New Dawuro Media

New Dawuro Media አዳስ ነገር | ጠቃሚ መረጃወች | ማህበራዊ አገልግሎቶች

New Dawuro Media is ideal page to knew the history , culture and entire society of Dawro Zone.

የዳውሮ ዞን እጅግ ሰፊ የሆነ የቆዳ ስፋት ያለዉ ፤ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት ፤ አኩሪ ባህል ፤ ታሪክ ፤ ቋንቋ ያለዉ ዞን መሆኑን ለዓለም ህዝብ ማሳወቅ ፤ በተጨማሪም በየማህበራዊ መሰረቶች እና በመንግስታዊ መዋቅሮች የሚዲያ ሥራዎችን ተከታትሎ መረጃዎችን ለህዝብ ማድረስ እና በዳዉሮ ዞን ሆነ በዓለም ዙሪያ የሚታዩ ክስተቶችን ለቻናላችን ቤተሰቦቸ ማድረስ ቀዳሚ ስራችን ነዉ፡፡

ዳዉሮ ዞን ከኢትዮጵያ ዉብ ገፅታ ማሳያዎች አንዱ ነዉ፡፡ ዞኑ በደቡብ ክልል የሚገኝ

ሲሆን የዞኑ ዋና ከተማ ታርጫ ትባላለች፡፡ ታርጫ ገስጋሽ ነገር ግን በሚሌኒየሙ ከተወለዱ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ ከሐዋሳ በ282 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ ደግሞ በሻሸመኔ አድርገዉ በወላይታ ሶዶ የሚጓዙ ከሆነ 455 ኪ.ሜ ከአዲስ አበባ በሌላኛዉ መንገድ በጅማ አርገዉ የሚጓዙ ከሆነ ደግሞ በ479 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚያገኟት ከተማ ስትሆን ከተማዋ በየግዜዉ እያስመዘገበች ባለዉ እድገት ሳቢያም የብዙዎችን ትኩረት ስባለች፡፡

በደቡብ ከጋሞ ጎፋ በምዕራብ ከኮንታ ልዩ ወረዳ በሰሜን ምዕራብ ከኦሮምያ ክልል በሰሜን እስከ ሰሜን ምስራቅ ከከንባታ ጠንባሮ ዞን በምስራቅ ከወላይታ ዞን ይዋሰናል፡፡ ከሰሜን ምዕራብ እስከ ደቡብ ጫፍ ድረስ በጎጀብና በኦሞ ወንዞች ተፋሰስ የተከበበዉ ..

02/03/2025

ነጮች የአፍሪካን ስኬት አያሳዩም ..... 🤭

02/03/2025

የድሮ እናቶች .... 🙏👌

02/01/2025

አየሁሽ 👌🙏

 !   !------------------------እጅግ ጣፋጭና ጥዑም ምግቦችን ፍለጋ ደክመዋል? እንግዲያውስ የኢሚ ናና ባርና ሬስቶራን  ለድካሞ መፍትሄ ይዞላችሁ መጥቷል።  ኑ ጣፋጭ እና ጥዑ...
01/29/2025

!

!
------------------------
እጅግ ጣፋጭና ጥዑም ምግቦችን ፍለጋ ደክመዋል? እንግዲያውስ የኢሚ ናና ባርና ሬስቶራን ለድካሞ መፍትሄ ይዞላችሁ መጥቷል። ኑ ጣፋጭ እና ጥዑም ምግቦችን፣ ከፍየል ጥብስ ጀምሮ በዳውሮ ባህል ተወዳጅ የሆኑ ባህላዊ ምግቦችን እኛው ዘንድ ያገኛሉ።

በተለዬ መልኩ ምርጥ የዳውሮ ሰንጋ ለደንበኞቻችን አዘጋጅተናል። ነገ መቅረት የለም : የጥሬ ስጋ አምሮቶን ጥሞን ይቆርጥሎታል። ከታላቅና ከታናሽ እንዲሁም ከሻኛ አማርጠው ይመገቡ ፣ ሱልሶ ፣ ክትፎ ፣ ፣ ጥብስ ፣ ጎረድ ጎረድ ፣ ቡራቶ እና ሌሎች ጣት ከሚያስቆረጥሙ ምግቦቻችን እና ሌሎች የጾም ምግቦች በተለየ ሁኔታ ይዘጋጃሉ።

👉 ሁሉም መጠጦች እኛ ዘንድ ይገኛሉ።

ለሰርግ ለልደት እና ለተለያዩ ድግሶች እና ፕሮግራሞች በትዕዛዝ ምግቦችን እናዘጋጃለን።

እርሶ ብቻ ወደ እኛ ይምጡ እንጂ የጠፋውን የምግብ ፍላጎቶን በጣፋጭ ምግቦቻችን እናክማለን።


አድራሻችን :- ከታርጫ ማዘጋጃ ቤት ጀርባ እንገኛለን።

ማስታዎቂያ----)))----በታርጫ ከተማ የምትገኙ የሞቴር ሳይክል እና የባጃጅ ተሸከርካሪ ተጠቃሚዎች በሙሉ የቤንዝን ምርት ከታርጫ NOK ማደያ በግዥ መጠቀም እንድትችሉ ሞተር ሳይክል፤ ባጃጅ...
01/29/2025

ማስታዎቂያ
----)))----
በታርጫ ከተማ የምትገኙ የሞቴር ሳይክል እና የባጃጅ ተሸከርካሪ ተጠቃሚዎች በሙሉ የቤንዝን ምርት ከታርጫ NOK ማደያ በግዥ መጠቀም እንድትችሉ ሞተር ሳይክል፤ ባጃጅ ይዛችሁ በመቅረብ ኩፖን በመዉሰድ አገልግሎት የምታገኙ ስሆን ኩፖን ለመዉሰድ ስትመጡ፡

1/ ማንነታችሁን የምገልጽ 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ

2/የሞተር ሳይክል ወይም የባጃጅ ታርጋ ቁጥር እና የቻንስ ቁጥር

3/ የታርጫ ከተማ አስ/ር ነዋሪ መሆኑን የምገልጽ የታደሰ መታወቂያ ኮፒ በመያዝ ከቀን 22/5/2017 ዓ/ም ጀምሮ ታ/ከ/ሥ/ክ/ን/ገ/ኢ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት ቀርባቸዉ ኩፖኑን እንድት ወስዱ እያሳሰብን፡

ታርጋ የሌላቸዉ የመንግስትም ሆነ የግል ሞቶር እና ባጃጅ ተጠቃሚዎች ታርጋ ያለ መኖሩን ከዳዉሮ ዞን መንገድ ትራንስፖት የድጋፍ ደብዳቤ የማታቀርቡ ከሆነ የማናስተናግድ መሆኑን ከወድሁ እናሳዉቃለን፡፡

መ/ቤቱ

01/29/2025

ወደፊት ምናልባት በዚህ ከቀጠለ የሚፈራው መምጣቱ አይቀርም። ከዚህ አጭር ቪድዮ ምን ተረዳችሁ? በኮመንት ሳጥን ሀሳብ አስተያየታችሁን አጋሩ።

በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሠራ እንደሚገባ የዳዉሮ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀበዞኑ የ2017 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ንቅናቄ  መድረክ በታርጫ ከ...
01/28/2025

በጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ትኩረት ተደርጎ ሊሠራ እንደሚገባ የዳዉሮ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ

በዞኑ የ2017 በጀት ዓመት የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ንቅናቄ መድረክ በታርጫ ከተማ ተካሂዷል ።

የዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አስራት ቸርነት እንደገለፁት በአገር ደረጃ በሽታን ቀድሞ ለመከላከልና አክሞ ለማዳን የሚያስችል ፖሊሲ ተቀርጾ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል።

በመሆኑም የዞኑ ጤና መምሪያ እንደአገር በሚሠራው የጤና ልማት ፖሊሲ መነሻ የጤና አገልግሎት ጥራት እንዲኖረው ለማስቻል በትኩረት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዞኑ ይህን በጤናውን ዘርፍ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አሃድ ጥምረት የጥራትና የበሽታ መከላከል ዘርፍ እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ውጤታማነት እንዲረጋገጥ በተቀናጀ ጥረት ተግባሩ እየተመራ ይገኛልም ብለዋል።

በዛሬው ንቅናቄ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አገልግሎት ጥራት ከአቻ ተቋማት ጋር በቅንጅት እንደሚሠራም ነው የገለጹት።

ለዚህም በወረርሽኝ ቁጥጥር፣ በማዐጤመ አፈፃፀም፣ የጤና ተቋማት ዕዳ ማስመለስ፣ የሴቶች ልማት ኅብረት አደረጃጀት ማጠናከር ለአገልግሎት ጥራት መተኪያ የሌለ መሆኑንም በማመላከት።

የጤና ልማት ዘርፍ ውጤታማነት እንዲረጋገጥ በሽታን በመከላከል ረገድ የጤና ተቋማት የተሻለ አፈፃፀም እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብ እንደሚፈልግ የገለጹት በዕለቱ የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳደሪ ተወካይ እና የመንገድ ልማት እና ትራንስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አጥናፉ አስፋው ናቸው።

በዳውሮ ዞን ጤና መምሪያ የበሽታ መከላከልና የጤና ማጎልበት ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ስዩም ከበደ በኩላቸው ተላላፊና ድንገተኛ በሽታዎችን ለመከላከል እንዲቻል ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ በየደረጃው ከሚገኙ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሠራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዞኑ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ በበኩላቸው የብልጽግና ጉዞን ለማሳካት ጤናማ ዜጋን በማፍራት ከመቼውም ጊዜ በላይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም ተናግረዋል።

እንደዞን ከጤና የልማት ዘርፍ የበለጠ ተጠቃሚ ለመሆን እንዲቻል በተቀናጀ ጥረት መሥራት አማራጭ የሌለ ጉዳይ እንደሆነም በንቅናቄው መድረክ ለተገኙ ተሳታፊዎች አብራርተዋል።

መምሪያው ከየወረዳዎቹ ጋር በቀጣይም ስለሚከናወኑት ተግባራትና የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን መፈጸምና ማስፈጸም በሚያስችሉ የአሠራር ሥርዓቶች ላይ የግብ ስምምነት ተፈራሟል ሲል የዘገበው የዞኑ መንግስት ኮምንኬሽን ነው።

 ? ------------------------በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ300 ካሬ ላይ ያረፈ G+2 እጅግ ማራኪና ደረጃውን የጠበቀ ህንፃ ለመከራየት ለሚፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ክፍት ነው። ...
01/25/2025

?

------------------------
በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ300 ካሬ ላይ ያረፈ G+2 እጅግ ማራኪና ደረጃውን የጠበቀ ህንፃ ለመከራየት ለሚፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ክፍት ነው።

👉G+0 ላይ ሳሎንን ጨምሮ አራት ክፍል ከሻወርና ሽንት ቤት ጋር
👉 G+1 ላይ ስድስት ሰፋፊ ክፍሎች ከሻወርና ሽንት ቤት ጋር
👉 G+2 ላይ ሙሉ አዳራሽ ከሻወርና ሽንት ቤት ጋር
👉 ለስድስት መኪናዎች በቂ ፓርኪንግ ያለው

👉 ለክሊኒንክ
👉 ለNGO ተቋማት
👉 ለተለያዩ ድርጅቶ
👉 ለግል መኖሪያ እና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውል ቤት ፈጥነው ይከራዩ ፣ እንዳይቀደሙ።

አድራሻ ፦ ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ኮሬ መንደር
ስልክ ፦ 0912780237 // 0911282255

ቲኬሻ ቤንጊን  ስናከብር አንድነትን፣ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጽናት ለልማት ይበልጥ የምንነሳሳበት ሊሆን ይገባል፦ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾየሸኮ ብሔር ዘመን ...
01/25/2025

ቲኬሻ ቤንጊን ስናከብር አንድነትን፣ወንድማማችነት እና እህትማማችነትን በማጽናት ለልማት ይበልጥ የምንነሳሳበት ሊሆን ይገባል፦ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ

የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ "ቲካሻ ቤንጊ " በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ተከብሯል ።

በበዓሉ የተገኙት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ቲካሻ ቤንጊ የመተሳሰብና የአንድነት በዓል ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

የሸኮ ብሔረሰብ በዓሉን ሲያከብር ይበልጥ የወንድማማችነት እና እህትማማችነት እንዲጠናከር የሚያስችል ታሪክና ባህል እንዲጎለብት የሚያስችል ነው ሲሉም ተናግረዋል ።

አካባቢው የሰብል ምርት፣የማር ምርት፣የቡና ምርት በስፋት የሚገኝበት በመሆኑ የአካባቢው ኢኮኖሚ ይበልጥ እንዲያንሰራራ በተገቢው ማልማት ይገባልም ብለዋል።

የህዝብ ባህሎች የአንድነትና የመተሳሰብ እሴት ያሏቸው በመሆኑ ማልማትና መንከባከብ እንደሚገባም በዕለቱ ገልጸዋል።

የክልሉ ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ የሸኮ ብሔር ያለውን አካፍሎ በጋራ ማዕድ የሚቃመስበት ለተፈጥሮ ጥበቃ ትልቅ ቦታ የሚሰጥ ህዝብ ነው ብለዋል።

ቲኬሻ ቤንጊ የተጣሉ የሚታረቁበት ህዝቡ ለሰላም ያለውን ትልቅ ቦታ ማሳያ ከሀይማኖትና ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ባህላዊ እሴት ያለው በዓል ነው ብለዋል።

በዓሉ ለረጂም ዓመታት ባለመከበሩ የታሪክ መሸራረፍ እንደገጠመውና ይህንን የታሪክ መሸራረፍ ለመቅረፍ አሁን ላይ የተጀመረው ስራ ለትውልዱ እንዲተላለፍ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ የሆኑት አቶ ፍቅሬ አማን በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክትም የብልጽግና ፓርቲ የህዝቦች በህልና ታሪክ በተገቢው እንዲለማ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ ቲካሻ ቤንጊ ሰላም ፣አንድነትና አብሮነት ይበልጥ በአካባቢው እንዲበለጽግ የሚያስችል መሆኑንም አቶ ፍቅሬ አማን ተናግረዋል ።

የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ጸጋዬ ማሞ አካባቢው በኢኮኖሚ የበለጸገ እንዲሆን ያሉንን ጸጋዎች በተገቢው ማልማት ይገባል ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን በዕለቱም ባስተላለፉት መልዕክት የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ ቲካሻ ቤንጊ የአብሮነት፣የመተሳሰብ ፣የአንድነትና የሰላም እሴት ያለው ባህላዊ በዓል ነው ብለዋል።

በዓሉ ሳይበረዝና ሳይከለስ ለትውልድ እንዲተላለፍ እየተደረገ ያለው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋለ።

ቲካሻ ቤንጊ ጠንካራ የህዝብ እና መንግስት ግንኙነቶችን የሚፈጥር የልማት ስራዎችን የሚያሳልጥ በዓል መሆኑንም ተናግረዋል ።

የሸኮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሪ ጉሩሙ የሸኮ ብሔር ዘመን መለወጫ "ቲካሻ "ቤንጊ በብሔረሰቡ ዘንድ እጅግ ተወዳጅና በባህላዊ ክዋኔዎች ከሚከበሩት በዓላት ውስጥ አንዱ ነው ብለዋል ።

በአካባቢው የደረሱ ሰብሎች፣ፍራፍሬዎች፣የማር ምርት እንደደረሰ ተሰብስቦ ህብረተሰቡ በጋራ በየጎሳቸው ማዕድ የሚቃመሱበት ለቀጣይ አዝመራ የሚመራረቁበትና ፈጣሪያቸውን የሚያመሰግኑበት በዓል መሆኑንም አቶ አሪ ተናግረዋል ።

በዓሉ ከጥር 8/2017 ዓ/ም ጀምሮ በዓሉ በወረዳው የተለያዩ አካባቢዎች መከበሩንና የዛሬው የፍጻሜ በዓል መሆኑን ተናግረዋል ።

ቲኬሻ ቤንጊ ከክልሉ የተለያዩ የመንግስት አካላት፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣ጎሳ መሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት በሸኮ ከተማ ተከብሯል ።

 ---------------------1. የስራ ቦታ አድራሻ ዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ  2, የስራ መደብ መጠሪያ ፋርማሲ ፕሮፌሽናል ወይንም የፋርማሲ ባለሙያ 3, የስራ መደብ የሚጠይቀዉ ዝቅተኛ ...
01/25/2025


---------------------
1. የስራ ቦታ አድራሻ ዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ 2, የስራ መደብ መጠሪያ ፋርማሲ ፕሮፌሽናል ወይንም የፋርማሲ ባለሙያ
3, የስራ መደብ የሚጠይቀዉ ዝቅተኛ ችሎታ ፋርማሲ ፕሮፌሽን
👉የመጀመሪያ ድግሪ ያለዉ(ያላት)
👉የ3 አመት ልምድ ያለዉ(የላት)
👉መልካም ስነ ምግባር ያለዉ(ያላት)
👉ደሞዝ በስምምነት
👉የታደሰ የሙያ ፍቃድ ያለዉ(ያላት)

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ዋናዉን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ
✓ ከታወቀ ተቋም የተሰጠ የትምህርት ማስረጃ
✓ የታደሰ የሙያ ፈቃድ
✓ የሲኦሲ ሰርተፊኬት /ማስረጃ/

በ0917411711 በመደወል መመዝገብ የምትችሉ መሆናችንን ለመግለጽ እንወዳለን።

01/25/2025

የኢትዮ ቴሌኮም ጥሪ ማዕከል ......

ታርጫ  ከተማ ተሞሽራ ነበር። 📷 Golden Picture
01/25/2025

ታርጫ ከተማ ተሞሽራ ነበር።
📷 Golden Picture

የተገለጠ ዓይን ሲኖር የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ የተቃና ይሆናል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)***************ዛሬ የጎበኘነው ልማት የሚያሳየው የተገለጠ ዓይን እና የጠራ...
01/24/2025

የተገለጠ ዓይን ሲኖር የኢትዮጵያ የብልፅግና ጉዞ የተቃና ይሆናል:- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************

ዛሬ የጎበኘነው ልማት የሚያሳየው የተገለጠ ዓይን እና የጠራ ሃሳብ ሲኖር በአጠረ ጊዜ ውስጥ ሀገር መቀየር የሚያስችል ዕድል መኖሩን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት፥ እንዲህ ያለው ዕድል ተግቶ የማየት እና የመስራት ልምምድ ሲጨመርበት ደግሞ በአጭር ጊዜ ከድህነት ለመውጣ እንድንችል ያደርገናል ብለዋል።

ከለውጡ በኋላ ኢኮኖሚው ብዝኃ ዘርፍ እንዲሆን በማድረግ አዲስ የእይታ መስክ ተፈጥሮ ሲሰራ መቆየቱንም አስታውሰዋል።

ይህን ተከትሎ ከዚህ በፊት በቱሪዝም እና በማዕድን ልማት እምብዛም የማይታወቀው ዳውሮ ዞን ቀደም ሲል በሀላላ ኬላ የቱሪስት መዳረሻ የጀመረው የአካባቢው ለውጥ አሁን ደግሞ በማዕድን ልማት ቀጥሎ የአካባቢው እምቅ አቅም እየወጣ መሆኑን ጠቁመዋል።

01/24/2025

25% የሀገራችንን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት የሚሸፍነው የET-Mining የድንጋይ ከሰል ኩባንያ

ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የነበሩ የተፈጥሮ ፀጋዎች ለህዝብ ጥቅም መዋል ጀምረዋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የነበሩ ...
01/24/2025

ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የነበሩ የተፈጥሮ ፀጋዎች ለህዝብ ጥቅም መዋል ጀምረዋል - ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)

ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የነበሩ የተፈጥሮ ፀጋዎች ለህዝብ ጥቅም መዋል መጀመራቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን የተገነባውን የኢቲ ማዕድን ልማት አክሲዮን ማህበር የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ለዛሬውና ለመጪው ትውልድ የሚጠቅሙ ትላልቅ የልማት አሻራዎች መቀመጣቸውን ጠቁመዋል።

የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ልማት ፍጥነትና ፈጠራን መሰረት ባደረገ መልኩ እየተተገበረ ነው ብለዋል።

በዚህም የህዝብን ተጠቃሚነት፣ የሀገርና የክልሉን ኢኮኖሚ ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት።

የክልሉን ፍትሐዊ የልማት ተጠቃሚነት የሚያሻሽሉ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሪዞርቶችን ጨምሮ በርካታ ፕሮጀክቶች ወደ አገልግሎት መግባታቸውን አመላክተዋል።

ክልሉ በግብርና ልማት በስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፥ እምቅ የማዕድን ጸጋ የሚገኝበት መሆኑንም ተናግረዋል።

እንደ ሀገር ለማዕድን ዘርፉ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ተደብቀው የቆዩ የከበሩ የማዕድን ጸጋዎች ለህዝብ ጥቅም መዋል መጀመራቸውን ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት በክልሉ ተመርቆ ወደ ስራ የገባው የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ መንግስት ጸጋን መለየት እና ሀብት መፍጠር ላይ ስኬታማ ስራ እያከናወነ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

የፋብሪካው መገንባት ከውጭ የሚገባውን የድንጋይ ከሰል ምርት በመተካት የውጭ ምንዛሪ ጫናን የሚቀንስ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለአካባቢው የኢኮኖሚ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትና ለበርካታ ዜጎችም የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።


01/24/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢቲ ማዕድን ልማት አ.ማ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ምርቃ መርሀ ግብር ላይ ያስተላለፉት መልዕክት!

Address

Sellersburg, IN
47172

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New Dawuro Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to New Dawuro Media:

Videos

Share