በአስቸኳይ እንዲሰጠን ስንል እንጠይቃለን።

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ባለሞያዎች ወንጌልን እና ሰላምን እኩል እንዲሰብኩ ጥሪ ቀረበ።ይህ ጥሪ የወረበው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከወንጌላውያን የሚዲያ ባለሞያዎ...
22/12/2024

ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ባለሞያዎች ወንጌልን እና ሰላምን እኩል እንዲሰብኩ ጥሪ ቀረበ።

ይህ ጥሪ የወረበው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከወንጌላውያን የሚዲያ ባለሞያዎች ማህበር ጋር በጋራ በመሆን “የወንጌላውያን ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በሰላም ግንባታ ላይ ያላቸው ሚና” በሚል ርዕስ የወንጌላውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተጾኖ ፈጣሪዎች ጋር ምክክር በተደረገበት ወቅት ነው።

በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ም/ቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ታምራት ታሪኩ የማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ልጆች ለሃጋአራችን ሰላም የራሳቸውን አስተዋጾኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።

መጋቢ ታምራት በመልዕክታቸው እያንዳንዱ ሰው ለሰላም የሚያበረክተው ጥቂት አስተዋጾኦ ሲተራቀም ለሀገራችን ሰላም ያለው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ ወጣቶች ወንጌልን እና ሰላምን እኩል በመስበክ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የወንጌላውያን ሚዲያ ባለሞያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት ወንድም ዘሪሁን ግርማ በበኩላቸው ማህበሩ ከተመሰረት ጀምሮ የአባላቱን አቅም ለመገነባት እየሰራ እንደሆነ አንስተው ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሰሩ ክርስቲያኖች ለሀገራችን ሰላም የራሳቸውን አበርክቶ ከፍ እንዲያደርጉ ይህ ሰልጠና በጋራ እንደተዘጋጀ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት የሰላም እና አድቮኬሲ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ደቻሳ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በሀገራችን የሰላም እና አድቮኬሲ እየሰራ ያለውን ስራ በማንሳት የማህበራዊ ሚዲያ ባለሞያዎች በሰላም ስራ ከፍተኛ ስራ እንደሚጠበቅባቸው አንስተዋል።

አቶ ደቻሳ ሚዲያ ያለውን አቀም ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን በመልካም ከተጠቀምን እንደ አጠቃቀማችን ለማህበረሰባችን የሚንሰጠው ጥቅም ከፍተኛ ይሆናል በማለት እንደ ክርስቲያን ሰላምን አበክረን ልንሰብክ እና አስተዋጽዓችንን ከፍ ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

ዮቲዩብ ፤ ፋስቡክ ፤ ቲክቶክ እና ሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚሰሩ ክርስቲያን ባለሞያዎች በበኩላቸው ባላቸው አቅም አበርክቶአቸውን ከፍ ለማድረግ በትብብር እንደሚሰሩ በመድረኩ የጠቀሱ ሲሆን የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት መሰል ስልጠናዎች በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት የመግባቢያ ስምምነት በማድረግ ሌሎች ተጨማሪ ሰራዎችን እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

22/12/2024

!!
ሲጄ ቲቪ ከቁላንቤ ቲቪ ጋር በመተባበር

የቡታጅራ መካነ የሱስ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ ልማቶች የማፈራረስ ዘመቻ ተካሂዶባታል። የዛሬው ፈረሳ ብዙ ሰዎች የተጎዱበትና የታሠሩበት ስለሆነ ለቡታጅራ መካነ የሱስ ቤተ ክርስቲያን ድምጽ እን...
22/12/2024

የቡታጅራ መካነ የሱስ ቤተክርስቲያን መሠረታዊ ልማቶች የማፈራረስ ዘመቻ ተካሂዶባታል። የዛሬው ፈረሳ ብዙ ሰዎች የተጎዱበትና የታሠሩበት ስለሆነ ለቡታጅራ መካነ የሱስ ቤተ ክርስቲያን ድምጽ እንድትሆኑልን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

የደረሠው ውድመት በቡታጅራ ከተማ አስተዳደር እና በታጠቁ ፖሊሶችና በሚያስፈሩ የአካባቢው ወጣቶች ስለሆነ ለቤተ ክርስቲያኑኗ አስቸጋሪ አድርጎታል። ስለሆነም ይህ ግፍና ጭካኔ ለህዝብ እንዲደርስ ቤተ ክርስቲያኗ ትጠይቃለች።

 ...ፓስተር ሔኖክ አለማየሁ በአውስትራሊያ ምድር የሚያገለግል የተወደደ ወንድማችን ሲሆን አሁን ደግሞ ጌታ ረድቶት እኔ ማነኝ የተሰኘ ድንቅ መፅሀፍ ይዞልን መጥቷል። መፅሀፉ የፊታችን ታህሳስ...
22/12/2024

...
ፓስተር ሔኖክ አለማየሁ በአውስትራሊያ ምድር የሚያገለግል የተወደደ ወንድማችን ሲሆን አሁን ደግሞ ጌታ ረድቶት እኔ ማነኝ የተሰኘ ድንቅ መፅሀፍ ይዞልን መጥቷል። መፅሀፉ የፊታችን ታህሳስ 20 በሀርመኒ ሆቴል ይመረቃል።
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል...

 ..😭የዚህ ዮሴፍ ተካ የተባለ ወጣት በሊብያ  ስደት ላይ እያለ መታገቱን ከቤተሰቦቹ ሰምተን ወደ እናንተ ካደረስን በኋላ ነገሩን የሰሙ  ብዙ ሰዎች አዝነዋል። ዮሴፍ አሁን በሊብያ  እጅግ አ...
21/12/2024

..😭
የዚህ ዮሴፍ ተካ የተባለ ወጣት በሊብያ ስደት ላይ እያለ መታገቱን ከቤተሰቦቹ ሰምተን ወደ እናንተ ካደረስን በኋላ ነገሩን የሰሙ ብዙ ሰዎች አዝነዋል። ዮሴፍ አሁን በሊብያ እጅግ አስጨናቂ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በቀናት ውስጥ ገንዘቡ (1,200,000 ብር) ካልተከፈለ ሊገድሉት እንደሆነ አጋቾቹ በየቀኑ ለቤተሰቡ እየተደወሉ እየዛቱባቸው ይገኛሉ። ልጁ የተያዘበት ሁኔታም በጣም አስጨናቂ ነው። እናም ይሄን የምትመለከቱ ቅዱሳን የአቅማችሁን በዮሴፍ ታላቅ ወንድም በተከፈተ አካውንት
CBE,1000131261218 Desalagn Teka Tufa እንድትለግሷቸው በታላቅ የልብ ሀዘን ይማፀናሉ።
ስለነገሩ በማንኛውም መንገድ ማጣራት የምትፈልጉ፣ በሊብያም ሰው የምታውቁ ልናግዘው እንችላለን የምትሉ ሰዎች በውስጥ መስመር የቤተሰቦቹን ስልክ እንሰጣችኋለን...
እባኮ መልዕክቱን ሼር ያድርጉ

  🙏የተወደዳችሁ የጌታ ቤተሰቦች የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፣በዘጸአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን ላለፉት ሁለት ወራት “የተነገረልንን የተስፋ ቃል የምንወርስበት ወግ” (Reset)...
21/12/2024

🙏

የተወደዳችሁ የጌታ ቤተሰቦች የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፣

በዘጸአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን ላለፉት ሁለት ወራት “የተነገረልንን የተስፋ ቃል የምንወርስበት ወግ” (Reset) በሚል ርዕስ ተከታታይ ትምህርት እየሰጠሁ ነበር። በታህሳስ 02 ቀን 2017 ዓ.ም እንደ ወትሮው የትምህርቱን የመጨረሻ ክፍል በመደበኛ የትምህርት ቀናችን ላይ እያስተማርኩ እንደነበረ የሚታወቅ ነው።

በዕለቱ ከተነሱ ሃሳቦች መካከል ሁለንተናዊ የሆነን ዕድገት እና ለውጥ ስለማምጣት የተነሳው አንዱ ሃሳብ ነበር። ከዚህም ጋር በተያያዘ ራሳችን እና ቤተሰባችን ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ስለማምጣት፣ ራስን ስለመጠበቅ፣ ስለ ግለ-ንጽህና እንዲሁም ከስንፍና ወጥቶ በትጋት ስለመስራት እና እግዚአብሔር የሰጠንን የተስፋ ቃል ስለመውረስ አጽንዖት በመስጠት ተናግሬያለሁ።
በዚህ ሁኔታ ለትውልዱ ካለኝ ልብ እና ቅናት የተነሳ አባት ልጁን እንደሚገስጽ፣ ህይወትን መለወጥ እንደሚቻል በማበረታታት መንፈስ፣ በቤተሰብ ድባብ ውስጥ በቀልድ መልክ የተጠቀምኳቸው ቃላት ነበሩ።

በጊዜው በጉባዔው ለነበሩ እና ለቋሚ የዩቱውብ ቤተሰቦቻችን የተነገረው ንግግር ከትምህርቱ ዓውድ አንጻር በበጎ የተወሰደ ሲሆን፣ በሌላ መልኩ ደግሞ ከቀጥታ የዩቱብ ስርጭቱ ላይ ተቀንጭቦ በመውጣት ትክክል ላልሆነ እና ዓላማውን ለሳተ ትርጉም ሊውል እንደቻለ ብሎም ጥያቄዎችን እንደፈጠረ አይቻለሁ።

ይህም፣ እኔም ሆንኩኝ ቤተክርስቲያን፣ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው ሰዎች የወረደ አመለካከት እንዳለን ተደርጎ እውነተኛ ማንነታችንን በማይወክል መልኩ በተሳሳተ ሁኔታ ሊተረጎም እንደቻለ ሲዘዋወሩ ከነበሩ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች አስተውያለሁ። እንደ ቤተክርስቲያን ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ልዩ ትኩረት በማድረግ ቃሉ እንደሚያስተምረን ራሱን የቻለ የአገልግሎት ክፍል በማቋቋም ማህበረሰባችንን በተለያየ መልኩ ስናገለግል መቆየታችን የሚታወቅ ነው።

በአካባቢያችንም ከወረዳው ጋር በመተባበር ችግረኛ ቤተሰቦችን የምንረዳ፣ ልጆቻቸውንም የምናስተምር ሲሆን በየጊዜው ልዩ ልዩ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍም እያደረግን እንደምንገኝ የሚታወቅ ነው። በግሌም ከቤተሰቤ ጋር በዚሁ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ ስሳተፍ ኖሬያለሁ።

ስለሆነም የተላለፈው ሃሳብ ድሆችን የማንኳሰስ እና ዝቅ የማድረግ ዓላማ ያለው ሳይሆን ራስን ስለመጠበቅ ብቻ የተደረገ ንግግር እንደሆነ በቅንነት እንዲወሰድ እጠይቃለሁ። ለትውልዱ እና ወድጄ ለማገለግለው ህዘብም የግራ መጋባት ምክንያት የሚሆን ንግግር ከመናገር ይልቅ በብዙ ትጋት ዝቅ ብዬ ማገልገል የሁልጊዜ አቋሜ ነው። በተፈጠረውም ነገር እጅግ ያዘንኩ እና እንደ ቤተክርሰቲያን ለቀጣይ አገልግሎታችን ብዙ ትምህርት እንደወሰድን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጥ እወዳለሁ።

በመጨረሻም፣ የተወደዳችሁ ቅዱሳን አላስፈላጊ ትርጉም ሊሰጥ ከሚችል በማህበራዊ ሚዲያ ከሚዘዋወረው የተቆረጠ ንግግር ይልቅ ሙሉውን መልዕክት ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንድታዩ እየጠየኩ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለተፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ቅሬታ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

https://youtu.be/eR8sjI0x6Wk?si=zSQ4L3duruN1HX3J

ጌታ ይባርካችሁ!
ሐዋርያ ዮሐንስ ግርማ
ታህሳስ 2017 ዓ/ም

  በ 9:00 ጀምሮ በሐርመኒ ሆቴል አይቀርም!!
21/12/2024

በ 9:00 ጀምሮ በሐርመኒ ሆቴል አይቀርም!!

 #ተለቀቀ ሰምተው ይባረኩ!!
21/12/2024

#ተለቀቀ ሰምተው ይባረኩ!!

Kenu Kerboal by Netsanet Tikuye #ቀኑ ቀርቧል protestant Gospel Song _ December 2024 /2025 Day Has Come Official Videoቀኑ ቀርቧልቀኑ ቀርቧል የጌታችን መምጫውሁላችንም እንዘ...

ጥር 4 በሚሊንየም አዳራሸ መሥዕዋት ለእግዚአብሔር በሚል ርዕስ ከዘማሪት ሀና ተክሌ ጋር አምላካችንን ለማክበር እንገናኝ  ይህን የአምልኮ ድግስ ያዘጋጀው ኤፔክስ ኢቨንትስ ሲሆን ብቸኛ አጋር ...
21/12/2024

ጥር 4 በሚሊንየም አዳራሸ መሥዕዋት ለእግዚአብሔር በሚል ርዕስ ከዘማሪት ሀና ተክሌ ጋር አምላካችንን ለማክበር እንገናኝ ይህን የአምልኮ ድግስ ያዘጋጀው ኤፔክስ ኢቨንትስ ሲሆን ብቸኛ አጋር ኤልሀዳር ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ነዉ #መሥዋዕት

የተወደድኩበት በልጁ መወለድ ዳግመኛ ወልዶ ልጆቹ ያደረገንን: እኔና ልጄ እግዚአብሔርን አባ: አባባ እያልን: ዘምርንለት:: እግዚአብሔር አባት ሆነን:: ሩቅ የነበርነውን አቀረበን:: ወደ ራሱ...
20/12/2024

የተወደድኩበት
በልጁ መወለድ ዳግመኛ ወልዶ ልጆቹ ያደረገንን: እኔና ልጄ እግዚአብሔርን አባ: አባባ እያልን: ዘምርንለት:: እግዚአብሔር አባት ሆነን:: ሩቅ የነበርነውን አቀረበን:: ወደ ራሱ አስጠጋን::በእቅፉ አስገባን:: ስለዚህ በአባታችሁ በእግዚአብሔር እቅፍ ሆናችሁ የተወደዳችሁበትን ፍቅር እያሰባችሁ ከእኛ ጋር "አባ" እያላችሁ እንድታመሰግኑት እንጋብዛችዋለን

20/12/2024

!!

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Christian ዜማ Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Christian ዜማ Tube:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share