Ahadu Radio & TV/ አሐዱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን

Ahadu Radio & TV/ አሐዱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን Broadcasting & Media Production · Addis Ababa, Ethiopia
(151)

ሳምንታዊ የፊልም ቅኝት
12/08/2023

ሳምንታዊ የፊልም ቅኝት

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

"የሃማስ እስራኤልን ማጥቃት ለሩስያ ገጸበረከት ነው"
12/08/2023

"የሃማስ እስራኤልን ማጥቃት ለሩስያ ገጸበረከት ነው"

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

የ 16 ዓመቷ  ታዳጊ ጥሪ
12/07/2023

የ 16 ዓመቷ ታዳጊ ጥሪ

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

የጠቅላይ ሚኒስተር የስልጣን ዘመን መገደብ አለበት !
12/07/2023

የጠቅላይ ሚኒስተር የስልጣን ዘመን መገደብ አለበት !

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

አሁን ካለው ትውልድ ይልቅ የዛሬ ሚሊዮን ዓመት የነበረችው ሉሲ ትሻላለች!
12/07/2023

አሁን ካለው ትውልድ ይልቅ የዛሬ ሚሊዮን ዓመት የነበረችው ሉሲ ትሻላለች!

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

ዩክሬን በጦር መሳሪያ እጥረት በሩስያ የምትሸነፍ ከሆነ ተጠያቂዋ አሜሪካ ናት !
12/07/2023

ዩክሬን በጦር መሳሪያ እጥረት በሩስያ የምትሸነፍ ከሆነ ተጠያቂዋ አሜሪካ ናት !

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

አሜሪካ ከ 3 የአፍሪካ ሀገራት ለሚገቡ ባለስልጣናት ቪዛ ከልክላለች፡፡የአሜሪካ መንግስት በዚህ ሳምንት ባስተላለፈው ውሳኔ ከሱዳን፣ ከዚምባቡዌና ከኡጋንዳ ለሚገቡ ባለስልጣናት ነው ቪዛውን የከ...
12/07/2023

አሜሪካ ከ 3 የአፍሪካ ሀገራት ለሚገቡ ባለስልጣናት ቪዛ ከልክላለች፡፡

የአሜሪካ መንግስት በዚህ ሳምንት ባስተላለፈው ውሳኔ ከሱዳን፣ ከዚምባቡዌና ከኡጋንዳ ለሚገቡ ባለስልጣናት ነው ቪዛውን የከለከለው፡፡

ይህንን ውሳኔ ለማስተላለፍ ያበቃው ደግሞ ሶስቱም ሀገራት በምድራቸው ጦርነት ለማስቆም ያለመቻላቸው፣ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ አለማድረጋቸው እንዲሁም ምርጫ እንዲደረግ ምቹ መደላድል አለመፍጠራቸው ነው ተብሏል፡፡

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ከተከለከሉት የሱዳን ባለስልጣናት መካከል የቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርን ጨምሮ 3 ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ናቸው፡፡
ዘገባው፡-የኒውስ 24 ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

ለማእድን አውጪዎች ፍቃድ የሚሰጠው አካል ተገቢውን ቁጥጥር እያደረገ አይደለም ሲል የጉምሩክ ኮሚሽን ወቀሳውን አቅርቧል፡፡  የገቢዎች ሚኒስቴር የ2016 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅ...
12/07/2023

ለማእድን አውጪዎች ፍቃድ የሚሰጠው አካል ተገቢውን ቁጥጥር እያደረገ አይደለም ሲል የጉምሩክ ኮሚሽን ወቀሳውን አቅርቧል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር የ2016 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቧል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ለቋሚ ኮሚቴው በሰጡት ማብራሪያ የማእድን ዘርፉ ለሙስና ተጋላጭ ነው ያሉ ሲሆን ይህም የሆነው በማእድን አውጪ ድርጅቶች እና ፍቃድ በሚሰጠው አካል መካከል ያለው የቁጥጥር ግንኙነት ክፍተት ያለበት በመሆኑ ነው ሲሉ ነው የገለጹት፡፡

ከቁጥጥር ስራው መላላት ባለፈም በጋምቤላ ፤ ቤንሻንጉል ጉምዝ ፤ ደቡብ እና ምእራብ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ላይ ያለው የጸጥታ ችግር ህገ-ወጥ የማእድን ዝውውርን እንዳባባሰው ነው ኮሚሽነሩ የገለጹት፡፡
አክለውም የጫት ኮንትሮባንድ ንግድ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ያሉት ኮሚሽነሩ በተለይም ድንበሮች አካባቢ የክልል ፤ የዞን እና ወረዳ አመራሮች ጭምር ተሳታፊ ናቸው ብለዋል፡፡
በተለይም የሶማሌ ክልል የንግድ ቢሮ ኃላፊዎች የዞንና ወረዳ አመራሮች ጭምር ከህገወጥ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ነው ለምክር ቤቱ ያብራሩት፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

በመንግስት እና በሸኔ መካከል በነበረው ድርድር የሰላም ሚኒስቴር አለመሳተፉ ግልጽ አይደለም ተብሏል፡፡ በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደ...
12/07/2023

በመንግስት እና በሸኔ መካከል በነበረው ድርድር የሰላም ሚኒስቴር አለመሳተፉ ግልጽ አይደለም ተብሏል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በፌዴራሉ መንግስት እና በሕወሓት መካከል በተደረገው ድርድር እንዲሁም በመንግስት እና በሸኔ መካከል በነበረው የድርድር ሒደት ላይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሳተፍ ነበረበት ያሉ ሲሆን ድርድሩ ውስጥ የሰላም ሚኒስቴር ለምን እንዳልተካተተም እንጠይቃለን ብለዋል።

ጉዳዩ በቀጥታ የማይመለከተው የፍትሕ ሚኒስቴር በድርድሩ ላይ ተሳትፎ የሰላም ሚኒስቴር እንዲሳተፍ አለመደረጉ ምክንያቱ ግልጽ አይደለም ነው ያሉት።
በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር እና በሶማሌ ክልሎች ብሎም በጉራጌ ዞን እንዲሁም በተለያዩ የሰላም መስፈን ችግር ባለባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች ላይ መረጋጋትን ለማምጣት ሚኒስቴሩ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።

የኢትዮጵያ የጸጥታ ችግር በዋነኝነት የብሔር ፖለቲካ አካሄድ በመሆኑ ከግጭት ቀጣና ወጥቶ ሀገራዊ የአንድነት ጥቅምን በማስቀደም ሰላም ማምጣት እንደሚያስፈልግ ነው የሰላም ሚኒስቴር ያሳሰበው።
ከዚህም ባሻገር ሰላም በጦርነት እንደማይመጣ ከግንዛቤ በማስገባት በኢትዮጵያ የሚታዩ የጸጥታ ችግሮች መፍትሔ እንዲያገኙ ከኃላፊነቴ ጎን ለጎን ተቋማት ሊያግዙኝ ያስፈልጋልም ብሏል ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ።

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

"በአሁን ሰዓት ምንም ተስፋ የማረገው ነገር የለኝም ደክሞኛል" ድምፃዊት ደመቀች መንግስቱ   -   (ሎሚ ተራ ተራ)
12/06/2023

"በአሁን ሰዓት ምንም ተስፋ የማረገው ነገር የለኝም ደክሞኛል" ድምፃዊት ደመቀች መንግስቱ - (ሎሚ ተራ ተራ)

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

,, አሐዱ አፋላጊ,,ተፈላጊዎቻችን የአቶ አታኽልቲ አረጋዊ ቤተሰቦች ናቸዉ፡፡ወይዘሮ ሽቱ ሙሄ እና አቶ አታኽልቲ አረጋዊ በትዳር ሲኖሩ 1 ወንድ ልጅ ወልደዉ እንደነበር የነገሩን ወይዘሮ ሽቱ ...
12/06/2023

,, አሐዱ አፋላጊ,,

ተፈላጊዎቻችን የአቶ አታኽልቲ አረጋዊ ቤተሰቦች ናቸዉ፡፡

ወይዘሮ ሽቱ ሙሄ እና አቶ አታኽልቲ አረጋዊ በትዳር ሲኖሩ 1 ወንድ ልጅ ወልደዉ እንደነበር የነገሩን ወይዘሮ ሽቱ ሙሄ ናቸዉ፡፡
በ1993 ህዳር 14 ቀን በጦር ሜዳ ሀይወታቸዉ ያለፈዉ አቶ አታኽልቲ አረጋዊ ደሱን ቤተሰቦች ባለቤታቸዉ እንደማያዉቋቸዉ እና ለመጨረሻ ጊዜ ግን ለእህቱ ልጅ ወልጃለሁ ብሎ በስልክ ሲናገር እንደሰሙትም አጫዉተዉናል፡፡
በመጨረሻም የመርዶ ደብዳቤ ሲመጣ አካባቢዉ ተጠቅሶ ነበር የሚሉት ባለቤቱ ወይዘሮ ሽቱ ሙሄ ሽሬ ከተማ ወረዳ ማይገባ ቀበሌዉ ዶሃርግዛና እንደሆነ እና የወላጅ እናቱ ስም ወይዘሮ ዉቢት በየነ እንደሆነ ለማወቅ መቻላቸዉን ነግረዉናል ፡፡

ከባለቤታቸዉ ያፈሩት ወንድ ልጃቸዉ አላዛር አታኽልቲ የአባቱን ቤተሰቦች ስለማያዉቅ በማፈላለግ እንድናግዛቸዉ ጠይቀዉናል፡፡
የአቶ አታህልቲ አረጋዊን ቤተሰቦች አድራሻ የምታቁ በስልክ ዉጥር 09 46 25 20 71 ላይ በመደወል ታሳዉቋቸዉ ዘንድ ፈላጊ ወይዘሮ ሽቱ ሙሄ ሙሳም በአክብሮት ይጠይቃሉ፡፡

አሐዱ አፋላጊ ፕሮግራም ዘወትር ረቡዕ በአሃዱ ልሳን ማለዳ የሚተላለፍ እና ጣቢያችን አሐዱ ሬዲዮ 94.3 ካለምንም ክፍያ ማህበራዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ሚያቀርበዉ ፕሮግራም ነዉ፡፡

" ሁላችንም አንድ እንሁን " ለነፃነታችን የተከፈለውን ዋጋ እናድን
12/06/2023

" ሁላችንም አንድ እንሁን " ለነፃነታችን የተከፈለውን ዋጋ እናድን

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

ለአሽባሪዎች ምቹ መርመስመሻ ምድር !
12/06/2023

ለአሽባሪዎች ምቹ መርመስመሻ ምድር !

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

ናይጄሪያ በሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ጥቃት በተገደሉባት ዜጎቿ ጉዳይ ጥልቅ ምርመራ ይደረግ ዘንድ ጥሪ አቅርባለች፡፡የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሰሜናዊ የካዱ...
12/06/2023

ናይጄሪያ በሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ጥቃት በተገደሉባት ዜጎቿ ጉዳይ ጥልቅ ምርመራ ይደረግ ዘንድ ጥሪ አቅርባለች፡፡

የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሰሜናዊ የካዱና ግዛት በሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ጥቃት የተገደሉት ሰዎች ጉዳይ ይጣራ ዘንድ ትእዛዝ ሰጥተዋል፡፡
በሰሜናዊ የካዱና ግዛት ባለፈው እሁድ የሀገሪቱ ጦር ሀይል የአሸባሪዎቹን ሀይሎች ኢላማ ባደረገበት የሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ጥቃት በትንሹ 85 ሰዎች ተገድለዋል፡፡
የአይን እማኞች፤ የሀይማኖት አባቶችና የግዛቱ አስተዳደር ባለስልጣናት ለሬወተርስ በሰጡት አስተያየት፤ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው ንጹሃን በሀገሪቱ ጦር ሀይል የሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ጥቃት መገደላቸውን ተናግረዋል፡፡

በሃያ ስምንተኛው የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ ላይ የተገኙት የናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኑቡ የተፈፀመው ነገር በጣም አሳዛኝና አስደንጋጭ ነውና በአስቸኳይ የተፈጠረው ሂደት ሁሉ እንዲጣራ ሲሉ ትእዛዝ መስጠታቸውን የሲ ኤን ኤን ዘገባ ያስረዳል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሚሰሩ ሴቶች የደሞዝ ወለል ዝቅተኛ ከመሆኑ ባሻገር የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚያጋጥሟቸዉ አስታወቀ፡፡በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሚሰሩ ሴቶች የሚደርስባቸዉን ...
12/06/2023

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሚሰሩ ሴቶች የደሞዝ ወለል ዝቅተኛ ከመሆኑ ባሻገር የተለያዩ የመብት ጥሰቶች እንደሚያጋጥሟቸዉ አስታወቀ፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሚሰሩ ሴቶች የሚደርስባቸዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት ብናዉቅም እሰካሁን በማህበራቱ በኩል የደረሰን ሪፖርት የለም ሲል የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ገልጻል፡፡

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሴቶች የሚያጋጥሟቸዉን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ችግሮቹን ብናዉቃቸዉም፤አሁን ላይ ፓርኮቹ አዲስ ስለሆኑ ማህበራቱ ተደራጅተዉ በተገቢዉ ሁኔታ ስራ ስላልጀመሩ መረጃ ጭምር መረጃ እየሰጡን አይደለም ሲሉ የተናገሩት የሰራተኛ ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝደንት አቶ ካሳሁን ናቸዉ፡፡
ያልተደራጀ አንድ ማህበር እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ የተደራጁትም በሚፈለገዉ ልክ እየተንቀሳቀሱ አይደለም ነዉ ያሉት ፕሬዝደንቱ፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ ተቀጥረዉ የሚሰሩ ሰራተኞች የደመወዝ ወለል አነስተኛ በመሆኑም ክፍተቱን ለመቅረፍ ትኩረት ሰጥተን እየሰራንበት እንገኛለን ሲሉ ነዉ ያብራሩት፡፡
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘም አሃዱ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽንን ቢጠይቅም ኮርፖሬሽኑ የእሱ ሃላፊነት እንዳልሆነ ገልፅዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

ለምክር ቤት አባላት ከሚቀርቡ ጥያቄዎች ውስጥ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር ከፍ ያለ መሆኑ ተገለፀ፡፡የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዓመት ሁለት ጊዜ ወደ ወከላቸው ማህበረሰብ ሄደው ውይይ...
12/06/2023

ለምክር ቤት አባላት ከሚቀርቡ ጥያቄዎች ውስጥ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር ከፍ ያለ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዓመት ሁለት ጊዜ ወደ ወከላቸው ማህበረሰብ ሄደው ውይይይት እንደሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ ውይይቶች ላይ ከሚቀርቡ ጥያቄዎች መካከል የመድሃኒት አቅርቦት ችግር በስፋት እንደሚቀርብላቸው የህዝብ ተወካች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ገልጸዋል፡፡

ከመድሃኒት አቅርቦት በተጨማሪም የህክምና ግብአት እና መድሃኒት አስተዳደር ስርአት ላይ ሰፊ ችግሮች እንዳሉ የሚያሳይ ቅሬታ እየቀረበ ነው ብለዋል፡፡
ክፍተቶቹ መፍትሄ እንዲያገኙ ባለመ መልኩ በዋናነት ከኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ያለውን የመድሀኒት አቅርቦት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ጠንካራ ክትትል እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
በተለይም ለችግሩ በምክንያትነት ከሚነሱት ጉዳዮች መካከል የበጀት እጥረት እንዲሁም የህግ እና የፖሊሲ ክፍተቶች መሆናቸውን አንስተው በዚህ በኩልም ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይነትም በመድሃኒት አቅርቦት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚቀርቡ ሪፖርቶችን ብቻ አድምጦ ውሳኔ ከመስጠት ባለፈ በአካል ተገኝቶ ክትትል በማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ስራ አስፈፃሚዎች የተለዩበት መንገድ ዋነኛ ባለድርሻ አካላትን ያገለለ ነበር ተብሏል፡፡የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ መልማይ ኮሚቴው የመጨረሻ ዕጩ አድርጎ ወይዘሮ ሜላት...
12/06/2023

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ ስራ አስፈፃሚዎች የተለዩበት መንገድ ዋነኛ ባለድርሻ አካላትን ያገለለ ነበር ተብሏል፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዕጩ መልማይ ኮሚቴው የመጨረሻ ዕጩ አድርጎ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እና አቶ ታደሰ ለማን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረባቸው የሚታወቅ ሲሆን እጩዎቹ የተለዩበትን ሂደት እንዴት ታዘባችሁት በማለት አሀዱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አነጋግሯል፡፡
የእናት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳዊት ብርሃኑ እንደሚሉት አስቀድሞ የመልማይ ኮሚቴው አባላት የተሰየሙበት መንገድም አግባብነት የሌለው እና ለመንግስት ካላቸው ቀረቤታ ጋር ተያይዞ የገለልተኛነት ጥያቄም የሚያስነሳ ነው ብለዋል፡፡
ሂደቱ የግልጸኝነት ችግር እንደነበረበት አንስተው ከመልማዮቹ መካከል የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካይ የሆኑ ግለሰቦች ሊካተቱበት ይገባ ነበር በማለት አሁን የመጨረሻ እጩዎች ተለይተው የቀረቡ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ምንም መፍጠር አይቻልም ነው ያሉት፡፡

በተለይም በኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርአት ላይ ከሚታዩ በርካታ ውስብስብ ችግሮች ጋር በተያያዘ መሰል ተቋማትን የሚመሩ ግለሰቦች የሚመረጡበት ሂደት ከፍተኛ ትንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዘዳንት ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄር ናቸው፡፡

በተጨማሪም የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ መልማይ ኮሚቴ ውስጥ ለገለልተኛነቱም ሆነ የተሻለ ምርጫ ለማካሄድ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና በፖለቲካው ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ያላቸው አካላት ሊካተቱበት ይገባ እንደነበረም ነው ፓርቲዎቹ የጠቆሙት፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

በኢትዮጵያ የአምቡላንሶች ቁጥር ማነስ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ የአየር ላይ አምቡላንሶች ሊገዙ ነው፡፡ በአገራችን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት አምቡላንሶች ቁጥር ከ4ሺ በታች ሲሆን ካለው...
12/06/2023

በኢትዮጵያ የአምቡላንሶች ቁጥር ማነስ አሳሳቢ መሆኑን ተከትሎ የአየር ላይ አምቡላንሶች ሊገዙ ነው፡፡

በአገራችን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙት አምቡላንሶች ቁጥር ከ4ሺ በታች ሲሆን ካለው ፍላጎት እንዲሁም ከተለያዩ ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች ብዛት አኳያ ሲታይ ደግሞ እጅግ አሳሳቢ ነው ያሉት በጤና ሚንስቴር የህክምና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢሉባቡር ቡኖ ናቸው፡፡
ካሉት አምቡላንሶች ውስጥ ከማጓጓዣነት ባለፈ መሰረታዊ አስቸኳይ የህክምና ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል ቁሳቁስ የተሟላላቸው እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ሲሆኑ ዘመናዊ እና በከፍተኛ ደረጃ የተሟላ አምቦላንሽ ምንም የለም ብለዋል፡፡

በጤና ሚንስቴር በኩል ይህን ለማሻሻል የተወሰኑ የአምቡላንስ ግዢ ተፈጽመዋል፡፡ በስራ ላይ የሚገኙትን ደግሞ የማዘመን እና በግብአት የተሟሉና ደረጃቸውን የጠበቁ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም የአውሮፕላን አምቡላንሶችን ለመግዛት ጨረታ ወትቶ በግዢ ሂደት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ ካለው የህዝብ ብዛት ባለፈ የጦርነቶች እና ግጭቶች መበራከት ሲታከልበት የእርዳታ ሰጪ አምቡላንሶች ቁጥር ብሎም የአገልግሎት አቅም እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ አሳሳቢ ነው ተብሏል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

እስራኤል አሉኝ የምትላቸው ወታደሮቿ  በአውደውጊያ ላይ ተገድለዋል
12/06/2023

እስራኤል አሉኝ የምትላቸው ወታደሮቿ በአውደውጊያ ላይ ተገድለዋል

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

መንግስት የማያቀው እስር ቤት ካለ ተጠያቂው እራሱ መንግስት ነው
12/05/2023

መንግስት የማያቀው እስር ቤት ካለ ተጠያቂው እራሱ መንግስት ነው

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

ዓለምን ያስፈራው የጦር ጥምረት
12/05/2023

ዓለምን ያስፈራው የጦር ጥምረት

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

ደራሲ ብቻ አይደለሁም ማንም የማያውቀው ሠዓሊም ነበርኩኝ
12/05/2023

ደራሲ ብቻ አይደለሁም ማንም የማያውቀው ሠዓሊም ነበርኩኝ

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the me...

መንግስት የሰጠው ምላሽ ሥርዓቱን የጠበቀ አይደለም !
12/05/2023

መንግስት የሰጠው ምላሽ ሥርዓቱን የጠበቀ አይደለም !

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

የሊባኖስ ታጣቂ ሀይል ሄዝቦላ በእስራኤል ኢላማውን መምታቱን አስታውቋል፡፡የሊባኖሱ ተዋጊ ሀይል ሄዝቦላ በእስራኤል በጣም በርካታ ስፍራዎችን የሚሳይል አላማው አድርጎ መደብደቡን ገልጿል፡፡በሄዝ...
12/05/2023

የሊባኖስ ታጣቂ ሀይል ሄዝቦላ በእስራኤል ኢላማውን መምታቱን አስታውቋል፡፡

የሊባኖሱ ተዋጊ ሀይል ሄዝቦላ በእስራኤል በጣም በርካታ ስፍራዎችን የሚሳይል አላማው አድርጎ መደብደቡን ገልጿል፡፡

በሄዝቦላ ዋናው የእስራኤል ምድር ኢላማ ውስጥ የገባው ስፍራ ቤይት ሂለል የሚባለው መሆኑ ሲገለፅ በሄዝቦላ ሚሳይል ከባድ ጥቃት ተፈጽሞበታል ነው የተባለው፡፡
የሊባኖሱ አልማያዲን ቴሌቪዢን ጣቢያ ባሰራጨው ዘገባው ሄዝቦላ ሚሳይሎቹን ወደ እስራኤል ያስወነጨፈበት ስፍራ ከሀገሪቱ ድንበር ሶስት ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ ከሚገኘው ስፍራ መሆኑን ያሳያል፡፡

የሊባኖሱ ታጣቂ ሀይል ሄዝቦላ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ ከዚህ በኃላ በእስራኤል ምድር ጥቃቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
ዘገባው፡-የመኸር ኒውስ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

በአፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት ከደረሰባቸው እርዳታ የሚሹ ከ6 መቶ ሺህ በላይ ዜጎች ቢኖሩም 200ሺው ብቻ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተገለጸ፡፡በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተከስቶ የነበረውን ችግር ተ...
12/05/2023

በአፋር ክልል በጦርነቱ ጉዳት ከደረሰባቸው እርዳታ የሚሹ ከ6 መቶ ሺህ በላይ ዜጎች ቢኖሩም 200ሺው ብቻ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተገለጸ፡፡

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ተከስቶ የነበረውን ችግር ተከትሎ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ክልሎች አንዱ የአፋር ክልል እንደሆነ ይታወቃል፡፡
ከአካባቢያቸው ከተፈናቀሉ ከስድስት መቶ ሺ በላይ ዜጎች ውስጥ 2 መቶ ሺህ ገደማው ብቻ እርዳታ እንዳገኙ እና ቀሪዎቹ ምንም አይነት ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ለአሃዱ የገለጹት የአፋር ክልል አደጋ ስጋት አመራር ኮምሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ማሄ አሊ ናቸው፡፡

የአለም ምግብ ድርጅት ከዚህ ቀደም ያደርግ የነበረውን ድጋፍ መቆሙን ተከትሎ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን እና ባለፉት ስድስት ወራት ምንም አይነት እርዳታ እንዳላገኙ ያስታወሱት አቶ ማሄ ለአንድ ወር ብቻ በፌደራል መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ለ200 ሺ ዜጎች ድጋፍ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

በክልሉ ያሉትን በርካታ ችግሮች ባገናዘበ መልኩ ድጋፍ የማድረግ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

ለመንጃ ፈቃድ የተግባር ስልጠና ከህግ አግባብ ውጭ ገንዘብ እየተጠየቅን ነው፣ በቀን ከ1 ሰዓት በታች እየሰለጠንን ነው ሲሉ ሰልጣኞች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር...
12/05/2023

ለመንጃ ፈቃድ የተግባር ስልጠና ከህግ አግባብ ውጭ ገንዘብ እየተጠየቅን ነው፣ በቀን ከ1 ሰዓት በታች እየሰለጠንን ነው ሲሉ ሰልጣኞች ቅሬታቸውን አቀረቡ፡፡

ከአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት ጋር በቀን ለአንድ ሰዓት ለመሰልጠን ውል ገብተን ክፍያ ብንፈጽምም ቢበዛ ለ40 ደቂቃ ብቻ ነው የምንሰለጥነው ሲሉ ሰልጣኞች ለአሃዱ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡
በተቋማቱ አሰልጣኞች ከህግ አግባብ ውጭ ለተግባር ልምምድ ብር እንጠየቃለን ሲሉም ቅሬታቸውን እንዲህ አሰምተዋል፡፡

አሃዱም ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ስለሚደረገው ቁጥጥር በአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ቁጥጥር ባለስልጣን የአሽከርካሪ ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ገብረማርያም ወልደአረጋይን ጠይቋል፡፡
ተቋሙ የተግባር ትምህርት ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ላይ ተቆጣጣሪዎችን በመመደብ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማቱ በቀን ምን ያህል ሰልጣኞችን እንደሚያሰለጥኑ እንዲሁም ሰልጣኞች በቀን ለአንድ ሰዓት የተግባር ልምምድ ማድረጋቸውን ቁጥጥር እንደሚያደርግ ነው የገለጹት፡፡ ሰልጣኞች በተቀመጠው ሰዓት መሰረት መሰልጠናቸውን በፊርማቸው እንዲያረጋግጡ ስርአት መዘርጋቱንም ነው ያነሱት፡፡

ባለስልጣኑ በተቋማቱ ላይ የሚያደርገው ቁጥጥር በዋናነት ከሰልጣኞች ከሚመጣው መረጃ ላይ የሚመሰረት መሆኑን አንስተው ሰልጣኞች ተገቢ ያልሆነ አሰራር ሲመለከቱ ለተቋሙ ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉም ተናግረዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመደበኛና ልዩ ስብሰባዎች የመገኘት ህገ መንግስታዊ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡አሃዱ በቅርብ በተደረጉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ...
12/05/2023

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመደበኛና ልዩ ስብሰባዎች የመገኘት ህገ መንግስታዊ ግዴታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡

አሃዱ በቅርብ በተደረጉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባዎች ላይ የአባላቱ ቁጥር መቀነሱን ለመታዘብ ችሏል፡፡ ይህ ጉዳይ በህግ አግባብ እንዴት ይታያል ሲልም የህግ ባለሙያዎችን አነጋግሯል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአባላት ስነ ስርአትና ስነ ምግባር ደንብ መሰረት እያንዳንዱ የህዝብ ተወካይ በመደበኛ ፣ ልዩና አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይ የመገኘት ግዴታ እንዳለበት መደንገጉን የሚናገሩት የህግ ባለሙያው አቶ ጥጋቡ ደሳለኝ ናቸው፡፡

አባላቱ በጤናና በሌሎች ሊጠቀሱ ከሚችሉ ህጋዊ ምክንያቶች በስተቀር በማናቸውም ሁኔታ ከምክር ቤቱ ስብሰባ ሊቀሩ የሚችሉበት አግባብ እንደሌለም አስረድተዋል፡፡
የህዝብን ማህበራዊ ፣ ምጣኔ ሃብታዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች አጀንዳ በማስያዝ ለመወያየትና በአስፈጻሚ አካል የሚቀርቡ ረቂቅ ህጎችን ለማጽደቅ አባላቱ መገኘት እንዳለባቸው አንስተው በህገ መንግስቱ መሰረት በህዝብ ዘንድ የአመኔታ ጥያቄን በማስነሳት ውክልናን ሊያሳጣ የሚችል መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
ሌላው የህግ ባለሙያና አማካሪ አቶ ካሳሁን ሙላቱ በበኩላቸው አልፎ አልፎ የምክር ቤቱ መቀመጫዎች ባዶ ሆነው እንደሚስተዋሉ ገልጸው ሊታሰበብት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታን ለማዳበር በተቋማት በኩል አባላቱ በህገ-መንግስቱ መሰረት በስብሰባዎች ላይ እየተገኙ አይደለም የሚሉ ጥያቄዎች መዳበር እንዳለባቸውም አንስተዋል፡፡

ባለሙያዎቹ አክለውም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በመደበኛና ልዩ ስብሰባዎች የመገኘት ህገ መንግስታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን

" ጫካ ወስደው አስረው ገረፉኝ  "
12/05/2023

" ጫካ ወስደው አስረው ገረፉኝ "

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

የሃውቲ  ሚሳኤሎች በቀይባህር  የእስራኤል መርከቦችን አክስለዋል
12/05/2023

የሃውቲ ሚሳኤሎች በቀይባህር የእስራኤል መርከቦችን አክስለዋል

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

ዓለም ማስቆም ያቃታት እልቂት እና ደም መፋሰስ
12/04/2023

ዓለም ማስቆም ያቃታት እልቂት እና ደም መፋሰስ

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

" የኛ ልፋት ብቻ በቂ አይደለም"
12/04/2023

" የኛ ልፋት ብቻ በቂ አይደለም"

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

12/04/2023

ቢዝነስ ሎዉ 24/03/16 ዓ.ም

በድጋሚ ያገረሸው ጦርነት
12/04/2023

በድጋሚ ያገረሸው ጦርነት

#አሐዱቲቪ AHADU TM- Television Network news organization and Television program produce, managed to shift the dynamics of the med...

Address

Joseph Tito Street
Saint Petersburg, FL

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ahadu Radio & TV/ አሐዱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ahadu Radio & TV/ አሐዱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን:

Videos

Share

AHADU RADIO FM 94.3

  • Press the LIKE button to see our posts in your newsfeed.
  • We want everyone to enjoy this page and welcome debate. Spam, bullying and offensive comments, however, will be removed and repeat offenders will be banned from the page.

    We aim to be as responsive as possible but unfortunately can't reply to every individual comment or message.

    ይህ የፌስ ቡክ መድረክ የአስተያየት፡ የሀሳብ እና የመረጃ ልውውጥን ለማበረታታት የታሰበ ነው። እና አስተያየት በምትልኩልን ጊዜ የተቋሙን መመሪያዎች እንድትከተሉ በትህትና እናሳስባለን።

    Other Saint Petersburg media companies

    Show All