MANKIRA MEDIA

MANKIRA MEDIA please follow our page for more info.

Mankira media's latest Ethiopian breaking news online video-sharing website providing Ethiopian News, Music videos, movies, Drama series, Comedy, politics, and fun culture.

New Syrian Rebel Leader Mohammad al-Jolani looks hot and youngest.
12/12/2024

New Syrian Rebel Leader Mohammad al-Jolani looks hot and youngest.

12/10/2024

በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማመረት እና ወደ አገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

በሻር አል-አሳድን ከሥልጣን ያስወገደው አማጺ ቡድን መሪ አቡ መሐመድ አል-ጃውላኒ
12/10/2024

በሻር አል-አሳድን ከሥልጣን ያስወገደው አማጺ ቡድን መሪ አቡ መሐመድ አል-ጃውላኒ

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሚኖሩ ኤርትራውያን በማህበረሰባቸው መካከል ከፍተኛ እስራት መፈጸሙን ገልጸው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ቤታቸውን ጥለው በወጡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ስጋት ፈጥሯ...
12/03/2024

በኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሚኖሩ ኤርትራውያን በማህበረሰባቸው መካከል ከፍተኛ እስራት መፈጸሙን ገልጸው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ቤታቸውን ጥለው በወጡ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ስጋት ፈጥሯል።

በበረራ ላይ እያለ ሕይወቱ አለፈ:)ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በሚጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ህይወቱ አለፈ      ባሳለፍነው አርብ November 15 ቀን 202...
11/20/2024

በበረራ ላይ እያለ ሕይወቱ አለፈ:)
ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በሚጓዝ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሳፋሪ አየር ላይ ህይወቱ አለፈ

ባሳለፍነው አርብ November 15 ቀን 2024 ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣ በበረራ ቁጥር ET 500 ፣ በAirbus A350 አውሮፕላን ተሳፋሮ የሚመጣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ መንገደኛ አየር ላይ እንዳለ ባጋጠመው ድንገተኛ ህመም ህይወቱ አለፈ።

    ዛሬ ንጋት ላይ በ58 ዓመቱ ማይክ ታይሰን እና ጄክ ፖውል መካከል የተካሄደው የቦክስ ውድድር በ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል አሸናፊነት ተጠናቋል።ሁለቱ ቦክሰኞች ከውድድሩ በኋላ እርስ በርሳቸው...
11/16/2024


ዛሬ ንጋት ላይ በ58 ዓመቱ ማይክ ታይሰን እና ጄክ ፖውል መካከል የተካሄደው የቦክስ ውድድር በ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሁለቱ ቦክሰኞች ከውድድሩ በኋላ እርስ በርሳቸው መከባበርና መሞጋገስ የታየበት አስተያየት ሰጥተዋል።

ወጣቱ ቦክሰኛ ጄክ ፖውል በሰጠው አስተያየት “ከሁሉም በፊት ማይክ ታይሰንን በመግጠሜ ከፍተኛ ክብር ይሰማኛል” በማለት ለሱ ያለውን አድናቆት ገልጿል። እሱ ምሳሌ ባይሆነኝ ኖሮ ዛሬ እዚህ አልደርስም ነበር፤ ማይክ የምንጊዜም ታላቅ ቦክሰኛ ነው ሲል አድናቆቱን አጉርፎለታል።

ከዚህ ታላቅ፣ ኃይለኛ እና አስቸጋሪ ሰው ጋር መጋጠም ታላቅ ክብር ነው ያለው ጄክ ፖውል ውድድሩ ከባድ እንደነበር አልካደም።

ማይክ ታይሰን ለስምንት ዙር መዝለቁ አቅሜን የለካሁበት ነው፤ በዚህም ደስተኛ ነኝ ያለ ሲሆን ጄክ ፓውልን በተመለከት ጥሩ ቦክሰኛ ነው፤ አድናቆት ይገባዋል ሲል አሞካሽቶታል።

የሁለቱን ቦክሰኞች ውድድር ከ70 ሺሕ በላይ ሰዎች በውድድሩ ቦታ ተገኝተው የተመለከቱ ሲሆን በቴሌቪዥንና ሌሎች ድጂታል አማራጮች ከ350 ሚሊዮን በላይ ሰዎቸ ተከታትለውታል።

ከውድድሩ የ27 ዓመቱ ጄክ ፓውል 40 ሚሊዮን ያገኘ ሲሆን ታይሰን 20 ሚሊዮን ዶላር እንደተከፈለው መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡      ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ሃላፊነ...
10/08/2024

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዛሬ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሆነው ሃላፊነት የተቀበሉት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ሀገርና ሕዝብን በላቀ ሁኔታ የሚያገለግሉበት የሃላፊነት ዘመን እንዲሆንላቸውም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የቀድሞ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ!!
10/08/2024

የቀድሞ ፕሬዚደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ!!


እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ተከለከለ      የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ የግዜ ቀጠሮ የወንጀል ችሎት እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ከልክሏል።   ...
09/17/2024

እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ተከለከለ
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ የግዜ ቀጠሮ የወንጀል ችሎት እነ ዮሀንስ ዳንኤል የጠየቁትን የዋስትና መብት ከልክሏል።
ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት ጠይቀው የነበረ ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱም በዛሬው ችሎት የዋስትና መብቱን ከልክሏል።
ችሎቱ የክስ መዝገቡን ለመመልከት ለጥቅምት 4 ቀን 2017 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ😢😢😢    ነፍስ ይማር ፣ ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መጽናናትን እንመኛለን !
09/17/2024

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ😢😢😢
ነፍስ ይማር ፣ ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑር
ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸዉ መጽናናትን እንመኛለን !

Breaking News
09/15/2024

Breaking News

ሰላም ንዋይ ደበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል🥲🥲የድምፃዊ ንዋይ ደበበ እና የአይዳ ሐሰን ወንድ ልጅ ነበር አይዳ እና ንዋይ ደበበ እንዲሁም መላዉ ቤተሰብ እግዚያብሔር ያጽናችሁ እንላለን።  ...
09/14/2024

ሰላም ንዋይ ደበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል
🥲🥲
የድምፃዊ ንዋይ ደበበ እና የአይዳ ሐሰን ወንድ ልጅ ነበር
አይዳ እና ንዋይ ደበበ እንዲሁም መላዉ ቤተሰብ እግዚያብሔር ያጽናችሁ እንላለን።

Age is just a number😂😂
09/09/2024

Age is just a number😂😂

08/29/2024

ሆይ ምን ታመጣለህ🤣🤣🤣

    የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ሰፊ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነ...
08/26/2024



የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ሰፊ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

በትላንትናው እለት ፌዴራል ፖሊስ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሽን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል።

የፌዴሬል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላይ የአቪዬሽን አሰራር ሕግ ከመጣስ ባለፈ በሽብር ወንጀልም ምርመራ ስለጀመርኩ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ይደረግ በማለት ተከራክሯል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሐንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

     ፌደራል ፖሊስ ነሀሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብ...
08/25/2024


ፌደራል ፖሊስ ነሀሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ፦
• ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣
• አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣
• ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣
• ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣
• ይዲድያ ነጻነት አበበ እና
• እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

Picture of the Day
08/21/2024

Picture of the Day

08/19/2024

Address

San Francisco, CA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MANKIRA MEDIA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to MANKIRA MEDIA:

Videos

Share

MANKIRA MEDIA


  • Mankira Media is an Ethiopian Online Video Sharing site. It has been providing Ethiopian News, Music, Video, Movie, Drama series, Comedy & Fun culture for diaspora community all over the world. please follow our page for more information. https://www.facebook.com/mankiramedia/ #mankira