Hagere Infotainment

Hagere Infotainment FELEG ETHIOPIA ይህ የቁምነገርና የመረጃ መለዋወጫ መማማሪያ ገጽ ነው ። ማንኛውንም አስተያየት ወይም ሀሳብ በጨዋነት መግለጽ የሀገራችን ሰው ባህል ነውና ካልተገባ ንግግር እንቆጠብ፣

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ እና የ1953 ዓ.ም መፈንቅለ መንግስት ታሪክ"የመፈንቀለ መንግስት ሙከራው በተካሄደ በአራተኛው ቀን መሰለኝ ጃንሆይ ጉብኝታቸውን አቋርጠው አዲስ አበባ ገቡ...
12/15/2024

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ እና የ1953 ዓ.ም መፈንቅለ መንግስት ታሪክ

"የመፈንቀለ መንግስት ሙከራው በተካሄደ በአራተኛው ቀን መሰለኝ ጃንሆይ ጉብኝታቸውን አቋርጠው አዲስ አበባ ገቡ። አሁን አገር ሰላም ነው አልሁና እኖርበት ወይም በጭንቅ ሆኜ ሁኔታውን እከታተልበት ከነበረው ፊት በር እየተባለ ከሚጠራው ሰፈር ወጣሁና አራት ኪሎ አቶ ሻወል ቤት ገባሁ። ለካ ጦር ሰራዊት ይከታተለኛል። ድንገት ጀርባዬን በሰደፍ ደቅኖ ቀጥል አለኝ።

ከዛ ሌሎችም በጥፊ በርግጫ እያዳፋ እንዲያውም የሌለኝን መአረግ ሁሉ እየስጡኝ ''የኛ መቶ አለቃ! የሾሙህ የሸለሙህ ጃንሆይ መጥተዋል ምን ይዋጥህ? አንተ ከሀዲ! ለሰንደቅ አላማህና ለንጉስህ የገባህውን ቃል በልተህ መንግስት ልትገለብጥ ሞከርህ አይደል...''አሳሬን ያሳዩኝ ጀመር። መልስ ለመስጠትና ''መቶ አለቃ ቀርቶ ወታደር አይደለሁም ሲቪል ነኝ ''ብዬ ለመናገር እንኳ ፋታ አልሰጡኝም ቁም ስቅሌን አሳዩኝ።

በዚህ አይነት ሁኔታ መከራዬን እያሳዩ ወስደው አሁን ሸራተን አዲስ ወደ ተሰራበት አካባቢ ከነበረ ሽንት ቤት ውስጥ አስገቡኝ። እውነት ለመናገር ያን ሁሉ መከራ ከማየት ያን እለት ብሞት እመርጥ ነበር። አንዴ በርግጫ ሊያውም በወታደር ጫማ ፣እንደገና በጥፊ ፣እንደገና በቆመጥ... እረ ስንቱ ይነገራል? እና እንዲህ እንደ አውድማ ላይ ገብስ ሲወቁኝ ውለው ሽንት ቤት ከዘጉብኝ ከተወሰነ ሰአት በኃላ ''አራተኛ ክፍለጦር '' ወሰዱኝ።

እዚያ ስደርስ የያዙኝ ወታደሮች በኩርንችት ጫማ እስከሚበቃቸው ከወቀሩኝ በሁዋላ ለዘቦች አስረከቡኝ። ሰውን እንደ እባብ መቀጥቀጥ በህግ የተፈቀደ እስኪ መስል ድረስ የአራተኛ ክፍለጦር ወታደሮችም መፈጠሬን እስክጠላ ገረፋኝ ። እረ ''ገረፋኝ'' የሚለው ቃል አይገልጸውም።

"ሕሊና ያለው ሰው በመሰሉ ላይ ይፈጽመዋል ተብሎ የማይታሰበውን የጭካኔ እርምጃ ወሰዱብኝ ።"

ጋሽ ጥላሁንን ያስጠረጠረው እና ለእስር ያበቃው ጉዳይ መፈንቀል መንግስቱ ሊደረግ ቀናት ሲቀረው “ኡኡታ አያስከፋም ሲለዩ ተዋዶ” በሚል ርዕስ ስር ለህዝብ ባቀረበው ተወዳጅ ሙዚቃ ተጠርጥሮ ነበር።

ኡኡታ አያስከፋም ሲለዩ ተዋዶ
ከዚህ የበለጠ ከየት ይምጣል መርዶ....

እያለ በመጫወቱ እና ከአቶ ንዋይ ልጆች ጋር በነበረው ወዳጅነት በአሸባሪነት ተጥርጥሮ ለብዙ ሳምንታት መታሰሩ የዘመኑ ሰበር ዜና እንደነበር በታሪክ ተጽፎአል።..ክቡር ዶ/ር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ እንደተናገረው። በምስሉ ላይ ጥላሁን ገሠሠ በወታደሮች በቁጥጥር ስር ሲውል ነው።(ታሪክን ወደኋላ)

ዘመን አይሽሬ ሙዚቃዎችን ያዳምጡ https://youtube.com/?sub_confirmation=1

ቻትጂፒቲን የፈጠረውን ተቋም ያጋለጠው የቀድሞ የድርጅቱ ሠራተኛ ሞቶ ተገኘኦፕንኤአይን ያጋለጠው የቀድሞ የድርጅቱ ሠራተኛ ሳን ፍራንሲስኮ የሚገኝ መኖሪያ ውስጥ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ። ...
12/15/2024

ቻትጂፒቲን የፈጠረውን ተቋም ያጋለጠው የቀድሞ የድርጅቱ ሠራተኛ ሞቶ ተገኘ

ኦፕንኤአይን ያጋለጠው የቀድሞ የድርጅቱ ሠራተኛ ሳን ፍራንሲስኮ የሚገኝ መኖሪያ ውስጥ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ አስታወቀ። የ26 ዓመቱ ሱቺር ባላጂ አስክሬን የተገኘው ፖሊስ ደኅንነቱን እንዲያጣራ የስልክ ጥቆማ ከደረሰው በኋላ ነበር።

የሳን ፍራንሲስኮ ሐኪም ሱቺር ራሱን እንዳጠፋ ገልጿል። ፖሊስም ይህንን የሚጻረር ማስረጃ አለማግኘቱን ገልጿል።
ሱቺር ባለፉት ጥቂት ወራት የኦፕንኤአይን አሠራር ሲቃወም ነበር። ኦፕንኤአይ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተቋም ሲሆን በዋናነትም ቻትጂፒቲን በመፍጠሩ ይታወቃል።

ኒው ዮርክ ታይምስ ባለፈው ጥቅምት ባተመው ቃለ ምልልስ ላይ የቀድሞ የኦፕንኤአይ ሠራተኛው ሱቺር ድርጅቱ ቻትጂፒቲን ሲሠራ የአሜሪካን የቅጂ መብት መጣሱን ተናግሯል።

ሱቺር ለአራት ዓመት በድርጅቱ ውስጥ በተመራማሪነት ሠርቷል። "የቅጂ መብትን በመጣስ ነው ቻትጂፒቲ የተሠራው። ሕግ የጣሰ ነው። እንደ ቻትጂፒቲ ያሉ ቴክኖሎጂዎች በይነ መረብ ላይ ጉዳት ያደርሳሉ" ሲልም ተናግሯል።

ኦፕንኤአይ በበኩሉ የሚሠራቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች "ለሕዝብ ይፋ የሆነ መረጃ" ላይ የተመረኮዙ ናቸው ብሏል። ሱቺር ኦፕንኤአይን የለ ቀቀው ያለፈው ነሐሴ መሆኑን ለኒው ዮርክ ታይምስ ገልጿል። የራሱን ፕሮጀክቶች እየሠራ መሆኑንም አስታውቋል።

በካሊፎርንያ ያደገው ሱቺር በዩኒቨርስቲ ኦፍ ካሊፎርንያ፣ በርክሊ ተምሯል።የኦፕንኤአይ ቃል አቀባይ "ይህንን ዜና በመስማታችን ልባችን ተሰብሯል። ለሱቺር ወዳጆች በዚህ ከባድ ጊዜ መጽናናትን እንመኛለን" ማለታቸውን ሲኤንቢሲ ዘግቧል።

የአሜሪካ እና ካናዳ አሳታሚዎች ኦፕንኤአይ መተግበሪያዎቹን ለማሠልጠን በሕገ ወጥ መንገድ ዘገባዎቻችንን ወስዷል ሲሉ ከሰዋል።በዚህ ክስ ውስጥ ኒው ዮርክ ታይምስና የዝነኛው ደራሲ ጆን ግሪሻም አሳታሚዎች ይገኙበታል። ኦፕንኤአይ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ "ዓለም አቀፍ የቅጂ መብትብ በማክበርና ለፈጠራ ባለቤቶች ፍትሐዊ መሆነ መንገድ ነው የምንሠራው" ብሏል።(ቢቢሲ)

ተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ላይ t.me/felegethiopia

መግለጫየበረራ ቁጥሩ ET 612 የሆነ የኢትዮጽያ አየር መንገድ አውሮፕላን ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ በሚያደርገው በረራ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ የቴክኒክ ች...
12/15/2024

መግለጫ

የበረራ ቁጥሩ ET 612 የሆነ የኢትዮጽያ አየር መንገድ አውሮፕላን ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም. ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ በሚያደርገው በረራ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም አርፏል።

ለጥንቃቄ ሲባል መንገዶች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ ተደርጓል።

ሁልጊዜም ቢሆን የኢትዮጽያ አየር መንገድ ለክቡራን መንገደኞቹ ደህንነት ቅድሚያ ይሰጣል። በዚህ አጋጣሚ ውድ መንገደኞች ለደረሰባቸው መጉላላት አየር መንገዱ ይቅርታ እየጠየቀ የቴክኒክ ችግሩ በመጣራት ላይ መሆኑን ይገልፃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

▣ t.me/felegethiopia

 #ቲክቶክ አንድ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ሲታገድ ምን ይከሰታል?ቲክቶክ ከአራት ዓመታት በፊት በሕንድ እስኪታገድ ድረስ በጣም ተወዳጅ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መተግበሪያ ነበር። አሁን ደ...
12/12/2024

#ቲክቶክ አንድ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያ ሲታገድ ምን ይከሰታል?

ቲክቶክ ከአራት ዓመታት በፊት በሕንድ እስኪታገድ ድረስ በጣም ተወዳጅ የማኅበራዊ ሚዲያ ትስስር መተግበሪያ ነበር። አሁን ደግሞ አሜሪካ ቲክቶክን ለማገድ ዳር ዳር እያለች ነው።

ከአራት ዓመት በፊት ሕንድ የቲክቶክ ትልቁ ገበያ ነበረች። በዚህም የ200 ሚሊዮን ተጠቃሚዎቹን ፍላጎት ለመሙላት፣ የይዘት እና ተፅእኖ ፈጣሪዎች ሕይወትን ለመቀየር ብዙ ዕድሎችን ፈጥሯል። በርካታ ባለ ተሰጥኦዎች እንዲሁም መደበኛው መገናኛ ብዙኃን የራቃቸው ማኅበረሰቦች መድረክ ሆኖ አገልግሏል። ይህ ሁሉ ግን በሕንድ እና በቻይና መካከል የድንበር ይገባኛል ውጥረት እስኪከሰት ድረስ ብቻ ነበር የዘለቀው።

የሁለቱ አገራት ውጥረት ሲካረር ቲክቶክ አገር አማን ብሎ በሕንድ ገበያ ውስጥ ይገማሸር እንደነበር ተጠቃሚዎቹ ያስታውሳሉ። የድንበር ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ግን፣ ከሰኔ 22/2012 ዓ.ም. ጀምሮ የሕንድ መንግሥት ቲክቶክን በግዛቴ እንዳላይ አለ።

በእርግጥ ሕንዳውያን ቲክቶከሮች የሠሯቸው ቪዲዮዎች አሁንም በመተግበሪያው ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ዛሬን ሳይሆን ትናንትን ለመዘከር የተቀመጡ ናቸው። የአሁን ሳይሆን የነበር ማስታወሻዎች ሆነዋል። ይህ በአሜሪካ ሊሆን ስላለው እንደ መጥፎ ምልክት ሆኖ ታይቷል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ላይ ቲክቶክን ከአሜሪካ ምድር ማገድ የሚያስችል ረቂቅ ሕግ ፈርመዋል። ይህ ሕግ የቲክቶክ ባለቤት የሆነው ባይትዳንስ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የመተግበሪያውን ድርሻ ከተጨማሪ የሦስት ወር የእፎይታ ጊዜ ጋር እንዲሸጥ ወይም በአገሪቱ ውስጥ ሊታገድ እንደሚችል ያዛል።

ባይትዳንስ ግን ማኅበራዊ ሚዲያውን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው አሳውቋል፤ ሕጉ ይሻርልኝ ብሎ ወደ ፍርድ ቤት ከሄደ በኋላም ኅዳር 27/ 2017 ዓ.ም. ይግባኙ ውድቅ ተደርጎበታል። ከዚህ በኋላም ወደ ሰበር ሰሚ ፍርድ ቤት እንደሚያመራ ቢጠበቅም ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት የሚቀለበስ ውሳኔ ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።

ምንም እንኳን እያንዣበበ ያለው የፍርድ ቤት ፍልሚያ በአሁኑ ጊዜ የቲክቶክን ዕጣ ፈንታ አጠራጣሪ ቢያደርገውም፣ ትልቅ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያን ማገድ በአሜሪካ የቴክኖሎጂ ታሪክ ውስጥ ታይቶ አይታወቅም። ነገር ግን የሕንድ ልምድ የሚያሳየው አንድ ትልቅ አገር ቲክቶክን ከዜጎቿ ስልክ ላይ ጠራርጋ ልታስወግድ እንደምትችል ነው።

ይህን ዓይነቱን እርምጃ የወሰደችው ሕንድ ብቻ አይደለችም። በ2016 ዓ.ም. ኔፓል ቲክቶክን ለማገድ ስትወስን፣ ፓኪስታን ደግሞ ከ2020 ጀምሮ በርካታ ጊዜያዊ ዕገዳዎችን በመተግበሪያው ላይ ጥላለች። በእርግጥ የሕንድ የቲክቶክ ዕገዳ ታሪክ ተጠቃሚዎች በፍጥነት አዲስ ነገርን መላመድ እንደሚችሉ ቢያሳይም፣ ነገር ግን ቲክቶክ ግብዓተ መሬቱ ሲፈጸም አብዛኛው ባህሉ አብሮ እንደሚሞት ቋሚ ተጠቃሚዎቹ ህያው ምስክር ሆነዋል።

በቦምቤይ የምትኖረው የፊልም ሃያሲዋ ሱሳሪታ ቲያጊ ቲክቶክ ሲታገድ አካውንቷ 11,000 ተከታዮች ነበሩት። "ቲክቶክ በጣም ትልቅ ነበር። ሰዎች በመላ አገሪቱ ይጨፍሩ፣ አጫጭር ድራማዎችን ይሠሩ፣ በኮረብታ ላይ በምትገኘው ትንሽ ቤታቸው ሕይወትን እንዴት እንደሚገፉ ያጋሩ ነበር" ትላለች ቲያጊ። "ብዙ ሰዎች ሁሌም የተነፈጉትን ይህንን ዕይታ ነበር በቲክቶክ ያገኙት።"

መተግበሪያው ልዩ ክስተት ነበር፤ ምክንያቱም ለገጠሪቷ ሕንድ ተጠቃሚዎች በሌላ መተግበሪያዎች የማይገኙ ከፍተኛ ተመልካቾችን የማግኘት፣ እንዲሁም በአንድ ጀንበር ታዋቂ የመሆን ከፍተኛ ዕድሎችን ሰጥቷል።

ተጨማሪ ቴሌግራም ላይ ▻https://t.me/felegethiopia/24686

ዓለምን የለወጡ እጅግ የላቁ ፈጠራዎች !የኤሌክትሪክሲቲን ሞገድ ፈጥሮ፤ በየቤቱ፣ በየፋብሪካውና በየኢንዱስትሪው ማከፋፈል ዓለምን የለወጠውን ኃይል አንድም የኤሌክትሪክ መሳሪያ አለወጠም፡፡ በእ...
12/11/2024

ዓለምን የለወጡ እጅግ የላቁ ፈጠራዎች !

የኤሌክትሪክሲቲን ሞገድ ፈጥሮ፤ በየቤቱ፣ በየፋብሪካውና በየኢንዱስትሪው ማከፋፈል ዓለምን የለወጠውን ኃይል አንድም የኤሌክትሪክ መሳሪያ አለወጠም፡፡

በእርግጥ ቶማስ ኤድሰን ሲሞቅ እንደፍም በሚግልና በሚያብረቀርቅ አምፑሉ በጣም ይታወቃል፡፡ ነገር ግን እሱ ያወረሰን እጅግ ጠቃሚ ነገር ምናልባትም የኤሌክትሪክ ኃይል ኢንዱስትሪው ሳይሆን አይቀርም፡፡

ኤድሰን በአሜሪካ፣ የመጀመሪያ የሆነውን ትልቅ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በኒውዮርክ የመሠረተው በ1882 ዓ.ም ነበር፡፡ ኤሌክትሪሲቲን ለመፍጠር ጥናት የተጀመረው በ1600 መጀመሪያ አካባቢ ነበር፡፡ በ18ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ አሜሪካዊው ባለሥልጣንና ሳይንቲስት ቤንጃሚን ፍራንክሊን የተከበረውን የኤሌክትሪክ ምርምር አካሄደ፡፡

በዚያን ጊዜ የነበረው የመብራት ኃይል የመጀመሪያዎቹና ያልተሻሻሉት ጥንታዊ ባትሪዎች በተወሰነ ደረጃ የሚያመርቱት ኃይል ብቻ ነበር፡፡ ለምሳሌ በ1840ዎቹ ዓመታት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ መድረክ ብቅ ያለው ቴሌግራፍ በባትሪ ኃይል የሚሠራ ነበር፡፡

ኤሌክትሪሲቲ በከፍተኛ መጠን ለሰው አገልግሎት እንዲውል ያደረገው የዲናሞ መፈጠር ሲሆን ዲናሞ፣ በመሳሪያ እንቅስቃሴ የተፈጠረን መካኒካል ኃይል ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚቀይር መሳሪያ ነው፡፡ ዲናሞ፣ እንግሊዛዊው ሳይንቲስት ሚካኤል ፋራዳይ በ1831 ዓ.ም ባፈለቀው ግኝት ላይ ተመሥርቶ የተሠራ መሳሪያ ነው፡፡ የፋራዳይ ግኝት የማግኔት ሞገድ ባለበት ስፍራ ሽቦ ቢጠመጠም የኤሌክትሪክ ሞገድ ሽቦው ላይ ይፈጠራል የሚል ነው፡፡

ይህም በእንፋሎት እየተሽከረከረ ኤሌክትሪክ የሚፈጥረውን የብረት ምሰሶ በቀጥታ በዚህ ዘዴ መተካት አስቻለ፡፡ ኤሌክትሪኩ አንዴ ከተፈጠረ በኋላ የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ ኃይሉን በየቤቱ፣ በየፋብሪካውና በየቢሮው የሚያደርስ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦና የትራንስፎርመር ሲስተም ብቻ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ማብሪያና ማጥፊያ በመጫን ብቻ ርካሽና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘት በአብዛኛው የዓለም ዙሪያ የአኗኗር ደረጃን ከፍ አደረገ፡፡

በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ ለመገንዘብ በተለያየ ምክንያት መብራት ሲጠፋ፣ ምን እንደሚፈጠር እስቲ አስቡት፡፡ ክብሪት ለማግኘት በጨለማ ይደናበራሉ፤ ኮምፒዩተርን ጨምሮ አብዛኛው የቤት ዕቃ አይሠሩም፤ ያለ መብራት ምንም ጥቅም በማይሰጠው ማቀዝቀዣ ውስጥ የተቀመጠ ምግብ ይበላሻል፡፡ ሕይወት ለጊዜውም ቢሆን ቀጥ ትልና መብራት ሲመጣ ዑደቷን ትቀጥላለች፡፡

ቴሌግራፍ፡-

በአብዛኛው የሰው ልጅ ታሪክ በረዥም ርቀት መልዕክት (ኢንፎርሜሽን) መለዋወጫ ዘዴ፣በዋነኛነት፣ በሰው በመላላክ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ተወዳጅ ከሆኑት የአትሌቲክስ ስፖርቶች አንዱ ማራቶን በጥንታዊት ግሪክ ፊዲፕዲስ የተባለ ወታደር 42ኪ.ሜ ከ195 ሜ ርቀት ሮጦ፣ ታላቁን ጣፋጭ ድል ያበሰረበትን ድርጊት ለማሰብ ነው፡፡ መልዕክተኛው የድሉን ዜና ከተናገረ በኋላ ተዝለፍልፎ ወዲያውኑ እንደሞተ አፈ-ታሪክ ይነግረናል፡፡

መጀመሪያ ፈረሶች ቀጥሎም የእንፋሎት ሞተር መልዕክቱ በጉዞ የሚያጠፋውን ጊዜ ቢያሳጥሩትም ያደረጉት መሻሻል መጠነኛ ነው፡፡ ከዚያም በመቀጠል ቴሌግራፍ መጣ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዓለም ሙሉ በሙሉ ተለወጠች፡፡

በቴሌግራፍ መልዕክት የማስተላለፊያ ዘዴ ቀላል ነው፡፡ መልዕክቱ በታይፕ ሲጻፍ የሚፈጠረው የኤሌክትሪክ ሞገድ ንዝረት በሽቦ አማካይነት ይላካል፡፡ ንዝረቱ መቀበያው ጋ ሲደርስ ማግኔት ይፈጥርና በመቀበያው ላይ የተጠቀለለውን ወረቀት በመርፌ ይበሳሳል፡፡

የተበሳሳውንም ምሥጢራዊ ወረቀት በሚያነብ መሳሪያ ውስጥ እንዲያልፍ ሲደረግ የተላከውን መልዕክት ያትማል፡፡ በዚህ ዓይነት፣ ቴሌግራፍ በጣም በተራራቁ ቦታዎች መካከል መልዕክት በቀላሉ ማስተላለፍ አስቻለ፡፡

በ1830ዎቹና በ1940ዎቹ ዓመታት በርካታ ሳይንቲስቶችና ዕቃ አዳሾች የቴሌግራፍ ናሙናዎች ሠርተው ነበር። ይሁን እንጂ ሳሙኤል ኤፍ.ቢ ሞርስ የተባለ አሜሪካዊ ሠዓሊና ቀራፂ፣ በ1843 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲ.ሲ እና በባልቲሞር-ሜሪላንድ መካከል የቴሌግራፍ መስመር ለመዘርጋት የአሜሪካ መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግለት እስካሳመነበት ጊዜ ድረስ፣ ቴክኖሎጂው እውን አልሆነም፡፡ ቀሪውን ዝርዝር በሊንኩ በኩል ቴሌግራም ላይ ያንብቡ ▻https://t.me/felegethiopia/24678

Hagere Infotainment

የምከፍላችሁ ብር የለኝም በማለቱ በጫኝ አዉራጆች የተደበደበው ባለ ንብረት ህይወቱ አለፈ!በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል  በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ማጫ ቀበሌ ተሽከርካሪ ላይ የጫነዉን ...
12/11/2024

የምከፍላችሁ ብር የለኝም በማለቱ በጫኝ አዉራጆች የተደበደበው ባለ ንብረት ህይወቱ አለፈ!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ማጫ ቀበሌ ተሽከርካሪ ላይ የጫነዉን ዕቃ አታወርዱም ያለዉን የግል ተበዳይ ደብድበዉ የገደሉ ሶስት ጫኝ አዉራጆች በእስራት መቀጣታቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ተከሳሾቹ በቁጥር ሦስት ሲሆኑ አማኑኤል ማናለ ፣አስራት አክሊሉ እና ታድዮስ ተስፋዮ የተባሉ ሲሆን የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንባቸዉ የቻለዉ የተጫነ ዕቃን ካላወረድን በሚል የግል ተበዳይን ደብድበዉ በመግደላቸዉና ጥፋተኝነታቸዉ በማስረጃ መረጋገጡ ተገልጿል ።

ተከሳሾቹ ሰዉ ለመግደል አስበዉ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ማጫ ቀበሌ ከቀኑ 8:00 ሰዓት በወረዳዉ ዳጊ ማጫ ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ አርብ ቀን በሚቆም ገበያ የግል ተበዳይ ባጃጅ ገብስ በኩንታል ጭኖ በማምጣት ለማዉረድ ሲል እኛ እያለን አታወርድም በሚል ነው ወንጀሉን የፈፀሙት።

ሦስቱም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በተደረገዉ ምርመራ ሁለተኛ ተከሳሽ የተጫነዉን ገብስ አወርዳለሁ ሲል የግል ተበዳይ የምከፍልህ ገንዘብ የለኝም አታወርድም በሚልበት ወቅት የግል ተበዳይን አንገቱን አንቆ ይዞ ደረቱ ላይ በቦክስ ሁለት ጊዜ ሲመታዉ ሶስተኛ ተከሳሽ ሁለት እጆቹን ይዞ ሽንጡ ላይ በእግሩ ደጋግሞ በመርገጥ አንደኛ ተከሳሽ ሆዱ ላይ በእግሩ በመርገጥ ከባድ ጉዳት አድርሰዋል::

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደገለፁት ተጎጂዉ ግለሰብ ማጫ ጤና ጣቢያ ቢወሰድም የደረሰበት ምት ከፍተኛ በመሆኑ ህይወቱ ማለፋን ገልጸዋል።

የወረዳዉ ፖሊስ ሶስቱ ወጣቶች የፈፀሙትን የወንጀል ድርጊት በሰዉ ምስክሮች እና በህክምና ማስረጃ የምርመራ መዝገቡን በማደራጀት ክስ እንዲመሠረትበት ለካፋ ዞን ፍትህ መምሪያ ዐቃቤ ህግ መዝገቡን ይልካል።

የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ ሶስቱም ግለሰቦች ላይ የቀረበዉ ክስ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ቆይቶ ሶስቱንም ተከሳሾች በቀረበባቸዉ ማስረጃ መሠረት ጥፋተኞች ናችሁ ሲል የጥፋተኝነት ብይን ይሰጣል።

በዚሁ መሠረት የካፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት አንደኛ አማኑኤል ማናለ፣ሁለተኛ ተከሳሽ አስራት አክሊሉ እና ሶስተኛ ተከሳሽ ታድዮስ ተስፋዬ እያንዳንዳቸዉ በ8 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ዉሳኔ አስተላልፎባቸዋል ሲሉ ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

▣ t.me/felegethiopia

በቻምፒየንስ ሊጉ አታላንታ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል  የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ሥድስተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ።  ምሽት 2 ሠአት ከ45 ላይ ዳይናሞ ዛ...
12/10/2024

በቻምፒየንስ ሊጉ አታላንታ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ሥድስተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ።

ምሽት 2 ሠአት ከ45 ላይ ዳይናሞ ዛግሬብ ከሴልቲክ እንዲሁም ጊሮና ከሊቨርፑል ይገናኛሉ። ምሽት 5 ሠአት ላይ የጣሊያኑ አታላንታ ከስፔኑ ሃያል ሪያል ማድሪድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በምሽቱ ጨዋታ በቻምፒየንስ ሊጉ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማድሪድ በውድድሩ ለመቆየት ማሸነፍን አማራጭ አድርጎ ይጫወታል። ባየርሌቨርኩዘን ከኢንተርሚላን፣ አር ቢ ሌብዢግ ከአስቶንቪላ፣ ሬድቡል ሳልዝበርግ ከፒ ኤስ ጂ፣ ብረስት ከፒ ኤስ ቪ፣ ክለብ ብሩጅ ከስፖርቲንግ ሊዝበን እንዲሁም ሻካታር ዶኔስክ ከባየርሙኒክ የምሽቱ መርሐ ግብሮች ናቸው።

▣ t.me/felegethiopia

አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ከሀላፊነት ለቀቀች!የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ዛሬ ባደረገው ስብስባ አዲስ ተመራጭ ስራ አስፈፃሚ የአርቲስት ሀረገወይን አሰፋን ጥያቄ ተቀብሎ ...
12/10/2024

አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ከሀላፊነት ለቀቀች!

የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ዛሬ ባደረገው ስብስባ አዲስ ተመራጭ ስራ አስፈፃሚ የአርቲስት ሀረገወይን አሰፋን ጥያቄ ተቀብሎ በሌላ ሀላፊነት መመደቡ ታውቋል።

አርቲስት ሀረገውይን የስራ መደራረብ ስላለበኝ ከአቃቤ ነዋይነት ሌላ ሀላፊነት ስጡኝ ብላ ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት በማግኘቱ በአዲሱ ስራ አስፈፃሚ የማርኬቲንግ ሀላፊው የአቶ ኢሳያስ ተፈሪ ምክትል ሆና እንድትሰራ ተመድባለች።

በአርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ምትክ የአቃቤ ነዋይ ቦታን ወ/ሮ አሰፋሽ ታገሰ ተክታ እንድትሰራ መመደቧ ተረጋግጧል። ምክትል ፕሬዝዳንት ተዋናይነት ማስተዋል ባለችበት ስራዋን እንድትቀጥልም ስራ አስፈፃሚው ወስኗል።(ባላገሩ ስፖርት)

▣ t.me/felegethiopia

በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ  የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ ነውበመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ  መሆኑን የብሔራዊ የኃይ...
12/07/2024

በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ ነው

በመላው ሀገሪቱ ከተቋረጠው ኃይል ከግማሽ በላይ የሚሆነው ወደነበረበት እየተመለሰ መሆኑን የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ 85 በመቶ በሚሆነው በአብዛኛዎቹ አካባቢ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በጅማ፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሻሸመኔ፣ ወልቂጤ፣ መቀሌ፣ አድዋ፣ አላማጣ፣ ዲላ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን እና ሀገረማርያም ኃይል ተመልሶ ተገናኝቷል።

እስካሁን ከ50 በመቶ በላይ በሚሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች ኃይል መመለሱን የገለፀው ማዕከሉ በቀሪዎቹ አካባቢዎች መልሶ ለማገናኘት ርብርቡ መቀጠሉን ገልጿል። የተፈጠረው ችግር ሙሉ በሙሉ እስኪቀረፍ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁም ጠይቋል።

FELEG ETHIOPIA

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃ...
12/07/2024

በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃ ▻ ▣ t.me/felegethiopia

ባለሀብቱ አቶ ምህረትአብ ሙሉጌታ  ለባቡል ኸይር  የማዕድ ማጋራት እና የገንዘብ  ድጋፍ አደረገባለሀብቱ አበበ ቢቂላ እስታዲየም በሚገኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ 4 ሺ ሰዎች የማዕድ ማጋራ...
12/07/2024

ባለሀብቱ አቶ ምህረትአብ ሙሉጌታ ለባቡል ኸይር የማዕድ ማጋራት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ባለሀብቱ አበበ ቢቂላ እስታዲየም በሚገኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ 4 ሺ ሰዎች የማዕድ ማጋራት እና ለድርጅቱ የ 1 ሚልዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

የባቡል ኸይር ዋና ስራ አስኪያጅ ሀናን መሃሙድ " ድርጅቱ በአሁን ሰአት ፎቅ እያስገነባ እንደሆነና አቶ ምህረትአብ ሙሉጌታ ድጋፍ ለመስጠት ባሳየው ተነሳሽነት እንዲሁም በድርጅቱ በመገኘቱ ደስተኛ ነኝ " ብለዋል። አቶ ምህረትአብ ሙሉጌታ " ከዚህ በኋላ በተለያዩ ስራዎች ከድርጅቱ ጎን እንደምቆም እናም የተለያዩ ወዳጅ ዘመዶቼን በማሰባሰብ በርካታ ስራዎችን እንሰራለን "ብለዋል።

በቅርብ አመታት የተመሰረተው ባብል ኸይር ሀናን መሃሙድን ጨምሮ በሌሎች 16 ሴቶች የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ ከ 4ሺ በላይ ሰዎች እየረዳ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አቶ ምህረትአብ ሙሉጌታ ከዚህ ቀደም ለመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ድርጅት አራት ሚልዮን ብር መስጠቱ ይታወሳል።

ተጨማሪ መረጃ ▣ t.me/felegethiopia

Address

Tucker, GA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hagere Infotainment posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hagere Infotainment:

Videos

Share


Other Digital creator in Tucker

Show All