Ardi

Ardi መዝናኛ ወቅታዊ ዜና አስቂኝ አስተማሪ ሁሉንም በአንድ ቦታ ?

ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል ። ..60 የሚደርሱ ተበዳይ ነን ባዬች ቤቴል አካባቢ የሚገኝ አንድ ሪል እስቴት ድርጅት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ያሳውቃሉ። ...
01/01/2023

ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል ። ..
60 የሚደርሱ ተበዳይ ነን ባዬች ቤቴል አካባቢ የሚገኝ አንድ ሪል እስቴት ድርጅት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ያሳውቃሉ።

ይህን የህዝብ ቅሬታ የሚድያ ሽፋን ለመስጠት የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባልደረባ የሆኑት ጋዜጠኛ ብስራት መንግስቱ እና የካሜራ ባለሙያ ሳሙኤል ሀ/ሚካኤል ደግሞ ቦታው ላይ ተገኝተው መረጃ በመስብሰብ ላይ እያሉ የፖሊስ ልብስ የለበሱ ህግ አስከባሪዎች ምንም ዘገባ መስራት እንደማይችሉ ገልፀው በማመናጨቅ ወደ ቤተል ፖሊስ ጣቢያ ወስደው ያስሯቸዋል።

በእርግጥ ጋዜጠኞቹ ፤ ከአራት ሰዓታት የፖሊስ ጣቢያ እስር በሁላ ሊፈቱ ችለዋል። ሆኖም ግን የተበዳዮቹ ጉዳይ የሚድያ ሽፋን አላገኘም።

" የምርመራ ጋዜጠኝነት በቋሚነት እንዲሰራ እናደርጋለን " ብለው ፓርላማ ላይ ለተናገሩት ጠቅላይ ሚንስትር ፤ ይሄን መረጃ አድርሷቸው።

ሲሆን ሲሆን መንግስት ምርመራ ዘገባዎችን ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ከለላ መሆን ይገባው ነበር። ጋዜጠኛ ውክልናው ለዜጎች ነው ። የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ደግሞ ሰብዓዊ መብት ነው። ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም !

#ማናየእውነቱ

ሰበር ዜና በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳ...
05/07/2022

ሰበር ዜና

በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዬች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል

አቶ ሀንጋሳ ዛሬ ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ
- አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣
- አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር ቤት በማስገባት ሰላም ይስፈን፣
- ዶ/ር አብይ ከለማ የቀረበ ወዳጅ አልነበረህም በሱ ላይ የጨከንክ በሽመልስ ላይ መጨከን እንዴት አቃተህ፣
- ዶ/ር አብይ የኦሮሚያ ክልልን ካቢኔን አፍርሰህ በአዲስ ተካ፣ ይህንን ካላደረክ አማራ እንዲጨፈጨፍ የምታደርገው አንተ ነህ ወደሚል ድምዳሜ እሄዳለው፣
- እኔ ብሞት እንኳን ወንድሞቼ (አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች) እውነቱን ስሙ (እወቁት)
- ዶ/ር አብይ መሬት ላይ ወርደህ ህዝቡን ይቅርታ ጠይቅ፣ አንተን እና ህዝቡን ለይተው ሊበሉህ ደጅህ ላይ የቆሙ ጅቦች አሉና ቅደማቸው፣
- ዶ/ር አብይ እሰር፣ ቀፍድድ፣ ወስን እና ጨክን፤ አንተን ገለው ቤተመንግስት ሊገቡ ያሰቡ ሰዎች ሰፈራችን ላይ ደርሰዋል (አጃቢዬን ዛሬ ገለውታል ነገ እኔንም ቢገሉኝ እውነት እናገራለሁ)
- ኦነግ ለዘመናት ወለጋ ውስጥ ነበር፣ ኦነግ ሀረርጌ እና አርሲ አለ፤ አሁን ኦነግ የመግደያ፣ የመጨፍጨፊያ አቅሙን ከየት አመጣው ብለህ ጠይቅ፤ እኔ ግን እነግርሃለው ሀይሉን እና አቅሙን ያገኘው ከክልሉ መንግስት ነው
- እነ ሽመልስ ዙሪያውን ከበው ሊበሉህ ነው፣ ሊጨርሱህ ነው የመጨረሻው ሰዓት ላይ ደርሰሃል አይንህን ግለጥ
- አማራን ኦሮሚያ ውስጥ መጨፍጨፍ የሚጎዳው ከአማራ ይልቅ ኦሮሞን ነው፣
- የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ስንት ገዳይ እንፈልጋለን፣ ለፍትህ እናቀርባለን ብላችሁ ስንቱን አሳካችሁ፤ ምኑንም አላሳካችሁም ወሬ ብቻ፤ በዚህ መሃል ግን ወንድም እና እህቶቼ (አማራዎች) ወለጋ ውስጥ አለቁ
- መቼ ነው ዶ/ር አብይ ከአትክልት ስራ ወጥተህ ጠንከር ያለ ስራ የምትሰራው፤ መቼ ነው የከበበህ መከራ የሚታይህ፣ መቼ ነው ሊበላህ የተነሳው ጅብ የሚታይህ
- ዛሬ አማራን እየገደለ የሚመጣው ሀይል መቆሚያው አንተ ቤት (አራት ኪሎ) ነው
- ሽመልስ እና ፍቃዱ ታደሰን ወደ እስር ቤት ካላስገባህ ከዚህ ጥቃት ጀርባ አንተ አለህ ማለት ነው፣
- ለአብዲ ኢሌ ክፍት የሆነ እስር ቤት ለሽመልስ እና ፍቃዱ ዝግ የሆነው ኦሮሞ ስለሆኑ ነው ወይስ አዛዡ አንተ ስለሆንክ
- አጉል ጥጋብ እና ሁኔታ ውስጥ ገብታችሁ የአማራን መገደል የምትደግፉ የኦሮሞ ወንድሞቼ እረፉ (ዋ እረፉ ብያለሁ)፣ ነገ ጠዋት አማራ ኦሮሞ ላይ እንዲነሳና እርስ በእርስ እንድንትላለቅ ነው ፍላጎቱ፣ የኦሮሞ ወንድሞቼ ንቁ (በጭራሽ በኦሮሞ ብልጽግና ገመድ እንዳትጠለፉ)
- አንተን (አብይን) እያስጠሉ ያሉት ዙሪያህን የከበቡህ እና ሰው ያደረካቸው መናዎች ናቸው
- ኦሮሚያ የሁላችንም ቤት ነው፣ አማራው ተመርጦ ሲታረድ ለምን ካላልን ነገ መከራው በኛና በልጆቻችን ላይ ይደርሳል
- ዶ/ር አብይ እስኪ ድንገት ጅማ፣ ሀረርጌ፣ ገራሙለታ፣ አርሲ፣ ወለጋ፣ ባሌ፣ ጭሮ ሂድና ህዝቡን ስማ (መሬት ላይ ያለውን መከራ እይ)፣ ያኔ ምን አይነት የሚመር ዜና እንደምትሰማ እነግርሃለው
- የኦሮሞ ካቢቤ ተጠራርጎ እስር ቤት ካልገባና ለፍርድ ካልቀረበ የአማራ መጨፍጨፍም አይቆምም ሀገርም ሰላም አትሆንም

በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ።------------------------...
18/04/2022

በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላለፈ።
------------------------------
ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በመግለጫው የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና እርማት በተመለከተ ያጋጠመ ችግር አለመኖሩን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በአብዛኞቹ ክልሎች ያጋጠመ የውጤት መቀነስ መኖሩን እና ትምህርት ሚኒስቴር አማራጮችን የማየት ስራ መስራቱንም በመግለጫው ተነስቷል።

በዚህም በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑ አካባቢዎች እና የማለፊያ ነጥብ ያላመጡና ወደ መንግስት ዩኒቨርስቲ መግባት ያልቻሉ ተማሪዎች በ2014ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ እንዲፈተኑ ውሳኔ ተላልፏል።

ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ውይይት በማድረግ ተጨማሪ የቅበላ አቅም እንዲኖር ከስምምነት ላይ መደረሱን እና ተጨማሪ የቅበላ አቅም በፍትሀዊነት በጦርነቱ ምክኒያት ለተጎዱ ክልሎችእንዲከፋፋል ውሳኔ ተላልፏል።

የፈተና ውጤት ማሳወቅን በተመለከተም በሁለት ዙር ፈተና በመሰጠቱ አጋጥሞ የነበረው ችግር መታረሙ በመግለጫው ተገልጿል።

በመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች በስነ-ዜጋ ትምህርት ካጋጠመዉ ችግር ውጪ ሌሎች ችግሮች ባለማጋጠማቸው የሌሎች ትምህርት ዓይነቶችን ውጤት ውድቅ ለማድረግ አሳማኝ የውጤት ትንተና አለመኖሩም ነው የተገለፀው ።

በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ቅበላ የሚያገኙትን በተመለከተ በቀደምት ዓመታት ከመሰናዶ ትምህርት በኋላ ከሚፈተኑ ጋር በማነፃፀር የተፈጠረ አለመረዳት መኖሩንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በቀጣይም እንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይፈጠሩ የተጠናከረ ስራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ! ገዥው ፓርቲ የውስጥ ልዩነቱን ወደ ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ለማውረድ የሚያደርገውን ኃላፊነት የጎደለው ሙከራ ያቁም!  ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜ...
05/04/2022

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የተሰጠ መግለጫ!

ገዥው ፓርቲ የውስጥ ልዩነቱን ወደ ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ለማውረድ የሚያደርገውን ኃላፊነት የጎደለው ሙከራ ያቁም!

ሰሞኑን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ አውራ ጎዳና ከተማ ተፈጥሮ በነበረ ግጭት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወቃል፡፡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ሕይወታቸው ላለፉ ወገኖቻችን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሐዘኑን ይገለጻል፤ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይመኛል፡፡

የአማራን ሕዝብ ማኅበራዊ እረፍት ይነሳል፣ በሂደትም ኢትዮጵያን ይበትናል ተብሎ ስራ ላይ የዋለው ሕገ-መንግሥት እና የአስተዳደር መዋቅር የአማራ ሕዝብ ከፍተኛ ዋጋ የከፈለበት እና እየከፈለበት የሚገኝ ቢሆንም ሥርዓቱ ሁሉንም ኢትዮጵያውንን ከባድ ዋጋ እያስከፈለ እና የጋራ ቤታችን የሆነችውን ሀገራችን ኢትዮጵያን ኅልውናም ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አደጋ ላይ እንደጣለ አብን ያምናል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመበትን፣ ኢትዮጵያውያንን በብሔር፣ በቋንቋ፣ በኃይማኖት ከፋፍሎ የማያቋርጥ የቀውስ አዙሪት ውስጥ ለማኖር በአሸባሪው ትሕነግ ስራ ላይ በዋለው ሥርዓትና መዋቅር ምክንያት የንጹሃን ደም በከንቱ ሳይፈስ የነጋ ሌሊት፣ የመሸ ቀን የለም፡፡

ሰሞኑን የአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በምንጃር- ሸንኮራ ወረዳ፤ አሞራ ቤት ቀበሌ፤ አውራ ጎዳና ከተማ ውስጥ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የሚታይ ሆኖ ሳለ ግጭቱን የተለየ ክስተት ለማስመሰል እና ችግሩን ወደ ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ለማውረድ የተሄደበትን ርቀት አብን ያወግዛል።

ገዥው ፓርቲ በውስጡ ያሉ ልዩነቶቹን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ሲገባው፣ የዜጎችን ሞት በማስታከክ ሕዝብ ከሕዝብ የሚያጋጭ እና ሀገራችንን ወደከፋ ቀውስ ውስጥ የሚከት የመግለጫ ጋጋታ ማውጣት ኃላፊነት የጎደለው እና እጅግ አደገኛ አካሄድ በመሆኑ በቶሎ እንዲታረም አብን አጥብቆ ይጠይቃል::

ሕብረ-ብሄራዊነት የሀገር ጌጥ መሆን የሚችለው በሴራም ሆነ በብልጣብጦች መንገድ ሳይሆን በእውነተኛ አስቻይ አማካይ የፖለቲካ መንገድ ነው፡፡ ወንድማማችነት የሚኖሩት የሕዝብ እውነታ እንጂ በየመድረኩና በየመግለጫው የሚደሰኩሩት ልፋፌ ሊሆን አይገባም፡፡

ኢትዮጵያ የበርካታ ማንነቶች ሀገር ነች፡፡ በቋንቋ፣ በባህል፣ በኃይማኖት፣ ብንለያየም አንዳችን ከሌላችን የሚያስተሳስሩን ማህበራዊ አንጓዎች ብዙ ናቸው፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ የጋራ ቤታችን ነች፡፡ ኢትዮጵያ በመከባበር ስሜት የሁላችንም መሆን ካልቻለች የማናችንም ልትሆን አትችልም፡፡

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከልሂቃን ሽኩቻ ወጥቶ ዜጎች የመብት ባለቤት የሚሆኑበትን አስቻይ የፖለቲካ ሥርዓት መፍጠር ካልተቻለ ከፊት ለፊታችን ያለው ሀገራዊ አደጋ ከእስካሁኑ የከፋ ከባድ ዋጋ እንዳያደስከፍለን ያሰጋል፡፡

የትኛውንም የፖለቲካ ቅራኔ ሰበብ እየፈጠሩ ወደሕዝብ ለሕዝብ ማውረድ ከፍ ሲል መንግሥታዊ ኃላፊነትን የመዘንጋት፤ ዝቅ ሲል የፖለቲካ ሸፍጥ ነው፡፡ ከአሸባሪው ትሕነግ የውድቀት ገፊ-ምክንያቶች መማር ለራሱ ለገዥው ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ለሕዝብና ለሀገርም ይጠቅማል፡፡


የአማራና የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ የሀገር ምስረታም ሆነ የሀገር-ግንባታ ታሪክ ውስጥ የገዘፈ ሚና ያላቸው ከቋንቋ ማንነት በላይ በጋራ የሚጋሯቸው ማህበራዊ ትስስራቸው የጎላ ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ አንድ ቤተሰብ ናቸው፡፡ ለዚህም ነው አብን በዚሁ መግለጫው ላይ "በሁለቱ የሸዋ ህዝቦች መካከል" የሚል አግባብ ያለው አገላለጽ የተጠቀመው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ገዥው ፓርቲ በውስጡ ያለበትን የፖለቲካ ልዩነት ተከትሎ ግጭትን ወደሕዝብ ለሕዝብ ለማውረድ የሚያደረገው ኃላፊነት የጎደለው ሙከራ በሕግም ሆነ በታሪክ ያስጠይቀዋል፡፡

በርግጥም የሚያስጨንቀን የዜጎች ሞት ከሆነ የተፈጠረውን ግጭት እና የሕይወት መጥፋት በተገቢው ገለልተኛ አካል ማጣራት እየተቻለ ጉዳዩን የተለየ ምስል ለመስጠት፣ በግልፅ አማራ ክልል ውስጥ ያለን የአስተዳደር ክልል ሌላ ስያሜ በመስጠት እና ባልተገባ ሁኔታ የእኔ ክልል አካል ነው በማለት ጸብ አጫሪ የሆኑ መግለጫዎችን መስጠት በአስቸኳይ እንዲቆም እየጠየቅን ገዥው ፓርቲ እና የሚመራው መንግሥት የሕዝብን ደኅንነት አደጋ ላይ ከሚጥሉ እንቅስቃሴዎች እራሱን እንዲያቅብ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡


ገዥው ፓርቲ የውስጥ ልዩነቱን ወደ ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት ለማውረድ የሚያደርገውን ኃላፊነት የጎደለው ሙከራ ያቁም!

መጋቢት 27/2014

አዲስ አበባ፣ ሸዋ - ኢትዮጵያ

♦ የጄነራሉ ምስጢሮች-------ይህን እጅግ ልብ አንጠልጣያ የብዙ ድብቅ ምስጢሮች ፍቺ የሆነው ቃለ መጠይቅ ለብዙዎች ይዳረስ ዘንድ የቀረበ !! እንዳትሰለች/ቺ እስከ መጨረሻው ይነበብ ፦---...
27/03/2022

♦ የጄነራሉ ምስጢሮች
-------
ይህን እጅግ ልብ አንጠልጣያ የብዙ ድብቅ ምስጢሮች ፍቺ የሆነው ቃለ መጠይቅ ለብዙዎች ይዳረስ ዘንድ የቀረበ !! እንዳትሰለች/ቺ እስከ መጨረሻው ይነበብ ፦
-------

የዐማራ ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ፣ ባለፈው ሳምንት በድንገት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ፣ ከ“ፍትሕ መጽሔት” ጋር ሰፊ ቃለ-መጠይቅ አድርገዋል፡፡ ጄነራሉ፣ በልዩ ኃይሉ ላይ ‹እየተፈጸመ ነው› ያሉትን ደባ ጨምሮ፤ በቀጣይ ወልቃይትና ራያን ለሕወሓት እስከ መስጠት የደፈረ ሴራ ሊከሰት እንደሚችል ዘርዝረዋል፡፡ በጦርነቱም መከላከያ ኃላፊነቱን በአግባቡ አለመወጣቱን ይጠቅሳሉ፡፡ መልካም ንባብ፡፡

፨ ጄነራል ወደ ዐማራ ልዩ ኃይል አዛዥነት በድጋሚ መቼና እንዴት ተመለሱ?

የተመለስኩት 2013 ዓ.ም ሐምሌ መጀመሪያ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ፣ የክልሉ መንግሥት የክተት ጥሪ በማስተላለፉ፣ እኔም እንደ ዐማራነቴ ጠላት በህልውናዬ ላይ የመጣ በመሆኑ ነው፡፡ በነገራችን ላይ፣ ጥሪውን ተቀብለን ለመግባት ስንጣደፍ፣ “ለምን ትገባላችሁ? ጦርነቱን ሕወሓት ማሸነፉ አይቀርም?!” የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ፡፡

፨ ከአመራሩ መሃል ነው?

ከአመራሩም ከጄነራል መኮንኖችም ‹ሕወሓትን የሚያቆመው ኃይል የለም› በሚል አንዳንድ ወጣ-ያሉ ነበሩ፡፡ በዚህ ላይ፣ የአዴፓ አመራር በፊት በእኛ ላይ ጤናማ አመለካከት ስለሌለው፣ እንዳንመለስ የነበረውን ፍላጎት በማስታወስ ነው ‹ባትገቡበትስ?› ሲሉ የመከሩን፡፡ በወቅቱ መከላከያ ሠራዊቱ የያዘውን ቦታ እየለቀቀ ወደኋላ እየመጣ ነበር፡፡ በርግጥ፣ ጄነራሎቹ ከፊት፣ ጦሩ ከኋላ እየተናደ መሆኑ፣ ትንሽ እንግዳ ክስተት ነበር፡፡ እነሱም ይሄንን እየጠቀሱ ነው ‹መከላከያ እየመከተው አይደለም› ይሉን የነበረው፡፡ ‹አይ ግዴለም! አማራጭ የለንም፡፡ የምንገባውም ለአመራሩ ሳይሆን፤ እየተመታ ላለው ሕዝብ የዐቅማችንን ለማድረግ ነው፡፡ መሞት ካለብንም እንሞታለን እንጂ፤ ጥሪውን እንቀበላለን፤› ብለን ገባን፡፡

፨ ስንት ናችሁ አብራችሁ የገባችሁት?

ከእኔ ጋር ስድስት ነን፡፡ ጄነራል አበራ፣ ጄነራል ባዩ፣ ጄነራል ዘውዱ፣ ጄነራል መሰለ ወይም (ጎበና) እና ጄነራል ማሞ፡፡ በአንድ ላይ እንደገባንም የመጀመሪያ ሥራ ያደረግነው፣ አጠቃላይ ልዩ ኃይሉን ማዋቀር በመሆኑ፣ ምልሱንና የነበረውን አሰባስበን አደራጀነው፡፡

፨ እናንተ ከመግባታችሁ በፊት ‹መከላከያውና ጄነራሎቹ እየሸሹ ነበር› ብለዋል፡፡ የዐማራ ልዩ ኃይልስ አልሸሸም እንዴ?

ልዩ ኃይሉ በመጀመሪያው ውጊያ በተደጋጋሚ ጥሩ ተዋግቷል፡፡ በኋላ፣ ሕወሓት የመከላከያ ሠራዊቱን ከባድ መሳሪያዎች በብዛት እያገኘና እየታጠቀ ሲሄድ፣ በልዩ ኃይሉ ላይ ከባድ ውጊያ ከፈተበት፡፡ ይህንን ያረጋገጥኩት፣ ከተመለስኩ በኋላ አዋጊዎቹ ከሰጡኝ ማብራሪያ ነው፡፡ በተለያየ መንገድ እንደተገለጸውም፣ መከላከያ፣ ትግራይ ላይ ችግር ከገጠመው በኋላ፣ የጦር መሳሪያውን ሕወሓት እንደተረከበው ይታወቃል፡፡ ዲሽቃውን፣ ሞርታሩን፣ መድፉን፣ ታንኩን ይዞ፣ ሙሉ የተኩስ ዐቅሙን የዐማራ ልዩ ኃይል ላይ አሳረፈው፡፡ ምክንያቱም እሱ ነበር፣ ከፊት ሆኖ ገትሮ የያዘው፡፡ በመጨረሻ፣ ምቱ ሲበዛበት፣ አብሮ ለማፈግፈግ ተገደደ፡፡

በአጭሩ፣ የዐማራ ልዩ ኃይል ወደኋላ የተመለሰው፣ ጠላት ከመከላከያ በገፈፈው ከባድ መሳሪያ በከፈተበት ያልተመጣጠነ የተኩስ ውርጅብኝ ነው፡፡ ይህ ሁኔታም፣ ከኮረም የጀመረ በመሆኑ፣ ቁጥሩን በከፍተኛ ደረጃ አመናምኖት ነበር፡፡

፨ እናንተ ስትመለሱ የጠላት ኃይል የት ድረስ ገብቷል?

ኮረምና ቆቦን ይዞ፤ ወደ ሮቢት፣ ጎብዬ… እያጠቃ ነበር፡፡

፨ ከተመለሳችሁ በኋላ ምን ሠራችሁ?

እኛ እንደተመለስን፣ በነበሩት ዘጠኝ ብርጌዶች ላይ የሚገባውን ዐዲስ ኃይል ጨምረን እንደገና አቋቋምናቸው፡፡ የአመራር ክፍተቶች ስለነበሩባቸውም ከላይ እስከ ታች አስተካክለን ሞላነው፡፡ ይሄን ሠርተን ስንጨርስ፣ በጊዜው የክልሉ አስተዳዳሪ ለነበሩት ለእነ አገኘውም ለሌሎቹም እቅዳችንን አቅርበን፣ ከተቀበሉት በኋላ፤ በልዩ ኃይሉ ላይ የሚታያቸውን ክፍተቶችና ወደፊት የሚጠበቅብንን ነገረውን፣ የሥራ ክፍፍል አደረግን፡፡

ከዚያም፣ ለተሟላ ግምገማ እኔና ጄነራል አበራ ወደ ወልዲያ ስንሄድ፤ እነ ጄነራል ጎበናን ወደ ደባርቅ ላኳቸው፡፡ ሌሎቹንም ሎጀስቲኩንና አስተዳደሩን እንዲሞሉ አድርገን በፍጥነት ተንቀሳቀስን፡፡ እኛም ወልዲያ ስንደርስ ቁጥሩ የማይናቅ የልዩ ኃይል አባላትን ከተማው ውስጥ ስላገኘን፣ ‹ምንድን ነው?› ብዬ ስጠይቅ፣ ‹ብቻችንን ተለይተን እየተመታን ነው፤›፣ ‹ጠላት ከመከላከያ በነጠቀው ታንክና መድፍ እኛን ለይቶ ቀጠቀጠን፣ ተዳከምን፤› የሚል ነገር አነሱ፡፡ የአብዛኛዎቹ አስተያየት ተመሳሳይ በመሆኑ ችግሩን ስለተረዳሁ ካረጋጋኋቸው በኋላ፣ ወደ ማወያየት ገባሁ፡፡ ሥነ-ልቦናቸው በጣም ተጎድቶ ነበር፡፡

ከውይይቱ በኋላ፣ ባለፈው የተሠራውን መነሻ አድርገን፣ እንደገና በደንብ አጠናክረናቸው ስናበቃ፤ ወደ ጎብዬ ሄድኩ፡፡ በአጋጣሚ ዶ/ር ሰማም አብሮን አለ፡፡ እዚያም የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ጄነራል ክንዱን አገኘነውና፣ ስለውጊያው አጠቃላይ ገለጻ ሰጠን፡፡ ሁኔታው ሲታይ፣ ወገን የሞተ መከላከል ውስጥ እንዳለ ያስረግጣል፡፡ በዚህ ላይ፣ ጠላት ከቀኝ-ከግራ እያሰፋ፡- ሮቢትን፣ ቆቦን ይዞ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡ ቀጠናውን ከገመገምን በኋላ የምነንወስነውን ወስነን ተመለስን፡፡

ነገር ግን፣ የጠላት ቁጥሩ የማይናቅ ኃይል ወደ ጊዳን አቅጣጫ፣ ከቆቦ ወደ ተኩለሽ እየመጣ መሆኑን ስናውቅ፤ ከሰቆጣ አንድ ሻለቃ ልዩ ኃይል፤ እንዲሁም የሰሜን ሸዋንና የጊዳን ሚሊሻዎችን ጨምሬ፣ በቀጥታ ወደ ተኩለሽ ማጥቃት ጀመርን፡፡ ተንደርድሮ የመጣውን የመጀመሪያውን ኃይል ጠረግነው፤ የተወሰነውንም ጉዳት አደረስንበት፡፡ ይሁንና፣ ጠላት ማታ አካባቢ በታንክና መድፍ የተጠናከረ ጥቃት ሰነዘረብን፡፡ ከወገን ጋር ሲታይ አሰላለፉ ያልተመጣጠነ ነበር፡፡

እዚህ ጋ፣ ማንሳት የምፈልገው ቁም-ነገር፣ በዚህ አቅጣጫ ብዙ ኃይል እየመጣ መሆኑንና ሌሎች ሁኔታዎችን ከገመገምኩ በኋላ፤ ለመከላከያ ጀነራሎች፡- ‹ጠላት ከፍተኛ ኃይል አሰልፎ እየመጣ ነው፡፡ ሊሄድ ያሰበበት አቅጣጫ ወደ ጎንደር ነው፡፡ የወልድያውን መስመር ይዞ ወደ ግዳን ከወጣ በኋላ፣ በላስታ አድርጎ ጎንደር ይመጣል!› የሚል ሪፖርት አቀረብኩ፡፡ ለክልሉ አመራሮችም ይህንኑ አስረዳኋቸው፡፡ እነሱ አምነው ሲቀበሉኝ፤ የመከላከያ ጀነራሎች ግን ‹አይ አያደርገውም! ጠላት ወደ ጎንደር ፈጽሞ አይሄድም፡፡ የእኛን ኃይል አሳስቶ ለመከፋፈል ነው፡፡ ወደዚያ ይሄዳል የምትለውን ነገር አትሰበው፤ አይሆንም፤› አሉ፡፡
‹ኧረ ተዉ፣ እንደዚያ ነው አመጣጡ› ብላቸውም፤ ‹በፍፁም አይደለም፤ እኛ የተሟላ መረጃ አለን፤› ብለው ሳይቀበሉት ቀሩ፡፡ ከሳምንት በኋላ እንዳያችሁት ግን ጠላት ጉና ድረስ መጣ፡፡

ጠላት በጥቂት ቀናት ጊዳን፣ ሙጃን ይዞ ኩል መስክ አካባቢ መጥቶ ሰፈረ፡፡ የያዝኩት ኃይል፣ በውጊያ የተዳከሙ ብርጌዶች ቢሆኑም፤ ድልብ (ወደ ወልዲያ የሚያስገባ ቁልፍ ወታደራዊ ቦታ ነው) እና ቀበሮ ሜዳ ላይ ማታውኑ ገጠምነው፡፡ በተለይ ወደ ቀበሮ ሜዳ ከዐሥር በማያንሱ አቅጣጫ ሲመጣ፣ እየመታን እንመልሰዋለን፤ ተመልሶ ይመጣል፣ እንመታዋለን፡፡ ሰባት ጊዜ ቢመላለስም፣ ሰባት ጊዜ መለስነው፡፡

ወደ ድልብ ግን በታንክ በተጠናከረ ውጊያ በማጥቃት፣ የወገንን ኃይል ገፋው፡፡
እዚህ ላይ ዋናው ችግር፣ በመጀመሪያው ሪፖርታችን ‹መከላከያ ድልብ ላይ የከባድ መሳሪያ ድጋፍ ይዞ ይምጣልን?› ብለን ጠይቀን ነበር፡፡ እነሱ ግን ቦታ ስላልሰጡት፣ አንድ ዙ-23 ብቻ ላኩልን፡፡ ማታ አንድ ሰዓት አካባቢ ድልብ እየተያዘ ሲሄድ፣ ለምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ አቶ ደመቀ በስልክ ስለውጊያው እያብራራሁለት እያለ፤ ‹ድልብ ላይ፣ መከላከያን የታንክ ድጋፍ ጠይቀን ሊያግዙን ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ጠላት አጋጣሚውን ተጠቅሞ የመከላከያ ወረዳችንን በታንክ ከፍቶት ገባ፤› አልኩት፡፡ ለካስ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድም እየሰማን ነበርና፣ ቆጣ ብሎ “ታንክ ልኬልህ ነበር አይደል እንዴ?!” አለኝ፡፡ እኔም ‹አይ፣ ውጊያ እኮ የሚመራው በጊዜና በቦታ ነው፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው ውጊያ አይደለም፤” ብዬ መለስኩ፡፡ በኋላ እንዳረጋገጥኩት ግን፣ ዶ/ር ዐቢይ የታንክ ድጋፍ እንዲደረግልን አዝዞ ነበር፡፡ ጀነራሎቹ ናቸው ትዕዛዙን ጥሰው፣ ታንኩ ወልዲያ ስታዲዮም እንዲቆም ያደረጉት፡፡
ጠላት የከባድ መሳሪያ ድጋፍ እየተደረገልን እንዳልሆነ ሲያውቅ፤ ሲዋጋን በነበረው ዘጠኝ ክፍለ-ጦሮች ባሉት “ሁለተኛ እዝ” በሚባለው ላይ፣ ሦስት ጨምሮ ዐሥራ ሁለት ክፍለ-ጦር አደረሰው፡፡ አዛዡ ጄነራል ዮሃንስ (መዲድ) ነው፡፡ ውጊያው ወደላይ ወደ ዋድላ ደጋው እየወጣ ሲሄድ፤ በቂ ኃይል ስላልነበረን የዐማራ ሚልሻና የአካባቢውን ሰው በብዛት አሰባስበን መዋጋታችንን ቀጠልን፡፡ ይሁንና፣ ጠላት ውጊያውን በዙ-23ና በሞርታር ሲያደርገው ግን፣ ከያዝነው ክላሽ ዐቅም በላይ ሆነ፡፡ በመጨረሻም፣ ኃይላችን በሁለት ተከፈለና ግማሹ ወደ ላሊበላ ግማሹ ወደ ጋሸና አቅጣጫ ተሰለፈ፡፡

እዚህ ጋ ላነሳ የፈለኩት፣ ልዩ ኃይሉ ከመከላከያ ጋር ተቀናጅቶ ቀጠናዎችን እየሸፈነ ቢዋጋም፣ በከባድ መሳሪያ ሲመታ፣ መከላከያ ከባድ መሳሪያዎቹን ታቅፎ በርቀት እየተመለከተ፣ ራሱ እስኪመታ እንዲጠብቅ መደረጉን ነው፡፡
በዚህ መሃል፣ የላሊበላውን ቦታ ለማስያዝ እኔ፣ ጸጋዬ አራጌና ደሳለኝ አበራ በመኪና ፈጥነን ሄድን፡፡ ፍላጎታችን ላሊበላ ያለውን ኃይልንና የአካባቢውን ታጣቂዎች በአንድ አድርገን፣ እንደ ሽምቅም እንደ መደበኛም ቦታ ይዘው እንዲዋጉ ለማሰማራት በመሆኑ፣ መሪዎቹን ሰበሰብናቸው፡፡ ነገር ግን፣ ጠላት እኛ እዚያ የመግባታችን መረጃ ደርሶት ስለነበረ፣ ልክ ስብሰባውን ስንጀምር ወደ ጋሸና ገብቶ ቆረጠን፡፡ እኛም ላሊበላ ያለውን ኃይል ቦታ ካሲያዝንና ካስተካከልን በኋላ፤ በጋሸና ስለተቆረጥን፣ ወደ ሰቆጣ ወጣን፡፡ ሰቆጣ ያለውን ብርጌድ አስተካክለን፣ እንደገና ወደ ጋሸና አቅጣጫ ተመለስን፡፡ ይሄ ሁሉ ሲሆን (ከተኩለሽ ጀምሮ እስከ ጋሸና እስከ ላሊበላ) አንድም መከላከያ አልተገኘም፡፡ በመጨረሻ፣ በኮሎኔል ሞላ የመትመራ ሁለት መቶ ሰው ያላት አንዲት ሻለቃ የተወሰነ ከባድ መሳሪያ ይዛ ስለመጣች፣ የእኛን አንድ ብርጌድና የተወሰኑ ሪጅመንቶችን ጨምረን፣ ጋሸና ላይ ትንሽ ውጊያ አደረግን፡፡

ነገር ግን፣ ጠላት ዐሥራ ሁለት ክፍለ-ጦሮች ይዞ ስለገጠመን፣ የኃይል ሚዛኑ በከፍተኛ ሁኔታ አየለብንና ወደኋላ ተመልሰን፣ ደብረ ዘቢጥ ላይ ቦታ ያዝን፡፡ ጨጨሆን ጨርሰህ ብቅ ስትል የምታገኛት ቁልፍ ቦታ ናት፡፡ ውጊያው ማታ ስለነበረም፣ ሌሊት ላይ ለአገኘሁ ተሻገር ስልክ ደውዬ ‹እዚህ ያለው ኃይል አብዛኛው ተዳክሟል፡፡ ከአንድ ብርጌድ የቀረው አምስት መቶና ሦስት መቶ ሰው ነው፡፡ ስለዚህ ሁመራ-ወልቃይት ካሉት ውስጥ አንድ ብርጌድ ይነሳና ይላክልን› አልኩት፡፡ አገኘሁም ‹እሺ፣ ጠዋት ተገኝ› ብሎኝ፣ ስብሰባ አድርገን “በላይ” የሚባለው ብርጌድ በመምጣቱ፣ ደብረ ዘቢጥ ላይ የመከላከል ቁመና አስያዝነው፡፡

አካባቢውንና የጠላትን አቀማመጥ ከገመገምን በኋላም፤ የእኛን ብርጌድ፣ ሚሊሻውን፣ ፋኖውን፣ ያቺ ሁለት መቶ ሰው ያላት የመከላከያ ሻለቃን አስተሳስረን፣ ለአምስት ቀን የጠላትን እንቅስቃሴ ዘግተን ያዝነው፡፡ በቀን ሃያና ሠላሳ ጊዜ ቢያጠቃም፣ ገትረን አቆምነው፡፡

በዚህ ሁኔታ እያለን፣ መከላከያ ኃይል እንዲጨምርልን ደጋግመን ስንጠይቅ፣ ‹ጥሩ ይዛችሁታል እኮ!› እያሉ ሊሰሙን አልፈለጉም፡፡ ‹ኧረ ይሄ ነገር እየመረረ ነው? ጠላት ከቁጥር ብልጫው በተጨማሪ፣ ከባድ መሳሪያ በመታጠቁ ከተደጋጋሚ ውጊያ በኋላ የሚቆስለው፣ የሚሰዋው ስለሚበዛ በወገን ላይ ክፍተት ይፈጥራል፤› ብዬ ላስረዳ ብሞክርም ሰሚ አጣሁ፡፡

አምስት ሌሊትና ቀን ከተዋጋን በኋላ፣ የተዳከሙት ብርጌዶችን እንዲቀይሩ፣ “ዐባይ” የሚባለውን ብርጌድ ወደ ሱዳን ጠረፍ ልኬ፣ “መቅደላ”ን ወደ እኛ እንዲመጣ ‹ተነቃነቅ› አልኩት፡፡ ግና፣ ይህ ብርጌድ መንገድ ላይ እያለ፣ ደበረ ዘቢጥ ያለው ኃይላችን ተገፋ፡፡ ምክንያቱም፣ ያለእረፍትና ተቀያሪ አምስት ቀንና ሌሊት በመዋጋቱ ቁስለኛው በጣም በዛ፡፡ ጠላት ያሰማራው አንድ ሙሉ እዝ ከመሆኑ በተጨማሪ፤ በየስድስት ሰዓቱ ይቀያየራሉ፡፡ የእኛ ሳይቀያየር፣ የሚሰዋውም የሚቆስለውም በእልህና ወኔ ተቀጣቀጠ፡፡ ይሄ ሁሉ እየሆነ አሁንም፣ መከላከያ ኃይል ሊልክልን አልፈለገም፡፡ በመጨረሻ ወደኋላ ተገፋን፡፡

እንደገና በሌላ ኃይል ጨጨሆ መድሃኒዓለም ከፍ ብሎ ያሉ ተራራዎች ላይ ቦታ ለማስያዝ ተረባረብን፡፡ የውጊያ ባህሪ እንዲህ ነው፡፡ ከአንዱ ስትገፋ፣ ሌላው ጋ ይዘህ ትዋጋለህ፡፡ በነገራችን ላይ፣ ለጠላት በስልክ ስለእኔም ሆነ ስለውጊያው መረጃ ሲሰጥ በማኀበራዊ ሚዲያ የተሰማው አጥናፉ ገ/ሚካኤል የተባለው ግለሰብ፣ እዚህ አካባቢ እኛ ቦታ ለማስያዝ ስንሯሯጥ ነው ሰርጎ የገባው፡፡ አይቸዋለሁ፣ ቀይ ነው፡፡ በእኔ አጠገብ እየተመላለሰ፣ በወረራው ቁጭት ያለው ተቆርቋሪ መስሎ ይንቆራጠጣል፡፡ በርግጥ፣ እሱ እንዳለው እኛ ቦታ ለማስያዝ ስንጣደፍ ጠላት ለጥቂት ደርሶብን ነበር፤ (የዞኑ አስተዳደር ወታደራዊ እርምጃ ወስዶበታል፡፡)
ከጨጨሆ ተራሮችም የከባድ መሳሪያ ድጋፍ ስላላገኘን ወደኋላ ተገፋን፡፡

በዚህ መሀል ሱዳን ጠረፍ የነበረችው የልዩ ኃይል ብርጌድ ደረሰች፡፡ አዛዡ አዱኛ ይባላል፡፡ መንገዱ እየተዘጋ፣ እያስከፈትን ስንጓዝ፣ ነፋስ መውጫ ላይ ጠላት እና እኛ እኩል ስለደረስን፣ የከተማ ውጊያ ጀመርን፡፡ ሁለት የጠላት ታንኮች ከመመታታቸው በተጨማሪ፣ ስንዋጋ ዋለን፡፡ ከሰዓት በኋላ፣ መከላከያ በስንት ግብ-ግብ በኮሎኔል ገበየሁ የሚመራ አንድ ብርጌድ ከሁመራ አካባቢ ልኮልን፣ ከእኛ ብርጌድ ጋር አቀናጀነው፡፡ በማግስቱ ደግሞ፣ ብ/ጀ ሰለሞን ቦጋለ የተወሰነ ኃይል ያለው ለሰላም አስከባሪ የተዘጋጀ አንድ ብርጌድ ይዞልን መጣ፡፡ እሱንም አቀናጅተን ጉና ተራራ ወገብ ላይ ውጊያው ቀጠለ፡፡ ጠላትን ባለበት አቆምነው፡፡
ማታ ደብረ ታቦር ላይ የዞኑን አመራሮች ጨምሮ፣ ከመከላከያ ጄነራል አዳምነህና ጄነራል ሰለሞን፣ ከእኛ እኔና ባምላኩ ሆነን ለስብሰባ ብንቀመጥም ሳንስማማ ቀርቶ፣ ልዩነት ተፈጠረ፡፡ ይኼኔ እኔም ጥርጣሬ አደረብኝ፡፡

፨ ልዩነቱ ምንድን ነው?

ልዩነቱ እኛ ‹መከላከያ ተገቢ ኃይል ማንቀሳቀስ ሲገባው፣ ይህን ባለማድረግ ክልሉን በጠላት እያስወረረው ነው› የሚል ግምገማ ስንይዝ፤ እነሱ በደፈናው ‹መከላከያ እየመጣ፣ እየሠራ ነው› አሉ፡፡ የእኔ ስጋት ተቋሙ ውስጥ፣ የኃይል ሚዛን አይተው ሊገለበጡ የተዘጋጁ፣ አፍቃሪ-ሕወሓት ጀነራሎች ስላሉ ነው፡፡ እንዲሁም፣ መከላከያ ላይ ለደረሰው ውድቀት ተጠያቂ ጀነራሎች በሥራ ላይ አሉ፡፡ ከዚህ አኳያም፡- ‹ይሄ ነገር፣ ታርጌቱ የዐማራ ክልልን ማስወረርና ማስወደም ነው፡፡ እውነተኛ ድጋፍ የማይደረግልንም ለዚህ ይሆናል፤› በሚል ተከራከርን፡፡ የዞኑ አመራሮችም በቅርብ ይከታተሉ ስለነበረ፣ እኛን ደግፈው ‹በመከላከያ ላይ እምነት የለንም፡፡ በዚህ ሁኔታ ነገ ደብረ ታቦር የማይያዝበት ምንም ምክንያት የለም፤› አሉ፡፡
በመጨረሻ፣ ‹ሁላችንም ለበላዮቻችን ሪፖርት እናድርግ፣ እየተፈለገ ያለው በግልጽ ክልሉን ማስወረር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ከተያዘ ደግሞ፣ መከላከያ ኖረ-አልኖረ ምናችንም አይደለም?!› ወደሚል ሄድን፡፡

በኋላ፣ ብ/ጀ ብርሃኑ ጥላሁን የሚመራው የመከላከያ “ሠላሳ አራተኛ ክፍለ-ጦር” መጣ፡፡ አሁንም ግን፣ አብዛኛዎቹ መኮንኖች ‹ተጨማሪ ክፍለ-ጦር መምጣት ነበረበት› የሚል ቅሬታ ነበራቸው፡፡ ብቻ እንዴት ጠላትን መከላከልና ማጥቃት እንዳለብን ከተነጋገርን በኋላ፤ ሠላሳ አራተኛን፣ የልዩ ኃይሉን “በላይ” እና “መቅደላ” ብርጌዶችን (የሰው ኃይላቸው ከክፍለ-ጦር አያንስም) ይዘን፤ ሌሎቹንም አጠናክረን ውጊያው ቀጠለ፡፡ አሁንም እንደገና ተገፋን፡፡

፨ ጉና ላይ?

አዎ፡፡ የተወሰነ ቦታ መግፋት ብቻ ሳይሆን፤ እየተዋጋን እያለ፣ ከጋሳይ አቅጣጫ በጎን እያጠቃ ከተማው መግቢያ ላይ ሙሉ-በሙሉ ቆረጠን፡፡ እኛም ፈጥነን መቅደላ ብርጌድን፣ ኮማንዶና ሌሎችንም ወደዛ ልከን፤ ውጊያውን አስፍተን በመቀጠል፣ የቆረጠንን የጠላት ኃይል ጠረግነው፡፡ “ቆረጣ” ሲባል ሰው ዝም ብሎ ይደነግጣል እንጂ፤ ተረጋግቶ የገባለትን ጠላት አስፍቶ በቀላሉ መምታት ይችላል፡፡ በውጊያው ሁለት መቶ የሰው ኃይል ያላት ሻለቃ ይዞ የመጣው ኮሎኔል ሞላ ተሰዋብን፡፡ እንዴት ያለ ጀግና ነበር! የዚያው አካባቢ የመቄት ልጅ ነው፡፡ በእልህና በቁጭት ነበር የተዋጋው፡፡ ሌላው በጣም ጀግና የነበረው የሠላሳ አራተኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አብርሃም በከፍተኛ ሁኔታ ቆሰለ፡፡ የመርሳ ወይም የቆቦ ልጅ ነው፡፡ እሱም በእልህና በቁጭት ተዋግቷል፡፡ አሁን እግሩ ተቆርጦ ባህር ዳር ነው ያለው፡፡ ለአገሩና ለሕዝቡ የከፈለው ዋጋ ቢሆንም፣ ያሳዝናል፡፡
ከዚህ በኋላ፣ ከጋሳይ ወጣ ብለን ቦታዎች ያዝን፡፡ ይሄን ጊዜ፣ በኮሎኔል ደስታ የሚመራው የመከላከያ ሠላሳ ሦስተኛ ዐባይ ክፍለ-ጦር መጣ፡፡ ጠላት በአካባቢው እየፈጠረ ስላለው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ከተወያየን በኋላ፤ ዐባይ ክፈለ-ጦርን ሙሉ-በሙሉ ወደ ውጊያ አስገባነው፡፡ የልዩ ኃይሉን መቅደላንና በላይን ጨምሮ፤ ሠላሳ አራተኛ ከፍለ-ጦርን ደግሞ፣ በመልሶ ማቋቋም አጠናከርናቸው፡፡ ከዚያም፣ ጠላትን ከቀኝ-ከግራ እያጣደፍን ስንመታው፣ እንደበፊቱ እያጠቃ መቀጠል ተሳነው፡፡ ብዛት ያላቸው ኮሎኔሎችና የበታች አመራሮችም ተሰውበት፤ አንድ ኮሎኔል ደግሞ ተማረከበት፡፡

ከምርኮኛው ኮሎኔል፣ ጠላት እንዴት እየተዋጋ እንደነበረና እንደተዳከመ የተሟላ መረጃ ስላገኘን፣ ወዲያውኑ በሙሉ ቁመና ወደ ማጥቃት ገባንና ተፈላጊ መሬቶችን ያዝን፡፡ በሌላ በኩል፣ በአካባቢውና በአብዛኛው የፖለቲካ አመራር ‹ደብረ ታቦር ሊያዝ ነው› የሚል አለመረጋጋት ስለነበረ፣ መግለጫ ለመስጠት ተገደድኩ፡፡ ጠላትን ማቆማችንንና ወደፊት ሊቀጥል እንደማይችል፣ እኛም እያሳደድን እንደምንመታው አስረግጬ፣ የማረጋጋት ሥራ ሠራሁ፡፡ በተለይ ደብረ ታቦር ላይ ራሳችን በግልጽ እየታየን በመዘዋወር ሕዝቡ እንዲረጋጋ አድርገናል፡፡

ጠላት አከታትለን ባሳረፍንበት ምት፣ በአንድ ጊዜ ተንዶ ሌሊቱን መቄት ገባ፡፡ የተወሰነ እየተጠባጠበ የቀረውን እየመታን ደብረ ዘቢት ጥጉ ድረስ ሄድን፡፡ እዚያም ወገን ሙሉ ቁመና መያዙን አረጋግጬ፣ ወደኋላ ተመለስኩ፡፡ ምክንያቱም እኔ ወደ አዛዥነት ስመጣ የጠላት ጥቃት ፋታ የሚሰጥ ስላልነበረ፣ የሠራዊታችንን ስታፍና አንዳንድ ጉዳዮችን ለማስተካከል ጊዜ አላገኘሁም ነበር፡፡ እናም ወደኋላ ተመልሼ በተወሰነ መልኩ አስተካክዬ፣ ወደ ሰቆጣ አቅጣጫ ሄድን፡፡

እዚያ የነበሩትን “ጣና” እና “ቴዎድሮስ” ብርጌዶችንም በመልሶ ማቋቋም ካጠናከርን በኋላ፤ በአካባቢው ስላለው ጠላት መረጃ ስናሰባስብ፡- ‹በዚህ በኩል ያጠቁኛል› ብሎ ስላልጠረጠረ ንብረት እያከማቸ ተረጋግቶ መቀመጡን ተረዳን፡፡ ንጋት ላይም በጣና ብርጌድ በድንገት አጥቅተን፣ ሰቆጣ የነበረውን ሙሉ-በሙሉ መትተን ወደ አበርገሌና ዛታ አሳደድነው፡፡ በአጋጣሚ ብዛት ያለው “የአገው ሸንጎ” የሚባለው ሕወሓት ያቋቋመው ባንዳ ስብስብንም ከተማ ውስጥ ተበትኖ አገኘነው፡፡ ሕዝቡም እያነቀ ይዞት መጣ፡፡ እሱንም ጠራርገን፣ ሰቆጣን ነፃ ካደረግን በኋላ፣ ወደ ላሊበላ አቅጣጫ ልናጠቃ ሄድን፡፡

ላሊበላ ላይ ጠላት ተዘጋጅቶ ጠበቀን፡፡ ሆኖም፣ በታችኛው ጫፍ በኩል መንገዱን ቆርጠን ወደ ከተማው አጠቃነው፡፡ ከባድ የከተማ ውጊያ እያደረግን እያለም፣ ከጋሸና አቅጣጫ ከፍተኛ ኃይል ያለው ሜካናይዝድ ይዞ መጣ፡፡ አሁን የኃይል ሚዛኑ ወደ ጠላት ስላጋደለ፣ ከአምስት ቀን ውጊያ በኋላ ለማፈግፈግ ተገደድን፡፡ በወታደራዊ ሳይንስም፣ አንድ የውጊያ መሪ አመቺ ሁኔታ ሲያገኝ ያጠቃል፤ እንቅፋት ሲኖር ይከላከላል፤ የኃይል ሚዛኑ ካየለበት ደግሞ ገለል ይላል፡፡ እኔም የተከተልኩት ስልት ይህንን ነው፡፡

የሆነው ሆኖ፣ ሰቆጣና ላሊበላ ላይ ጠላትን የመታነው በከፍተኛ ደረጃ ስለነበረ፣ ከተለያየ አቅጣጫ ኃይል አሰባስቦ ከቡግና እስከ ተከዜ ጫፍ ድረስ መጣ፡፡ ሰቆጣ የነበረውም፣ እንደገና ኃይል አደራጅቶ እስከ አምደ ወርቅ ድረስ መጣ፡፡ እኛ ግን መሥራት ያለብንን በጥንቃቄ ስለሠራን፣ ሁለት ነገር አሳክተናል፡፡ አንዱ፣ ጠላትን በተገኘው አጋጣሚ ማዳከማችን ሲሆን፤ ሁለተኛው፣ የወገንን የውጊያ ብቃት ማሳደግ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ያለ ውጊያ ተሳትፎ አይገኝም፡፡ የማጥቃቱን እርምጃ የወሰድነው በራሳችን ተነሳሽነት ቢሆንም፤ በቅድሚያ ግን ያለንን ኃይልና የጠላትን ወታደራዊ ቁመና ገምግመናል፡፡

፨ ጉና ላይ ሕዝቡ ተሳትፏል?

አዎ፡፡ በተለይ መስተዳድሩ፣ የመንግሥት ሠራተኛው፣ ፖሊሱ፣ ሚሊሻው፣ ፋኖው የተሰጠውን ተልዕኮ ተወጥቷል፡፡ ከሕዝቡም ብረት ያላቸው ወደ ውጊያ የገቡ አሉ፡፡ አብዛኛው ግን ምግብ በማቀበል ነው ትልቅ ድጋፍ ያደረገው፡፡ ጠላት መቋቋም ተስኖት ሲበታተን ደግሞ፣ ሕዝቡ እየመታና መሳሪያውን እየነጠቀ አስቀርቶታል፡፡ በነገራችን ላይ፣ የጠላት ዋና አዛዦች እነ ጄነራል ፃድቃን ደብረ ታቦር ለመግባት በጣም ከመንሰፍሰፋቸው በላይ፤ እርግጠኛ ስለነበሩ ንፋስ መውጪያ ድረስ መጥተው ነበር፡፡ ጋሳይ ላይ ምቱ ሲጠነክርባቸው ነው የሸሹት፡፡ ከቀኝ-ከግራ ስናጣድፋቸው የውሸት ወሬያቸውን ማናፈስ ጀመሩ፡፡ ‹በስቴ እየገባን ነው›፣ ‹በደብረ ታቦር ታቹን አልፈን ቆርጠናችኋል› የሚሉ ወሬዎችን ቢነዙም፤ ሕወሓትን ስለምናውቀው፣ ሳንደናገጥ ከፊታችን የመጣው ዋና የጠላት ኃይል ላይ ተረባረብንበት፡፡ በመጨረሻም ጠርገን አወጣነው፡፡
እዚህ ጋ፣ መታወቅ ያለበት የጠላትን ቅስም ከሰበሩ ውጊያዎች፣ የጉናው ዋንኛው መሆኑን ነው፡፡

፨ ጉና ላይ ብዙ ኃይል ነበረ ያሰለፈው?

ዐሥራ ሁለት ክፍለ ጦር፡፡ ጋሸና ላይም ያስቀመጠው አለ፡፡ ዓላማው አንዱን ተደራቢ ኮር ጋሸና አካባቢ አድርጎ፣ ሦስት ኮሮችን ወደ ወረታ በመላክ፣ አንዱ እዛው ወረታ እንዲሆን፤ ሁለቱ ደግሞ አንዳቸው ባህር ዳር፣ አንዳቸው ጎንደርን እንዲይዙ ነበር፡፡ ‹እይዛለሁ› ብሎም ርግጠኛ ነበር፡፡ እያሳደድን ስንጠርገው ግን ተስፋ ቆረጠ፡፡ ምክንያቱም፣ የጎጃምንና የጎንደርን ከተሞች ለመዝረፋ በጣም ቋምጦ ነበር፡፡ በርግጥ፣ በተለያዩ ውጊያዎች እንደታዘብኩት፣ ወያኔ ከመዋጋት በላይ፣ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለዘረፋ ነው፡፡
ሌላኛው የጠላትን ቅስም የሰበረው ውጊያ የጭናው ነው፡፡ በዚህ ግንባር ምክትሌ ነው የተሰለፈው፡፡ እቅዱ ወደ ጎንደር ሰንጥቆ በመግባት፣ ከጽንፈኛው የቅማንት ቡድን ጋር ለመገናኘት በመሆኑ፣ በዳባትና ደባርቅ መሃል ነበር የመጣው፡፡ እዚህ ላይ፣ ትልቅ ዋጋ የከፈለው የአካባቢው ሕዝብ ነው፡፡ በቱልቱላ ተቀስቅሶ ግልብጥ ብሎ ከመከላከያ ጎን ተሰልፎና መስመሩን በጥይት ቶክስ አስሮ እንደ ቅጠል አርግፎታል፡፡ በዚህ ግንባር የነበረው ምግበ የሚባለው አዛዥ “ጠብቀኝ፣ ከአንድ ሰዓት በኋላ ደባርቅን እይዛታለሁ!” እያለ ይፎክር ነበር፡፡ እዛ የነበረው መከላከያ ጥሩ ተዋጊ በመሆኑ፣ እስኪበቃው ቀጥቅጦታል፡፡ የእኛም ተከዜ ብርጌድ በደንብ ተፋልሟል፡፡ ፋኖና ሚሊሻውም ክቡድ መስዋእትነትን ከፍለዋል፡፡

፨ ከጉና በኋላ አልተከተላችሁትም እንዴ?

ተከትለነውማ ነው፣ የወገን ኃይል ደብረ ዘቢጥን አጥቅቶ የያዘው፡፡ እንደገና እየቆራረጠ ወደ መቄትና ገረገራ ወገብ ይዞት ገባ፡፡ እዚያ ላይ ጠላት ተደጋጋሚ ማጥቃት ቢያደርግም፣ ስንዝር መራመድ አልቻለም፡፡ ወገን ወደፊት “አንቺው” ወደሚባሉ ቦታዎች ተጠግቶ፣ በማጥቃት ላይ የተመሰረተ ጥሩ የመከላከል ቁመና ያዘ፡፡ ያ አካባቢም የተረጋጋ ሆነ፡፡ ጠላትም እየተመታና የያዘውን እየተነጠቀ በመሄዱ፣ ጋሸናን ብቻ ይዞ ተቀመጠ፡፡ ቁልፍ ቦታ በመሆኗ ተሟሟተባት፡፡

በጎንደር ሲያቅተው ነው፣ በወሎ በኩል የሄደው ማለት ነው?
አዎ፡፡ ጠላት በጎንደር የሞከረው አልሆን ሲለው፣ ቀጥታ ወደ ደሴ መስመር ሄዶ ማጥቃት ጀመረ፡፡ በዚያ ክፍተት አገኘ፡፡ መከላከያ የሚችለውን ያህል ተዋግቷል፡፡ ልዩ ኃይሉም በሁሉቱም አቅጣጫ ተዋግቷል፡፡

እኛም ከደባርቅና ከእብናት አካባቢ የተወሰነ ልዩ ኃይል ይዘን ወደ ደሴ መጥተን፣ እየተፋለሙ ከነበሩ የጦር መኮንኖች ጋር ስለውጊያው አቅጣጫ ከተነጋገርን በኋላ፤ ወደ ሃይቅ ሄደን ለመዋጋት ተንቀሳቀስን፡፡ እዚያ ስንደርስ በቦታው የነበረው መከላከያ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገና ዋጋ እየከፈለ ነበር፡፡ ልዩ ኃይሉም ከመከላከያ ጋር ሆኖ በሃይቅ፣ ቢስቲማን… በሁሉም በኩል ሲዋጋ ነበር፡፡ ሌላ ተጨማሪ ኃይል ይዘን ወደ ኩታበር ወደታች ስር ገብተን ማጥቃት ጀመርን፡፡ ኩታበርንም አልፈን “ተንታ መለያያ” የሚባለው ላይ እየተዋጋን እያለ፣ ጠላት ሙሉ-በሙሉ ከጀርባ ቆረጠን፡፡ እንደ ቆረጠን ያወቅነው ማታ ነው፡፡ እኛም መልሰን ከጀርባ ቆረጥነውና ወደ ኩታበር ጠርገን ይዘነው መጣን፡፡ ከታች የነበረውን ኃይላችንንም በሙሉ አወጣነው፡፡ ተጨማሪ ሌላ ኃይል አስገብተን፣ ውጊያው ኩታበር ላይ ቀጠለ፡፡

ጠላት እንደገና በሌላ አቅጣጫ በቦሩ ሜዳ መጣ፡፡ እዚያም ኃይል አስገብተን ባለበት አቆምነው፡፡ ማታ አካባቢ የሰሜን እዝ ክፍለ-ጦሮች ስለመጡ የበለጠ ተጠናከርን፡፡ የጠላት ፍላጎት ከፍተኛ ውጊያ ሃይቅ አካባቢ ከፍቶ፣ አዘናግቶ መግባት ነበር፡፡

አሁንም ሌላ ድብቅ ኃይል አምጥቶ፣ በታች በገራዶ አድርጎ ወደ ጦሳ አናት ሊገባ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ደረስንበትና፣ በቂ የዐማራ ልዩ ኃይል አስቀመጥን፡፡ ወያኔም ወደ ጦሳ ተራራ አናት ሊያጠቃ ሲሞክር፣ የተራራው ወገብ ላይ ገትሮ ይዞ፣ እንደ ቅጠል አረገፈው፡፡ በእዚህ ውጊያ፣ አንድ ፈረንጅ ለጠላት ወግኖ ሲዋጋ ተገድሏል፡፡
መጀመሪያውኑ ሕወሓት ደሴ ድረስ እንዴት መጣ?
ከወልዲያ ተነስቶ የአምባሰል ተራራዎችን እየነጠቀ፣ እየነጠቀ… በመጠጋት ነው የመጣው፡፡

፨ በጎንደር በኩል ያደረጋችሁትን መከላከል፣ ለምን በደሴ አላደረጋችሁም?

እንግዲህ፣ በወሎ የተዋጋውን የመከላከያ ኃይል ሳየው፣ ከመቀሌ ጀምሮ እየተዋጋ የመጣ ነው፡፡ ልዩ ኃይሉን መጀመሪያውኑም፡- በላስታ፣ በዋግ፣ በደብረ ታቦር ነው ያረባረብነው፡፡ ደሴ አካባቢ ትርጉም ያለው ኃይል አልነበረንም፡፡

፨ ለምን?

የመከላከያ ከፍተኛ ኃይል እዚያ ስለነበረ፣ በእሱ ተማምነን፡- በጋሸና፣ በሰቆጣ፣ በላሊበላ፣ በደብረ ታቦር፣ በጭና… ተጠመድን፡፡ ይህም ሆኖ፣ መጀመሪያ ወደ ደሴ ሊገባ ሲል ሃይቅ ላይ ገትሮ የያዘው፣ ከሰቆጣ የላክነው በኮሎኔል አምሳሉ የሚመራ “ጋፋት” የሚባለው የልዩ ኃይላችን ብርጌድ ሁለት ሁለት ሻለቃ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ፣ በደሴ ውጊያ እኔም ራሴ ኃይል ይዤ ገብቼ፣ በኩታበር በኩል በደንብ መተነው ነበር፡፡ እንደገና ወደ ጦሳ የመጣው የሕወሓት የኮማንዶ ኃይልም፣ ተንደርድሮ አናቱ ላይ ሊወጣ ሲል፣ ተራራው ወገብ ላይ ይዘን ከቀኝ-ከግራ አጣበቅን ፈጅተነዋል፡፡ ደሴ እንዳይያዝ ተረባርበን፣ ከዐሥር ቀን በላይ አቁመነዋል፡፡

በመጨረሻ፣ ‹ወደፊት ሊቀጥል አይችልም› ያልነው ጠላት፣ ከሌላ ቦታ ዐዲስ ኃይል አምጥቶ በሃይቅና በቦሩሜዳ አቅጣጫ ያለውን የመከላከያ ኃይልን ጠረገው፡፡ በዚህም ደሴን ያዘ፡፡

፨ ልዩ ኃይል ማምጣት አልቻላችሁም ነበር?

ከደባርቅና ከእብነት የነበሩትን አመጥቼ፣ እዚያ ከነበሩት ጋር አቀናጅተን ከዘጠኝ ሻለቃ በላይ ነበረን፡፡ የእኛ ኃይል የሰጠነውን ተልእኮ እየፈፀም ነበር፡፡ የገራዶ አናቱን እኮ ይዟል፡፡ ክፍተቱ የተፈጠረው በታች መከላከያ ከተደጋጋሚ ውጊያ በኋላ በመዳከሙ ነው፡፡

ከመከላከያ አዛዦች ጋር እየተነናበባችሁ አልነበረም?
እንናበባለን፡፡ ለምሳሌ፣ ከእኔ ጋር ጄነራል ሀሰን ኢብራሂም ነበር፡፡ እሱ መከላከያውን እያመጣ፣ ከልዩ ኃይሉ ጋር እያቀናጀነው ነበር፡፡ ከሌሎች የመከላከያ አዛዦች ጋርም እንመካከራለን፡፡ ችግር የተፈጠረው፣ በውጊያው ላይ የነበረው የወገን ጦር ባለመቀያየሩ ነው፡፡ ጠላት በየስድስት ሰዓቱ ይቀያየራል፡፡

፨ መከላከያም አይቀያየርም እንዴ?

መከላከያውም ልዩ ኃይሉም አንዳንድ ጊዜ ስልታቸው አንድ ነው፡፡ ዝም ብሎ እስከመጨረሻው ሳይቀያየሩ ይዋጋሉ፡፡ ጠላት ይሄንን ክፍተት ተጠቅሞ ነው፣ በዐዲስ ኃይል ጥሶት የገባው፡፡ በተረፈ፣ እዚያ አካባቢ፣ በተለይ ቦሩሜዳና ከታች የነበሩት ተፋልመዋል፡፡ ያን ያህል ጊዜ ከመርሳ፣ ወርጌሳ፣ ውጫሌ… እየተዋጉ ነው የመጡት፡፡ አብዛኛው ኃይል መከፈል ያለበትን ዋጋ ከፍሏል፡፡

፨ ደሴ ላይ ‹በትግርኛ ተናጋሪዎች ከጀርባ ተመታችኋል› የተባለው እውነት ነው?

አዎ፡፡ የተወሰኑ ሰዎች እንደዛ አድርገዋል፡፡ አስቀድመው ተዘጋጅተው የነበሩ ናቸው፡፡ የሚያሳዝነው፣ አሁንም ወንጀለኞቹ ላይ እርምጃ አልተወሰደም፡፡ ‹እነዚህ ሰዎች ደሴ ለመያዙ አስተዋጽኦ አላቸው› የተባለው ግን ውሸት ነው፡፡ መጨረሻ ላይ፣ የወገንን መውጣት አይተው ነው መተኮስ የጀመሩት፡፡

፨ ደሴ ሲያዝ ወዴት ሄዳችሁ?

ደሴ ከተያዘ በኋላ፣ ጠላት በአንድ በኩል ወደ ኮምቦልቻ አቅጣጫ አድርጎ ወደ ሸዋሮቢትና ደብረ-ሲና ቀጠለ፡፡ ሌላው ደግሞ፣ ወደ ቦረና ወሎ፣ ቦረና ተንታ አቅጣጫ እያጠቃ ሄደ፡፡ መከላከያም እየተዋጋም በጠላትም እየተገፋ ሙሉ-በሙሉ ወደ መራቤቴ አቅጣጫ አፈገፈገ፡፡ ይሄኔ፣ በጎጃም መስመር የመርጦ ለማርያም መንገድ ክፍት ሆነ፡፡ እኛም በፍጥነት “ገነት” የሚባል ወታደራዊ መሬት ላይ ከልዩ ኃይሉ በተጨማሪ፣ የምስራቅ ጎጃምና የደቡብ ወሎ ሚሊሻዎችን አምጥተን አስቀመጥን፡፡ ፋኖዎችም አሉ፡፡ በዋነኛነት ግን የልዩ ኃይሉ ጣና ብርጌድ እዛ ላይ እንዲዘጋ ተደረገ፡፡ ጠላት ከፍቶ ለመግባት ሠላሳ ሰባት ጊዜ የማጥቃት ሙከራ ቢያደርግም፣ ገትሮ ያዘው፡፡
በዚህን ጊዜ ነው፣ ‹አዲስ አበባን ለመከላከል ሁለት የዐማራ ልዩ ኃይል ብርጌድ ወደ ጣርማ-በር ላኩ› የተባልነው፡፡

፨ ማነው ያለው?
ዶ/ር ዐቢይና አቶ ደመቀ፡፡

፨ ታዲያ ላካችሁ?

አዎ፡፡ ቴዎድሮስ ብርጌድ ወደ ጋሸና ሄዶ ስለነበረ፤ ደጀን ብርጌድን ላክን፡፡ የተሰጠው ዋንኛ ተልዕኮም መጀመሪያ ጣርማ በርን እንዲይዝ፤ ከዚያ ወደ መዘዞ፣ ባሽ፣ ሰላ ድንጋይ እንዲያጠቃ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ ወደ ጣርማ-በር እያጠቃ የሚመጣው የሕወሓት አዛዥ፣ በ1983 ዓ.ም ይቺን ቦታ ቆርጧት ስለነበረ፤ ‹አሁንም ከቆረጣት፣ ሌላው ያከትምለታል› በሚል ነው፡፡ እኛም አዛዦቹን ‹መጀመሪያ በደንብ አረጋግጡ፤ ከዚያ በኋላ ወደ መዘዞ፣ ባሽ፣ ሰላ ድንጋይ አጥቁ› የሚል መመሪያ ሰጥተናቸው ስለነበረ፣ በዚያ መሰረት አጠቁ፡፡ በወቅቱ ልዩ ኃይሉ ብቻውን ነው የተዋጋው፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ፣ መከላከያ ከሸዋሮቢት ተገፍቶ በመምጣቱ፣ ተቀናጅተው ወደ ሸዋሮቢት አቅጣጫ አጠቁ፡፡ እንግዲህ፣ ጠላት ወደኋላ መመለሰ የጀመረው እዚህ ጋ በደንብ ሲመታ ነው፡፡

በሌላ ግንባር ደግሞ፡- መቅደላ፣ በላይ፣ ምንሊክ፣ ቴዎድሮስ እና ነብሮ የሚባሉ የዐማራ ልዩ ኃይል ብርጌዶች ሙሉ-በሙሉ ጋሸናን ተቆጣጠሩት፡፡ መከላከያ ጋሸና ላይ ትርጉም ያለው ኃይል አልነበረውም፡፡ መጀመሪያውኑም ልዩ ኃይሉ ነው፣ ገትሮ የያዘው፡፡ በመጨረሻ የጋሸናው ውጊያ እየተጋገለ ሲገፋ፣ የሸዋውም እየጠነከረ ሄደ፡፡ በተለይ በአፋር አቅጣጫ የገባው መከላከያ ትልቅ ጀብዱ ሠርቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ፣ ጠላት እየተሰበሰበ የሄደበት ሁኔታ ተፈጠረ፡፡

በጥቅሉ፣ የሕወሓት ግስጋሴ እንዴት ተቀለበስ?
ጠላት ወደ አዲስ አበባ የሚያደርገው ግስጋሴ ከተቀለበሰበት ምክንያት ዋንኛው፣ ከደጀኑ ርቆ በጥልቀት መግባቱ ነው፡፡ በዚህም ሕዝቡ፣ መከላከያው፣ ልዩ ኃይሉ፣ ሚሊሻው፣ ፋኖው እንዲረባረብበት አደረገ፡፡ የሚገርመው ነገር፣ የወያኔ ጄነራሎች ‹የጦር ጠበብት ነን› እያሉ እየፎከሩ፤ ያለምንም ፖለቲካ ሥራ፣ ተዋጊዎቻቸውን በዚህ ደረጃ ‹ጠላቴ› በሚሉት ሕዝብ መሃል ጠልቆ እንዲገባ ማድረጋቸው ነው፡፡ ስትራቴጂያቸው በወታደራዊ ዓይን ሲታይ፣ ከጋሸና አቅጣጫ፣ ከአፋር አቅጣጫ የወገን ኃይል እያጠቃ ነው የመጣው፡፡ ይሄ ትልቅ የውሳኔ ስህተት ነው፡፡ የኋላ ደጀን ሳይፈጥሩ፣ በድፍኑ ‹ጣርማ-በር ሲያዝ ነገሩ ይቀያየራል› ብለው ነው የገቡበት፡፡ በኋላ ምቱ እየበረታባቸው ሲሄድ፣ የአየር ድብደባውም ሲያይል፣ ወደፊት መቀጠል በማይችሉበት ደረጃ መሀል ላይ ተቀረቀሩ፡፡ እየወደቁ፣ እየተነሱ፣ እየተንጠባጠቡ ነው የሸሹት፡፡
በርግጥ፣ የላይኞቹ አዛዦች በጣም ስሜታዊና ችኩል ስለሆኑ፣ ትንሽ ድል ሲያገኙ፤ የወደፊቱን አርቀው ማየት እንደማይችሉ አውቃቸዋለሁ፡፡

፨ የአየር ኃይል አስተዋጽኦ እንዴት ነበር?

አየር ኃይል፣ ትልቅ ሚና የነበረው በድሮን ነው፡፡ አውሮፕላኖቹ በጣም አልፎ-አልፎ ነበር የሚያጠቁት፡፡ በተለይ ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች በዲሽቃ የመመታት እድላቸው ሰፊ ስለነበረ፣ በአብዛኛው አፈር በረሃ ላይ ነው፣ የሚሸሸውን የለቀሙት፡፡ ይሄ በኢትዮ-ኤርትራ ውጊያም ያጋጠመን ነው፡፡
ጠላት በሙሉ ዐቅሙ ነው የተመለሰው ወይስ ተዳክሞ?
ሲመለስ በውጊያው የደረሰበት ጉዳት አለ፡፡ በተለይ በጣም ያለቁበት ውጊያውን የሚመሩት መስመራዊ መኮንኖች (ከኮሎኔል በታች) ያሉት ናቸው፡፡ በውጊያው ለመቀጠል ያስቸገረው አንዱ ገፊ-ምክንያትም ይህ ነው፡፡
በተቀረ፣ የተኩስ ዐቅሙ ላይ የደረሰበት ኪሳራ ቢኖርም፤ የሰሜን እዝ ኃይሉን ይዞ ነው የወጣው፡፡ ጠላት በዚህ ደረጃ ተዛብቶ እየሸሸ ሳለ፤ ወገን እያሳደደ እንዲደመስሰው አለመደረጉ ዳተኝነት ነው፡፡

፨ ይሄ የሆነው ለምንድን ነው?

መከላከያው ስለተዳከመ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ነው እኮ፣ ደብረ-ሲና ድረስ ከፋፍቶት የገባው፡፡

፨ አሻጥር ሊሆን አይችልም?

አይ፣ አሻጥር አይደለም፡፡
በ1983ቱ እና በዛሬው የሕወሓት ተዋጊዎች መሃል የታዘቡት

፨ ልዩነት አለ?

አዎ፣ በዚያን ጊዜ የነበረው፣ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሩ፣ ሎጀስቲኩ በደንብ የተጠናከረ ነው፡፡ ሠራዊታቸውም በዲሲፕሊን የታነፀና ዐቅም ያለው ነበር፡፡ ዐማራውን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው አቅደውና ተጠንቅቀው በጥበብ ነው የተገበሩት፡፡ መሬት ላይ የወረደ ፖለቲካ ሠርተዋል፡፡ ኦሮሞውንም፣ ሌሎችንም ከጎናቸው ለማሰለፍ ሞከረዋል፡፡ በወቅቱ የነበረውን የመንግሥት ሠራዊትንም ሳይቀር፣ እያፈረሱ ‹የመኮንኖች ድርጅት› በሚል ያሰባስቡ ነበር፡፡ በየትኛውም አካባቢ ሕዝብን ስለሚያከብሩ፣ ነፃ አውጪ አድርጎ ነበር የተቀበላቸው፡፡

የአሁኖቹ ግን፣ የመሪዎቹም የተዋጊዎቹም ድርጊት የእብድ ነው፡፡ የሚንቀሳቀሱትም በወታደራዊ ሥነ-ሥርዐት ሳይሆን፤ እንደ ማጅራት መቺና በደመ-ነፍስ ነው፡፡ ዐማራን እንደ ሕዝብ ማጥቃት አልነበራቸውም፡፡ ጭራሽ፣ ወደ ዐማራ ክልል መግባት አያስፈልግም ነበር፡፡ ‹የትግራይን እምባ መጥረግ› ለሚሉት ረብ-የለሽ ዓላማቸው፤ ‹ዐማራን ማድማትና ማስለቀስ አለብን› ብለው ደመደሙ፡፡ ትልቁ ስህተት ይህ ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብን በትክክል ካየኸው፣ ከዐማራ በላይ ወዳጅ የለውም፡፡ ችግር ሲገጥማቸው የሚሰደዱት ወደ ዐማራ ነው፡፡ የአሁኖቹ መሪዎች እብድ ስለሆኑ፣ ‹ዐማራን እንበቀላለን፣ ሂሳብ እናወራርዳለን› ብለው ፎክረው፣ ፈጸሙት፡፡ የዚህ ገፊ-ምክንያት፣ የድርጅቱ መሪዎች ወታደራዊ አዛዦቹ በመሆናቸው ነው፡፡ እነሱ ደግሞ፣ ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ ሌባ የነበሩና አራት አምስት ህንፃ የገነቡ ናቸው፡፡ በዐማራና አፋር መሬት የትግራይ ወጣቶችን እያስጨረሱ እንኳ፣ የሚታያቸው አዲስ አበባ ያሉት ህንፃዎቻቸው ብቻ ነው፡፡ አዛዦቹ የነቀዙ ዘራፊ በመሆናቸው ነው፣ ሠራዊታቸው እናቶች መቀነታቸው ላይ የቋጠሯትን ሳንቲም ሳትቀር ፈትሾ የወሰደው፡፡ ‹የትግራይ ሕዝብ እንደዚህ ነው እንዴ?!› እስክትል ድረስ፣ ሊጥና ሰፌድ ዘረፍዋል፡፡

በ1983 ዓ.ም ሲመጡ ግን፣ ከንዋይ ፍቅር ይልቅ፤ እንደ ድርጅት ‹እናሳካዋለን› የሚሉት ዓላማ ነበራቸው፡፡
ጌታቸው ረዳም ቢሆን የተረጋጋ አይደለም፡፡ መጀመሪያም የተጠጋቸው ቁሳዊ ፍጎቱን ለማሟላት ነው፡፡ እነሱም የሚፈልጉት የዐማርኛ ችግር ስላለባቸው፣ ዐማራንም ሆነ ሌላውን ብሔር እንዲሰድብላቸው ነው፡፡

፨ ከልዩ ኃይል አዛዥነት የተነሱት ፈልገው ነው?

አይደለም፡፡ መጀመሪያ በክተት ጥሪው ስንገባ፣ ልዩ ኃይሉ በጣም ተዳክሞ ነበር፡፡ ቀስ እያልን፣ ግን በስፋት እየሠራን ጥሩ ተዋጊ እንዲሆን፣ በቁጥር እንዲበዛ አደረግነው፡፡ በሁሉም የዐማራ መሬቶች መዋጋት የሚችልበን ቁመናም ፈጠርንለት፡፡ ልዩ ኃይሉም ግዳጁን በሚገባ በመወጣት አስመስክሯል፡፡

ጦርነቱን በከፊል ድል ካደረግን በኋላም፣ ‹ውጊያው እንዴት ነበር?› በሚል የስድስት ወር ግምገማ አካሄድን፡፡ በተደራጀ ሁኔታ እንደመራነው፣ የተሻለ ቁመና ላይ እንዳለ፣ ጥሩ ጥሩ አዛዦችን ከላይ እስከ ታች እንዳበቃን፣ ትጥቁም በንፅፅር የተሻለ እንደሆነ…፤ እንዲሁም ‹አሉ› የምንላቸውን የዲሲፕሊን ችግሮች አንስተን ገመገምን፡፡ ግምገማው ሲጠናቀቅም የክልሉን ፕሬዚዳንት፣ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የሰላምና ደህንነት ኃላፊን ጋብዘናቸው የሥራነውን ሥራ አድነቀው፣ አስተያየትና መመሪያ ሰጥተውን ተለያየን፡፡
ከዚያ በኋላም፣ የአዛዦችን የፊልድና የአመራር ስልጠናን ጨምሮ፤ ለየት ያሉ ኃይሎችን ለማሰልጠን አቅደን ሥራ ጀመርን፡፡ ጎን-ለጎንም በዛ ያለ ኃይል ሁመራ አካባቢ፤ ሌላውን ደባርቅ፣ ሰቆጣና ቆቦ ተፈላጊ መሬቶች ላይ አስይዘን፣ ከመከላከያ ጋር ሆኖ እየሰለጠነ እንዲዋጋ አመቻቸን፡፡ የፖለቲካ አመራሩም በውጊያው ትልቅ ሚና ያላቸውን የልዩ ኃይሉን አዛዦችንና አባላትን ለመሸለምና ማዕረግ ለመስጠት ወስኖ፣ ‹ስም ዝርዝር አምጡልን?› ብሎ ስለጠየቀን፣ በኮሚቴ ሠርተን ሰጥተነዋል፡፡
በዚህ ሁኔታ እያለን፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ምክትሎቹንና ሌሎቹን ይዞ ስብሰባ ጠራን፡፡

፨ ድንገት ነው?

አዎ፡፡ ‹ኮሚቴዎችህን ይዘህ ና› ስላለኝ፣ ይዤ ሄድኩ፡፡ አብዛኛውን ሰዓትም ስለጥሩ ሥራዎቻችን አብራርተው፣ የከፈልነውን ዋጋ አስታውሰው፣ በችግር ጊዜ መምጣታችንን አድንቀው… ካመሰገኑ በኋላ፤ ‹ለተሻለ ማስተካከል› በሚል፣ እኔን የፕሬዚዳንቱ አማካሪ፤ በእኔ ቦታ ደግሞ መጀመሪያ ምክትሌ፣ ቀጥሎ ሰላምና ደህንነት የመደቡትን ጄነራል ‹እንሾማለን› አሉ፡፡

ሹም-ሽሩን ሲጨርሱ፣ ‹አስተያየትህ ምንድን ነው?› ብለው ጠየቁኝ፡፡ ‹የምትወስኑት እናንተ ስለሆናችሁ የፈለጋችሁትን መሾም ትችላላችሁ፡፡ እኔ ወደዚህ ኃላፊነት የመጣሁት ለግል ፍላጎቴ ሳይሆን፤ ክልሉ ትልቅ ክፍተት ስለነበረበት የበኩሌን ለማድረግ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተሳክቶልኛል፡፡ እንደምታስታውሱት መከላከያ እየሸሸ በነበረበት ሰዓት ነው እኛ ገብተን፣ ጠላትን እየጠረግን የተከተልነው፡፡ የጠላትን ቅስም የሰበረው ትልቁ የደብረ ታቦሩ ውጊያ የእኛ የአመራር ውጤት ነው፡፡ የእኔ የአመራር ውጤት አለበት፡፡ ከወልቃይት ኃይል ቀይሬ እያመጣሁ፣ በዐዲስ ኃይል እያጠቃን ነው የተዋጋ ነው፡፡ በጋሸና ግንባርም ትልቁን ሚና የተጫወተው ልዩ ኃይሉ ነው፡፡ ሰቆጣ ላይም ‹ሕወሓትን ማጥቃት አይቻልም› በሚባልበት ጊዜ፣ በራሴ ተነሳሽነት ማጥቃት እንደሚቻል አሳይቻለሁ፡፡ ላሊበላም እንደዚያው፡፡ በቦረናም ወሳኙን የጠላት ኃይል ገተነዋል፡፡ አጠቃላይ የጠላት ግስጋሴ የተቀለበሰበት የጣርማ-በሩ ውጊያም በልዩ ኃይሉ የተሠራ ጀብዱ ነው፤› ብዬ ዘረዘርኩ፡፡

፨ አሁን ያለው የዐማራ ልዩ ኃይል እናንተ ከተመለሳችሁ በኋላ የተፈጠረ ነው እንዴ?

ከላይ እንደጠቀስኩት እኛ ስንመጣ፣ ወያኔ ከመከላከያ በገፈፈው ከባድ መሳሪያ፣ ክላሽ ብቻ የታጠቀውን የዐማራ ልዩ ኃይል በእጅጉ አዳክሞት ነበር፡፡ ቁጥሩም በጦርነቱ ከመናመኑ ባሻገር፤ ‹ተበደልኩ› ብሎ ለቆ የሚሄደው በጣም ብዙ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ነው፣ የተበተነውን አሳባስበን፣ ዐዳዲስ ምልምሎችን ጨምረን ያደራጀነው፡፡ የማሰልጠኑና የማዋጋቱ ሥራ የእኔና አብረውኝ የነበሩት ጓዶች ነው፡፡
በአጭሩ፣ ዐሥር ቦታ የጥይት ምት እያለብኝ፣ በዚያ ክረምት ገብቼ በዱላ እያነከስኩ ያዋጋሁት ለዝና ወይም ለሌላ አይደለም፡፡ ‹ዐማራን እንበቀላለን› በሚል ፎክሮ የመጣውን ኃይል፣ ለመደምሰስ ነው፡፡ በከፊልም ቢሆን ተሳክቶልኛል ያልኩት ይህንን ነው፡፡

፨ አሁን ቁጥሩ ምን ያህል ደርሷል?

በፊት ከነበረበት ዐሥር እጥፍ አሳድገነዋል፡፡

፨ የአማካሪነት ሹመቱን ተቀበሉት?

አልተቀበልኩትም፡፡ እነሱ የፈለጉትን መሾም እንደሚችሉም ሆነ ይሄኛውን ሥራ እንደማልፈልገው ነግሬያቸዋለሁ፡፡

፨ ከኃላፊነትዎ የተነሱት ለምን ይመስልዎታል?

ዋንኛው ምክንያት፣ የዐማራ ልዩ ኃይል እንዲደራጅ የማይፈልጉ ጄነራል መኮንኖች መከላከያ ውስጥ ስላሉ ነው፡፡ ገና ከመጀመሪያው ስናደራጅ ‹ይፍረስ› ሲሉ የነበሩ፣ አንዳንዶቹ የእኛው ድርጅት አባል የሆኑ የሕወሓት አለቅላቂዎች አሉ፡፡ እኔ ‹እገሌ፣ እገሌ› ብዬ የግለሰብ ስም አላነሳም፡፡ ነገር ግን፣ እነዚያ የሕወሓት ኮርቻ ተሸካሚዎች፣ በ1998 ዓ.ም ከሃያ ሺሕ በላይ ዐማራ ከመከላከያ ሲባረር መረጃ አቀባይ ነበሩ፡፡ አንዳንዶቹ በመጨረሻ ‹ዐማራውን አባራችሁ ደግፋችሁናል፤ ከዚህ በኋላ ግን አታስፈልጉም› ተብለው የተባረሩ ናቸው፡፡ ከኃላፊነቴ እንድነሳና ልዩ ኃይሉ እንዲዳከም በማድረጉ ረገድ የእነዚህኞቹ እጅ አለበት፡፡
ገና ውጊያ ላይ እያለን እኮ ነው፣ የልዩ ኃይሉን አዛዦች በተናጠል እያነጋገሩ ‹ለቃችሁ ኑ› ከማለት አልፈው፤ ‹በግድ ወደ መከላከያ ካልወሰድናቸው› ብለው ሲያስቸግሩኝ የነበሩት፡፡ ዓላማቸው መከላከያን ማጠናከር ሳይሆን፤ በሚፈጠረው ክፍተት ልዩ ኃይሉን መበተን ነው፡፡ ‹ይሄ ኃይል የተደራጀው የክልሉ ሕዝብ ስጋት ስላለበት ነው፤ መከላከያ የጠላትን ጥቃት ሊያስቆም ስላልቻለ ነው፣ ከመቀሌ እስከ ደሴ የተያዘው፤› ብላቸውም መስማት አልፈለጉም፡፡ ጭራሽ ‹የልዩ ኃይሉ አዛዦች ወደ መከላከያ እንዳይገቡ የሚያደርገው ተፈራ ነው›፣ ‹ልዩ ኃይሉን አለቅጥ እየገነባ ያለው ተፈራ ነው›፣ ‹ተፈራ ማሰልጠን የሚፈልገው በኮማንዶ ደረጃ ነው!› እያሉ መውቀስ ጀመሩ፡፡ በኮማንዶ ደረጃ ልናሰለጥን የነበረውንም ‹አትችሉም!› በለው ከለከሉን፡፡

መከላከያ ቢጠናከርና ክፍተቱ ቢሞላ፣ የእኔ እዛ መቀመጥ ፋይዳ የለውም፡፡ እስካልተጠናከረ ድረስ ግን፣ ሕዝባችንን የሚታደገውን ልዩ ኃይል ለማዳከምና ለመበተን መሞከር የሕወሓትን ያህል የከፋ ወንጀል ነው፡፡

፨ ኮማንዶ እንዳታሰለጥኑ ማነው የከለከለው?

ሦስት ብርጌዶችን በኮማንዶ ደረጃ ልናሰለጥን ዝግጅታችንን ስንጨርስ፣ መከላከያ ውስጥ ያሉም፣ የፖለቲካ አመራሩም ተንጫጩብን፡፡ የእኔ እቅድ ብዙ ኮማንዶዎችና አየር ወለዶች ስላሉን፣ ልዩ ኃይሉን እነሱ አሰልጥነውት ክልሉንም ሆነ ኢትዮጵያን ከጠላት የሚከላከል ጥሩ ተዋጊ ለመፍጠር ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ‹ተፈራ እስካለ ድረስ ልዩ ኃይሉ አላስፈላጊ ወታደራዊ ቁመና ነው የሚይዘው፣ አስወጡት!› የሚል የበላይ ፍላጎት መጣ፤ የፌደራል መንግሥቱን አመራሮች ጨምሮ፡፡ እኛ በቀና መንገድ፣ ለአገራችንና ሕዝባችን ብለን፣ አብረናቸው እየተዋጋን በስጋት ያዩናል፡፡ መከላከያ በብዙ ውጊያዎች ላይ ተገቢውን የተኩስ ድጋፍ ሳይሰጠን ቀርቷል፡፡ ‹ኃይል ላኩልን› ስንል፣ ‹የለም ነበር› የሚሉን፡፡

የሆነው ሆኖ፣ በበኩሌ ሕዝብና አገር ሰላም እንዲሆን የምችለውን አስተዋጽኦ ከማድረግ በቀር፤ ሌላ ፍላጎት የለኝም፡፡ አስገድዶ ያስገባኝም ህሊናዬ ብቻ ነው፡፡ መሥራት እፈልጋለሁ፤ ሠርቼም አሳይቻለሁ፡፡ ሲያልፈሰፍሱት የነበረው ልዩ ኃይል ነው፣ ዛሬ ተራራ የሆነው፡፡ ሁሉም ቦታ ሄዳችሁ ተመልከቱ፣ የልዩ ኃይሉ የመምታት ብቃት ከዶ/ር ዐቢይ እና አቶ ደመቀ ጀምሮ የመሰከሩት ሃቅ ነው፡፡ በተለይ ጣርማ-በር ላይ ‹ፈጥናችሁ ሁለት ብርጌድ ላኩልን› ብለው፣ ፈጥኖ የሄደው ልዩ ኃይላችን በታሪክ የሚዘከር ጀብዱ ፈጽሞ ጠላትን እንዴት እንደጠራረገው ያውቃሉ፡፡ ዛሬ ቤንሻንጉል ሰላም የሰፈነው እኛ “ጋፋት ብርጌድ”ን ልከን በሠራነው ሥራ ነው፡፡ ግድቡንም እየጠበቀ ያለው ይህ ብርጌድ ነው፡፡
አሁን ደግሞ፣ ልዩ ኃይሉን ማዳከም ተፈልጓል፡፡

እውነቴን ነው የምናገረው የዐማራ ሕዝብ ልብ ብለህ ስማ፡- ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ያፈርሱታል፡፡ ወይም እጅግ በጣም ያዳክሙታል፡፡ የእኔን አዛዥነት ያልወደዱትም ‹እንዳይፈርስ ምሶሶ የሆነው ተፈራ ነው› በሚል ነው፡፡ የክልሉ አመራር፣ ራሱን ችሎ የሚቆም ስላልሆነ፣ የባሰ ያስጠቃል እንጂ፤ እውነታውን አብሮ እየሠራ እያየ ‹ትክክል አይደለም› ብሎ አይጋፈጥም፡፡
የሚገርመው፣ ወደዚህ ዐይነት ውሳኔ የገቡት፣ ‹የዐማራ ልዩ ኃይል ለፈጸመው ጀብዱ የሚሸለሙትን ለይታችሁ› አምጡ ብለውን፣ አቅርበን የሽልማቱን ቀን እየጠበቅን እያለ ነው፡፡ አሁን፣ በልዩ ኃይሉ ውስጥ ሚና ያልነበራቸውን ሰዎች እየመደቡ ነው፡፡

፨ ለሽልማቱ?

ሽልማቱ ዞሮ-ዞሮ ቦታው ስላለ፣ በዛ ደረጃ የሚሰጥ ነው፡፡ በትክክል ከሄደ እናየዋለን፡፡ ነገሩ በቀናነት ላለመሆኑ ግን፣ አንድ ማሳያ ነው፡፡ ወደፊት ታሪክ፣ ‹አሸናፊ ብለህ የሸለምከው ሠራዊት አዛዥ ማነው?› ብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡
እዚህ ጋ፣ ሌላው መግለጽ የምፈልገው፣ የወልቃይት ጉዳይን ነው፡፡ እኛ ወልቃይት ላይ በቂ ኃይል አስገብተናል፡፡ ዋና ፍላጎታችን ሕወሓት ድንገት ለማጥቃት ቢሞከር፣ ከመከላከያው ጋር አብሮ እንዲመክት ነው፡፡ ነገር ግን፣ ተዟዙረን አስሰን የሳሳ አካባቢ አግኝተን ኃይል ስንመድብ፣ የመከላከያ ጄኔራሎች ‹እኛ ሳናውቀው እንዴት ታስገባላችሁ?› ብለው ይጮኸሉ፡፡ ‹እያንዳንዱን ሥራችንን እኮ ለእናንተ ማሳወቅ የለብንም፡፡ እናንተ ሠራዊታችሁን ማብቃት ነው ያለባችሁ እንጂ፤ የዐማራ ልዩ ኃይል፣ በዐማራ መሬት ላይ የሚሰጠውን ስምሪት፣ ለምን በዚህ ዓይን ታዩታላችሁ?› ስላቸው ያኮርፋሉ፡፡ ለጊዜው ምክንያታቸው ባይገባኝም፣ ወልቃይት ላይ ጠንካራ ጥበቃ መመደባችንን እንደማይፈልጉት ግን ተረድቻለሁ፡፡

ሌላው ነገር፣ ልዩ ኃይሉን አላስፈላጊ ተልዕኮ ሰጥተው እንዲበሳጭና እንዲማረር ለማድረግ ሲሞክሩ፣ እኔ አልስማማም፡፡ ‹መፈፀም ያለብንን ብቻ ነው የምንፈፅመው› ብዬ አቋም እይዛለሁ፡፡

፨“አላስፈላጊ” ምን ማለት ነው?

ምንም ስጋት የሌለበትን አንዱን በረሃ ይመርጡና ‹እዛ አስገቡት› ይሉናል፡፡ እቅዳቸው በውሃ ጥም ተማርሮ ወደ ቤቱ እንዲበተን በመሆኑ፣ እኔ አልፈቅድም፡፡ ግፊታቸው ሲበዛ፣ ‹እናንተ ሥራችሁን በቀላል መንገድ ሥሩ፤ ወይም እዚህ ዐማራ ድንበር ላይ ከምታስቸግሩን፣ ራሳችሁን ችላችሁ ተዋግታችሁ ትግራይ ግቡና ግዳጃችሁን ተወጡ፤› ብዬ እመልሳለሁ፡፡
እንግዲህ እነዚህን ሁኔታዎች ነው ጨማምረው፣ ከላይ ያሉትን መሪዎች የሞሏቸው፡፡

በአጠቃላይ ግን፣ በዐማራ ልዩ ኃይል ላይ ብዙ ችግሮች እየፈጠሩ ነው፡፡ እኔም ‹እምቢይ!› ብዬ እንጂ፤ በነፃነት ሊያሠሩኝ አልቻሉም ነበር፡፡ ይህንን ሁኔታ፣ ሕዝቡ ሊያወቀው ይገባል፡፡ እያንዳንዱን ተንኮል ተቋቁመን ነው፣ እዚህ የደረስነው፡፡ ልዩ ኃይሉን ለመበተን ሲሞክሩ፣ ስንዘጋባቸው፤ እኛን ለማደናቀፍ ሲሞክሩ፣ ስንዘጋባቸው… ነው የቆየነው፡፡
ሌላው ስጋቴ፣ ወደፊት ወል

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ardi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share